Pages

Apr 24, 2013

ትንሽ ወሬ፤ የፓርላማ አባል አባላቱ ተደፋፍረዋል!


Untitled-2እኔ የምለው ፓርላማው ውስጥ ግን ጭብጨባ ለምን ቀረ… ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያንን ሁሉ ሰዓት መከራቸውን አይተው ሪፖርት ሲያነቡ ቆይተው አመሰግናለሁ… ብለው ሲጨርሱ በጭብጨባ አባላቱ ምስጋናቸውን ቢቀበሏቸው፤ በአፀፋውም ቢያመሰግኗቸው ምን አለበት…?
ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ይቺ ህግ የወጣችው ያኔ በ 97 በዛ ተዓምረኛ ወር የቅንጅት አባላት በኢህአዴግ ላይ ዝረራ በፓርላማው ላይ ወረራ የፈጸሙ ዕለት በርካታ የፓርላማ ህጎች ተሸሽለዋል፡፡  አዳዲስ ህጎችም ወጥተው ነበር፡፡ “አንድ የፓርላማ አባል የፓርላማ ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቢገኝ ከተቀመጠበት ወንበር ፖሊስ አንጠልጥሎ ያስወጣዋል…” የሚል ነገር ሁሉ ነበረበት፡፡ እና በፓርላማ ውስጥ የፈለገ ደስታ ቢነገር ጭብጨባ አይደረግም ተብሎ አዳራሹ የጉባኤ ሳይሆን የሱባኤ እንዲመስል የተደረገው የዛኔ ነበር፡፡ (መሰለኝ)
የሆነው ሆኖ የፓርላማ አባላቱ ተደፋፍረዋል፡፡
ዛሬ በስንት ጊዜዬ ዛሬ ፓርላማውን ብመለከተው አባላቱ ቀላል ተደፋፍረዋል እንዴ… (በእርግጥ እኔም ትንሽ አጋንኛለሁ…) ነገር ግን  ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ንግግር በሚያደርጉበት ጊዜ አቶ አባ ዱላ ገመዳን ጨምሮ ሌሎች የፓርላማ አባላት ሲያፋሽኩ እና ሲያንሾካሹኩ ማየቴ ሲገርመኝ፤ ወይዘሮ እምዬ ቢተው የተባሉ የፓርላማ አባል ደግሞ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን፤  እንደ ዋዛ ሚኒስትሩ ብለው ሲጠሯቸው ሰማሁ፡፡
ይቺን ይወዳል የደሳለኝ ልጅ! “ታላቁ” መባል ቢያንሳቸው …ጠቅላይ ሚኒስትር… መባል ደግሞ ሊበዛባቸው ነው እንዴ!?
ከሁሉ ከሁሉ ግን ማፋሸኩም ይሁን፣ ማንሾካሾኩም ምንም አይደል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተራ ሚኒስቴር አድርጎ መጥራትም እንግዲህ ምን ደረጋል… ነገር ግን በርካታ የፓርላማ አባላት ድሮ በመለስ ጊዜ እንኳንስ መለስ መጥተው ይቅርና ለተለያዩ “ኮከስ” ስብሰባዎች ላይ የማይቀሩት ሁሉ ዛሬ ከምክር ቤቱ በቀሪ መመዝገባቸው ትልቅ መደፋፈር አይደለምን!

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate