Pages

Apr 5, 2013

የሞተበት ሲላጭ፤ ያልሞተበት ቅቤ ይቀባል (የጉራጌ ተረት)

ከዕለታት አንድ ቀን የዱር አራዊት ከአንድ ውጊያ ድል በኋላ፤ እስቲ ያሳለፍነውን ጦርነት እንዴት እንዳሸነፍ
እንመርምር ይባባላሉ፡፡
ነብር - “የእኔ መኖር ነው ዋናው፡፡ የእኔ ፍጥነት ጠላቶቻቸውን አደነጋግሩዋቸዋል” አለ፡፡
ዝሆን - “የእኔ ግዙፍነት ጠላቶቻችንን ብርክ አሲዞዋቸው እንደነበር ሁላችሁም ምስክር ናችሁ” አለ፡፡
ዝንጀሮ - “እኔ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በየዛፉ ላይ እየተንጠላጠልኩ ‘ወዮላችሁ! የአያ አንበሶ ጦር ዶጋመድ
ሊያደርጋችሁ እየመጣ ነው’ ስላቸው ጫካውን እየለቀቁ ሲፈረጥጡ አይታችኋል፡፡ ‘ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው’
የሚባለው ዕውነት መሆኑን ታዝባችኋል፤” አለ፡፡
አጋዘን - “እኔ በስንቅ፣ በትጥቅና በንብረት ጥበቃ ማገልገሌን መቼም አትክዱም፡፡ ዞሮ ዞሮ ዋናው ሁላችንም
የአያ አንበሶ ምልምሎች መሆናችን ነው፡፡ ያ መቼም አሌ አይባልም፡፡ ሁላችንንም የረዳን የሳቸው አቅምና ዝና ነው፡
፡ ድሉም የእሳቸው ውጤት ነው” አለና ተቀመጠ፡፡
ሁሉም በተራ በተራ ዘራፍ እያሉ ራሳቸውን እያደነቁ ተቀመጡ፡፡
በመጨረሻ ጦጢት ተነስታ፤
“እኔ ግን በመጠኑ ቅር ብሎኛል” አለች
“ለምን? ምክንያትሽን አስረጂና?” ተባለች፡፡
ጦጢትም እንዴት ስሜቷን ተቆጣጥራ እንደምትናገር በማስላት፤ ድምፁዋን አጠራችና፤
“ጌቶቼ! ወንድሞቼ! እህቶቼ! ጠላቶቻችንን በወኔ መደምሰሳችን እርግጥ ነው እጅግ አስደሳች ነገር ነው፡፡ ዕድሜ
ለጀግናው መሪያችን፤ በማያወላውል ሁኔታ ድል መትተናቸዋል!! የሚቀጥለውንም ውጊያ እንደምናሸንፍ ምንም
ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆኖም ከእኛ ጋር ሊሆኑ የሚችሉትን ሁሉ ከጠላት ጋር ደርበን ማጥፋት ያለወገን ያስቀረናል፤
ብዬ እገምታለሁ፡፡ እና እንደምታውቁት በሌሎች ደኖች ደግሞ እኛን ለማጥቃት ጊዜ የሚጠብቁ በርካቶች እንዳሉ
እናውቃለን፡፡ ዓለም ተገለባባጭ ነው፡፡ አሮጌው ይሄድና አዲሱ ይተካል፡፡ እኛ ሄደን ተተኪው ይመጣል፡፡ ስለዚህ
እንዳለፈው ጊዜ ስለጦርነቱ እንኳ የሚያወራ አንድ አውሬ ሳናስቀር ሁሉንም መደምሰሱ፣ ነገ ይህን ጫካ ለቅቀን
ስንሄድ ወሬ ነጋሪ እንኳ እንዳይቀር ያደርጋል፡፡ ከጠላትም ለዓይነት አንዳንድ ብናስተርፍ ይሻላል፡፡ ደሞም እንደኛ
ሊያስብ የሚችለውን ብንለይና አብረን ብንጓዝ ጥሩ ነው”፡፡
ሁሉም “ጦጢት ውነቷን ነው” አሉ፡፡
***
ሁሉንም ጠራርጌ አጥፍቼ እኔ ብቻ ልቅር ማለት ጐጂ እንደሆነ እናስተውል፡፡ ሁሉን እንደመስሳለን፤ ሁሉን
ድባቅ እንመታለን ያሉ ከሂትለር እስከ ፒኖቼ Apre moi le deluge (እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል) ካለው የፈረንሳዩ
ሉዊ፤ ከቦልሼቪክ ደበኞች፣ በሴራ ተተኪ ነን እስካሉት እስከ “ጋንግ ኦፍ ፎር” በየዘመኑ ገነው ሲጠፉ አይተናል፡፡
ማንም ፊቴ አይቆምም የሚለው የሞንጐሊያዊው ጄንጂስ ካን ታሪክ መልካም ምሳሌ ይሆነናል፡፡
ሞንጐሊያውያን ቻይናን በወረሩ ሰዓት፤ ጄንጂስ ካን የተባለው መሪያቸው አሸንፎ ቻይና ሲገባ፣ ይቺ አገር
ለምንም አትሆንም ብሎ ከማሰብ ተነስቶ “ለፈረሴ እንኳን ለግጦሽ መሬት የሌላት አገር ናት ቻይና፡፡ ድምጥማጧን
ማጥፋት አለብኝ” አለ፡፡ “ለምን ታጠፋታለህ?” ሲባል፤
“እነዚህን ቻይናውያን ከምድረ - ገጽ አጥፍቼ መሬታቸው ላይ ለፈረሴ የግጦሽ ሣር ባበቅል ይሻላል” አለ፡፡ ይሄኔ
አንድ ቹ ሴይ የሚባል ብልህ ሰው፤ እንደምንም ተጣጥሮ የጄንጂስ ካን አማካሪ ሆኖ ነበርና፤ “ቻይናን ከምታጠፋት
እያንዳንዱ ቻይናዊ ቀረጥ እንዲከፍል ብታደርግ ብዙ ገንዘብ ልታገኝ ትችላለህ” አለው፡፡ ጄንጂስ ካን በምክሩ
ተስማማ፡፡ ቀጥሎ ግን አንዲት ካይ ፌንግ የምትባል ከተማ ወርሮ ሊያወድም ፈለገ፡፡ አማካሪው ቹ ሴይ፤ “ጄንጂስ
ካን ሆይ! የቻይና ጠበብት ሁሉ መሀንዲሶቹ፣ ሐኪሞቹ፣ ባለ እጆቹ … ሌሎች ከተሞቻቸው ሲወረሩ የመጡት
ወደዚች ከተማ ነው፡፡ ከተማይቱን ከማጥፋት ለምን በባለሙያዎቹ አትጠቀምባቸውም” ሲል መከረው፡፡ ጄንጂስ
ካን ምክሩን ተቀበለ፡፡ መንገዶች ተሠሩ፡፡ ህንፃዎች ተገነቡ፡፡ ሆስፒታሎች ተቋቋሙ፡፡
“ሰዎችን የሚነዳቸው የግል ፍላጐት ነው፡፡ ይህንን ፍላጐት ለማሳካት የሚያረጉትን ጥረት በማየትና በዘዴ
በማግባባት አገር ልታድን ትችላለህ” ይላል ቹ ሴይ፡፡
ችግሩ የሚመጣው ምክር የማይሰሙ መሪዎች ሲኖሩ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ሰው ቀረጥ እንዲከፍል አድርግ
ሲባል በአንድ ጀንበር ሱሪ ባንገት አውልቅ ልበል ያለ እንደሆን ነው፡፡ የግል ፍላጐታቸው የአገር ካዝና የሚያራቁት
ከሆነ፣ ሙስናው ካጠጠና የዚህ መሸፈኛ ደግሞ “እኔ ብቻ ነኝ” የሚያስችል ሥልጣን ከሆነ አገር አለቀች፡፡
ከዚህ ቀደም ለዚች አገር ህልውና ሲባል መስዋዕትነት ተከፍሏል፡፡ ዛሬም ነገም ይከፈላል፡፡ መስዋዕትነቱ
የተከፈለው ተወዶ፣ ለውጥ በማምጣት ታምኖ፣ ከልብ ታግሎ ነበር፡፡
የተቀደሰ መስዋዕትነት የሚባለውም ያ ነው፡፡ አግባብ ነው፡፡ አግባብ የማይሆነው ተገዶ፣ ሳያስቡና ሳያልሙ፣
ምናልባትም ለምን እንደሆነ ሳያውቁ መስዋዕትነት መክፈል የሆነ እንደሆነ ነው፡፡ ህዝብ ማናቸውም ነገር ለምን
እንደሚከናወን የማወቅ፣ መረጃ የማግኘት መብት አለው፡፡ ያ ካልተከበረለት በገዛ አገሩ ባይተዋር፣ በገዛ ቤቱ እንግዳ
ይሆናል፡፡ “ሁሉም ነገር ለጽድቅ ነው - ዝም በል” ሲባል አሜን ካለ፤ የአቦ - ሰጡኝ መስዋዕትነት ከፈለ ማለት ነው፡፡
ለልጁ፣ ለትውልዱ የሚያስተላልፈው የመረጃ ቅርስ ሳይኖረው፣ በሕግ አምላክ የሚልበት ልሣን ሳይኖረው፣ አንዲት
የሰለጠነች አገር እየተመኘ ካለፈ፤ ለአገርም ለታሪክም ደግ አይሆንም፡፡
ጠንካራ ተቃዋሚ ስለሌለውም “ይሄ አይሆንም” ብሎ ሽንጡን ገትሮ፣ ታግሎ የሚያታግለው የለምና፣ ውሎ
አድሮ፤ ሁሉንም እየተካሄደ ያለውን ነገር “ይሁን ግዴለም ለበጐ ነው!” የሚልና “ለምን ይሆናል?” ብሎ የማይጠይቅ
ህዝብ ይፈጠራል፡፡ ይሄ አደጋ ነው! አንዱ ከአገር ጋር ሲያለቅስና አገር እንዴት ላድን ሲል፤ ሌለው አገር የሚገድል
ከሆነ፤ ገጣሚው
“..ዘመንና ዘመን እየተባረረ
ይሄው ጅምሩ አልቆ፣ ማለቂያው ጀመረ” እንዳለው ሊሆን ነው፡፡ የመተካካት ዘመን የራሱ አባዜ አለው፤ ሁሉም
እኩል ካልተሳሰበ ግን “የሞተበት ሲላጭ፣ ያልሞተበት ቅቤ ይቀባል” የሚለው የጉራጌ ተረት ዓይነት ይሆናል፡፡
ከዚያ ይሰውረን፡፡

ሊነበብ የሚገባው .... ታላላቅ የታሪክ ክህደቶች ከ“ፍኖተ ገድል” (ገብረመድህን አርአያ )

"ተራው ታጋይ በእንደ ወዲ ዜናዊ እና ብስራት አማረ ባሉ ፍጹም አደገኛ አወናባጆች እና ከሃዲዎች እየተነዳ ነው የአገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ታሪክም ፤ የአገራችን ኢትዮጵያም ክብር እና ሉኣላዊነትም አደጋ ላይ የወደቁት። "
"እንደ ወዲ ዜናዊ እና አቶ ብስራት ያሉ የታሪክ አሽክላዎች ግን ገና ለገና እነሱ ከቤተሰባቸው የኋላ የባንዳ አሳፋሪ ታሪክ ከመነጨ ከፍተኛ የበታችነት ስሜት ተነስተው ጠላት ነው የሚሉትን አማራውን ህዝብ አንገት እናስደፋለን ብለው መሬት ጠብ የማይል የታሪክ ቡትቶ አምጥተው አቧራቸውን ያቦኑብናል።"
"እኔ መቼም አውሮፓዊ ቅኝ ገዢን ያለፍርሃት በጀግንነት ተጋፍጦ በነጻነት ያቆየውን ሰው "ዘር" ቆጥሮ አማራ በመሆኑ ብቻ እንደምን ሊያኮሰምን ይፈልጋል?? እኔ በበኩሌ ይሄ አስከፊ የጥላቻ ደዌ ከመሆን ያለፈ ምንም ምክንያት ላገኝለት አልቻልኩም።"
"ነገሮችን እንደዚህ አገናዝቦ ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ልበሰፊነትን ይጠይቃል። በጥላቻ የታሰሩ ፤ ሃሳበ ድውይ የህወሃት መሪዎች ግን ቅንነት በጣም የጎደላቸው ሰዎች ስለሆኑ አጼ ምኒልክ አማራ መሆናቸው ፤ አማራም የትግራይ ጠላት ነው ከሚል ቆሻሻ አመለካከት ውጭ ሌላ ነገር ማሰብ ፈጽሞ አይቻላቸውም። "



ለአንድ ሰሞን ለአመታት በአሜሪካኗ ግዛት ኦሃዮ ውስጥ በስደት ሲኖር የነበረው የወያኔ ነባር ታጋይ፣ በስለላ የሰለጠነ … እና መሪህ ባኽታ ብስራት አማረ የጻፈው መጽሃፍ በህትመት ወጥቶ ጉድ፣ ጉድ ከተባለለት በኋላ እኔም እንደ ኢትዮጵያዊነቴ እና እንደ ቀድሞ የህወሃት ቀዳሚ ታጋይነቴ መጽሃፉን አግኝቼ ለማንበብ እና የግሌን ግምገማ ለማድረግ መፈለጌ አልቀረም። ዘግይቶም ቢሆን መጽሃፉ በእጄ ገብቶ የማንበብ እድል አገኘሁ። መቼም ጉድ ነው የሚባለው!! ህወሃት እና በዙሪያው የከበቡት ጉዶች የቅጥፈት እና የክህደት ጉድ ማለቂያ የለውም። 
ይህ መጽሃፍ በተከታይ እትም ሊታረም የሚችል ግድፈት አይደለም የተሸከመው፤ እንደዚህ በአገጠጠ ውሸት፣ በህወሃታዊ የታሪክ ክህደት፣ በጥላቻ እና በተንኮል የታጨቀ መጽሃፍ አይቼም፣ አንብቤም አላውቅም። ብስራት አማረ ታሪክ ለዚያውም በጣም የቅርብ ጊዜ ታሪክ አንድ ሰው እንዳሻው ስለጻፈው የመጨረሻው እውነት ሆኖ ይቆያል ብሎ ያምናል። ይህ አስተሳሰብ ላዩን ሲያዩት በጣም ገራገር ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በጊዜ አስፈላጊው የእርምት እና የማጋለጥ እርምጃ ካለተወሰደ የኋላ ኋላ ብዙሃን እንደ እውነተኛ ታሪክ እና ትንታኔ ዋጋ ሰጥተው ሊያዩት ይችሉ ይሆናል።
የህወሃትን ማንነት ህወሃት ገና የስልጣን መንበር ላይ ሳይወጣ አበክሬ ተናግሬም፤ አስጠንቅቄም ነበር። እምብዛም የሰማኝም ሰው አልነበረም እና ዛሬ ገና በበረሃ እያሉ የተናገርኩት ነገር እንደ ትንቢት ይኸው ባለፉት 21 አመታት ሲፈጸም አየን። ዛሬም ይህን የምናገረው አገር እና ህዝብን ወደ ኋላ ሄጄ ለመውቀስ አይደለም። ምናልባትም መወቃቀስ ካለብን ለሱ ወደፊት ጊዜ ይኖረዋል። ለአሁኑ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ቀዳሚው ጉዳይ መሆን ያለበት የቅጥረኛው እና የሁሉ ኢትዮጵያውያን ዋና ጠላት የሆነው የህወሃት ቡድን እና እንደብስራት ያሉ ጀሌዎቹ ናቸው። ለዛሬው ከዚህ መጽህፍ ውስጥ የታዘብኳቸውን ስምንት በጣም አደገኛ እና የዘቀጡ የታሪክ ቅጥፈቶችን አንጥሬ ያነቡ ዘንድ እነሆ እላለሁ።
ለአነባበብ ይረዳ ዘንድ ጽሁፌን ከመጽሃፉ እያጣቀስኩ ለመልሱ ከራሴ እና አስረጅ ይሆናሉ ካልኳቸው ዋቢ ማስረጃዎች ጋር አድርጌ የራሴን እነሆ እላለሁኝ።





የታሪክ ክህደት ቁጥር 1:
ይህ ጉዳይ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የትግሪኛ ፕሮግራም ላይ አረጋዊ በርሄ እና ስብሃት ነጋ ቀርበው የተወያዩበት/የተከራከሩበት እና እና ስለ መጽሃፉ በተለይ እኛ ከአገር ውጪ ያለን ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማንበት ጭብጥ ነው -የአክሱም ስልጣኔ ጉዳይ።
ከመጽሃፉ እጠቅሳለሁ:-
<< በርካታ ተመራማሪዎችና ጸሃፊዎች "አክሱም አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ የአማራ ነዋሪዎች ወዳሉበት ደቡባዊ ክፍል ስለመስፋፋቷ የጽሁፍ ማስረጃዎች የሉም። እንደኢትዮጵያ(አማራ) አባባል ሳይሆን የአክሱም ታሪክ ከሁሉ በላይ የደቡብ ኤርትራና የሰሜን ትግራይ ታሪክ ስለ መሆኑን(sic) ማስረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ በተጨማሪ አማራ የአክሱም አፄአዊ ግዛት አካል የነበረ ስለመሆኑ ምንም አይነት ታሪካዊ ጥቁምታ የለም: :>>[1]
የህወሃት መሪዎች የተጠናወታቸው የዘረኝነት በሽታ እንዲሁ በመድሃኒት ወይም በጸበል የሚለቅም አይነት አይደለም። መቼም ዘረኝነት አንዴ ከጀመረ እንደካንሰር ከጀመረበት ቦታ ተወስኖ አይቀርም። እየመዘመዘ ፣ ውስጡን እየበላ መጨረሻ ላይ ታማሚውን ላይመለስ እስከ ወዲያኛው አለም ይወስደዋል። ይኸው ዘረኝነት ዛሬ በአውራጃ ደረጃ ወርዶ የአክሱማዊት መንግስት በሙሉ ትግራይም ቦታ የለውም የሚል መከራከሪያ ከነባሩ የህወሃት ታጋይ በድርጅቱ ከፍተኛ መሪዎች ቡራኬ እና ይሁንታ ተሰጥቶት በመጽሃፍ ተጠርዞ ድል ባለ ድግስ ተመርቆ ለንባብ በቃ። እንደ ጎጠኞቹ መከራከሪያ የአክሱማዊ ኪንግደም የሚያጠቃልለው ሰሜን ትግራይ ፣ አክሱም፣ አድዋ ፣ ደቡብ ኤርትራ ፣ ሰራየ እና አካለጉዛይን ብቻ ነው። በአቶ ብስራት መጽሃፍም ሆነ በአቶ ስብሃት ነጋ ክርክር አዲግራት እና ተምቤን በአክሱማዊ ኪንግደም ውስጥ ቦታ የላቸውም።
ጉዳይ በመከራከሪያነት የተነሳው የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ለማንሳትም አይደለም። አቶ ብስራት የስርዓቱ ቁንጮ እና ዋና ታሪክ አበላሺ አወናባጁ መለስ ዜናዊ የርዕዮተ አለም እና ምግባር ልጅ ነው። መለስ በአንድ ወቅት “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?” ማለቱ በምስለ ድምጽ ተመዝግቦ ያለ የታሪክ ክህደት ነው። ይኸው ዘረኝነት ዛሬ ላይ መዝምዞ ፣ መዝምዞ የአክሱም ሃውልት ለአጋሜው እና ለተምቤኑ ምኑ ነው ላይ ደርሷል። ይሄ ዘረኝነት እና ጥበት ነገ የሚሄድበትን ለመናገር ጠንቋይ ቀላቢ አያሻም።
የታሪክ ጽሁፎች በእውን ያሉ ማስረጃዎች እና ማሳያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ? በብዙ የታሪክ አጥኚዎች መግባባት የተደረሰበት እና ማመሳከሪያ የጽሁፍ ማስረጃዎች እንዲሁም በቁም ያሉ እና በአርኪዎሎጂ ቁፋሮ የተገኙ ቁሶች በማሳያነት ማስቀመጥ የሚቻልባቸው የአክሱም ኪንግደም የግዛት ክልል በጣም ሰፊ ግዛት ሲሆን ይኸውም ከሰሜን አቅጣጫ ከደቡባዊ ግብጽ ጀምሮ ፤ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሰሜናዊ ሱዳንን እንዲህም በስተ ምስራቅ በኩል መላውን የመንን እና ደቡባዊ ሳውዲ አረቢያን ያጠቃልላል።
በዚሁ አንቀጽ ላይ "ኢትዮጵያ" የሚለውን የሁሉም ብሄረሰብ የወል ማንነት በቅንፍ ውስጥ "አማራ" እያለ የለየለት አላዋቂ ትንታኔውን ሲሰጥ ይስተዋላል። የለመዱት "የአማራ የበላይነት" ክስ ምናልባት ለክርክርም ይመች ነበር። ዛሬ ፣ ዛሬ ደግሞ ወርዶ "አማራ" እና "ኢትዮጵያ" ሁለት ተተካኪ ስሞች አድርጎ ለማቅረብ ይሞክራል። አወይ ሰው መናቅ ፤ አወይ ታሪክ መናቅ ፤ አወይ አገር መናቅ አለ የአገሬ ሰው!!





