ለአመታት የፒያሳ ግርማ ሆነው የቆዩትእምቢ ባዩ አርበኛው አቡን ከነገ በስተያ ሀሙስ “ለቀላል ባቡር መንገድ ዝርጋታ” ተብሎ ሊነሱ መሆኑን ሸገር ራዲዮ ጣቢያ ነገረን፡፡
ቀጥሎ የኔ ብስጭታዊ ወሬ ይቀጥላል፤
…አንድ የተለከፈ መንገድ ቀያሽ ካላጣው ቦታ ለቅኝ ገዢዎች አልንበረከክም ብለው መስዋት የሆኑትን አባትን ሀውልት “ካላፈረስኩ ባቡር መንገድ መዘርጋት አልችልም” ብሎ በቀየሰው መሰረት የአቡኑ ሀውልት መፍረስ እርግጥ ሆኗል፡፡
በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ “አቡን” ሆነው በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ “ለተሰዉት” “አቡነ” መለስ ሀውልት እየተገነባ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የእውነተኛው ሰማህት እና የእውነተኛው አቡን ሀውልት ይፍረስ መባሉ ብዙዎችን ሲያበሳጭ ሰንብቷል፡፡
አፍራሽ ግብረ ሀይሉ ሀውልቱ ከፈረሰ በኋላ በቦታው ተመልሶ ይተከላል ቢልም ንግግሩን በጥርጣሬ የሚያዩት ብዙዎች ናቸው ከብዙዎቹ ውስጥ አንዱም እኔ ነኝ!
ነገሮች ግድ በሚሏቸው ሀገራት መንገድ በሚቀየስ ጊዜ ታሪካዊ ሀውልቶችን ይቅርና የዕድሜ ባለፀጋ ዛፎችን እንኳ ላለመጉዳት ጥረት ሲደረግ አይተን አቡነ ጴጥሮስን ካላፈርስኩ መንገድ አልሰራም የሚለው መሀንዲስ በተለይ ጣሊያናዊ ካልሆነ፤ ከአቡኑ ጋር ምን እንዳቀያየመው ወደፊት የሚጣራ ይሆናል፡፡
እኔ ደግሞ ረስተውት መስሎኝ ነበርኮ… ለካስ ሰዎቻችን መገንባት እንጂ ማፈረስ አይረሱምና!
ለማስታወስ ያህል፤
ባለፈው ወቅት በጣሊያን የግራዚያኔን ሀውልት መሰራት ተቃወሙ ሰልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውን በገዛ መንግስታቸው ምን ሲደረግ ግራዚያኔን ተቃወማችሁ… ተብለው ታስረው ነበር፡፡ ይሄንን አስታውሰን የአቡኑን መፍረስ አይተን ብስጭት ይነሰን….!?
No comments:
Post a Comment