Pages

Dec 14, 2012

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቶ ሀይለማርያም ከኤርትራ ጋር ስለሚደረገው እግርኳስ ጫወታ የተናገሩትን ቆርጦ አቀረበ

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቶ ሀይለማርያም ከኤርትራ ጋር ስለሚደረገው እግርኳስ ጫወታ የተናገሩትን ቆርጦ አቀረበ



ኢሳት ዜና:-የመንግስቱ ቴሌቪዥን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኤርትራ ጋር የእግር ኳስ ጨዋታ በአስመራ ለማካሄድ ችግር የለብንም በማለት የተናገሩት መንግስት ቀደም ብሎ ጨዋታው በገለልተኛ አገር እንዲካሄድ ከጠየቀው ጋር የሚጋጭ መሆኑን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወሳል።

ኢቲቪ የአቶ ሀይለማርያምን ቃለምልልስ በአማርኛ ተርጉሞ ያቀረበ ሲሆን፣ የእግር ኳስ ጫወታውን በተመለከተ ያለውን ክፍል ቆርጦታል።

ኢቲቪ ቃለምልልሱን ቆርጦ ማቅረቡ የኢሳትን ዘገባ ለማስተባበል ተብሎ ይሁን በተለመደው ባህሪው የታወቀ ነገር የለም። በግልጽ በሚታይ እና በቀላሉ ሊረጋገጥ የሚችልን ዘገባ ቆራርጦ ማቅረቡ፣ ኢቲቪ በምን ያክል ደረጃ እንደወረደ ያሳያል በማለት አስተያየታቸውን በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ያስቀመጡ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate