Pages

Jan 21, 2014

የአንድነት ፓርቲ አባል ከጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ጀምሮ በእስር እየተንገላቱ ነው

1535663_666890236703062_1047828726_n

 

አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ በሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ አርሲ ሚጣ ነሴቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከታሰሩበት ወረዳ ያንተ ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ስለሆነ እዚህ አይታይም በማለት ጥር 9 ቀን ወደ ሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ተወስደው ታሰሩ፡፡ ፖሊስ ጣቢያውም እንድትለቀቅ ከፈለግክ
1ኛ እስከዛሬ የታሰርኩበትን አልጠይቅም
2ኛ ከዚህ በኋላ ወደ ፖለቲካ አልገባም
3ኛ በተፈለኩኝ ሰዓት እቀርባለሁ ብለህ ፈርምና ውጣ የሚል ቅድመ ሁኔታ ቢያቀርብላቸውም አቶ አለማየሁ ግን በሰላማዊ መንገድ የሚታገልና በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አባል ነኝ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም፣ በፍጹም አልፈርምም ብለዋል፡፡ በ 5 ክስ ከሰንሃል 4ቱን ውድቅ አድርገናል በአንዱ ግን እንከስሃለን በሚል ለማስፈራራት ቢሞክሩም አቶ አለማየሁ በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡ የሻሸመኔ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተጫን ለምን እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ አቶ አለማየሁ በአሁኑ ሰዓት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ጣቢያ በአደራ ታሰረው የሚገኙ እስረኛ ናቸው፡፡
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6117#sthash.kjFjQJ5L.HKbXZUAK.dpuf

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate