skip to main |
skip to sidebar
“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” – ከአቤ ቶኪቻው
አቶ በረከት
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡ አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴትነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!አስታውሳለሁ፤ “አባይ ይገደብ በቃ” ብለው ጠቅላዩ የወሰኑት ከሁለት አመት በፊት “በቃ” በሚል ሀይለ ቃል …ኢህአዴግይበቃዋል ግንቦት ሃያን ዘንድሮ ለመጨረሻ ጊዜ እናከብራለን ከዛም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተን በዛው እንቀራለን፡፡ ኢህአዴግእስካልወረደ ድረስም እቤታችን አንገባም…. የሚል እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ በኩል ተጀምሮ የነበረ ጊዜ ነው፡፡በዚህ በ”በቃ” ጦስ እነ ርዮት አለሙ እነ ውብሸት ታዬ እነ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር እነ ሂሩት ክፍሌ ወድያው ለእስርሲዳረጉ ቀስ በቀስ ደግሞ ሌሎችም ለቃሊቲ እና ለቂሊጦ ተዳርገዋል፡፡ (በተለይ የነዚህ ወዳጆቼን ፍርድ ሂደት ስከታተል ነበር እናአጋነንክ ቢሉኝም ባይሉኝም የአቃቤ ህግ ማስረጃ “በቃ የሚለውን የፌስ ቡክ እና የአደባባይ እንቅስቃሴ ትኩር ብላችሁአይታችኋል” የሚል ነበር)እንቅስቃሴው በፌስ ቡክ ተጀምሮ በየአደባባዩም “በቃ” የሚል ሃይለቃል በመፃፍ ተሟሙቆ የቀጠለ ነበር፡፡ በርካቶችም ግንቦትሃያ መስቀል አደባባይ የሚፈጠረውን ተዓምር እያሰቡ አንድም ደስታ አንድም ፍርሃት ሲፈራረቅባቸው አንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ይሄኔ አቶ መለስ ፈርሸው ዘየዱ፤ (ሁል ጊዜ ቁጭ ብለው አሰቡ… እያልንኮ ፍራሽ የሌላቸው አስመሰልናቸው… “ፈርቸው” ማለትፍራሽ ዘርግተው እጅግ በተመስጦ ማሰብ ማለት ነው…) አስበው አስበውም፤ “ለምን አባይን አንገድበውም…” አሉ እርሳቸውብለው እምቢ… እንዴት… ለምን… በምን… አይባልምና እሺ እሺ ተብሎ ተጀመረ፡፡ የዛን ጊዜውን ግንቦት ሃያም መንግስታችንለአባይ ግድብ ድጋፍ ሰልፍ ውጡልኝ፡፡ አለ… በዛውም የህዝቡ የተቃውሞ ሃሳብ ተገደበ፡፡የአቶ መለስን ብልጠት በመኮረጅ ፈተናዎች ይታለፋሉ ብለው የሚያምኑት አቶ በረከት ደግሞ ዛሬ እነሆ በግንቦት ሃያው አባይወንዝን የማስቀየስ ስራ እነደሚሰራ በቴሌቪዥናቸው ብቅ ብለው ነገሩን፡፡ጥሩ ኮርጀዋል…! አኮራረጃቸው ስም ሁሉ ሳይቀር እንደሚቀዳ አይነት ኮራጅ ነው፡፡ህዝቡ ይህንን ዜና ሲሰማ ምን አላቸው… የሚለውን ቤት ለቤት ሄደን መጠየቅ ብንችል ጥሩ ነበር፡፡ መጠየቅ ባንችል ግንመጠርጠር እንችላለን እና አንዲህ እንጠረጥራለን፤“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” ሳይላቸው አይቀርም፡፡
No comments:
Post a Comment