Pages

Oct 13, 2013

እስክንድር ነጋ በአራት ጎብኚዎች ብቻ እንዲጎበኝ ተደረገ

ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡
የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን ጠያቂዎች ቁጥር በአራት መወሰኑ ታውቋል፡፡
ህገ መንግስቱ በግልጽ እስረኞች በወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሊጠይቋቸው በሚፈልጓቸው ሰዎች መጎብኘት እንደሚገባቸው ቢደነግግም የቃሊቲው መንግስት ግን ህገ መንግስታዊውን ድንጋጌ በመጣስ በማን አለብኝነት የእስክንድር ጠያቂዎችን በዝቅተኛ ቁጥር ገድቧል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ምንጮች እስረኞች ጥፋት ሲፈጽሙ እንዲህ አይነት ህግ ለተወሰነ ግዜ እንደሚወጣባቸው በማስታወስ በእነ እስክንድር ላይ የተላለፈው ውሳኔ ግን ‹‹ጥፋት መፈጸማቸው ሳይነገራቸው ፣ፈጸሙት ለተባለው ጥፋትም ቀርበው መከራከሪያ ሳያቀርቡ መሆኑ ውሳኔውን ፖለቲካዊ ያደርገዋል››ብለዋል፡፡
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተመሳሳይ መልኩ ከጥቂት ሰዎች ውጪ እንደማትጎበኝ እርሷን ለመጠየቅ የሚፈቀድላቸው ሰዎችም ለአስር ደቂቃ ብቻ እንደሚያገኟት ከዚህ ቀደም መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል:: MUST READ !!!

"አገሪቱ በልማት ጎዳና ላይ እየነጎደች ...." ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በትእዛዝ የካዱት
"የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል::" ሪፖርተር ርእስ አንቀጽ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ሪፖርተር መግለጫ ግጭት #1 ምንሊክ ሳልሳዊ

ኖሚናል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባሉት እና በህገመንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን በትእዛዝ ብቻ የሚሰሩበት ምንም አይነት አገራዊ ፋይዳ የማያደርጉት ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሕወሓት ታማኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ያሰፈረው ርእስ አንቀጽ የሃገሪቷ ላይ የሰፈነው አብዮታዊ ዲሞክራሲ አምባገነንነት እያደረሰ ያለውን ችግር እና መጪውን አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገሪቱ ምንም አይነት ችግር እንዳሌለ እና ሁሉም ነገር በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለ በዲሞክራሲ እና በልማት እየነጎድን ህዝባዊ ድሎችን እየተጎናጸፍን ..ምናምን...የሚሉ እና ሃሰትን የተሞሉ የማደናገሪያ እና የማስፈራሪያ ቃላት ፍርሃት በሚነበብበት ፊታቸው እያስገመገሙ ደስኩረዋል:: የእርሳቸው ንግግር እንደተጠበቀ የሕወሓት ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ እንዲህ ብሎናል::የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳ እና የሚከተለውን የሪፖርተር ወቀሳ ይመዝኑት::ሪፖርተር እንደውስጥ አዋቂነቱ ያየውን እና የታዘበውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ግን በትእዛዝ የካዱት እኛ ደሞ ያነበብነውን የተከፋፈልነው የታዘብነውን እንደራሳችን እይታ እንደሚከተው በዝርዝር ለማየት እንፈቅዳለን::

ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሌለ እና እንደሚያስፈልግ በግልጽ አስቀምቷል:: የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰየሙ ምንም ችግርና ብጥብጥ እንዳልነበር ይህ ማለት መሪ አልተተካም ሳይሆን ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ መንግሥትና አመራር ስላሌለ አገራችን ያያስፈልጋል እያልን ዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ እኛንም እየጐዳን ነው፡፡ ትላልቅና በርካታ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሲደረጉ በደመነፍስ ባጀት ተመድቦ ከፍተኛ ፋይናንስ ሳይኖር ወደ ላማት ይገባል ፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበረ የሃይማኖት ግጭትና ልዩነት እየታየ ነው፡፡ ችግሩ ካልተፈታ አስጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹና የማይመኙ ጠላቶች በእጅጉ እየተፈታተኑን ናቸው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥትና ጠንካራ አመራር የግድ ይላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ተንካራ መንግስት እና አመራር እንደሌለ በግልጽ ሪፖርተር አስቀምጧል::

ገዥው ፓርቲ እርስ በኤርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሓዴግ አራት ድርጅቶችን አክፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከልመራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ቃላቶች ተክቶ አቅርቦታል::


የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ጋዜጣ ሪፖርተር ግጭት === #2 ምንሊክ ሳልሳዊ
 
-ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር
-ሙሰኞችን ማደን - ‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል
-የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡

ገዥው ፓርቲ እርስ በእርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሕኣዴግ አራት ድርጅቶችን አቅፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል መራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን በሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ተክቶ አቅርቦታል::

ሙስናው በስፋት ተንሰራፍቷል ያልው የሪፖርተር ጋዜጣ "አገር በሙስና እየተጨማለቀች ናት" ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናገሩት በተቃራኒ ጎኑ መጭውን አደገኛ የሃገር ኢኮኖሚ የዳግም ስርኣተቀብር ሙስናው እያሳየን መሆኑን ጠቁሟል:: ሙስናን ለመዋጋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የውስጥ የፖለቲካ ባላንጣዎችን ለማፈን እና ለማስወገድ የእጅ አዙር መጥረቢያነት ከማገልገል ውጭ ምንም አይነት እርምጃ በሙሰኞች ላይ ሲወሰድ አልታየም ይባስ ሙስና በሃገሪቱ እየተስፋፋ እና እያበበ ነው::‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል እንደሆነ ይጠቁማል::ሙስና ኢትዮጵያን እያጨማለቀ ሲሆን ከስርቆትና ከዝርፊያ በፊት ሙስናን የሚያስቆሙና የሚያጋልጡ አሠራሮች፣ ሕጐች፣ መዋቅሮችና የሥነ ምግባር ደንቦች እንዳይወጡ የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት ሁነዋል::የመንግስት ባለስልጣናት በራሳቸው ለሙስና የሚያመች ሁኔታ እየፈጠሩ ሙስናን እንዋጋለን ማለት አያስኬድም፡፡ ከአሿሿም ጀምሮ፣ ከቁጥጥር ጀምሮ፣ ከቅጥር ጀምሮ አሠራሩ ሁሉ ሙስናን የሚያስወግድ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነትን የጠበቀ ነው፡፡

አገሪቷ በሙስና መጨማለቋ የመልካም አስተዳደር እጦት ፈጥሯል:: ጠቅላያችን እንዳሉን ማንጫውንም ነገር መልካም አስተዳደርን ጨምሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸው እና በሂደት እየተሻሻሉ እንደሚሄዱ ነግረውናል ይህ ነገር ላለፉት 22 አመታት ሲነገረን የነበረ እና ምንም አይነት ለውጥ ከማየት ይልቅ በካድሬዎች ብልሹ አሰራር እና ቢሮክራሲ የመልካም አስተዳደሩ እየተበላሸ ገደል መግባቱን ብቻ ነው::የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝቡን ተስፋ እያስቆረጠ ነው ብሎናል ለገዢው ፓርቲ ቅርብ የሆነው ሪፖርተር- አዎን ገዥው ፓርቲ መልካም አስተዳደር አለመኖሩን እያመነ ነው፡፡ ዕርምጃም እወስዳለሁ ቢባልም ለስልጣኑ ማራዘሚያ የሚጠቀምባቸው በጥቅም የተተበተቡ ካድሬዎቹ ይገለበጡብኛል በሚል ፍራቻ ምንም አይነት ርምጃ ሳይወስድ የመልካም አስተዳደር እጦቱ እንደቀጠለ ነው ፡፡

መልካም አስተዳደር ይኑር ይስፋፋም የሚሉ የመንግስት ሚዲያዎችም ይሁኑ ፕሮፓጋንዲስቶች ቃላቶችን ህዝብን ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ በቃላት ላይ ችግር የለም፡፡ በተግባር ግን መልካም አስተዳደር እውን ሊሆን አልቻለም፡፡ የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡ ሕገ መንግሥቱና የተለያዩ ሕጎች ተግባር ላይ የሚያውላቸው አጥተዋል፡፡ የሙስና ተጠርጣሪዎች ታሰሩ ቢባልም ፈጥረውታል የተባለው በደል ግን ሲስተካከል አይታይም፡፡ ይህ ችግር በእጅጉ አደገኛ ነው፡፡ ዜጋ አገሩን እንዲጠላና ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገ ያለ ችግር ነው፡፡ 


#3 ምንሊክ ሳልሳዊ 
በአንድ አገር ላይ ሁለት አገር የለም ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለ የትኛው አገር መግለጫ እንደሰጡን አሁንም አልገባንም::ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ የታዘብኩት ያየሁት የሰማሁት በሚል አበይት ብሎ ያለውን የሃገርቱን እውነታዎች በከፊት አስቀምጧል:: በርግጥ የተሸፋፈነ ቢሆንም ፍንጭ ግን አገሪቷ አደጋ ላይ እንዳለች ጋዜጣው መስክሯል:: እኛም ያየነውን የምናውቀውን ጤቅላይ ሚኒስትሩን እና ጋዜጣውን ይዘን ተንትነናል ::

የሃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ እና የሪፖርተር ጋዜጣ ግጭት
- የመንግስት የጥንቃቄ ጉድለት እና የፖለቲካ አጀንዳ ሃይማኖቶችን እየበረዘ ነው:;
- የኢኮኖምው ድቀት አገ

ሪቷን ወደማትወጣበት አደጋ ውስጥ የከተተ ሲሆን ከፍተኛ ስራ አጥነት ፈጥሯል::
- በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው::

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የድርጅታቸው የበላይ አካሎች በሰጧቸው ኦረንቴሽን መሰረት አጥንተው ገብተው በሃገሪቱ የተከሰቱ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን እና መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን በተለመደው አሸባሪ አክራሪ እና ጽንፈኛ በሚሉ ወያኔያዊ ቃላት ተጠቅመው ሲያስፈራሩ ... ይህን መሰል የመንግስት ማስፈራሪያ በህዝቦች መብት ላይ መስጠት በሃገሪቱ ያሉ ሃይማኖቶች ነጻነታቸውን መጋፋት ሲሆን ዋናው የችግሩ ፈጣሪ ወያኔ የፈጠረው የስልጣን ማስረዘሚያ የወንጀል ቃላቶች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል :: ሃይማኖቶች በመርሃቸውም ይሁን በተግባራቸው አይጋጩም፡፡ ሁሉም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ችግሩ ያለው እምነት ላይ አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው የዚህ ሃይማኖት ጠበቃና አለኝታ እኔ ብቻ ነኝ፣ አንተ ወይም ያኛው አይደለም በሚል ሃይማኖትን ተገን በማድረግ በሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስለዚህ የችግሩ መንሴ የሆነው ወያኔ የሃይማኖቶ ጠበቃ በመምሰል በህገመንግስት ንግድ ውስጥ ተጀቡኖ እጁን ወደ ሃይማኖቶች በማስገባት ራሱን የሃይማኖት አለኝታ በማስመሰል ሃይማኖቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉ የህዝብ ጥያቄዎች በአደባባይ መሰማት ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል::
የክርስትና፣ የእስልምናና የአይሁድ እምነቶች በጋራ በሚኖሩበት አገር ውስጥ፣ ጋብቻ ፈጽመውና ተፋቅረው መኖር የሚችሉ የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች ያሉበት አገር አለን እያልን፣ የወያኔ መንግስት በፈጠረው የፕሮፓጋንዳ እና የከፋፍለህ ግዛ ድርጊት ተጋጨ፣ ጠንካራ የነበረን ሕዝብ ተፋጀ ወደሚል አሳፋሪ ታሪክ እየቀየርነው ነው፡፡ ወያኔ ለስልጣን ማስረዘሚያ ብሎ የተጤቀመበት ስልት ነገ ለቁጭት የሚዳርገን እና ወደማንወጣበት ውድቀት የሚከተን ሲሆን ታሪካችንን፣ ማንነታችንና ደኅንነታችንን ለአደጋ እያጋለጠ ነው::

የሃገሪቷ ኢኮኖሚ በወያኔ ባለስልታናት እና በብሄራዊ ጥቅም በታወሩ ምእራባውያን እንደሚወራል ሳዮን እጅግ በጣም እየተንኮታኮተ መሆኑ እሙን ነው::በመንግስት ካዝና ውስጥ ከባድ የሆነ የገንዘብ ችግር አለ:: የመንግስት ካዝና ባዶ ነው ቢባል የሚያስኬድበት ደረጃ ላይ ተኩኖ የሃገሪቷን በጀት ማጽደቅ እንደት እንደሚቻል ግራ እየገባን ነው:: በጀት ሲጸድቅ እንጂ ሲለቀቅ የማይታይባት ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እየዳከረች ነው:: የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ከጥቂት ነጋዴዎች እና ብሄርተኞች ጋር በሙስና ተጨማልቀው የሚሰሩት የአየር በአየር ንግድ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ አይደለም የመንደር ኢኮኖሚ ሊባይ አይችልም::ክፍያ አፈጻጸም ላይ እንኳን ግለሰብ መንግሥትም እየተቸገረ ነው፡፡ የግል ባንኮች እየተዳከሙ ናቸው፡፡ የብድርና የውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት አለ፡፡ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚወሰደው ዕርምጃ የራሱን ችግር እየስከተለ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ፣ የውኃ መጥፋት፣ የኔትወርክ አለመኖር፣ በሁሉም ዘርፍ ችግር እያስከተለ ነው፡፡ ገንዘብ ማሸሽና መደበቅ እየታየ ነው፡፡ ሌባው ሲፈራ ባይገርምም፣ ንፁኃን ሲሸማቀቁና ብታሰርስ እያሉ በመፍራት ከቢዝነስ እንቅስቃሴ ሲቆጠቡ እየታየ ነው፡ ይህንን ወያንኤ አምኖ ሊቀበለው አይደለም ጭራሽ በጠላይ ሚኒስትር ደረጃ መካድ ተጀምሯል:: ከሕዝብ ብዛትና ከሚመረቁ ተማሪዎች አንፃር በቂ የሥራ ዕድል አልተፈጠረም፡፡ ሥራ ለማግኘት ወደ ዓረብ አገሮች የሚደረገው ስደት በአስፈሪ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ወደ ወንጀል እየተገባ ነው፡፡ ለባለ ገንዘብ ራስን ለሽያጭ ማቅረብ እየተስተዋለ ነው፡፡ ይህ ችግር ካልተፈታ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ያሰጋል፡፡ ልዩ ትኩረትና መፍትሔ ይደረግበት፡፡ የተራበ ሆድ አደገኛ ነውና፡፡

በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው:: በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ችግሮች ኢትዮጵያዊያን ሊፈቱዋቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ በመንግሥትና በሕዝብ፣ በመንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ፣ በመንግሥትና በሲቪል ማኅበረሰቡ፣ በመንግሥትና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች መካከል መቀራረብ፣ መወያየትና መመካከር ስለሌለ በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮች እየተባባሱ ናቸው፡፡ ችግሮችን ለመንግሥት ማቅረብ አልተቻለም፡፡ መንግሥትም የሕዝብን ችግርና ስሜት ማወቅ አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ቀላል ችግሮች እየተካበዱና ወደማያስፈልግ አቅጣጫ እየተሸጋገሩ ናቸው፡፡ መንግሥት በአስቸኳይ ቲንክ ታንክ ያቅድ፣ የጋራ መድረክ ይፍጠር፣ የሕዝብና የመንግሥት፣ የመንግሥትና የባለሙያዎችን ግንኙነት ያጠናክር፡፡ 

   ምንሊክ ሳልሳዊ

 

Oct 12, 2013

Africa vs ICC: Quotes on court before Kenya trial

By JASON STRAZIUSO and TOM ODULA
The Associated Press

FILE - In this Thursday, Jan. 3, 2008 file photo, a young girl cries as she is carried by a man and woman fleeing an area of wooden kiosks which was set on fire by supporters of Raila Odinga's party, the Orange Democratic Movement (ODM), during post-election violence in the Kibera slum area of Nairobi, Kenya. Kenya's foreign minister Amina Mohamed said at a news conference Wednesday, Oct. 9, 2013 that no sitting president in the world has had to appear before a court, a statement that comes as Kenya appears to be laying the groundwork to avoid having President Uhuru Kenyatta appear at the International Criminal Court next month. BEN CURTIS, FILE — AP Photo Read more here: http://www.adn.com/2013/10/10/3119796/africa-vs-icc-quotes-on-court.html#storylink=cpyFILE – In this Thursday, Jan. 3, 2008 file photo, a young girl cries as she is carried by a man and woman fleeing an area of wooden kiosks which was set on fire by supporters of Raila Odinga’s party, the Orange Democratic Movement (ODM), during post-election violence in the Kibera slum area of Nairobi, Kenya. Kenya’s foreign minister Amina Mohamed said at a news conference Wednesday, Oct. 9, 2013 that no sitting president in the world has had to appear before a court, a statement that comes as Kenya appears to be laying the groundwork to avoid having President Uhuru Kenyatta appear at the International Criminal Court next month.
BEN CURTIS, FILE — AP Photo
ADDIS ABABA, ETHIOPIA â€” Foreign ministers from around Africa on Friday meet at the African Union headquarters in Ethiopia to discuss Africa’s relationship with the International Criminal Court.
The meeting comes a month before Kenyan President Uhuru Kenyatta is scheduled to appear in The Hague, Netherlands court to answer charges of crimes against humanity for his alleged role in Kenya’s 2007-08 post-election violence that killed more than 1,000 people.
Kenya’s parliament, in a nonbinding resolution, voted last month to pull out of the treaty that created the ICC, amid indications Kenyatta may not show up in The Hague for his November court case. Kenya has petitioned the court for Kenyatta to appear by video link.
There is growing criticism inside Africa that the ICC has only prosecuted Africans. On Saturday African heads of state and government meet on the ICC issue. Below are different views on Africa’s relationship to the ICC and Kenyatta’s judicial dilemma.
—
— “Why should the Kenyan flag be dragged into the court? Kenyatta should not leave the country. If the president goes to the ICC it’s like the whole country is being prosecuted. … Kenyatta wants to go but his advisers are telling him not to go.” — James Gakuya, Kenyan member of parliament from Kenyatta’s political party.
— “Needless to say, the work and functioning of the ICC should not be beyond scrutiny and improvement. However, considerations of withdrawal risk grave consequences for civilians in Africa, who tend to bear the brunt of serious crimes committed in violation of international law.” — Statement by 130 African and international civil society organizations.
— “Instead of promoting justice and reconciliation and contributing to peace and stability, (the ICC) has degenerated into a political instrument targeting Africa and Africans. This is totally unacceptable and that is why Africa has been expressing its serious reservation against the ICC.” — Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, in his role as chairman of African Union, as told to the U.N. General Assembly last month.
— “He has cooperated fully with the court up until now. … Are the circumstances different? Absolutely. Totally. Completely different. Before he wasn’t the head of state of the republic. … It’s going to be the first time that a sitting head is brought before any court of any time, not just here but anywhere in the world.” — Kenyan Foreign Minister Amina Mohamed, speaking on Wednesday.
— “He won’t go.” David M. Crane, professor at Syracuse University College of Law, on whether Kenyatta will report to the ICC.
— “Whatever its merits as an institution of international law, the ICC is apparently tone deaf to growing public perception in Africa … that the tribunal has it out for Africans, given that all eight of its current investigations involve Africans. … Nevertheless, I doubt that President Kenyatta will blow off the ICC entirely; that would be overplaying his hand.” — J. Peter Pham, director of the Africa Center at the Atlantic Council.
— “This trial could well sound the death knell for the ICC. … Kenya is a fully functioning democracy, more than capable of prosecuting violators of its laws. Not only have no charges been brought against Kenyatta and Ruto in Kenya, they were recently elected in a free and fair election to run the country. That should be the only verdict that matters.” — Charles Stith, director of Boston University’s African Presidential Center, former U.S. ambassador to Tanzania.
— “Impunity for politically-motivated violence has been the norm in Kenya for far too long and, so far, the Kenyan authorities have failed to undertake any domestic accountability process to address the crimes committed during the post-election violence that rocked the country in late 2007 and early 2008.” Statement by No Peace Without Justice, a group promoting human rights and international justice.

MIGRANT BOAT SINKS 10 DEAD, EXCEPT 200IN

A ship carrying about 250 people capsized Friday off the coast of Sicily, according to the Maltese military and the Italian news agency ANSA.
The ship is believed to have been carrying migrants.
The incident occurred in international waters about 60 nautical miles south of Lampedusa, Italy, according to a posting on the Armed Forces of Malta Facebook page.
Malta's military Rescue Coordination Centre has assumed control of what it called a "major search and rescue incident," according to the Facebook posting.
According to the Maltese military, the ship was being followed by military chase planes and "appeared unstable."
"A few minutes later, the aircraft reported that the boat had capsized and that numerous persons were in the water. Initial assistance was provided by the aircraft, which dropped a life raft in close proximity of the persons in distress," according to the Facebook posting.
The fate of those aboard the capsized ship was not immediately clear.
It is the second such incident this month in the region.
Earlier this week, a boat carrying more than 500 African migrants sank off the coast of Lampedusa, killing 309 people in what Lampedusa Mayor Giusi Nicolini called "the biggest sea tragedy in the Mediterranean Sea since World War II."
That ship originated in Libya, caught fire off the Italian coast and sank.
Survivors, many of them from Eritrea, told CNN they used bodies to keep themselves afloat until they were rescued.
The incident sparked calls for efforts to reform migration policies in the region.
A week ago Friday, the United Nations' human rights office urged the European Union to work to prevent another such incident.
The agency called on authorities to work to reduce migrant trafficking and address economic and security issues that have driven thousands of African residents to make the risky voyage to Europe in search of a better life.

MIGRANT BOAT SINKS 10 DEAD, EXCEPT 200IN
In the Strait of Sicily, a boat full of migrants sank. On board were about 250 people. At least a dozen dead, as confirmation that the Navy with ships and helicopters took part in the rescue. The survivors rescued so far are 200, about 150soccorsi by Maltese vessels and about 50 from Italian means, including ten children.
The tragedy occurred in Maltese waters, on the border with Libya, 70 miles from Lampedusa, where a week ago died 339 refugees.

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።
ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።
እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።
ሌላው ኃይለማሪያም የሚናገረዉ ቃል ጠፍቶት በተደጋጋሚ ሲንተባተብ የታየዉ በሽብርተኝነት አካባቢ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ ነዉ። በእኛ እይታ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋነኛው አገር በቀል አሸባሪ ህወሃት እና ህውሃት ብቻ ነው። ህወሃት ስልጣን ላይ ያቆየኛል ብሎ ከገመተ የማይመሰርተው የክስ ዓይነት፤ የማያፈሰው የንጹህ ሰው ደም ፤የማያፈነዳው የቦንብ እና የፈንጂ ዓይነት እንደሌለ ከሃውዜን እስከ አዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ቋሚ ምስክሮች ናቸው። ይህንን እኩይ ተግባሩን ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው በዊክ-ሊክ ላይ የወጣው መረጃም አሳይቷል።
የህውሃት ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሠላማዊ ትግሉን ለማፈን ከፈለገ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰቡትን ዜጎች ከሌላ ከማንም ጋር ማነካካት አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሁሉ አንደ ኃይለማሪያም ሞቶ የተቀበረን ሰዉ ራዕይ የተሸከሙ የአመለካከት ደሃዎች ሳይሆኑ የራሳቸው አስተሳሰብና ህያዉ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አነዚህን ሠላማዊ ታጋዮች ከማይገናኝ ሌላ ኃይል ጋር አቆራኝቶ ለመምታት መሞከር ለኃይለማሪያምም ሆነ ለጌቶቹ አይበጃቸዉም። ዛሬ በወያኔ ነብሰ ገዳይ ወታደሮች ተከብቦ እዩኝ እዩኝ የሚለዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ የነደደ ቀን ደብቁኝ ማለት ይመጣልና ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት የበደለዉን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ የነጻነት ኃይሎችን እንዲቀላቀል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።
በመጨረሻም ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ስለ ግንቦት ሰባት ተጠይቆ ሲመልስ ግንቦት ሰባት “በህልም ውስጥ ያለ ድርጅት” ነው ብሏል። ታድያ ምነዉ ተኝቶ ህልም የሚያልም ድርጅት ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል? ለምንስ ይሆን ወያኔና ታማኝ ሎሌዉ ኃ/ማሪያም ያገኙትን ሁሉ ግንቦት ሰባት እያሉ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት? ያገኛችሁትን ሁሉ የግንቦት ሰባት አባል እያላችሁ ትከሳላችሁ? ለምንስ በግንቦት ሰባት ስም ታስራላችሁ? ትገርፋላችሁ? ትገድላላችሁ? ተኝቶ ለሚያንቀላፋ ድርጅት ለምን ትሸበራላችሁ፤ ለምንስ እንቅልፍ አጥታችሁ ትባዝናላችሁ? ግንቦት ሰባት እናንተ አልገባችሁም አንጂ መነሻውንና መድረሻውን አጥርቶ የሚያውቅ፤ ከደመናው ባሻገር ፍንትው ያለ የነፃነት ዉጋገን የሚታየው ባለ ታላቅ ራዕይ ድርጅት ነው። አስኪ ምናልባት ቢገባችሁ ተረት ቢጤ እንንገራችሁ፤
“አንዲት ሚዳቋ ነበርች አሉ። ሚዳቆ ከመሬት ገንዘብ ተበድራ ሲትኖር ከእለታት አንድ ቀን መሬት አፍ አውጥታ ብድሬን መልሽ አንጂ ብላ ትጠይቃታለች። ሚዳቆዋም ደንግጣ ከነበረችበት ቦታ ፈትለክ ብላ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥታ እፎይ ያንን ድምጽ ከአሁን በኋላ አልሰማም አለች። መሬትም በይ ብሬን ክፈይኝ ስትል ዳግም ጠየቀቻት። እንዴ ይህች መሬት የሌለችበት ዬት አገር ሊሂድ ብላ ሚዳቆ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተፈተለከች። ከዚያም እያለከለከች በቃ አሁንስ አታገኚኝም ስትል አሁንም መሬት ብቅ ብላ እየጠበኩሽ ነውኮ ብድሬን ክፈይ እንጂ ስትል ጠንከር አድርጋ ጠየቀቻት። ሚዳቆዋም መሬት የሌለችበት ልትደረስ ስትበር ስትበር ሳንባዋ ፈንድቶ ሞተች”ይባላል።
የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንደ መሬት ናቸው። የትም ሂዱ፤ የትም ግቡ ይከተሏችኋል። መስጊድ ዉስጥ አሉ፤ ቤተክርስትያናት ውስጥ አሉ። ቤተመንግሰት ዉስጥም አሉ። የሌሉበት ቦታ የለም። መፍትሄው እንደ ሚዳቆዋ መሸሽ አይደለም። መፍትሄው ዜጎች የሚያነሷቸውን የፍትህ፤ የእኩልነ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አድምጦ ትክክለኛ መልስ መስጠትና ከዕዳ ነጻ መሆን ብቻ ነዉ ። ከዚህ ዉጭ ጥያቄን ላለመስማት ወይም ሰምቶ ለመደፍጠጥ የሚደረገው ከንቱ ሩጫ መጨረሻው እንደ ሚዳቆዋ መፈንዳት እንጂ ህይወት አይሆንላችሁም።
እኛ ግንቦት ሰባቶች ዘረኛዉንና አሸባሪውንና የወያኔ ስርዐት ለመደምሰስና ህዝብ በነፃነት ያለፍርሃት የሚኖርበትን አገር ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ከእንግዲህ የሚያቆመን ምንም ነገር የለም። የምንታገለዉ ለህዝብ ጥያቄያችንም ህዝባዊ ጥያቄ ነዉና እኛም አንደጥያቄዉ በየመስጊዱ፤ በየቤተክርሲቲያኑና በየሰፈሩ ዉስጥ አለን።እኛ የሌለንበት ስፍራ የለም። በዚህ አጋጣሚ የዘመናት ትግላችን ፍሬዉ የሚታይበት ቀን እጅግ በጣም ቅርብ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አገር ተረካቢ የሆነዉ ወጣቱ ትዉልድ እራሱን፤ ወገኖቹንና እናት አገሩን ለማዳን የሚደረገዉን የነጻነት ትግል እየመጣ እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን አቅርበናል። ኑ እና ተቀላቀሉን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Oct 11, 2013

አንድ ላይ በመዋሐድ የትጥቅ ትግሉን በጋራ እያካሄድን ነው” – ት.ህ.ዴ.ን እና ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ

ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ት.ህ.ዴ.ን) እና ከኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር (ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ) የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ትግራይ ትብብርየኢትዮጵያ ህዝብ ከሚደርስበት ጭቅናና ስቃይ እራሱን ነጻ ለማውጣትና መብቱን ለማስከበር ለዓያሌ አመታት ያካደው እልህ አስጨራሽ ትግል በህዝብ ስም በሚነግዱና በሃገሪቱ እየተፈራረቁ ወደ ስልጣን በሚመጡ አምባገነኖች መብቱ እየተረገጠ ምኞቱ ሳይሰምርለት አሁንም በአስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛል፣
በተለይም የህዝብን ጥያቄን መነሻ በማድረግ የተነሳው የኢህአዴግ ስርዓት፤ የአገሪቱ ጭቁን ህዝቦች ነጻነታቸውንና መብታቸውን ለማስጠበቅ ያካሄዱት ወደር የለሽ መራራ የትጥቅ ትግል፤ የተከፈለው መስዋእትነት፤ የተነሳለት ህዝባዊ ዓላማና የሰማእታትን አደራ በመካድ ከደርግ ስርዓት በከፋ መልኩ ህዝቡን በማፈን፤ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን በመርገጥና የሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ትግል አማራጮችን ሁሉ በመዝጋት እራሱን አውራ ፓርቲ ብሎ በመሰየም በማን አለብኝነት አምባገነናዊ አገዛዙን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፣
ከአንድ አምባገነናዊ ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት እንደ ህዝብ ነጻ ለመውጣት እርግጠኛው መንገድ ህዝባዊና ህዝባዊ ትግል ብቻ መሆኑ አሌ የሚባል አይደለም፣ በአገራችን ኢትዮጵያም አገሪቱንና ህዝቧን ከአምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት ለመታደግ በየአቅጣጫው የትጥቅ ትግልን ጨምሮ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል እየተካሄደ ነው ፣ የትግሉ ዓላማም በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እዳይኖር ጋሬጣ የሆነውን የኢህአዴግ ስርዓትን በማስወገድ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጥ ነው፣
በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች ጸረ-ዴሞክራሲውን ስርዓት በመቃወም መታገላችን የሚደገፍ ቢሆንም በየአቅጣጫው በተናጠል እያካሄድነው ያለ ትግል ግን አንድ የተዋሃደ ሃይል ፈጥሮ መንቀሳቀስ ባልመቻሉ እንደ ሃገር የሚፈለገውን ውጤት ሊያስገኝልን አልቻለም፣
በዚህ ረገድ የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/ትህዴንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር (ኢህፍእግ) ከኣመታት በፊት ማለት የአሁኑ ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት (ደ.ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ) ግንባር ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለቱም ድርጅቶች የህዝብን ጥያቄ አንግበው ለዘመናት ምላሽ ያላገኘውን የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በህብረት እየሰራን በተለያዩ አውደ ውጊያዎችም በመሳተፍም በጋራ መስዋእትነት በመክፈል የድርሻችን እየተወጣን መጥተናል፣
አሁንም የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም የህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄ ወቅቱን የጠበቀ ምላሽ እንዲያገኝ በተናጠል ከሚካሄየድ ትግል ይልቅ ውህደት ፈጥሮ ተቀናጅቶ በጋራ መታገል ወሳኝ እና ተገቢ መሆኑን በማመን ውህደታችንን አጠናክረን የትግላችን አላማ ግቡ እስኪመታ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን ለጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብና ወዳጆቹ እናበስራለን፣
በሁለቱም የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የዓላማም ሆነ የፕሮግራም መሰረታዊ ልዩነት ስለሌለ እስካሁን ድረስም በመተባበር እየሰራን ቆይተናል። ይበልጥ እየተቀራረብንና የህብረት ስራ ውጤትን በተግባር እያየንና እየተገነዘብን የመጣን በመሆናችን በሁለቱም ድርጅቶች መካከል እየተጠናከረ የመጣውን ግኝነትና ህብረት ከመስከረም 18 ቀን 2006 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ውህደት በማሸጋገር አንድ አካል ሆነን ለመንቀሳቀስ ወስነናል፣
በዚህ አጋጣሚ ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የኛን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፣
እያካሄድን ባለው የትጥቅ ትግል ሁለንተናዊ ድጋፉን ያልነፈገን መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የተለመደው ድጋፉን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት ጥሪያችንን እናቀርባለን፣
ድል ለጭቁኖች!!
መስከረም 2006 ዓ/ም
ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር (ት.ህ.ዴ.ን) (ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ)

Oct 7, 2013

ከቀይ ሽብር ተፅዕኖ ያልተላቀቀው ፖለቲካ



‹‹የምን ይቅርታ? ለሕዝብና ለአገር ዕድገት ነው የተነሳነው፡፡ በትግሉ ሒደት ስህተት ፈጽመናል፤ ስህተቱ የትግሉ አካል ነው፡፡ ዘውዳዊ ሥርዓቱን ጥለናል፤ የኢትዮጵያንም ሕዝብ ነፃ አውጥተናል፡፡
የደቡብና የምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ይናገሩ፡፡ ከወላይታ የመጣውና ከአናሳ ሃይማኖት የመጣው ግለሰብ አገር የሚመራው በእኛ ትግል ምክንያት ነው፡፡ በማያውቀውና ባላነበበው ታሪክ የበሰበሰ ይለናል? የመጀመሪያ ዘመቻችን የዕውቀት ዘመቻ መሆን አለበት፡፡››
ከቀይ ሽብር ተፅዕኖ ያልተላቀቀው ፖለቲካይህን የተናገሩት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ሲሆኑ መልስ እየሰጡ የነበረው ደግሞ ፓርቲያቸው ኢሕአፓንና የትግል አጋሮቻቸውን አስመልክቶ ትችት ላቀረበ አንድ ወጣት ነበር፡፡ ወጣቱ፣ ‹‹በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ዘግናኝና ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል፡፡ መድረክ ላይ ያላችሁት ሰዎች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ በተለያየ መሾመር ተሰማርታችሁ ባመናችሁበት አቋም የአገሪቱን የፖለቲካ እመርታ ለማስለወጥም ሆነ ለማሳደግ የራሳችሁን ሚና ተጫውታችኋል፡፡ የ60ዎቹና 70ዎቹ ትንታግ ትውልድ ዳፋ አሁንም ባለንበት የፖለቲካ ተግባራዊ ሁኔታ ላይ በእጅጉ ሲንፀባረቅ ነው የምናየው፡፡ መጠላላቱና ጥቅመኝነቱ እንዳለ ነው፡፡ እዚህ አዳራሽ ውስጥ በመኢሶን፣ በኢሕአፓና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ የታገላችሁ ሰዎች አላችሁ፡፡ ያ የከሰረ፣ የበሰበሰ፣ የተቀበረና የሞተ የትግል ውጤት እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ግን አሁንም ሰንኮፉ አልለቀቀንም፡፡ በምትጽፏቸው መጽሐፎችና በምታቀርቧቸው ፕሮግራሞች ላይ አሁንም የቀይ ሽብር ትውስታዎች እንዳሉ እናያለን፡፡ መቼ ነው ኢሕአፓዎችና መኢሶኖች በአደባባይ ወጥታችሁ የሠራነው ስህተት፣ የፈጸምነው በደል ይኼ ነበር፤ ትውልድ ከእኛ ተምሮ እዚህ ላይ ትኩረት ያድርግ በማለት ይቅርታ የምትጠይቁት? አሁንም እየተታኮሳችሁ ነው፣ ዛሬም ኢትዮጵያን የምትተረጉሙት በተለያየ መንገድ ነው፤›› በማለት ነበር አስተያየት የሰጠው፡፡ 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን የገለጸው ወጣት አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰው በፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ላይ ብቻ አልነበረም፡፡ መድረኩ ላይ የጥናት ሥራዎቻቸውን ያቀረቡትን ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ፣ ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ፣ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ፣ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን ጨምሮ ከታዳሚዎቹ ውስጥ “Tower in the Sky” በተሰኘ መጽሐፏ በአጭር ጊዜ ዝነኛ የሆነችው የኢሕአፓ የቀድሞ ታጋይ ሕይወት ተፈራና ከኢሕአፓ መሥራቾች አንዱ የሆነው የብርሃነ መስቀል ረዳ ባለቤት አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤልን ጨምሮ፣ የ1960ዎቹ እና የ1970ዎቹ ትግል አካል የነበሩ በርካታ ሰዎች ተገኝተው ነበር፡፡ 
መስከረም 19 ቀን በደሳለኝ ሆቴል የተዘጋጀው ሕዝባዊ መድረክ በአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብት መታሰቢያ፣ በኢንተር አፍሪካ ግሩፕና በጀስቲስ አፍሪካ ትብብር ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማው ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ ዳግም እንዳይከሰት ምን ማድረግ ይገባል? በሚለው ጥያቄ ላይ ውይይት ለማድረግ ቢሆንም፣ በመድረኩ ላይ የተንፀባረቁት የሐሳብ ልዩነቶች የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዛሬም ከቀይ ሽብር ተፅዕኖ ያልተላቀቀ መሆኑን ያረጋገጠ ነበር፡፡ 
ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ የፖለቲካ ትግል ተሳታፊ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት የዛሬዋ ኢትዮጵያን የመንግሥትና የተቃውሞ ፖለቲካ መዋቅርን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉ ወሳኝ ዘርፎችን በበላይነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዕድሜና በጤና ምክንያት ከመድረኩ ሲገለሉም ከማርክሲስታዊ ሌኒኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም የተቀዳውን አካሄዳቸውን ለአዲሱ ትውልድ እያወረሱ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግም ዲሞክራሲን የሚሰብከውን ሕገ መንግሥት፣ ከሕገ መንግሥት ጀርባ ያለው ሌላው ሕገ መንግሥት በሚባለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ እንዲሸረሸር ያደረገው ከዚሁ ከማርክሲስታዊ ሌኒኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም ጋር ካለው ጥብቅ ቁርኝት አንፃር እንደሆነም ይጠቁማሉ፡፡ የቡድኖቹ ቅርበትና ልዩነት ርዕዮተ ዓለምን መሠረት ያደረገና ከኋላ ታሪክ መቀዳቱ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ለውጥ እጅግ አዝጋሚ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ 
በመድረኩም የተስተዋለው ይኼው እውነታ ነው፡፡ የወጣቱ ትውልድ አባላት ጥያቄ በአላዋቂነት ነው የተዘጋው፡፡ አንድ የመኢሶን አባል የነበሩ ግለሰብ ጥያቄም በተቃውሞ ነው የተመለሰው፡፡ ለነገሩ ግለሰቡም ውስብስቡን ፖለቲካ እጅግ አቃለው ኢሕአፓ ለኤርትራ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ማሰቡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለውጭ ኃይል አሳልፎ ከመስጠት ጋር ነው ያያያዙት፡፡ ኤርትራ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል ነበረች፡፡ የኢሕአፓ አባል የነበሩ ምሁራን የፓርቲውን ስህተት ይደፋፍናሉ ለሚለው ጥያቄም ምላሽ አልነበረም፡፡ ለዘመኑ ወጣት አክብሮት አትሰጡም ተብለውም ሲተቹ አንድ ዕድሜያቸው ገፋ ያለ ግለሰብ፣ ‹‹የዘመኑ ወጣት እንደያኔው በቀላሉ አይነዳም›› ሲሉ፣ የአብዮቱ ተሳታፊዎች በጥቂት ወራት ባዕድ የሆነ የሌላ አገር ርዕዮተ ዓለምን ወደ ኢትዮጵያ አውድ ለመቀየር እንኳን ሳይሞክሩና በጥልቀት ሳይረዱት በመከተላቸው አገሪቱ መታመሷን ሲገልጹም ድጋፍ አላገኙም፡፡ 
ወጣቱ ትውልድ ከእናንተ ምን ይማር? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ከመድረክ ጥናት አቅራቢዎቹና ከታዳሚዎቹ መካከል የተለያዩ ምላሾች ቀርበዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ‹‹የዕውቀትን አስፈላጊነት መማር ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታና የሕዝቡን ሁኔታ በማርክስ ጽሑፎች መመለሾ አይቻልም ነበር፡፡ መቻቻልና መደማመጥ መማር ይቻላል፡፡ ስህተትን መቀበል መማር ይቻላል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ በበኩላቸው፣ ‹‹የኢትዮጵያን ታሪክ በብቸኝነት ልንይዝ እንደማይገባ ልንማር ይገባናል፡፡ ታሪካችን ከሌሎች አገሮች ጋር ተመሳሳይነት ነበረው፡፡ እያነፃፀርን ልንረዳው ይገባናል፤›› ብለዋል፡፡ 
በአብዮቱ ዕጣ ፈንታ ላይ የዳያስፖራው ሚና ምን ነበር? የመኢሶንና የኢሕአፓ ልዩነት ምን ያህል ሰፊ ነበር? መኢሶን ወይም ኢሕአፓ ከሕዋሓት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስል ነበር? ከመኢሶን ወይም ከኢሕአፓ አንዳቸው በደርግ ቦታ ሥልጣን ቢይዙ ቀይ ሽብር እንደማይኖር ምን ማረጋገጫ አለ? በአሁኑ ወቅት የአደባባይ ምሁራን የጠፉት ከቀይ ሽብር ጋር በተያያዘ ነው ወይ? ቀይ ሽብር ለመንግሥትና ለሕዝብ አሉታዊ ግንኙነት እንዴት ነው አስተዋጽኦ ያደረገው? በኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዴት መፍጠር ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎችም ከተሳታፊዎች የተሰነዘሩ ሲሆን የተወሰኑት ብቻ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ 
ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ መኢሶንና ኢሕአፓ ‹እናሸንፋለን› እና ‹እናቸንፋለን› ከሚለው እጅግ የዘለለ ልዩነት እንደነበራቸው በመጥቀስ ልዩነታቸው ጥቃቅን እንዳልነበር ያመለከቱ ሲሆን፣ ሁለቱም ድርጅቶች በትክክል ማርክሲስታዊ ሌኒኒስታዊ ነበሩ ለማለት እንደማይቻልም አስረድተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ልዩነቱ የፖለቲካ ሥልጣን ጉዳይ እንደነበር አስገንዝበው፣ ደርግም ሆነ እሱን ለመፋለም የተሠለፉት ኃይሎች ጥፋተኞች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ መኢሶንና ኢሕአፓ በጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ እስከ ጥር ወር 1967 ዓ.ም. ድረስ አንድ የነበሩ ቢሆንም፣ መኢሶን ‹ሒሳዊ ድጋፍ› በሚል ከደርግ ጋር ለመሥራት መወሰኑ በሥልጣን አያያዝ አካሄድ ላይ መሠረታዊ ልዩነት እንዲኖራቸው ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡ 
የመኢሶንና የኢሕአፓን የአደባባይ ይቅርታ በተመለከተ ዶ/ር ካሳሁን በግለሰቦችና በመጻሕፍት ውስጥ ይቅርታቸው ቢታይም፣ በአሁኑ ወቅት ድርጅቶቹ ሕልውና ስለሌላቸው ያን ማድረግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ በስሜት መናገር እንደማይጠቅም የገለጹት ፕሮፌሰር ባህሩ፣ ድርጅቶቹ ይቅርታ የመጠየቅ ፍላጎት የሌላቸው መነሻቸው ለኢትዮጵያ በጎ ነገር ለመሥራት መሆኑን በመጥቀስ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ የያኔውን የዳያስፖራ ተፅዕኖ በተመለከተ አስተያየት ሲሰጡ የያኔው የዲያስፖራ ተፅዕኖ እንዳሁኑ ጠንካራ እንዳልነበር አስገንዝበዋል፡፡ 
አንድ አስተያየት ሰጪ የቀይ ሽብር ተጎጂዎችን ለመደገፍና በእነሱ ዙሪያ የተሟላ መረጃ የመስጠት ችግር እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤል በቀይ ሽብር ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር በውል ሊታወቅ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ 
ቀይ ሽብር እንዳይደገም
የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሲመረቅ የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብት መታሰቢያ ስብሰባ አዳራሹ ላይ የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡ የመታሰቢያው ጊዜያዊ የአመራር ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ እ.ኤ.አ. ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. መሠረት ድንጋይ ሲጣል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለሾ ዜናዊ የቦታውን ልዩ አብነት አስመልክቶ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር በጥሞና ማውሳታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ቦታው የቀድሞው የከርቸሌ እሥር ቤት እንደነበርና ‹ዓለም በቃኝ› የተሰኘ በጣልያን ወረራ ጊዜና በኋላም በደርግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰቃዩበትና የገደሉበት ቦታ እንደነበርም ፕሮፌሰሩ ጠቁመዋል፡፡ 
መታሰቢያው ቀይ ሽብርን ጨምሮ በሩዋንዳና በደቡብ አፍሪካ የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋትና የአፓርታይድ ጭቆና፣ ባርነትና ቅኝ ግዛት የሚታወሱበት እንደሚሆንም አክለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በመታሰቢያው ብዙኃን ጉዳተኞችን ከማስታወስ አልፎ በአፍሪካውያን መሠረታዊ ለውጦች ላይ መሰል አደጋ መቼም በማንም ላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖረው በአፍሪካ ኅብረት ውስጥ ያሉ ሕዝቦች አቋም የሚያንፀባርቁበት ነው፤›› በማለትም ዋነኛ ዓላማውን አመልክተዋል፡፡ 
የመጀመሪያው ዙር ስብሰባ በሩዋንዳ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 10 እስከ 12 ቀን 2012 መካሄዱን የጠቆሙት ፕሮፌሰር አንድሪያስ፣ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በየዓመቱ የ100 ቀን የሐዘን ጊዜ መኖሩን አስታውሰው፣ በኢትዮጵያም ለቀይ ሽብር ሰማዕታት የሐዘን ጊዜ መመደብ ያስፈልግ ይሆን ወይ? ብለው እንዲጠይቁ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ የተደረገው የመታሰቢያው ስብሰባ ሾለ ቀይ ሽብር የሚመለከታቸው አካላት ሐሳብ በመለዋወጥ የተሻለ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 
የቀይ ሽብር ፖለቲካዊ አንድምታዎች
የ1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ አብዮት ሒደት የተጀመረውና አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎቹን እያሳደረ የተጓዘው የዳበረ ሰላማዊ ፖለቲካ ሽግግር ባሕልም ሆነ የነቃ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ባልተለመደበትና ባልዳበረበት አጠቃላይ ማዕቀፍ እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ፣ አብዮቱ ተስፋ እንደተደረገው ሰላማዊና ከደም መፋሰስ የፀዳ እንዳልነበር አስታውሰዋል፡፡
ለቀይ ሽብር መከሰት ዋነኛው ምክንያት በለውጡ እንቅስቃሴ መፍትሔ በሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ በቂ የሐሳብ ልውውጥ ተደርጎ ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የአብዮቱ መቀጣጠል ድንገተኛነትና ግብታዊነት፣ እንዲሁም ብሔራዊ ፍላጎቶችን አቀናጅቶ ሒደቱን መምራት የሚችል ግንባር ቀደም ድርጅት ተዘጋጅቶ አለመቆየቱ እንደሆነ ዶ/ር ካሳሁን አስረድተዋል፡፡ 
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የተባለው ድርጅት በርካታ አባላትና ደጋፊዎችን አፍርቶ የጀመረው የከተማ ሽምቅ ውጊያ የበርካታ ሺሕ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውንና በአጠቃላይ የኅብረተሰቡን ሕይወት ያናጋውን ቀይ ሽብር ተብሎ የሚታወቅ ክስተት ማስከተሉን የጠቆሙት ዶ/ር ካሳሁን፣ ይህ አሉታዊ ውጤት በአገሪቱና በዜጎቿ ላይ ያደረሰውን ፈርጀ ብዙ ጉዳት ተቋቁሞ በትክክለኛ መሾመር ላይ የተመረኮዘ ግንባታና ተሃድሶ ለማካሄድ እስካሁንም ድረስ እጅግ ሰፊ ልፋትና ጥረት የሚጠይቅ ዓብይ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ 
ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ በቀይ ሽብር የተነሳ ሦስት መሠረታዊ የፖለቲካ አንድምታዎች መድረሳቸውን ያስረዳሉ፡፡ የመጀመሪያው ተፅዕኖ ከመንግሥትና ከሕዝብ ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ በአብዛኛው የኅብረተሰቡ ክፍል ባሕልና እምነት መንግሥት ሕዝብን ከአደጋና ክፉ ነገሮች የሚጠብቅ፣ የሚከላከልና የሚታደግ አካል ተደርጐ ሲወሰድ የነበረበት ሁኔታ ቀይ ሽብር ባደረሳቸው ጥፋቶችና መናጋቶች የተነሳ ተቀይሮ የሕዝብ አስተዳዳሪ የሆነው መንግሥት በአጥፊነት፣ በግፈኝነትና በመከራ ምንጭነት በሚታይበት ሁኔታ የመተካት ዝንባሌ በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡ የኅብረተሰቡና የመንግሥት ግንኙነት የጥርጣሬ፣ የፍርኃትና ያለመተማመን ገጽታዎች እንዲላበስ አስገድዷል፤›› ብለዋል፡፡
ሁለተኛው ተፅዕኖ ከዜጎች የፍርኃት ስሜት ጋር የተያያዘ እንደሆነም ዶ/ር ካሳሁን ገልጸዋል፡፡ “ቀይ ሽብር በአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ውስጥ ያሳደረው የፍርኃትና የጭንቀት ድባብ በርካታ ዜጎች በአገሪቱ የፖለቲካ ዋና ዋና ጉዳዮች በንቃት የመሳተፍና የየበኩላቸውን ገንቢ አስተዋጽኦ የማድረግ አስፈላጊነትን በርቀት እንዲሸሹና በገለልተኛነት እንዲያዩት የሚያደርግ አዝማሚያ አስፍኗል፤” በማለት አስረድተዋል፡፡
ሦስተኛው ተፅዕኖ ከዜጎች ባሕሪ መለወጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ዶ/ር ካሳሁን ጠቁመዋል፡፡ “በቀይ ሽብር ሳቢያ ብዙዎች የፖለቲካ አስመሳይነት፣ የአድርባይነትና የለዘብተኝነት ባህሪያትን ተላብሰው ነገሮችን ከአጭር ጊዜና ግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ማሟያ አንፃር ብቻ የመመልከት አጉል ባሕሪ እንደ ዓላማ እንዲይዙ አድርጓል፡፡” 
ዶ/ር ካሳሁን ስለ ቀይ ሽብር በተደጋጋሚ ከማውሳትና የድርጊቱን ተዋናዮች ከማውገዝና ከመኮነን በዘለለ፣ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይደገሙ በተለያዩ ጎራዎች ተሰልፈው ደም የተቃቡና ቂም የተያያዙ ወገኖችን በማገናኘት ከቁርሾ ከመራራቅ ተቆጥበው የየግላቸውና የጋራ ስህተቶቻቸውን የሚገመግሙባቸውን መድረኮች በማመቻቸት፣ ለጋራ ጥቅምና አብሮነት በትብብር የሚሠሩበትን ሁኔታ ማገዝና ማበረታታት አስፈላጊ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡ የተፈጸመውን ሳይረሱ ይቅር መባባል እንዳለባቸውም ዶ/ር ካሳሁን መክረዋል፡፡
የቀይ ሽብር ታሪካዊ ዳራዎች
ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ ለቀይ ሽብር የዳረገው አብዮት በ1966 ዓ.ም. ሲከሰት አገሪቱ ለአብዮት ፈጽሞ ዝግጁ እንዳልነበረች አስረድተዋል፡፡ በዓለም ታሪክ እጅግ ጥቂት የሆኑት ማኅበራዊ አብዮቶች የኅብረተሰቡን የፖለቲካ ሥርዓትና ማኅበራዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የሚቀይሩ፣ ኅብረተሰቡን የሚመራውን ገዥ ርዕዮተ ዓለም ቀይረው በሌላ የሚተኩና በኅብረተሰቡ በኩል ትልቅ ምስቅልቅል የሚያመጡ ክስተቶች በመሆናቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከእነዚህ ጥቂት ማኅበራዊ አብዮቶች መካከል አንዱን በ1966 ዓ.ም. ማስተናገዷንም ገልጸዋል፡፡
ከ1933 ዓ.ም. እስከ 1966 ዓ.ም. ባለው ጊዜ አገሪቱ በግንባታና በለውጥ ላይ የነበረች ብትሆንም፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የራሱ ለውጥ የፈጠራቸውን የለውጥ ኃይሎች ሊቆጣጠራቸውና ሊቀድማቸው እንዳልቻለ ፕሮፌሰር ሽፈራው አስታውሰዋል፡፡ ከአራት እስከ አምስት በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በ1950ዎቹ ሲመዘገብ በዓለም ባንክ ጭምር የተከበረ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንደነበር የገለጹት ፕሮፌሰር ሽፈራው፣ የኢኮኖሚ ዕድገቱ የሕዝብ ብዛት እንዲጨምር ገዳይ በሽታዎችን በመቆጣጠር አስተዋጽኦ ቢያደርግም፣ የሕዝቡ ብዛት ግን ቤት አልበኝነትንና ፍፁም ድህነትን በማምጣት የተማረው የኅብረተሰብ ክፍል ጥያቄ እንዲያነሳ መጋበዙን ያስረዳሉ፡፡ “መንግሥት መዋቅር ቢለውጥም ንጉሣዊ አገዛዙ ስላልተለወጠ በአዲሱ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያለው ኃይል ከንጉሣዊ አገዛዙ ጋር ሊሄድ አልቻለም፡፡ የመንግሥት መዋቅሩ ለውጥ በጣም ፈጣን ሲሆን፣ ንጉሣዊ አገዛዙ የሚያደርገው ለውጥ እጅግ ዘገምተኛ ነበር፡፡ አዲሱ ኃይል በጣም ትዕግሥት ያጣ፣ መሄድ መወርወር አለብን የሚል ነበር፡፡ አባቶቹ የነበሩትን ጊዜ ጨርሶ አያመዛዝንም ነበር፤›› ብለዋል፡፡
አዲስ የፖለቲካ ባሕል
የተማሪዎች ንቅናቄ ብዙ በጎ ጎኖች ቢኖሩትም በርካታ አሉታዊ አሻራዎች እንዳሉት ያስታወሱት ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ፣ አብዮቱ በውስጡ ቀይ ሽብርን የፈጠሩ መሠረታዊ ምክንያቶች እንደነበሩትም አመልክተዋል፡፡ ‹‹የመጀመሪያው ምክንያት ቀኖናዊ የሆነ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም አስተሳሰብ ማስረፅ ነው፡፡ ሁለተኛው የአመፅ ባሕል ፈጥሯል፡፡ ሦስተኛው የተፈጠረው ነገር ተፈጥሮአዊ ክፍፍል ነው፤›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ሌላው የቀይ ሽብር ምንጭ የአመፅ ባሕል እንደሆነ ፕሮፌሰር ባህሩ ያስረዳሉ፡፡ ‹‹የአመፅ ባሕል የተለያዩ ዘርፎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው የሃይማኖት ዘርፍ ነው፡፡ ሁለተኛው ወታደራዊ ዘርፍ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው ጦርነት የተደረገው እርስ በርስ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ገለን መሸለል ባሕላችን ነው፤›› ብለዋል፡፡
ሦስተኛው የቀይ ሽብር ምንጭ የ1953 ዓ.ም. የእነ ብርጋዴር ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ሁለት አንድምታዎች አሉት፡፡ ሙከራው በመክሸፉ ከመንግሥት ይልቅ የተማሩት ተቃዋሚዎች ናቸው፡፡ ወታደሮቹ በተለይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፍ ማለት ሞት መሆኑን ተምረውበታል፡፡ ሌላው ሙከራው ከከሸፈ በኋላ ተሳትፎ አድርገዋል በተባሉት ሰዎች ላይ የተፈጸመው ግድያ ከቀይ ሽብር ጋር የተገናኘ ነበር፤›› በማለት አነፃፅረዋል፡፡
የቀይ ሽብር ውጤት ብሩህ አዕምሮ ያላቸውን ወጣቶች በመፍጀት፣ አምባገነናዊ ሥርዓት በመፍጠርና ኅብረ ብሔራዊ ተቃውሞን በማክሰም እንደሚገለጽ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ባህሩ፣ ቀይ ሽብር እንዳይደገም ከዝክር ባሻገር አዲስ ፖለቲካዊ ባሕል መፍጠር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ጃፓንና ጀርመን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፅልመት መጥተው ብሩህ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ገንብተዋል፡፡ ያ ታሪክ ሆኖ ቀርቷል፡፡ በጀርመን በየጊዜው የሒትለር ሥራ በኤግዚቢሽን ይታያል፡፡ አዲሱ ትውልድ ያን እያየ ወላጆቹን ‹ይኼ ሁሉ ሲሆን ምን ታደርጉ ነበር?› ብሎ ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ይህን ለማምጣት አዲሱ ትውልድ ከሥር ከሥርዓተ ትምህርቱ ጀምሮ ቀይ ሽብርን እንዲያውቀው ማድረግና ዲሞክራሲን በተላበሰ መንገድ እንዲያድጉ መደረግ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
በውይይቱ ጥናት አቅራቢዎቹም ሆኑ ተሳታፊዎቹ አገሪቱ ወደፊት ልትሄድበት የሚገባው ጎዳና ሙሉ በሙሉ ከቀይ ሽብር የፀዳ እንዲሆን የተስማሙ ቢሆንም፣ በቀይ ሽብር ተፅዕኖ ስሜታዊነት ተስተውሎባቸዋል፡፡ ቢያንስ ግን በአንድ መድረክ መነጋገርና ሐሳብ መለዋወጥ (በአብዛኛው ራስን በመከላከል መንፈስ ቢሆንም) አንድ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ተሳታፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

