Pages

Apr 14, 2013

የኢትዮጵያ አደገኛ የፖከቲካና ማህባዊ ጉዞ ያሳሰባቸዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እራሰቸዉን በህቡዕ እያደራጁ መሆኑ ተነገረ


ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ባለፉት ሃያ አንድ አመታት የተከተላቸዉ የፖለቲካ፤የኤኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ያደረሰዉ ጥፋትና አሁንም አገሪቱ የምትጓዝበት አደገኛ አቅጣጫ ያሳሰባቸዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እራሳቸዉን በህቡዕ እያደራጁ መሆኑን አንድ ምስራቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኘዉ የዚሁ የህቡዕ ድርጅት ህዋስ መሪ ከግንቦት ሰባት ድምጽ ጋር ባደረጉት የስልክ ምልልስ ገለጹ። እኚህ ለደህንነታቸዉ በመስጋት ቃለምልልሳቸዉ በሬድዮ እንዳይደተላለፍ የጠየቁን ከፈተኛ የጦር መኮንን በህቡዕ የመደራጀቱ እንቅስቃሴ ሠራዊቱ በብዛት በሚገኝባቸዉ ቦታዎች ሁሉ እየተካሄደ ሲሆን በቅርብ ግዜ ዉስጥ ከሌሎች ለለዉጥ ከሚታገሉ ሀይሎች ጋር በመሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጅምሩ ተናግረዋል።
የዚህ “አገርህን አድን” በሚል ስያሜ የሚጠራዉ አገር ወዳድ ቡድን አባላት የወያኔ ደህንነት የሚያደርግባቻዉን የሃያ አራት ሰአት ክትትል ጥሰዉ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰባሰቡት ከአራት አመታት በፊት ሲሆን ያሰባሰባቸዉም ወያኔ ሠራዊቱ ዉስጥ የሚከተለዉን ጭፍን የዘረኝነት ፖሊሲ ለመቋቋም እንደሆነ ታዉቋል። ሆኖም ይህ በ“አገርህን አድን” ቡድን ስር በመደራጀት ላይ የሚገኘዉ ሠራዊት አላማ የሠራዊቱን መብትና ነጻነት አስጠብቆ ወደ ሠፈሩ መመለስ ሳይሆን የቡድኑ ተቀዳሚ አላማ ለህዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ኢትጵያንና ህዝቧን ከወያኔ ዘረኝነትና ከፋፍለህ ግዛዉ ፓሊሱ ማዳን ነዉ ሲሉ የቡድኑ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
የወያኔ አገዛዝ በአማራዉ ወገናችን ላይ የሚያደርሰዉን ጥቃት በቅርብ እየተከታሉት እንደሆነ የተናገሩት እኚሁ ቃል አቀባይ እንደዚህ አይነቱን የማን አለብኝነት ወንጀልና ባጠቃላይ የወያኔ ዘረኞች በግልጽ የሚያካሄዱት መብት ረገጣ፤ግድያ፤ዝርፍያና የአገርን ብሔራዊ ጥቅም ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት ወያኔ አስካልተወገደ ድረስ የማይቆም በመሆኑ ያለን አማራጭ በቻልነዉና በምናዉቀዉ መንገድ ሁሉ ወያኔን ለማስወገድ መታገል ዋናዉ አላማችን ነዉ ብለዋል።
በመጫረሻም ከነማን ጋር ትሰራላችሁ ተብሎ የተጠየቁትን ጥያቄ ሲመልሱ ዛሬ አገራችን ለመዉደቅ በመንገዳገድ ላይ በምትገኝበት ወቅት ያለን አማራጭ አልገዛም ካለና የእኩሎች አገር የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባት ፍላጎቱና ቆራጥነቱ ካላቸዉ ወገኖች ጋር ሁሉ አብረን እንታገላለን ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አያሌ ኢትዮጵአዉያን ወያኔን ለመታገል መሳሪያ ካነሱ ወገኖች ጋር በየቀኑ እየተቀላቀሉ ስለሆነ የኛም አላማ የትግል ስልትና የተለየ የትግል ቦታ ሳንመርጥ ወያኔን ያዋጣናል ባልነዉ ስልትና ይመቸናል ባልነዉ ቦታ ሁሉ እስከእለተ ሞቱ እንታገለዋለን ብለዋል።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate