ከእንግሊዝ አገር የተመለሰ የእንግሊዝ አግር ዜግነት ያለው ኢትዮጲያዊ ከግንቦት 7 በተገናኘ ታስሮ ክስ ተመሰረተበት። ፈንጂ ቀርቶ ጅራፍ እንኳን ማጮህ ስልጠና በማይሰጥበት አገር ሰውን ፈንጂ ማፈንዳት ሲያሰለጥን ተያዘ ብሎ አገሩን እንዲጠላ ማድረግ ግፍ ነው።
መንግስት “ሽብርተኛ” ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነውና በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው የግንቦት 7 አባል በመሆን የፈንጂ ስልጠና ሰጥተዋል በተባሉት ሻለቃ ማሞ ለማና አቶ አበበ ወንድማገኝ ላይ የቀረበው ክስ ከትላንት በስቲያ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰማ፡፡ በእለቱ በተነበበው የክስ መዝገብ ላይ አቶ አበበ ወንድማገኝ፤ በእንግሊዝ ሃገር ከሚገኙት ሻለቃ ማሞ ለማ ጋር በተደጋጋሚ በዱባይና ለንደን በመገኘት የፈንጂ ጥቃት ለማድረስ የሚያስችል ስልጠና በኤርትራ ወስደዋል ይላል፡፡
ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ፣ ግለሰቦችን በመመልመል የትጥቅ ትግል ለማድረግ በማሰልጠን ለሽብር ተግባር አነሳስተዋል በማለት አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ፣ አቶ አበበ ወንድማገኝ ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም ቦሌ ሰሚት አካባቢ መኪና ውስጥ 10 “c4” የተሰኙ ፈንጂዎችንና ማቀጣጠያ ገመዶችን ይዘው ተገኝተዋል ብሏል፡፡ የተከሳሽ ጠበቃ ባቀረቡት መቃወሚያ፤ የአቃቤ ህግ ክስ በየትኛው አዋጅ እንደቀረበ ክሱ እንደማያመለክት ጠቁመው፤ አቃቤ ህግ ያቀረበው የክስ አንቀፅ እንዲያሻሽል ፍ/ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ስልጠና መስጠትን ብቻ የሚመለከት ስላልሆነ ራሱን አንዲያሻሽል ጠይቀዋል፡፡ አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ የተከሳሽ ድርጊት በሰው ህይወት፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል እንደነበር የሚያካትት ክስ እንዳቀረበ ገልጿል፡፡ “ተከሳሹ ስልጠና ብቻ ነው የሰጠው” የሚባለው ጉዳይ ማስረጃ የምናረጋግጠው ነው በማለት አቃቤ ህግ አክለው ገልፀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ለማስታወስ ያህል:-ተቀማጭነቱ ለንደን የሆነው የኢትዮጵያ ዳንኪራ የዳንስ ግሩፕ አባል የሆነችው አርቲስት እስከዳር ታምሩ እና ባለቤቷ አበበ ወንድምአገኝ በደህንነት ሃይሎች ቦሌ አካባቢ ተይዘው ታስረው እንደነበር ይታወሳል። ከሎንደን ወደ አዲስ አበባ የሁለት አመት ልጃቸውን ይዘው የሔዱት በአል ለማክበር ነበር። እስከዳር ስትለቀቅ አበበ አሑንም እስር ቤት ሲሆን ፍርድ ቤት ቀርቦ የሃያ ቀን ቀጠሮተሰቶት እንደነበር ይታወሳል። ቤተሰቦቹ የእንግሊዝን ኤምባሲ ስለጉዳዩ አሳውቀው ነበር። ምክንያቱ “ፖለቲካዊ” ነው እሚል ጥርጣሬ ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment