
ባመነበት የወሰነ
ወስኖ የሚሰራ
ለሚሰራው የማይፈራ
ዘልቆ ገደብ ለቋል የፍቅር ጥልቀቱ
ከኖረበት ምድር ደምና እትብቱ
አገር ቤትም ሆነ ከባህር ባሻገር
የትም የትም ቢሆን የትም ሀገር ቢኖር
የኢትዮጵያን ችግር ሲሰማ ሲናገር
የነጻነት ፍትህ ምሰሶና ማገር
ምሳሌ አታገኙም መሬትን ብትዞሩ
እንደታማኝ ያለ ለህዝብ ለአገሩ
አይፈራም ማንንም ይመስክር ስሙ
ታማኝ በየነ ነው ፀንቶ በአቋሙ
ሌላውማ ሌላውማ
እማማ
እኔ ምን አገባኝ የሚሏትን ወግ
እሱ ነው ያረዳት ኢትዮጵያን እንደ በግ
አዳሪ ለሆዱ ክብሩን አስነጣቂ
ሲጣልበት ውሻ የእጅ እባሽ ናፋቂ
የሚታመን ጠፋ ለእውነት ያደረ
ውሽት ገኖ ናኝ በቀይሽ ከበረ
ሊወርድ ዘብጥያ እውነትም ታሰረ
ታሪክ ተረት ተረት ብስራት ተበሰረ
ሆኖም ግን ሆኖም ግን
እማማ
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝብ ቢቸገርም
ታማኝ ደርሶልሻል አይዞሽ በዛው አይቀርም
እስከ ግዜው ድረስ ያቆየው በጤና
ለአገሩ ያብቃው ጥሩ ሰው ነውና
ያሬድ ኤልያስ ኖርዌይ ቴሌማርክ
No comments:
Post a Comment