skip to main
|
skip to sidebar
freedom more than food !!!
Pages
Home
About Me
Unknown
View my complete profile
Popular Posts
must watch very painfullllllll Italy, says coastguards stopped him saving more people
A fisherman who rescued 47 people after a migrant boat sank off the coast of Lampedusa, Italy, says coastguards stopped...
የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ
በአንድ ወቅትአንድ ዘጋቢ የኢትዮጵያን ባንዲራ በሚመለከት ተዘዋውሮ ካናገራቸው የመዲናይቱ ነዋሪዎች አንዱ፥ “እኛ አገራችንን የምንወደው ወያኔዎች ስለነገሩን አይደለም። እሱማ ባንዲራችንን ባጥላሉበት ዘመንም አገራችንን ...
ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀዋል
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከ3 እስከ 4 ሺ የሚሆኑ ከቤንሻcccጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ከመስተዳድሩ ፊት ለፊት ባለ ሜዳ ...
(no title)
http://www.facebook.com/photo.php?fbid=267236960061508&set=a.120473778071161.20651.100003256176895&type=1&ref=nf
EPRDF, no identity and no vision
FOR IMMEDIATE RELEASE EPRDF, no identity and no vision ...
ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ:ነኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተመልሳ ልትመጣ ነው… “የት ሄደሽ ነበር…?” አለ ፋንቱ! | አቤ ቶኪቻው
ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተመልሳ ልትመጣ ነው… “የት ሄደሽ ነበር…?” አለ ፋንቱ! | አቤ ቶኪቻው
Blog Archive
Sep
(4)
Nov
(64)
Dec
(172)
Jan
(133)
Feb
(35)
Mar
(35)
Apr
(39)
May
(36)
Jun
(32)
Jul
(71)
Aug
(14)
Sep
(11)
Oct
(28)
Nov
(9)
Dec
(7)
Jan
(6)
Mar
(2)
Jun
(1)
Jul
(1)
Feb
(1)
ESAT NORWAY
You can replace this text by going to "Layout" and then "Page Elements" section. Edit " About "
noway. Powered by
Blogger
.
Social Icons
Followers
Featured Posts
Jul 13, 2013
የማለዳ ወግ. . .ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ ፣ መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም (አልጀዚራ)
ነቢዩ ሲራክ
*”በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! “
አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌ
ልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia’s unemployment “በኢትዮጵያ ስራ
አጥንትን ለመሸሸ ” ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥ
አሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
እማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል
አልጀዚራ ያቀረበወን ዜና እዚህ ላይ ይጫኑና ይመልከቱ
።
በዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶች
ስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ዶላር ያበድራል ተብሎ ሰምቻለሁ። የተባለው በእኛ
ሃገር ይሆን ? ስልም ጠየቅኩ ! ” ጀሮ ለራሱ ባዳ ነው “ብየ አላየሁ አልሰማሁም ብየ ልለፈው! አሁን ሰምቻለሁና
ይሰጣልም ብየ ለቀበለው ። ግናስ ለብድር አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው? ይህ ግን አልገባኝም ! መስፈርቱ ወሳኝ
ሆኖም ይህንንም አድልኦ ሰዎች በፖለቲካ አምለካከት በሃይማኖትና በዘር ሳይለዩ እኩል ታይተው ድጋፉ ይደረጋል
በሚል ልቀበለው ። የተባለው ሁሉ እውነት ቢሆን እንኳ የተጠናን ስራ አውርቦ ጠቀም ያለ ብድር የማግኘት እድሉ
ተምሮ ስራ ላጣው አለያም ለነቃው እና ለተደራጀው የከተማ ወጣት እንጅ ለቀረው መፍትሄ አይደለም ።
ይህ መፍትሄ በዘገባው ቀርበው ላየናቸው
በማንኛውምወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ
ለመሰደድ ለተዘጋጁት እና ከህጋ የሃገራት ሁለትዮሽ
ስምምነት ውጭ ለሰደዱት ከገጠሩ ክፍል የሚጋዙት
ቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱት
እህቶች የሚፈይደው ነገር የለም ።በአረብ ሃገር
በኮንትራት ስም የሚሰደዱ እህቶችን እንዳይሰደዱ
ለማገድ አሸጋጋሪ ደላላዎችን ከመቆጣጠሩ ጎን ለጎን
ዜጎችን ከድህንት የሚዎጡበትን መንገድ መንደፍ ፣
የዜጎችን ነጻነት ማክበር አና ሁሉንም ዜጎች እኩል
በማየት መሰረተ ልማቶቸን በማስፋፋት የስራ እድል
መክፈት ዋናው መፍትሔ ሊሆን ይገባል።
“ኢኮኖሚያችን አደገ ተመነደገ” እየተባለ አቅማችን
ይህ ማድረግ ካልቻለ ብቸኛው መፍትሄው ” አትሰደዱ” ብሎ መልፈፉና እና “ለሚሰሩት እድሉ ” አለ ብሎ መደስኮሩ
ከመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም ! ስደት ክፉ ነገር ነው ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑት
እያላቸው ካላቸው ለመጨመር ከሚሹ ስግንግቦች ውጭ ብዙው ስደተኛ ለመሰደዱ የስራ ማጣት ፣ የድህነትና የኑሮ
ውድነት በቂ ምክንያት እናዳለው በስደቱ አለም ስኖር ካገኘኋቸው ስደተኛ ወገኖቸ የተረዳሁት ሃቅ ነው ።
የኑሮ ውድነት ሳያንገሸግሽ ፣ ሳያጨናንቀው ስደትን የሚፈልግ የለም ፣ በሃገሩ ተምሮና ሰርቶ እሱንና ቤተሰቡን መደገፍ
እየቻለ ስደትን የሚመርጥ የለም ! የመንግስት ሃላፊዎች ለገጽታ ግንባታ የሚለቋቸውን መረጃዎች ገታ አድርገው
በስደተኛው ችግር ላይ ቢያንስ ትክክለኛ መረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር ። ከሁሉም በላይ ወደ አረብ ሃገራት
በኮንተራት ስራ ስም የሚላኩ ዜጎችን ጉዳይ ቆም ብለው ሊመረምሩት ይገባል። ሰው ” በሃገሬ ተቸገርኩ ፣ ተምሬ ስራ
አጣሁ !” እያለ ስደቱን ማቆም ይከብዳል። ያም ሆኖ በህገ ወጥ ደላላ ተታልለው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱትን
ለማስቆም መንግስት በስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ስም እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥ የበከተ ድልላ በሰውር የሚሰራውን
ስራ ሰንሰለቱን ከቁንጮው ሊበጣጥሰው ይገባል ። ስደትን ማሰወቆም ካልቻልን አማራጩ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገር
እና ሊሰሩት ስለሚችሉት ስራ ትክክለኛ መረጃ እና ቅድም ዝግጅቶችን በትክክል አሟልቶ ማቅረብ አማራጭ ሊታይ
ይገባል። ከዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ዜጎችን በሃገራት መካከል በሚደረግ የሰራተኛ ውል መሰረት በህጋዊ ኮንትራት ስራ
ዜጎችን መላክ እና ከተላኩም በኋላ በመብት ማስከበሩ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት በፖለቲካ
ታማኝነት ሳይሆን ዲፕሎማሲው ጥብብ የተካኑትን ከሃላፊዎች በበቂ ሁኔታ በአረብ ሃገራት ሊመድብ ይገባል! ያለንት
የስልጣኔ ዘመን ነውና መረጃን በመደባበቅ እውነትን ማጥፋት አይቻልም።
ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማቀበል ያዋርዳል እንጂ አያስከብርም ፣ ከሃቅ የራቀ መረጃ ገጽታን ያጨለማል እንጅ ፈካ
አድርጎ ቀይሮ አያሳይም ! በአልጀዚራ ዘገባ እንደተነገሩት አንዳንድ መረጃዎች አጋጣሚውን ገጽታ መገንቢያ አድርገን
እውነቱን የምንሸፋፍን ከሆነ ትልቅ ስህተት ተሳስተናል ! እውነትን በውሸት ለመድፈን ስንቆፍር ነገም እንደ ትናነቱ
ከመከራ መውጣት አይቻለንም ! ዛሬም ጉዟችን ቅጥፈት ከሆነ በምናየው የወገን ሮሮ ፣ የሰቆቃ ድግግሞሽ ስናለቅስ
እንደኖርን ስናለቅስ እንኖራለን ! አባቶች “በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! ” እኛው ራሳችን በሽታችን
ስንነግራቸሁ ስሙን ፣ መድሃኒቱንም ፈልጉልን ! የማለዳ ወጌን አበቃሁ !በሽታችን ተረድቶ መድሃኒት ጀባ የሚል
የህዝብ አገልጋይ ይስጠን!
ነቢዩ ሲ
ራክ
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Total Pageviews
Translate
POLETICAL PARTIS
DCESON
ENTC
EPRP
ginbot 7
Ginbot 7 Popular Force (GPF)
ETHIO NEWS AND NEWS
goolgule
ecadforum
zehabesha
esat tv
finote nesanet
abbaymedia
EAGLEWINGS
ethiopia reporter
ethiopianreview
ethiopia zare
quatero
esat radio
ethioline
aweramba
addisneger
abe tokichaw
abugida
ethiomedia
maledatimes
RADIO AND TV
Addis Dimts
ከኦሮምያ ባለስልጣን የተላከ – የኦህዴድ ባለስልጣኑ የአብይ አህመድን ስውር ቡድን አጋለጠ
4 months ago
የአሜሪካ ድምፅ
በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሣን የእሳት ቃጠሎ ለማስቆም ጥረቱ ቀጥሏል
8 months ago
(ESAT)
Ethiopia -Esat Amharic Day Time News Thu 5 Jul 2022
2 years ago
Blogger templates
No comments:
Post a Comment