ኢሳት ዜና:- በአየር መንገዱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በኢህአዴግ አባሉ ስራ አስኪያጅ በአቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ በተጠባባቂው ስራ አስኪያጅ በአቶ ኢሳያስ ወልደማርያም እና በኦዲተሩ በአቶ ዋሱ ዘለለው አነሳሽነት ነባር ሰራተኞች ከስራ እየተቀነሱ በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት እየተተኩ ነው። በቅርቡ 36 የትኬት ሽያጭ ሰራተኞች እና 14 ኤጀንቶች ከስራ ተባረው በፎረሙ አባላት ተተክተዋል። ከእነዚህም መካከል 5 የትኬት ሰራተኞች እና 14 በተለያዩ ሀላፊነት ላይ ያሉ የድርጅቱ ሰራተኞች በሰበብ አስባቡ ወደ እስር ቤት እንዲላኩ መደረጉን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል ኢማም ያሲን፣ ሳሙኤል እንዳለ፣ ቤተልሄም ጌታቸው፣ ኤደን በየነ፣ የአመቱ ምርጥ የትኬት ሽያጭ ኤጀንት ተብሎ የተሸለመው ይርጋለም ታደሰ፣ ቤተልሄም ተፈራ፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛዊት ኤፍሬም፣ አንተንሳይ አማረ፣ ሰለሞን በቀለ ይገኙበታል።
ከታሰሩት ሰራተኞች መካከል ደግሞ ሳሙኤል እንዳለ፣ አማኑኤል ጸጋው፣ ብርሀኑ ሰለሞን፣ እኑ ገብረእግዚአብሄር፣ አይዳ ዘልኡል፣ እና በረከት ግርማ የሚገኙበት ሲሆን፣ በረከት ግርማ ስራውን ለቆ በቱርክ አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ በማገልገል ላይ ሳለ የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር አውለውታል።
ከስራ ከታገዱት መካከል ትንግርት ደምሴ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ሀይማኖት ንጉሴ፣ ሳምራዊት ገረመው፣ ሜላት አስራት፣ አማኑኤል በልስቲ፣ አማኑኤል ነጋሽ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤ፣ አንዱአለም ግርማ ይገኙበታል።
ከተባረሩት፣ ከታገዱትና ከታሰሩት መካከል ከ10 እሰከ 30 አመታት የሰሩ ነባር አየር መንገዱ ሰራተኞች የሚገኙበት ሲሆን፣ የተባረሩበት ወይም የታገዱበት ምክንያትም የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ተጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ሰራተኞች ይገልጻሉ።
አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኢትዮጵያን አየር መንገድ በስራ አስኪያጅነት ለመምራት ስልጣኑን ከተረከቡ በሁዋላ፣ በተለያዩ መንገዶች የኢህአዴግ የወጣት አደረጃጀት አባላት በድርጅቱ ውስጥ በስፋት እንዲቀጠሩ አድርገዋል።
እቃዎችን በማውረድና በመስቀል ስራ ላይ የስሩ የነበሩ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተባረው በኢህአዴግ ወጣት ፎረም አባላት እንዲተኩ ማድረጋቸውን ከወር በፊት መዘገባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment