Pages

Dec 14, 2012

ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች”ህፃናትና ኣዛውንቶች ከታሕሳስ 5/2005ዓ/ም ጀምረው ስራቸውን እንዲያቆሙ የከተማው ኣስተዳደር ከፖሊስና ሚሊሻ ሓይሎች ጋር በመቀናጀት ኣስቁመዋቸዋል$ እነዚህ ወገኖች ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞር”መንገድ ዳር ተቀምጦው በመሸጥ የዕለት ገቢያቸው ንየሚያገኙ ሲሆኑ የከተማው ኣስተዳደር ጋዜጣና መፅሄት እንዳያዞሩና ኣንድ ቦታ ላይ ተቀምጠውም እንዳይሸጡ ያዘዘ ሲሆን፣ ያላቸው መጽሄት እና ጋዜጣ ሽጠው እንዲጨርሱ የኣምስት ቀን ዕድል ሰጧቸዋል


በመቀሌ ከተማ ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞርና መንገድ ዳር በመዘርጋት ሽጠው የሚተዳደሩ ወገኖች ስራቸውን እንዲያቆሙ ታዘዙ

ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች”ህፃናትና ኣዛውንቶች ከታሕሳስ 5/2005ዓ/ም ጀምረው ስራቸውን እንዲያቆሙ የከተማው ኣስተዳደር ከፖሊስና ሚሊሻ ሓይሎች ጋር በመቀናጀት ኣስቁመዋቸዋል$ እነዚህ ወገኖች ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞር”መንገድ ዳር ተቀምጦው በመሸጥ የዕለት ገቢያቸው ንየሚያገኙ ሲሆኑ የከተማው ኣስተዳደር ጋዜጣና መፅሄት እንዳያዞሩና ኣንድ ቦታ ላይ ተቀምጠውም እንዳይሸጡ ያዘዘ ሲሆን፣ ያላቸው መጽሄት እና ጋዜጣ ሽጠው እንዲጨርሱ የኣምስት ቀን ዕድል ሰጧቸዋል

እነዚህ ወገኖች “እኛ ሰርተን ራሳችንን ችለን ለመኖር ያለንን ብቸኛ ዕድል ሊነፈገን ኣይገባም$ ይህንን የምትከለክሉን ከሆነ ኣንድ ላይ ተሰባስበን የምንሸጥበት ቦታ ስጡን ወይም ሌላ የተሻለ የስራ ዕድል ስጡን” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም !የከተማው ባለስልጣናት “ለናንተ የሚሆን የመሸጫ ቦታ ይሁን ሌላ የስራ ዕድል የለንም$ ከፈለጋችሁ ወደየመጣችሁበት ወረዳ ተመልሳችሁ መስራት ትችላላችሁ$ “የሚል ኣሳዛኝ መልስ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል$

በፖሊስ”በሚሊሻና በካድሬ እየተባረረ የተገኘ ወጣት ሲናገር “እኛ ሰርተን ለፍተን ደክመን የሰው እጅ ከማየትና ማጅራት መትተን የሰው ሀብት ከመዝረፍ እንላቀቅ ብለን ስንቀሳቀስ መንግስት ሊያበረታታን ይገባል እንጂ ሊያሳድደንና እግር እግራራችን እየተከተለ ሊያባርረን ባልተገባ ነበር$ እኔ ኣሁን በእጄ ላይ ያሉት መፃሕፍቶች በውድ ዋጋ የገዛሁዋቸው ናቸው ፣ ነገር ግን እንድንነሳ የተሰጠን ቀን ገደብ 5 ቀን ብቻ ስለሆነ የግደ ትልቅ የዋጋ ቅናሽ ኣድርጌና ከስሬ መሸጥ እገደዳሎህ$ ኣልበለዚያ ንብረቴን ዘርፈው ሊያስሩኝ እንደሚችሉ በስብሰባው ለሁሉም ጋዜጣና መፅሄት ኣዟሪዎችና መንገድ ዳር ላይ ተቀምጠን ለምንሸጥ ተነግሮናል” ሲል በምሬት ተናግረዋል$

አንድ የተቃዋሚ አባል ” የትግራይ መስተዳዳር የወሰደው እርምጃ የትግራይ ህዝብ ህወሀት ከሚያቀርበው መረጃ ውጭ ሌላ መረጃ እንዳያገኝ ለማድረግ ነው” በማለት ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ኣስተዳደር ከዚህ በፊት በክልሉ ይታተሙ የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ የፕረስ ውጤቶች የተለያዩ ጫናዎች በመፍጠር እንዲዘጉ ማድረጉ የሚታወስ ነው$

ከክልሉ ዜና ሳንወጣ የሽሬ እንዳስላሴ ህዝብ የኤች ኣይ ቪ ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በተጠራ ሰልፍ ላይ ሳይገኝ ቀርቷል።

በእየአመቱ ህዳር 22 በሚከበረው ዓለም ኣቀፍ የኤድስ ቀን ላይ ለሰልፍ እንዲወጣ የተጠየቁት የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪዎች በሰልፉ ባለመገኘት ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል$

የህወሓት ባለስልጣናት በፖሊስ”በሚሊሻና በቀበሌ ሴት ካድሬዎች ህዝቡ ለሰልፍ እንዲወጣ ቢያስገድዱም ህ/ሰቡ ተቃውመውን በሰልፉ ባለመገኘት ገልጿል$

ተማሪዎች ፈተና እንዳላቸው ተነግሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ቢደረግም የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች በሰልፉ ቢካፈሉም፣ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችእና የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ሽሬ ግቢ ተማሪዎች ኣሻፈረኝ በማለት ሳይገኙ ቀርተዋል$

በሰልፉ የከተማዋ ታቦታትም የተገኙ ቢሆኑም የቀሳውስቱ ቁጥር አነስተኛ ነበር$ ከመስጊድ እንዲመጡ የታዘዙ የሃይማኖት መሪዎችም ከኣንድ መስጊድ ከመጡ ጥቂት ሰዎች በስተቀር በሰልፉ ኣልተገኙም $

ከሽሬ የሚነሱ ኣገር ኣቋራጭ ኣውቶብሶች የኣንድ ቀን ጉዞ በመሰረዝ በሰልፉ እንዲገኙ የተገደዱ ሲሆን የኣጭር ርቀት ተሽከርካሪዎች እንደ ባጃጅና ጋሪም ጭምር ተገድደው በሰልፉ እንዲሳተፉ ተደርገዋል$

“ የመለስ መሪነት ተከትለን ወደ ተግባር እንሸጋገራለን” “ ኣሁንም መለስ የ50 ዓመት መሪያችን ነው” “ የመለስ ዕቅድ ወደ ተግባር እናሸጋግራለን” የሚሉ መፈክሮች በመያዝ የተወሰኑ የህወሀት አባላትና የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ተጉዘዋል$

ሚሊሻያዎች “ፖሊሶችና ካድሬዎች ቤት ለቤት እየተንቀሳቀሱ ህዝቡን ወደ ሰልፉ እንዲወጣ ቢሞክሩም ህዝቡ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል$ ቤታችሁ ዝጉ የተባሉ የከተማዋ ንግድ ቤቶችም ነዋሪውን ሲያስተናግዱ ውለዋል $ የከተማዋ ነዋሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች በየ ሻሂ ቤቱ ተቀምጠው በሰልፈኞ ላይ ሲያቬዙ ይታይ እንደነበር ዘገባው አመልክቷል።

በተያያዘ ዜና በሽሬ ከተማ ዙርያ ከ10 ዓመት በፊት ለመኖርያ ተብሎ 20 በ20 ስፋት ያለው መሬት ተሰጥቶዋቸው ቤት ገንብተው የሚኖሩ ነዋሪዎች አካባቢው ወደ ከተማ ገብቷል በሚል ሊፈርስባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል$

የሰፈሩ ነዋሪዎች እንደሚሉት ስርዓትና ሕግን ተከትለው ቤቶችን ቢገነቡም የመንግስት ባለስልጣናት ግን የሚሰሙ አልሆኑም ። በቀበሌ 03፣ 110 “በቀበሌ 05 ፣ 560 እንዲሁም በቀበሌ 04 600 ቤቶች እንደሚፈርሱ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate