Pages

Jul 13, 2013

የማለዳ ወግ. . .ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ ፣ መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም (አልጀዚራ)

ነቢዩ ሲራክ*”በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! “አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia’s unemployment “በኢትዮጵያ ስራአጥንትን ለመሸሸ ” ያለው ዘገባ ሾለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥአሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንእማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል áŠ áˆáŒ€á‹šáˆŤ ያቀረበወን ዜና እዚህ ላይ ይጫኑና ይመልከቱበዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ሾል ላቀረቡ ወጣቶችስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ዶላር ያበድራል ተብሎ ሰምቻለሁ። የተባለው በእኛሃገር ይሆን ? ስልም ጠየቅኩ ! ” ጀሮ ለልሹ ባዳ ነው “ብየ አላየሁ አልሰማሁም ብየ ልለፈው! አሁን ሰምቻለሁናይሰጣልም ብየ ለቀበለው ። ግናስ ለብድር አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው? ይህ ግን አልገባኝም ! መስፈርቱ ወሳኝሆኖም ይህንንም አድልኦ ሰዎች በፖለቲካ አምለካከት በሃይማኖትና በዘር ሳይለዩ እኩል ታይተው ድጋፉ ይደረጋልበሚል ልቀበለው ። የተባለው ሁሉ እውነት ቢሆን እንኳ የተጠናን ሾል አውርቦ ጠቀም ያለ ብድር የማግኘት እድሉተምሮ ሾል ላጣው አለያም ለነቃው እና ለተደራጀው የከተማ ወጣት እንጅ ለቀረው መፍትሄ አይደለም ።ይህ መፍትሄ በዘገባው ቀርበው ላየናቸውበማንኛውምወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራለመሰደድ ለተዘጋጁት እና ከህጋ የሃገራት ሁለትዮሽስምምነት ውጭ ለሰደዱት ከገጠሩ ክፍል የሚጋዙትቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱትእህቶች የሚፈይደው ነገር የለም ።በአረብ ሃገርበኮንትራት ስም የሚሰደዱ እህቶችን እንዳይሰደዱለማገድ አሸጋጋሪ ደላላዎችን ከመቆጣጠሩ ጎን ለጎንዜጎችን ከድህንት የሚዎጡበትን መንገድ መንደፍ ፣የዜጎችን ነጻነት ማክበር አና ሁሉንም ዜጎች እኩልበማየት መሰረተ ልማቶቸን በማስፋፋት የስራ እድልመክፈት ዋናው መፍትሔ ሊሆን ይገባል።“ኢኮኖሚያችን አደገ ተመነደገ” እየተባለ አቅማችንይህ ማድረግ ካልቻለ ብቸኛው መፍትሄው ” አትሰደዱ” ብሎ መልፈፉና እና “ለሚሰሩት እድሉ ” አለ ብሎ መደስኮሩከመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም ! ስደት ክፉ ነገር ነው ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑትእያላቸው ካላቸው ለመጨመር ከሚሹ ስግንግቦች ውጭ ብዙው ስደተኛ ለመሰደዱ የስራ ማጣት ፣ የድህነትና የኑሮውድነት በቂ ምክንያት እናዳለው በስደቱ አለም ስኖር ካገኘኋቸው ስደተኛ ወገኖቸ የተረዳሁት ሃቅ ነው ።የኑሮ ውድነት ሳያንገሸግሽ ፣ ሳያጨናንቀው ስደትን የሚፈልግ የለም ፣ በሃገሩ ተምሮና ሰርቶ እሱንና ቤተሰቡን መደገፍእየቻለ ስደትን የሚመርጥ የለም ! የመንግስት ሃላፊዎች ለገጽታ ግንባታ የሚለቋቸውን መረጃዎች ገታ አድርገውበስደተኛው ችግር ላይ ቢያንስ ትክክለኛ መረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር ። ከሁሉም በላይ ወደ አረብ ሃገራትበኮንተራት ሾል ስም የሚላኩ ዜጎችን ጉዳይ ቆም ብለው ሊመረምሩት ይገባል። ሰው ” በሃገሬ ተቸገርኩ ፣ ተምሬ ስራአጣሁ !” እያለ ስደቱን ማቆም ይከብዳል። ያም ሆኖ በህገ ወጥ ደላላ ተታልለው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱትንለማስቆም መንግስት በስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ስም እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥ የበከተ ድልላ በሰውር የሚሰራውንስራ ሰንሰለቱን ከቁንጮው ሊበጣጥሰው ይገባል ። ስደትን ማሰወቆም ካልቻልን አማራጩ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገርእና ሊሰሩት ስለሚችሉት ሾል ትክክለኛ መረጃ እና ቅድም ዝግጅቶችን በትክክል አሟልቶ ማቅረብ አማራጭ ሊታይይገባል። ከዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ዜጎችን በሃገራት መካከል በሚደረግ የሰራተኛ ውል መሰረት በህጋዊ ኮንትራት ስራዜጎችን መላክ እና ከተላኩም በኋላ በመብት ማስከበሩ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት በፖለቲካታማኝነት ሳይሆን ዲፕሎማሲው ጥብብ የተካኑትን ከሃላፊዎች በበቂ ሁኔታ በአረብ ሃገራት ሊመድብ ይገባል! ያለንትየስልጣኔ ዘመን ነውና መረጃን በመደባበቅ እውነትን ማጥፋት አይቻልም።ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማቀበል ያዋርዳል እንጂ አያስከብርም ፣ ከሃቅ የራቀ መረጃ ገጽታን ያጨለማል እንጅ ፈካአድርጎ ቀይሮ አያሳይም ! በአልጀዚራ ዘገባ እንደተነገሩት አንዳንድ መረጃዎች አጋጣሚውን ገጽታ መገንቢያ አድርገንእውነቱን የምንሸፋፍን ከሆነ ትልቅ ስህተት ተሳስተናል ! እውነትን በውሸት ለመድፈን ስንቆፍር ነገም እንደ ትናነቱከመከራ መውጣት አይቻለንም ! ዛሬም ጉዟችን ቅጥፈት ከሆነ በምናየው የወገን ሎሎ ፣ የሰቆቃ ድግግሞሽ ስናለቅስእንደኖርን ስናለቅስ እንኖራለን ! አባቶች “በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! ” እኛው ራሳችን በሽታችንስንነግራቸሁ ስሙን ፣ መድሃኒቱንም ፈልጉልን ! የማለዳ ወጌን አበቃሁ !በሽታችን ተረድቶ መድሃኒት ጀባ የሚልየህዝብ አገልጋይ ይስጠን!ነቢዩ ሲራክ

መታየት ያለበት መንግስት በዛሬው የሐምሌ 5 ተቃውሞ አንዋር መስጅድ ላይ አንበሳ አውቶብሶችን ደርድሮ ነበር ...

የአልጀዚራ ዘገባ ‹‹á‰ á‹łá‹Žá‰˝ ድል የተነሱበት ቀን›› የጁምአ ተቃውሞ

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!!!

ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል። ዋና ከተማችን አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት። በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ታሪክን ወደኋላ መለሾ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል። ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው። ወያኔ በያዛቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘኛቸውን ውድ ዋጋና ትላልቅ ጥቅሞች የሚሰጡ በርካታ ንብረቶችን ከተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ተቋሞች፤ ዩኒቨርስቲዎች፤ ሆስፒታሎች፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫዎች ዘርፎ እስከዛሬ ትክክለኛ አደራሻው ለሕዝብ ይፋ ወደ አልተደረገ የሰሜን አካባቢ አይናችን እያየ በረጃጅም የጭነት መኪናዎች አጓጉዞአል። በቀድሞ መንግሥት ዘመን ምንም ዕጥረት እንዳልነበረው የሚታወቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የ24 ሰዓት መብራት አገልግሎትን እንኳ ሳይቀር በማስተጓጎል የከተማውን ሕዝብ ተበቅሎአል።
ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ጥላቻ በጥቂቱም ቢሆን ረገብ ያደረገ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመረው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት በቃኝ የማያውቁት የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እንዲበዘብዙ በተመቻቸላቸው እድል ዘርፈው የያዙትን ገንዘብ ከውልደታቸው ጀምሮ ከሚታወቁበት አካባቢ ሕዝብ እይታ አርቀው “ለደም ካሳ” በዋና ከተማችን እምብርት በነፃ በታደላቸው የከተማ ቦታዎች ላይ ህንጻዎችን በመገንባት ንብረት እንዲይዙ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ በሆነቺው አዲስ አበባ ምርጫ 97ን ተከትሎ ገጥሞት የነበረው ሽንፈት ባስከተለው መዘዝ የተበላሸ ገጽታውን በህንጻና መንገዶች ግንባታ ስም ለማሳመር መጣር ናቸው።
የአዲስ አበባ ኮንደሚኒዬም ቤቶቾ ግንባታ ከምርጫ 97 ቦኋላ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት የሚሰቃየውን ሕዝብ ልብ ለማማለልና የፖለቲካ ድጋፍ ለመግዛት ያስችላል ተብሎ የታሰበ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ድብቅ ዓላማዎችም አሉት።
  1. በዘረፋ የከበሩ የቀድሞ ተጋዳላዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አይናቸው ያረፈባቸውን ቁልፍ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ለዘመናት በባለይዞታነት ይዘው የኖሩትን በልማትና በእንቨስትመንት ሥም በማፈናቀል ወደ ግላቸው ላማዞር ያስችላቸዋል፤
  2. በተለያዩ ሥም የተቋቋሙ የህንጻ ሼል ተቋራጭ ድርጅቶቻቸው በግንባታው ሼል በመሳተፍ መጠነ ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ያመቻቸዋል፤
  3. የሥርዓቱን ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከሌላ ቦታ አምጥቶ በማስፈር በጠላትነት የተፈረጀውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጽዕኖ ለማምከን ይረዳል፤
  4. በሀብት ዘረፋው ለመሳተፍ እድል የሌላቸው የበታች ካድሬዎችና ታማኝ አገልጋዮችን ተጠቃሚ በማድረግ በአለቆቻቸው ዘረፋ ተማረው ልባቸው እንዳይሸፍት ይከላከላል ፤
  5. ከተወለዱበትና ካደጉበት የግልና የቀበሌ ቤቶች ያለውደታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የኮኖዶሚኒየሙን ሂሳብ መክፈል እስከቻሉ ድረስ “ከቤታችን ተፈናቅለን ሜዳ ላይ ተጣልን” የሚል እሮሮ በማሰማት መንግስት ላይ አመጽ እንዳያስነሱ ስጋት ለመቀነስ ይረዳል፤
  6. ከሰሞኑ 40 ከመቶ ተብሎ በወጣው ፖሊሲ እንደታዘብነው ደግሞ ዜጎችን በማጓጓት ተቸግረው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ የገንዘብ እጥረት አንገቱ ድረስ የዘለቀውን አገዛዝ ለመታደግ ያስችላል (በ16 የሥራ ቀናት ብቻ ከተመዘገበው 750, 000 የኮንዶሚንዬም ቤት አመልካች 750 000 000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር መሰብሰቡን ልብ ይሏል)
ከዚህም በተጨማሪ የኮንደሚኒዬም ቤቶች ግንባታ በቂ ጥናትና ዝግጅት ያልተደረገበት የይድረስ ይድረስ ሼል መሆኑን የቤቶቹ ርክክብ በተፈጸመ ማግሥት ሾለ ህንጻው መሬት ውስጥ መስጠምና መጣመም መጀመር እየወጥ ያሉ ዜገባዎች ዋቤ ምስክር ናቸው።
የወያኔ መሪዎችና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከኮንደሚኒዬም ግንባታ በተጨማሪ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ እያግበሰበሱ ያሉት የከተማ ቦታዎችን በውድ ዋጋ የልጅ ልጆቻቸው እንኳ ሊደርሱበት ለማይችል የግዜ ገደብ በሊዝ በመቸብቸብ ነው። በዚህ የመሬት ቅሪሚያ አንዳንድ ስግብግቦች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” እንዲሉ “ወያኔዎች መሬታችንን እየተቀራመቱ ስለሆነ ተሻምተን ማስቆም አለብን” በሚል ብልጣ ብልጥነት ከሚኖሩበት የስደት አገር እየተጓዙ የወያኔን ገቢያ በማድራት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት ተመልክቶአል። አገርን ዘርፎ ለዘራፊ እየሰጠ ያለ መንግሥት ሴል ተባባሪ መሆን በሞራልም ሆነ በህሊና ዳኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ሳያንስ እነዚህ በስግብግብነት የተጠመዱ ወገኖች ለንብረታቸው ደህንነት ሲባል ወያኔ ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃዎች እንኳ ለመቃወም ድፍረት በማጣት ሌላ ትዝብት ውስጥ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የገዙት ባርነትን ነው ወይስ የንብረት ባለቤትነትን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይኖራቸዋል?
የዜጎች መብት በተከበረበት አገር ከዜግነት መብቶች አንዱ የግል ሀብት ባለቤት ለመሆን ገደብ የሌለው ነፃነትና እድል መኖሩ ነው:: ወያኔ በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያችን ግን የንብረት ባለቤት ለመሆን የሥርዓቱ ባለሟል መሆን አለያም ከፖለቲካ ባላንጣነት መራቅ ዋና መስፈርት ናቸው። በዚህ መስፈርት ከወያኔ ጋር ተሻምተው ወይም ተሻርከው የንብረት ባለቤት ለመሆን እየተሽቀዳደሙ ያሉ ወገኖች ሊያውቁት የሚገባው ሃቅ ቢኖር አድሎአዊነት በሰፈነበት መንገድ የተገኘ ማንኛውም አይነት ሀብት ወይም ንብረት ወደፊት በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ በሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ህገዊ ጥበቃ የሚኖረው አለመሆኑን ነው። ብሄራው የአገር ጥቅም ላይ ክህደት ከፈጸመ ፤ ዜጎችን በማፈን ሰቆቃ ካደረሰ ፤ የአገሪቷን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል መሬታቸውን ቀምቶ ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ለዘራፍ ከሰጠ ወንጀለኛ መንግሥት ጉያ ውስጥ ተወሽቆ እስከ ወዲያኛው የህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ንብረት ባለቤት መሆን ማሰብ እጅግ ይቸግራል። ዜጎች በራሳቸው ወዝ ለፍተው ያገኙትን ንብረት ሳይቀር በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ብቻ በሽብርተኝነት እየፈርጀ የሚነጥቅ ሥርዓት ዕድሜ እንደምንጠብቀው ረዥም ሊሆን እንደማይችል ማሰብ ብልህነት ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ አገዛዝ በውጭው ዓለም በስደት ከሚኖረው ወገናችን በአባይ ግድብ የቦንድ ሺያጭ ሥም ለመሰብሰብ ሞክሮ ያልተሳካለትን ገንዘብ በመሬት ሺያጭ እና በኮንደሚኒዬም ቤት ግዥ ሥም እንዲያገኝ ሊፈቀድለት አይገባም ብሎ ያምናል:: ስለዚህም እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች በስተጀርባ ያለውን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥ ጥረቱን በማምከን የሕዝባዊ እምብተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ማስፈጸም አይችልም "ጉቦኝነት 44% ሆኗል"


city


“ዕድገት”፣ “ትራንስፎርሜሽን”፣ “ህዳሴ”፣ “የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)”፣ … በሚመሯት ኢትዮጵያ ሙስና እየከፋ መሄዱ ታወቀ፤ ከመቶ ሰዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ጉቦ የሚሰጡ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡
ሰሞኑን ዓለምአቀፉ የግልጽነት ድርጅት (Transparency International) ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በርካታ የአፍሪካ አገራት በሙስና “መበስበሳቸውን” ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ አገራት መካከል እንደምትገኝ ዘግቧል፡፡
ከዚህ በፊት በያዝነው ዓመት ጥር ወር የሙስና አደጋ የተጋረጠባቸው አገራትን ዝርዝርና የአደጋውን መጠን በሰባት ደረጃ በመከፋፈል ይኸው ድርጅት ባወጣበት ጊዜ ኢትዮጵያን በከፍተኛ የሙስና አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት ዝርዝር ውስጥ አስገብቷት ነበር፡፡ በዚህ ዘገባ መሠረት በሙስና የተዘፈቁትን አገራት በመከፋፈል ባስቀመጠው ባለዘጠኝ መዘርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሁለተኛው ውስጥ አካትቷታል፡፡
bribe 1ሰሞኑን የወጣው ዘገባ ይህንን እንዲል ያስቻለው አንዱ መረጃ “ጉቦ ሰጥተዋል ወይ (ያውቃል)?” በማለት ለአንድ ሺህ ሰዎች ያቀረበውን ናሙና መሠረት በማድረግ ነው፡፡ በጥያቄው መሠረት በኢትዮጵያ 44በመቶው “አዎን” በማለት መመለሳቸውን ዘግቧል፡፡
ጥናቱ የ3በመቶ የስህተት ገደብ ያደረገ ቢሆንም፤ የነጻ ሚዲያ፣ በነጻነት የመናገር፣ ያለፍርሃትና ዛቻ ሃሳብን የመግለጽ፣ ወዘተ መብት በተረገጠባት ኢትዮጵያ የዘገባው ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡ በቅርቡ ልሹ ኢህአዴግ በሙስና ላይ ዘመቻ ጀምሬያለሁ በማለት የወሰደው እርምጃ ጎልጉል “ሙስናን በስንጥር” በማለት የዘገበው ቢሆንም ዓለምአቀፉ የግልጽነት ድርጅት ካወጣው መረጃ ጋር ሲነጻጸር “የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀውንና የሚኖረውን ብታውቁና ብትኖሩ ኖሮ” የሚያስብል ነው፡፡
ከህዝቧ ግማሽ በላይ ሥራአጥ በሆነባት (የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ነው)፣ 86በመቶ ምንጥ ያለ ድሃና 80በመቶ በግብርና የተሰማራ ችግረኛ ሕዝብ በሚኖርባት አገር፤ ዘገባው ያወጣው አኃዝ ጉዳይ ከሚያስፈጽመው ሕዝብ መካከል ግማሽ ያህሉ ጉቦ መስጠት ግዴታው መሆኑ፤ ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ለማስፈጸም ጨርሶ አቅቶታል ወይም ጉዳዩን ከማስፈጸም ተቆጥቧል የሚያስብል ነው፡፡
ለ5ዓመታት በአዲስአበባ ኃላፊነት ከቆዩ በኋላ ሰሞኑን ወደ ጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት “ማቀዝቀዣ” የገቡት ኩማ ደመቅሳ በስንብታቸው ወቅት በኢህአዴግኛ “ኪራይ ሰብሳቢነት” አሁንም የከተማዋ አሳሳቢ ችግር እንደሆነ አምርረው ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁኔታና አሁን የወጣው ዘገባ “ውርሳቸውን እናስጠበቃለን” የሚባሉት ሟቹ መለሾ፤ በረሃ በነጻአውጪነት ከዚያም በመንግሥትነት ራሳቸው ስለመሩት ድርጅት የተናገሩትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት “ከእንጥላችን ገምተናል”(የዘገባውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ)

ፕሬዚዳንት ሆኖ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቆመ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መልሚ áˆŤá‹˛á‹Ž ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ  á‹áŠ“ ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡ á‰ áŠ áˆáŠ‘ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ከአንድ ወር በኋላ á‹¨áˆšá‹ŤáŒ áŠ“ቅቁ ሲሆን በመስከረም ወር 2006 መጨረሻ አዲስ ፕሬዚዳንት በፓርላማው አብላጫ ወንበር ያለው ገዥው á“áˆ­á‰˛ ኢህአዴግ ዕጩ አቅርቦ ያስመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በፓርላማ የግል ተመራጭ የሆኑት የጥርስ ሐኪም ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ሰፊ ግምት ተሰጥቷቸው የቆዩ ሲሆን እሳቸውም ለኢህአዴግ ያላቸውን ታማኝነት በየአጋጣሚው ሲያሳዩና ሲገልጹ መክረማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኃይሌ ሰሞኑን ፕሬዚዳንት እንደሚሆን መግለጫ የሰጠው ምናልባት ከኢህአዴግ ታጭቶና እሱም ዕጩነቱን ተቀብሎ ሊሆን áŠĽáŠ•á‹°áˆšá‰˝áˆáŠ“ ይህም ወሬውን አስቀድሞ ሕዝብ ውስጥ በማስገባት የልብ ትርታውን የማዳመጥ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ጠንካራ áŒáˆá‰łá‰¸á‹áŠ• አስቀምጠዋል፡፡

በለንደን ሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ 787 ድሪምላይነር መጠነኛ ቃጠሎ ደረሰበት (video)

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን ሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ቆሞ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን መጠነኛ ቃጠሎ ደረሰበት ።
ቃጠሎው ሲደርስ ምንም ዓይነት ተሳፋሪ በአውሮፕላኑ ውስጥ እንዳልነበር ነው የተገለፀው ።
የቃጠሎው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም ።
ቢቢሲ በዘገባው መጠነኛው ቃጠሎ በቁጥጥር ሾር ከዋለ በኋላ ተዘግቶ የነበረው አውሮፕላን ማረፊያው በድጋሚ ተከፍቷል ።
LONDON — London’s Heathrow airport suspended both of its runways on Friday after a parked Ethiopian Airlines Boeing 787 Dreamliner caught fire, but no casualties were reported.
“Both runways have been suspended after a fire onboard an Ethiopian Airlines plane,” a spokeswoman for the west London airport told AFP.
“Emergency services are currently dealing with the incident. No one was on board so there were no casualties.”
Television images showed the Dreamliner surrounded by pools of foam, with three fire engines on the scene.
 
Boeing temporarily withdrew its troubled next-generation jet from service earlier this year for modifications after concerns that batteries on board could cause fires.
The global grounding order was issued in January after lithium-ion batteries overheated on two different jets, with one of them catching fire while the aircraft was parked.
Boeing has not been able to identify the root cause of the problems, but rolled out modifications it said would ensure they were safe.
In April, an Ethiopian Airlines Dreamliner — reported to be the same plane that caught fire at Heathrow — flew from Addis Ababa to Nairobi on the first commercial flight since the grounding.
Heathrow is London’s main airport and one of the busiest passenger hubs in the world.

Jul 12, 2013

ገዢው ፓርቲ በደሴና ጎንደር የሚካሄዱትን ሰላማዊ ሰልፎች ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው የፓርቲው ሰዎች በአቋማቸው ጸንተዋል

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና ከማስፈራራት አልፈው ፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ የሆቴል ባለንብረቶችን እስከ ማስፈራራት መድረሳቸውን የፓርቲው አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል።
የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሀን ፣ የደሴ ከንቲባ ፣ አፈ ጉባኤውና 7 የምክር ቤት አባሎች በተገኙበት ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የደሴ ከንቲባ አቶ አለባቸው ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ከረመዳን ጾም በሁዋላ እንዲያካሂድ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከንቲባው ካቀረቡዋቸው ምክንያቶች መካከል “ወሩ የረመዳን ጾም የተጀመረበት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ጸጥ ብሎ እንዲጾም እና እንዳይረበሽ፣ በቅርቡ በደሴ ከተማ ተገደሉት ሼክ ሟች ቤተሰቦች ብስጭት ላይ ስለሆኑ በሰልፉ ላይ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ፣ ገዳዮችን ለማፈላለግ የጸጥታ ሀይሎችን ስላሰማራን ሀይል ባለመኖሩ” የሚሉት ይገኝበታል። ፓርቲው ” በቅዱስ ረመዳን ወቅት ጽዱስ ሾል መስራት ተገቢ ነው” በማለት በከንቲባው የቀረቡትን ምክንያቶች ውድቅ አድርጓል፡፡
ፓርቲው በጸጥታ ሀይሎች እየደረሱ ናቸው ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሮ ለከንቲባው አቅርቧል። ከንቲባውም ስራችሁን ቀጥሉ ችግሮች ካሉ እንነጋገራለን ማለታቸውን አቶ ዛካሪያስ አስታውሳው ይሁን እንጅ ቅስቀሳ ለማድረግ የወጡ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ መታሳራቸውን ገልጸዋል።  á‹¨áŒ¸áŒĽá‰ł ሀይሎች በአንድነት አመራሮች ላይ የሚደርሱትን እንግልት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ” ለምን?’ በማለት ሲቃወሙ መታየታቸውንም አቶ ዘካሪያስ ገልጸዋል:: በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች በመጪው እሁድ በሚደረገው ሰልፍ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል
በጎንደር ከተማ ደግሞ ከአዲስ አበባ የሄዱ ፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ እስከመከልከል የደረሰ እርምጃ መሰዱን የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን ተወካይ አቶ እእምሮ አወቀ ገልጸዋል ። በነገው እለት ከአዲስ አበባ ከሄዱት አባሎች ጋር በመሆን  ወረቀት ማሰራጨት እና በመኪና ላይ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ አቶ አእምሮ አስታውቀዋል።

Jul 11, 2013

ልብ የሚነካ ግጥም፡ ‘የህጻኑ ጥሪ’ መታሰቢያነቱ ለ እስክንድርና በግፍ ለታሰሩ ወላጆች (በድምጽ) መታየት ያለበት (የህጻኑ ጥሪ ምላሽ ይፈልጋል)


በአዲስ አበባ በረዶ የተቀላቀለበት ዝናብ ጥሎ በንብረት ላይ ጉዳት አስከተለ

ዛሬ በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ከስፍራው
ክለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች አመለከቱ።
በአውቶቡስ ተራ፣ በአፍንጮ በር ድልድይ እና በሌሎችም አካባቢዎች በጣለው ዝናብና በረዶ መኪናዎች እና ሰዎች
ለመጓጓዝ ችግር ገጥሟቸው ሲሰተጓጎሉ ውለዋል ያሉት የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች በተለይም የንግድ ቤቶች ውስጥ
እየተዝናኑ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ውሃው ጉዳት እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል። ምንጮቹ አክለውም ውሃው በአንዳንድ
የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሳይቀር በመግባት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ማህበረሰቡም ከቤቱ ውስጥ የገባውን ዝናብ ለማውጣት
ሲታገል በአንዳንድ ሰፈሮች ታይቷል።
የዛሬውን ዝናብ ተከትሎ ጋዜጠና ገጣሚ ፋሲል ተካልኝ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን ከፎቶ ግራፍ ጋር አስፍሯል። ____ወይ ጥጋብ! ¡!____ የአፍሪካ መዲና..ውዴ አዲስ አበባ ከባቡሩ በፊት..አሰኘሽ ወይ ጀልባ?!?
* * *
___ፋሲል
ተካልኝ አደሬ___
በአዲስ አበባ በረዶ የተቀላቀለበት ዝናብጥሎ በንብረት ላይ ጉዳት አስከተለ

Jul 9, 2013

በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ450 በላይ መድረሱ ታወቀ

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል።
ወደ  አርባምንጭ እስር ቤት ከተላኩት መካከል አቶ አማኑኤል ጎቶሮ ፣ ደፋሩ ዶሬ ፣  እዮብ ጦና፣  ሻምበል ሻዋ፣ አልመሳ አርባ፣ አቶ ባንቲርጉ ሄባና፣ ወ/ሎ ጊፍታነህ ፈርአ፣ ባሻ ፋንታሁን ታደሰ፣ አቶ አበራ ገ/መስቀል፣ መ/ር ዶለቦ ቦንጃ ፣ መምህር መሸም ማላ፣ አቶ ጴጥሮስ ሀላላ እና አቶ ቲንኮ አሻንጎ ይገኙበታል።
የወረዳው ፖሊስ በዛሬው እለት 15 የሚሆኑ ወጣቶችን ከእስር ለመልቀቅ መፈለጉን ቢያስታውቅም፣ “እስረኞቹ ግን መጀመሪያውኑ ለምን አሰራችሁን አሁንስ በምን ምክንያት ትለቁናላችሁ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው እስካሁን እንዳልተለቀቁ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው በከተማዋ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንደተናገሩት ፖሊስ ምግብ ከሚያቀብሉ ሴቶች እና ልጆች  በስተቀር ሌሎች ነዋሪዎች ወደ አካባቢው እንዳይጠጉ በመከልከሉ የእስረኞችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ከ470 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።
ኢሳት ከ86  በላይ የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል።  áŠ¨áŠĽáˆľáˆ¨áŠžá‰˝ መካከል á‹¨áˆ˜áŒ€áˆ˜áˆŞá‹Ť ዲግሪ ያላቸው በሙያቸው ረዥም ዓመታትን ያገለገሉ  ከ22 የማያንሱት ደግሞ የኢህአዴግ አመራር አባላት የነበሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ሼል አጦች፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ሌክቼሬሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፤ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው፡፡
አካባቢው ዛሬም በመከላከያ እና በልዩ ፖሊስ አባላት እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል
እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ማሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ? ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?

workneh and bereket
ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።
ሚዲያውን መዳፋቸው ሾር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” á‹¨áˆšáˆ ጥያቄ አስነስቷል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት ከድርጅታቸው ይሁንታ ውጪ “አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ይሆናሉ። የሚቀረው የስርዓት ማሟላት ጉዳይ ነው” ማለታቸው  የህወሃትና የኦህዴድ ሰዎችን ክፉኛ አበሳጭቶ እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች “አቶ በረከት አማካሪ ሆነው ወደ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ መዛወራቸው ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር የመገፋት ወይም ሾል አልባ የማድረግና ከቀጥተኛ ተሳታፊነት የመታቀብ ያህል ነው” ባይ ናቸው።
“በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሳተፍ መብት የሌላቸው አቶ በረከት ሲፈነጩበት ከነበረው የኢህአዴግ ሚዲያ bereketመሰናበታቸው በራሱ በርካታ ጉዳዮችን የሚያመላክት ነው” የሚሉት ምንጮች “የፖሊሲና የጥናት ጉዳዮች ከፍተኛ የቀለም እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ኩማ ለዚህ አይመጥኑም። ውሳኔው ማቀዝቀዣ ውስጥ የማስገባት ያህል ነው” ሲሉ አቶ በረከት ያላቸው የአደባባይ ሚና ማክተሙን ያወሳሉ።
በሌላ በኩል የተለየ አስተያየት የሚሰነዝሩ ክፍሎች እንደሚሉት “አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሾል እለት እለት ሥርስራቸው ሆነው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ስልጣን ነው። ይህ የሚያሳየው እሳቸው አሁንም ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቀጠላቸውን ነው” በማለት የሃሳብ ልዩነታቸውን ያስቀምጣሉ።
አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ አቶ መለሾ በህይወት እያሉም ቢሆን ሶስቱ እንደማይለያዩ ያመለከቱት ክፍሎች፣ የህወሃት የበላይ አመራርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስትር ውስጥ የሚሰይሙት ሚኒስትር፤ ሪፖርትር እንዳለው አቶ በረከት ካልሆኑና የህወሃት ሰው ከተሾመ “በትክክልም አቶ በረከት ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው” ሲሉ ሁለት ጫፍ ያለው አስተያየት ሰንዝረዋል።
አቶ ኩማ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት የተመለሱ፣ kumaኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ። አቶ ኩማ ካላቸው ልምድና ዕውቀት አንጻር አቶ ሃይለማርያምን በፖሊሲ ጉዳዮችና በጥናት ረገድ ለማማከር የሚችሉ ሰው እንዳልሆኑ ስምምነት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም። ከዚህ አንጻር በዓለምቀፋዊ ዋና ከተማነት ከምትታወቀው አዲስአበባ ከንቲባነት ወደ አማካሪነት ኩማ ደመቅሳ “ሲሾሙ” እንደ ሥልጣን ሽረት ከተቆጠረ፤ የበረከት ስምዖን በተመሳሳይ መልኩ መታየት የማይችልበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የሚከራከሩ አሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሥልጣን በምክትል ጠ/ሚ/ርነት ሲያድግና ኢህአዴግ በምርጫ የመሸነፍ ቅንጣት ችግር ሳይኖረው ኩማን ከከንቲባነት ሥልጣን ማንሳቱ የብቃት ማነስና አለመፈለግ እንደሆነ ተጨማሪ አስተያየቶች አሉ፡፡
ለሶስትና አራት ዓመት ህጻን “ከክልላችን ስለተባረርክ የትምህርት ገበታህ ላይ መቀመጥ አትችልም” የሚል ደብዳቤ የሚጽፉና በሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል። ሃዋሳ ነዋሪ የሆኑ ለጎልጉል áŠĽáŠ•á‹°áŒˆáˆˆáŒšá‰ľ አቶ ሽፈራው የዘረጉት ድር መበጣጠስ እንዳለበት የታመነው አሁን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠር የክልል በጀት እንደፈለጉ ከሚያስኬዱበትና ያለገደብ ሥልጣናቸውን ከሚያከናውኑበት የክልል ፕሬዚዳንትነት ወደ ሚኒስትርነት “መሾም”፤ የሥልጣን ሽረት ተብሎ ከመጠራት ውጪ ምንም ሊባል እንደማይችል በሽፈራው ሽጉጤ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻቸውም ያመኑበት ጉዳይ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርን መምራት ያቃታቸው አቶ ደመቀ በስራ ብዛት ሰበብ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸውን ወንበር ብቻ እንዲይዙshiferaw áˆ˜á‹°áˆ¨áŒ‰áŠ• ያመለከቱት ክፍሎች “አቶ ሽፈራው በሹመቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከሚቀርቧቸው ሰምተናል። ሃዋሳ በክልሉ መስተዳድር ውስጥ እሳቸው የሰገሰጓቸውም ስጋት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሃይለማርያም “ታማኛቸውን” በመሾም (“በማስመረጥ”) እውነተኛ የደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል፡፡
ደመቀ መኮንን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸው ብቻ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ምን አልባትም አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ በአማራ ክልል ከነበራቸው “ልምድ” አኳያ ለኮታ ማሟያ ታስበው ነው በሚል ካድሬው በስፋት እንደሚያወራ እየተሰማ ነው። አቶ ደመቀ በአማራ ክልል የደህንነቱ መሪ እንደነበሩና በዚሁ በተግባራቸው “የተመሰገኑ ታማኝ” ለመሆን መብቃታቸውን የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር የሚያስታውሱት እኒህ ክፍሎች “አቶ ደመቀ የአማራው ክልል መሬት ተላልፎ ሲሰጥ አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም ሲሉ፣ እሳቸው መፈረማቸው ይፋ ከሆነ በኋላ DemekeM‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” በማለት አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ጀምሮ ከደህንነቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ታማኝ እንዳሰኛቸው አስታውቀዋል። ከዚሁ ውለታቸውና ልምዳቸው አንጻር በደህንነት መ/ቤት ውስጥ ይካተታሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሰኔ 27 ቀን ለተሰየመው ፓርላማ በቀረበው ሹመት መነጋገሪያ ከሆኑት መካካል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ችግር እንደተጣባው የተመሰከረለትን የትምህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ መመደባቸው፣ አንዲሁም የአቶ ደመቀ በ”ስልጣን በዛባቸው” ሰበብ የሚኒስትርነት ቦታቸውን መነጠቃቸው በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።

የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉልአስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።
በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።
አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው Workineh-Gebeyehu-መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።
አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።
ዝርዝር ጉዳዩን ለማብራራት እንደሚቸገሩ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንዲዋቀር አዋጅ የታወጀለት የደህንነት መ/ቤት ሚኒስትርና የበላይ ሃላፊዎች ይፋ ሲሆኑ ነገሮች ይበልጥ እንደሚጠሩ ተናግረዋል። በኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረውና አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልጠራ የሚነገርለትን ልዩነት ተከትሎ የተሸናፊውን ወገኖች የማጥራት ሾል በተለያዩ ስልቶች እንደሚሰሩ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ የደህንነት ሚኒስትር ሲቋቋም የሚሾሙት ባለስልጣን ከቀድሞዎቹ መካከል እንደማይሆን ምልክት ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን የአዲስ ሹመትና ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።በዚህም መሰረት
አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ – የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸም – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሆነው የተሾሙ ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

Ethiopia Intelligence, Security Services Powers Extended


The Ethiopian government has announced plans to transform the National Intelligence and Security Service (NISS) into an autonomous federal government office.
This is expected to strengthen its ability to act on national security issues and ensure it can respond to issues today and in the future.
The National Intelligence and Security Service (NISS) was established in 1994/95 as the Security, Immigration and Nationality Affairs Authority. Its name was changed to the NISS in 2006/07.
On Tuesday, the plan to re-establish the NISS was presented to the House of People’s Representatives.
Three reasons were given: To strengthen the NISS to allow it to protect and defend the sovereignty of the country, the constitution and constitutional order; to determine the power, duties and accountability of the NISS to promote peace, development, democracy and good governance; and build a modern and strong NISS, loyal and resilient to the constitution and constitutional order of Ethiopia and conscious of national and international interests 
The aim of the NISS is to protect national security by providing quality intelligence and reliable security services. Under the plans presented, it is accountable to the Prime Minister.
The proclamation preventing the establishment of other intelligence and security institutions has given other powers to the NISS.
The agency has a wide permit to lead intelligence and security work both inside and outside Ethiopia, formulate national security and intelligence policies and establish and run intelligence and security training institutions.
Under the new plans, the NISS will also work with foreign intelligence and security organisations to share intelligence and conduct joint operations.
It will also investigate domestic or foreign threats to the constitution and constitutional order, threats to economic growth or governance within Ethiopia and collect intelligence.
It will also lead on national counter-terrorism co-operation and co-ordination and represent the country in international and continental counter-terrorism relations and co-operation.
The service will follow up and investigate terrorism and extremism and collect information. 
Its security role includes providing and controlling immigration and nationality services to Ethiopian and foreigners, studying and submitting to the government service charge rates and implement same upon approval; providing the necessary service for refugees based on the Refugee Proclamation and in co-operation with other appropriate organs; leading aviation security activities, providing aviation security services and coordinating other aviation security stake holders in accordance with the Ethiopian Aviation Security Proclamation; providing security protection to the president and prime minister of the country as well as to heads of states and governments of foreign countries in collaboration with other relevant organs. 
Girma Seifu, the only opposition MP, said that NISS employees should be separate from the civil service, in the interests of professionalism.
He said they should also have different ID cards to distinguish them from support staff. “Other support staff might use the ID to harass people as they might not have the ethics,” he said.
He cautioned that the new NISS should provide security to society and should not intimidate people

Jul 8, 2013

እዩልኝ ሲያቅመኝ፤ “አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት” ጎንደር ዘ ኢትዮጵያ (Abe Tokichaw)

996816_481813375244363_822890382_n
እዩልኝ ሲያቅመኝ፤  ”አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት”
አንድ አማርኛ መመህር ነበሩን ጺማቸው የጎፈረ ጸጉራቸው የተንጨበረረ ነበር፤ በአንዱ ቀን ታድያ ፊት ለፊታችሁ በምታዩት ነገር ግጥም ጻፉ አሉና አዘዙን፡፡ ሁላችንም አንገታችንን ደፍተን ስንንደፋደፍ አንዱ ሳተና ጨርሻለሁ… ሲል እጁ
ን አወጣ… በል እስቲ አጋራን… አሉና መድረኩን ሰጡት፡፡ እርሱም ጀመረ፤
ያጎፈረው ጢምዎ…
ዝንጀሮ አስመስልዎ…
አቤት የፀጉርዎ…. ብሎ ገና ከመጀመሩ ተማሪው ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ከት…ት ብሎ መሳቅ ጀመረ፡፡ ይሄን ጊዜ መምህሩ ተቆጡ…
ተዉ እንጂ ተማሪዎች… ገና እኮ ነው በደንብ ያቅመኝ እንጂ… አሉን፡፡ ሌላ ሳቅ…
አንድ ወዳጄ ባለፈው ግብጽን አስመልክቶ ያወጋሁትን በእንዲህ መልኩ ይዋጋዋል… ደህና አድርጎ አቅሞኛል፡፡ ለነገሩ እኔም የምለቀው አይመስለኝም…  ሾለ ባዕድ ሀገር የማውራት ሞራሌ እስኪሰባሰብ ግን እስቲ እርሱ ያቃመኝን ላልደረሰው ላዳርሰው ብዬ በድረ ገፃችን ላይ ለጥፌዋለሁ፡፡
አንዳንዴ ሁለት ተዋጊ ጀቶች ከአንድ የጦር ሰፈራቸው ቦምብና ሮኬት ወይም ሚሳይል አንግበው ይነሱና በጠላት ወረዳ ደርሰው ከማጥቃታቸው በፊት በሚፈጠር ስህተት እርስ በርሳቸው ተላትመው ቦምቡም፣ ሚሳይሉም፣ ሮኬቱም ለጠላት መሆኑ ቀርቶ ለራሳቸውና ለአብራሪዎቻቸው ይተርፋል። አቤ “ደግሞ በግብፅ እንጣላ እንዴ” በሚል አርእስት የላካቸው ጀቶች (ፌስቡክ ላይ ያሰፈራቸው መልእክቶች) ይህ ዕጣ ገጥሟቸዋል እያልኩ ይህን ከበላይ አካል ፈቃድና እውቅና ያገኘ ፅሑፍ ልጋብዝ።
ግጭቱ እንዲህ ነው፤ አቤ በአንድ በኩል ‘ሙርሲ ዋጋውን አገኘ’ ይልና በሌላ በኩል ‘የተመረጠን የገለበጡትን መቃዎም ተገቢ ነው’ á‹­áˆˆáŠ“ል። እዚህ ላይ አቤን እንደ ፌስቡከኛ ብቻ በማየት ባለማለፍ በጉዳዩ ላይ መነጋገር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ። ለምን አቤ ኢሳት ላይም የሰራልና ነገሮችና የነገሮች ሂደት የሚገዙበት ደንብ መጣረስ የለበትምና። መጣረስ ደግሞ አንዱ የኢሳት ችግር ነው፤ ለምሳሌ ኢሳት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ውስጥ መከራና ችግር በዛ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጣሱ፣ አምባገነንነቱ ገደብ አጣ፣ የኢትዮጵያ ጉዞ ወደ ጥፋትና ወደ በመበታተን እየሆነ ነው ወዘተ የሚሉ መልዕክቶችን ያስተጋባል። በሌላ በኩል ደግሞ “ምንም የለም በሉ ከደስታ በቀር … ምንም ችግር የለም… አዲስ ነው ዘመኑ … ኧረ አዲስ ነው! ክፉው ዘመን አልፏል…” የሚለውን ዘፈን ደጋግሞ ይጋብዘን ነበር። የአሁኑን እንጃ በናይል ሳት ላይ በነበረበትና እንደ ልብ እንከታተለው በነበረበት ጊዜ ግን ይህ ነገር በተደጋጋሚ ነበር የሚሰማው። ለመሆኑ ዘፈን የምንጋበዘው ሾለ መልዕክቱ ነው ወይስ ስለዘፋኙ ወይስ ስለዘፋኙ ቲፎዞዎች ሲባል? አንድ ጊዜ ‘ኢሳቶች ገና ከመጀመራችን ለትችት ተሽቀዳደሙ’ ሲል ሰምቻቸው ነው እንጅ ይህን መሰል ነገር ቀደም ብሎ ማድረግ ጥሩ ነበር። ‘እናቴ ሆይ በእንቁላሉ … ’ አለ ነው የተባለው በሬ ሰርቆ ለስቅላት የቀረበው ሰውዬ?!
በኢሳት የተላለፉ ተመሳሳይ መጣረሶችንና በደንብ ያልታሰበባቸው የሚመስሉ ዝግጅቶችን ከተለያዩ ፕሮግራሞቹ በመሞነታተፍ ማቅረብ ይቻላል። አንድ ቀን ይህን ማድረግ ተገቢ ነው።
ወደ አቤ እንመለስና በመጀመሪያ ሁለቱን ጀቶቹን እንያቸው።
ጀት ቁጥር አንድ
“እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም፡፡ በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ … ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ… አሉት ..። ስለዚህ በእኔ በምስኪኑ እምነት የእነዚህ ብዙሃን አቤቱታ መሰማት አለበት፡፡ ለዚህም ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለብዙሃኑ ጆሮ ሰጥቷልና!” ጥቅስ አቤ ቶኪቻው።
ጀት ቁጥር ሁለት
“ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች (የሙርሲ ደጋፊዎች) እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…! እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡… እኔ ይቺን እየተየብኩ ባለበት ሰዓት የወታደሩን ጣልቃ ገብነት በመቃወም በተቀሰቀሰው አዲሱ ተቃውሞ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሊደርስ እየተንደረደረ ነበር፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…! እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡” አሁንም ጥቅስ ከአቤ ቶኪቻው ነው።
የሁለቱ ጀቶች ፍፃሜ
የአሜ ጥቅስ ሲቀጥል የሚከተለውም ይገኝበታል “መጨረሻ ላይ እንደኔ አስቴየት ያኛውም ትክክል ይሄኛውም ትክክል ሆነ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ዲሞክራሲ አጣብቂኝ ውስጥ የምትገባው ይሄኔ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የሚል ሌላ አስተያየት ልጨምራ!”
አቤ ይቀጥላል፤ “አሁን ከሙርሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ማረፊያ ቤት መውረድ በኋላ ተቃዋሚዎቹ (የሙርሲ ተቃዋሚዎች) የልባቸው ደርሶ ወደ ጎጇቸው ሲመለሹ የሙርሲ ደጋፊዎች ደግሞ ይቺን ይወዳል የሙርሲ ልጅ ብለው እየቀወጡት ይገኛሉ፡፡ ይህ ሊመጣ እንደሚችል ተንታኞቹ ድሮውንም ገምተዋል፡፡ ማለቂያው ምን ሊሆን እንደሚችል ግን የሚያውቀው የላይኛው ብቻ ነው፡፡”
የአቤን ጀቶች ይዘት እንመርምራቸው!!
አቤ ጀት ቁጥር አንድን “ብዙሃን” እና “ህዝብ” የሚል ታርጋ በመለጠፍ ጥሩና ትልቅ ጀት አድርጎ ሲያሳየን፤ ቁጥር ሁለት ጀትን ግን “ተቃዋሚዎች” እና “ሰዎች’ የሚል ታርጋ በመስጠት አሳንሰን እንድናያት በዘዴ እየሰራ ነው።
አቤ የሙርሲን ተቃዋሚዎች በወታደራዊ ሃይል መደገፋቸውን እሰየው የሚያስብል፣ በሰዎች ሊደረግ የሚገባው እርምጃ አድርጎ ወሰደውና የመርሲ ደጋፊዎች ወዮታን ግን ከፈለገ የላይኛው ይርዳቸው በሚል ለበጣ አልፎታል።
አቤ እንዳሻኝ እፅፋለሁ ለማለት ‘መቼም ለሙርሲ ሞራል ተጠንቀቅ [አትሉኝም]…’ ሲል ፅፏል። በቀልድ መልክ አስተምራለሁ ብሎ መጣጥፍ የሚያቀርብ ሰው ግን በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ መመራት የለበትም እላለሁ። ይህ ፅሑፍ የአበበን አመለካከት ብቻ ሳይሆን አቤ ነገሮችን የሚፈርድበትን ሚዛንም ነው የሚያሳየን። አቤ ሾለ ምንም ነገር ሲፅፍ የሱን ፅሑፍ ለሚከታተሉ ሰዎች ስለሚለግሰው እውቀት፣ በልባቸው ሊያኖረው ስለሚችለው ተስፋና ሞራል፣ ዝንባሌና አመለካከት መጠንቀቅ እንደሚጋባው ማሰብ የለበትም ይሆን?
አቤ በድፍረት “እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም” ብሏልና ይህ ነገር ብዙ ብዙ ይናገራል።
“በሕዝብ የተመረጠ መሪ አጉራ ዘለል ሆኖ ተገኘ ከተባለ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት ድጋሚ ምርጫ ማድረግ ነው የሚገባው ወይስ የአደባባይ ግርግርን መሰረት አድርጎ መዘርጠጥ?” ይህ ለአቤ የማቀርበው ጥያቄ ነው። አቤን የምጠይቀው ሌላም ጥያቄ አለኝ “ይህን ያህል ሃይል ያለው የግብፅ ጦር ለምን ሕዝብ ድምፁን በስነ ስርዓት የሚያሰማበትን ወይም በሕጋዊና ‘ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት’ ባለው የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት የሚካሄድበትን መንገድ አላመቻቸም?”
ሾለ ሰልፍ ካነሳን አይቀር የሙርሲ ደጋፊዎችም ገና ከመጀመሪያው አንስቶ አደባባዮች ላይ ነበሩ። በቢቢሲ መስኮት ያልታየ ሕዝብ “ሕዝብ” አይባል ይሆን? ብየም ልጠይቅ።
ሚዲያንና ድምፅን የማሰማትን ነገር ከወሳን አይቀር ከሐምሌ 5-7/ 2013 ባለው ጊዜ ብዙዎቹ የአውሮፓ ሚዲያዎች ለመጥቀስ ያህልም ቢቢሲ፣ ዩሮ ኒውስ፣ ፍራንስ-24 ወዘተ ገና ከማህፀን ያልወጣው ከእንግሊዛዊ ልዑል ባለቤቷ ኬቲ የፀነሰችውን ልጅ ‘መጣ፣ ደረሰ፣ ቀረበ’ ሲሉና ሾለ ህፃን አልጋ፣ ሾለ ህፃን ልብስ፣ ሾለ አራስ ልብስ ወዘተ ሃተታ ብቻ ሳይሆን የዜናቸው ዋና ክፍልም አድርገውት አይተናል። እንግሊዝ ውስጥ ሌሎች የተወለዱ፣ የሚታዩና እዚህና እዚያ የሚኖሩ ድምፃቸው ሊሰማ የሚገባ ሰዎች የሉምና ነው ለአንድ ‘እጭ’ ይህ ሁሉ ጫጫታ?! Mail On Line የተባለው የእንግሊዝ ድረ ገፅ Royal birth the world is waiting for ሲል ነው ነገሩን የዘገበው። ምን ያህል ሕዝብ ቢጓጓ ነው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው መወለድ ያለው? ሚሊዮን ወይስ ቢሊዮን? ሚዲያ እንዲህ ነው። ለልሾ ሲቆርሱ…
ሚዲያዎች የተቋቋሙበት ዓላማ አላቸው። ነገራቸው ሁሉ በዚህ የተቃኘ ነው። የግብፅ ጦር ከሄሊኮፕተር አበባና በመልዕክት የተሞላ ወረቀት እየበተነ ያበረታታው ሰልፈኛ (ሕዝብ) የመኖሩን ያህል በተመሳሳይ ዕለት በታጠቀ ሃይል ከበባ ውስጥ አስገብቶ መንቀሳቀሻና መላዎሻ ያሳጣው ሕዝብም ነበር። አቤ ‘ቢቢሲ ሁለቱን ሰልፎች ጎን ለጎን እያሳየ ነው’ ያለን የሙርሲ ቁርጥ ከታወቀ በኋላ ነው፤ ቢቢሲ ለቀናት የሙርሲን ደጋፊዎች ችላ ብሎቿ ነው የነበረው። የአሜሪካ ባለስልጣናትና የአውሮፓ ጋዜጠኞች የስልጣንና የስራ ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ ችላ ያሉትን ሃቅ ወደ ኋላ ተመልሰው በማስተጋባት ይታወቃሉ። ይህን የሚያደርጉት የህሊና ወቀሳ አላስተኛ ብሏቸው ወይም በዚያ ሚስጢር ቀዳሚ (ብቸኛ) ተጠቃሚ በመሆን ታዋቂነት ወይም ‘ታላቅነት’ ወይም ገንዘብ ለማግበስበስም ሊሆን ይችላል። ቢቢሲም ይህን ባህል በመጠቀም ይታወቃል። ሾለ ቦብ ጌልዶፍና እሱ ያሰባሰበው የዕርዳ ገንዘብ የት ገባ በሚል ፕሮግራም የተሰራው ነገሩ ከተፈፀመ ከ25 ዓመታት በኋላ ነው። መጀመሪያ ላይ ይህ ፕሮግራም ለሕዝብ ቀርቧል። ከዚያም ይህ ታሪክ ብዙ ውዝግብ ፈጥሮ ከቢቢሲ ከድረ ገፅ እስከመሰረዝ ደርሷል። ይህ ለአቤ ቅርብ የሆነው ታሪክ ነውና አቤ የሚዲያዎችን አካሄድ በዚህ ሊመዝነው ይችላል። ቦብ ጌልዶፍ በእንግሊዝ ንግስታዊ መንግስት “ሰር” ተብሎ የተሾመ ነውና ቢቢሲን አናውጦታል። ከማናወጥም አልፎ ቢቢሲን አፉን ይይዝ ዘንድ አስገድዶታል። ሌላም ታሪክ እናስታውስ፤ በአጠያያቂ ሁኔታ ሕይወታቸው ስላለፈው ሾለ እንግሊዛዊው ዶክተር ኬሊ እና በግድያው (በሞታቸው) ዙሪያ ጉዱን ለማጋለጥ ያስችላል የተባለን አንድ ፕሮግራም ቢቢሲ ለሕዝብ በማቅረቡ አታካራ መፈጠሩንና አታካራው አንድሬ ግሊጋንን (የቢቢሲ ዳይሬክተር የነበረ) ከሓላፊነቱ ሾለ ማስነሳቱ ታሪክ ፈተሽ ፈተሽ እናድርግ!!
ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ። ወንድሜ ሚዲያን ማመን ብዙ መርምሮ ነው። ሰሞኑን ኦባማ አፍሪካን ሲጎበኙ “ኦባማ አምባገነን ናቸው ያሏቸውን አገራት አይጎበኙም” እያልን የበኩላችንን ደረት የመንፋትና ክብረ ቢስ ‘ጌቶቻችንን’ የማሸማቀቅ መከራዎችን እያደረግን ነው የሰነበትነው። ለነገሩ ይህን እያልን ሰዎችን እንጎሻሽም እንጅ ኦባማ የአምባገነን አገር አይጎበኝም የሚለው እውነት ሆኖ አይደለም። ኦባማም ይሁን እየተነሳ ያለፈ የአሜሪካ ፕሬዘደንት ሁሉ ከአምባገነን ጋር ሳይላላስ የቀረበት ጊዜ የለም። አዲስ የአሜሪካ ፕሬዘደንት በተመረጠ ቁጥር ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ለገብኝት ይጠራል፣ ይሄዳል፣ የውሻ ሰንሰለት የሚያክል የወርቅ ሃብል ከነ ሜዳሊያ ከሳውዲ ነገስታት እጅ በአንገቱ ተጠልቆለት ይመለሳል። በኔ አመለካከት ሳውዲ ውስጥ የለየለት ኋላቀር፣ የለየለት የምዕራባውያን (በተለይ የአሜሪካ) አሻንጉሊት ወይም ገረድ፣ ሰው አራጅ (ሾለ ‘Chop Chop Square’ ማንበብ ጥሩ ነው )፣ ሴቶችን እንደ እቃና እንድ እንስሳ የሚቆጥር ወዘተ ወዘተ መንግስት ነው ያለው። ዕድሜ ሚዲያን በገንዘብ ሃይል ሰለመቆጣጠር በሰሜን ኮርያ ስልጣን የቤተሰብ ‘ቮሊቦል’ ሲሆን የተከፉት ‘ዲሞክራቶችና’ ‘ጋዜጠኞች’ በሳውዲ ስልጣን ብቻ ሳይሆን አገር ‘ቮሊቦል’ ሲሆን ጭጭ ነው።
አቤ አንተ እነዚህን ሚዲያዎች ሰምቶ ነው የግብፅ ሕዝብ ሰልፍ ሲባል እነማንን ማሰብ እንደሚገባ የፈረደው። የነፃነትና የዲሞክራሲ ሰባኪ የሆነችው እንግሊዝ ያቋቋመችው የመገናኛ ቢሮ (Office of Communication- OFCOM) ያገዳቸው ወይም አፈና ያካሄደባቸውና በምድረ እንግሊዝ እንዳይሰራጩ የከለከላቸው እነ ፕረስ-ቲቪን ብታይ ደግሞ የተሰለፈው ሕዝብ የሚለው አመለካከትህ ሰፋ ይላል ወይም ይቀየራል ብዬ እገምታለሁ። በእርግጥ እኔ የማምነው ከቢቢሲ፣ ከቪኦኤ፣ ከስካይ ኒውስ፣ ከፎክስ ኒውስ የምሰማውን ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ይህ ግን ወደ ትክክለኛና ሚዛናዊ ፍርድ አያመራም።
አቤ “በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ… ሀቂቃውን ለመናገር ግን በግብጽ ተቃውሞ የወጡት ብዙሃን አንደነበሩ እድሜ ለቴክኖሎጂ በወቅቱ በቦታው ተገኝተው ሲዘግቡ የነበሩቱ ቀጥታ ሲያነፃጽሩልን ነበርና፤ ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ… ያሉት ብዙ እንደነበሩ ድንጋይ ነክሰን ብንምልም አንፈራም” ብሎናል። ይህ አቤ ከምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች የወረደን ነገር እንዳለ የመቀበልና አማራጭ ሚዲያዎችስ ምን ይላሉ ብሎ ቅራና ቀኝ ለማየት እንደማይፈልግ ወይም ለዚህ ጊዜ እንደሌለው ወይም ከቢቢሲ ወዲያ ለአሳር ብሎ የማለ መሆኑን ያሳየናል ለማለት ልድፈር ይሆን? አቤ ለጠቅ አደረገና ሚዛኑን ሲያሳየን በድጋሜ “ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለብዙሃኑ ጆሮ ሰጥቷልና!” ብሎናል። ለአቤ መረጃ አቀባይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማለት ቢቢሲ እና መሰሎቹ ብቻ ይሆኑን? ብዙ ድረ ገፆችና ነፃ ሚዲያዎች እንደ ልብ በሞሉበት በዚህ ዘመን… ምነው… ምነው… ?
አቤ በዜማ (በግጥም) ይህን ብሏል “ተመረጥኩኝ ብለሽ አትበይ ደንበር ገተር… ከልተመቸው “ንኪው” ይልሻል ባላገር…” የሚል ዘፈን አለ አይደል…። የዚህን ዘፈን ዜማ ባልሰማውም ከ1997 ምርጫ በኋላ የአና ጎሜዝን ሪፖርት ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለአንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ‘ምርጫ ተጭበርብሯል እየተባለ የአውሮፓ መንግስታትም ሆኑ የአውሮፓ ህብረት ለምን ጠንካራ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጠቡ?’ ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። ለዚህ መልስ ነው ብለው የፓርላማ አባሉ ብዙ ነገር ነው የተናገሩት። ዋና ዋና ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል “… የአካባቢው (የአፍሪካ ቀንድ) ወታደራዊ ሚዛን ሊዛባና ክልሉ ሊበጣበጥ ብሎም የሽብር መነሃሪያ ሊሆን ይችላል… የመለስ ተቃዋሚዎች ከአዲስ አበባ ውጭ ጠንካራ መሰረት የላቸውምና… ሂትለር ወደ ስልጣን የመጣው በምርጫ ነበር፤ የሰው ልጅ ነገሮችን አስቀድሞ የሚያይ ቢሆንና ያንን የምርጫ ውጤት ቢቀለብሰው ኖሮ ለዓለማችን ትልቅ በረከት በሆነ ነበር። ያ የምርጫ ውጤት ቢገለበጥ ለዓለማችን ትልቅ ጠቀሜታ ነበረው ነገር ግን ይህ ነገር ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ምርጫ ተጭበረበረ እያልን እንተቸው ነበር እንጅ ምርጫው መገልበጡ ያስቀረውን ችግርና መከራ ስለማናውቀው እናመሰግነውም ነበር…” እኝህ ሰው በግልፅ ይናገሩት እንጅ ምዕራባውያን ለጥቅማቸው ሲሉ ከዚህ የከፋ ምክንያትም ሊዘረዝሩ ይችላሉ። የ1997ተን ምርጫ ከታዘበ በኋላ ጂሚ ካርተር ቦሌ ላይ ምን ብሎ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰጠ ሰምተኸዋል የሚል ግምት አለኝ። ካርተር ሃሳቡን የቀየረው የአና ጎሜዝን መግለጫና ጥንካሬ ካየ በኋላ አልነበረምን?
አቤ! ወደራዊ ጣልቃ ገብነት በለው መፈንቅለ መንግስት ይህ ነገር በቱርክ ቢፈፀ ምን ትለን ነበር? የቱርክ ወታደር አደባባይ የወጡ ቱርካውያንን በመደገፍ ተመሳሳዩን እርምጃ ቢወስድ እነ ኦባማ እነ ሜርክል ምን ይሉ ይመስልሃል? ሚዲያዎችስ?
የሙርሲንና የጓደኞቹን መታሰርም ልትቀልድበት ሞክረሃል። ማንም ሰው በምንም ላይ ቢቀልድ ‘መብቱ’ ሊሆን ይችላል ወይም በማን አለብኝነት መብቴ ነው ብሎ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን ሁልጊዜም አሳሪ ትክክለኛ ታሳሪ ወንጀለኛ አድርገን ከወሰድን ምርጡ ኢትዮጵያዊ ወንድማችንንና ምርጧን ኢትዮጵያዊት እህታችንን (እስክንድርና ርዕዮት) ከነ ምርጥ የሙያና የአላማ ጓደኞቻቸው እስር ቤት ናቸው። ጊዜ የሰጣቸው ደግሞ ‘አሸባሪዎቹ’ እያሉ ነው የሚያብጠጥሏቸው። ሰው የፈለገው አቋም ሊኖረው ይችላል በሚዲያ ላይ የሚቀርብ ሲሆን ግን ቢያንስ የህሊና ተጠያቂነትን ግምት ውስጥ ያስገባ ሾል ቢሰራና አስተሳሰቡንም በዚሁ ቢቃኝ ጥሩ ነው። ምዕራባውያን ድሮ ለቅኝ ግዛት ሲመጡ እንስረቅ፣ እንግደል ብለው አልመጡም። ክርስትና እናስፋፋ፣ ጣዖት አምልኮና አረመኔነትን እናስወግድ፣ የባሪያ ንግድን እናጥፋ ወዘተ ነበር ያሉት። እዚህ ላይ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወርር የሰጠውን ምክንያት ለማወቅ ‘The Lion of Judah’ የሚለውን ጥናታዊ ፊልም ልጋብዝ።
ለነገሩ አቤ ባለስልጣናትን አስመልክቶ ለበጣ ይፅፋል ይናገራል፤ ይህን ሾለ እንግሊዟ ንግስት ማድረግ የሚቻል ይመስላችኋል? አቤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለእነሱ በሚገባ ጥሩ እንግሊዝኛ የዚህ ዓይነት ነገር መፃፍ ቢጀምር ከሁለትና ከሶስት መጣጥፍ አያልፍም። ቀልድ አይደለም ወቅቶችን ጠብቀው ንግስቲቱንና የቤተመንግስቱን ቡድን የሚቃዎሙ እንግሊዛውያንን ሰልፍ እየተከታተለ በጥሩ እንግሊዝኛ ቀጥተኛ ዘገባ ቢሰራበት መዘዝ ያለው መሆኑን መርሳት አይገባም። እኛ ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ እንደምንለው በእንግሊዝም “What happens in the Palace Remains in The Palace” የሚል መመሪያ አለ። በደም የጨቀየ ታሪክ ያለው ቤተመንግስት ነው ባኪንግሃም ፓላስ። ሾለ ዲያና አሟሟት የተሰራውን ፊልም እንውሰድ። ይህ ፊልም እንግሊዝ ውስጥ ለመታየት ከ80 በላይ ክፍሎች ተቆርጠው መውጣት አለባቸው ተብሎ ታግዷል። ልክ ነው ‘ዘ-ዲክታተር’ የተባለው ልብ-ወለድና በተራ ጭብጥ ላይ ተመርኩዞ የተሰራ ፊልም በአፍሪካና በዓረቡ ዓለም ሲከለከል ብዙ የተጮኸውን ያህል በዲያና ታሪክና በአሟሟቷ ላይ ብዙ መረጃዎችን አጭቆ የተሰራው እውነተኛ ፊልም በምድር እንግሊዝ እንዳይታይ ሲከለከል ሚዲያዎች ብዙ አልደሰኮሩም። ከዚህ ሌላ በቅርቡ ሰሞኑን ብዙ የተወራለት የኬቲ ፅንስ ምርመራ እየተካሄደለት በነበረበት ጊዜ ወደ ሆስፒታሉ ስልክ ተደውሎ ነበር፣ ይህን ተከትሎ ስልኩን ተቀብላ ነበር የተባለችና በዚያ የምትሰራ አንዲት ነርስ ሞታ ወይም ተገድላ መጠነኛ ውዝግብ ተከትሎ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳቀጥል ጭጭ ተብሎ ታልፏል- What happens in the Palace Remains in The Palace። ይህ ደግሞ ገና በፅንስነቱ ማስገደል ጀመረ ያሉ ግን አሉ።
አበበ ሆይ ይህን መሰል (የግብፅንና የመርሲን) ነገር ለሕዝብ የምታቀርብ ከሆነ ግራና ቀኝ ማየት አለብህ ብዬ አልመክርህም። ምክንያቱም ይህን አንተ አታጣውምና። በተጨማሪም የታላላቅ ሚዲያዎችን አሰራር ታውቀዋለህና። አበበ ገላው በዋሽንግተኑ የሬገን አዳራሽ የቃውሞውን ባወረደበት ወቅት በዚያ ወኪሉን (ሪፖርተሩን) ያልላከ የሚዲያ ድርጅት አልነበረም። የአበበ ጩኸት ለሁሉ ተሰምቶ ይሆን የሚል ጥርጣሬ የሚያጭርም አልነበረም። በዚያች ደቂቃ በዚያ አዳራሽ ሁሉም ነገር ሰአቶች ሳይቀሩ የቆሙ የሚያስመስል ተአምር ስለተፈጠረ በዚያ የተገኘ ሁሉ የአበበን ሾል ተግቶታል። “አቶ መለሾ ሆይ ንግግርዎ አይሰማም፣ ድምፅ ይጨምሩ” ያለ መስሎን ነው እንዳይሉ ደግሞ በጠራ እንግሊዝኛ ነው መልዕክቱን ያስተጋባው። በዚያ ቦታ በዚያች ዕለት እንግሊዝኛ ቋንቋ የማይሰማ ጋዜጠኛ ወይም ሪፖርተር የላካል ብሎ መገመት ጅልነት ነው የሚሆነው። ነገር ግን ይህ ነገር ዜና ላይ አልተሰማም። ቪኦኤን ጨምሮ በዝምታ ነው ያለፉት። ቪኦኤ ነገሩን የዘገበው ከአድማጮች ብዙ ኡኡታና ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ነው። በተቃራኒው የኢራኑን መሪ በአንድ የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ውስጥ አንድ ተማሪ ኢራን የግብረ ሰዶማውያንን መብት አታከበርም ብሎ ዘለፋ ሲሰነዝርባቸው ግን ሚዲያዎች እንዴት እየተቀባበሉ እንዳስተጋቡት እናስታውሰዋለን!!
የግብፅን ነገር ወይም የሙርሲን መውደቅ ብዙ ሰዎች ነገሩን የክርስቲያን-ሙስሊም ቁርቁስ አድርገው ያዩትና ሙርሲ እንኳን ሄደ ሲሉ ይሰማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ሙርሲና ደጋፊዎቹ ‘እስማለዊ’ ስለሚባሉ በጭፍን እስልምና ተጠቃ የሚሉ ወገኖች ይታያሉ። እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ?
የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች ለምንድን ነው የሙርሲን ደጋፊዎች ‘ኢስላሚስቶች’ የሚሏቸው?
ይህ ብቻ አይደለም አልሸባብ፣ ቦኮሃራም፣ የማሊ ተዋጊዎች ወዘተ ሲጠቀሱ ይህ ‘እስላማዊው’ የሚለው ቅጥያ ተዘውትሮ ጥቅም ላይ ይውላል። ቪኦኤ የአማርኛና የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ‘እስላማዊው’ ሲሉ ቪኦኤ ኦሮምኛ ደግሞ ‘ኢስላሙማ’ ሲል ይሰማል። የቸችኒያ፣ የሶርያ፣ እየኮሰመኑ የመጡት የኢራን መጂሃዲኖችና የመሳሰሉት የአሜሪካ ጠላት የሆኑ መንግስታትን ያጠቃሉ የሚባሉ ተዋጊዎች ሙስሊሞችና የእስልምናን መመሪያ አንግበው የሚዋጉ ቢሆንም ‘እስላማዊ’ ሲባሉ አይሰሙም። በአውሮፓና በአሜሪካ ለእስልምና ጥላቻን ማራመድ እየተስፋፋ ነው፤ ታዲያ ይህ ‘እስላማዊው’ ማለት ‘የምትጠሉት’ ወይም ‘መጠላት ያለበት’ እንደማለት ሆኖ እያገለገለ ነውን? በኡጋንዳ የጌታን ትዕዛዛት ለማስከበርና ይህን መሰረት ያደረገ መንግስት ለመመስረት እዋጋለሁ የሚለው ‘የጌታ ተፋላሚ ጦር (Lord’s Resistance Army- LRA) መኖሩ ይታወቃል። ለምን ይህንን ቡድን ‘ክርስቲያናዊው’ እያሉ ሲጠሩት አልተሰሙም?
እኔ ሙስሊም አይደሁም። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ለዘመናት አብረን የኖርን ወንድማማቾች ነንና አንዱ የውስጥ ወይም የውጭ አካል ለልሹ ይመቸው ዘንድ እኛን ሊያጫርስ የሚጭራትን ትንሽ እሳት ገና በእንጭጯ ለማጥፋት ንቁ መሆን እንዳለብን ይሰማኛል።
በመጨረሻም የሙርሲን አባባል ያጋነንከውና ልዩ ትርጉም የሰጠኸው ይመስለኛል። ይህን ያደረግከው ለአገርህ ብለህ ነው ወይስ ሙግትህን ለማጠናከር። አቶ ሙርሲ “ኢትዮጵያውንን እርስ በርስ እናበጣብጣታቸው ብለው ሲዶልቱ” ያልከው የኢትዮጵያን ተቀዋዋሚዎች በመርዳት የኢትዮጵያን መንግስት እናዳክመው ያሉትን ነው? እዚህ ላይ ምን እንደምልህ እንጃ! አንድ ታሪክ ግን ልንገርህ። ዚያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ፣ ከሸፈበት። ዚያድ ባሬ ያልተቋጨ የግዛት ጥያቄ አለውና ኢትዮጵያን እያዳከመ መቆየትና ሌላ ጦርነት ማካሄድ እንዳለበት ተሰማው። ሻዕቢያንና ወያኔን ማገዝ ጀመረ፣ አስታጠቀ፣ ፓስፖርት ሰጥቶ በፈለጉበት እየተንቀሳቀሱ የውጭ ሃይሎችን ድጋፍ እንዲያገኙና ደጋፊዎዎቻቸውን ማደራጀት ይችሉ ዘንድ ሀኔታዎችን አመቻቸ። በዚህ ግዙፍ እገዛ ዚያድ ባሬና ሶማሊያ ባይጠቀሙም ዚያድ ባሬ የረዳቸው በጣም እንደተጠቀሙ፣ ኢትዮጵያችን በእጅጉ እንደተጎዳች እያየን ነው። ይህ ጉዳት ይሽር ይሆን? “የጠላቴ ጠላት…” ሲባል ምን ማለት ነው?
የቪኦኤዋነ አዳነች ፍስሃዬ የሙርሲን ንግግር በዚህ መልኩ ደጋግማ አስተጋብታዋልች። ሙርሲ ሲወድቁም ለውድቀታቸው ድጋፍ የመሰለ ፕሮግራም ሰርታለች። ለኢትዮጵያ አስባ ነው ወይስ በአሜሪካ ሲገደፍ የነበረው የሙባረክ መውደቅ አሳስቧት ወይስ የአሜሪካ አሻንጉሊቶች የሆኑ አምባገነኖችን መገልበጥ አደጋ አለው የሚል ትምህርት ልትሰጠን ፈልጋ?
ቻው!!

አቶ መለሾ ዜናዊ ለትውልድና ለሀገራችን ጥለውት ያልፉት እኩይ፣ መራራና አሳዛኝ ሀቆች

ከፊሊጶስ

የአቶ መለሾ፣ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ግንኙነት ሁሌም ይደንቀኛል። በሀገርና በትውልድ ላይ የፈጸሙትንና
ጥለውት የሄዱትን ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሚትላልፍ መርዝ ሳስብ፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን የነበራቸውን
ጥላቻ ስቃኝ ፤ በ’ርግጥ የሰው አዕምሮ ተመራምሮ ይደርስብት ይሆን? እላለሁ። አሁንም ከኢትዮጵያና ከዚች ዓለም
ተለይተው ሄደው ግፋቸውን ሳስታውስ እጅግ አድርጎ ይገርመኛል ። ዘፋኙ ምን ነበር ያለው?……
’’….ግርም ያደርገኛል ያሰበኩት እንደሆን
ሰው በገዛ ሀገሩ ስደተኛ ሲሆን።….”
እስቲ ባለፉት አመታት አቶ መለስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ የሰሩትንና የፈጸሙትን መራራ ሀቆችና ለዚህ
ትውልድ ጥለውት ያለፉትን ታሪክ እጅግ ባጭር ባጭሩ (የውቅያኖስን ውሀ በጭልፋ ጨለፎ ለመጨረስ እንደመሞከር
ይቆጠራል።) እናስታውስ።
1ኛ/ አቶ መለሾ፣ኢትዮጵያና
ኢትዮጵያዊነታቸው፤
አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵም ሆነ
በኢትዮጵያዊነታቸው አያምኑም ነበር። ”ኢትዮጵያዊ
ነኝ” ወይም ”ኢትዮጵያ ሀገራችን” ወይም ”ሀገሬ”
ሲሉ ተሰምተው አያውቁም።
አቶ መለስ የድሮው ለገሰ ዜናዊ ሚያዚያ 30/1947
በኢትዮጵያ በትግራይ ክፍለ ሀገር በአደዋ ተወለዱ።
ገና ከጅምሩ አቶ መለስ ለኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን
አልታገሉም። የወላጆቻቸው ክፍለ ሀገር፤ “ኤርትሪያና
ትግራይ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛቶች ናቸውና።”
እሳቸውም በኢትዮጵያዊነታቸው አያምኑም ነበር።
ሕወሓትን እንደተቀላቀሉ፤ ላልተወሰነ ግዜ ጠፍተው
ወደ ኤርትራ፣ ወደ እናታቸው መንደር አዲቋላ ነበሩ። ከዚያም ተመልስው ለሕወሓትን እጅ ሰጡ። የሻአቢያን ትግል
ለመቀላቀል ፈልገው ግን ስላልተመቻቸላችው ወይስ ተቀባይነት ስላጡ? ይህ መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው። ትውልድ
እውነቱን እንዲያውቅ። (‘’ኤርትራ ከየት ወዴት” የሚለውን የራሳቸውን ድርሳን ይመልከቱ) ታዲያ ”ኢትዮጵያዊ
ያልሆኑና በኢትዮጵያ ቅኝ ተገዥ የሆኑት” አቶ መለሾ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመት የቻሉትን ያህል ከፋፍለውና አፈራርሰው
ገዙ። ሸጡ። በታሪካችንና በትውልድ ላይ ቀለዱ።
2ኛ/ አቶ መለሾ ሾለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ግንዛቤ፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ ያላትና በአጼ ምኒሊክ የተቆረቆረች ሀገር ናት ብለው የራሳቸውን የፈጠራ
ታሪክ ያምናሉ። ማመን ብቻ አይደለም፤ እምነታቸውን ባገኙት መድረክና አጋጣሚ ሁሉ ሌላውን ወገን፣ በተለይም
ለአፍሪካዊያንና ለምዕራባዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የበታችነትና የንቀት ስሜት እንዲያሳድሩ ከማስረዳትና ታሪክን
ከማዛባት ቦዘነው አያውቁም። ደጋፊዎቻቸውንም በዙ ድርሳናት እንዲደርሱ አድገዋል። የክህደትና የፈጠራ ታሪካቸውን
ለፓለቲካ ግባቸው ተጠቀሙበት። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ”ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላትና ታላቅ ሀገር ነች።” ለማለት
ሲከጅሉ ተሰምተዋል። ዋይ!…..ንሰሀ ሊገቡ አስበው ነበር ይሆን? ወይስ አዲሱ የፓለቲካ አክሮባት? ግን ተቀደሙ።
3ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ባንዲራ፤
አቶ መለሾ ለኢትዮጰያ ባንዲራ ያላቸው ጥላቻ እጅግ የከፋ ብቻ ሳይሆን “ከጨርቅ ጉዳይ የለንም!” በማለት
የራሳቸውን ባንዲራ ሰርተው፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳይፈልግ ”እንዲቀበል” አድርገውታል።
4ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ሠራዊት፤
አቶ መለስ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ጥላቻና ማን አለበኝነት ካሳዮበት መንገድ አንዱ በብዙ ድካምና
ወጭ ሲገነባ የኖረውን የኢትዮጵያን ሠራዊት በአንድ ጀምበር በመበታተንና በማፈራረስ የጎዳና ተዳዳሪ አደረጉት።
የባህርና የጦር መርከቦቻቸን ከፊሎቹን ለሻአቢያ ሰጡ፤ ሻአቢያ የማትፈልጋቸውን ደግሞ ለታሪካዊ ጥላቶቻችን ተሸጡ።
5ኛ/ አቶ መለሾ፣ የኢትዮጵያ ለዕልናና ዳር ድንበር፤
በ1983 አቶ መለሾ ከደርግ ጋር በሚደራደሩበት ወቅት፤ የሳቸው አሸናፊነተ ሲረጋገጥ፤ አሜሪካዊ አደራዳሪ ኸርማን
ኮኸን ለንደን ላይ ‘’የባህር በር ጉዳይ እንዴት ነው? መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል።’’ ሲሏቸው፤
የአቶ መለሾ መልስ “ሾለ ባህር በር ጉዳይ ከሻአቢያ ጋር እንነጋገርበታለን” ነበር ያሉት። እናም ታሪካዊ ጥላቶቻችን
ዘመናት ሙሉ ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት የማድረግ ህልም አቶ መለሾ እውን አደረጉላቸው። በእርግጥ አቶ መለሾ
ሌላም ዓላማ ነበራቸው። ኢትዮጵያን ከቻሉ አፈራርሰው፣ ካልቻሉ ደግሞ ደካማና የተከፋፈለ ህዝብ በመፍጠር፣
ታላቋን ትግራይን በመመስረት ከኤርትራ ጋር በመስማማት አሰብን የትግራይ ማድረግ ነበር። ይህን ህልማቸውን እውን
ሳያደርጉ አቶ መለሾ አለፉ። ግብረ-አበሮቻቸው ግን ”ትግላችን ይቀጥላል” በማልት ሲፎክሩ ይሰማሉ።
6ኛ/ አቶ መለስና የኤርትራ ተውኔት፤
ተውኔት-1፡ አቶ መለሾ “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች።” በማለት፤ ይህን ቋንቋ ሊገጸው፣አዕምሮ ሊያስበው
የሚከብደውን ዓይን አውጣ የክፍለ ዘመኑን የክህድት ታሪክ ለመስበክና ለማስተማር ያላቸውን ሀይል ሁሉ ተጠቀሙ።
በታሪክና በትውልድ ላይ አፌዙ።
ተውኔት-2፡ ”ኢትዮጵያዊያን ሾለ ኤርትራ ምንም የሚመለከታቸው ነገር የለም።” በማለት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ
የዳር ተመልካች ሆኖ ቀረ። ለሺ’ ዘመናት ሙሉ ሲከፈል የነበረው የደምና የአጥንት መሰዋዕትነት ትርጉም የሌለውና
”የትምህክተኞች” እንደነበር በመግለጽ፤ በጀግኖች ሙታን ወገኖቻችን ላይ ሲደነፉ ኖሩ።
ተውኔት-3፡ ‘’ነጻነት ወይም ባርነት’’ ለሚጠይቀው ህዝበ ውሳኔ ህጋዊ እውቅና በመስጠት ኢትዮጵያን የመበታተኑን
የጥላቶቻችንን ሴል ተገበሩ:: አቶ መለሾ በዚህም አድራጎታቸው በጣም ይመኩ ነበር።
ተውኔት-4: “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነበረች።” በማለት “ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነጻ መውጣቷን” ለተባበሩት
መንግሥታትና ለአፍሪካ አድነት ድርጅት ደበዳቤ በመጻፍ እውቅና እንዲሰጧት ተማጸኑ፤ አቶ መለሾ። ባለስልጣናቱ
ከዓለም ህግ አንጻር እንደማይቻል ሊያስረዷቸው ቢሞክሩ (ከቡትረስ ቡትረስ ጋሊ ውጭ፤ እሳቸው ያገራቸውን
የግብጽን ዓላማ ማስፍጸም ነበረባቸው።) ”ባገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ” አሏቸው።
ተውኔት-5: በኤርትራ ምድር ከአሁን በኋላ ጥይት አይጮህም። ወ.ዘ.ተ.
አቶ መለሾ ኤርትራ ከኢትዮጵያዊ እንድትገነጠል ሳይሆን ገንጥለዋል። አቶ ኢሳያስ አፈወርቂም የአቶ መለስን ያሀል
የደከሙ አይመስለኝም። አቶ መለሾ ኤርትራን ገንጥለውና አስገንጥለው ከጨረሱና ሁሉንም ካመቻቹ በኋላ፤ የኤርትራ
ተወላጅ ወገኖቻችን ኢትዮጵያን እንዲገዙ ይፈልጉ ነበር። (በእርግጥ ፍታዊ በሆነ መንገድ ከሆነ አቶ ኢሳያስም
የኢትዮጵያ መሪ ቢሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተኛ በሆነ። ችግራችን ከሚከተሉት ዓላማ እንጅ።) ለዚህም ሲሉ
በሻአቢያ የወርቅ ጥርሳቸውን ሳይቀር እየተወለቀ ለተባረሩት ዜጎች፤ ”ይህም ሲያንስ ነው፣ እንዲያውም ኢትዮጵያ ካሳ
መክፈል ነበረባት” ነበር ያሉት። እናም ቀጠሉ… ለሻቢያዎች ኢትዮጵያዊያኖችን የሚያስሩብት ከርቸሌ አዘጋጅተው
አሳሰሩ፣ አስገርፉ፣ አስገደሉ። ሻአቢያዎች የሀሰት ገንዘብ አሳትመው የፈለጉትን ነገር ሁሉ እንዲሸጡ፣ እንዲገዙ፣
እንዲለውጡና እንዲያግዙ ተደረገ። እናም ሻአቢያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ቡና ላኪ ሆኑ።
7ኛ/ መሬት ለሱዳንና ኢትዮጵያን መግዛት ለሚፈለጉ ሁሉ፤
አቶ መለሾ ኤርትራን ገንጥለውና አስገንጥለው ከወገኖቻችን ለያይተውን ብቻ አልቀሩም። ስልጣናቸው መደላደሉን
ሲያረጋግጡ፣ ሱዳኖች ጫካ በነበሩበት ወቅት ለዋሉላቸው ውለታና ተቀናቃኝ ጠላት ቢነሳባቸው አሳልፈው
እንዲሰጧቸው የኢትዮጵያዊያን ገበሬዎችን በማባረር የኢትዮጵያን ክቡር መሬት ቆርሰው በገጸ-በረከትነት አበረከቱ።
አቶ መለሾ በዚህ አላቆሙም….. የሀገሪቱን አንጡራ መሬትና ማዕድን ዜጋውን እያፈናቅሉ ለባዕዳንና ለታሪካዊ
ጠላቶቻችን ቸበቸቡ። እስከልተ ሞታቸው ድረስ እንግሊዝን የሚያክል ሀገር እንደሸጡ ይገምታል። አላማውም
ኢትዮጵያ ማፈራረስ ቀላሉ መንግድ በመሆኑ ነው።
8ኛ/ የአቶ መለስና ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤
አቶ መለሾ የስልጣን ኮርቻቸውን እንደተፈናጠጡ፣ አ’ዱና ዋና ሾል አድርገው የያዙት ኢትዮጵያዊ ስብእናና ለኢትዮጵያ
ክብርና አንድንት ሊታገሉ ይችላሉ ያሏቸውን ምሁራንን ከየትምህርት ትቋሞት አሳደዋል። አባረዋል። ገለዋል።
የትምህርት ተቋማቱንም ለሆዳቸው ባደሩ ሆድ አምላኪ ‘’ምሁራንን’’ ተኩበት። ዓላማቸውም ተጠራጣሪ፣
የማይትማምን፣ ለኢትዮጵያ አንድንትና ለክብሩ ብዙም የማይጨነቅ፣ እንደገዥዎቻችን በአፍቅሮ ንዋይ የታወረ፣
ገንዝብ (ሀብት) የሁሉም ነገር መጀመሪያና መጨረሻ ነው ብሎ የሚያምን ለውጭ አለም ማንነቱን ያስረከበ ትውልድ
ለማፍራት የታቀደ ነበር። ነውም።
9ኛ/ የአቶ መለሾ የዘር ጥላቻ፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ያፈራረሳል ብለው የተጠቀሙበትና ዋና መሳሪያ ያደረጉት ኢትዮጵያዊያንን
በተቻለ መጠን በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል፤ ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ ጥላቻንና ቂምን በማሰራጨት፤”የክልል
ይገባኛል” የርስ-በ’ርሾ እልቂት እንዲኖር ማድረግ ነው። ” ከወርቅ ዘር መወልዴ፣ ለወላይታው አክሱም ምኑ ነው፣
ወዘተ. የመሳሰሉትን አባባሎቻቸውን ስናሰብ፣ አቶ መለሾ የጥላቻና የበታችነት ስሜታቸውን ለመወጣት፤የኢትዮጵያን
የህዝብ እልቂት እንደማለዳ ጸሀይ ይናፍቁና ሌት ተቀን ይደክሙ ነበር።
10ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ሃይማኖት፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አዳክሞ ያፈራርሳታል ብለው ካምኑበት ውስጥ አንዱ በሃይማኖት ከፋፍሎ
እርስ በ’ርሾ ማናቆርና ማበጣብጥ ነው። በተለይም የኦርቶዶክሳዊያንን ዶግማ እምነት በማፈራረስ፤ ጳጳሱን በማባረር
ከራሳቸው መንደር የሚወልዱ “ጳጳስ” አስቀመጡ። ቤተክርስቲያንን ለሁለት ከፈሉ። እስልምናንም ከክርስቲያኑ ጋር
ማበጣበጡ እንደፈለጉት አልሆን ሲል እርስ-በርስ ለማነካከስ ብዙ ጥረዋል። ሞት ቀደማቸው እንጅ።
11ኛ/ የአቶ መለሾ ሰባአዊ ‘ረገጣዎች፤
አቶ መለሾ ገና ጫካ እያሉ ከ’ርሳቸው የተለየ ሀሳብ ያራምዳሉ ወይም ያስባሉ ብለው የጠርጠሯቸውን፤ በተለይ ደግሞ
ኢትዮጵያዊነትን በሚያንጸባርቁና ትግላችን የመደብ ትግል ነው በሚሉ ታጋዮችን ያለ ‘ርኅራሄ ‘ረሽነዋል።
አስረሽነዋል።
መሀል ሀገር ከገቡም በኋላ በተለያዮ የሀገሪቱ ክፍሎች ዜጎች በቀለማቸው፣ በቋንቋቸውና በአመለካከታቸው ብቻ
ከገደል ከነ ነፍሳቸው ተወርውረዋል። ቤታቸው ተዝግቶባቸው እንዲቃጠሉ ተደርጒል። ተረሽነዋል። ተሳደዋል።
ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ በጥይት ተደብድበዋል። ታስረው ተገርፈዋል። ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ስደተኛና እንደሁለትኛ ዜጋ
ተቆጥረዋል።
አቶ መለስ ከወዳጃቸው ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂም ጋር በኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት አዘራረፋ ላይ አለመስማማት
ሲፈጠር “አማራ ለያይቶን እንጅ፤ እኛ እኮ በአንድ ሳንባ መተንፈስ የምንችል አንድ ህዝቦች ነን!” እንዳልተባለ
ሁሉ፤በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ማግደው አቃጠሉ። ብዙ ዜጎችንም ተወልደው ካደጉበትና በስጋም በነፍስም
ከተሳሰሩበት ወገናቸው ለይተው አባረሩ።
ለአሜሪካ ተላለኪ በመሆንም በሱማሊያ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ሬሳቸው በመቋድሾ
ጎዳናወች እንዲጎተትና የዓለም መሳለቂያ በማድረግ ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ ጥላቻና ቂም በቀል ዘሩልን።
12ኛ/አቶ መለሾ፣ የሀገር ሀብትና ሙስና፤
በአጠቃላይ ማለት ይቻላል፤ የሀገሪቱ ሀብት በሳቸው አካባቢ ባሉ ሰዎች፣ ለስልጣናቸው ታማኝና ለኢትዮጵያን
ኢትዮጵያዊያን ደንታ በሌላቸው ባባእዳን የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ ዜጎች እጅ እንዲገባ አደረጉ። ሀገሪቱን የግል
ሀብታቸውና ንብረታቸው በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆነ። ከፊሉ ተሰደደ። ከፊሉንም በርሀ፣
ባህርና ውቅያኖስ በላው። ወጣት እህቶቻችን ለዝሙትና ለአረብ ግርድና አደሩ። አንዳንዶቹም እራሳቸውን አጠፋ።
በፈላ ውህ ተቀቀሉ። ህጻናት ለስዶማዊያን ሳይቀር በጉዲፈቻ ተቸበቸቡ። ኢትዮጵያዊ ከዓለም ዜጋ ሁሉ የተጠላና
የተዋረደ ሆነ።
አቶ መለስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያን ከምድረ-ገጽ መጥፋት ከሚፈልጉ ምእራባዊ አጋሮቻቸው ቢያንስ በአመት 4
ቢልዮን ዶላር ያገኙ ነበር። ግን ለሀገሪቱ ልማት የዋለው 14% ብቻ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት አረጋግጦላቸዋል።
ቀሪው ግን የአቶ መለስንና የመሰሎቻቸውን ካዝና እያጣበበ፣ኢትዮጵያኖችን ግን እያራቆተ ነው። ከ11.4 ቢሊዎን
ዶላር በላይ በውጭ ሀገር ባንኮች አስቀምጠዋል። በቀርቡ ደግሞ ገዥዎቻችን በያዝነው ዓመት ብቻ ከ3 ቢሊዎን ዶላር
በላይ ከሀገር አሽሽተዋል። እንገዲህ ይህ ጸሀይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ነው። በድብቅ፣ በቤተሰብ ስምና በንግድ ስም
21 ዓምት ሙሉ የተዘረፈውን እሱ ይቁጠረው። ሙስናማ በአቶ መለሾ ዘመን አዲሱ ባህላችን አድርገውልናል።
13ኛ/ አቶ መለስና ፍትህ፤
የአቶ መለሾ ፍርድ ቤቶች አስቂኝና አሳዛኝ ቲያትር ቤቶች ናቸው። የፈለጉትን ሰው በፈለጉት መንገድ በአንድ ቀን
ውስጥም ቢሆን ህግ አርቅቀው የማሰር፣ የመወንጀል፣ የመግደልና የመፍረድ መብት በእጃቸው መዳፍ ውስጥ ነው።
በአሁኑ ወቅት ብዙ ዜጎች በእስር ቤት በፍትህ እጦት ይሰቃያሉ።
14ኛ አቶ መለሾ፣ ተሳዳቢነትና ውሸታምነት፤
አቶ መለሾ የበታችነት ስሜታቸው ሲገነፍልባቸውና የተደፈሩ ሲመስላቸው፤ አንድ አዕምሮው የተነካ ሰው እንኳን
ቢናገረው ሊቀፈን የሚችል የስድብና የንቅት ቃላቶችን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከመለደፍ ቦዝነው አያውቁም ነበር።
ውሸታምነታቸው ግን አገርን ሲያፈርስና ህዝብን ሲያበጣብጥ ከመኖሩ አልፎ፤ ተከታዮቻቸው ሞታቸውን እንኳን
ሲዋሹን ከርመዋል።
ማጠቃለያ፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስና የማጥፋት ተግባራቸውን እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስ
ሰርተው በጽናት አልፈዋል። ስለዚህም ተከታዮቻቸው ‘’ሳያርፍ ያረፈው መለሾ” ቢሏቸውና ሌላም ሌላም የመወድስ
ስም ቢያወጡላቸው ያንሳቸዋል እንጅ አይበዛባቸውም። በእርግጥ አላማ አድርገው የተነሱበትን ሙሉ በሙሉ
አላሳኩም። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ዜጋ አሁንም አለና። እንዲያውም ይህ ትውልድ አቶ መለስና ባልደረቦቻቸው
ለፈጸሙብን ግፍና በደል፤በኢትዮጵያዊነታችን ላይ ላደረሱብን ውርደትና ከፋፍልህ ግዛው የበለጠ ግንዛቤ እያገኘን
መ’ተናል።
-4-
አዎ…አቶ መለሾ ላይመለሱ ሄደዋል። ነገር ግን ላለፉት ዓመታት የደከሙበትና የለፉበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የስደት፣
የክህደትና የሙስና በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስና የማጥፋት ዓላማቸውን ለተከታዮቻቸው
ጥለው አልፈዋል። አዲሱ ገዥዎቻችን ደግሞ የአቶ መለስን ዓላማ ተከትለው እስከመጨረሻው እንደሚጓዙ አበክረው
ገልጸውልናል። ታዲያ እኛስ አሁንም እንዳለፈው በዚሁ በተገዥነት ጉዞ እንቀጥላለን? ወይስ ካለፈው ተምረን፣ አዲስ
የትግል ስልት ቀይሰን ኢትዮጵያን ከመፈራረስ አድነን፣ ሁሉም ዜጎቿ በፍትህና በእኩልነት የሚኖሩባት የሁላችን ሀገር
እገነባለን? ጥያቄውና ጠሪው ለሁላችንም ነው።
——————-//——————
ፊልጶስ / ጳጉሜ 3/2004 ኢ-ሜል፡philiposmw@gmail.com
(በዚህ አጋጣሚ ይህችን የመለስን ምግባር እንድጽፍ ሀሳቡን ላቀረብክልኝና ለገፈፋህኝ ለያደቴ ሙሉጌታ የከበረ
ምስጋና ይድረስህ።)

ኢህአዴግ ደንግጧል!! በአዲስ አበባ የአንድነት አባላትን ማሰር ተጀምሯል

Image
በአዲስ አበባ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት የበተነ የአንድነት አባል በአደራ ታሰረ፡፡


አንድነት ፓርቲ ‹‹á‹¨áˆšáˆŠá‹ŽáŠ–ች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መንግስት የማደናቀፍ ተግባሩን በአዲስ አበባም ጀምሯል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ሙሉጌታ ተፈሪ የተባለውን የአንድነት ፓርቲ የወረዳ 15 አባል ካዛንችስ አካባቢ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስሯል፡፡... ሙሉጌታ ካዛንችስ አካባቢ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጭ መታሰሩን ፖሊስ ተናግሯል፡፡

የአባሉን መታሰር የሰሙት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ ግርማ ሰይፉና አቶ በላይ ፍቃዱ ካዛንችስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው ሙሉጌታ በህገወጥ መንገድ መታሰሩን በማስረዳት ተከራክረዋል፡፡ የጣቢያው ፖሊሶች ግን “ሙሉጌታን ያሰረው ፖሊስ ስለሌለ እሱ ሳይመጣ አይፈታም” በማለት “የአደራ እስር” ከጎንደር በተጨማሪ በአዲስ አበባም መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ አመራሮቹም “እኛም ወረቀቱን እየበተንን በመሆኑ እሰሩን” በማለት ተሟግተዋል፡፡

ዘግይቶ በደረሰን ዜና የአንድነት አመራሮች የታሳሪውን ጉዳይ መከታተላቸውን ተከትሎ ሙሉጌታ ተፈሪ ክቤ በተባለች ፖሊስ “ተመርምሮ” ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሊወሰድ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን አባላት ዛሬ ጠዋት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ህዝባዊ ንቅናቄውን በአዲስ አበባ ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮ ተቀብለው ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ100ሺ በላይ የሆነ በራሪ ወረቀትም በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ ፍ ኖተ ነፃነት

Total Pageviews

Translate