በኢትዮጵያ አገራችን በተለያየ ጊዜ የተነሱ የዉጪ እና የውስጥ ጠላቶች ያሴሩትን አደጋ ለመቋቋም ባለመቻላችን በየወቅቱ ትኩሳታችን እየፈላ እርስ በርስ እየተጠላለፍን በመውደቅ ላምንም የማንበጅ እና የራሳችንም ቤት አፍራሽ ሆነን እንዳገጠትን እንገኛለን::በቅርብ ርቀት እንኳን ወያነን ለመጣል እልህ አስጨራች ትግል እያደረጉ ካሉ ድርጅቶች መሃል በግለሰብ በገንዘብ በመግዛት ለመበጥበጥ የተደረጉ ሴራዎች የከሸፉበት አጋጣሚ መኖሩ እሙን ነው::እንደ ኦነግ እህኣፓ ኢዲዩ የመሳሰሉ አንጋፋ ድርጅቶችን ጠልፎ ለመጣል የተደረጉ ሙከራዎች በተለጣፊነት .....ዲሞክራቲክ በማለት የወያኔ የዲያስፖራ የስለላ መዋቕር በራሱ ጊዜ እየፈጠራቸው ከሚያከስማቸው ልጥፍ ማታለያዎች ተጠቃሽ ናቸው::
ከጥቂት ወራት ቀደም ብሎ በገንዘብ የሆን በወሬ አይታወቅም የተገዛ ግለሰብ ከአባሪ ተነባባሪ የወያኔ ዲያስፖራዎች ጋር በመሆን የግንቦት ሰባት ንቅናቄን ስም በማጉደፍ በመሰሪ ሴራ ላይ ለመሰማራት በማሰብ የድለላ ስራ በመስራት የወያኔን የፖለቲካ ፍጆታ ለማሟላት ደፋቀና ሲል ሃፍረት ተከናንቦ የስልጣን ጥሙ እና የገንዘብ ፍላጎቱ አንቆት በቁሙ መሞቱ የሚታወስ ነው:; ትላንት ሚሊዮን መሃላዎችን ሲደረድር የነበረው ግለሰብ አይጋ ፎረምን በመጠቀም የፈጠራ ኢሜይል መልእክቶችን በማሰራጨት አባላትን ለማዋከብ ያደረገው ሴራ በደቂቃዎች ከሽፎበታል:: ከጀርባው የነበሩትም የአይጋ ፍሮእም እና የትግራይ ኦንላየን ዘረኛ ሚዲያዎች አፋቸውን ይዘዋል:: ምንሊክ ሳልሳዊ
ይህም አልበቃ ያለው ይህ በግንቦት 7 ንቅናቄ ላይ ሲያሴር የለመደ ምግባሩን አለቀው በሎ ከአንድ ካፑቺኖ ግብዣ በኋላ አብሮ የታገሉትን በቃልኪዳን የተያያዙትን የንቅናቄውን ታጋዮች ስም ለማጉደፍ ሲንጠራራ ተነቅቶብሃል በማለት አፉን እንዳሲያዝነው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው ::
የግንቦት ሰባት አባል ባልሆንም ይህን ፓርቲ ጨምሮ ከእያንዳንዱ የፖለቲካድርጅት ጀርባ እየተሸረበ ያለው ሴራ በየጊዜው የምከታተለው ጉዳይ ነው::ምክንያቱም ማንኛውም የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ዉድመት እና ድቀት ማየት ለወያኔ ደስታ ከመፍጠር ዉጪ የሚፈይደው ምንም ፋይዳ ካለመኖሩም በተጨማሪ የህዝቦች አንድነት ለፓርቲዎቹ ጥንካሬ መሆኑን በማመን ነው::
ግንቦት ሰባትን በተመለከት አሳፋሪ እና የዉሸት ፕሮፓጋንዳ ከመርጨቱ ጀርባ ያሉ የወያኔ ጀሌዎች እንጂ ማንም የግንቦት ሰባት አባላት በዚህ ሂደት ዉስጥ አለመሳተፋቸው ለማረጋገጥ ተችሏል:: እንደ ልደቱ አያሌው አይነቶች በቅንጅት ዉስጥ የተጫወቱት ሚና ድጋሚ ሊያገለግል የሚችል ጨዋታ አለመሆኑን ሁሌ ወደኋላ የሚያስበው ወያኔ አልተረዳውም::
የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን በአይጋ ፎረም እና በትግራይ ኦንላየን በኩል በመርጨት እንዲሁም ግንቦት 7 ዲሞክራቲክ በማለት በፈጠሩት የምላስ ተለጣፊ ስም መግለጫ በመጻፍ ተቀዳሚ ሚና እየተጫወተ ያለው " ሥሑለሚካኤል ኣባይ " ተብሎ የሚጠራው የወያኔ የስለላ ጀሌ ዋናው ሲሆን የወያኔ ጁንታ ለዚህ ስራው የሚመድብለን በጀት ከ30.000 እስከ 40...ዶላር ሲሆን ለዚሁ የመጠላለፍ ሴራው በየተጓዘበት አገር የአየር ቲኬት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በስልክ ትዕዛዝ ብቻ እንደሚሰጠው ለማረጋገጥ እወዳለሁ::
ሥሁለሚካኤል በዘረኝነት አቋሙ የሚታወቅ እና የትግራይን ታላቅነት የሚሰብክ ትግራይ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ አሰብን የዛ እንድትኖር የሚመኝ ሲሆን ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥላቻ ያለው ግለሰብ ነው:: በተለያዩ ጊዜያት በደህንነት ሹሙ በአቶ ጌታቸው በኩል ለወያኔ የስለላ መረብ ያቀረበው የዘረኝነት ፕሮፖዛል እንደሚያሳየው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እና ጠንካያ አባላትን ለመግደል ንብረቶቻቸውን ለማጥፋት እንዳቀደ ያስገነዝባል:: በየ3 ወር ጊዜ ወደ አስመራ በመሄድ እንዲሁም በተለያዮ የመገናኛ መስመሮች በመጠቀም አስመራ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲሁም በሱዳን የሚደረጉ የተቃውሞ ስራዎች ሪፖርት በማዘጋጀት ለሻዕቢያ ከወያኔ የሚላኩ ስጦታዎችን በመስጠት የሚሰራ የወያኔ ጀሌ ነው::በዚሁ በተጨማሪ የተለያዩ የተቃዋሚ ሃይሎች ከአስመራ ተንክረው እንዳይወጡ ላማድረግ እያሳፈነ እያስገደለ እና እያሳሰረ በቁም እየገደለ የሚገኝ ጸረ ዲያስፖራ የወያኔ አሽከር ነው::
የግንቦት ሰባት ንቅናቄ የግብጽ ቢሮ በተመለከተ እስከዚህ መግለጫ የሚያሰጥ ነገር የለም ትክክለኛ ለኢትዮጵያ ለውጥ የሚያስብ ግለሰብ ካለ ከሆነ ራሱን ገንጥያለሁ የሚል ቡድንም ቢሆን ለሃገር በጎ ለወገን ለውጥ ለማድረግ የሚሰራን ስራ አይቃወምም:: በተለየ እና ግልጥ በሆነ ህኡነታ የምንረዳው ነገር ቢኖር የህ መግለጫ ወያኔ የጻፈው እና በዚህ ግለሰብ የተዘጋጀ ሲሆን ምክንያቱ ደሞ ወያኔ ለመደንገጡ ያስተላለፈው መልእክት ነው::ወያኔ ራሱ እንዴት ያለፉትን 17 የትግል አመታት በነማን እርዳታ እንዳለፈው ስለሚያውቅ አሁንም የግንቦት 7 ካይሮ ለመክተም ማሰቡ የእግር እሳት ሆኖበታል ስለዚህም...ዲሞክራቲክ በሚል ተቀጽላ የህን አደፋም መግለጫ ሥሁለሚካኤል በማዘጋጀት እንዲለቀው ተደርጓል:: ምንሊክ ሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment