ወ/ሮ የስራሽ ወርቁ (የቀን ሰራተኛ)
አቶ ታደለ ያለው (ነጋዴ)
ወ/ሮ አስማሩ ለገሰ
አቶ አሰፋ በላቸው
አቶ በአለምላይ ባዩ
ዮሐንስ ዋቤ የቅፅል ስሙ ጃጏር (የፖሊስ
ባልደረባ የነበረ)
ተካ ማሩ (የቀን ሰራተኛ)
ወ/ሮ ገነት ባሲ
ሞገስ ሐሰን
ሙሉቀን ቸኮል
እናት መነኩሴ
የሁለት አመቱ ሕፃን ቸርነት ዜና(ናቲ)
ቆስለው በፈለገ ሆስፒታል የሚገኙት ደግሞ
ወ/ሮ እናት ማሩ
አቶ ደረጄ ማሩ እንደሆኑ ታውቋል።
እኔ ምለው ጎበዝ…"መንግስት" ገዳዩ በፍቅር ያበደ እብድ ነው እያለን ነው። እሺ ይሁን እንበል፣ ተፋቃሪዋን ፈልጎ ቤት ሲሄድ አጣት(አልፈለግህም ብላው ስለነበር) የመጀመሪያውን ጥይት እናቷ ላይ ተኩሶ ገደለ… ከዛ…በጋኘው የአዳም ዘር ላይ አርከፈከፈው……ይላል "መንግስት"…ሌላውን ለግዜው እንተወው እና አንድ ጥያቄ ልጠይቅ… ከሟቾች ውስጥ የትያኛዋ ናቸው የ "በፍቅሯ ሰው አስገዳይ" እናት? ? "አፍቃሪዋ" ፍቃዱ ናሻ ከሆነ "ተፈቃሪዋ" ማን ትባላለች?? ፍቃዱ ናሻስ ማነው? ጓደኞች ፣ቤተሰቦች የሉትም??
ይህን ጥያቄ "መንግስት" መመለስ አልቻለም ምክንያቱም የውሸቱ መሰረት ይናዳላ! ፍቃዱ ናሻ ተብሎ በድኑ የታየው የፌድራል ፖሊስ ፋቲክ ለባሽ ከሟቾቹ እኩል የሚያሳዝን የመስዋእት ፍየል (scapegoated) ነው። በማያውቀው፣ባልዋለበት የድሆች ለጅ። የፌድራል ፖሊስም ላይሆን ይችላል፣ ስሙም ፍቃዱ ናሻ ላይሆን ይችላል።
እና ማነው ታድያ ትክክለኛ ጨፍጫፊው? ለምን? አሁን የት ነው ያለው…እንደዛ ቀብረር በሎ ሲገል የነበረው ማን ቢሆን ነው? ሲያርድ እያዩ ሊያስቆሙት ያልቻሉት ለምንድን ነው?
ተለባብሶ የማይቀር ሃቅ አለ! ሃቁን እንፈልግ………በተለይ ጋዜጠኞች ሃቁን ቆፍራችሁ(ብዙም መቆፈር አያስፈልግም ፣ጫር ጫር ማድረግ ብቻ) ማውጣት ሞያዊም ሃገራዊም ግዴታ አለባችሁ!! ከህዝብ አይን እና ጆሮ ማንም ማምለጥ አይችልም!
ሌላው እዚሁ ፌስቡክ ላይ ያገኘነው ታሪክ፣ የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን) መግለጫ ነው። አወጋን ማነው? አላማው? ግቡ?………? ? ? …የሚሉት ጥያቄዎች ለግዜው ትኩረቴን አልሳቡትም ፣ ቀልቤን የሳበው "መግለጫው" ነው…………እንደ አወጋን አባባል አሁድ እለት ከቀኑ በ9:05 ሰአት(ልብ በሉ ሰአትን ደቂቃ ጠቅሰዋል) ላይ መብርሃቱ ኪሮስ የተባለ በባህርዳር የፌድራል ፖሊስ አዛዥ ፣ድሮ የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ ፣አድግራት ተወልዶ እስቴ(ደቡብ ጎንደር) ያደገ ከሌሎች ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ጋር (ስማቸውን አልጠቀሰም……"???") በ"አወጋን " በጥይትተመተው ተገለዋል። ይቀጥላል "አውጋን" …ዳዊት ኪሮስ ፣ የሟች መብርሃቱ ኪሮስ ወንድም…እዛው ባህርዳር ውስጥ የፌድራል ፖሊስ የሆነ…የወንድሙን ሞት በስልክ ሲነገረው (ማነው የነገረው? ከስንት ሰዓት በኋላ? ……) ደም ፍላታሙ ዳዊት ኪሮስ መሳሪያወን አንስቶ በንፁሃን ላይ ቀብረር በሎ አርከፈከፈው። ደክሞት ይሁን ፣ በቅቶት ወይም በክልሉ ፖሊሶች ተይዞ ፣ ግድያወን አቆመ……
የ"አውጋን" መግለጫ ፉርሽ ለማድረግ
#ፍቃዱ ናሻ፣ተፋቃሪ ተብየዋ እስከ እናቷ
በዝርዝር መታወቅ አለባቸው።(ይህን የማድረግ ስራ የ" መንግስት" ሰራ ነው።)
#መብርሃቱ ኪሮስ ፣ዳዊት ኪሮስ የሚባሉ የፌድራል ፖሊሶች( በስም ያልተጠቀሱትን ሁለቱን ትተን) እውነት በባህርዳር ከተማ የፌድራል ፖሊስ የአባላት ስም መዝገብ ውስጥ አሉ? ካሉስ አሁን የት ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዊች መመለስ ግድ ይለናል………
እነዚህ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ግን ፣ "ከመንግስት" የዜና አውታሮች ይልቅ ፣እዚሁ ፌስቡክ ላይ ያነበብኩት የ"አወጋን" ኤዲተር ያልዞረው "እውነቱ ይህ" ነው አይነት መግለጫ ቢጤ እውነት እውነት የሚሸት ነገር አግኝቸበታለሁ።
በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችን ደመ ከልብ ሁነው አይቀርም!
"ቃየል ሆይ ፣ ወንድምህ አቤል የት አለ?…………"
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment