ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ጃንዋሪ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በመተማ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የከተማው የብአዴን ጽ/
ቤት ኃላፊ፣ የከተማው የአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ 18 ሰዎች በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ
ሕይወታቸው ወዲያዉኑ ሲያልፍ ሌሎች 4 ሰዎች መቁሰላቸውን ኢዩኤፍኤፍ ቢያሳውቅም መንግስት ዜናውን ላፉት
17 ቀናት እንዳልዘገበውና ምንም አይነት መረጃ እንዳላወጣ ምንጮች ገለጹ። ከዚህ ቀደም በደብረማርቆስ፣
በአዲግራት በአዲግራት እና በተለያዩ ከተሞች እርምጃዎችን እየወሰደ የሚገኘው የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል
(Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) ለዚህ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን መውሰዱን የደረሱን
መረጃዎች አመልክተዋል።
በዚህ ጥቃት አቶ ተስፋ (የአባታቸውን ስም እያጣራን ነው) - የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ፤ እንዲሁም አበበ ወርቁ –
የመተማ ወረዳ የብ አዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የተባሉት በአውቶቡሱ ውስጥ እንደተሳፈሩ የጋዩ ሲሆን የአቢሲኒያ ባንኩ
ሥራ እስኪያጅ ሙሉ ስም በማጣራት ላይ እንገኛለን። በተለምዶ “አባዱላ” እየተባለ በሚጠራው ሚኒባስ ውስጥ
ተጭነው በመተማ ሲሄዱ የተጠመደው ቦምብ እንደፈነዳ ያሳወቁት የዜና ምኝጮቻን ቦምቡ በተለምዶ እንጀራ በጨው
በሚባለው የመተማ አካባቢ ፈንድቶ ወዲያውኑ አውቶቡሱ ሲጋይ ከተጫኑት 22 የኢሕአዴግ የኮር
አባላትና ደጋፊዎች ውስጥ አደገኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ወደ ህክምና ተልከዋል ሲሉ የኢዩኤፍኤፍ ምንጮች
ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል ከዚህ ቀደም በደብረማርቆስ እርስቤትን አጥቅቶ 17 የ እስርቤቱን ጠባቂዎች
መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በአዲግራት እስቤት ቤትም ቦምብ በመጣል እስረኞች ለመሞታቸው ይኸው ኃይል
ራሱን ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ይኸው ድርጅት “ከኢሕአዴግ ሥርዓት ጋር አትተባበሩ የሚል
ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ላልሰሙ ደጋፊዎች ክምር ድንጋይ የሚባለው
አካባቢ የነዳጅ ዘይት ማጠራቀሚያ ማጋየቱና፤ እንዲሁምጨጨሆ ላይ ላይ ደግሞ አውቶቡስ ማቃጠሉ መዘገቡ
አይዘነጋም። የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force –
EUFF) በመተማ ይህን እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ለሕዝቡ ከመንግስት ጋር እንዳይተባበር፤ ይልቁንም ለነፃነቱ
እንዲነሳ፤ ሲቀሰቅስ እንደነበር የሚገልጹት እነዚሁ ዘጋቢዎች ይህን አልሰማ ባሉት ላይ ነው እርምጃውን ሊወስድ
የቻለው ብለዋል።
ከኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል ይህን መረጃ ካገኘን በኋላ ከመንግስት በኩል የሚሰጠንን ማስተባበያም ሆነ
ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment