Pages

Jan 16, 2013

ኢትዮጵያ፤ የመዳኛ ወቅትና፤ የዕረቀሰላም ጊዜ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
የረፖርተር ድሕረ ገፅ ሲዘግብ:
በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት  ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል:: በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል፡፡ ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል፡፡ ይህም መሰረታዊ ችግሩና መንስኤው አስተዳደራዊ ድክመት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ ባለፈው በእለተ ዕረቡ ጃንዋሪ 2 2013 የተቀሰቀሰው ግጭትም በተለይ በሁለት ጎሳዎች በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መሃል የተከሰተ ነበር፡፡ ምስክሮች እንደሚሉት፤ግጭቱ የተቀሰቀሰው የትግራይ ተወላጅ የሆነው ተማሪ፤ በመጸዳጃ ቤት፤ በቤተመጻህፍትና በተማሪዎች መኝታ ቤቶች  ግድግዳዎች ላይ የጎሳን ክብር የሚነካ ጽሁፍ በመጻፉ ነበር፡፡
እንደ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣን አባባል ‹‹ግጭቱ የተቀሰቀሰው ያንን የጎሣ ክብር የሚነካ ክብረነክ ጽሁፍ በተመለከቱት ተማሪዎች  መሆኑን ነው::›› በዚህም የተነሳ 20Addis Ababa University, Ethiopia ተማሪዎች መቁሰላችውንና 3ቱ የጠናባቸው ወደ ሆስፒታ፤ል መወሰዳቸውን በተጨማሪ ሁለቱ የቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ ሌሎች 20ዎችም በፖሊስ ባልለየለት ውንጀላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
ስለኢትዮጵያ ‹‹የብልሆች መፍለቂያ ከነበረው ዩኒቨርሲቲ›› ይህን ሁኔታ ሳነበው ያደረብኝ ግብታዊ አስተያየት፤ ማመን እስኪያቅተኝ ነበር፡፡ ሳስበዉም ‹‹ይህ ፈጽሞ ሊታመን የሚችል ጉዳይ አይደልም፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ አነሮች ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) በዚህ ፈሪነትና የማያስፈራራ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ መግባት ተግባራቸው አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ቆሻሻ እና እጣቢ አተላ የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ከመንደፋደፍ የተሸለና የበለጠ ተግባር ማከናውን ይችላሉ›› አልኩኝ :: ይህን የመሰለ የረከሰ የጥላቻ ምግባር፤የወዲፊቶቹ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤የቀጣዩ ትውልድ መምህራን፤ ሳይንቲስቶች፤ እና የፈጠራ ሰዎች ምግባር እንዳልሆነ ነበር እራሴን ማሳመን የሞከርኩት፡፡
ነገሩን የበለጠ ሳጤነው አምአሮ የሚነካና የሚአስቀፍፍ ሆኖ አገኘሁት፡፡ እራሴንም ጠየቅሁ፡፡ ምናልባትስ ይህ የጎሳ ክብር የሚነካ ጽሁፍ በሌሎች የአ አ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የተፈጠረ ቢሆንስ? ይህን የመሰለው ዝቃጭ፤ወኔቢስ፤ባለጌ ተግባር ስለነዚህ ተማሪዎች ምን ይላል? ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለአጠቃላዮቹ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለ መላው የኢትዮጵያ ወጣቶችስ?
ከዚህ ጥየቄ ጋር በመታገል ላይ እንዳለሁ፤ ሊገታ የማይችል ሃፍረትና ውርደት ሰሜት ወረረኝ፡፡ እራሴን ደጋግሜ መረመርኩት፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አእምሮ ያለቸው ተማሪዎች—- የኢዮጵያ አነሮች —- ይህን በመሰል ኋላ ቀር፤ አረመኔያዊ፤ ጨካኝና አሰቃቂ፤ ተናካሽ፤ ተንኮል የተመላበት፤ተግባር አንዴት ሊሰሩ ይችላሉ?  በምን መንስኤ ነው፤ አንድ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ስብስብ ሌላውን ወገን ስብእና ለመድፈር፤ የጋኔን ተግባር ለመፈጸም፤ ዝቅ አድርጎ ለመመልከት፤ አውሬ በማስመሰል፤ አካሄድና ተግባር የሚሰማሩት? ለምን? እኮ ለምን? ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችም ምክንያታዊ ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም፡፡
ይህ የ ጎሳ  ጥላቻ ወንጀል የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሰለ አትዮጴያ ወጣቶች ክብርና ወደፊት ላገራቸው ሰለምተበቀባቸው ግዴታ በመፅፈበት ወቅት ነበር :: ሆነ በተባለው የጎሳ ጥላቻ ወንጀል የበለጠ ግራ እየተጋባሁ ሄድኩ፡፡ ይህን አስጠያፊና አስፈሪ፤ ቀፋፊ ሁኔታ በምክንያታዊነት በጥልቀት ለመረዳትና በዚህ አስገራሚ ትርኢት ውስጥ አንዳንድ የኢትዮጵያ አነሮች እንደ ጉማሬዎቹ በመንቀሳቀስ እንደጅቦቹ ለመሆን መከጀላቸው አስገረመኝ፡፡ አሳፈረኝ፡፡ አሳዘነኝ፡፡
ያን ግልብ ስሜቴን ወደ ጎን አልኩና ረጋ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ:: ከምር ጠንክሬ አሰብኩ፡፡ ይህ በዩኒቨርሲቲው የተከናወነው ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተውን አልመግባባት›› ድርጊት ከጥሩ እምነት ካላቸው ሁነኛ መደበኛ ተማሪዎች ተጠንስሶ በስራ ላይ የዋለ ነው  ለማለት ምን ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል? በእውነትስ  የተባለውና በዚህ በየግድግዳው ላይ የሰፈሩትን ክብረ ነክ ጽሁፎች የጻፈው ‹‹ተማሪ›› ማነው?  በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሙዚቃ ሸክላ አጫዋች መሰል የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ተቀምሞ የተበተነውን መሸንገያ አባባል ማመን አለብን? እንዴት ነው የዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪዎች  ‹‹ለአሰርት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወኑ የነበሩትን የጎሳ ግጭቶች” ያሳለፏቸውና አሁንም ሲቀጥሉ  አጃቸዉን አጣጥፈው  መመልከት የቻሉት? በዩኒቨርሲቲውስ ውስጥ ምራቃቸውን የዋጡና የበሰሉ፤ችግሮችን ለማክሸፍና ለማግባባት ፈቃደኛ የሆኑ አመራሮች የሉም?
ጥርጣሬ ቀስ እያለ፤ድንጋጤዬንና ሃፍረቴ  መተካት ስለጀመረ፤ የዚህ ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተ ብጥብጥ›› በገዢው መንግስት ጀብደኛ ባለማዕረግ የተዋቀረና፤ የተተለመ እንደሆነስ የሚለው ጥያቄ አያፈጠጠ ያየኝ ጀመር፡፡ በኋላም የወንጀል መመርመርያ ማስረጃ ማፈላለጊያ “መነጽሬን” ሳደርገው፤ እንደገና በመሹለክለክ ድምጽዋን አጥፍታ ጨለማና ወቅትን መከለያ በማድረግ አንዲት መናጢና ቆሻሻ አይጥ ተንኮሏን ከፈጸመችና ተልእኮዋን ከፈጸመች በኋላ ሳትታይ ጥላው  የሄደችውን የእጇንና የእግሯን አሸራ በግድገዳ ላይ ከተጻፈው አስጠያፊ ጥሁፍ አግርጌ ታትሞ አየሁት፡፡
በሜይ 2010 ጃዋር ሲራጅ ሞሃመድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሐተታ ሰጪ እንዲሁም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ እንደዘገበው  በዩኒ ቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር በርካታ ውይይት ካካሄደ በኋላ እንዲሁም በሁለት ክፍል በሃራማያና፤በአዳማ  ዩኒ ቨርሲቲ በ2006 የተከናወነውን ድርጊት  ሰበቡን የአካዳሚክ ነጻነት ማጣትና በኢትዮጵያ የደህንነት ሚስጥራዊ ተቀጣሪዎች ተማሪ በመምሰል ሰርገው በመግባት የግጭቱ መሰሪ ጠንሳሾች መሆናቸውን ለማመን በቅቷል፡፡
ደግሞም በሴፕቴምበር 2011 ላይ በይፋ የዎጣው ማስረጃ አንዳሳየው በሴፕቴምበር 16 2006 “ የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 3 ፈንጂዎች መቅበራቸውንና በመፈንዳቱና፤ በወቅቱም የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ የሚካሄድበት ስለነበረ ከረር ያለ ጥያቄ ያስነሳውን  ፍንዳታም ኤርትራንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርን ተጠያቂ እንዳደረጉ ነበር::” በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን መንግስት ኤምባሲ ባካሄደው ‹‹የሚስጢር ዘገባ›› በጉዳዩ ላይ የመርማሪዎቹ ጣት  ወደ ኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የደህንነት አባላትን በመጠቆም ለዚህ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡
በሌላም በኩል በ2006 የተገኘው ሚስጥራዊው ባለ 52 ገጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ሰነድ፤ የዲያስፖራው ዳይሬክቶሬት በዲያስፖራው ያሉትን የተቃዋሚ ሃይላትና አባሎቻቸውን የሚነዘንዝ፤ በሃይማኖት፤ በዘር፤ በፖለቲካ ጥላቻ የሚከፋፍልና ማንኛቸውንም ገዢውን ፓርቲ የሚቃወሙትን ለመከፋፈልና በመሃላቸው መግባባት እንዲጠፋ ያደረገው ጥረትና ዝግጅት ተጋልጦ ነበር ፡፡ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋጣሚ በይበልጥ ባሰብኩ ቁጥር፤የገዢው መንግስት ተቃዋሚዎችን ለማስጠላት ለመከፋፈል ለመበታተን ለማክሸፍ ብሎ የሚዘራውን ቆሻሻና የብልግና ባህሪ ያጋልጡት ጀምረዋል፡፡
በተጨባጭ ምርምሬ አንደተርዳሁት ‹‹በጎሳ ላይ ለተመሰረተው ግጭት›› ወንጀል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ተጠያቂው ማን እንደሆነ ግልጽ የሆነው ማስረጃ  የሚጠቆመው ወደ ተለመዱት ወንጀል ፈጻሚ የገዢው መንገስት ወንጀለኞች ነው፡፡
ሊታለፍ የማይችለው መደምደሚያም፤ (ሌላ ተቃራኒ  ማስረጃ  እስካልቀረበ ድረስ) በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለተፈጸመው ወንጀላዊ  ተግባር ተጠያቂዎቹ፤ በግቢው ውስጥ በድብቅ የተቀመጡት መዘዝ ፈጣሪዎችና ምግባረ ብልሹ ሕሊና ቢስ  ወኪል ተንኳሾችና ደባ ፈጻሚዎች እንጂ ጨርሶ ለጥሩ ዕምነት የተፈጠሩት ወጣት አቦሸማኔዎቹ የነገ የሃገር አለኝተ ዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የማጠቃለያው ግምገማም ይህንን መደምደሚያ የማያጠያይቅ ማስረጃ በመሆን ያረጋግጠዋል፡፡ ያለዉን ማስረጃ በጥቂቱ ብንመለከተው: በመጀመርያ እንድ ብቸኛ “ተማሪ”ብቻ ነው ድርጊቱን በመተንኮሱ  የተወነጀለው፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎች በአንድ ጎሳ ስር ተቧድነው ለዚህ ድርጊት መንቀሳቀሳቸውንና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላም ለማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም፤ መደራጀታቸውን ተአማኒነት ያሳጣዋል፡፡  ይህን እንቅሳቃሴ ለመጀመርና መነሻ ሆነ የተባለውም ብቸኛ “ተማሪ” የየት ጎሳ አባል እንደሆነ በግልጽ አልተረጋገጠም፡፡ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት: ስምና መለያው ያልታወቀ፤ አንድ ተማሪ በማለት ወንጀለኛ ብለውታል፡፡ ይሁንና ይህ ‹‹ተማሪ›› ዓላማ ያለው እርገግጠኛ  መደበኛ “ተማሪስ” ነው? ወይስ ተቀጣሪ ነገር ቆስቋሽ የስለላ ድርጅት ወኪል ግን እንደተማሪ ተመሳስሎ ተወሻቂ አባል (የቀበሮ መንኩሴ በግ መሃል ይጸለያል አንደሚባለው ሁሉ ) ነው? ይህስ ተማሪ በዘር ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ባሕሪ ግለ ታሪክስ ያለው ነው?
ሶስተኛ፤ በሶስት ቦታዎች ማለትም በላይብረሪ፤ በመጻሕፍት ቤትና በተማሪ  መኝታ ቤት ይህን መሰሉን የጎሳን ክብር የሚያዋርድና የሚያንቋሽሽ ጽሁፍ ለመጻፉ ምንም የተጠቀሰ ማስረጃ የለም፡፡ በጥላቻ ወንጀል ድርጊት፤ እንዲህ መሰሎች የጥላቻና የማዋረድ ተግባር ያለባቸው ጽሁፎች ሲጻፉ ዓላማቸው አንድን የጎሳ አባል የሚመለከቱ ሲሆኑ፤ ኢላማ የተደረጉት ግለሰብም ይሁን ቡድኖች ሊደርሱበትና ሊያዩት በሚችሉት ስፍራ ይሆናል እንጂ የግል ጥላቻውንና ብሶት ጣውን  ከተለያዩ ብዙ ጎሳዎች የመጡ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ የማይመለከታቸውም እንዲመለከቱት ለምን ይደረጋል?
አራተኛ፤ ከዚህ አስቀያሚ  የግድግዳ ጽሁፍ ሌላ ማስረጃ ሊሆን የሚችል አንዳችም ነገር ከዚህ የችግሩ ጠንሳሽ በተባለው ‹‹ተማሪ›› ላይ አልተገኘም፡፡
አምስተኛ፤ በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው ደባ የተለየ ሁኔታ ሆኖ ሊታይ አይችልም፡፡ ላለፉት በርካታ አሰርት ዓመታት ይህን መሰል በጎሳ ላይ ተመሰረተ አምባጓሮ ይነሳ እንደነበር የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለምንስ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩ ሲያቆጠቁጥ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ለዚህ ከመብቃቱ ቀደም ብለው አላከሸፉትም፡፡ ድርጊቱ በአስከፊና ሊቀለበስ ወደማይችልበት ሁኔታ ከደረሰና አዳገው ሁሉ ከተከናወነም በኋላ በሌሎች ተማሪዎች ላይ አመጹ ተስፋፍቶ እንዳይቀጥልም ባለስላጣናቱ የወሰዱት እርምጃ የለም፡፡
ስድስተኛ፤ በነጻ አካላት ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ከመጣራቱስ አስቀድመው የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት “አመጹ የተጀመረው በግድግዳዎች ላይ የተጻፈውን ምግባረ ብልሹና ጎሳን የሚያንኳስስ ጥሁፍ ያዩት ተማሪዎች ነው በማለት ለምነስ መግለጫ አወጡ? ጉዳዩን ከመሰረቱ አንስተው የሚያጣሩ ገለልተኛ ወገኖች በማዋቀርና በመመርመር ለወዲቱ ይህን መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይከሰት ማድረግ የሚቻልበትን ዘዴ ለምን አልቀያሱም? የዩኒቬርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩን እራሳቸውን ከተጠያቂነትና ከሃላፊነት በማግለል ለፖሊስ ሙሉ በሙሉ ለምን አስረከቡት? ምናልባት በዩኒቨርሲቲው የሚከሰተውን የጎሳ ጥላቻ ወንጀል ቸል ያሉት አይታችሁ እንዳላየ ሁኑ የሚል መመርያ ስለተሰጣቸው ይሆን?
ሰባተኛ፤ የዚህ የጥላቻ ብጥብጥ ወንጀል ተጠቂ የሆኑትስ በፖሊስ ለመደብደብ ለመያዝና ለመታሰር ለጉዳት ለምን ተዳረጉ?
በአጭሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመው የጥላቻ ወንጀል የቀረበው ሁኔታና ማስረጃ ጨርሶ ወደ ተከሳሾቹ ተማሪዎች ጣት አያመላክትም፡፡ ይልቁንስ ያአመልካች ጣት በወንጀለከኝነት የሚጠቁመው ወደ ከሳሾቹ ነው፡፡ የዚህን የጥላቻ ወንጀል ፈጻሚዎች ለማጣራትና ለመያዝ የሚያስፈልገው፤ ያንን የግድግዳ ላይ ጽሁፍ የከተቡትን የማይታዩ ጣቶች ብቻ ሳይሆን  እነዚያን ተማሪዎቹን እስኪጠወልጉ ድረስ የቀጠቀጡና ያሰቃዩ፤ ከዚያም በረጩት የአመጽ ነዳጅ ላይ እንዳይጠፋና የበለጥ እንዲቀጣጠል ንዳድ የረጩበትንና የጎሳ ግጭቱን ያቀጣጠሉትን፤በተማሪዎች መሃል ጥላቻ  ንትረክና ዉዝግብ አንድፈጠር የሚዶልቱ ወንጀል ጠንሳሶች ነው፡፡
ያም እንዳለ ሆኖ፤አሁን ወቅቱ ነው፤ አስፈላጊው ወቅት ነው፤ትክክለኛው ጊዜ ……..
የማገገሚያጊዜ፤የመቀበያውየመተቃቀፊያ  የእርቀሠላምጊዜ አሁን ነው
በክዱስ ጽሁፍ እንደሰፈረው፤ ‹‹ለማንኛውም ሁኔታ ወቅት አለው፤ከሰማይ በታች ላሉት ነገሮች ሁሉ  ለየምክንያቱ ጊዜ አለው::›› ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለሃዘንም ወቅት አለው፤ ድንጋይ ለመወርወርም ጊዜ አለው፡፡ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፡፡ እንዲሁም ለመተቃቀፍም ጊዜ አለው ለሠላምና ለማገገምም ጊዜ አለው፡፡ ለእርቀሰላምም  የራሱ ጊዜ አለው፡፡
አሁን ነው ጊዜው፤ — ትክለኛው ጊዜ– ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በትምህርት ቤቶች፤ በዩኒቬርስቲዎች፤ በስራ ቦታዎች፤ በአጎራባች መንደሮችና በመንገድም ላይ  የማገገሚያው ወቅት፡፡ ጊዜው—– ትክክለኛው ጊዜ—- የኢትዮጵያ ወጣቶች በወንድማማችነት በአህትማማችነት ስሜት መተቃቀፍ  መተሳሰብ እጅ ለእጅ በመያያዝና አንድ በመሆን ብዛታቸውን  ለቅድመአያቶቻቸው ክብርና ለታሪካቸው መከበርያ ማድረግ የሚገባቸው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የጎሳ ጥላቻን  የብጥብጥን አዙሪት የመበጠሻ ጊዜው አሁንነው:: አላስፈላጊውን የቅሬታ ልምድ የማክተሚያ፤ የፍርሃትን ባህል፤ ጥላቻን፤ አውልቆ የመጣያው ትክክለኛው ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጣቶቻቸውን በማቆላለፍ እጅ ለእጅ በመያያዝ የፍርሃትን እከክ ማራገፊያቸው፤ ጥላቻን፤ግጭትን፤ከልባቸው ፤ ከሕሊናቸው፤ ከመንፈሳቸው አውጥተው መጣያ ጊዜያቸው አሁን ነው፡፡ ጓደኞቻቸውንና የትምህርት ባልደረቦቻቸውን እንደጠላትና  ባላጋራ መመልከትን ማቆሚያቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ሰላም ፈጥረው እርስ በርሳቸው እንደወንድምና እህት የሚተቃቀፉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብልህና ምርጦች አንድ ላይ በመስራትና በመተጋገዝ የተሸለን ነገ ለመፍጠር የሚችሉበት፤በረጋና ጠንካራ በሆነ የሕግ የበላይነት ላይ፤ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የተከበሩበት አማራጭ ሂደቶች ያሉበት መትለሚያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላት ጋር ሠላምን መፍጠር ካስፈለገህ፤ከጠላትህ ጋር ተጓድነህ መስራት አለብህ፤ ያን ጊዜ ጠላትህ ወዳጅህ ይሆናል::›› እነዚያን ጠላት የምንላቸውን ወንድምና አህት አብሮ ተማሪዎች  ና ወዳጅ ማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢያችን ውስጥና ከግቢያችንም ውጪ ጥላቻንና የጥላቻ ወንጀልን ለማጥፋት መተባበርያው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ከሕሊናችንና ከመንፈሳችን ውስጥ የጥላቻ ቋጠሯችንን ማጥፊያው፤ የፍርሃትን ሰንሰለትና ካቴና መበጠሸውጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫና እራሳቸውን ለማላቀቅና ነጻ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ቆንጨራውን በመቅበር ለአንድዬና ለመጨረሻው ጊዜ ‹‹አሻፈረን! አንዳችን ሌላውን የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ስለሆንን ለመጠላላት አሻፈረን፤ እምቢ! መባያችን ጊዜው አሁን ነው፡፡ አሻፈረን! ምክንያቱም ሁላችንም በተለያየ ስም በምንጠራው የጋራችን በሆነው አምላክ ስር አለያም የሁላችን በሆነችው ሀጋራችን የተለያየ ማእዘን ነዋሪዎች ነንና፡፡ እምቢ! በምንም መልኩ ለመጠቀሚያነትና እንደ አሻንጉሊትነት ሆነን በሚጠቀሙብን ለጥላቻ ለእርስ በርስ መቆራቆስ መጠቀሚያ አንሆንም፤ እምቢኝ! የሠለጠንን ነንና ለጥላቻ አንሰለፍም፡፡ አዳኝ እንደሚያሳድደው የሚታደን አውሬ ለመሆን እምቢኝ!
ከአንድጉማሬጥቂትቃላትለበርካታዎቹአቦሸማኔዎች
በርካታ አቦሸማኔዎች ምናልባትም ጉማሬውን ትውልድ ማዳመጡ ያስገርማቸው ይሆናል፡፡
እኛ ጉማሬዎች ‹‹በዕውቀት የተጋረድን›› ‹‹ራዕይ የጎደለን››  ‹‹የራሳችን ምንጭ እስካልደረቀብን ድረስ ጠቅላላው ሃገር ቢደረማመስ ደንታ የሌለን ›› ነን ተበለን አነታወቃለን:: ያም ሆኖ ወጣቱን ትውልድ  በአክብሮት እባካችሁ ጆሯችሁን አውሱኝና ለመደመጥ እድል ስጡኝ እላለሁ፡፡
ጀግኑ!
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ እራሳችሁን ከሰንሰለቱ ነጻ በማድረግ ካለፈው የጫና ሰቆቃ እኛንም አራሳችህሁንም ለማላቀቅ ብቁ፡፡
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ ታሪካዊ ጥላቻን፤ ቅሬታን በማጥፋት፤ መግባባትንና መቻቻልን በማምጣት አዲስ እርቀሰላም በኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሩ፡፡
የጥላቻን ቁስል ለማዳን የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለዘመናት ያመረቀዘውን በማጥፋት ለመጪው ትውልድ ያለፈው ትውልድ ስህተትና ጥፋት እስረኞች እንደማይሆኑ አረጋግጡላቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ሁላችንም በእኩልነት የሰው ዘር አባላት በመሆናችን ይህንንም በጎሰኝነት ለማቀደም ብለን አዘቅት አንውረድ ::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አንደኛችን ለሌላው ይቅርታን በመቸር ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ ቆንጨራውን በመቅበር፤ ጣቶቻችንም የጠመንጃ  ቃታና ምላጭ ለመሳብ፤ጣቶቻችን የጥላቻ መነሾ የሆኑ ቃላትን በየግድግዳው ላይ ለመለቅለቅ ሳይሆን እጆቻችን የሚዘረጉት የመግባባት የመተሳሰብ ሰላምታ ለመለዋወጥና ለችግርም ይሁን ለደስታ እጅ ለመዋዋስ ብቻ አንድሆን ማረግ ያሻል፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የተለያዩት እምነቶቻችን መለኮታዊነታቸውን ማረጋገጥ እንቻል::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አሻፈረኝ! አምቢ! በማለት ውስጥ ውስጡን ከሚበላን የጎሳ የሃይሞነት የጻታ ልዩነት በተቃርኖ እንቁም::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን በመኝታ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍት፤በመጸዳጃ ቤቶችም ያሉትን አስነዋሪና በታታኝ፤ ጎሰኝነትን የሚያቅራሩ ቃላታን በእርቀሰላም፤ በመግባባት፤ በውህደት፤ በፍቅር አሰባሳቢ ቃላቶች እንሸፍናቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የወደፊቷ ሃገራችን መሪ ሻምበሎች እናንት ኩሩ አቦሸማኔዎችእንጂ፤ የደከሙት፤ሙሰኞቹ፤ ምግባረብልሹዎቹ፤ እራሳቸውን የሚያስተናግዱ ጉማሬዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን  ለመሆን የምትመኘውን ሁሉ በመሆን፤ለመሆንም ለማሰብ ቀደምት አንሁን፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን  የትላንቱን የመረረ ስሜት በዛሬውና በነገው ጣፋጭ እርቀሰላም፤ መግባባት፤ አንድነት፤ መሰረት ላይ መልሳችሁ አዋቅሩት፡፡
የሃቅ ወቅቱ ደርሷል፡ አቦሸማኔዎቹ እራሳቸውን በማዳን ለእኛም መድህን ይሆኑን ይሆን ?
ለኢትዮጵያ ምርጡና ብሩሁ የሃቅ ወቅት ደርሷል!
የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫናና መከራ እራሳቸውን በማዳንና የጎሳ መጎጃጃ፤ የሃይሞነት አክራሪነትን  የጨቋኝ ስጦታ በመጣል እራሳቸውን ማዳን ይችሉ ይሆን?
እነዚህ አቦሸማኔዎች ተጠራጣሪዎቹን፤ የመሸጉትን ምስኪን ጉማሬዎች ከራሳቸው ነጻ ያወጧቸው ይሆን?
ከጎሳ መቆራቆስ ወደ ጎሳ ፍቅር፤መቻቻል አንድነት፤ መግባባትን ያበቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎቹ ስብእናችንን ከጎግፍ ማነቆና ከአውሬ አስተሳሰብ ያላቅቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎች የእርቀ ሰላምን ጥበብ ያስተምሩን ይሆን? በእርቀሰላም ቋንቋ ያናግሩን ይሆን?
የኢትዮጵያ ብልህና ብሩሆች አንድ የወጣት ግብረሃይል በመሆን 2013ን የአቦሸማኔዎች ዓመት ያደርጉት ይሆን? አንድ ላይ በመቆም የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ በመስበር የወገንተኛነትን ጎራዴ በማቅለጥ የእርቀሰላምን ሙሉነት ያስመርቱን ይሆን?
የአላንዳች ጥርጥር አዎን ይቻላቸዋል!
ባለፈው ሳምንት 2013 የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ዓመት ብዬ ስተነብይ፤  የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ለማዳረስ፤ለማሳመን ቃል ገብቼ ነበር፡፡ አኛ ጉማሬዎች አቦሸማነዎችን አናስተመራለን የሚል አምነትም ነበረኝ:: ጉማሬዎችን አቦሸማኔዎችን ያስተምራሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር::  ለዚህ ነው እኛ ጉማሬዎች ግራ የተጋባ ሸውራራ (የተዛባ አመለካከት) ቅርብ አዳሪነት፤ጠባብ አስተሳሰብ፤ የምያጠቃን::  ለአቦሸማኔዎች የማስተማርያ ወቅት ሊኖር ስለመቻሉ ጥርጣሬዬ የመጣው::
ስለዚህም የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች በርካታ ግብግቦች የሚገጥሟቸው፡፡ የአቦሸማኔዎቹ ፈታና ጉማሬዎቹን የእርቀሰላምን ጥበብ ማስተማሩ ላይ ነው፡፡ የጉማሬዎቹ ፈተና ደግሞ ከአቦሸማኔዎች የእርቀሰላምን ጥበብ መማሩ ላይ ነው፡፡
አቦሸማኔዎች ታሪካዊ ገድል የመፈጸም እድል ቀርቦላቸዋል፡- ይሄዉም በምሳሌነት ማስተማር፡፡
በአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ አጋጣሚ የተሳተፉትን፤ ወዳዳጆቻቸውንና ሌሎቹም ጭምር በግቢያቸው የተፈጸመውን አስጸያፊ የግጭት ሁኔታና ሁከት አስመልክቼ የማቀርበው ጥሪ ሁኔታውን ወደ ውብና ያማረ ፍቅርና ሰላም የሞላበት ፍሬያማ ውጤት ለማምጣት የአንድነት አውድማ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ወደ ሌላው በመቅረብ ይቅርታን እንዲጠይቁና እንዲቀባበሉ እጠይቃለሁ፡፡ አንዲት በጣም ትንሽ የሆነችውን ‹‹ይቅርታ›› የምትለውን ቃል ለመተንፈስ ወኔ ይጠይቃል፡፡
በራሳቸው ውህደት እንዲፈጥሩ እጠይቃለሁ—-አንድ ለአንድ፤ በትንሹና በበርካታው ስብስብ—–ልዩነታቸውን ይወያዩበት ይነጋገሩበት ይምከሩበት፡፡ አንደኛቸው የሌላው ጉዳትና ግፍ ይሰማው፡፡ አንዱ የሌላው ፍርሃትና ጥርጣሬ ይሰማው:: አንዱ ለሌላው እንባ ንቀት አይኑረው፡፡

በብሩህ ህሊና፤ በንጹህ ልቦና፤ አእምሮና መንፈስ ሊነጋገሩ ግድ ነውና ይህንንም እጠይቃለሁ፡፡
እያንዳንዳቸው የሌላውን ስሜትና ጥርጣሬ እንዲረዱ እጠይቃለሁ፡፡ በጓደኞቻቸው ጫማ ውስጥ ሆነው ለኪሎሜትር  እንዲራመዱ እጠይቃለሁ:: በመጫሚያም ይሁን በባዶ እግራቸው ፈገግ ሊያሰኛቸው የሚችል ሁኔታ ያጋጥማቸዋል፡፡
የኢትጵያ አቦሸማኔዎችን 2013ን የእርቀሰላምና የሰላም ዓመት እንዲያደርጉት እጠይቃለሁ፡፡
ጃንዋሪ 2 1013 በታሪክ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ፤የሃይሞነት ወገንተኝነት፤ የጾታ ልዩነት የተቀበሩበት ዕለት ሆኖ ዘወትር አንድታሰብ ይሁን፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አስጸያፊ ሁኔታ ለሕዝብ ማስተማሪያነት ያገልግል፡፡
ጥንካሬን ከችግር ወልዳችሁ፤ አንድነትን ከከፋፋይ ተምራችሁ፤ ከጓደኞቻችሁ ተማሪዎች ጋር ለመደማመጥና የመግባባትን፤ የመቻቻልን፤ የውህደትን ዘር ለማፈስ እንድትበቁ እማጸናችኋለሁ፡፡
የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ጉማሬዎችን እንደመሩ እጠይቃለሁ፡፡ እኛን አትከተሉን፤መሄጃችንን አናውቀውምና፡፡እኛ የጠፋው የጉማሬ ትውልዶች ነን፡፡
ይህን ግብግብ በመቀበል፤ትክክለኛውን እንደትክክል፤ስህተቱንም ወደ ትክክለኛነት ካልለወጣችሁት፤ አቦሸማኔዎች በስልጠና ላይ ያሉ ደካማ ጉማሬዎች ናቸው የሚል ትችት ላይ መውደቅ ይመጣል::
ለሁሉም ጊዜ አለው::   ለኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች፤ ለማገገምና ለእርቀሰላም ሰዓቱ አሁን ነው፡፡
የኔ ጥያቄ ለእዮጵያ ወጣቶች  ይህ ነው:-  አሁን ስንት ሰአት ነው!?!
የተባበሩት የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ፈጽሞ ለውድቀትና ለሽንፈት አይዳረጉም!

ሰበር ዜና፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል

(ከአዘጋጁ፡ ውድ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አንባቢዎች በቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት እንዲመጣ የተለያዩ ዘገባዎችን
ስናቀርብ ቆይተናል። በርከት ያሉ አንባቢዎቻችን በምናቀርባቸው ዘገባዎች ያላቸውን ማበረታቻ ስለለገሱን
እናመሰግናለን) ከሁለት ሰዓት በፊት በሰበር ዜናችን አቶ አባይ ጸሐዬ በስደት ያለውን ሲኖዶስ በአሸባሪነት
መንግስታቸው እንደሚከስ መናገራቸውንና የቅዱስ ሲኖዶሱም አስቸኳይ ስብሰባ ለሰላምና ለአንድነቱ መፍትሄ
የማይሰጥ ውሳኔ በማሳለፍ የዛሬውን ውሎ ማጠናቀቁን መዘገባችን ይታወሳል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አሁንም በዚህ
ዙሪያ ጠለቅ ያለ መረጃ እንዲኖራቸው በማሰብ ወደ ሃገር ቤት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎችን ወደ ምንጮቻችን
ስናደርግ ቆይተናል። ምንጮቻችን ያደረሱን አዲስ መረጃ ቢኖር “የሰላምና የአንድነት ፍጻሜው እልባት ካገኘ በኋላ
ውጭ ሃገር ከሚገኙት አባቶች ጋር በጋራ የፓትርያርክ ምርጫውን እናድርግ በሚለው አቋማቸው የጸኑት የቅዱስ
ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል (ፎቶ) አባይ ጸሐዬና ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የተገኙበትን ስብሰባ
ረግጠው መውጣታቸው ነው። የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ እዝቅኤል ስብሰባውን ረግጠው ለምን እንደወጡና
የልዩነት አቋማቸውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንደሚናገሩ ዝተዋል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት
በከፍተኛ የደህንነቶች ክትትል ሥር እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።)
ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን አሁንም ተከታትላ አዳዲስ መረጃዎችን ለአንባቢዎቿ ታቀርባለች።

Marathon runner Shumye dies in car crash


(Iaaf News ) Ethiopian marathon runner Alemayehu Shumye died
in a car crash on Friday (11). He was 24.
His marathon career began in 2008 with much promise and in his
first three races at the distance he won in Vercelli, Warsaw and
Beirut.
His lifetime best, 2:08:46, was set at the 2009 Frankfurt
Marathon where he finished fifth. His most recent Marathon
victory came at last year’s Gold Coast Marathon.
Shumye competed just six days before the car crash, finishing
10th in Xiamen with a time of 2:12:57.

አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ


አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ

ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የቻይና አምባሳደር ስዩም መስፍን ከሲሲቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ማእድናትን በምታወጣበት ጊዜ የአካባቢ ውድመት ታደርሳለች እየተባለ በአፍሪካውያንና በምእራባዊያን ዜጎች የሚደርስባትን ወቀሳ መከላከል አያስፈልጋትም ብለዋል።ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
አምባሳደሩ ይህን መልስ የሰጡት የሲሲቲ ጋዜጠኛ ” ብዙውን ጊዜ አገራችን በሌሎች አገሮች ማእድናትን ስታወጣ የአካባቢውን ህዝቦች ታፈናቅላለች፣ በአካባቢውም ላይ ውድመት ታደርሳለች እየተባለች ትወቀሳለች፣ ይህ ችግር በኢትዮጵያም ውስጥ አለ?’ የሚል ጥያቄ ካቀረበላቸው በሁዋላ ነው።
አምባሳደር ስዩም መስፍን ሲመልሱ ” ቻይና የአፍሪካን ማእድን ለማልማት እዚህና እዛ ለሚቀርብባት ወቀሳ ራሱዋን መመከላከል አያስፈልጋትም፣  የእኛ ነባር ወዳጆች እኮ ይህንኑ ለዘመናት ሲያካሂዱ ነበር” ብለዋል።
“የምእራባዊያን ኩባንያዎች ማእድናትን በአፍሪካ ውስጥ አውጥተው በተወሰነ ደረጃ ቀይረው ወደ ወደ አውሮፓ ሲልኩ ቀረጥ ይከፍላሉ፣ ማእድናትን እንዳለ ሲልኩ ግን ቀረጥ አይከፍሉም ይህ በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ እንዱስትሪ ላይ እድገት እንዳይኖር አድርጓል” የሚሉት አምባሳደር ስዩም  ቻይና ይህንን እስካልኮረጀች ድረስ በአካባቢ ውድመት ዙሪያ ለሚደርስባት ክስ ትኩረት መስጠት እንደማይገባት መክረዋል።
ጋዜጠኛው ” ቻይናዎች ጥሩ ምክር ከእውነተኛ ወዳጅ ይገኛል ይላሉ” በማለት በአምባሳደር ስዩም መስፍን መልስ መርካቱን ገልጿል።
ቻይና በአፍሪካ ውስጥ ማእድናትን ፍለጋ በምታካሂደው እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ ጉዳት ታዳረስላች ለህዝብ መፈናቀልና ችግር ትኩረት አትሰጥም በማለት ወቀሳ እንደሚቀርብባት ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ


ኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ

ኢሳት ዜና:-የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የ እስርፍርድ ወስነውበታል::
በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎችእንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበትተወስኖባቸዋል::

የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለውየሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙንማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነውይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደሱማሊያ ዳግም መዝመቶንም አስታውሷል::

በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ


በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ

ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ከመቶ ደኖን አታለች::
በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል::
ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና ከእንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቶል::
በኢትዮጵያ በደን የተሸፈኑ መሬቶች ተጨፍጭፈው በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል:፡

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ


የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ

ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ:: በተለይ የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ  ሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ::ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ባለፈው አርብ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ሪፓርት እንዳመለከተው በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሂደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ሪፓርቱ አመልክቶል::
የሀገሪቱን የሙስና መጠን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያጠና የቆየው የአለም ባንክ በተለይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ብሎ በመደባቸው
ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ የተካተቱት ቴሌኮም፣ የኤች አይ ቪ መከላከልና ህክምና የመድሀኒት ዘርፉን ጨምሮ በሙስና ቀለበት ውስጥ የወደቁ ናቸው ብሎል::
በመሰረታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቆማት ብሎ ባንኩ በመደባቸው ትምህርት፣ ጤና፣ ፍትህና የመሳሰሉት ተቆማት ቀላል የማይባል ሙስና የሚታይባቸው መሆኑን አጋልጦል::
ባንኩ ያፋ ባደረገው በዚ ሪፓርት ከፍተኛ ሙስና ከሚታይበት ከቴሌኮም ኢንዱስትሪ ቀጥሎ መሬትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ በሙስና መዘፈቁን ይፋ አድርጎል::

ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ


ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልጸዋል::ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
መንግስትም አቡነ መርቆሪዎስ መንበራቸው ላይ ተመልሰው ማየት እንደማይፈልግ በአቶ አባይ ጸሀዬ በኩል ግልጽ አቆሙን ያንጸባረቀ በመሆኑ የዕርቁ ጉዳይ ፍጻሜ ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሎል::
በውጭ የሚገኙ አባቶች በዛሬው እለት በሎስ አንጀለስ በጀመሩት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ በትላንትናው እለት ከካናዳ ሎስአንጀለስ ገብተዋል::
ትላንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለተገኙት አባቶች አቶ  አባይ ጸሀዬ በግልጽ እንዳስታወቁት አቡነ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ማለት መንግስቱ ሀይለማሪያም ይመለስ ከማለት ተለይቶ አይታይም ማለታቸው ተሰምቶል::
መንግስት  አቡነ መርቆሪዎስ ቢመለሱ ግድ እንደሌለው ነገር ግን ፓትሪያርክ ሆነው ማየት እንደምይፈልግ አቶ አባይ ጸሀዬ አረጋግጠዋል::
ስለሆነም የ 6 ኛውን የፓትርያርክ ምርጫ ሂደት እንዲያፋጥኑ እንዳሳሰቦቸውም መረዳት ተችሎል::
አንዳንድ ከመንግስት ጋር የሚሰሩ ጳጳሳት በተለይም ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመለሱ ከሆነ እኛም አክሱም ላይ የራሳችን ሲኖዶስ እናቆቁማለን በማለት ቤተክርስቲያኒቱን በግልጽ በዘር መስመር ለማስቀመጥ ሀሳብ መሰንዘራቸውን የተገኘው ዜና ያብራራል::
ዕርቁን የሚደግፉና አቡነ መርቆሪዎስን በመንበር ማየት የሚፈልጉ ጳጳሳት ቁጥር እየጨመረ የመጣ ቢሆንም መንግስት አቆሙን በግልጽ ማስቀመጡን ተከትሎ የመንግስት  ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ ስብሰባው እንዲጠናቀቅ እየተጠበቀ ነው::

Jan 15, 2013

ESAT Daily News-Amsterdam Jan. 15 2013 Ethiopia

አስደማሚ ለማመን የሚያዳግት ተዓምራዊ ታሪክ

አስደማሚ ለማመን የሚያዳግት ተዓምራዊ ታሪክ
አሏሁአክበር ቁርዓንን ሃፍዞ የተወለደው እና ስምንት ቋንቋዎችን ተናጋሪው የዘጠኝ ዓመት ህጻን
ከ8 ዐመት በፊት ያረገዘችውን ህፃን ለመገላገል ከሆስፒታል የተኛችን አንዲት እናት ለማዋለድ ዶ/ ሮች እና ነርሶች የህክምና እርዳታቸውን እያደረጉ የህፃኑን መወለድ ይጠባበቃሉ በአሏህ ፈቃድ ልጁ ተወለደ ጉዳዩን አስገራሚ ያደረገው ይህ
አይደለም ህፃኑ ከእናቱ ሆድ ሲወጣ የአሏህን ተዓምራዊ መመሪያ እያነበበ (ቁርዓንን እየቀራ) መውጣቱ ነው ታዲያ በዚህ ወቅት እናት እና አባቱ አዲስ
ተዓምርን ይዞ በመጣው ልጃቸው ከመደመም አልፈው በአሏህ ቀድር ደንግጠው ይሞታሉ, በዚህ ወቅት ይህንን አስደንጋጭ ተዓምርን የያዘው mohammed አሳዳጊ ወላጅ ጠፋ በወቅቱ አጠገብ የነበሩት አዋላጁ ዶ/ር ልጁን ለማሣደግ ይነሳሱና ወደ ቤታቸው ይወስዱታል ከዚህ ዶ/ር ቤተሰብ ጋር እየኖረ በኣጋጣሚ ዶ/ሩ ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ይሄዳሉ ታዲያ በዚህ ሰዓት የዶ/ሩ ልጆች መሃመድን መቆሚያ መቀመጫ ያሳጡት ጀመር ይመቱታል, ይሰድቡታል, ይሳለቁበታል, በዚህ ሁኔታ የተማረረው መሃመድ ከዚህ ቤት መውጣት ግድ ሆነበት በወቅቱ የመሐመድን ተዓምር በመስማት የተማረኩት አንዲት እናት መሐመድን ለማሣደግ ይወስናሉ ከእርሳቸው አብሮ መኖር ይጀምራል:የሙሐመድ ታዓምራቶች ብዙናቸው: አረብኛ,አፋርኛ, ሱማልኛ, አማርኛ, እንግሊዝኛ, ፈረንሳይኛ, ቻይንኛ ሱዳንኛን ሳይማር መናገc ይችላል የት/ት bet ደጅን ረግጦ ማያውቀው ይህ የ9 ዓመት ታዳጊ አሏህ ተዓምራቶችን አሲዞ ፈጥሮታል:ይህ ብሩህ ታዳጊ በተለያዩ ሰዎች የተፈተነ ሲሆን 8 ቋንቋዎችን እንደሚያቅ ተረጋግጦለታል:በአሁኑ ሰዓት በልጅነቱ ሊያሳድጉት ከወሰዱት አንዲት እናት ጋር ይኖራል ይህች ሚስኪን እናት እንኳን መሐመድን አሳድገው ለዚህ አድርሰውታል ከእናቱ ሆድ ቁርዓን ሐፍዞ የወጣው መሐመድ የተሻለ ኑሮን እና አሏህ የሰጠውን ችሎታ ለማደበር ተጨማሪ እርዳታን ይሻል:
በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሜታቢራ መንደር ይገኛል:

ፅናት እንደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች

እንደገና ጩኸት፣ አንደገና ዋይታ እንደገና ግድያ በሀረር ከተማ! ባለፈዉ ሳምንት ሙስሊም ወገኖቻችን በሰላማዊ ተቃዉሞ ያቀረቡትን መበታችን ይከበር የሚል ጥያቄ ወያኔ አንደለመደዉ ነብስ ያላወቀ የሰባት አመት ልጅ በመግደል አረመኔያዊ መልስ ሰጥቷል። ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ታዳጊ ህጻን ላይመለስ በወያኔ ጥይት ተገድሏል፤ ረጅሙ ተስፋ ከዚህበፊት እንደተጨፈጨፉት ለጋ ህጻናት በወያኔ ጥይት ህይወቱ በአጭር ሊገታ ግድ ሆኗል።

የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን “በእምነታችን ላይ የዘረኛው ወያኔ የደም እጅ ጣልቃ ገብነት በአስቸኳይ ይቁም! የሃይማኖት ነጻነት ይከበር! “ሲሉ እያሰሙ ያሉት ተቃውሞ 365 ቀናትን በማስቆጠር በመላው ሀገሪቱ ተስፋፍቶ በሀረር የ7 አመት ህጻን ልጅና ወላጅ እናቱ የጨካኙ ወያኔ የጥይት ሰለባ በመሆን ወያኔ መንበረ ስልጣኑን እንደያዘ ለመቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ እየሞተ ነጻነቱን ለማስከበር የሚደረገው ግብግብ ቀጥሏል።

በአወልያ የተጀመረውና ዛሬ ወደ ሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተዛመተውና አሁን ወደክርስትና እምነት ተከታዮችምም እያጠቃለለ ያለው የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ጥያቄ ዛሬም ለነጻነታችን እንታገላለን እየሞትን እንወለዳለን፤ ወያኔ ለነጻነት ለጥያቄያችን የጥይትምላሽ እየሰጠ ወገኖቻችንን እየጨፈጨፈ ቢሆንም ለቀቆምንለት አላማ፤ ለእምነታችን ነጻነትና፣ ለማንነታችን ባይተዋር ሳንሆን ትግላችን ድል እስከተገኘ ድረስ ይቀጥላል ሲሉ ለወያኔ በድጋሜ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

ይሁን እንጅ ቅንጣት ያህል ለዜጎች መብት መከበር ደንታ የሌለው ወያኔ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት በመቅጠፍ፣ ርህራሄ የሌለው ግፈኛ መሆኑንና በስልጣኑ የሚመጣበትን ለመመከት ማናቸውንም ወንጀሎች ከመፈጸም እንደማይመለስ ለማሳየት የአርፋችሁ ተቀመጡ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ህጻናትን በመግደል የአውሬነት ባህሪውን ቀጥሎበታል።

ዛሬ በመላው አለም የዜጎች መብት ተብለው የተደነገጉት የንግግር፣ የመሰብሰብ፣ የመጻፍ፣ የመጠየቅ፣ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነቶች በእኛ ሀገር ወይም በወያኔ መንደር እነዚህን መብቶች መጠየቅ የሽብርተኛ ታርጋ የሚያስለጥፍና የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት የሚያስቀጥፍ መሆኑ እየታየ ነው።

የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላለፉት 365 ቀናት ለነጻነት ባላቸው ቆራጥነት፣ ፅናትና ፍቅር የተነሱለትን አላማ ከግብ ለማድረስ የትግል ስልታቸው አይሎ ከፍርሃት አረንቋ በመውጣት የሃይማኖት ነጻነት ይከበር ዘንድ በአንድ ድምጽ ትግላቸውን ቀጥለዋል፤ ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ትምህርት እየሰጠ በየአቅጣጫው የመብታችን ይከበር ጩኸቶች እየተነሱና እተፋፋሙ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ህዝብ የሙስሊሙ ህብረተስበ ጥያቄ የመብትና የነጻነት ጥያቄ መሆኑን ተረድቶ ትግሉን በመቀላቀል የአገሩን አንድነትና የራሱን መብትና ነጻነት እንዲያስከብር ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራዊ ጥሪ ያደርጋል።

የዜጎችን የነጻነት ጥያቄ በወያኔ የጥይት አፈ ሙዝ ከቶ ማፈን እንደማይቻል የተረዱት ወያኔዎች፤ የእርስ በርስ ብጥብጥ ለማስነሳት ሙከራዎችን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ራሱ ወያኔ እንጅ ሌላ አለመሆኑን ተረድቶ ህዝቡ ከዚህ የህወሃት መሰሪ እቅድ መጠንቀቅ ይኖርበታል።

ህዝቡ ነፃነቱን ለመከላከል አቅም የሚሰጡትን የራሱን ነጻ ማህበራዊ የእምነት ተቋማትን የሚያጠናክርበትን ግንባታ በንቃት መስራት ያስፈልገዋል። በተለይም አሁን በኦርቶዶክስ እምነት እየተስተዋለ ያለውን የወያኔን ጣልቃ ገብነት ለመታገል ህዝበ ምእመናኑ በአንድ ድምጽ የሃይማኖታችን ነጻነት ይከበር ዘንድ እንደሙስሊሙ ወገናችን እጅ ለእጅ ተያይዞ በሀገራችን ሰላም፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ነጻነት እና አንድነት እንዲኖር በጽናት መታገል ያስፈልገዋል።

መደገገፍና ሰበአዊነት ከባህላችን የወረስናቸው ሲሆኑ፣ ለቆምንለት አላማና ለሃገራችን፣ ለነጻነታችን፣ ለአንድነታችን በእምቢተኝነት የምንታወቅ እኛ ኢትዮጵያውያን አሁንም ለወያኔ በየቦታው ጣልቃ ገብነትና ከፋፍለህ ግዛ ድርጊት በዝምታ እጃችንን አጣጥፈን ልንመለከተው አይገባም።

የሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ እንዲሁም የኢትዮጰያ ወጣቶች ስብስብ የሆነው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ጨምሮ እየተናገሩት ያሉት፤ ነጻነትና ፍትህ፣ መልካም አስተዳደር፣ ሰርቶ ማደግ፣ እኩልነትና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብትና ሌሎች፣ በዜግነት የሚገኙ መብቶች እንጅ አምባገነኖች የሚቸሩህ ችሮታዎች አይደሉምና ለቆምንለት አላማ በጋራ በጽናት በመታገል ለቀጣዩ ትውልድ መልካም አሻራን ለመጣል አሁን ተነሱ ነው ጥሪው።

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባችን እንደሙስሊሙ ወገኑ በጽናት እየታገለ የሚያስፈልገውን መሰዋእት በመክፈል የህዝብ፣ የሀገር እድገትንና ደህንነትን አንቀው የያዙ ዘረኞችን በማስገደድ አሊያም በማስወገድ ለሀገራችን ነጻነትና የዴሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ ፈር ቀዳጆች እንሁን ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ለመለስ አለቀስኩ ለምን ቢሉኝ…”

ለመለስ አለቀስኩ ለምን ቢሉኝ…”

ፓውል ኩልሆ ” The Alchemist” በሚለው መጽሀፉ እንዲህ ጻፈ ፦
ናርሲስ ተወዳዳሪ የሌለው ቆንጆ ወጣት ነበር አሉ፤  ከውበቱ ጋር ፍቅር ስለያዘው  በእየለቱ ወደ አንድ ሀይቅ እየሄደ መልኩን በውሀው ነጸብራቅ ሲያይ ይውላል። አንድ ቀን አጎንብሶMeles Zenawi and Ethiopian history ሲመለከት አሸንራተተውና ሀይቁ ውስጥ ገብቶ ሞተ።
በማግስቱ የጫካ ንግስት ውሀ ለመጠጣት ወደ ሀይቁ ወረደች፤  ነገር ግን በፊት የምታውቀው  የሀይቁ ውሀ ወደ ጨውነት ተለውጦ ለመጠጣት አስቸጋሪ ሆኖ አገኘችው።
የጫካዋ ንግስትም የሀይቋን ንግስት ጠየቀቻት
“ስለምን እንባዎችሽን ታፈሻለሽ? እንባዎችሽ እኮ ውሀውን ጨው አደረጉብን?”
“ምን ላድርግ ብለሽ ነው ናርሲስ እኮ ሞተ”
“አንችማ አልቅሽለት ፣ እኔ እሱን ለማደን በየጫካው እዞራለሁ፣  እሱ ደግሞ ካንጂ ጎን ተደፍቶ ቁንጅናውን ሲመለከት ይውላል።”
“ናርሲሰስ ቆንጆ ነበር እንዴ?” ጠየቀች የሐይቋ ንግስት
“ቆንጆ ነበር ትያለሽ? ስለሱ ውበት ካንች የተሻለ ማን ሊነግረን ይችላል? ካንች አጠገብ አይደለም እንዴ ተንበርክኮ የሚውለው?”
የጫካዋ ንግስት በሀሳብ ተውጣ ለትንሽ ጊዜ ጸጥ አለች።
ቀጠለች  “አየሽ የናርሲሰስን ውበት አንድም ቀን አስተውየው አላውቅም ነበር፣  ነገር ግን እሱ ከጎኔ መጥቶ አንገቱን አዘቅዝቆ ሲመለከተኝ እኔ በእሱ አይኖች ውስጥ የራሴን ውበት መልሼ ስለማየው እደሰት ነበር። ያለቀስኩትም ለዚህ ነው።”
መለስ በተቀበረ በሳልስቱ ኢህአዴግ ደስ ብሎት “ለመለስ ዜናዊ  ያነባህ የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ ምስጋና ይገባሀል” የሚል መግለጫ አወጣ።
የኢትዮጵያ ህዝብም እንዲህ ሲል መለሰ “አይ ኢህአዴግ ያለቀስነው እኮ ለራሳችን ነው። መለስ የውበታችን ማሳያ ነበር ፤ በእሱ ክፋት የኛን ደግነት፣ በእሱ ጥጋብ የኛን ረሀብ፣ በእሱ ውሸት የኛን እውነት፣ በእሱ ጉራ የኛን ትሁትነት፣ በእሱ ስድብ  የኛን ጨዋነት እያየን እራሳችንን እያደነቅን እንጽናና ነበር።”
ኤሎን ሳምሶን ( elonsamson@gmail.com)

ቴረሪስቱ ማነው ?አባቶቻችን ነገርን በምሳሌ ሲያስረዱ “ይች ወፍ ገልብጣ ነፋች ይላሉ” ምሳሌዊ አነጋገሩን ያለምክንያት አላመጣሁትም። ከአቶ መለስ ሞት ወዲሕ በኢሕአዴግ ስም ወያኔ ያጠለቆው ጭንብል እየወለቀ ሲመጣ ትክክለኛ ማንነቱን ለመደበቅ በማይችልበት መልኩ መከሰቱ ወያኔዊ ተግባሩን ብቻ ሳይሆን በማጭበረበር ተወልዶ በማጭበርበር ያረጀና የበሰበሰ የነፍሰ ገዳዮች ቡድን መሆኑ የተረጋገጠበት ሀቅ በመሆኑ ነው።

ቴረሪስቱ ማን ነው? – መሠረት ቀለመወርቅ (ከአውስትራሊያ)

አባቶቻችን ነገርን በምሳሌ ሲያስረዱ "ይች ወፍ ገልብጣ ነፋች ይላሉ " ምሳሌዊ አነጋገሩን
ያለምክንያት አላመጣሁትም። ከአቶ መለስ ሞት ወዲሕ በኢሕአዴግ ስም ወያኔ ያጠለቆው
ጭንብል እየወለቀ ሲመጣ ትክክለኛ ማንነቱን ለመደበቅ በማይችልበት መልኩ መከሰቱ
ወያኔዊ ተግባሩን ብቻ ሳይሆን በማጭበረበር ተወልዶ በማጭበርበር ያረጀና የበሰበሰ የነፍሰ
ገዳዮች ቡድን መሆኑ የተረጋገጠበት ሀቅ በመሆኑ ነው። ባለፉት 21 ዓመታት ውስጥ
በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ ላደረሰው ጠቅላላ ውድመት በአቶ መለስ ዜናዊ
የሚመራው ወያኔ የተባለው የሺፍቶች አሸባሪ ቡድን ለመሆኑ የማያወቅ ኢትዮጵያዊ አለ
ብየም አልገምትም።ዛሬም የመለስን የጥፋት እራእይ አንግቦ የሚውተረተረው ወያኔ
ሐይለማርያም ደሳለኝን እና መሰሎቻቸውን ባሻንገለትንት አስቀምጦ የፖለቲካ ሺምጥ
ለመጋለብ ቢሞክርም አሸባሪው ሕወሐት ከቴረሪሰቶች መዝገብ ውስጥ የተመዘገበበትን የታሪክ
አጋጣሚ ለመደበቅ ከቶውንም አይችልም። ከሚገርመው ነገር ወያኔ ዛሬ ለነጣነቱ የሚዋጋውን
አረበኛ፤የእምነት ነጣነቱን ለማስከበር ሰላም ፍቅረነና አንድነትን በመጠየቅ ላይ የሚገኘውን
ክረሰቲያንና ሞሰሊም፤በኢተዮጵያ ውስጥ ሉዓላዊነት የሕግ የበላይነት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት
እኩልነትና ወንድም አማችነት እንዲሰፍን የጠየቁ ምሁራን፤ ጋዜጠኞች፤ አዛውንት አባቶችና
እናቶችን፤ ወጣቶችንና ተማሪወችን በቴረሪስት ቅባት እየቀባ በመግደልና በማሰር ሕዝባችን
ማሸበሩን ከቀጠለበት 21 ዓመታት ተቆጥረዋል። ይች ወፍ ገልብጣ ነፋች ማለት ይኸ ነው።
አሸባሪው ንጡሐኑን አሸባሪ የሚልበት አሸባሪው ሕግ አውጭ ሆኖ ሰላማዊ ዜጎችን የሚቀጣበት
የተገላበጠ ዘመን።
ነገርን ነገር ያነሳዋልና አለማቀፍ ምሁራን ቴረሪሰት የሚለውን ቃል ትረጉም ሲያስቀምጡ
ሰላማዊ ሕዝብን በመኖረያ ስፈሩ በስራገበታው በመዝናኛ ማዘውተሪያው በቤተጰሎት
ማድረሻው ባልታሰበና ባልተጠረጠረ ስዓት አሸምቆ የጦር መሳሪያ በማፈንዳትና በመተኮስ
ሲቢሊያንን የሚገደል ነው፤በተጨማሪም የሰውልጅ ለእለታዊ ኖሮና ለማሕበራዊ እድገቱ
የሚጠቀምባቸውን የቴክኖሎጅ ውጤቶች መዝረፍ ማቃጠልና ማውደም ሌላው ተገባሩ
እንደሆነ ያስረዳሉ።ታዲያ ለቃሉ ከተሰጠው አለም አቀፍ ትርጉም አነጣር በሐገራችን ውስጥ
ተግባር የማንነት መግለጫ ነውና አሸባሪው ወያኔ ከዘመነ ሺፍትነቱ አሁን እስካለበት
የቤተመንግሰት ስልጣኑ ድረስ የተጉዘባቸውን የታሪክ አጋጣሚወችና የፈጠማቸውን ድርጊቶች
ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ ጨዋነትና በቅን ዓዕምሮ ለተመለከተ ሰው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ
ቴረሪስቱ ማነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከባድ መስሎ አይታየኝም ወያኔ በዓለም አቀፉ
መንግስታት የቴረሪስት ድረጅቶች ምዝገባ ውሰጥ ባሸባሪነት ለመመዝገብ የበቃው ቅድመ
ምዝገባ መመዘኛውን በሚገባ አሟልቶ እንጅ እንዲያው ባጋጣሚም አይደለም።
ሺብርተኛው ወያኔ በጫካ ዘመኑ በትግራይ፤በጎንደርና በወሎ በአፋር ሕዝባችን ላይ
በፈጠማቸው ከፍተኛ ወንጀሎች ምክነያት በአለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡት ቴረሪስት
ግሩፖች ውስጥ አንዱ ወያኔ መሆኑን እረስቶት ከሆነ ልናስታውሰው ይገባል።አሸባሪው ወያኔ
ገና ከአፈጣጠሩ በደደቢት በኩል ሺፍትነቱን ሲጀምር ትግራይ ውስጥ የገበሬውን ቤት
ከነቤተሰቡ ዘግቶ በማቃጠል፤ ወጣቱንና አዛውነቱን በጨለማና በጠራራ ጠሐይ በማፈን
እየገደለ ጉልበቱን እንዳሳበጠ የትናት ትዘታችን ነው። በከተሞችም ቢሆን በመቀሌ ከተማ
በአውራጃና በወረዳ ከተሞች ዘራፊ ነፍሰገዳይና አፋኝ ስኩዶችን በማሰማራት ይቃወሙኛል
የሚላቸውን ንጡሐን ወገኖች ይገድል ያሸብር ስለነበር በሺህ የሚቆጠሩ ህጣናት ያለ አሳዳጊ
አባትና እናት መቅረታቸውን እናስታውሳለን። በተመሳሳይ ሁኔታ የግለሰቦችን ሐብት
ከመዝረፍ አንስቶ ያልተሰበረ ድልድይ ያልተመዘብረ ባንክ ያልተሰረቀ ሕክምና መስጫ
ተቁም ያልተቃጠል ትምሕረትቤት አልነበረም እንዲያውም በወቀቱ ድርቅ ያስከተለውን ሰባዊ
ቀውስ ወያኔ ለሺብር ተግባሩ በመጠቀም እራሐብተኛ ወገናችን 20 ሰው በአንድ ጉድጉድ
እየቀበረ የመጣላቸውን ነፍስ አድን አለማቀፍ እርዳታ ከአፋቸው እየነጠቀ ሲሸጥ ነበር።
ስለዚሕ ጨካኝ ቡድን በዙ የተባለበት ስለሁነ መድገም አያስፈልገኝም።
ነፍሰ በላው ወያኔ የሺብር ድረጊቱን ወደመሐል አገር በማስፋፋት በ 21 ዓመታቱ የግድያና
የዝርፊያ የሺበርና የአፈና ግዛቱ በጎንደር በወሎና በአፋር በሐረር በወለጋ በሲደሞ በሸዋ
ገጠሮችና ከተሞች ውስጥ በሰው ሕይወትና በንብረት የፈጠመውን ወንጀል ታሪክና ትውልድ
የመዘገበውና ሕዝባችንም በጠጠት የሚያስታውሰው ስለሆነ በዚች አጭር ማስታወሻ መዘርዘር
ከቶውንም አይቻልም። ይሁንና በትንሹም ቢሆን ለማስታወስ በአዋሳ በጎንደር በሐረር በደሴ
በደበረማረቆስ በጋንቤላ በአምቦ በአሰላ በደብረብርሓን በባሌ በአዲስአበባና በሌሎቹም
ከተሞች እየገደለና ቤትንብረቶን እየዘረፈ የፈጀው ሕዝብ ቁጥር እንዲህ ቀላል እንዳልሆነ
ማንም ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ታዛቢወችም ያረጋገጡት ጉዳይ
ነው።በአውቶቢሰ በባቡር በታክሲ በገበያ ቦታና በመሰብሰቢያ አዳራሾች ቦንብ በማፈንዳት
የሰላማዊ ሰወችን ህይወት በመቅጠፍ በወጡበት አስቀርቶል። ይቃወሙኛል ያላቸውን ስላመዊ
ሰለፈኞች በጠራራ ጠሐይ እረሺኖል። በቀያቸው የሚጫወቱ ሕጣናትን ገድሎል። በገጠሩ
ነዋሪ ሕዝባችን ላይም በመኖሪያ መንደሮቹ አልሞ ተኩሾችና ነፍሰ ገዳይ ጉጅሌወችን
በማሰማራት ጫካው ወንዙ ሳርቅጠሉ ዋሻው በሬሳ ክምር ተሞልቶ ዘመድ አልቅሶ
ሳይቀብረው አሞራ ቁራ የበላውና የዱር አራዊት የተጫወተበት ስንቱን እንደሆነ የሚታወቅ
ነው። ወያኔ ባሰማራቸው ጀሮጠቢወች አማካኝነት ሰላማዊው ሕዝባችን በደስታውም ሆነ
በመከራው ያካበተውን አብሮ የመኖር አኩሪ ባህል በማፍረስና በማሸማቀቅ የግዞት የሺብር
ሕይወት እንዲገፋ ከመገደዱም በላይ በስርቤት የሚማቅቀው በኤሌክትሪክ የተጠበሰው በዱላ
የተቀጠቀተውና አካለ ስንኩል የሆነው ቤት ይቁጠረው። እንዲያውም በየትኛውም አለም
ታይቶም ተሰምቶም በማየታወቅ ዘግናኝ ሁናታ ባልና ሚስት እራቁታቸውን በሕዝብ ፊት
ቆመው ሚስት የባሏን ብልት ባደባባይ እንድትጎትት የተደረገበት አገር ቢኖር የዛሬዋ
የወያኔው ኢትዮጵያ ናት። መከራ የወረደበት ሕዝባችን ከእንዲሕ አይነቱ ስቃይ ለመዳን
ስደትን እንደአማራጭ ቢጠቀምም በተሰደደባቸው አጎራበች ሐገራት ካሸባሪው ወያኔ ግድያና
እስራት ለመዳን አልቻለም።
ወገን ሆይ ታዲያ በዓለማችን ላይ ከዚህ በላይ አሸባሪነትና የሺብር ተግባር ምን አለ ?

የሐገርሕ የወገንሕ መከራ ለሚሰማሕ ወገን ሆይ !!

ዛሬ ሁላችንም እንደምነረዳውና ከላይ በግርድፉ ለማመላከት እንደሞከርኩት ኢትዮጵያና
ኢተዮጵያውያን በአሸባሪው ወያኔ የሚሰቃዩበትና የሚታመሱበት ወቅት ነው። በአንጣሩ ደግሞ
ይሕ የወያኔው የሺብር ድርጊት እንዲቆም የብሶትና የመከራ ድምጥ ገንፍሎ ከየትኛውም
የሐገራችን አቀጣጫ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰተጋባ መጥቶል። ጥያቄው አሸባሪው ወያኔ
የሚፈጥመውን ወንጀል የቡድኑን መሰረታዊ አፈጣጠርና ባህርይ ለሺብር ተግባሩ
የሚጠቀምባቸውን ተቁማት ለይቶ በመረዳት ሕዝባችን ከሺብርተኛው ወያኔ ነጣ በማውጣት
ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም በሐገራችን ለመትከል በተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፈው ወገን
ተመጣጠኝ የትግልና የአሰላለፍ ስልት አውጥቶ የጉዳቱ ሰለባ የሆነውን ሕዝብ ለማስተባበር
ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ ነው ወይ ? የሚለው ጉዳይ በኔ እምነት የወቅቱ ጥያቄ
ይመስለኛል።ነገር ግን ከዚህ ላይ መታወቅ ያለበት በተቃዋሚው ጎራ በኢትዮጵያና
በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጠመ ያለውን የሺብር ተግባር በቀጥታ ከሚደግፉትና የወንጀሉ
ተባባሪ ከሆኑት ተቃዋሚ መሰል ድርጅቶች ሌላ በወያኔ ተቃዋሚነታችን እንከን
አይወጣልንም በሚሉ ተቃዋሚወች በኩል በወያኔ የሚደርሰውን ጥፋት በየጊዜው በአይናቸው
እየተመለከቱ በጀሮቸው እየሰሙ እነሱ ራሳቸው የችግሩ ሰለባ ሆነው እያለ ነገር ግን ድፍረቱ
ኖሮቸው አሸባሪው ወያኔ የመፈጥመውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የማጥፈት እረምጃ
ለማስቆም የሚያስችሉትን የትግል እረምጃወች አቁሞችና ክንዋኔወችን በተገባር ለይቶ
በማውጣት ከሕዝባቸው ፊትለፈት ቆመው ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት በፖለቲካ
ድርጅት ደረጃ ሲከፍሉ አይታዩም እንዲያውም ችግሩ የዲሞክራሲ ጥያቄ ችግሩ የስልጣን
ክፍፍል ችግር ችገሩ የወያኔው መንግሰት የስራ አፈጣጠም ችገር …....... ወዘተ እንደሆነ
አስመስሎ በማቅረብ ወያኔው ለሚፈጥመው የሺብር ተግባር ሺፋን ሆነው የሚያገለግሉ አሉ።
በእርግጥ ከመካከላቸው አንዳንድ ወገኖች የከፈሉትና በመክፈል ላይ ያሉት መሰዋትነት
ታረክና ትወልድ የማይረሰው ቢሆንም ትግላቸው ቀጣይነት ባለው መንገድ በድርጅት ደረጃ
የተጠናከረ ባለመሆኑ የሕዝባችን የመከራ ዘመን ለማሳጥር አልተቻለም። ከዚሕ ላይ ብዙ
ዙሪያ ገባ ሳንመለከት አሸባሪወች በዓለማችን ላይ የሚያደርሱት ሰባዊና ቁሳዊ ቀውሰ ምን
ያህል በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አስከፊ እንደሆነ የምንረዳው ጎዳይ ነው። ለዚሕም ነው መላው
አሜሪካኖች፤ ምዕራባውያን፤ ምስራቃዊያንና ጠቅላላው ዓለምችን አለማቀፍ ሺብርን
ለመግታት በመደራደር ሳይሆን ያለየሌላቸውን ወታደርና የጦር መሳሪያቸውን አሰልፈው
በቢለዮን የሚቀጠር በጀት መድበው ዓለማቀፍ የመረጃና የዲፕሎመሲ ስራቸውን አጠናክረው
መተኪያ የሌለውን የዜጎቻቸውን ሕይወት በመገበር ሺብርተኝነትን እያንበረከኩት ነው
ከፍተኛ አለም አቀፍ ውጤትም አግኝተውበታል እኛም በተገኘው አንጣራዊ ሶላም
ተጠቃሚወች ነንና ልናመሰግን ይገባል ብየ አምናለሁ። ነገር ግን እኛ አትዮጵያዊያን
በሕዝባችንና በሐገራችን ሕልውና ላይ የሚፈጠመውን ሺብር እያየንና እየሰማን የፖለቲካችን
ጭብት ወሬ አሳባቂና ቃላት ሰንታቂ ሆነን ጥርስ የሌለው ውሻ በመሆን ከቴረሪስቱ ወያኔ
የጥፋት በትር በማያድን ጉንጭ አልፋ ንትርክ ስንደናበርና ስንላፋ 21 አመታትን
አስቆጥረናል። እንዲያውም አሸባሪውን ወያኔ ከማሸበር ተግባሩ ውጫ ያለተፈጥሮው የሌለውን
መልክና ቅርጥ እየሰጠን ብሔራዊ እርቅ ድርድር ምርጫ ሰላማዊ ትግል እያልን አሸባሪው
ወያኔ በተቆጣጠራት ሐገር የማናገኘውን ስልጣን በመመኘት የሕልም ጉዞ አላሚወች
ሆነናል።ይሕ አስተዛዛቢ ሁናታ ከአሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ የበለጠ አጋጣሚ ተገኝቶ መቸይሆን
የሚታረመው በሚል እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ያደረብኝን በርቱ ስጋት በተለይም በውጭ
ለሚኖረው ኢተዮጵያዊ ወገኔ ምንም እንኩን አቅሜም ሆነ ችሎታየ ትንሺ ቢሆንም
የተሰማኝን ስሜት በከፍተኛ ሐዘን መግለጥን መርጫለሁ።
ከደስታየ ጥቂቶቹ ደገሞ አርበኞቻችን ወያኔን በሚገባው ቁንቁዋ እያናገሩት መሆኑን በራሱ
በወያኔው አንድበት ምሰክርነቱን ወዶ ሳይሆን ተገዶ በመስጠት ላይ እንደሆነ ስረዳ ደግሞ
በጀግኖች ወገኖቸ ከፍተኛ ኩራትና ተስፋ ይሰማኛል እንዲያውም ወያኔ በጦር ሚዳው ውሎው
በየትኛውም አቅጣጫ እየደረሰበት ያለውን ሺንፈት ጭንቀትና ፍርሐት በወለደው አንደበቱ
እያስተጋባ ነው ። ተፋላሚወቸ ብሎ ከሚመስክርላቸው ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አረበኞች
ግንባር የትግራይ ዲሞከራሲያዊ ንቅናቄን የጋቤላ ነጣነት ንቅናቄ የተባሉ ኢተዮጵያውያን
ድርጅቶች ዋናወቹ እንደሆኑ ተናግሮል።
በዚሕ አጋጣሚ ወያኔ ያፈረሳትን ሐገር፤ወያኔ የረገጣትን ሰንደቅ አላማ፤ወያኔ የዘረፈውን
የሕዝብ ሐብት፤ ወያኔ የበተነውን ሕዘብ ፤ወያኔ ያረከሰውን እምነቶች፤ወያኔ የበከለውን አኩሪ
ባሕል፤ ወያኔ ያነገሰውን ሕግ አልባነት ግድያ አፈና ሺብር ስደትና የግዞት ስርዓት
ለማስወገድ መተኪያ የሌላትን ውድ ሕይወታቸውን በመገበር በዚህ ወቅት በየትኛውም
የፍልሚያ ጎራ ተሰልፈው የወያኔን እብሪት ለማስተንፈስና ለኢትዮጵያዊያን ነጣነት፤
አንድነት፤ለጋራ እድገት ፤ፍቅርና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ነጣነት ያለመስዋእትነት
አይገኝምና የታሪክና የትውልድ አደራቸውን ከሕዝባቸው ጎን ሆነው ግዳጃቸውን በመወጣት
ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና በቅርቡ ከግንባሩ ጋር ሕብረት
በመፍጠር የአሸባሪውን ወያኔውን ጎራ በማንቀጥቀጥ ላይ ለሚገኙት ስድስት ኢትዮጵያውያን
ድርጅቶች ለሚፈጥሙት የላቀ ጀግንነት ምሰጋናየ ይድረሳቸው እላለሁ ይንን የተቀደሰ
ሐገርና ሕዝብን የማዳን ተግባር ለዲሰፖራው ወገን እግዚአብሔር ቅን ልቦና ስጥቶት
አርበኞቹን እንዲቀላቀል ጥሪየን እያቀረብኩ ፈጣሚው እሱ ነውና ለሐያሉ ጌታም ልመናየን
አቀርባለሁ.......//..
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
መሰረት ቀለመወረቅ
አውሰትራሊያ

ESAT Yesamintu engeda Martin and Yohann part II

‹‹አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሁለት ወቅታዊ ጉዳዮች – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ከተመስገን ደሳለኝ
1. ከመለስ ሞት በኋላ መረጋጋት የተሳነው ኢህአዴግ ከበርካታ ችግሮች ጋር ፊት ለፊት ተፋጧል፡፡ ከችግሮቹ በከፊልም
የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ …በረከት ስምኦን የነበራው ተደማጭነት እየተሸረሸረ ነው፣ የበረከት ባለቤት የበረከትን መፅሃፍ
ለመሸጥ (ገዥ ፍለጋ) በየተቋማቱ እየተንከራተቱ ነው፤ አዲሱ ለገሰ የተደማጭነት መስመሩን ‹‹ኢህአዴግን ለማጠናከር››
በሚል ምክንያት ይበልጥ እያደረጀ ነው፤ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከቀን ወደ ቀን በህወሓት ውስጥ ተሰሚነቱ እየጨመረ ነው፣
በእርግጥም ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የአስጊ ህመም ችግር የሌለባቸው ተብለው የሚመደቡት ደብረፅዮን፣ አባይ ፀሀዬና
ቴውድሮስ አድሃኖም ናቸው፣ አቦይ ስብሃት ነጋ ‹‹መፈንቅለ ፓርቲ›› በህወሓት ውስጥ ለማድረግ ቀን ከለሌት እያሴሩ ነው፣
ከሁለት ወር በኋላ የሚደረገው የኢህአዴግ ጠቀላላ ጉባኤ አዲስ ነገር ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል፤ ኦህዴድ በሹም ሽር ሊናጥ
ነው፣ አለማየሁ አቱምሳ በሩቅ ምስራቅ ለሚከታተለው ህክምና እስከአሁን ያለውንም ሆነ በቀጣይ የሚያስፈልገውን ወጪውን
እየሸፈነ ያለው ሼክ መሀመድ አላሙዲ ነው፤ ለምን? አለማየሁ የመንግስት ባለስልጣን ነው፣ በተጨማሪም ሆን ተብሎ
በተሰጠው መርዝ ነው ታማሚ የሆነው የሚባለውን ወሬ ይዘን፣ ከዚህ ጀርባ ማን ነው ያለው? የሚል ጥያቄ መቀርቡ አይቀርም
(የሰማሁት መረጃ ጆሮ ያቃጥላል) ግን ለምን? ኩማ ደመቅሳ መልካም አስተዳደር ባለማስፈንና ሙስናን መቆጣጠር ባለመቻል
እየተወቀሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው አባዱላ ገመዳ በኦህዴድ ውስጥ መረጋጋትን በማስፈንና ስራውን በብቃት በመወጣት በሚል
ተመስግኗል፣ (የማኪያቬሊ ከፋፍለ ግዛ ማለት ይህ ይሆን?) በሚያዚያ ወር የሚደረገውን ምርጫ ተከትሎ የቱኒዝያንና የግብፅን
መሰል ህዝባዊ አመፅ ይቀሰቀሳል በሚል አገዛዙ ፍርሃት አድሮበታል፣ 33ት ፓርቲዎች ነገ በምርጫው ላይ የሚኖራቸውን አቁም
በሰማያዊ ፓርቲ ፅፈት ቤት ከጠዋቱ አራት ሰአት ላይ የፋ ያደርጋሉ (በእርግጥ የደረሱበት ውሳኔን ብግሌ ትክክል ነው ብዬ
አምናለሁ፣ ከዚህ ውጪም ገዥው ፓርቲን ለድርድር የሚያስገድድ ዕድል የላቸውም)፣ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር
ኦስትሪያዊውን አገር ጎብኚ ማን ገደለው? ለምን ተገደለ? የደብረማርቆስ ማረሚያ ቤት ድራማስ በማን የተቀነባበረ ነው?
ኃላፊነቱንስ ማን ነው የሚወስደው? የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ¬¬‹‹ለሽብር ድርጊት ሊውል ሲል ደረስኩበት››
በማለት ከተቀበረበት እንዳወጣው የነገረንን የጦር መሳሪያ ማነው የቀበረው? ይህ መሳሪያስ በእነማን የክስ መዝገብ ላይ ማስረጃ
ሆኖ ሊቀርብ ነው የታቀደው? በቀጣይስ የቦንብ ፍንዳታ በየትኛው ከተማ፣ መቼ፣ ስንት ሰዓት ላይና በምን ሁኔታ ይደርስ
ይሆን? …ይህኛው መንገድስ የት ድረስ ያስኬዳል? ‹‹አዲስ ታይምስ›› መፅሄትን ማፈኑስ ለምን አስፈለገ?
2. በሽብርተኝነት የተከሰሱትን የህዝብ ሙስሊም መሪዎችን በይቅርታ ለመፍታት መንግስት የማጭበርበሪያ ስልቱን እየተጠቀመ
ነው፡፡ በዕለት ሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎች ውስጥ የተዘጋጀ ሶስት
ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡ ከቡድኑ አባላት ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ
ዘካርያስ ለታሳሪዎቹ እንዲህ የሚል የማጭበርበሪያ መደራደሪያ አቅርቦ ነበር፡-
‹‹ጉዳያችሁ በፍርድ ቤት እየታየ ነው፤ ስለዚህም ክሱ አሁን ባለበት ደረጃ ሊቋረጥ አይችልም፡፡ እናም ክርክራችሁን አቋርጡና ጥፋተኛ ነን በሉ፣ ከዛም ፍርድ ቤቱ ከፈረደባችሁ በኋላ
‹ይቅርታ› ጠይቃችሁ እናስፈታችኋለን››
ሆኖም የሙስሊሙ መሪዎች ‹‹ይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነኝም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሲሉ በድፍረትና በቁርጠኝነት መልሰውላቸው ወደ እስር
ክፍላቸው ተመልሰዋል፡፡ በእርግጥም የኮሚቴው አባላት ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰኑት፡፡ ምክንያቱም ይህ የሽምግልና ቡድን ቀንደኛ የስርአቱ ደጋፊ ሲሆን፣ መደራደሪያ ብሎ የሚያቀርበው
ሁሉም ነገር የአገዛዙን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስከብር ነውና፡፡ በድህረ ምርጫ 97 የታሰሩትን የቅንጅት አመራርንም በዚህ አይነት መልኩ መሸወዱ ይታወሳል፡፡
(በነገራችን ላይ ሽማግሌዎቹ በተጠቀሰው ዕለት አንዱአለም አራጌን ጠርተው አናግረውታል፤ እስክንድር ነጋን ግን ዘለውታል፡፡ ለምን? ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ የሽማግሌ ቡድኑ
ለሙስሊሙ መሪዎች ‹‹የመጣነው አንዱአለምን ፈልገን ነው፣ እናንተን እግረ መንገዳችንን ሰላም እንበላችሁ ብለን ነው›› ሲሏቸው፣ ለአንዱአለም ደግሞ የዚህን ግልባጭ ምክንያት
ሰጥተውታል፡፡

ሰበር ዜና – 33ቱ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ ራሳቸውን ሊያገሉ ነው

ፍኖተ ነፃነት
33ቱ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው በመጪው የአዲስ አበባ እና የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ ላይ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን የፍኖተ ነፃነት የዜና ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ ጥር 7, 2005 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚሰጡት መግለጫ ውሳኔያቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መግለጫውን ከቦታው ከስር ከስር ፍኖተ ነፃነት ገጾች ለማስተላለፍ ጥረት ይደረጋል፡፡የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አመራር አባለትን ለማሰር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመራሮቹ አጋለጡ የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ ሰባሳቢ ወጣት ሀብታሙ አያልው ከፍኖተ ነፃነት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደጠቆመው መንግስት እሱን ጨምሮ የማህበሩን አመራሮች ለማሰር ዝግጅት እያደረገ እንዳለ መረጃ ደርሷቸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አዳራሽ ሊያደርጉት የነበረው መስራች ጉባኤም የማህበሩ አባላት ባልሆኑና ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰባች ከታወከና እንዲበተን ከተደረገ በኋላ 6 የማህበሩ አመራሮች እስከምሽቱ 12፡30 ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ወጣት ሀብታሙ ጨምሮ ገልጧል፡፡

(ሰበር ዜና) በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አስገራሚ ነገሮች ተሰሙ

“አቡነ መርቆርዮስ ከሚመለሱ፤ ለምን መንግስቱ ኃይለማርያም ይምጣ አትሉም” አባይ ፀሐዬ

“አቡነ መርቆርዮስ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ ትሰይማለች” የትግራይ ጳጳሳት

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጠው የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎው የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ጳጳሳት ፍላጎት በአሸናፊነት ጎልቶ በመውጣት ላይ እንዳለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው ዘገቡ። እንደምንጮቹ ገለጻ ከትግራይ የመጡት ጳጳሳት “አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ በመሾም በእርሱ እንመራለን፤ ቤተክርስቲያንንም እንከፍላለን” የሚል አቋማቸውን ማሳየታቸውን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ዘግበዋል።
ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረውና ምናልባት ነገ ሊጠናቀቅ አልያም ሊቀጥል ይችላል የተባለው ይኸው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከትግራይ ተወላጅ የሆኑት 18ቱም ጳጳሳት መገኘታቸው የታወቀ ሲሆን “አዲስ ፓትርያርክ ይመረጥ የሚለውን አቋማቸውን” አጠናቅረውበት ከመቀጠላቸውም በተጨማሪ ሌሎች ፓትርያርክ እንዳይመረጥ የሚፈልጉ አባቶች ከቅዳሜ ጀምሮ በድህነነት ኃይሎች እንግልት ውስጥ በመግባት ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ በመደረግ ላይ እንዳሉ እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል።
በተለይም የመንግስት ተወካይ ሆነው የቀረቡት አቶ አባይ ጸሐዬ በግልጽ አዲስ ፓትርያርክ መሾሙን ለማይደግፉ አባቶች “አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ ከምትሉ ለምን መንግስቱ ኃይለማርያም ይምጣ አትሉም?” በማለት እንደተናገሯቸውና እንዳስፈራሯቸው ያረጋገጡት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይ ከትግራይ የመጡት ጳጳስት አቡነ ሳሙኤል (ፎቶ)ና አቡነ ጎርጎርዮስ የአቡነ መርቆርዮስን መመለስም ሆነ ፓትርያርክ እንዳይሾም የሚጠይቁትን አባቶች ስም ዝርዝር ለመንግስት በመስጠት በደህንነት ኃይሎች አቋማቸውን እንዲቀይሩ ትልቅ ሥራ እየሰሩ መሆኑም ተጋልጧል። በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተለይ አቡነ መርቆርዮስ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጣለች የሚል የማስፈራሪያና ቤተክርስቲያንን አደጋ ላይ የሚጥል አነጋገር መሠማቱ ብዙ የ ዕምነቱን ተከታዮችን አስደንግጧል። በአጠቃላይ በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ጳጳሳት በአሸናፊነት እየመሩ ነው። ስብሰባው ነገ ይቀጥላል። በስብሰባው ውስጥ ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች መረጃውን እንዳደረሱን ለአንባቢዎቻችን ያለውን ነገር እናሳውቃለን።

Jan 14, 2013

ESAT Daily News Amsterdam 14 January 2013 Ethiopia

ሰፈር ያሸበረ ዶሮ በፍርድ ቤት ሞት ተወሰነበት


ሰፈር ያሸበረ ዶሮ በፍርድ ቤት ሞት ተወሰነበት

ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከጽዮን ሆቴል ጀርባ በሚገኘው መደዴ ሰፈር ውስጥ ነዋሪውን   ያመሰ ዶሮ፤ በፍርድ ቤት ሞት ተፈረደበት።ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ሸገር ራዲዮ ዶሮውን << አሸባሪ>> ብሎታል።
በጽዮን ሆቴል ጀርባ በሚገኘው መደዴ ሰፈር ወጪ ወራጁን፣አላፊ አግዳሚውን እየደበደበ ያስቸገረ ጉልበተኛ አለ የሚል ጥቆማ በደረሳቸው መሰረት ወደ ስፍራው ማቅናቸውን ነው የሸገር ጋዜጠኞች የሚናገሩት።
ይህን ጉልበተኛ የደፈረችውም፤ ሰናይት የምትባል የሰፈሩ ሴት ብቻ መሆኗን የአካባቢው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ሰናይት ደፈረችው የተባለውም፤ ያሰደረሰባትን ከፍተኛ ደብድባ ተከትሎ መብቷን ለማስከበር ለፖሊስ ክስ መስርታበት በፍርድ ቤት ስላስፈረደችበት ነው።
እንደዘገባው ከሆነ ከሰፈሩ ነዋሪዎች በተጨማሪ ቆራሌ የሚሉ አነስተኛ ነጋዴዎችን የኔ ብጤዎች በተደጋጋሚ በጉልበተኛው ዶሮ ከፍ ያለ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።
የ አካባቢው ድመቶችና ውሾች ሳይቀሩ በጉልበተኛው ዶሮ የሚደርስባቸውን ንክሻና ጥቃት አሜን ብለው ከተቀበሉም ሰንብተዋል።
ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱት የሸገር ዘጋቢዎች በቦታው ሲደርሱ በነሱም ላይ ጥቃት እንዳይደርስባቸው በመስጋት ሁኔታውን በርቀት መከታተልን እንደመረጡ ተናግረዋል።
እግሮቹ ወፋፍራምና ዓይኖቹ ድፍርስ የሆኑት ይህ ጉልበተኛ፤ ከድብድብ ብዛት ግንባሩ እና ጀርባው ላይ መቁሰሉን የጠቀሱት ዘጋቢዎቹ፤ ካሉበት ስፍራ ሆነው ሰዎች በርቀት ሲያሷያቸው- እሱም  ከጉራንጉር ውስጥ ሆኖ እንዳያቸው ጠቁመዋል።
በነሱም ጥቃት እንዳይፈጽምባቸው  ዶሮውን በ አንድ ዓይናቸው የጎሪጥ እየተከታተሉ  በሰሩት ቃለ ምልልስ፤በርካታ የአካባባው ወላጆችና ወጣቶች ሳይቀሩ በዚህ ጉልበተኛ ዶሮ መነከሳቸውን በምሬት ለጋዜጠኞቹ ተናግረዋል።
ከሰፈሩ ሰው አልፎ መንገደኞችን፤ቆራሌዎችንና የኔብጤዎችን ድንገት  ዘልሎ ትከሻቸው ላይ ድረስ እየወጣ በተደጋጋሚ ከፍ ያለ ጥቃት እንደፈጸመባቸው የተናገሩት አንዲት እናት፤ በዚህም ሳቢያ የኔብጤዎች ወደ መንደሩ መምጣታቸውን ጨርሶ እንዳቆሙ ገልጸዋል፡፡
ቃለ-ምልልስ የተደረገለት የመንደሩ ኮስታራና ጎረምሳ ወጣት በበኩሉ፦<<  …በጣም ሀርደኛ ነው፤ እኔ ራሴ እፈራዋለሁ። ፈጽሞ አይመቸኝም>> ሲል በምሬት መልክ ተናግሯል።
የመደዴ ሰፈሩ ዶሮ “ኩኩሉ ሲል ደስ ይላል፤ በጧት ይቀሰቅሰናል ተብሎ ለሰዓት ነጋሪነት እንዲሰነብት ቢደረግም ሳይታሰብ የ የአውሬነት ባህሪይ ማምጣቱ ያስገረማቸው የሰፈሩ ነዋሪዎች፤ <<ምን ታሪክ ነው?>> ሲሉ አግራሞታቸውን ገልጸዋል።
በዶሮው ከፍተኛ ጥቃት ከደረሰባቸው በርካታ ሰዎች መካከል፤ ሴት ሰናይት የተባለች የአካባቢው ነዋሪ አንዷ ነች።
ሁሉም  የደረሰባቸውን ጥቃት አሜን ብለው በቁጭትና በዝምታ ሲመለከቱት፤ሰናይት ግን <፣መብቴ በጉልበተኛ ሲገሰስ በዝምታ አላይም>> በማለት ፍርድ ቤት ገትራዋለች።
ሰናይት   ጥጋበኛው ዶሮ ላደረሰባት የሀይል ጥቃት በወረዳ 10 ፖሊስ ጣቢያ  ክስ እንደመሰረተችበትና ጉዳዩ እስከ ፍርድ ቤት እንደደረሰ የገለጹት የሰፈሩ ነዋሪዎች፤ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከተመለከተ በሁዋላ፦<<የገና በዓልን እንዳያልፍ>> በማለት የሞት ፍርድ ቢወስንበትም፤ የዶሮው ባለቤት ውሳኔውን ተግባራዊ ሳታደርግ ገናን እንዳሳለፈችው ተናግረዋል።
<< በፍርድ ቤት የተወሰነበት ውሳኔ ለምን ተግባራዊ አልሆነም?>> ተብለው የተጠየቁት የዶሮው ባለቤት፤ ስለ ዶሮው  እድሜና ሁኔታ ካብራሩ በሁዋላ፦<< ውሳኔውን ለመጪው ጥምቀት ተግባራዊ አደርጋለሁ፤ለጥምቀት ይታረዳል>> ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
የመንደሩ ትልቋ እማማ በበኩላቸው ለጋዜጠኞቹ ቡድን፦<<በጉዳዩ ዙሪያ ትናንት ተሰባስበን  ውይይት አድርገንበታል።  በአስቸኳይ እረዱ ብለን ተናግረናል። ወስነናል።  የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መጽናቱ የማይቀር ነገር ነው>>ብለዋል።

በሁስተን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል ተንበሸበሹ


በሁስተን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል ተንበሸበሹ

ኢሳት ዜና:-ትናንት እሁድ ሁስተን/አሜሪካ ላይ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶቹም ሆነ በሴቶቹ ምድብ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ የአሸናፊነትን ድል መቀዳጀታቸው ታወቀ።ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት በዙ ወርቁ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ በመግባት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሲሆን፣ አትሌት ተፈሪ ባልቻ 2፡12፡50 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ፣  ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሞላ ሰለሞን ደግሞ 2:14:37 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።
በሴቶቹ ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ መሪማ መሃመድ 2 ሰዓት 23 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ በሆነ ግዜ አንደኛ ሆና የአሸናፊነትን ክብር ተቀዳጅታለች። በውድድሩ ላይ የግራ እግሯ ላይ በደረሰባት ጉዳት ውድድሩን በመሃል አቋርጣ የነበረችው መሪማ፣ እግሯን በፋሻ በማሰርና፣ ሕመሟን በመቋቋም አሸናፊ መሆን መቻሏ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አስችሯታል። ከውድድሩ በኋላ ቃለመጠይቅ ላደረጉላት ጋዜጠኞች እንደገለፀችው ይሰማት የነበረው ህመም ከፍተኛ ነበር። መሪማ ያጠናቀቀችበት ሰዓትም የሁስተን ማራቶን ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ተብሎ ተመዝግቦላታል።
በዚሁ ውድድር ላይ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ብዙነሽ ዳባ በመሪማ መሃመድ በ47 ሰከንድ ብቻ ተቀድማ በሁለተኛነት ስታጠናቅቅ፣ አትሌት መስከረም አሰፋ ደግሞ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ ሶስተኛ ሆና ውድድሩን ማጠናቀቋ ታውቋል።
በግማሽ ማራቶን ውድድርም ባለፈው ዓመት 0፡59፡22 በሆነ ፈጣን ሰዓት አሸናፊ የነበረው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ 1፡01፡54 በሆነ ሰዓት ቀድሞ ሲገባ፣ ሌላው ኢትዪጵያዊ አትሌት ድሪባ መርጋ በሰባት ሴኮንድ ልዩነት ብቻ በፈይሳ ተቀድሞ ውድድሩን በሁለተኛነት አጠናቋል። በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድርም ባለፈው ዓመትም አሸናፊ የነበረችው አትሌት ማሚቱ ደሳካ 1 ሰዓት ከዘጠኝ ደቂቃ ከ53 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

በአዲስ አበባ የባዶ መሬትና የንግድ ቤቶች ሽያጭ ጣራ ነካ


በአዲስ አበባ የባዶ መሬትና የንግድ ቤቶች ሽያጭ ጣራ ነካ

ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ በመንግስት የሚቀርቡ የቤት መስሪያ ቦታና የንግድ ሱቆች ሽያጭ ከግዜ ወደ ግዜ በአስደንጋጭ መልኩ ዋጋቸው እየተሰቀለ መምጣቱን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
የአዲስአበባ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በልደታ ክፍለከተማ የተሰሩ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ጋር ተያይዞ የሚገኙ 150 የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለመሸጥ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ለአንድ ካሬሜትር እስከ ብር 56 ሺ164 ከ11 ሳንቲም እጅግ አስደንጋጭ ዋጋ የሠጡ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ታውቋል፡፡
ኤጀንሲው የ149 ቤቶች አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ከሳምንት በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን ከጥር 6 ቀን ጀምሮ ቤቶቹን ለአሸናፊዎቹ ማስተላለፍ ጀምሯል፡፡
አስተዳደሩ ለንግድ ቤቶቹ በካሬሜትር  የሰጠው መነሻ ዋጋ 6ሺ 600 ብር ሲሆን አሸናፊዎች የሰጡት ዋጋ ግን ከፍተኛው በካሬሜትር 56ሺ164ብር ከ11 ሳንቲም ሲሆን ዝቅተ =ኛው ደግሞ በካሬሜትር 13 ሺ ብር ሆኗል፡፡
በዚሁ መሰረት ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው አሸናፊ የተወዳደረው ለ19 ነጥብ 25 ካሬሜትር በመሆኑ በጠቅላላው 1ሚሊየን 81ሺ157ብር ከ12 ሳንቲም ሲሆን ዝቅተኛ የሰጡት አሸናፊ ለ79 ነጥብ 56 ካሬሜትር 1ሚሊየን 34ሺ 280ብር ይከፍላሉ፡፡
ለዚሁ ለልደታ ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች ከፍተኛ ብር ከሰጡት ተጫራቾች መካከል በካሬሜትር 52 ሺ600 ብር የሰጡት አንድ አሸናፊ ላሸነፉበት 91 ነጥብ 26 ካሬ ሜትር በድምሩ 4 ሚሊየን 800 ሺ 276 ብር ይከፍላሉ፡፡
ከነዚሁ የንግድ ቤቶች አሸናፊዎች መካከል 23 ያህሉ  በካሬሜትር ከ40ሺብር በላይ እጅግ የተጋነነ ዋጋ በመስጠት ያሸነፉ ሲሆን በካሬሜትር ከ20ሺብር በታች አነስተኛ ዋጋ በመስጠት ያሸነፉት 9 ያህል ተጫራቾች ናቸው፡፡

በአዲስአበባ ለንግድና ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት ከመንግስት ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ከግዜ ወደግዜ የመሬትና የንግድ ሱቆች ዋጋ እየናረ ሊመጣ ችሏል፡፡መንግስት ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከመርዳት ይልቅ በየግዜው የሊዝ መነሻ ዋጋውን እያሳደገ ገቢ ወይም ትርፍ ላይ ብቻ ማተኮሩ ክፉኛ እያስተቸው ይገኛል፡፡

የአስተዳደሩ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ከቪላ ቤቶች እስከ ባለአራት ፎቅ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ ባዶ ቦታዎችን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች አጫርቶ ለመሸጥ በጥቅምት ወር 2005  ባወጣውና በአሁኑ ወቅት ለአሸናፊዎቹ እያስተላለፈ ባለው ጨረታ ውጤት መሰረት ለቦሌ ክፍለከተማ በካሬሜትር 11ሺ700 ብር ሒሳብ ለ420 ካሬሜትር ባዶ ቦታ 4 ሚሊየን 922ሺ 400 ብር ተሸጧል፡፡
ንፋስስልክ ላፍቶ ክ/ከ ደግሞ ከቦሌ በባሰ ሁኔታ ተጫራቾች ለአንድ ካሬሜትር ቦታ 12ሺ500 ብር በመስጠት አሽንፈዋል፡፡ ይህኛው ተጫራች ለ191 ነጥብ 21 ካሬሜትር ቦታ 2 ሚሊየን 390ሺ125 ብር ይከፍላል፡፡
ለመኖሪያ እና ለንግድ  ቤቶች መገንቢያ ቦታ ፈላጊዎች አስተዳደሩ ያቀረበው ሊዝ መነሻ ዋጋ ዝቅተኛው በካሬሜትር 191 ብር፣ከፍተኛው 299 ብር ነው፡፡ ይህ መነሻ ብር በተጫራቾች ውድድር በካሬሜትር ከ10ሺ ብር በላይ የሚሰጥበት በመሆኑ አነስተኛና መካከለኛ አቅም ያላቸው ዜጎች በዕድሉ ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡
አንድ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ ስለጉዳዩ አስተያየት ተጠይቀው በተለይ ከልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር ተያይዞ አዲስ የተሰሩት የንግድ ቤቶች እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ ዋጋ እንደተሰጠባቸው አረጋግጠዋል፡፡ “በጨረታው ላይ ተሳትፌ ያውም ተበድሬ ለማሟላት በማሰብ በካሬሜትር 9ሺብር ገደማ አስገብቼ ነበር፡፡ ነገር ግን የማይታወቁ ነጋዴዎች ጭምር ዋጋውን ከአምስት እጥፍ በላይ ሰቅለውት በማግኘቴ ግርም ብሎኛል፡፡ ሰው በገንዘቡ እንኳን በቀላሉ መጠቀም የማይቻልበት አገር እየሆነ መምጣቱ ብቻም ሳይሆን መንግስትም የለየለት ኪራይ ሰብሳቢ ሆኖ መቀመጡ በጣም አሳሳቢ ነው” ብለዋል፡፡
በልደታ የሚገኙት አብዛኞቹ የመኖሪያ በህወሀት ታጋዮች መያዛቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የውሃ ያለህ ይላሉ



ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ውሀ እጥረት ማጋጠሙን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በስድስት ኪሎ፣  መነን፣ ፈረንሳይ፣ ጃን ሜዳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ሰሜን ማዘጋጃ እና በተለያዩ የሰሜን አዲስ አበባ  የሚገኙ ሰፈሮች ውሀ ለማግኘት ውሀ ያለባቸውን አካባቢዎች ማሰስ ግድ ብሎቸአዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ውሀ ለሳምንታት የማይመጣ ሲሆን፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሳምንት አንድ ጊዜ ጥሩ ከተባለም በሳምንት ሁለት ጊዜ ያገኛሉ። በተለይ ፈርነሳይና ሽሮ ሜዳ በከፍተኛ ሁኔታ የውሀ እጥረት አጋጠማቸው አካባቢዎች መሆናቸው ታውቋል።
11 በመቶ እድገት እንደተገኘ በሚነገርባት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ውሀና መብራት ያለማቋረጥ ማግኘት ህልም እየሆነ ነው።
የውሀ መጥፋቱ በሰሜን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በደቡብ አዲስ አበባም የተለመደ ክስተት ሆኗል።
ውሀ ሲባል መብራት መብራት ሲባል ውሀ ይጠፋል፣ መስተዳድሩ ከተማዋን ለማስተዳዳር የተሳነው ይመስላል ይላሉ አንድ የሽሮ ሜዳ ነዋሪ። በእርሳቸው አካባቢ ውሀ ከተቋረጥ ድፍን አንድ ሳምንት ሞልቷል።

Total Pageviews

Translate