Pages

Dec 14, 2012

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በዳላስ ቴክሳስ የተካሄደው ውይይት ለጊዜው ባለመስማማትና ለሌላ ውይይት ቀጠሮ ተይዞ ቢጠናቀቅም፤ የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ የውዝግቡ መነሻ የነበሩት ሰነዶች ለኢሳት ደርሰዋል።

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. አባቶች ድርድር ላይ ያወዛገቡት ደብዳቤዎች እየወጡ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በዳላስ ቴክሳስ የተካሄደው ውይይት ለጊዜው ባለመስማማትና ለሌላ ውይይት ቀጠሮ ተይዞ ቢጠናቀቅም፤ የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ የውዝግቡ መነሻ የነበሩት ሰነዶች ለኢሳት ደርሰዋል።

በቤተክርስቲያኒቷ አባቶች መካከል አንዱ የልዩነቱ መነሻ የሆነው የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ የጻፉት ደብዳቤ መሆኑ ታውቋል።

የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ ፓትሪያርኩ እንዲነሱ ደብዳቤ መጻፋቸውን አምነው ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ መናገራቸውን ዊኪሊክስ ከሁለት አመት በፊት ማድረጉ ይታወሳል።

የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ ፓትሪያርክ መርቆሬዎስን ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ እንደሆኑም ሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ከሁለት ወር በፊት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።

በተጨማሪም አቶ ታምራት ላይኔ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲነሱ ካዘዙበት ደብዳቤ ባሻገር የጠቅላይ ቤተክህነት በጀት እንዳይንቀሳቀስ ለገንዘብ ሚኒስቴር ትእዛዝ የሰጡበት ደብዳቤ ኢሳት እጅ ገብቷል።

እንዲሁም ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ በመንገስት ግፊት ቅዱስ ሲኖዶስ መስከረም 28 ቀን 1984 ያሳለፈውን ውሳኔ በተመለከተ በወቅቱ የሰጡት ምላሽም እጃችን ገብቷል።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate