በዚሁ ሰበብ ፖሊስ ከቢሮው ንብረቶች እንደወሰደበት እንዲሁም እሁድ እለት ሰልፉን ሊያካሂዱ ሲሉ መንገድ በመዝጋት ሰልፉን እንዳቋረጠባቸው ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። አንድነት ፓርቲም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ሌላ አማራጭ ቦታዎች አቅርብ ከተባለ በኋላ ያቀረበው ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰልፉን ጃንሜዳ አድርግ እንደተባለ አስታውቋል። በዚሁ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መውጣቱን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን ቦታና ጊዜ የሚወስነው መስተዳድሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ “አሁን የቀራቸው የምትቃወሙትንም የምንሰጣችሁ እኛ ነን” ማለት ብቻ ነው ሲሉ ክፉኛ አሽሟጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አዲስ ወጣ በተባለው መመሪያ ተናዶ ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? “እንደዚያ ከሆነማ ለምን ሰልፍ የሚወጣውንም ህዝብ እነሱ አይመድቡልንም?” በአሁኑ ጊዜ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎች ሰልፍ በጣም አስፈርቶታል የሚለው ይሄው የተቃዋሚ ደጋፊ፤ “በመኪና ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ለመበተን፣ ወዘተ--- ለሁሉ ነገር አስፈቅዱኝ እያለ ነው፣ ለምን መፈክሮቹንም እሱ አያዘጋጅልንም” በማለት አዲስ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለገዢው ፓርቲ አበርክቶለታል። “እናም ኢህአዴግ በቅርቡ “ሰላማዊ ሰልፍ እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ አጀንዳዎችን እንቀርፃለን፣ ለሰልፍ የሚወጣ ህዝብ እንመለምላለን፣ በራሪ ወረቀቶችን እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እናደርጋለን ወዘተ-- የሚል ልዩ ማስታወቂያ በኢቴቪ ሲያስተላልፍ ልንሰማ እንችላለን” ብሏል - የተቃዋሚ ደጋፊው። (ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!) ምንጭ፦ ሚኒሊክ ሳልሳዊ
Sep 29, 2013
ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!!!
“የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ ---- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ---- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ።
ማን ነው የሚለየው ይህ ትውልድ ለወያኔ ፍም እሳት ነው !!! የዕለቱ ምርጥ ዘፈን በኖርዌይ ኦስሎ ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ !!!!
በኖርዌይ የሚገኘው ይህ የምትመለከቱት ዌብሳይት ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ የተደረገውን ለግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በ26.09.2013 13:23 ላይ የተለመደውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የነዛበት ሊንክ እና ፕሮግራሙን እንዳይካሄድ ለማድረግ ብዙ የደከመበት ስራ ይህን ይመስል ነበር
ይቺን ሊንክ ይጫኑ http://www.abesha.no/P%C3%A5-Amharisk/1372
ወያኔ ጥጋብ በወለደው እብሪቱ በማንአለብኝነት የህዝብን መብትና ነጻነት ረግጦ በአፈና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አለኝታየ በሚላቸው የፖሊስ፣ የደህንነትና ወታደራዊ ኃይሎች እስከ መጨረሻው አጠናክር ለመቀጠል የሚችል አድርጎ ያስባል። በዚህም ምክንያት እስካፍንጫው ባስታጠቀው ወታደር ብዛትና በነዋሪው ቁጥር ልክ ህዝብ መሃል ባሰማራው ሰላዮች የተገነባው የፍርሃት ግምብ የሚናድም መስሎ አይታየውም። ሃቁ ግን በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተሰባሰቡ ወጣቶችም ሆኑ መላው አለም ላይ የሚገኙ በተለይም በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች እና ወያኔን በአራቱም የአገራችን ማዕዘናት ለመግጠም ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወያኔ ህዝባችንን ሊያስፈራራ የሚችልበትን ሁሉ በጣጥሰው ለመውጣት ምንም ችግር የሌለባቸው መሆኑን በትላንቱ በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ግንባሩን ወክለው የመጡት እንግዳ እና ኢትዮጵያኖቹ በኩራት እና በቁርጠኝነት ተናግረዋል።
በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የተገደዱት የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን በገንዘብ ለመርዳት ታስቦ የነበረውን ቀን በኖርዌይ የሚገኙ ጸረ ኢትዮጵያን የወያኔ ደጋፊ ጉጅሌዎች ለተወሰነ ሰዓታት ባደረጉት የተሳሳተ ወይንም ያልተገባ ውሸት በደስታ የተፍነከነኩበት በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያን ቁርጥ ልጆች ድል ተጠናቋል
ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። በመጨረሻም በኖርዌይ የምንገኝ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የምናስተላልፈው ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው።
፦ ወያኔ ገንብቻለሁ ብሎ የሚኮፈስበትን የፍርሃት ግምብ ደርምሰው ለነጻነታቸው ሲሉ ውድ የህይወት ዋጋ ለመክፈል በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ዙሪያ መሰባሰባቸውን ይፋ ያደረጉ እነዚህ ወጣቶችን በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የተነሱለትን ክቡር አላማ ያደንቃል። በዚህም ምክንያት ለነጻነቱ ቀናኢ ለሆነው ለህዝባችን ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ወቅታዊነት ሁሉም እንዲረዳው እና በመላው ዓለም ላይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የበኩሉን አሰተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ያሬድ ኤልያስ nome telemark
ያሬድ ኤልያስ nome telemark
Sep 24, 2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!
የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ዋነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊና ዘላቂ ጥቅም ጠላት ወያኔ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ይህንን አባባል አንድ ተቃዋሚ ለተቃውሞ ያህል ወይም ስርዓቱን የሚጠላ አንድ ግለሰብ ስርአቱን ስለሚጠላዉ ብቻ እንደተናገረው አድርጎ አቃልሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከአሁኑ ቅጽበት ድረስ በሀገራችን ላይ የፈጸመውን ደባ በቅጡ ያላዩ ሰዎች ይህ አባባል የተጋነነ ይመስላቸው ይሆናል። ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ አገር የቆመችዉ በህዝቦቿ ታላቅነትና እንዲሁም ለታሪካቸው ባሳዩት ክብርና ብርታት ነዉ እንጂ እንደወያኔማ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ከወደቀ ሰንብቷል።
ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።
መገነጣጠል ግብ እንዲሆን በህገ መንግስት ደረጃ አንቀጽ ጽፎ ያስቀመጠው ወያኔ እሱ እንደሚለዉ ለብሔረሰቦች መብት አስቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ አልዘረፍ ካለችን በትነናት ብንሄድስ ከሚል አላማ መሆኑን ሌናጤን ይገባል። ከምር ለብሄረሰቦች መብት በመቆርቆር ቢሆን ኖሮ ከጠመንጃና ከፍጅት በፊት የብሄረሰቦችን መብትና ነጻነት አክብሮ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ይተዋቸዉ ነበር።።
ወያኔ ኢትዮጵያን የሚፈልጋት ለርሱና ለጋሻ ጃግሬዎቹ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሆና ስላገኛት ብቻ ነው። ሀገሪቱን እያለማሁ፣ እያሳደግኩ ነው የሚለው ዲስኩር ለተራ መደለያ እንኳን የማይሆን ውሸት ለተራበው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ያውቀዋል።
የሀገሪቱን ለም መሬት በሄክታር ባንድ ፓኮ ሲጋራ ዋጋ የሚቸረችረው ወያኔ እነዚህ ባእዳን በጎን የሚሰጡትን የሀገራችንን መሬት ዋጋ ኪሱ መክተቱን አረጋግጦ ነው። ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚነዛው የኬሚካል ማዳበሪያ በጥቂት አመታት ውስጥ የሀገሪቱን አፈር ድራሽ እንደሚያጠፋ ወያኔ የአዋቂዎች ምክር ሳይሰማ ስለቀረ አይደለም። በአጥፊ ስራው የቀጠለው መዝረፍ የሚችለዉን ንብረት ካጋበሰና ከዘረፈ በኋላ ነገ ኢትዮጵያ እንደአለ ባድማ ብትሆን ቅንጣት ስለማይሰማዉ ነዉ። ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአገሪቱ ወጣትና የተማረ የሰዉ ኃይል እንደ ጎርፍ ከአገሪቱ እየጎረፈ ሲወጣ ይቆረቆር ነበር። ወያኔ የተማረ ሰው ቢሰደድ፣ ዜጎች ቢራቡና በገዛ አገራቸዉ ቢዋረዱ ጉዳዩ አይደለም። በሰላማዊና ህገመንግስታዊ መንገድ ጥያቄ ያነሳን ዜጋ ሁሉ እንደአውሬ የሚቀጠቅጠውና ወህኒ ቤት የሚያጉረው ይህ በደል ነገ በሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና ላይ የሚያመጣውን መዘዝ አጥቶት አይደለም። የአገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጉዳዩ ስላልሆነ እንጂ።
የኢትዮጵያን ብሄር ቤሄረሰቦች የሚያይዟቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድነት ክሮች እያንቋሸሸና እንደሌሉ እየሰበከ በሚለያዩንን ጥቃቅን ውጭያዊ የቋንቋና የዘር ግንዶች አጉልቶ የሚያሳየን አገራችንንና ህዝቧን እንደ አንድ ሀገር ሳይሆን እንደጊዚያዊ የዝርፊያ ቀጠና ስለሚመለከት ብቻ ነው።
ወያኔና ሎሌዎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላቶቹ ናቸው እያሉ አንዴ የፈረሰችዉ ሶማሊያን፤ ሌላ ጊዜ ወደ ኤርትራና ግብጽ ጣቱን የሚጠነቁሉት አይናችንን ከወያኔ ላይ እንድናነሳ ነዉ እንጂ ከወያኔ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላት የለም። ወያኔ በአካል እኛን ከሚመስሉ ኢትዮጵያውያን መሃል ይውጣ እንጂ፣ በተግባር ከቀን ጅብ ያልተናነሰ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ራሱ የጻፈውን ህግ ሲጥስ ለምን ብለን የምንገረም አለን። ወያኔ ሕግና ሕገ-መንግስት፣ ለአገራቸዉ የሚቆረቆሩ ምሁራንን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ የሚታመን ሰራዊት፣ ለህግ ብቻ የሚሰራ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ዘላቂ ተቋማት እንዳይኖሩን የሚያደርገውና ያሉትንም የሚያፈርሰው ለኢትዮጵያ ብሄራዊና ዘላቂ ጥቅም ምንም ደንታ ስለሌለዉ ነዉመሆኑን የሚዘነጋ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ የዋህ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።
