(ዘ-ሐበሻ) የደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ
ለዋሊያዎች መሸኛ የሚሆን የራት ምሽት ከትግራይ
ልማት ማህበር ጋር በመተባበር አዘጋጀ። በዚህ የራት
ግብዣ ላይ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ብቻ እንዲገኙ
ሲደረግ በተለይ ለብሔራዊ ቡድኑ ደማቅ አቀባበል
ለማድረግ ከማስተባበር አንስቶ በርከት ያሉ ነገሮችን
ያከናወኑት የቤተ ኢትዮጵያውያን ማህበርና ሌሎችም
ሃገር ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሳይጋበዙ
ቀርተዋል።
ዛሬ ማምሻውን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ
ባዘጋጀው የመሸኛ የራት ግብዣ ላይ በተለይ
ኢምባሲው ለኢትዮጵያ ጉዳይ የሕወሓት ደጋፊዎችንና
የትግራይ ልማት ማህበር አባላትን ብቻ ተቆርቋሪ
አድርጎ ማቅረቡና ሌሎቹን ገሸሽ ማድረጉ በስፍራው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እንዳስቆጣ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች
አስታውቀዋል። ለደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል በተለይም በቡርኪና ፋሶው እና በናይጄሪያው
ጨዋታ ላይ ስርዓቱ አሁን የሚጠቀምበትንና በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀዩ መሃል የቀስተዳመና ምስል የሌለበትን ባንዲራ
የያዙ ሰዎች በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጥለው እንዲገቡ እንዲፈተሹ አስደርጓል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰበት
የኢትዮጵያ ኢምባሲ በስታዲየሙ ውስጥ ተሰቅለው የነበሩት የሞአ አንበሳ ምስል ያለበት ባንዲራና ምንም ከመሃሉ
ያልገባለት ንጹህ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀዩን ባንዲራዎችን ማስነሳቱ ይታወሳል። በዚህም ድርጊት ደቡብ አፍሪካ ድረስ
የሄዱ የብሔራዊ ቡድናችን ለመደገፍ የሄዱ ወገኖች ሁሉ ማዘናቸውን በየማህበራዊ ድረገጾች ጭምር ስሜታቸውን
በመግለጽ ላይ ናቸው።
ለብሄራዊ ቡድኑ ድጋፍ ሲሰጡ የቆዩት ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ቡድኑን ወያኔዎች ብቻ ለመሸኘት መወሰናቸው
“ይህች ሃገር የኛ እንጂ የናንተ አይደለችም” እንደማለትም ጭምር ነው በሚል በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሟቸውን
በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment