ሰላም ገረመው
ፒያሳ በሚገኘው ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ክሊኒክ አካባቢ በቋሚነት የሚያንዣብቡት ደላሎች ወደክሊኒኩ የሚያመሩ የመሰሏቸውን ወጣት እንስቶች አያሳልፉም “ክሊኒኩ ተዘግቷል፤ ወዴት ናችሁ?” በማለት በጥያቄ ጣድፋሉ፡፡ ከቀናቸውና የሚያነጋግራቸው ካገኙ የክሊኒኩ ዋና ዶክተር የግሉን ክሊኒክ ስለከፈተ እዛ ልውሠድሽ” በማለት ማግባባት ይጀምራሉ፡፡ አሁንም ከተሳካላቸው (በአብዛኛው ይሳካላቸዋል) አገልግሎት ፈላጊዋን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ የሚካሄድበት ቦታ (መንደር ውስጥ) ይወስዳሉ፡፡ በዚህ ሰዓት ደላሎቹ የሚያሳዩት ትህትናና ሽቁጥቁጥነት ማንኛዋም ሴት ለክፉ አደጋ ወደሚዳርጋት ሥፍራ ይወስዱኛል ብላ እንዳታስብ ያደርጋታል፡፡ ፅንስ ማቋረጥ የሚፈፀምበት ቦታ ከወሰዳት በኋላም ምናልባት በክፍያ ላትስማማ ትችላለች፡፡ ይኼኔ ደላላው መሀል በመግባት ያደራድራል፡፡ ይሄ ደግሞ የደላላውን የኮሚሽን ክፍያ ይጨምርለታል፡፡ ደላላው ሁሉን ደማምሮ ኮሚሽኑን ተቀበለ በኋላ እብስ ይላል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ክፉና ደግ ደግሞ ገባሁ፡፡ ደላላውም ተከትሎኝ ገባ፡፡ የሃኪሙ ጭ ቀለም የተቀባ የሚመስል ጠረጴዛ ለዓይን እንኳን ይዘገንናል፡፡ መሀሉ የተቦረቸፈ ስትሬቸር ግድግዳው ጥግ ይታየኛል፡፡ የእርግዝና ማዳመጫ መሳሪያ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡ በቃ እኒሁ ናቸው የህክምና ቁሳቁሶቹ - ሌላ ነገር የለም፡፡ “ስንት ወርሽ ነው?” ሃኪሙ ጠየቀኝ“አራት ወር ገደማ ይሆነኛል” አልኩት- የውሸቴን መሆኑ ንዳይታወቅብኝ በመጠንቀቅ ችግር የለም እስከ ሠባት ወር እንሠራለን ---- ትንሽ ግን ክፍያው ወደድብሻል” አለኝ ሃኪሙ“እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ---- ጓደኛዬ ነው የሚከፍልልኝ፤ዋጋውን ንገረኝና ገንዘቡን ተቀብዬው እመጣለሁ” “እሺ አራት ወር ከሆነሽ ሠባት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤በመድሃኒት ወይም በማሽን ይሰራልሻል፤ ብሩ ተወደደብኝ ካልሽ ደግሞ በግሉኮስ ላስቲክ ሊሰራልሽ ይችላል” ሲለኝ የእያንዳንዱን ዋጋ እንዲነግረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱም ማብራራቱን ቀጠለ በመድሃኒት ለሚሠራው ነው ሠባት መቶ ብር ያልኩሽ፤ በማሽን ከሆነ ስድስት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤ በግሉኮስ ሶስት መቶ ብር” ከጓደኛዬ ጋር ልምከርበት አልኩትና ሙን አመሥግኜው ወጣሁ፡፡ ከቤቱ እንደወጣን “ቤቱ ደስ አላለኝም” በሚል ሰበብ ወንዱ ሌላ ቦታ እንዲወስደኝ ጠየቅሁት፡ “ችግር የለም” አለኝና መንገዳችንን ቀጠልን - ወደ ሁለተኛው አማራጭ፡፡ ብዙም ሳንደክም ነው የደረስነው፡፡ “በርጌስ ክሊኒክ” የሚል ማስታወቂያ ያለበት የህክምና ተቋም ውስጥ ይዞኝ ገባ - ፈቃዴን ከጠየቀኝ በኋላ፡፡ ክሊኒኩ መጀመሪያ ከገባንበት ቦታ በንፅህና አስር እጅ የተሻለ ነው፡፡ ታካሚዎች ተራ ይጠብቃሉ፡፡ ወንዱ ልክ እንደጓደኛው እጄን ይዞኝ ካርድ ክፍል ሠራተኞች ምልክት ሠጥቷቸው ወደ ሃኪሙ ክፍል ወሰደኝ፡፡ ታዳጊው ደላላ ለክሊኒኩ ቤተኛ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ ይሄኛው እንኳን የክሊኒክም ወግ አለው፡፡ የተራቀቁና ዘመን አመጣሽ ባይሆኑም የተለመዱት የህክምና መሳሪያዎች ይታያሉ፡፡ ዶክተሩ ወንዱን ስላየ ነው መሠለኝ በቀጥታ “ስንት ወርሽ ነው?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “አራት ወሯ ነው፤ ጓደኛዋ አደራ ብሎኝ ነው” ሲል ወንዱ ፈጠን ብሎ መለሰ “እሺ አሁን ትሠሪያለሽ?” የዶክተሩ ጥያቄ ነበር ጋውን እንዲነግረኝ እና ከጓደኛዬ ጋር ተማክሬ “እዚህ ክሊኒክ ግሉኮስ የሚባል ነገር የለም፤ ዋጋው ደግሞ አንድ ሺህ ሠባት መቶ ብር ነው” አለኝ ፍርጥም ብሎ፡፡ ከሃኪሙ ክፍል እንደወጣን ለወንዱ የፍርሃት ስሜት ውስጥ እንደገባሁና እዚህ ክሊኒክ ውስጥ ያሰራች አንዲት ሴት ባገኝ ሁኔታውን ጠይቄያት እንደምደፋፈር ነገርኩት፡፡ እኔ ግን የፈለግሁት ሊያሰሩ የመጡ ሴቶችን ለማነጋገር ነበር፡፡ ወንዱም ያልኩትን ለመፈፀም ለአፍታ እንኳ ሳያመነታ “ተከተይኝ” ብሎ ይዞኝ ሄደ፡፡ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው የሚያቃስቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ባሉ አልጋዎች ላይ በሆዳቸውየተኙም ሴቶች ተመልክቼአለሁ፡፡ ወደ አንዷ ሴት ጋ አልኩና ጠየቅኋት “ህመሙ ለትንሽ ደቂቃ ነው አትፍሪ” የሚል ማበረታቺያ ሰጠችኝ፡፡ “የስንት ወር ነው ያሰራሽው?” አልኳት፡፡ “እኔ መውለድ ነበር የምፈልገው፤ሆኖም የአረብ አገር ቪዛ መጣልኝና ላስወርድ ፈለግሁኝ፤ ሜሪስቶፕስ ሄጄ ወርሽ ገፍቷል አንሰራም ሲሉኝ ደላላው ወደዚህ አመጣኝ” አለችኝ፡፡ ልጅቱ በነበረችበት ክፍል ውስጥ 18 ሴቶች ነበሩ፡፡ ዘጠኙ ወደ አረብ አገር የሚሔዱ ናቸው፡፡ የዕለቱ ዕለትና በንጋታው የሚበሩ ሴቶችም ነበሩ፡፡ ከክፍሉ ስንወጣ ለደላላው ሀያ ብር ሠጠሁትና ስልኩን ተቀብዬ እንደምደውልለት ነግሬው ተለያየን፡፡ በዚያው ሰሞን በአንድ የዘመድ ለቅሶ ላይ በሜሪስቶፕስ ክሊኒክ ውስጥ የምትሰራ አንዲት ሲስተር አገኘሁና በፅንስ ማቋረጥ ዙሪያ አንዳንድ ነገር ተጨዋወትን፡፡ ሲስተሯ እንደነገረችኝ ወደ ክሊኒኩ ፅንስ ለማቋረጥ ከሚመጡ ሴቶች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ናቸው፡፡ እሷን የሚያስጨንቃት ታዲያ ሦስት ወር ከሆናቸው በኋላ ወደክሊኒኩ መጥተው የሚመልሷቸው ነፍሰጡር ሴቶች ጉዳይ ነው፡፡ ክሊኒኩ ከፀነሱ ሦስት ወር ለሞላቸው እንስቶች አገልግሎት እንደማይሰጥሲ ግራቸው፤ ወደ ህገወጥ ቦታ መሄዳቸው ክፉኛ ንደሚያሳስባት ትናገራለች፡፡አንዲት ሴት እስከ ሁለት ወር የሚደርስ ፅንስ በመድሀኒት ማቋረጥ ትችላለች፡፡ አንድ ፍሬ ክኒን በመጀመርያው ቀን ትውጥና በሶስተኛው ቀን ደግሞ አራት ፍሬ እንድትውጥ ይደረጋል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ግን መድሃኒቱን አይመርጡም፡፡” ያለችው ሲስተሯ፤ ምክንያቱን ስንጠይቃቸው አረብ አገር ስለሚሄዱ እንደሆነ ይነግሩናል ትላለች፡፡ አንዳንዶቹ ግን ፅንሱ በመጀመሪያ በዋጡት መድሃኒት ብቻ የሚወርድ ስለሚመስላቸው በዛው ይቀራሉ፤ ይሔ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብላለች፡፡ “አንዳንዶቹ እንደውም የሔዱበት አገር ተመርምረው ነፍሠ ጡር መሆናቸው ሲታወቅ ተመልሠው ይመጣሉ፤ይሔም ሌላ ኪሳራ ነው” የምትለው ባለሙያዋ፤ አረብ አገር እሄዳለሁ ብላ ፅንስ ለማቋረጥ የመጣች አንዲት ሴት የገጠማትን አሳዛኝ አደጋ ታስታውሳለች፡፡ “ልጅቷ ወደ አረብ አገር ልትሄድ ስትል ነው ለማስጠረግ የመጣችው፤ ቀኗ በመግፋቱአንሠራምአልናትና ሌላም ቦታ መሄድ እንደሌለባት መክረን ሸኘናት፤ እሷ ግን ባህላዊ ፅንስ የማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ በመሄድ በሠጧት የግሉኮስ ላስቲክ ምክንያት ማህፀኗ በመበሳቱ፤ደሟ ወደ ሆዷ ፈስሶ ህይወቷ አለፈ” ብላለች - ሲስተሯ፡፡ ተዘዋውሬ ባየኋቸው የሜሪስቶፕስ ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ፈላጊዎች ወደአረብ አገር የሚጓዙ ሴቶች መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት በቀን ጥቂት ሴቶችን ብቻ ያስተናግዱ የነበሩ የክሊኒኩ ቅርንጫፎች፤ አሁን ከአቅማቸው በላይ እየሆነባቸው ቀጠሮ እስከ መስጠት ደርሠዋል፡፡ ክሊኒኩን ያጨናነቁት በዋናነት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ቢሆኑም ክሊኒኩ በፊት ከሚሠጠው በማሽን የመጥረግ አገልግሎት በተጨማሪ በመድሀኒት የመጥረግ አገልግሎት ጀመሩም የተጠቃሚዎቹን ቁጥር እንደጨመረው ሲስተሯ ትናገራለች፡፡ “በመድሃኒት ፅንስ ማቋረጥን ብዙዎች እንደጨዋታ ነው የሚያዩት፤ ምክንያቱም እምብዛም የህመም ስሜት የለውም” የምትለው ጊዜ “በጣም ነው የምወዳችሁ!” እያሉ በመወሻከት ቁርጥ ቀን ሲመጣ “ልጄ ሁሉም ለራሱ ነው!” ብሎ ነገር የለም፡፡ ፀማይ የእውነት ምድር ነው፡፡ መውደድ ንዳይረክስ በቃል አይጠራም፤ በተግባር ነው የሚገለፀው፡፡ እነዚህን ሁሉ በረከቶች አግኝቷል፡፡ ፀማይ ሰላም ነው! በፀማይ ኮረብቶች፣ በፀማይ ሜዳዎች ላይ ቀን ከምሽት ሳይመርጥ ሲንጐራደድ፣ አፉ ውስጥ የቀረች አንዲት ግጥምን እንደ ብሔራዊ መዝሙር ይደጋግማታል፡፡“ፍላጐት ምኞትህ ወደብ ድንበር አለው?ብለህ አትጠይቀኝ ህልሜ አንተን መሆን ነው!ያለ ስም ቅጥያ ግቤ ሰው መሆን ነው፡፡ሰው መሆን! ሰው መሆን! በቃ ነፃ መሆን!ግጥሟ የአንድ ፋርሳዊ ፀሃፊ ነው ብሎ ጓደኛው ነበር በቃሉ ያስጠናው፡፡ ነፃ ሰው የመሆን ስሜቱን በፀማይ አፈር፣ በፀማይ አየር፣ በፀማይ ሰዎች መካከል አግኝቶታል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከኦሞ ወንዝ ጋር የማይደበዝዝ ፍቅር አዳብሮ ነበር፡፡ኦሞን እንደሰው እያዋራ፣ በኦሞ የቅዝቃዜ በረከት ሲረሰርስ፣ በኦሞ ፈሳሽ ውሃ ሲዳሰስ ዘላለማዊ መኖሪያው በኦሞ ዳርቻ እንደሚሆን ወስኖ ነበር፡፡ በሰለሞን ውሳኔ ግን ኦሞ የተስማማ አይመስልም፡፡ እጣውን ኦሞ እራሱ ፅፎ ሰጠው፡፡ እጣ ደግሞ የሚመርጡት ሳይሆን የሚወጣ ነው፡፡ በአንድ ወበቃማ ቀን ሰለሞን ወደ ኦሞ ሲወርድ ለሁለት ወራት ያህል ከውሀው ሲገባ ለወትሮ ሚያገኘውን ደስታ በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ወደ ወንዙ የሚያመራውን ጉብታ ቁልቁል እያቋረጠ ሳለ ግን የድረሱልኝ የሚመስል ድምፅ የሰማ መሰለው፡፡ እየሮጠ ወደ ወንዙ ደረሰ፡፡ ብቅ ጥልቅ የሚል ሰው ታየው፡፡ በውሀው ላለመወሰድ የሚታገል፡፡ዘሎ ከውሀው ገባ፡፡ የውሃውን ሃይል እየታገለ ሰው ወዳየበት አቅጣጫ ተምዘገዘገ፡፡ ያየውን ሰው እጅ እንዳገኘ ሽቅብ ገፋው እና ከውሀው በላይ አደረገው፡፡ በአንድ እጁ እየዋኘ ወደ ወንዙ ዳር ተጠጋ፡፡ ኦሞ እንደለማዳ ፈረስ እሺ ብሎ የሚጋልብለት ይመስል በቀላሉ አቋረጠው፡፡ የተሸከመውን ሰው አውጥቶ ከወንዙ ዳር አስተኛው፡፡ በውሀ ሊወሰድ የነበረው ሰው ግዙፍ ወንድ ነበር - ፈረንጅ! ከአለባበሱ ቱሪስት እንደሆነ ገምቷል፡፡ ከነልብሱ ምን ሊያደርግ ኦሞ ውስጥ እንደገባ ለሰለሞን ሊገባው አልቻለም፡፡“እንደኔ የከተማ ቱማታ ናላውን ያዞረው ይሆናል!” ብሎ እያሰበ ሳለ፣ የፈረንጁን ጩኸት የሰሙ ፀማዮች እየተጠራሩ ከቦታው ደረሱ፡፡ የሰውዬውን ደረት እየተጫኑ ከሆዱ የገባውን ውሀ ሲያስወጡለት ቀስ በቀስ ነፍስ ዘራ፡፡ሰለሞን የሰው ነፍስ ማትረፍ መቻሉ ከፍተኛ ደስታ አጐናፅፎት ነበር፡፡ የፀማዮች ተደጋጋሚ የምስጋና ቃል ሲቸረው በሙሉ ልብ ሲቀበል ቆየ፡፡ ያረፈባት ቤት ፈረንጁን ከውሀ ውስጥ መንጥቆ ያወጣውን ጀግና ለማየት ከአቅራቢያ መንደሮች ጭምር በሚመጡ እንግዶች እስከምሽት ድረስ ተጨናነቀች፡፡ የሰለሞን ዝና በአንድ ምሽት ፀማይን አልፎ ጅንካ ደረሰ፡፡ ከጅንካ ምድር አልፎ አዋሳ ለመድረስ አንድ ቀን አልፈጀበትም፡፡ ከአዋሳ አዲስ አበባ በዚያው ቀን ምሽት ዜናው ተሰራጨ፡፡የጋዜጠኞች ቡድን ካሜራ እና ማይኩን ደቅኖ ጀርመናዊውን ቱሪስት ያዳነውን ጀግና ለማየት ወደ ፀማይ አመራ፡፡ሰለሞን ከከተማ የመጡ ሰዎች ሊያናግሩት እንደሚፈልጉ በብሔረሰቡ አባት ሲነገረው፤ ብዙም ደስ ባይለውም እሳቸውን ላለማስቀየም ወጥቶ መጡትን ሰዎች ማነጋገር ነበረበት፡፡“ለመንደራችን ልዩ ሲሳይ ነው ይዘህ የመጣኸው!... አሁንም ከከተማ ትላልቅ ሰዎች አንተን ለማነጋገር መጥተዋል፡፡ እንደምታየው መንደራችን ብዙም አላደገችም፡፡ አንተ የሰራኸው ስራ መንደራችንን ለማስተዋወቅ ጠቃሚ ነው!” የሚለው ንግግራቸው ይበልጥ አሳማኝ ሆነለት፡፡ ጋዜጠኞቹ ሰለሞንን ሲያዩ አይናቸውን ተጠራጥረው ነበር፡፡ ከመካከላቸው አንዱ፤“ዝነኛው አርቲስት ሰለሞን?” አለ ባለማመን ስሜት ተውጦሰለሞን በአዎንታ እራሱን ነቀነቀ፡፡የፎቶ ካሜራዎች ብልጭታ ከየቦታው ሲተኮስበት፣ የካሜራዎች እይታ እሱ ላይ ሲያነጣጥርበት አንድ ነገር ገባው፡፡ ዝነኝነት ምርጫው ባይሆንም እጣው ነበረ፡፡ ቢሸሽ የማያመልጠው! እንደ ጥላ!ዝነኛው ከገፅ 17 የዞረየምትቀበለው እንስቷ ብቻ ናት፡፡በዚህ ዓይነቱ የድለላ ስራ ላይ የተሠማራው የ16 አመቱ ታዳጊ ወንዱ (ጩቤ በሚል ቅፅል ስሙ ይበልጥ ይታወቃል) በቀን ከ8-10 የሚደርሱ ወጣት እንስቶችን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ ወደሚፈፀምባቸው ሥፍራዎች እንደሚወስድ ይናገራል፡፡ ወንዱ እንደሌሎች ደላሎች “ክሊኒኩ ተዘግቷል” አይልም፡፡ በክሊኒኩ ሲሰሩ የነበሩ ዕውቅ ዶክተሮች የራሳቸውን ክሊኒክ ከፍተው መውጣታቸውንና አሁን ያሉት ተማሪዎች (ተለማማጅ ሃኪሞች) ስለሆኑ “እንዳያበላሿችሁ” በሚል እያስፈራራ ጭምር ነው ሴቶችን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ወደሚሰጡባቸው ሥፍራዎች አግባብቶ የሚወስደው፡፡ይሄ ደላላ አንደበቱን አምነው የተከተሉትን ተላላ ሴቶች፤ እሪ በከንቱ አካባቢ ወደሚገኝ ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ የሚካሄድበት ሥፍራ ይወስዳቸዋል፡፡ እኔ ወደዚህ ሥፍራ ልሄድ የቻልኩት ሜሪስቶፕስ አካባቢ ወንዱን አግኝቼው የአራት ወር ነፍሠጡር መሆኔን ከነገርኩት በኋላ ነው፡፡ እሪበከንቱ አካባቢ ስደርስ ግን አንድም ክሊኒክ የሚመስል ነገር አላገኘሁም፡፡ ሆኖም ደላላው ይሄ ዓይነቱ ጥያቄ ከእንስቶቹ ከመምጣቱ በፊት እያዋከበ በጭቃ የተሠራ ቤት ውስጥ ይዟቸው ዘው ይላል፡፡ ቤቱ ለእንስቶቹ እንጂ ወንዱን ለመሰሉ ደላሎች አዲስ አይደለም፡፡ በዚህ ቤት ውስጥ አንዲት ካርድ የምትሰጥ ሴት፣ አንድ ሃኪምና የፅንስ ማቋረጡን የሚሰራ “ባለሙያ” መኖራቸውን አይቼአለሁ፡፡ ቤቷ አንዲት ክፍል ብትሆንም በአቡጀዲ ጨርቅ ሦስት ቦታ ተከፋፍላለች - ሦስት ክፍሎች ለመፍጠር፡፡ ወደዚህች ቤት እንደገባን በወንዱ መሪነት ለካርድ ሀያ ብር ከፍዬ ከተደረደሩት ወንበሮች በአንደኛው ላይ ተቀመጥን፡፡ ከጎኔ ሁለት የምኒሊክ ት/ቤት ዩኒፎርም የለበሱ ወጣት እንስቶች ተቀምጠው ነበር፡፡ ጠጋ ብዬ ለምን እንደመጡ ጠየቅኋቸው፡፡ ጓደኛቸው አርግዛ ለማስወረድ ይዘዋት እንደመጡና ሃኪሙን ልታነጋግር ወደውስጥ እንደገባች ነገሩኝ፡፡ “አያስፈራም?” ስል ጠየቅኋቸው፡፡ እንደማያስፈራ ከነገሩኝ በኋላ የተለያዩ አማራጮች እንዳሉና አንዱን መምረጥ እንዳለብኝ ምክር ቢጤ ለገሱኝ፡፡ ወዲያው ጓደኛቸው ሃኪሙን አናግራ በመውጣቷ በተራዬ እኔደግሞ ገባሁ፡፡ ደላላውም ተከትሎኝ ገባ፡፡ የሃኪሙ ነጭ ቀለም የተቀባ የሚመስል ጠረጴዛ ለዓይን እንኳን ይዘገንናል፡፡ መሀሉ የተቦረቸፈ ስትሬቸር ግድግዳው ጥግ ይታየኛል፡፡ የእርግዝና ማዳመጫ መሳሪያ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡ በቃ እኒሁ ናቸው የህክምና ቁሳቁሶቹ - ሌላ ነገር የለም፡፡ “ስንት ወርሽ ነው?” ሃኪሙ ጠየቀኝ“አራት ወር ገደማ ይሆነኛል” አልኩት- የውሸቴን መሆኑ እንዳይታወቅብኝ በመጠንቀቅ “ችግር የለም እስከ ሠባት ወር እንሠራለን ---- ትንሽ ግን ክፍያው ይወደድብሻል” አለኝ ሃኪሙ “እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ---- ጓደኛዬ ነው የሚከፍልልኝ፤ዋጋውን ንገረኝና ገንዘቡን ተቀብዬው እመጣለሁ”
“እሺ አራት ወር ከሆነሽ ሠባት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤በመድሃኒት ወይም በማሽን ይሰራልሻል፤ ብሩ ተወደደብኝ ካልሽ ደግሞ በግሉኮስ ላስቲክ ሊሰራልሽ ይችላል” ሲለኝ የእያንዳንዱን ዋጋ
እንዲነግረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱም ማብራራቱን ቀጠለ “በመድሃኒት ለሚሠራው ነው ሠባት መቶ ብር ያልኩሽ፤ በማሽን ከሆነ ስድስት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤ በግሉኮስ ሶስት መቶ ብር” ከጓደኛዬ ጋር ልምከርበት አልኩትና ሃኪሙን አመሥግኜው ወጣሁ፡፡ ከቤቱ እንደወጣን “ቤቱ ደስ አላለኝም” በሚል ሰበብ ወንዱ ሌላ ቦታ እንዲወስደኝ ጠየቅሁት፡፡ “ችግር የለም” አለኝና መንገዳችንን ቀጠልን - ወደ ሁለተኛው አማራጭ፡፡ ብዙም ሳንደክም ነው የደረስነው፡፡ “በርጌስ ክሊኒክ” የሚል ማስታወቂያ ያለበት የህክምና ተቋም ውስጥ ይዞኝ ገባ - ፈቃዴን ጠየቀኝ በኋላ፡፡ ክሊኒኩ መጀመሪያ ከገባንበት ቦታ በንፅህና አስር እጅ የተሻለ ነው፡፡ ታካሚዎች ተራ ይጠብቃሉ፡፡ ወንዱ ልክ እንደጓደኛው እጄን ይዞኝ ለካርድ ክፍል ሠራተኞች ምልክት ሠጥቷቸው ወደ ኪሙ ክፍል ወሰደኝ፡፡ ታዳጊው ደላላ ለክሊኒኩ ቤተኛ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ ይሄኛው እንኳን የክሊኒክም ወግ አለው፡፡ የተራቀቁና ዘመን አመጣሽ ባይሆኑም የተለመዱት የህክምና መሳሪያዎች ይታያሉ፡፡ ዶክተሩ ወንዱን ስላየ ነው መሠለኝ በቀጥታ “ስንት ወርሽ ነው?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “አራት ወሯ ነው፤ ጓደኛዋ አደራ ብሎኝ ነው” ሲል ወንዱ ፈጠን ብሎ መለሰ እሺ አሁን ትሠሪያለሽ?” የዶክተሩ ጥያቄ ነበርዋጋውን እንዲነግረኝ እና ከጓደኛዬ ጋር ተማክሬ እንደምወስን ገለፅኩለት፡፡ “እዚህ ክሊኒክ ግሉኮስ የሚባል ነገር የለም፤ ዋጋው ደግሞ አንድ ሺህ ሠባት መቶ ብር ነው” አለኝ ፍርጥም ብሎ፡፡ ከሃኪሙ ክፍል እንደወጣን ለወንዱ የፍርሃት ስሜት ውስጥ እንደገባሁና እዚህ ክሊኒክ ውስጥ ያሰራች አንዲት ሴት ባገኝ ሁኔታውን ጠይቄያት እንደምደፋፈር ነገርኩት፡፡ እኔ ግን የፈለግሁት ሊያሰሩ የመጡ ሴቶችን ለማነጋገር ነበር፡፡ ወንዱም ያልኩትን ለመፈፀም ለአፍታ እንኳ ሳያመነታ “ተከተይኝ” ብሎ ይዞኝ ሄደ፡፡ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው የሚያቃስቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ባሉ አልጋዎች ላይ በሆዳቸው የተኙም ሴቶች ተመልክቼአለሁ፡፡ ወደ አንዷ ሴት ጠጋ አልኩና ጠየቅኋት “ህመሙ ለትንሽ ደቂቃ ነው አትፍሪ” የሚል ማበረታቺያ ሰጠችኝ፡፡ “የስንት ወር ነው ያሰራሽው?” አልኳት፡፡ “እኔ መውለድ ነበር የምፈልገው፤ሆኖም የአረብ አገር ቪዛ መጣልኝና ላስወርድ ፈለግሁኝ፤ ሜሪስቶፕስ ጄ ወርሽ ገፍቷል አንሰራም ሲሉኝ ደላላው ወደዚህ አመጣኝ” አለችኝ፡፡ ልጅቱ በነበረችበት ክፍል ውስጥ 18 ሴቶች ነበሩ፡፡ ዘጠኙ ወደ አረብ አገር የሚሔዱ ናቸው፡፡ የዕለቱ ዕለትና በንጋታው የሚበሩ ሴቶችም ነበሩ፡፡ ከክፍሉ ስንወጣ ለደላላው ሀያ ብር ሠጠሁትና ስልኩን ተቀብዬ እንደምደውልለት ነግሬው ተለያየን፡፡ በዚያው ሰሞን በአንድ የዘመድ ለቅሶ ላይ በሜሪስቶፕስ ክሊኒክ ውስጥ የምትሰራ አንዲት ስተር አገኘሁና በፅንስ ማቋረጥ ዙሪያ አንዳንድ ነገር ተጨዋወትን፡፡ ሲስተሯ እንደነገረችኝ ወደ ክሊኒኩ ፅንስ ለማቋረጥ ከሚመጡ ሴቶች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ናቸው፡፡ እሷን የሚያስጨንቃት ታዲያ ሦስት ወር ከሆናቸው በኋላ ወደክሊኒኩ መጥተው የሚመልሷቸው ነፍሰጡር ሴቶች ጉዳይ ነው፡፡ ክሊኒኩ ከፀነሱ ሦስት ወር ለሞላቸው እንስቶች አገልግሎት እንደማይሰጥ ሲነግራቸው፤ ወደ ህገወጥ ቦታ መሄዳቸው ክፉኛ እንደሚያሳስባት ትናገራለች፡፡ “አንዲት ሴት እስከ ሁለት ወር የሚደርስ ፅንስ በመድሀኒት ማቋረጥ ትችላለች፡፡ አንድ ፍሬ ክኒን በመጀመርያው ቀን ትውጥና በሶስተኛው ቀን ደግሞ አራት ፍሬ እንድትውጥ ይደረጋል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ግን መድሃኒቱን አይመርጡም፡፡” ያለችው ሲስተሯ፤ ምክንያቱን ስንጠይቃቸው አረብ አገር ስለሚሄዱ እንደሆነ ይነግሩናል ትላለች፡፡ አንዳንዶቹ ግን ፅንሱ በመጀመሪያ በዋጡት መድሃኒት ብቻ የሚወርድ ስለሚመስላቸው በዛው ይቀራሉ፤ ይሔ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብላለች፡፡ “አንዳንዶቹ እንደውም የሔዱበት አገር ተመርምረው ነፍሠ ጡር መሆናቸው ሲታወቅ ተመልሠው ይመጣሉ፤ይሔም ሌላ ኪሳራ ነው” የምትለው ባለሙያዋ፤ አረብ አገር እሄዳለሁ ብላ ፅንስ ለማቋረጥ የመጣች አንዲት ሴት የገጠማትን አሳዛኝ አደጋ ታስታውሳለች፡፡ “ልጅቷ ወደ አረብ አገር ልትሄድ ስትል ነው ለማስጠረግ የመጣችው፤ ኗ በመግፋቱ አንሠራም አልናትና ሌላም ቦታ መሄድ እንደሌለባት መክረን ሸኘናት፤ እሷ ግን ባህላዊ ፅንስ የማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ በመሄድ በሠጧት የግሉኮስ ላስቲክ ምክንያት ማህፀኗ በመበሳቱ፤ደሟ ወደ ሆዷ ፈስሶ ህይወቷ አለፈ” ብላለች - ሲስተሯ፡፡ ተዘዋውሬ ባየኋቸው የሜሪስቶፕስ ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ፈላጊዎች ወደአረብ አገር የሚጓዙ ሴቶች መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት በቀን ጥቂት ሴቶችን ብቻ ያስተናግዱ የነበሩ የክሊኒኩ ቅርንጫፎች፤ አሁን ከአቅማቸው በላይ እየሆነባቸው ቀጠሮ እስከ መስጠት ደርሠዋል፡፡ ክሊኒኩን ያጨናነቁት በዋናነት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ቢሆኑም ክሊኒኩ በፊት ከሚሠጠው በማሽን የመጥረግ አገልግሎት በተጨማሪ በመድሀኒት የመጥረግ አገልግሎት መጀመሩም የተጠቃሚዎቹን ቁጥር እንደጨመረው ሲስተሯ ትናገራለች፡፡ “በመድሃኒት ፅንስ ማቋረጥን ብዙዎች እንደጨዋታ ነው የሚያዩት፤ ምክንያቱም እምብዛም የህመም ስሜት የለውም” የምትለውባለሙያዋ፤ ዋናው ነገር ሴቶች ፅንስ ለማቋረጥ ብለው በየመንደሩ በመሄድ ህይወታቸውን ለአደጋ ከማጋለጥ መቆጠባቸው ነው፤ ማናቸውንም ጉዳዮች የህክምና ባለሙያዎች በማማከር ቢፈፅሙት ራሳቸውን ከሞት አደጋና ከጤና እክሎች ሊጠብቁ ይችላሉ ስትል ትመክራለች፡፡ በአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ዶክተር ገላኔ ሌሊሳ ሲናገሩ፤ ማንኛውም ህክምና በትክክለኛ ባለሙያ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፣ የእርግዝናው እድሜ እየገፋ በመ ቁጥር አደጋዎቹም እየከበዱ እንደሚሄዱ ያስረዳሉ፡፡ አንዲት ሴት በመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ሳምንት የምታደርገው ውርጃዎች ትንሽም ቦሆን ችግር አላቸው ምንኛውም ሴት እስከ ስምንት ሳምንት ያልሞላው ጽንስ አንዳንዴ በተፈጥሮም የሚቋረጥበት አጋጣሚ ይኖራል፤ በህክምናም ሊቋረጥ ይችላል የሚሉት ዶ/ር ገላኔ፤ ይሄ የተለየ ችግር ያመጣል ተብሎ አይታሰብም ብለዋል፡፡ አንዲት ሴት ፅንሷ ከተቋረጠ በኋላ እረፍት ሳታደርግ ለጉዞ ብትነሳ ወይም ወደ ስራ ብትገባ ችግር ያጋጥማታል ማለት አይደለም ያሉት ዶ/ር ገላኔ፣ ነገር ግን ማንኛውም ህክምና ሁሌም ክትትል ያስፈልገዋል፤ ህክምናው ትክክለኛ ውጤት ማስገኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ከህክምና በኋላ፣ እንደተጠበቀው ፅንሱ ሳይቋረጥ ቢቀር በጣም አስጊ ስለሚሆን ክትትል ማድረግ ይኖርባታል ብለዋል ዶ/ር ገላኔ፡፡ የፅንስ ማቋረጥ ህክምና በሁለት መንገድ እንደሚካሄድ ዶ/ር ገላኔ ጠቅሰው፣ አስር ሳምንት ያልሞላው ጽንስ በመድሀኒት ሊቋረጥ ይችላል፤ የፅንሱ እድሜ ከዚህ በላይ ከሆነ ግን የግድ መጠረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ከሁለቱ ዘዴዎች መካከል በመድሃኒት ጽንስ የማቋረጥ ዘዴ ተመራጭ ነው፣ ምክንያቱም ከማህፀን ጋር ምንም ንክኪ ስለሌለው የማህፀን መኮማተርን አያስከትልም፡፡ ስለዚህ ያልተፈለገ እርግዝና ሲከሰት ጊዜው ሳያልፍ ወደ ትክክለኛው የህክምና ባለሙያ መሄድ ያስፈልጋል ሲሉ ዶ/ር ገላኔ ይመክራሉ፡፡
No comments:
Post a Comment