ስለዚህም እንላለን እኛ የግንቦት 7 ልጆችህ ሀገርህ ትውልድ ተሻግራ እንድትቀጥል አንተም የምትኮራባት ዜጋ እንድትሆናት የምትሻ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ሀገርህን ከወያኔ የቀን ጅቦችና ወራሪዎች አድን። አጎንብሰህ ሳይሆን ቀና ብለህ የምትሄድባት ሀገር እንድትኖርህ የምትሻ ሁሉ ለማይቀረው የጀመርነውን የአርበኝነትና የነጻነት ትግል ጉዞ ተቀላቀለን። እኛ የተባበርን እለት አብረን የተነሳንና በቃ ያልን እለት ታሪካዊቷ ሀገራችንና ታላቁ ሕዝባችን ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅማቸው ይከበራል።
አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።
መገነጣጠል ግብ እንዲሆን በህገ መንግስት ደረጃ አንቀጽ ጽፎ ያስቀመጠው ወያኔ እሱ እንደሚለዉ ለብሔረሰቦች መብት አስቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ አልዘረፍ ካለችን በትነናት ብንሄድስ ከሚል አላማ መሆኑን ሌናጤን ይገባል። ከምር ለብሄረሰቦች መብት በመቆርቆር ቢሆን ኖሮ ከጠመንጃና ከፍጅት በፊት የብሄረሰቦችን መብትና ነጻነት አክብሮ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ይተዋቸዉ ነበር።።
ወያኔ ኢትዮጵያን የሚፈልጋት ለርሱና ለጋሻ ጃግሬዎቹ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሆና ስላገኛት ብቻ ነው። ሀገሪቱን እያለማሁ፣ እያሳደግኩ ነው የሚለው ዲስኩር ለተራ መደለያ እንኳን የማይሆን ውሸት ለተራበው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ያውቀዋል።
የሀገሪቱን ለም መሬት በሄክታር ባንድ ፓኮ ሲጋራ ዋጋ የሚቸረችረው ወያኔ እነዚህ ባእዳን በጎን የሚሰጡትን የሀገራችንን መሬት ዋጋ ኪሱ መክተቱን አረጋግጦ ነው። ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚነዛው የኬሚካል ማዳበሪያ በጥቂት አመታት ውስጥ የሀገሪቱን አፈር ድራሽ እንደሚያጠፋ ወያኔ የአዋቂዎች ምክር ሳይሰማ ስለቀረ አይደለም። በአጥፊ ስራው የቀጠለው መዝረፍ የሚችለዉን ንብረት ካጋበሰና ከዘረፈ በኋላ ነገ ኢትዮጵያ እንደአለ ባድማ ብትሆን ቅንጣት ስለማይሰማዉ ነዉ። ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአገሪቱ ወጣትና የተማረ የሰዉ ኃይል እንደ ጎርፍ ከአገሪቱ እየጎረፈ ሲወጣ ይቆረቆር ነበር። ወያኔ የተማረ ሰው ቢሰደድ፣ ዜጎች ቢራቡና በገዛ አገራቸዉ ቢዋረዱ ጉዳዩ አይደለም። በሰላማዊና ህገመንግስታዊ መንገድ ጥያቄ ያነሳን ዜጋ ሁሉ እንደአውሬ የሚቀጠቅጠውና ወህኒ ቤት የሚያጉረው ይህ በደል ነገ በሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና ላይ የሚያመጣውን መዘዝ አጥቶት አይደለም። የአገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጉዳዩ ስላልሆነ እንጂ።
የኢትዮጵያን ብሄር ቤሄረሰቦች የሚያይዟቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድነት ክሮች እያንቋሸሸና እንደሌሉ እየሰበከ በሚለያዩንን ጥቃቅን ውጭያዊ የቋንቋና የዘር ግንዶች አጉልቶ የሚያሳየን አገራችንንና ህዝቧን እንደ አንድ ሀገር ሳይሆን እንደጊዚያዊ የዝርፊያ ቀጠና ስለሚመለከት ብቻ ነው።
ወያኔና ሎሌዎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላቶቹ ናቸው እያሉ አንዴ የፈረሰችዉ ሶማሊያን፤ ሌላ ጊዜ ወደ ኤርትራና ግብጽ ጣቱን የሚጠነቁሉት አይናችንን ከወያኔ ላይ እንድናነሳ ነዉ እንጂ ከወያኔ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላት የለም። ወያኔ በአካል እኛን ከሚመስሉ ኢትዮጵያውያን መሃል ይውጣ እንጂ፣ በተግባር ከቀን ጅብ ያልተናነሰ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ራሱ የጻፈውን ህግ ሲጥስ ለምን ብለን የምንገረም አለን። ወያኔ ሕግና ሕገ-መንግስት፣ ለአገራቸዉ የሚቆረቆሩ ምሁራንን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ የሚታመን ሰራዊት፣ ለህግ ብቻ የሚሰራ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ዘላቂ ተቋማት እንዳይኖሩን የሚያደርገውና ያሉትንም የሚያፈርሰው ለኢትዮጵያ ብሄራዊና ዘላቂ ጥቅም ምንም ደንታ ስለሌለዉ ነዉመሆኑን የሚዘነጋ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ የዋህ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።
ስለዚህም እንላለን እኛ የግንቦት 7 ልጆችህ ሀገርህ ትውልድ ተሻግራ እንድትቀጥል አንተም የምትኮራባት ዜጋ እንድትሆናት የምትሻ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ሀገርህን ከወያኔ የቀን ጅቦችና ወራሪዎች አድን። አጎንብሰህ ሳይሆን ቀና ብለህ የምትሄድባት ሀገር እንድትኖርህ የምትሻ ሁሉ ለማይቀረው የጀመርነውን የአርበኝነትና የነጻነት ትግል ጉዞ ተቀላቀለን። እኛ የተባበርን እለት አብረን የተነሳንና በቃ ያልን እለት ታሪካዊቷ ሀገራችንና ታላቁ ሕዝባችን ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅማቸው ይከበራል።
አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Sep 23, 2013
Sep 21, 2013
Sep 20, 2013
Sep 19, 2013
ጉዲፈቻ የሰው ልጆች ንግድ ‹‹ከቤተሰቤ ተሰርቄ ነው የተወሰድኩት››
ታሪኳ ለማ፣ በጉዲፈቻ አሜሪካ የተወሰደችው ጉብል
በተለያዩ ምክንያቶች አሳዳጊ የሌላቸው ተብለው የሚታሰቡ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ወደ ተለያዩ አገሮች ይሄዳሉ፡፡ ‹‹የተሻለ ሕይወት›› ይኖራቸዋልም በሚል እሳቤ ቤተሰብ ያላቸውን ሕፃናትም ሕገወጥ በሆነ ሰርቆ መስጠት እንዲሁም በደላሎች አማካይነት የሚሠሩ ሥራዎችም እንዳሉበት በርካታ ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሲኤንኤን መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ያወጣው ይህንኑ አስከፊ እውነታ የሚመሰክር ነው፡፡
ታሪኳ ለማ የ19 ዓመት ዕድሜ ያላት ወጣት ናት፡፡ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ነበር ከሁለት ታናናሽ እህቶቿ ጋር ትምህርታቸውን በአሜሪካ እንደሚከታተሉና ትምህርት በማይኖርበት በማንኛውም የዕረፍት ጊዜ ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ እየመጡ ቤተሰቦቻቸውን እንደሚያዩ ቃል ተገብቶላቸው እናት አገራቸውን የለቀቁት፡፡
ዛሬ ማይኒ የምትኖረው ታሪኳ ለማ የኮሌጅ ተማሪ ስትሆን፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ የመሆን ህልም አላት፡፡ በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ ተወስደው ስላለፉት የሕይወት ውጣ ውረድ እንደሚከተለው ተርካዋለች፡፡
‹‹የተሸጥኩት አሥራ ሦስት ዓመቴ ላይ ነበር፡፡ ከቤተሰቤ ተሰርቄ የተወሰድኩት፡፡ እኔና እህቶቼን ለትምህርት ወደ አሜሪካ ሊልከን እንደሚገባ አባቴን ያሳመኑት የአባቴ ጓደኞች ነበሩ፡፡ እኤአ በ2006 በተገባልን የሐሰት ቃል ኪዳን ወላጅ አባቴን አሞኝተው እንድንሄድ ተገደድን፡፡ ይህንን የሚያደርጉት የአባቴ ጓደኞች በሙስና እጃቸው የተጨማለቀና አጭበርባሪ የጉዲፈቻ ወኪል ውስጥ የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ይህም ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡
‹‹አባቴም ሆነ እኛ ስለ ጉዲፈቻ የምናውቀው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ወላጅ አባታችን የላከን ለትምህርት፣ እኛም ለመማር እንደመጣን ነበር የምናውቀው፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሹን ሆኖ ነበር ያገኘነው፡፡ ዋሽተውናል፤ የዋሹት ግን እኛን ብቻ ሳይሆን በጉዲፈቻ የወሰዱንን አሳዳጊ ቤተሰቦቻችንን ጭምር ነበር፡፡ ያመጣንላችሁ ወላጆቻቸውን በኤድስ ያጡ ሦስት ሕፃናትን ነው፤ ትልቋ ዘጠኝ ዓመቷ ነው ብለው ነበር ሴራውን ያቀነባበሩት፡፡ ይሁንና እውነታው ግን እኔ የአሥራ ሦስት ዓመት ታዳጊ ነበርኩ፡፡ የቤተሰቤም የበኩር ልጅ ነኝ፡፡ ታናሾቼ የአሥራ አንድና የስድስት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ታዳጊዎች ነበሩ፡፡
‹‹አዲሶቹ ‹ቤተሰቦቻችን› ስማችንን ቀየሩትና በአፍ መፍቻ ቋንቋችን በአማርኛና በወላይትኛ ማውራት እንደማንችልና ካወራንም ቅጣት እንደሚጠብቀን አስጠነቀቁን፡፡ እናም በስተመጨረሻ አፍ በፈታንበት ቋንቋ መናገር ተሳነን፤ እስከነ አካቴውም ረሳነው፡፡
‹‹በጣም ልጅ ነበርኩኝ፡፡ ከዚህ ካለሁበት የእሥር ቤት ሕይወት ጠፍቼ ብወጣ ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ተመልሼ የምገባ ይመስለኝ ነበር፡፡ እነኚህ ቀጣፊዎች ከትውልድ አገሬ፣ ከባህሌና ከቤተሰቤ እንደነጠሉኝ ሳስበው ውስጤ በሐዘንና በምሬት ይሞላል፡፡
‹‹ከስምንት ወራት በኋላ ከእህቶቼ ተነጥዬ ወደ ሌላ ቤት እንድጓዝ ተደረግኩኝ፡፡ አዲሱ መኖሪያዬ የተደረገው ከአሳዳጊ እናቴ ቤተሰቦች ጋር ነበር፡፡ ያም ወደ መካከለኛው ምዕራብ ነበር፡፡ እህቶቼን ለመጐብኘት የታደልኩት በጣት ለሚቆጠሩ ጊዜያት ነበር፡፡ አሁን ባለሁበት አገር መኖር ይከብዳል፡፡ ከአገሬ ኢትዮጵያና ከእህቶቼ ተነጥያለሁ፡፡ አጋጣሚዎች ክፉ ቢሆኑብኝም እጅ መስጠት አልፈለግኩም፡፡ ያለኝን አቅም ሁሉ አሰባስቤ ከአገር ውጪ በሚደረግ ጉዲፈቻ ምን ዓይነት ብልሹ አሠራርና የሰው ልጆች ንግድ እየተካሄደ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ ወሰንኩ፡፡
‹‹ከአገር ውጪ የሚደረግ ጉዲፈቻን የሚያበረታቱ አካላት 151 ሚሊዮን ወላጅ የሌላቸው ታዳጊዎች እንዳሉ ይጠቁማሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱንም ወላጅ ያጡ ሕፃናት 18 ሚሊዮን ብቻ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ከእናት ወይም ከአባት ጋር የሚኖሩ ናቸው፡፡ ይህንንም ወላጅ የሌለው ብሎ መጥራት እጅግ የሚከብድ ነው፡፡ እኔ ወላጅ አልባ አይደለሁም፡፡ በእርግጥ እናቴ ሞታለች፤ ነገር ግን አባት አለኝ፣ እህቶች ወንድሞች እናም ሌሎች የሚወዱኝና የሚናፍቁኝ ቤተሰቦች አሉኝ፡፡
‹‹ውሸቱም ሆነ ማጭበርበሩ ለገንዘብ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ዛሬ ዛሬ ለገንዘብ ሲሉ ወላጅ የሌላቸው ሕፃናት መፍጠር ጀምረዋል፡፡ ለዚህም የገንዘብ ክፍያ አላቸው፡፡ ክፍያውም ከአገር አገር ይለያያል፡፡ ከፍ ዝቅ ይላል፣ ነጭ ሕፃን በጉዲፈቻ ለመውሰድ የሚከፍሉት ክፍያ ከፍ ያለ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የጥቁር ዝቅ ያለ ነው፡፡ ተመልከቱ ምን ያህል አስከፊ ሕይወት እንደሆነ፡፡
‹‹ዛሬ ውጣ ውረዶች ጠንካራ አድርገውኛል፡፡ ይህም በሕይወቴ አንድ ጥሩ ነገር እንድሠራ አነሳስቶኛል፡፡ በጉዲፈቻ ዙሪያ የሚሠሩ ተቋማት እየሠሩ ያሉትን ንግድ የሚያጋልጥ መጽሐፍ በመጻፍ ላይ እገኛለሁ፡፡ ወደ አገሬም ለመመለስ የሚበቃኝን ገንዘብ እያጠራቀምኩ ነው፡፡ በቅርቡም ወደ ፍርድ ቤት በመሄድም ትክክለኛ ስሜን ለማግኘት እሞክራለሁ፡፡››
Sep 15, 2013
G7 POPULAR FORCE FUNDRASING EVENT OSLO NORWAY 28 SEPTMBER 2013
Ginbot 7 Popular Force fundraising event in oslo norway September,28, 2013. During this event representatives of the G7PF leadership will be present and the program of the event comprises, discussions, fundraising and entertaining activities Freedom,
justice and democracy to all Ethiopians!
Sep 14, 2013
በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
- ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
- የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
- የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
- የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
- በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
- በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
- በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
- መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
- ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
- የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
- ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
Sep 9, 2013
የሰው ለሰዉ አስናቀ - 18ሺ ብር ከፈለ!
የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡ አበበ ባልቻ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊሔድ የቻለው ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሸገር ሕንፃ ስር በሚገኘው ዩጎቪያ ክለብ በመዝናናት ላይ ነበር፡፡ በቦታው ለእረፍት ከኖርዌይ የመጣውና በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኖርዌያዊ የሆነው ሐሰን መሐመድና የወንድሙ እጮኛ እየተዝናኑ ነበር፡፡ ከሐሰን ጋር የነበረችው ሴትም አበበ አስናቀን ሆኖ በሚጫወትበት የሰው ለሰው ድራማ ታደንቀው ስለነበር ወደ እሱ በመሄድ አብራው ፎቶ ለመነሳት ትጠይቃለች፡፡ አበበም ፈቃደኛ በመሆን አብሯቸው ይነሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መበሳጨት ይጀምራል፡፡ ከዚያም ወደ ሰዎቹ በመሄድ ከሐሰን ላይ ፎቶ ያነሳበትን አይፎን 5 ይቀበለውና መሬት ላይ በመጣል በእግሩ ይሰባብረዋል፡፡ ከልጁም ጋር ለመደባደብ መተናነቅ ሲጀምር የክለቡ ጠባቂዎች ይገላግሏቸዋል፡፡
ሞባይሉ የተሰበረበት ሐሰን አበበን እንዲሁ ሊለቀው ስላልፈለገ ወደ ሕግ ሊወስደው ሲጥር እሱ ባልጠበቀው ሁኔታ ጠባቂዎቹ አበበን ከቤቱ ያወጡታል፡፡ የአበበን መውጣት ያወቀው ሐሰን ግን ከአበበ ጋር አብሮ ይዝናና የነበረውን አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን በመያዝ “አንተ ስለሆንክ ያስመለጥከኝ አንተን ወደ ሕግ እወስድሃለሁ” በማለት ይዞት አቅራቢያው ወደሚገኝ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ይሄዳሉ፡፡ ጣቢያ ደርሰውም ጉዳዩን ያስረዳሉ፡፡ ስለ ሁኔታ የተጠየቀው ሰለሞንም ድርጊቱ መፈፀሙንና በማግስቱ አበበን እንደሚያቀርበው ተናግሮ የአበበንም ስልክ ለፖሊሶች በመስጠት ይለቀቃል፡፡
በማግስቱም ከሳሾች በንብረት ማጉደል ክስ መስርተው ለአበበ በወኪሉ አማካኝነት መጥሪያ በመስጠት ይመለሳሉ፡፡ አበበም ፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ ሁኔታ መፈፀሙን እንደማያስታወስ ግን ምናልባት በትከሻው ገፍቶት ወድቆ ሊሆን እንደሚችል ይናገራል፡፡ አቃቤ ሕግና ፖሊስም እነ አበበ ጉዳዩን በሰላም እንዲፈቱት በማግባባታቸው አበበ ለሰበረው ሞባይል 18 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እንዲከፍል በመወሰኑ ተያይዘው ወደ ቢሮው በመሄድ ቼክ ፈርሞ ለሐሰን በመስጠቱና ይቅርታ በመጠየቁ ችግሩ ሊፈታ ችሏል፡፡
Sep 4, 2013
በሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደረሰው ወያኔያዊ ጥቃት ተቆጭተናል!!! ወጣቶች መንገዳችሁን እንድትመርምሩ እንመክራለን!!!
ነሐሴ 25 ና 26 ቀን 2005 ዓ. ም. ወያኔ በአብዛኛው በወጣቶች በተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ላይ ያደረሰው ወንበዴያዊ የመብት ጥሰት አሳዝኖናል፤ አስቆጭቶናልም። ይህንን ጥቃት አጥብቀን እንቃወማለን። ከወራት በፊት በይፋ አስታውቀውና ደጋፊዎቻቸውን በይፋ ጠርተው ለሰላማዊ ተቃውሞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ወጣቶችን በቅልብ ኮማንዶዎች ማስደብደብ ተራ የመንደር ወንበዴ እንኳን የማይፈጽመው ወራዳ ተግባር ነው፤ ወያኔ ግን አድርጎታል።
የመፈክር መፃፊያ ቡርሾችና ማርከሮች ካልሆነ በስተቀር ራሳቸውን መከላከያ ዱላ እንኳን ያልያዙ ወጣቶችን በጠመንጃዎች ሰደፍ፣ በጁዶና በካራቴ ተደብድበዋል። ልጃገረዶች ጤንነታቸውን ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን በሚነካ መንገድ እተሰደቡና እየተደበደቡ ጭቃ ውስጥ እንዲከባለሉ ተደርገዋል። ጋጠወጦቹ የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ከወያኔ ሹማምንት ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተላከውን መልዕክት በቃልም በተግባርም አድርሰዋል።
የመልዕክቱ ይዘት ባጭሩ የሚከተለው ነው።
ሞተን አጥንታችንን ከስክሰን ያገኘነው ሥልጣን ትንፋሻችን እያለ ከእጃችን አይወጣም። እንኳንስ በሰላማዊ ትግል የመንግሥት ሥልጣንን ልትይዙ ቀርቶ፤ እኛ ሳንፈቅድላችሁ እደጅም አትወጡም። እንገዛችኋለን!!! እንረግጣችኋለን!!! ሕግ አያግደንም። እኛ ራሳችን ሕግ ነን። ምን ታመጣላችሁ? ምን አቅም አላችሁ?
ይህ መልዕክት ለሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላት በዱላና እርግጫ ታጅቦ ቃል በቃል ተነግሯቸዋል።ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። ዛሬ ጥያቄው ከመቼውም በላይ አፍጦ መጥቷል። ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ? ፍርዱን ለእናነተ እንተዋለን።
ወያኔ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የላከው መልክት ለፓርቲው አባላት ብቻ የተላከ አይደለም። መልዕክቱ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ምላሽህ ምንድነው? እስከ መቼ የወያኔን እብሪት እንታገሳለን? ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው?
ግንቦት 7፤ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁለገብ የትግል ስልትን ሲመርጥ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት በማመን ሆኖም ግን ብቻውን የትም እንደማያደርሰን በመገንዘብ ነው። ስለዚህም ሁለቱም የትግል ስልቶች ተደጋግፈው መሄድ አለባቸው ይላል። ግንቦት 7 ይህንን የትግል ስልት የቀየሰው በወያኔ ባህሪ ላይ ተመሥርቶ ነው። የወያኔ ዓይነቱ እብሪተኛ ሥልጣን በያዘበት አገር ሰላማዊ ትግል ከአመጽ ትግል በላይ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ሰላማዊ ትግልና የአመጽ ትግል ውሃና ዘይት ወይም እሳትና ጭድ አይደሉም። እንዲያውም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እና ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ አንዱ ያለሌላኛው ዋጋ የለውም።
ስለሆነም ከደረሰባችሁ ወንበዴያዊ ጥቃት ትምህርት በመውሰድ፤ ወደፊት ደግሞ ከዚህ የባሰ ሊመጣ እንደሚችል በመገንዘብ፤ ሁኔታዎችን መርምራችሁ በግል የስትራቴጂ ለውጥ ለማድረግ የወሰናችሁ ወጣቶች ግንቦት 7ን ማግኘት አይቸግራችሁም። ሆኖም ጊዜ የለም። በወያኔ ዓይን እና በወያኔ ፍርድ ቤት እይታ መብቱን የጠየቀ ሁሉ የግንቦት 7 አባል ነውና የምታጡት ነገር የለም። ዛሬውኑ ወስኑ!!!!
ግንቦት 7፤ በዚሁ እለት ክርስቲያኑንና ሙስሊሙን ኢትዮጵያዊያንን ለማቃቃር ወያኔ የጠራውን ሰልፍ ጥበብ በተሞላበት ስልት ላከሸፈው “የድምፃችን ይሰማ” አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Subscribe to:
Posts (Atom)