Pages

Mar 1, 2014

የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ

 በአንድ ወቅትአንድ ዘጋቢ የኢትዮጵያን ባንዲራ  በሚመለከት ተዘዋውሮ ካናገራቸው የመዲናይቱ ነዋሪዎች አንዱ፥ “እኛ አገራችንን የምንወደው ወያኔዎች ስለነገሩን አይደለም።  እሱማ ባንዲራችንን ባጥላሉበት ዘመንም አገራችንን እንወድ ነበር፤ አሁንም እንወዳለን፤ ወደፊትም እንወዳለን። ይህ በደማችን ውስጥ ያለና መቼም ቢሆን ከልባችን ሊወገድ የማይችል ነገር ነው፤” ብለው እንደነበር አስታውሳለው ።
ወያኔ ወደ ሥልጣን የመጣው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያጋየ ነበር። በመጣም በነጋታው ሕገ-መንግሥቴ የሚለውን መጨቆኛ መሣሪያ ለማጽደቁ ኑ ብሎ በጠራቸው የሱ ብጤ ዘረኞች ስብሰባ ላይ ሰንደቅ ዓላማችን፣ ሲዋረድ፣ ሲብጠረጠር እንደነበር ለታሪክ ዩ-ትዩብ በተባለው የዘመኑ የድምጽና የተንቀሳቃሽ ስዕል ማሳያ የድረ ገጽ ማሳያ ላይ ለሕብረተሰቡ ለዕይታ በቅቶ ይገኛል።
ሰንደቅ ዓላማችን እንዳገራችን እራሷ ባለታሪክ ናት። ሰንደቅ ዓላማችን፣ እነሱ እንዳሏት “ጨርቅ” ብቻ ሳትሆን ስንት ደም የፈሰሰባት ወድቃ የተነሳች ልዩ የታሪካችን መዘክርና የማንነታችን ማብሰሪያ ሰንደቅ ናት።
ይችን ያክል ሰለባንዲራችን ካልኩ እስቲ ማለት ወደፈለገኩት ነገር ልሂድ ፦ ለብዙ ግዜ መልስ ያላገኘውለት ጥያቄ ነው ይህ በዚህ ምስል ላይ
የሚታየው. Ebbelsgata1,.0183Oslo.Norway ያለ የወያኔ ትኬት ኦፊስ ነው ።
ባንዲራውንም ጨምሮ  ማለት ነው ። የማን ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወይስ የወያኔአየር መንገድ ባጋጣሚ በዚህ በኩል ባለፍኩ
ቁጥር ያው የሚታየኝ ነገር ቢኖር የእነዚህ ጨካኝ የሰው አውሬ ሆዳሞች ኢትዮጵያን እየመዘበረና እየገዛ ያለ ሌባ ቀማኛና ሰዶማዊ አገዛዝ  ወይንም ደግሞ ዘረኝነት ኧረ ስንቱ ነገር ተነገሮ የማያልቅ መጥፎ ትዝታዎች ብቻ
 ፦ እስቲ መለስ ብለን እናስብ የወያኔ መንግስት ባሳለፍነው23 ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን አይነት ጢባጢቤ
 እየተጫወተበት እንደሆነ መቼም በየቀኑ እያደረገ ባለው ወይም እያየንባለውነገር መቼም ሳንበሳጭ የቀረን ኢትዮጵያዊ ምድሩ 
ይቁጠረን ግን እስከመቼ  ድረስ እስከመቼስ ነው በማናምንበት እና በምንጠላው ነገር ላይ መወሰን የማንችለው
-ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ የግድ የዚህ የወያኔ ትኬት ኦፊስ ብቻ ነው ያለው ?
-ወያኔን መቃወም ካለብንስ በማንኛውምና በምንችለው መንገድ መሆኑን ረስተነዋል ማለት ነው ?
-ወይስ የሃገር ኢኮኖሚ ምና ምን  ኧባካችሁ እንዳትሉኝ ወያኔዎች ጢባጢቤ የተጫወቱብን ይበቃናል ለነገሩ  እድገትእኮ 11% lol በመቶ ????
 በትንሹ ማድረግ ያልቻልነውን እንዴት በትልቁ ማድረግ እንችላለን?
እስከ መቼ ድረስ ነው እነዚህ ሰዎችስ በእንደዚህሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ  እና ባንዲራዋ ላይ በእንዲህ አይነት መልኩ የሚቀልዱት   እስቲ ተመልከቱት ከዚህ በታች ያለውን ፎቶ የማን ነው የቄሳርን ለቄሳር የሕግዚኃብሔርን ለሕግዚኃብሔር አይደል
እንግዲያውንስ የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ

 

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate