
በአሁኑ ሠዓት አብዛኛው ኢትዮዽያዊ ከዓለም ጫፍ እስከ ዓለም ጫፍ በሳዑዲ በመከራና ስቃይ ላይ ላሉት ለብዙ ሺህ ወገኖቹ በአንድነት ቆሞ እየተንጫጫ ባለበት ወቅት ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ በግምት 45 000 ኢትዮዽያዊ እንደሚኖር ተገልጿል።
እስካሁን ድረስ በውሽታሙ ቲቪ የገቡት ገቡ የተባሉት ገብተዋል ብለን እንኯን ብናስብ በየቀኑ ቢያንስ 1 ወይም 2 ኢትዮዽያዊ ህይወቱን ያጣል ይባስ ብለው በሳውዲ የሚገኘውን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ላልተወሰነ ግዜ ዘግተው በድብቅ ፍራንክ ላላቸው ኢትዮዽያኖቹ ብቻ ወደሀገራቸው ለመግባት እንኯን ብር እየከፈሉ እንደሆነ ከስፍራው በየቀኑ በሚደርሰን መረጃ መሰረት ለማወቅ ችለናል ፍራንክ የሌለውን እዛው እንዲበሰብስ ወይም ሀገር እንደሌለው 2ኛ ሞት እንዲሞት እያደርጉም እንደሆነ ማለት ነው ።
ሰለዚህ ይህንን ከኢትዮዽያ ህዝብ የተደበቀ መሪር ሃዘንና ምሬት በአንድ ላይ በመሆን ለኢትዮዽያ ህዝብ የምናሳወቀበት ቀን እንዲሆን በአክብሮት እንጠይቃለን ።
በሳውዲ የሚገኙ የኢትዮዽያ ህዝብ በደልና ጥቃት በአዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ ኤምባሲ እሁድ ህዳር 08 ቀን ሊያደርገው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ እንደሁም በጣም ብዙ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የነበሩትን ስዎች በመደብደብ እና በማሰር በሃገራቸው እንኯን መናገር እንዳይችሉ አድርገው እንደነበር ይታወሳል።
በመሆኑም በመጪው ህዳር 15 ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ላይ ከ35 000 ህዝብ በላይ ስለሚኖር ሁሉም ኢትዮዽያዊ ይህን መልዕክት ላልሰማው በማስተላለፍ ሁሉም ጥቁር ጨርቅ በማሰር ብሶቱን ባደባባይ የሚያሰማበትን ቀን በጉጉት እንጠብቃለን ።
yared elias
No comments:
Post a Comment