Oct 6, 2013

must watch very painfullllllll Italy, says coastguards stopped him saving more people

 
 
 
 

A fisherman who rescued 47 people after a migrant boat sank off the coast of Lampedusa, Italy, says coastguards stopped him saving more people. He claims rescue workers refused to take people from his full boat so he rescue more, because it was against their protocol. More than 300 people are thought to have died in the disaster
the autorities are talking badly about those of us who rescued people that's why i'm angry.

now the coastguard saying that they are the ones who saved the people.

and we're the idiots who only pulled 47 people onto our boat.

we would have saved more but they refused to take the people away from the boat and let us save the others.

they were 55 of us on the boat, not a just few, and they refused because it was not the right protocol .

i had to say, am going to the port . with this people . you do what you need to do. that's why i did .

i don't know if you know what it's like to see the sight i saw.

a see filled with the people. all calling to help it wouldn't have been hard to save these people.







Oct 5, 2013

ለሕዝባዊ ተቃውሞ የወያኔ ፈቃድ የማይጠየቅበት ቀን እንዲመጣ እንታገላለን!!!

መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም. አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ከሌሎች በርካታ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር የጠራው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ይህ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ከዝግጅቱ እስከ ፍፃሚው ብቻ ሳይሆን ከፍፃሚው በኋላም በድርጊቶች የታጀበ ነበር።
ወያኔ ለሰልፉ እውቅና ሰጥቶ እያለ “መቀስቀስ አይቻልም፤ ፓስተር መለጠፍ አይቻልም፤ በዚህ ማለፍ፣ በዚያ መዞር አይቻልም” እያለ የፓርቲው መሪዎችን፣ አባላትንና ደጋፊዎችን ሲያስር፣ ሲፈታ፣ ሲያዋክብ ሰንብቷል። ይህም ሆኖ ግን የፓርቲ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ወከባውን ተቋቁመው ሰላማዊ ሰልፉን መጀመር ቻሉ።
ወያኔ ሰልፈኛው ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይደርስ የለመደውን ጉልበት ተጠቀመ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች ይተሙ የነበሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች እንዳይገናኙ በፓሊሶች ታገቱ። ኢትዮጵያ ውስጥ አፈና የደረሰበት ደረጃ ጎልቶ ታየ። ሰልፈኛው ሊደርስ ያሰበው ቦታ – መስቀል አደባባይ – መድረስ ሳይችል ቀረ። የሰልፉ አስተባባሪዎች የነበሩበት ብዛቱ በመቶ ሺህ የተገመተ ስብስብ ሊደርስ በቻለበት ቦታ የመዝጊያ ሥነሥርዓት ፈጽሞ ተበተነ።
የወያኔ ጆሮ ጠቢዎች ከሰልፊ በፊት፣ በሰልፉ ጊዜ እና ከሰልፉ በኋላ ግንባር ቀደም የሰልፉ ተዋንያንን የማደን፣ የማዋከብ፣ የማሠር፣ የመደብደብ “ሥራ” በዝቶባቸው ሰንብቷል። ባሠሩና ባዋከቡ መጠን ግን የሕዝብ ምሬት እየበረታ መጥቷል።
ወያኔ ሰልፉን ለመቆጣጠር እጅግ ብዙ የሆነ የፓሊስ፣ የጦርና የሰላይ ሠራዊት ለማሠማራት ተገዷል። ይህ ራሱ አንድ ድል ነው።
ከዚህ ሰልፍ የተገኘው ጥቅም ግን ይህ ብቻ አይለም። ወያኔ በሕዝብ ልብ ውስጥ ዘራሁት ያለው ፍርሀት በኖ የሚጠፋ መሆኑ፤ እድል በተፈጠረ ጊዜ ሁሉ ወጣቶች በፈጠራ ሥራዎቻቸው ተመልካችን ማስደመም የሚችሉ መሆኑን፤ የተለያዩ ሀይማኖቶች ተከታዮችን ለማጋጨት ወያኔ የሸረበው ድር የተበጣጠሰበት መሆኑ ሰልፉ አሳይቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ በወታደር እና በሰላዮች ብርታት ላይ የቆመ ሥርዓት መሆኑን አሳይቷል። ወያኔ በጠመንጃና በስለላ ላይ ያለው ሞኖፓሊ ካልተሰበረ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችንም እሱ ከሚፈልጋቸው ክበብ እንዳይመጡ ማፈን የሚችል መሆኑ አሳይቷል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን የወያኔ ወታደራዊና የስለላ ሞኖፖሊ መስበር የሥራው አንድ አካል አድርጎ ይመለከታል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ አምባገነኑን ወያኔ በመገዳደር ላይ ያሉትን ወገኖች ትግል ያደንቃል። እንዳንዳንዳችን የየበኩላችን ጥረት ካደረግን የኢትዮጵያን የመከራ ጊዜ በእጅጉ እንደምናሳጥር ያምናል።
ግንቦት 7 ሕዝብ ተቃውሞ ለማቅረብ የወያኔን ባለሥልጣኖች ፈቃድ መጠየቅ የሚያበቃበት ጊዜ እንዲመጣ ተግቶ ይሠራል። ለዚህ ዓላማም ተባብረን እንድንቆምም ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Sep 29, 2013

ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!!!

       “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ ---- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ---- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ።




ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!) ምን እንደምል ታውቃላችሁ? “የእኔን እድል ይስጣችሁ” (እርግማን እኮ አይደለም!) “እንደእኔ ፕሬዚዳንት ሆናችሁ እዩት” ለማለት ነው። ልክ ነዋ! ኢህአዴግ በፕሬዚዳንትነት የሾመው ሰው ያለው ሥልጣንና ሃላፊነት የቱ ድረስ እንደሆነ ሳያውቁ እኮ ነው ተመቸን ብለው የሚናገሩት። ኢህአዴግ የሾመው ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ ተዓምር እንዲሰራ መጠበቅ “ፌር” አይደለም። (በኢህአዴግ ደግሞ ትግል እንጂ “ተዓምር” መስራት አይፈቀድም!) ከፓርቲው አፈንግጦ ተዓምር ለመስራት የሚወራጭ ካለም የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዓይነት እጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ከቤተመንግስት ወጥቶ ጣራው የሚያፈስ የኪራይ ቤቶች ቤት ውስጥ ይገባል።

ይሄም ታዲያ እጁን ከፖለቲካ ሰብስቦ ከተቀመጠ ብቻ ነው። ነጋሶ ግን እጃቸውን ሰብስበው አልተቀመጡም። በግላቸው በምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ ፓርላማ ገቡ። ራሴ ባረቀቅሁት ህገመንግስት ውስጥ የሰፈረውን ፖለቲካዊ መብቴን ከማስወስድ የሚያፈስ ቤታችሁን ውሰዱልኝ አሉ። (“የነጋሶ መንገድ” በሚለው መፅሃፋቸው እንደነገሩን) በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ “ውጤታማ አልነበሩም” የሚለውን የተቃዋሚዎች ትችት እየተቃወምኩም ሆነ እየደገፍኩኝ አይደለም። (“አይቻልም ወይ መኖር የማንም ሳይሆኑ” ያለችው ድምፃዊት ማን ነበረች?) እኔ ግን ጥያቄ አለኝ - በፕሬዚዳንቱ ላይ በተሰነዘሩት አስተያየቶች ዙሪያ። ፕሬዚዳንቱ ይሄን ሁሉ ዘመን ኖረው ኖረው ከቤተመንግስት ሊወጡ አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው “ውጤታማ ነበሩ? አልነበሩም?” የሚለውን የጦፈ ሙግት ምን አመጣው? ምናልባት ኢህአዴግ አዲስ ለሚሾመው ፕሬዚዳንት ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ለተሰናባቹ እኮ የሚተርፋቸው ፀፀት ብቻ ነው። (The damage is already done! አለ ፈረንጅ) እውነቱን ለመናገር--- ተቃዋሚዎች ስለፕሬዚዳንቱ የሰጡት አስተያየት የድሮ ተረት ከማስታወስ ያለፈ ፋይዳ አለው ብዬ አላስብም (“ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” አሉ) የሚገርመው ደግሞ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መሃል ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ወይም ስኬትና ውድቀታቸው ብሎ ከፋፍሎ ለማየት አንድ እንኳን የሞከረ የለም። ተቃዋሚዎቹ “የማርያም ጠላት” ያደረጓቸውን ያህል በፓርላማ የኢህአዴግ ደጋፊና ብቸኛው የግል ተመራጭ ዶ/ር አሸብርም እንከን የሌለባቸው ፍፁም ፕሬዚዳንት አድርገው ነው ያቀረቧቸው። (“ወልደህ ሳትጨርስ---”የሚለው ተረት ትዝ ብሏቸው ይሆን?) የፕሬዚዳንት ግርማ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ እንኳን የቱንም ያህል መላዕክ ቢያደርጓቸው አይፈረድባቸውም (ሥራቸው ነዋ!) እኔ ተቃዋሚዎችን ብሆን ግን ትችቴን አንድም ኢህአዴግ ላይ አሊያም የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን በገደበው ህገመንግስቱ ላይ ነበር የማነጣጥረው።

(“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” አሉ!) እኔ የምለው ግን--- ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በፕሬዚዳንት ግርማ ላይ የወረደውን የትችት ውርጅብኝ ሰምቶ ይሆን? ከሩጫ በኋላ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት አለኝ ስላለ እኮ ነው! (ፍላጎት ነው ምኞት?) በኋላ ከሚቆጨኝ ለአትሌታችን ምክር ቢጤ ጣል ባደርግለት ደስ ይለኛል። ለፖለቲካ ዲሲፕሊንና ልምምድ ብቻ በቂ አይደሉም። (ሩጫና ፖለቲካ ለየቅል ናቸው!) እንግዲህ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፉት 12 ዓመታት ሰሩም ተባለ አልሰሩ በቅርቡ ከሥልጣናቸው ይሰናበታሉ። ከወር በፊት ይመስለኛል--- ፕሬዚዳንቱ ከ“ሚት ኢቲቪ” አዘጋጅ ተፈራ ገዳሙ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ሲመረጡ የፍርሃት ስሜት አድሮባቸው እንደሆነ ጠይቋቸው፣ በመጀመርያው ጊዜ እንጂ በሁለተኛው ምንም ዓይነት ፍርሃት እንዳልተሰማቸው ገልፀው፣ለሦስተኛ ዙር በፕሬዚዳንትነት መቀጠል አለመቻሉ ትንሽ እንደሚያናድድ ተናግረዋል - በቀልድ መልክ። (ከአንጀታቸውም ሊሆን ይችላል!) ግን አያችሁልኝ--- የኢህአዴግን ምስጢር ወዳድነት። እስካሁን እኮ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ እንኳ አልሰጠንም። (ኢህአዴግ “ሰርፕራይዝ” ማድረግም ነፍሱ ነው አሉ!) እናላችሁ--- ችግር የለም፤ ቀኑ ሲደርስ አዲሱን ፕሬዚዳንት በፓርላማ አቅርቦ ሰርፕራይዝ ይለናል - እንደ ልደት ስጦታ (ስጦታውስ ለኛ ሳይሆን ለተሿሚው ነው!) ባለፈው ሳምንት “ታጋይ ደከመኝ አይልም እንጂ ኢህአዴግ ድክም ብሎታል” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ፅሁፍ ያነበቡ አንድ ደንበኛ ስልክ ደውለው እንዴት እንደወቀሱኝ አልነግራችሁም። ወቀሳው ምን መሰላችሁ? “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ነው። በመቆርቆር ግን አይመስልም፤ “23 ዓመት አንቀጥቅጦ ገዝቶን እንዴት 21 ዓመት ብቻ ትላለህ? ሁለቱን የት ደብቀህለት ነው?” ነበር ያሉኝ።

እኔ እንኳን መደበቄ አልነበረም። ሁለቷ ዓመት የልምምድ ጊዜ ናት ብዬ ነበር የተውኳት (ለካስ ሂሳብ ማወራረድ ተጀምሯል!) እኔ ግን 30 እና 40 ዓመት የመግዛት ራዕይ ላለው ፓርቲ ገና ወገቡ ላይ ሆነን ሂሳብ መተሳሰብ ፋይዳው አልታየኝም። ባይሆን 30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ የሥልጣን ዘመኑን መቆጣጠር እንጀምራለን፤ አሁንማ ምን ተነካና። በነገራችሁ ላይ --- ኢህአዴግ የሥራ ብዛትና ጫና ስላደከመው ከመውደቁ በፊት የአንድ ዓመት እረፍት ይውሰድ በሚል ያቀረብኩትን ሃሳብ አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት ክፉኛ እንደተቃወሙትና እንዳወገዙት ሰምቻለሁ - “ታጋይ አይደክመውም” በማለት። ከዚህ ሃሳቤ የማልታቀብ ከሆነም በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት እንደዛቱብኝ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ ብለውኛል። ከሁሉም የገረመኝ ግን ምን መሰላችሁ? አንዳንድ የኢህአዴግ ካድሬዎች በእኔ ላይ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ገና ካሁኑ መፈክሮች ማዘጋጀት መጀመራቸው ነው። (የሰልፍ ፈቃድ ሳያገኙ?) እስቲ ከመፈክሮቹ ጥቂቶቹን እንያቸው - “ኢህአዴግ ደክሞታል በሚል ማደናገርያ ሥልጣን በአቋራጭ መያዝ የህልም እንጀራ ነው!” “ሥልጣን ለኢህአዴግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” “ኢህአዴግ አረፍ እንዲል የሚፈልጉት የኒዮሊበራል ተላላኪዎች ናቸው!” እኔ ግን እንደነሱ አይደለሁም።

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ቀንደኛ አቀንቃኝ ስለሆንኩ በዛቻውም ሆነ በመፈክሮቻቸው ቅያሜ አላደረብኝም። እንደውም ያለውዝግብ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ካገኙ ከእነሱ ጋር ሰልፍ ለመውጣት ሁሉ አስቤአለሁ - ተቃውሞው በእኔ ላይ ቢሆንም። ከገዢ ፓርቲ ጋር ተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚፈጥር ማወቅ እፈልጋለሁ (ለጠቅላላ እውቀት እኮ ነው!) በዚያ ላይ ተቃዋሚዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚጠሩት በእያንዳንዱ ሰልፍ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍልና ከፖሊስ ጋር የሚጋቡትን እልህና ውዝግብ ሰበብ ለማወቅ እፈልጋለሁ። ኢህአዴግስ ተመሳሳይ ውዝግብና እልህ ውስጥ ይገባል ወይስ ነገሩ አልጋ በአልጋ ይሆንለታል? (የባለቤቱ ልጅ መሆኑ እኮ አልጠፋኝም!) ይሄን ሁሉ የመፈተሽና የማጥናት ፍላጎት አለኝ። ስፖንሰር ተደርጌ እኮ አይደለም። (የሃገሬ ጉዳይ አያገባኝም እንዴ?) ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ቦታው በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንደሆነና “ለልማት ነው ቅድምያ የምንሰጠው” የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልጿል።

በዚሁ ሰበብ ፖሊስ ከቢሮው ንብረቶች እንደወሰደበት እንዲሁም እሁድ እለት ሰልፉን ሊያካሂዱ ሲሉ መንገድ በመዝጋት ሰልፉን እንዳቋረጠባቸው ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። አንድነት ፓርቲም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ሌላ አማራጭ ቦታዎች አቅርብ ከተባለ በኋላ ያቀረበው ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰልፉን ጃንሜዳ አድርግ እንደተባለ አስታውቋል። በዚሁ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መውጣቱን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን ቦታና ጊዜ የሚወስነው መስተዳድሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ “አሁን የቀራቸው የምትቃወሙትንም የምንሰጣችሁ እኛ ነን” ማለት ብቻ ነው ሲሉ ክፉኛ አሽሟጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አዲስ ወጣ በተባለው መመሪያ ተናዶ ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? “እንደዚያ ከሆነማ ለምን ሰልፍ የሚወጣውንም ህዝብ እነሱ አይመድቡልንም?” በአሁኑ ጊዜ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎች ሰልፍ በጣም አስፈርቶታል የሚለው ይሄው የተቃዋሚ ደጋፊ፤ “በመኪና ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ለመበተን፣ ወዘተ--- ለሁሉ ነገር አስፈቅዱኝ እያለ ነው፣ ለምን መፈክሮቹንም እሱ አያዘጋጅልንም” በማለት አዲስ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለገዢው ፓርቲ አበርክቶለታል። “እናም ኢህአዴግ በቅርቡ “ሰላማዊ ሰልፍ እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ አጀንዳዎችን እንቀርፃለን፣ ለሰልፍ የሚወጣ ህዝብ እንመለምላለን፣ በራሪ ወረቀቶችን እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እናደርጋለን ወዘተ-- የሚል ልዩ ማስታወቂያ በኢቴቪ ሲያስተላልፍ ልንሰማ እንችላለን” ብሏል - የተቃዋሚ ደጋፊው። (ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!)       áˆáŠ•áŒ­áŚ  ሚኒሊክ ሳልሳዊ

ማን ነው የሚለየው ይህ ትውልድ ለወያኔ ፍም እሳት ነው !!! የዕለቱ ምርጥ ዘፈን በኖርዌይ ኦስሎ ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ !!!!

በኖርዌይ የሚገኘው ይህ የምትመለከቱት ዌብሳይት ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ የተደረገውን ለግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል á‹¨áŒˆá‰˘ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በ26.09.2013 13:23 ላይ የተለመደውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የነዛበት ሊንክ እና ፕሮግራሙን እንዳይካሄድ ለማድረግ ብዙ የደከመበት ሾል ይህን ይመስል ነበር 
ይቺን ሊንክ ይጫኑ http://www.abesha.no/P%C3%A5-Amharisk/1372
ወያኔ ጥጋብ በወለደው እብሪቱ በማንአለብኝነት የህዝብን መብትና ነጻነት ረግጦ በአፈና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አለኝታየ በሚላቸው የፖሊስ፣ የደህንነትና ወታደራዊ ኃይሎች እስከ መጨረሻው አጠናክር ለመቀጠል የሚችል አድርጎ ያስባል። በዚህም ምክንያት እስካፍንጫው ባስታጠቀው ወታደር ብዛትና በነዋሪው ቁጥር ልክ ህዝብ መሃል ባሰማራው ሰላዮች የተገነባው የፍርሃት ግምብ የሚናድም መስሎ አይታየውም። 
     ሃቁ ግን በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተሰባሰቡ ወጣቶችም ሆኑ መላው አለም ላይ የሚገኙ በተለይም በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች እና ወያኔን በአራቱም የአገራችን ማዕዘናት ለመግጠም ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወያኔ ህዝባችንን ሊያስፈራራ የሚችልበትን ሁሉ በጣጥሰው ለመውጣት ምንም ችግር የሌለባቸው መሆኑን በትላንቱ  በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል  የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ግንባሩን ወክለው የመጡት እንግዳ እና áŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹ŤáŠ–á‰š በኩራት እና በቁርጠኝነት á‰°áŠ“áŒáˆ¨á‹‹áˆá˘
      በአገራችን ኢትዮጵያ á‹áˆľáŒĽ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው  ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የተገደዱት የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን በገንዘብ ለመርዳት ታስቦ የነበረውን ቀን በኖርዌይ የሚገኙ ጸረ ኢትዮጵያን የወያኔ ደጋፊ ጉጅሌዎች ለተወሰነ ሰዓታት ባደረጉት የተሳሳተ ወይንም ያልተገባ ውሸት á‰ á‹°áˆľá‰ł የተፍነከነኩበት በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያን ቁርጥ ልጆች ድል  á‰°áŒ áŠ“á‰‹áˆ
Norway G7 fundrise

ትላንት áˆ´á•ቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ።  á‰ áŒˆá‰˘ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። á‰ áˆ˜áŒ¨áˆ¨áˆťáˆ በኖርዌይ የምንገኝ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የምናስተላልፈው ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው።

፦ á‹ˆá‹ŤáŠ” ገንብቻለሁ ብሎ የሚኮፈስበትን የፍርሃት ግምብ ደርምሰው ለነጻነታቸው ሲሉ ውድ የህይወት ዋጋ ለመክፈል በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ዙሪያ መሰባሰባቸውን ይፋ ያደረጉ እነዚህ á‹ˆáŒŁá‰śá‰˝áŠ• በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች  á‹¨á‰°áŠáˆąáˆˆá‰ľáŠ• ክቡር አላማ ያደንቃል። በዚህም ምክንያት ለነጻነቱ ቀናኢ ለሆነው ለህዝባችን ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ወቅታዊነት ሁሉም እንዲረዳው እና በመላው ዓለም ላይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ  á‹¨á‰ áŠŠáˆ‰áŠ• አሰተዋጽኦ áŠĽáŠ•á‹˛á‹Ťá‹°áˆ­áŒ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ያሬድ ኤልያስ nome telemark

Sep 24, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ዋነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊና ዘላቂ ጥቅም ጠላት ወያኔ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ይህንን አባባል አንድ ተቃዋሚ ለተቃውሞ ያህል ወይም ስርዓቱን የሚጠላ አንድ ግለሰብ ስርአቱን ስለሚጠላዉ ብቻ እንደተናገረው አድርጎ አቃልሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከአሁኑ ቅጽበት ድረስ በሀገራችን ላይ የፈጸመውን ደባ በቅጡ ያላዩ ሰዎች ይህ አባባል የተጋነነ ይመስላቸው ይሆናል። ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ አገር የቆመችዉ በህዝቦቿ ታላቅነትና እንዲሁም ለታሪካቸው ባሳዩት ክብርና ብርታት ነዉ እንጂ እንደወያኔማ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ከወደቀ ሰንብቷል።
ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።
መገነጣጠል ግብ እንዲሆን በህገ መንግስት ደረጃ አንቀጽ ጽፎ ያስቀመጠው ወያኔ እሱ እንደሚለዉ ለብሔረሰቦች መብት አስቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ አልዘረፍ ካለችን በትነናት ብንሄድስ ከሚል አላማ መሆኑን ሌናጤን ይገባል። ከምር ለብሄረሰቦች መብት በመቆርቆር ቢሆን ኖሮ ከጠመንጃና ከፍጅት በፊት የብሄረሰቦችን መብትና ነጻነት አክብሮ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ይተዋቸዉ ነበር።።
ወያኔ ኢትዮጵያን የሚፈልጋት ለርሱና ለጋሻ ጃግሬዎቹ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሆና ስላገኛት ብቻ ነው። ሀገሪቱን እያለማሁ፣ እያሳደግኩ ነው የሚለው ዲስኩር ለተራ መደለያ እንኳን የማይሆን ውሸት ለተራበው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ያውቀዋል።
የሀገሪቱን ለም መሬት በሄክታር ባንድ ፓኮ ሲጋራ ዋጋ የሚቸረችረው ወያኔ እነዚህ ባእዳን በጎን የሚሰጡትን የሀገራችንን መሬት ዋጋ ኪሱ መክተቱን አረጋግጦ ነው። ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚነዛው የኬሚካል ማዳበሪያ በጥቂት አመታት ውስጥ የሀገሪቱን አፈር ድራሽ እንደሚያጠፋ ወያኔ የአዋቂዎች ምክር ሳይሰማ ስለቀረ አይደለም። በአጥፊ ስራው የቀጠለው መዝረፍ የሚችለዉን ንብረት ካጋበሰና ከዘረፈ በኋላ ነገ ኢትዮጵያ እንደአለ ባድማ ብትሆን ቅንጣት ስለማይሰማዉ ነዉ። ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአገሪቱ ወጣትና የተማረ የሰዉ ኃይል እንደ ጎርፍ ከአገሪቱ እየጎረፈ ሲወጣ ይቆረቆር ነበር። ወያኔ የተማረ ሰው ቢሰደድ፣ ዜጎች ቢራቡና በገዛ አገራቸዉ ቢዋረዱ ጉዳዩ አይደለም። በሰላማዊና ህገመንግስታዊ መንገድ ጥያቄ ያነሳን ዜጋ ሁሉ እንደአውሬ የሚቀጠቅጠውና ወህኒ ቤት የሚያጉረው ይህ በደል ነገ በሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና ላይ የሚያመጣውን መዘዝ አጥቶት አይደለም። የአገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጉዳዩ ስላልሆነ እንጂ።
የኢትዮጵያን ብሄር ቤሄረሰቦች የሚያይዟቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድነት ክሮች እያንቋሸሸና እንደሌሉ እየሰበከ በሚለያዩንን ጥቃቅን ውጭያዊ የቋንቋና የዘር ግንዶች አጉልቶ የሚያሳየን አገራችንንና ህዝቧን እንደ አንድ ሀገር ሳይሆን እንደጊዚያዊ የዝርፊያ ቀጠና ስለሚመለከት ብቻ ነው።
ወያኔና ሎሌዎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላቶቹ ናቸው እያሉ አንዴ የፈረሰችዉ ሶማሊያን፤ ሌላ ጊዜ ወደ ኤርትራና ግብጽ ጣቱን የሚጠነቁሉት አይናችንን ከወያኔ ላይ እንድናነሳ ነዉ እንጂ ከወያኔ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላት የለም። ወያኔ በአካል እኛን ከሚመስሉ ኢትዮጵያውያን መሃል ይውጣ እንጂ፣ በተግባር ከቀን ጅብ ያልተናነሰ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ራሱ የጻፈውን ህግ ሲጥስ ለምን ብለን የምንገረም አለን። ወያኔ ሕግና ሕገ-መንግስት፣ ለአገራቸዉ የሚቆረቆሩ ምሁራንን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ የሚታመን ሰራዊት፣ ለህግ ብቻ የሚሰራ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ዘላቂ ተቋማት እንዳይኖሩን የሚያደርገውና ያሉትንም የሚያፈርሰው ለኢትዮጵያ ብሄራዊና ዘላቂ ጥቅም ምንም ደንታ ስለሌለዉ ነዉመሆኑን የሚዘነጋ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ የዋህ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።
ስለዚህም እንላለን እኛ የግንቦት 7 ልጆችህ ሀገርህ ትውልድ ተሻግራ እንድትቀጥል አንተም የምትኮራባት ዜጋ እንድትሆናት የምትሻ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ሀገርህን ከወያኔ የቀን ጅቦችና ወራሪዎች አድን። አጎንብሰህ ሳይሆን ቀና ብለህ የምትሄድባት ሀገር እንድትኖርህ የምትሻ ሁሉ ለማይቀረው የጀመርነውን የአርበኝነትና የነጻነት ትግል ጉዞ ተቀላቀለን። እኛ የተባበርን እለት አብረን የተነሳንና በቃ ያልን እለት ታሪካዊቷ ሀገራችንና ታላቁ ሕዝባችን ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅማቸው ይከበራል።
አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Sep 19, 2013

ጉዲፈቻ የሰው ልጆች ንግድ ‹‹ከቤተሰቤ ተሰርቄ ነው የተወሰድኩት››

 á‰łáˆŞáŠł ለማ፣ በጉዲፈቻ አሜሪካ የተወሰደችው ጉብል
‹‹ከቤተሰቤ ተሰርቄ ነው የተወሰድኩት››በአሁን ጊዜ በዓለም ላይ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ከሚያስነሳት ጉዳይ አንዱ ጉዲፈቻ ነው፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች አሳዳጊ የሌላቸው ተብለው የሚታሰቡ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ወደ ተለያዩ አገሮች ይሄዳሉ፡፡ ‹‹የተሻለ ሕይወት›› ይኖራቸዋልም በሚል እሳቤ ቤተሰብ ያላቸውን ሕፃናትም ሕገወጥ በሆነ ሰርቆ መስጠት እንዲሁም በደላሎች አማካይነት የሚሠሩ ሥራዎችም እንዳሉበት በርካታ ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሲኤንኤን መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ያወጣው ይህንኑ አስከፊ እውነታ የሚመሰክር ነው፡፡
ታሪኳ ለማ የ19 ዓመት ዕድሜ ያላት ወጣት ናት፡፡ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ነበር ከሁለት ታናናሽ እህቶቿ ጋር ትምህርታቸውን በአሜሪካ እንደሚከታተሉና  á‰ľáˆáˆ…áˆ­á‰ľ በማይኖርበት በማንኛውም የዕረፍት ጊዜ ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ እየመጡ ቤተሰቦቻቸውን እንደሚያዩ ቃል ተገብቶላቸው እናት አገራቸውን የለቀቁት፡፡ 
ዛሬ ማይኒ የምትኖረው ታሪኳ ለማ የኮሌጅ ተማሪ ስትሆን፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ የመሆን ህልም አላት፡፡ በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ ተወስደው ስላለፉት የሕይወት ውጣ ውረድ እንደሚከተለው ተርካዋለች፡፡ 
‹‹የተሸጥኩት አሥራ ሦስት ዓመቴ ላይ ነበር፡፡ ከቤተሰቤ ተሰርቄ የተወሰድኩት፡፡ እኔና እህቶቼን  áˆˆá‰ľáˆáˆ…áˆ­á‰ľ ወደ አሜሪካ ሊልከን እንደሚገባ አባቴን ያሳመኑት የአባቴ ጓደኞች ነበሩ፡፡ እኤአ በ2006 በተገባልን የሐሰት ቃል ኪዳን ወላጅ አባቴን አሞኝተው እንድንሄድ ተገደድን፡፡ ይህንን የሚያደርጉት የአባቴ ጓደኞች በሙስና እጃቸው የተጨማለቀና አጭበርባሪ የጉዲፈቻ ወኪል ውስጥ የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ይህም ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ 
‹‹አባቴም ሆነ እኛ ሾለ ጉዲፈቻ የምናውቀው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ወላጅ አባታችን የላከን ለትምህርት፣ እኛም ለመማር እንደመጣን ነበር የምናውቀው፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሹን ሆኖ ነበር ያገኘነው፡፡ ዋሽተውናል፤ የዋሹት ግን እኛን ብቻ ሳይሆን በጉዲፈቻ የወሰዱንን አሳዳጊ ቤተሰቦቻችንን ጭምር ነበር፡፡  á‹Ťáˆ˜áŒŁáŠ•áˆ‹á‰˝áˆ ወላጆቻቸውን በኤድስ ያጡ ሦስት ሕፃናትን ነው፤ ትልቋ ዘጠኝ ዓመቷ ነው ብለው ነበር ሴራውን ያቀነባበሩት፡፡ ይሁንና እውነታው ግን እኔ የአሥራ ሦስት ዓመት ታዳጊ ነበርኩ፡፡ የቤተሰቤም የበኩር ልጅ ነኝ፡፡ ታናሾቼ የአሥራ አንድና የስድስት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ታዳጊዎች ነበሩ፡፡ 
‹‹አዲሶቹ ‹ቤተሰቦቻችን› ስማችንን ቀየሩትና በአፍ መፍቻ ቋንቋችን በአማርኛና በወላይትኛ ማውራት እንደማንችልና ካወራንም ቅጣት እንደሚጠብቀን አስጠነቀቁን፡፡ እናም በስተመጨረሻ አፍ በፈታንበት ቋንቋ መናገር ተሳነን፤ እስከነ አካቴውም ረሳነው፡፡ 
‹‹በጣም ልጅ ነበርኩኝ፡፡ ከዚህ ካለሁበት የእሥር ቤት ሕይወት ጠፍቼ ብወጣ ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ተመልሼ የምገባ ይመስለኝ ነበር፡፡ እነኚህ ቀጣፊዎች ከትውልድ አገሬ፣ ከባህሌና ከቤተሰቤ እንደነጠሉኝ ሳስበው ውስጤ በሐዘንና በምሬት ይሞላል፡፡ 
‹‹ከስምንት ወራት በኋላ ከእህቶቼ ተነጥዬ ወደ ሌላ ቤት እንድጓዝ ተደረግኩኝ፡፡ አዲሱ መኖሪያዬ የተደረገው ከአሳዳጊ እናቴ ቤተሰቦች ጋር ነበር፡፡ ያም ወደ መካከለኛው ምዕራብ ነበር፡፡ እህቶቼን ለመጐብኘት የታደልኩት በጣት ለሚቆጠሩ ጊዜያት ነበር፡፡ አሁን ባለሁበት አገር መኖር ይከብዳል፡፡ ከአገሬ ኢትዮጵያና ከእህቶቼ ተነጥያለሁ፡፡ አጋጣሚዎች ክፉ ቢሆኑብኝም እጅ መስጠት አልፈለግኩም፡፡ ያለኝን አቅም ሁሉ አሰባስቤ ከአገር ውጪ በሚደረግ ጉዲፈቻ ምን ዓይነት ብልሹ አሠራርና የሰው ልጆች ንግድ እየተካሄደ መሆኑን  áˆˆá‹“ለም ሕዝብ ለማሳወቅ ወሰንኩ፡፡ 
‹‹ከአገር ውጪ የሚደረግ ጉዲፈቻን የሚያበረታቱ አካላት 151 ሚሊዮን ወላጅ የሌላቸው ታዳጊዎች እንዳሉ ይጠቁማሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱንም ወላጅ ያጡ ሕፃናት 18 ሚሊዮን ብቻ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ከእናት ወይም ከአባት ጋር የሚኖሩ ናቸው፡፡ ይህንንም ወላጅ የሌለው ብሎ መጥራት እጅግ የሚከብድ ነው፡፡ እኔ ወላጅ አልባ አይደለሁም፡፡ በእርግጥ እናቴ ሞታለች፤ ነገር ግን አባት አለኝ፣ እህቶች ወንድሞች እናም ሌሎች የሚወዱኝና የሚናፍቁኝ ቤተሰቦች አሉኝ፡፡ 
‹‹ውሸቱም  áˆ†áА ማጭበርበሩ ለገንዘብ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ዛሬ ዛሬ ለገንዘብ ሲሉ ወላጅ የሌላቸው ሕፃናት መፍጠር ጀምረዋል፡፡ ለዚህም የገንዘብ ክፍያ አላቸው፡፡ ክፍያውም ከአገር አገር ይለያያል፡፡ ከፍ ዝቅ ይላል፣ ነጭ ሕፃን በጉዲፈቻ ለመውሰድ የሚከፍሉት ክፍያ ከፍ ያለ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የጥቁር ዝቅ ያለ ነው፡፡ ተመልከቱ ምን ያህል አስከፊ ሕይወት እንደሆነ፡፡ 
‹‹ዛሬ ውጣ ውረዶች ጠንካራ አድርገውኛል፡፡ ይህም በሕይወቴ አንድ ጥሩ ነገር እንድሠራ አነሳስቶኛል፡፡ በጉዲፈቻ ዙሪያ የሚሠሩ ተቋማት እየሠሩ ያሉትን ንግድ የሚያጋልጥ መጽሐፍ በመጻፍ ላይ እገኛለሁ፡፡ ወደ አገሬም ለመመለስ የሚበቃኝን ገንዘብ እያጠራቀምኩ ነው፡፡ በቅርቡም ወደ ፍርድ ቤት በመሄድም ትክክለኛ ስሜን ለማግኘት እሞክራለሁ፡፡››

Sep 15, 2013

G7 POPULAR FORCE FUNDRASING EVENT OSLO NORWAY 28 SEPTMBER 2013


Ginbot 7 Popular Force fundraising event in oslo norway September,28, 2013. During this event representatives of the G7PF leadership will be present and the program of the event comprises, discussions, fundraising and entertaining activities Freedom,
justice and democracy to all Ethiopians!

Sep 14, 2013

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

  
ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
  1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
  2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
  3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
  4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
  5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
  6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
  7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
  8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤
  1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
  2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
  3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Sep 9, 2013

የሰው ለሰዉ አስናቀ - 18ሺ ብር ከፈለ!


የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡ አበበ ባልቻ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊሔድ የቻለው ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሸገር ሕንፃ ስር በሚገኘው ዩጎቪያ ክለብ በመዝናናት ላይ ነበር፡፡ በቦታው ለእረፍት ከኖርዌይ የመጣውና በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኖርዌያዊ የሆነው ሐሰን መሐመድና የወንድሙ እጮኛ እየተዝናኑ ነበር፡፡ ከሐሰን ጋር የነበረችው ሴትም አበበ አስናቀን ሆኖ በሚጫወትበት የሰው ለሰው ድራማ ታደንቀው ስለነበር ወደ እሱ በመሄድ አብራው ፎቶ ለመነሳት ትጠይቃለች፡፡ አበበም ፈቃደኛ በመሆን አብሯቸው ይነሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መበሳጨት ይጀምራል፡፡ ከዚያም ወደ ሰዎቹ በመሄድ ከሐሰን ላይ ፎቶ ያነሳበትን አይፎን 5 ይቀበለውና መሬት ላይ በመጣል በእግሩ ይሰባብረዋል፡፡ ከልጁም ጋር ለመደባደብ መተናነቅ ሲጀምር የክለቡ ጠባቂዎች ይገላግሏቸዋል፡፡
ሞባይሉ የተሰበረበት ሐሰን አበበን እንዲሁ ሊለቀው ስላልፈለገ ወደ ሕግ ሊወስደው ሲጥር እሱ ባልጠበቀው ሁኔታ ጠባቂዎቹ አበበን ከቤቱ ያወጡታል፡፡ የአበበን መውጣት ያወቀው ሐሰን ግን ከአበበ ጋር አብሮ ይዝናና የነበረውን አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን በመያዝ “አንተ ስለሆንክ ያስመለጥከኝ አንተን ወደ ሕግ እወስድሃለሁ” በማለት ይዞት አቅራቢያው ወደሚገኝ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ይሄዳሉ፡፡ ጣቢያ ደርሰውም ጉዳዩን ያስረዳሉ፡፡ ስለ ሁኔታ የተጠየቀው ሰለሞንም ድርጊቱ መፈፀሙንና በማግስቱ አበበን እንደሚያቀርበው ተናግሮ የአበበንም ስልክ ለፖሊሶች በመስጠት ይለቀቃል፡፡
በማግስቱም ከሳሾች በንብረት ማጉደል ክስ መስርተው ለአበበ በወኪሉ አማካኝነት መጥሪያ በመስጠት ይመለሳሉ፡፡ አበበም ፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ ሁኔታ መፈፀሙን እንደማያስታወስ ግን ምናልባት በትከሻው ገፍቶት ወድቆ ሊሆን እንደሚችል ይናገራል፡፡ አቃቤ ሕግና ፖሊስም እነ አበበ ጉዳዩን በሰላም እንዲፈቱት በማግባባታቸው አበበ ለሰበረው ሞባይል 18 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እንዲከፍል በመወሰኑ ተያይዘው ወደ ቢሮው በመሄድ ቼክ ፈርሞ ለሐሰን በመስጠቱና ይቅርታ በመጠየቁ ችግሩ ሊፈታ ችሏል፡፡

Sep 4, 2013

በሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደረሰው ወያኔያዊ ጥቃት ተቆጭተናል!!! ወጣቶች መንገዳችሁን እንድትመርምሩ እንመክራለን!!!


ነሐሴ 25 ና 26 ቀን 2005 ዓ. ም. ወያኔ በአብዛኛው በወጣቶች በተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ላይ ያደረሰው ወንበዴያዊ የመብት ጥሰት አሳዝኖናል፤ አስቆጭቶናልም። ይህንን ጥቃት አጥብቀን እንቃወማለን። ከወራት በፊት በይፋ አስታውቀውና ደጋፊዎቻቸውን በይፋ ጠርተው ለሰላማዊ ተቃውሞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ወጣቶችን በቅልብ ኮማንዶዎች ማስደብደብ ተራ የመንደር ወንበዴ እንኳን የማይፈጽመው ወራዳ ተግባር ነው፤ ወያኔ ግን አድርጎታል።
የመፈክር መፃፊያ ቡርሾችና ማርከሮች ካልሆነ በስተቀር ራሳቸውን መከላከያ ዱላ እንኳን ያልያዙ ወጣቶችን በጠመንጃዎች ሰደፍ፣ በጁዶና በካራቴ ተደብድበዋል። ልጃገረዶች ጤንነታቸውን ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን በሚነካ መንገድ እተሰደቡና እየተደበደቡ ጭቃ ውስጥ እንዲከባለሉ ተደርገዋል። ጋጠወጦቹ የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ከወያኔ ሹማምንት ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተላከውን መልዕክት በቃልም በተግባርም አድርሰዋል።
የመልዕክቱ ይዘት ባጭሩ የሚከተለው ነው።
ሞተን አጥንታችንን ከስክሰን ያገኘነው ሥልጣን ትንፋሻችን እያለ ከእጃችን አይወጣም። እንኳንስ በሰላማዊ ትግል የመንግሥት ሥልጣንን ልትይዙ ቀርቶ፤ እኛ ሳንፈቅድላችሁ እደጅም አትወጡም። እንገዛችኋለን!!! እንረግጣችኋለን!!! ሕግ አያግደንም። እኛ ራሳችን ሕግ ነን። ምን ታመጣላችሁ? ምን አቅም አላችሁ?
ይህ መልዕክት ለሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላት በዱላና እርግጫ ታጅቦ ቃል በቃል ተነግሯቸዋል።
ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። ዛሬ ጥያቄው ከመቼውም በላይ አፍጦ መጥቷል። ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ? ፍርዱን ለእናነተ እንተዋለን።
ወያኔ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የላከው መልክት ለፓርቲው አባላት ብቻ የተላከ አይደለም። መልዕክቱ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ምላሽህ ምንድነው? እስከ መቼ የወያኔን እብሪት እንታገሳለን? ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው?
ግንቦት 7፤ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁለገብ የትግል ስልትን ሲመርጥ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት በማመን ሆኖም ግን ብቻውን የትም እንደማያደርሰን በመገንዘብ ነው። ስለዚህም ሁለቱም የትግል ስልቶች ተደጋግፈው መሄድ አለባቸው ይላል። ግንቦት 7 ይህንን የትግል ስልት የቀየሰው በወያኔ ባህሪ ላይ ተመሥርቶ ነው። የወያኔ ዓይነቱ እብሪተኛ ሥልጣን በያዘበት አገር ሰላማዊ ትግል ከአመጽ ትግል በላይ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ሰላማዊ ትግልና የአመጽ ትግል ውሃና ዘይት ወይም እሳትና ጭድ አይደሉም። እንዲያውም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እና ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ አንዱ ያለሌላኛው ዋጋ የለውም።
ስለሆነም ከደረሰባችሁ ወንበዴያዊ ጥቃት ትምህርት በመውሰድ፤ ወደፊት ደግሞ ከዚህ የባሰ ሊመጣ እንደሚችል በመገንዘብ፤ ሁኔታዎችን መርምራችሁ በግል የስትራቴጂ ለውጥ ለማድረግ የወሰናችሁ ወጣቶች ግንቦት 7ን ማግኘት አይቸግራችሁም። ሆኖም ጊዜ የለም። በወያኔ ዓይን እና በወያኔ ፍርድ ቤት እይታ መብቱን የጠየቀ ሁሉ የግንቦት 7 አባል ነውና የምታጡት ነገር የለም። ዛሬውኑ ወስኑ!!!!
ግንቦት 7፤ በዚሁ እለት ክርስቲያኑንና ሙስሊሙን ኢትዮጵያዊያንን ለማቃቃር ወያኔ የጠራውን ሰልፍ ጥበብ በተሞላበት ስልት ላከሸፈው “የድምፃችን ይሰማ” አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Total Pageviews

110935

Translate