የታሪክ ክህደት ቁጥር 2.
ጸሃፊው ለአጼ ሚኒልክ እና ለአማራ ህዝብ ያለው ጥላቻ ወደር የለውም። በአማራ ህዝብ እና በአጼ ሚኒልክ ላይ የሚያቀርበው የስድብ ውርጅብኝ፣ የቅጥፈት ውንጀላ እና የጥላቻ ደረጃ አስደንጋጭ ነው። ምናልባትም ጸሃፊው እራሱ ለአጼ ምኒልክ እና ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ ገልጾ ቢያቆም በበቃ፤ ችግሩ ግን በዚህ አያበቃም። አፉን ሞልቶ በልበ ሙሉነት አጼ ምኒሊክ ለትግራይ ህዝብ የተለየ ጥላቻ ነበራቸው ብሎ ምንም የታሪክ ማስረጃ የሌለው ይልቅም ፍጹም ህወሃታዊ ከሆነ የራስ መተማመን ጉድለት ካለበት አእምሮ ከመነጨ አስተሳሰብ በመጽሃፍ ጽፎ ማውጣት ከምንም ነገር በላይ የሚያሳየው የጸሃፊውን ደካማ አስተሳሰብ ነው። ሌላው ጉዳይ ዛሬ ላይ ቆመው የሚቀርባበቸውን ክስ መከራክር የማይችሉ ስመ ገናና እና አስተዋይ ንጉስን ምንም የታሪክ መሰረት በሌለው የቅጥፈት ክስ በለመደው ልቅ እና ተሳዳቢ አፉ ሲዘልፍ ማየቱ በእውነቱ በጣም የሚያሳዝን እውነታ ነው።

እስቲ ስለ አጼ ምኒሊክ ከመጽሃፉ ልጥቀስ፤
<<ከቴውድሮስ እና ከዮሃንስ ይልቅ የምኒሊክ ወደ ስልጣን መምጣት ኢትዮጵያ አሁንም ድረስ የገጠሟትን ሰፊና ውስብስብ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ጎሳዊ ችግሮች ያስከተለ ክስተት ነበር። ኢትዮጵያን በሚገርም ጀግንነት እና ልበ-ሙሉነት ማስከበሩ ተረስቶ በሴራ እና በክህደት የተካው የአጼ ምኒሊክ ስራ በኢትዮጵያ ህዝቦች ቅራኔን ቀስቃሽ ሆኖ ተግኝቷል። ግዛቶችን ለውጭ ሃይሎች ፈርሞ መስጠት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቀውስ በየቦታው ተደጋግሞ የሚከሰት የጎሳ ግጭት እና የማያባራ የኢኮኖሚ ድቀት አገሪቷን ለረዢም ጊዜ ሲያጨናንቁ ታይቷል። >>[2]
<<አጼ ምኒልክ እና ተከታዮቹ ወደ ስልጣን ሲመጡ ስለ ሀገሪቷ የተጠራቀመ ባህላዊ እና ታሪካዊ ገጽታ እምብዛም አልተጨነቁም። ስልጣን እንደያዙ በሃገሪቱ ባሉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ጎሰኝነትንና አድልዎ ፈጥሮ ለማዋከብ ጊዜ አልፈጀባቸውም። በጣም ብዙ ጥንታዊ ቋንቋዎችና ባህሎች ቢኖሩም የአንድን ቋንቋና ባህል የበላይነት አበርታቱ። ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ በሁሉም የማስግደድ መንገድ በማጠናከር ባርነት እና የተማከለ አስተደደራዊ ስርዓት ለማስፋፋት ታገለ። >>[3]
<<የምኒሊክ የስልጣን ጥማተኛ ለትግሪኛ ተናጋሪ ህዝብ የነበረው ከባድ ጥላቻ ኢትዮጵያን ወደ ቀውስ እንደመራ ይታመናል።>>[4]
<<...ይኸውም የህዝባቸውን መለያየት ያስከተለው ምኒሊክን ተከታዮቹ ብሄራዊ ግዛቶችን ለውጭ ሀይሎች ፈርሞ በመስጠት የሰሩት ክህደት የትግራይ ህዝብ በሁለት ከመክፈሉ ባሻገር ኢትዮጵያ ከወደብ መውጫ ችግር እንድትሰቃይ አድርገዋል።>>[5]
<< ምኒሊክ እና ተከታዮቹ በአሳፋሪ ሁኔታ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ቅርስ በመስበር ኤርትራ ተብላ የምትታወቅ አዲስ ግዛት እንድትመሰረት ምክንያት ከመሆን ባሻገር 20ኛው ክፍለ ዘመን በሸዋ ገዢዎች ተረታ ተረት የሰለሞን ንግስና የዘር ውርስ ቅሌት የተወሳሰበ ሴራ ያየለበት ዘመን እንዲሆንም አድርገዋል።>>[6]
ከዚህም የበለጠ ብዛት ያለው ጆሮ ጭው የሚያደርጉ እና የለየላቸው የመንገድ ዳር መደዴ የታሪክ ክህደቶችን መጥቀስ ይቻላል። ለጊዜው በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ይህን ያህል ከጠቀስኩ ይብቃኝና እኔ በግሌ የተሰማኝን እና እውነተኛው እና በቅጡ የተመዘገበው ታሪክ የሚለውን ልዘርዝር።
ጸሐፊው የአጼ ምኒሊክን የሰለሞን ዘር ሃረግ "የዘር ውርስ ቅሌት የተወሳሰብ ሴራ" ምናምን እያለ ከሰከረ ሰው የወጣ በሚመስል ንግግር ሲተነትን ዋናው የመጽሃፉ እኩይ ግብን ዘንግቶም ጭምር ነው። አጸ ዮሃንስ 4ኛም የሰለሞን ዘር ሃረግ ውርስ ተቀባይ (በሴት ወግን) መሆናቸውንም የዘነጋ ይመስላል። የንግስና መሰረታቸውም ይህ የዘር ሃረጋቸው ነበር።
አጼ ምኒሊክን በጨካኝነት በተለይ ከአጼ ቴዎድሮስ ና አጼ ዮሃንስ ጋር እያነጻጸሩ መወንጀል በጣሙን የለየለት የታሪክ አላዋቂነት ወይንም ህወሃታዊ ከሃዲነት ከመሆነ የዘለለ አይደለም። እውነተኛውን ታሪክ ለመረዳት ሰዎች እጁን በደም ከታጠበ የወያኔ አላዋቂ ካድሬ አይደለም መስማት ያለባቸው። እድሜ ዘመን ላመጣው ቴክኖሎጂ በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ እንደ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን[7] እና ፕሮፌሰር ሬይመንድ ጆናስ[8] ያሉ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናት ያደረጉ ፤ በጣም ተነባቢ የሆኑ ተጠቃሽ መጻህፍቶችንም የጻፉ እና ምንም አይነት አድልዎ ወይም ጥላቻ ሊኖራቸው የማይችል የባዕድ አገር ምሁራን የሰጡትን ምስክርነት ማድመጡ ብቻ በቂ ነው።ሌላም ብዙ ማጣቀሻ ማቅረብ ይቻላል። ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ወቅት በአጼ ምኒልክ ላይ የሚደርሰው አጸያፊ የወያኔ ክስ እና ውንጀላ አላስችል ብሏቸው መሰለኝ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌም የምኒልክን ብልሃት ማስተዋል የተመላበት አመራር በተመዘገቡ ታሪካዊ ኩነቶች አስደገፈው የተከላከሉበትን የሃተታ ጽሁፍ ለማንበብ ችያለሁኝ። ግሩም ጽሁፍ ነውና ቢያነቡት ይመከራል። “መለስ አርገው ጋሜ ፤ በምኒልክ ነፍስ” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ይህንን ጽሁፍ ከኢትዮሚዲያ ድረገጽ ከታች ባለው አድራሻ ያገኙታል።[9]
እንዲያው ለነገሩ አጼ ምኒሊክ ከነስማቸው "እምዬ ምኒሊክ" አልነበር የሚባሉት??
አጼ ምኒሊክ ወራሪውን የኢጣልያ ጦር አድዋ ላይ ረትተው ሲያበቁ ወደ ኤርትራ መዝለቅ አለመቻላቸው በጣም ግልጽ የሆነ የታሪክ ትንታኔ ያለው በመሆኑ እዚህ መዘርዘሩ ብዙም ፋይዳ የለውም። ምናልባትም ብዙ ማወቅ ለፈለገ በኢሳት የዩቱይብ ድረ ገጽ ላይ የምሁራኑ ሙሉ ቃለ ምልልስ ስላለ ያንን ተመልክቶ አጼ ምኒሊክ በሰአቱ ያለውን የሃይል አሰላለፍ ተመልከትው በጊዜው ያገኙትን ድል ለማጽናት እና በጦርነት፣ በረሃብ እና በውሃ ጥም የተዳከመውን ጦራቸውን መልሶ ለማደራጀት ጦርነቱን እዚያ ላይ ከማቆም በላይ ምንም አማራጭ እንዳልነበራቸው መረዳት ይቻላል።። ምንአልባትም የተዳከመውን ጦራቸውን ይዘው ውጊያውን ከመረብ ወዲያ ቢቀጥሉ በርግጠኝነት በአድዋ ያገኙትን ድል መልሰው አሳልፈው የሚሰጡብት ኢትዮጵያውያንም የሌሎቹ አፍሪካውያን የቅኝ ተገዢነት እጣ የሚደርሳቸው እንደሚሆን በብዙ የታሪክ አዋቂዎች የታመነበት ትንተና ስለሆነ የአቶ ብስራት ቁምጣ አጠር የቅጥፈት ታሪክ ምንም ቦታ የለውም። የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት እና የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል መለስ ዜናዊ በሙሉ አፉ ደግሞ ደጋግሞ እንዲሚያጣጥለው ሳይሆን እንደዚህ በጣም የሚከነክን ጉዳይ ከሆነ ምናልባት ጸሀፊው እራሱን ወይም አለቃውን ወዲ ዜናዊን ነው መክሰስ ያለበት እንጂ እናቶቻችንን ፣ አባቶቻችንን እና እኛን የጣሊያን አሽከር ከመሆን ሞተው ያዳኑንን አያቶቻችንን አይደለም።
እንግሊዝ ህንድን ለቃ ስትወጣ እንደ አፍሪካ ቀንድ ሁሉ አገራቱ በሰላም ይቀጥሉ ዘንድ ሁሉን አሰናድታ አይደለም የወጣችው። የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ህንዶች እና ብዙሃኑ የሂንዲ እምነት ተከታዮች የኋላ ኋላ ተፋጠው በስተመጨረሻ ፓኪስታን ራሷን ችላ ነጻነት በማወጇ ለሁለት መከፈል የተገደዱበት የታሪክ ኹነት እናያለን: የህንዶች የነጻነት አርበኛ እና የነጻነት ትግሉ ሰላማዊ መሪ የነበረው ሞሃንድራስ ጋንዲ ብዙም አማራጭ ስላልነበረው ጊዜው የሰጠውን የታሪክ እውነታ ይዞ ነጻይቱን ህንድ ወደፊት ማራመድ ቻለ። ፓኪስታንም ሌላ አገር እንደውም የህንድ የዘመናት ባላንጣ መሆን ቻለች። በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ህንዳውያንም ሆኑ ሌሎች የታሪክ አዋቂዎች ጋንዲን ሲወቅሱት አይታይም። እንደ አቶ ብስራት እና መለስ ዜናዊ አይነት የአእምሮ በሽተኛ ካልሆነ ጤነኛ ጭንቅላት ያለው ሰው ታሪክን በቅንነት እና በትክክለኛ አገባቡ ነው ማየት ያለበት።
አጼ ምኒሊክ በኢትዮጵያ የተማከለ ስርዓት ማምጣታቸው ምንም የማይካድ የታሪክ ሃቅ ነው። እንደ ጊዜውም ሲቻል በብልሃት እና ማግባባት ሳይሆን ደግሞ በጉልበት በዘመኑ የነበሩ ያለ ጦርነት በቀር ስራ የሌላቸው የሚመስሉ መሳፍንትን መትተው የኢትዮጵያን ማዕከላዊ አስተዳደር እንደመሰረቱ ማንም የማይክደው ሃቅ ነው። አጼ ምኒሊክ ይህን ሲያደርጉ በአገሪቷ ላይ የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት አፍርሰው አይደለም። ኢትዮጵያ ውል እና ማለቂያ በሌለው ውጊያ የምትታመስበት የዘመነ መሳፍንት ወቅት መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ሌላው አቶ ብስራት አጼ ምኒልክን በስልጣን ጥመኝነት ይከሳል። መቼም አጼ ምኒልክ ንጉስ ናቸው። ንጉስ ደግሞ በየትም አገር እንደነበረው አሁንም እንዳለው ሲነግስ ተመርጦ ወይም እንደ ዘመናዊ የፖለቲካ ስርዓት በገደብ አይደለም። ስለዚህም እሳቸውን ነጥሎ "በስልጣን ጥማት" መወንጀል ምንም ትርጉም የለውም። ዘውዳዊ ስርዓት ለኢትዮጵያ አይበጅም አንድ ክርክር ነው ነገር ግን ዘውዳዊ ስርዓትን በስልጣን ጥመኝነት መክሰስ የጅል ክስ ካልሆነ በቀር ምንም ፋይዳ የለውም። ምን አልባትም አውሮፕላንን ስለምን በአየር በረረ ብሎ የመጠየቅ አይነት ነው። እሳቸውም ቢሆኑ በ 99.6 በመቶ ድምጽ ተመረጥኩ ብለውም አልዋሹም። ጊዜው እንደሚፈቅደው አስገብረው ስልጣን ላይ ወጡ በቃ። ጥያቄው መሆን ያለበት እንደንጉስነታቸው በዘመነ ንግስናቸው ምን አደረጉ ነው እንጂ በስልጣን ላይ ለምን ቆዩ ወይም በስልጣን ላይ ስለቆዩ የስልጣን ጥም አለባቸው የሚል ሊሆን አይችልም።
እስከ ዛሬ አጼ ምኒሊክን የሚወቅሱ ሰዎችን እንሰማ የነበረው የሌሎችን ብሄሮች ማንነት ጨፍልቀው ኢትዮጵያን በማዕከል ከአዲስ አበባ ሆነው አስተዳደሩ ነበር። ዛሬ ደግም ሌላ አዲስ ከዚህ ክስ በተጻራሪ የሚቆም የክህደት ታሪክ እየሰማን ነው። በጣም የሚደንቀው ነገር ሁልቱም ፍጹም ተቃራኒ ክሶች የሚመጡት ከወያኔው ጎራ ነው። መቼም ሁለቱም ክስ በአንድ ጊዜ እውነት ሊሆን አይችልም።
አጼ ምንሊክ የዘመናዊ የተማከለ አስተዳደርን በጊዜው ባላቸው የግንዛቤ ደረጃ ሞክረውት ለቀጣይ ትውልድ አሳልፈው ሄደዋል። እውን አቶ ብስራት አስተዋይ ሰው ከሆነ ከዛ በኋላ ያለው ትውልድ ይኼኛውን ጨምሮ ምን ያህል ከዚያ ወዲህ አደረገ ብሎ ነበር መጠየቅ ያለበት። በወቅቱ የነበረውን ቅጥ የለሽ የመሳፍንት ውጊያ አደብ ያስያዙት አጼ ምኒልክ ናቸው። ሌሎቹ ነገስታት ከዚህ በፊት ሊያደርጉ ያልቻሉትን ነገር ነው ንጉሱ ሊያደርጉ የቻሉት። አሜሪካኖች አብርሃም ሊንከንን በአሜሪካን የርስ በርስ ጦርነት ጊዜ በደቡብዊ የአሜሪካ ግዛቶች በሸንኮራ አገዳ እና ጥጥ እርሻዎች ውስጥ የሚሰሩ ባሪያዎችን ጉልበት ብዝበዛ ማስቀጠል ከሚፈልጉ ግዛቶች ጋር ውጊያ አድርገው የአገሪቷን አንድነት ማስጠበቅ ችለዋል። በአብርሃም ሊንከን ጊዜ ግን ባርነት ነበር ጥቁሮችም በተጻፈ ህግ እንደ 3/4 ዜጋ ነበር የሚታዩት መምረጥም ፤ መመረጥም አይችሉም ነበር። የሆኖ ሆኖ አብርሃም ሊንክንን በባሪያ ንግድም ሆነ በሌላ የሚከስ ጥቁር አሜሪካዊ አይገኝም። ይልቁንም የአሁኑ የአሜሪካን ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአብርሃም ሊንከን ቀንደኛ አድናቂ እንደሆኑ ብዙ የተባለለት ጉዳይ ነው። ፕሬዚደንቱ ወደ ዋሽንግተን ጠቅለው ከመግባታቸው በፊት የሚኖሩባትን ግዛት እና አብርሃም ሊንከን የተወለደባትን ኢሊኖይን ብዙ ጊዜ "የሊንከን አገር" እያሉም ነው የሚጠሯት። ነገሮችን እንደዚህ አገናዝቦ ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ልበሰፊነትን ይጠይቃል። በጥላቻ የታሰሩ ፤ ሃሳበ ድውይ የህወሃት መሪዎች ግን ቅንነት በጣም የጎደላቸው ሰዎች ስለሆኑ አጼ ምኒልክ አማራ መሆናቸው ፤ አማራም የትግራይ ጠላት ነው ከሚል ቆሻሻ አመለካከት ውጭ ሌላ ነገር ማሰብ ፈጽሞ አይቻላቸውም።
አጼ ምኒሊክ እንደ አሁኑ የወያኔ ከሃዲዎች አገር በመሸጥ ታምተውም አያውቁም። አንድ ሰው ምን አይነት የአእምሮ ደሃ ቢሆን ነው አጼ ምኒሊክን በአገር መሸጥ የሚወነጅለው? ለዚያውም እንደ ወያኔ አይነት ከሃዲ እና አገር ሸቃጭ። አገሪቷን ወደብ አልባ ያደረገ፣ በሱዳን በኩል 1600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለም የአገሪቱን ግዛት ቆርጦ የሰጠ፣ በጋምቤላ ፣ በቤኒሻንጉል ፣ በኦሮሚያ እና በአፋር በዚህ በአሁኑ ሰኣት ኢትዮጵያውያን ገበሬዎችን እያፈናቀለ አገር እየሸጠ ያለ የሌቦች ቡድን ነው አጼ ምኒሊክን በአገር መሸጥ እየወነጀለ ያለው።
በእውነቱ የአጼ ምኒሊክን መልካም ስም እና በጎ ምግባር በጥላሸት የሚለውሱት የህወሃት ከሃዲዎች ዋንኛ መነሻቸው መሰረታዊው የአያቶቻቸው አሳፋሪ የባንዳ ታሪክ ነው። ሌላው ደግሞ ፍጹም በደማቸው የሚዛወረው እጅግ ከፍተኛ የሆነ የበታችነት ስሜት ነው። አጼ ምኒልክ ከኢጣልያ ጋር ለተደረገው ጦርነት "አመልህን በጉያህ፤ ስንቅህን በአህያህ" ብለው ክተት ሲያውጁ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊባል በሚችል መልኩ ነው አብሯቸው የተሰለፈው። ሁሉም ኢትዮጵያዊም ዋጋ ከፍሏል። ዋጋ ከፍለው ነጻነት ያመጡትን ጀግኖች ኢትዮጵያውያንን ዘርህ ከዚህ ነው ወይም ከዚያ ብለው ዋጋ አልነሷቸውም።ዋና የሚባሉት የጦር ጀነራላቸውም የዶጋሊው ጀግና ራስ አሉላ አባነጋ ነበሩ። የትግራይ ህዝብ የአጼ ምኒሊክን የጀግንነት ታሪክ ከልብ የሚያደንቅ እና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት በሆነው የአድዋ ድል ታሪክ እርሱም እንደማንኛውም ኢትዮጵያውያን የሚኮራበት እና የሚጠብቀውም ጭምር ነው። የመለስ ዜናዊም ሆነ የከሃዲ ካድሬዎቹ የክህደት ታሪክ በፍጹም የትግራይን ህዝብ አመለካከት ይወክላል ብዬም አላስብምም፣ አላምንምም።

አዎን አጼ ምንሊክ በዛን ወቅት እንደቅጣት ይፈጸም የነበረውን እጅ እና እግር የመቁረጥ ነገር መጀመሪያ አካባቢ ይፈጽሙ ነበር። ይህን ያደርጉ የነበረው እሳቸው ብቻም አልነበሩም። አጼ ቴዎድሮስም ይህን ያደርጉ ነበር አጼ ዮሃንስም ይህን ያደርጉ ነበር። ንጉስ አሊም የሳቸው ልጅ የሆነችም ንግስት መነንም ይህን ያደርጉ ነበር። ነገሩ የዘመኑ የፍትህ አሰጣጥ ኋላ ቀርነት እንጂ የሰዎቹን የክፋት መጠን አይገልጽም። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ግን በፍጹም አጼ ዮህንስንም ሆነ አጼ ቴዎድሮስን በክፉ ሲያነሱ ሰምቼም አንብቤም አላውቅም። ይህ ሊሆን የቻለም ምናልባትም ሌሎች ኢትዮጵያውያን ታሪክን በታሪክነቱ ለመረዳት ስለመረጡ ይሆናል።
ይህም ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ቅጣት በአዋጅ ያስቀሩት አጼ ምኒልክ ነበሩ። ታዲያ የታለ ለዚህ በጎ ስራቸው ክብሩ?? የህወሃት ከሃዲዎች እውነት እና ክብር የት ያውቁና?!
የባንዳ ልጆች ምን ያህል በአያቶቻቸው እንዲሁም በአባቶቻቸው ታሪክ ቂም ይዘው ይህን ህዝብ እና አገር እንደሚያሰቃዩ የግለሰቦቹን ቀዳሚ የቤተሰብ ታሪክ በማየት መገንዘብ ይቻላል። የስርዓቱ ቁንጮ እና የክህደቱ ዋና መሪ መለስ ዜናዊ የሚያስተዳድረውን ህዝብ እና አገር ባለፈ ባገደመ ቁጥር የሚዘልፈው ወዶ እንዳይደል የትግራይም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ሊገነዘብው ይገባል።
ከታች በአቶ መለስ ዜናዊ መኖሪያ ቤት በኩራት ተሰቅሎ በልጅነት ዘመን ያየሁት እና ዛሬ በዘመን አመጣሹ ኢንተርኔት ተበትኖ ከብዙ አመታት በኋላ እንደገና ለማየት የበቃሁትን የአቶ መለስ ዜናዊ የክህደት መሰረት የሆኑት የአያቱ የባሻ አስረስን ፎቶ ለአስረጅነት ከዚህ አያይዣለሁ። ጀግኖች ዱር ቤቴ ብለው ለአገር ነጻነት ሲዋደቁ እሳቸው ከወራሪው ሰራዊት ወታደር ጋር በኩራት ካባ ደርበው ይታያሉ።





የታሪክ ክህደት ቁጥር 3
<<በ1881 ዓ.ም. ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ የትግራይን ህዝብ ኑሮና የወደፊት ዕጣ የጎዳ ድርቅና በሽታ በድንገት ተከሰተ። እስከ ዛሬ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ የእያንዳንዱ ቤተሰብ የቁም ከብቶች እንዳለ አለቁ። ከቁም ከብቶች ባለፍ የዱር አራዊት የመሞት ምክንያት በምኒሊክ ከተተገበረ የኢጣልያ እቅድ መመንጨቱን የሚጠረጥሩ አሉ። ይህ ዕቅድ አፍሪካውያንን በበታችነት ከሚቆጥሩ የአውሮፓ ሃያላን አገራት ኢጣልያን በመቋቋም ላሳየው ቆራጥ ድፍረት የትግራይ ህዝብ ለመቅጣት የታቀደ እንደነበር የሚያምኑ በርካታ ናቸው።>>[10]
አቶ ብስራት እንዳሉት በዘመኑ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ መጥቶ እንስሳቱን ፣ አራዊቱን እና ሰዉንም ጭምር አጥቅቶ እንደነበር የተዘገበ የታሪክ ኹነት ስለሆነ እሱ ላይ ክርክር ማንሳት አልፈልግም። ነገር ግን ከልጅነት ጀምሮ አባቶቻችን እንደነገሩን ይህ ድርቅ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በመልከዓምድራዊ አቀማመጥ በአብዛኛው ተመሳሳይ በሆነው በወሎ ፣ በጎጃም ፤ በዛኔው አጠራር በበጌምድር እንዲሁም በኤርትራም ጭምር ነበር የተከሰተው። ታዲያ ለዚህ የተፈጥሮ ክስተት እንዴት ሆኖ ነው አጼ ምኒሊክ ሊጠየቁ የሚገባው?? የእርዳታ ገንዘብ አሸዋ እየሞሉ እህል ነው ብለው ሸጠው ገንዘብ አልሰበሰቡ። እሳቸው የህፃናትን ነብስ ለማዳን ተብሎ ከውጪ ለጋሾች የተላከን ብር በትግራይ ህጻናት ነብስ ላይ ተረማምደው አልበሉት። የተለገሰውን እህል በየመንገዱ ከምረው ህዝብ በረሃብ እያለቀ እንዲበሰብስ አላደረጉ። ወይም የተለገሰውን እህል በመኪና እየጫኑ ወደሱዳን እና አረብ አገራት ወስደው አልቸበቸቡት[11]። እንደው በምን የንጉሱን መልካም ስም ላጉድፍ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል?? በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጣሊያን ጋር ተባብረው ይላል። ምን ብለው ነው የሚተባበሩት?? እባክይ የጣሊያን መንግስት ሆይ በቫቲካን ያሉት ፖፕ ለእግዚያብሄር ትግራይ ላይ ዝናብ እንዲያቆም ጸልዩ ብለው ነው ወይስ ሌላ ጣልያኖች የሚያውቁት ዝናብ ማቆም የሚይስችል ተዓምር ነበራቸው?? በኢትዮጵያ ከዚያም በፊትም ሆነ በኋላ የዝናብ መዛባት እና ድርቅ እንግዳ ነገር አይደለም። እናስ በቅርብ ጊዜ የታዩትን ተከታታይ የድርቅ እና የተፈጥሮ መዛባት ክስተቶች አጼ ምኒሊክ ከሞቱ ከ100 ዓመት በኋላ ማነው ያስከሰታቸው? የንጉሱ መንፈስ?? እንኚህ ናቸው እንግዲህ ሚኒስቴርም ፣ ኮሚሽነርም ሆነው አገር እያስተዳድሩ ያሉት። በትግሪኛ አንድ ተረት አለ "ልማደኛ ሓሳውስያ በቕሊ ቀርኒ አውፂኣ ኢሉ ይምስከር" ወደ አማርኛ ስመልሰው "ልማደኛ ውሸታም በቅሎ ቅንድ አወጣች ብሎ ይመሰክራል" ማለት ነው። ብስራት አማረ እና የህወሃት መሪዎች በምን አይነት አፀያፊ የውሸት ጥበብ እንደተካኑ በግልፅ የሚያሳይ ነው። የትግራይ ህዝብ ዛሬ ከውስጡ በወጡ አሪዎሶች አፉ ተለጉሞ ቢያዝም የሚሆነውን እና የሚባለውን በአይኑ እያየ በስሙ ሲነገድ እና አገር ሲሸጥ አይቶ እንዳላየ ሆኖ እንደ ሌላው ወንድሙ ቀን እስኪወጣ እየጠበቀ ቢሆን እንጂ ይህን የተጨማለቀ የህወሃትን ስራ መቼም ቢሆን ትክክል ብሎ ይቀበላል የሚል እምነት ኖሮኝ አያውቅም።





የታሪክ ክህደት ቁጥር 4
<<የሃሰት ታሪክ በመመንዘር የሃገሪቷን ታላቅ ቅርስና ትክክለኛ ገጽታም መሸርሸር ችለዋል።የማህበረሰቡ አብዛኛው ክፍል ማንበብ እና መጻፍ በማይችልበት ሁኔታ ታሪክን ጠምዝዞ በመቸርቸር ፈጠራው የተሳካና እውነተኛ እንዲመስል አድርጎት ቆይቷል። ያለመሰረታዊ ማስረጃ ብዙ መጻህፍት ተጽፈዋል።እንደ እውነተኛ የኢትዮጵያ ታሪክ ተደርጎ ታዳጊ ህጻናት በትምህርት ቤቶች ተረታ ተረት ተምረውበታል። እነዚህ ሁሉ ለሸዋ ገዢዎች ዙፋን መጠናከር ታሳቢ ያደርጉ ከእውነት የራቁ ተረቶች መሆናቸው ግን አልቀረም ። በአሜሪካ ላይብራሪ ኦፍ ኮንግረስ ምርምር ዋና ክፍል ኢትዮጵያ የተዘጋጁ ጥናታዎ ጽሁፎች ሃሰቱን በተመለከት ያረጋግጡታል።>>
ይልና አንድ ከኋላ ኪሱ አውጥቶ የጻፈው የሚመስል ከእንደርሱ አይነት ጭንቅላት እንጂ ከአንድ የታሪክ ተመራማሪ አእምሮ የወጣ በማይመስል አጻጻፍ የተጻፈ ጽሁፍ በትምህርተ ጥቅስ አድርጎ ያስቀምጣል። በጥቅስ የተቀመጠው ጽሁፍ ሳይቴሽን ስላለው በጉጉት የጽሁፍን ምንጭ ለማየት ወደ መጽሃፉ የመጨረሻ ገጾች ላይ ሄድኩኝ። ያገኘሁት ሳይቴሽን ግን እንዲህ ይላል:-Ethiopia: a county study, p. 91. መቼም ጉድ ነው። አንድ የታሪክ ምርምር ለዚያውም ከአለማችን ትልቁ በሆነው የኮንግረስ ቤተ መጻህፍት የተደረገ ምርምር እንዲህች ያለች ኩርማን ለመጀመሪያ አመት የኮሌጅ ተማሪ የሳምንት የቤት ስራ እንኳን የማትበቃ ርዕስ ተሰጥቶት ሊሰራ ይችላል ብሎ ሰው ያምናል ማለቱ ያው የተለመደው የህወሃት ሰው መናቅ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላ። ለነገሩስ የክህደቱ ጳጳስ መለስ ዜናዊስ አፉን ሞልቶ የአድዋ ድል የነፍጠኛው ተረት ተረት ነው ብሎስ አልነበር። ከፕሮፌሰር መስፍን አማርኛ ልዋስና ሰዎቹ የለየለት የክህደት ቁልቁለት ላይ የተቀመጡ ስለሆነ ለማያውቃቸው እንጂ ለኛማ ከበቁን ዘመናት ተቆጠረ።
ወደ ዋናው የክርክሬ ጭብጥ ልመለስና በአብዛኛው በኢትዮጵያ በጽሁፍም ሆነ በአፈ ታሪክ ያሉ የቅርብ ጊዜ ታሪኮቻችን የትርጉም ካልሆነ የኹነት ክርክር ሊያስነሳበቸው የሚችል ጉዳይ የለም። ይህም የሆነው ከበቂ በላይ በአገር ውስጥ የታሪክ ጸሃፊውችም ፤ አውሮፓውያንም ጭምር የተጻፈባቸው በመሆኑ ነው። ስለዚህ ይህን "ተረታ-ተረት" ለማለት ወኔው ካለህ ለፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ፈልገህ ንገራቸው። ማሞ ቂሎ እንደሆንክ በትህትና ነገረው ይመልሱሃል።
የኢትዮጵያን ታሪክ ሞቅ ሲል ማናናቅ የመቶ አመት ነው ማለት ፤ ሲቀዘቅዝ ደግሞ ኑ 2ሺኛውን ዘመን እናክብር ብሎ ማላዘን የወያኔ መገለጫ ባህሪ ነው። ታሪክ እንዲህ አንድ መደዴ መሃይም ካድሬ እንደፈለገ የሚሰቅለውና የሚያወርደው ጉዳይ አይደለም። ይልቁንስ የታሪክ ምርምር ለሙያው የበቁ ሰዎች ማስረጃ እያጣቀሱ ለብዙ ጊዜያት በአንድ የጋራ አተረጓጎም ላይ እስኪሰክኑ ድረስ ከግል የፖለቲካም ሆነ ጊዜያዊ የስሜት ጥቅም ታቅበው የሚሟገቱበት ውስብስብ ሳይንስ ነው። እንደ ወዲ ዜናዊ እና አቶ ብስራት ያሉ የታሪክ አሽክላዎች ግን ገና ለገና እነሱ ከቤተሰባቸው የኋላ የባንዳ አሳፋሪ ታሪክ ከመነጨ ከፍተኛ የበታችነት ስሜት ተነስተው ጠላት ነው የሚሉትን አማራውን ህዝብ አንገት እናስደፋለን ብለው መሬት ጠብ የማይል የታሪክ ቡትቶ አምጥተው አቧራቸውን ያቦኑብናል።





የታሪክ ክህደት ቁጥር 5
<<የአድዋ ጦርነት የምኒሊክን ታሪክ ትልቅ ሰው አስመስሎ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ብሔርተኛ እና ጀግና መሪ በምትፈልግበት ወቅት ያለ ቦታው የተገኘ (ሰረዝ የተጨመረ) ሰው ምኒሊክ ወደደም ጠላ የአድዋ ጦርነት የማይቀር ታሪካዊ አጋጣሚ ነበር። ምኒሊክ ግዛቷ የተቀናነሰ አነስተኛ ኢትዮጵያ አጼ ብቻ ተብሎ ለመንገስ እቅድ እንዳለው ጣልያኖች አስልተው ደርሰውበት ነበር። አዲሱ ታዛዣቸው(ሰረዝ የተጨመረ) ሀገሩን በማስከበር ረገድ እንድ ዮሐንስ ሃገር ወዳድ አለመሆኑን ተገንዝበዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያውን የጥንት እና ህዝቦችዋ ለነጻነት ያላቸውን ቀናኢነት ታሳቢ ሳያደርጉ በምኒልክ ፍርሐት እና ስግብግብ ተፈጥሮ(ሰረዝ የተጨመረ) ብቻ ሀገሪቷን በቅኝ አገዛዛቸው ስር ለማስገባት ያነሳሳቸው ስሌት ለውድቀትና ሽንፈትም ዳርጓቸዋል። የራስ አሉላና ሌሎች ጀግኖች በህይወት መኖር ሌላው የጣሊያኖች የተሳሳተ ስሌት አድዋ ላይ ራሳቸውን አዋርደዋል። የአድዋን የአንድ ቀን ጦርነት በድል ለመፈጸም መረጃዎች ወሳኝ እንደነበሩ ይታወቃል በረቀቀ የጦርነት ጥበብና ወታደራዊ ታክቲኮች ከሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ልቀው የተገኙት አሉላ የኢጣልያ ሽንፈት አድዋ ላይ ዳግም እውን እንዲሆን ጥሩ አጋጣሚ ሆነዋል።>> [12]
መቼም ህወሃት ከሁለት አስርት አመታት በላይ ጆሮ ሰጥቶ ለሰማኝና ላዳመጠኝ ሁል ምን ያህል በውሸት የሰከረ አደገኛ ቡድን እንደሆነ ለማስረዳት የቻልኩትን ያህል ሞክሬያለሁኝ። ተራው ታጋይ በእንደ ወዲ ዜናዊ እና ብስራት አማረ ባሉ ፍጹም አደገኛ አወናባጆች እና ከሃዲዎች እየተነዳ ነው የአገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ታሪክም ፤ የአገራችን ኢትዮጵያም ክብር እና ሉኣላዊነትም አደጋ ላይ የወደቁት።
በምኒሊክ፣ በአጼ ሃይለስላሴ ጊዜም ሆነ በደርግ ወቅት አጼ ዮሃንስን እና ራስ አሉላ አባነጋን በመደበኛው የታሪክ ስርዓተ ትምህርትም ውስጥ ሆነ በአፍአዊ የታሪክ ትምህርት ከጀግንነታቸው እና አገር ወዳድነታቸው በቀር በክፉ ስማቸውን የሚያነሳ ኖርም የሚያውቅ አይመስለኝም። ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነውና ውስጡን በርብረን እናውራ ቢባል ግን ምንም ረብ የለሽ እንከን ማውጣት ይቻላል። ያ ግን ጥቅም የለውም። ይልቁንስ ታሪክ ለትውልድ መኩርያ እና አቅጣጫ ማሳያ ነውና ለበጎ ታሪካችን ተገቢውን ቦታ ሰጥተን መንከባከብ ተገቢ ነው። ለደንቆሮው አቶ ብስራት ግን ጀግና ለመባል አንድ ሰው ከትግራይ መምጣት አለበት። ታሪኩ ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ ህወሃት የስልጣን መንበሩ ላይ እስኪወጣ ድረስ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞውን የምኒልክ የጦር መሪ ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴን ፣ ኦሮሞውን ጀግና አብዲሳ አጋን ፣ የትግራዩን ጀግና ዘርኣይ ደረስን ፣ የትግራዩን ጀነራል ራስ አሉላ አባነጋን ፣ ዛሬ ዛሬ በኤርትራዊነት የሚመደቡትን ነገር ግን ያኔ በኢትዮጵያዊነት መስዋትነት የከፈሉትን አብርሃም ደሞጭ እና ሞገስ አስገዶምን ጀግንነታቸውን ሲያከብር ፣ ሲዘክር እና ሲያስብ ነው የኖረው። አጼ ዮሃንስን ጀግና ብሎ አጼ ምኒልክን ፈሪ ለማለት መከጀል ከፍጹም ዘረኝነት የዘለለ ሌላ ትንታኔ ሊሰጠው አይችልም።
ከዚህ ዘባተሎ የታሪክ ክህደት በፊት የምኒሊክን የአድዋ ድል ወሳኝ አመራር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገባ መጽሃፍም ይሁን ንግግር ሰምቼም አላውቅም። ስለ አጼ ምኒሊክ የጦር ስትራቴጂ አወጣጥ እና አመራር ብዙ የተጻፈለት እና የተነገረለት በመሆኑ ለዚህ ተራ እና የወረደ ቅጥፈት ማስተባበያ ለመስጠት ጊዜ አላጠፋም። ይልቁንስ ከላይ ስላሰመርኩባቸው ጉዳዮች ትንሽ ልበል። "ያለቦታው የተገኘ ሰው" ምን ማለት ነው??እናስ ጣልያን አገር ሲወር ሸዋ ላይ እጃቸውን አጣጥፈው መቀመጥ ነበረባቸው ማለት ነው? ሻዕቢያ ባድመን ሲወር እዛ ሊዋጋ የመጣው ኢትዮጵያዊ መምጣት አልነበረበትም ማለት ነው?? እንደዚህ ነው ለአገር ነጻነት ለመሞት የመጡ ኢትዮጵያውያንን የትግራይ ህዝብ የሚያመሰግነው?? መቼስ ነው በታሪክ አጼ ምኒሊክ የጣሊያን ታዛዥ ተብለው የሚታወቁት?? በአድዋ ድል የተደመደምው ጦርነት የተጀመረውስ የኢጣልያ መንግስት የውጫሌ ውል አንቀጽ አስራ ሰባትን የአማርኛውን እና ጣሊያንኛውን ትርጉም አዛብቶ በማቅረቡ ለውሉ አልገዛም በማለታቸው አልነበረምንም?? ተስማምተው ለፈረሙት ውል አልገዛም ፤ አይን ያወጣ ማጭበርበር መኖሩን ሲያውቁ በዘመናዊ ወታደር እና መሳሪያ ለታጠቅ አውሮፓዊ ሃይል እምቢ ከማለት በላይ ምን ጀግንነት አለ። አዎን ለእውነት ፣ ለነጻነት ፣ ለሉአላዊነት ከመቆም በላይ ምን ጀግንነት አለ?? አዎን የህወሃት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግስታት የድንበር ማካለያ ኮምሽን በባድመ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ ባድመ ለኛ ተወሰነች ውጡና ጨፍሩ ብሉ ህዝቡን ከበሮ ሲያስደልቅ አልነበረም ወይ?? ኋላ ላይስ በርግጥም ባደመ የተካለለችው ወደ ኤርትራ መሆኑ ግልጽ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ የሞተለትን ጉዳይ ለቁራጭ መሬት ብለን ጦርነት አንገባም ያለው ወዲዜናዊ አልነበረም ወይ?? ይሄኮ ከመቶ አመት በፊት የሆነ ጉዳይ አይደለም። ሁላችንም በህይወት አለን።
እኔ መቼም አውሮፓዊ ቅኝ ገዢን ያለፍርሃት በጀግንነት ተጋፍጦ በነጻነት ያቆየውን ሰው "ዘር" ቆጥሮ አማራ በመሆኑ ብቻ እንደምን ሊያኮሰምን ይፈልጋል?? እኔ በበኩሌ ይሄ አስከፊ የጥላቻ ደዌ ከመሆን ያለፈ ምንም ምክንያት ላገኝለት አልቻልኩም።
"በምኒልክ ፍርሐት እና ስግብግብ ተፈጥሮ" አጼ ምኒሊክ በየትኛው ማስረጃ በፍርሃት እና በስግብግብነት ተወንጅለው እንደሚያውቁ አንብቤም አላውቅ። ንጉሱ ገና በልጅነታቸው የሸዋው ንጉስ ልጅ በመሆናቸው ለስልጣኔ ያሰጋኛል በማለት ይመስላል አጼ ቴዎድሮስ በመቅደላ አስረዋቸው ነበር። ታዲያ የያኔው አቤቶ ምኒሊክ በኦሮሞዎቹ የየጁ ንጉስ አሊ እና ንግስት ወርቂቱ ትብብር ከአስቸጋሪው የአጼ ቴዎድሮስ የመቅደላ እስር ቤት አምልጠው ነው ወደሸዋ በመመለስ የሸዋ ንጉስ ተብለው የተሰየሙት። መቼም እንደ አጼ ቴዎድሮስ ተፈሪነት ከሳቸው እስር ቤት ለማምለጥ መሞከር የማይታሰብ እና ብዙዎች ሞክረው ያልሆነላቸው ጉዳይ ነው። እርግጥ ነው የየጁ ኦሮሞው ራስ አሊ እና የወሎዋ ንግስት ወርቂቱ ትብብር እና ድጋፍ ታክሎበት ነው አቤቶ ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው ሊወጡ የቻሉት። መቼም ይሄ የፈሪ ስራ አይደለም። አጼ ቴዎድሮስ ያሰሯቸውን አውሮፓዎያንን ለማስለቀቅ እኮ የእንግሊዝዋ የወቅቱ ንግስት ቪክቶሪያ በጀነራል ናፒየር የሚመራ ብዙ ሺህ ጦር መላክ አስፈልጓት ነበር።
ይልቁንስ አጼ ምኒልክ የሚታወቁት ድርቅ ሲመጣ ግብር በመቀነስ እና በፍትሃዊነታቸው ነው። መቼም ከእንደ ብስራት አይነቱ የህሊና ደሃ እና ሃሳበ ጉድጉድ ግለሰብ ካልሆነ በቀር አጼ ምኒሊክን በስግብግብነት መወንጀል ይቅር የማይባል ቅጥፈት ነው። እንዲያው ለመሆኑ አቶ ብስራት ስግብግብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ከፈለግክ "ስግብግብ" ማለት አሁን ልክ በኢትዮጵያ በወያኔ አገዛዝ እየሆነ እንዳለው ነው። ሰዎች በረሃብ እየረገፉ ባሉበት አገር የስርዓቱ ቁንጮዎች በርዳታ እና ብድር ወደ አገር ከሚገባው ገንዘብ ውስጥ ከ11.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ በተለያየ መንገድ ከአገር ማሸሽ ፤ ገንዘብ ተገኘ ተብሎ ቅዱሱን የጉዲፈቻ ባህል በመቶ ሚሊዮን ዶላር ወደሚያስገኝ የመበልጸጊያ መንገድ መቀየር፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ሳውዲ አረቢያ ብቻ ሴት ኢትዮጵያውያንን በወር እስከ 45,000 ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እንደሚደርስባቸው እየታወቅ ወያኔ ገንዘብ ስለሚያገኝበት ብቻ መላክ፤ ሰፋፊ የአገሪቷን የ እርሻ መሬቶች ገንዘብ ተገኘ ተብሎ ለአረብ እና ህንድ ባለሃብቶች መቸብቸብ ነው መስገብገብ ማለት።
ሰዎች ስለ አጼ ምኒሊክ ታሪክ መስማት ካለባቸው ከበቁ የታሪክ ጸሃፊዎች እንጂ ከካድሬ ለዚያውም ከህወሃት ካድሬ መሆን የለበምትም። ስለ አጼ ምኒሊክ ታላቅነት ታላቁ ኬኒያዊ ምሁር እና የታሪክ ተመራማሪ አሊ ማርዙዪ የምኒሊክን ታላቅነት ከባራክ ኦባማ መመረጥ ጋር አያይዘው በአሜሪካ በሚተላለፈ "ዲሞክራሲ ናው" ቴሌቪዢን ከአዘጋጇ ኤሚ ጉድማን ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በዋቢነት ከዚህ ገጽ ግርጌ ያለውን ሊንክ ጠቅ በማድረግ ይመልከቱ።[13]
የአድዋ ድል አኩሪ ታሪክ በምኒሊክ ወሳኝ አመራር፤ በጦር መሪዎቻቸው ብቁ እና ቆራጥ ፊት አውራሪነት እንዲሁም በብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ቆራጥ ተጋድሎ እውን የሆነ ድል ነው። አጼ ምኒሊክ በጦር መሪነት ካሰለፏቸው ኢትዮጵያውያን ውስጥ ጣይቱ ብጡል፣ ራስ ወሌ ብጡል ፣ ራስ መንገሻ አትከም፣ ባሻይ ሓጎስ ፣ ራስ አሉላ አባነጋ ፣ ራስ መንገሻ ዮሃንስ ፣ ዋግሹም ጓንጉል ፣ የወሎው ራስ ሚካኤል ፣ ደጃዝማች ሰንጋል ፣ ራስ መኮንን ፣ ራስ ገበየሁ፣ ራስ ስብሃት ፣ በጅሮንድ ባህታ ገሰሰ ፣ የጎጃሙ ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ተሰማ እንዲሁም ደጃዝማች ገሰሰ ይጠቀሳሉ።
ከወያኔ በፊት የትኛውንም ድል በተለይ እንደ አድዋ ያለውን በውጭ ወራሪዎች ላይ የተገኘን ታላቅ ድል የኢትዮጵያ ነገስታት "የኢትዮጵያውያን ድል" ከማለት በዘለለ የአማራ ፣ የትግሬ ወይ የኦሮሞ ድል ብለው አሳንሰውም አያውቁም። ያ ደግሞ ትልቅነታቸውን እንጂ አቶ ብስራት እንደሚወሸክቱት የነገስታቱን ክፉ ጎን የሚያሳይ ጉዳይ አይደለም።
እርግጥ ነው አገር ተወሮ ፣ ነጻነት ተደፍሮ ፣ ህልውና አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት ለጠላት አድረው አገር ሲያስወጉ ፤ መረጃ ሲያቀብሉ ፤ መንገድ ሲመሩ ፤ ወገን ሲፈጁ እና ሲያስፈጁ በነበሩት ላይ የጊዜው የፍትህ ስርዓት በሚለው መሰረት እርምጃ ተወስዷል። 
የ እርምጃዎቹ ተመጣጣኝነት ላይ ክርክር ማንሳት ይቻል ይሆናል። ነገር ግን አገር ክህደት አሁንም ድረስ በየትኛውን አገር ከፍተኛ ወንጀል ነው ከፍተኛውንም ቅጣት ያስጥላል። ለዘመናት ሲባል እንደ ነበረው እኛም ፤ አባቶቻችንንም ምናልባትም አያቶቻችንም ለጣሊያን እንቁላል እየገበርን በገዛ አገራችን በባርነት እንቀር ነበር። ከነተረቱስ እንደዚህ አይደል የሚባለው :- "ምኒሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ ፤ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ።"





የታሪክ ክህደት ቁጥር 6
ጸሃፊው አጼ ምኒሊክን በቀጥታ እንዲሁም አጼ ኃይለስላሴን ደግሞ የንግስና ዘመናቸውን በመጥቀስ በባሪያ ንግድ የበለጸጉ አድርጎ ይወቅሳል። እስቲ ይህን ጉዳይ ያነሳበትን አንቀጾች እያነሳው የራሴን ምላሽ ልስጥ።
<< ስለኢትዮጵያ በርካታ ጥናቶች ያካሄዱ የታሪክ ተመራማሪዎች እና ጸሃፊዎች ምኒሊክን ለዚህ ተግባሩ <<የኢትዮጵያ የባሪያ ንግድ ድርጅት ባለቤት>> ማለታቸው አልተሳሳቱም።>>[14]
<< እነዚህ ብሔረሰቦች ፍትህ የማግኘት መብት የተነፈጉና በአብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች ተደርገው የማይታዩ ነበሩ። በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎችም በጎንደር እና ጎጃም መስመር ፣ መተማ ፣ አርማጭሆ በተባሉ ስፍራዎችና በተወሰነ መጠን ከአርማጭሆ ጋር በሚዋሰኑ የወልቃይት ምዕራባዊ ክፍሎች የባሪያ ንግድ ሲካሄድ እስክ 1960ዎቹ ታይቷል። በታሪካዊ እይታ በክርስቲያን ኢትዮጵያ ማህጸን ውስጥ መጀመሪያ በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ በምኒሊክ አባት በሃይለመለኮት በመጨረሻም እስክ ህልፈቱ ድረስ በዓጼ ምኒሊክ የባሪያ ንግድ ስራ የሸዋ ገዢዎች ቅርስ መሆኑ ታውቋል።>>[15]
በኢትዮጵያ ታሪክ ባሪያ ፍንገላ እንደነበረ ማንም የሚክደው ሃቅ አለነበረም። በጠራ ሁኔታ አጼ ምኒልክን ዋና ባሪያ ፈንጋይ አድርጎ የሚከስ ታሪካዊ ማስረጃ የለም። እርግጥ ነው እሳቸው ወደ ስልጣን መንበር ከመምጣታቸው በፊት ጀምሮ ለዘመናት ይካሄድ የነበረው የባሪያ ፍንገላ በዘመናቸውም ቢሆን ይካሄድ ነበር። ለዛ ደግሞ በቀጥታ እሳቸውን ተጠያቂ አድርጎ ማቅረቡ እምብዛም የሚያስኬድ ጉዳይ አይደለም። በኢትዮጵያ በአብዛኛው ይካሄድ የነበረው የባሪያ ስርዓት በአሜሪካ እና አውሮፓውያን ሰፋፊ የሸንኮራ ፣ ጥጥ እና ሻይ ቅጠል እርሻዎች ውስጥ በነጻ ጉልበት ማሰራት አልነበረም። ይልቁንም በመሳፍንቱ እና መኳንንቱ መኖሪያ ቤት የቤተሰቡ አባላት ሊሰሩ የማይፈቅዱትን የግርድና ስራዎች ማጽዳት ፣ ማብሰል ፣ እንዲሁም ቤት መጠበቅን የመሳሰሉ ስራዎችን ነበር የሚሰሩት። ይህም ቢሆን ባርነት ነው ና በምንም አይነት ማህበረሰቡ ሊያደርገው አይገባም ነበር።
ለማጣቀሻነት የአፊካን ሆሎኮስት የሚባል በአፍሪካ የተደርጉ እልቂትን ያስከተሉ ታርካዊ ክስተቶችን የሚመዘግበው ድረ ገጽ ላይ ያለውን በኢትዮጵያ ስለነበረው የባሪያ ፍንገላ ስርዓት የተጻፈውን ለአንባቢያን ከዚህ ገጽ ግርጌ አስቀምጫለሁኝ።[16]
ቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴን በሚመለከት በዚህ ጉዳይ ላይ ክስ ማቅረቡ የሞኝ ክርክር ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ገና ከመንገሳቸው በፊት እና በንግስት ዘውዲቱ የንግስና ዘመን በ1924 ልዑል አልጋ ወራሽ እያሉ ነው የባሪያ ፍንገላን በህግ በኢትዮጵያ እንዲታገድ ያደረጉት። ልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ይህን ከማድረጋቸውም በፊት የባሪያ ፍንገላ በኢትዮጵያ እንዲቀር ከሳቸው በፊት የነበሩት ነገስታት አጼ ምኒልክን ጨምሮ የራሳችውን አስተዋጽኦ አድርገዋል።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ልክ በባሪያ ንግድ እንደከበሩ አድርጎ የነገስታቱን መልካም ስም በጭቃ ለመለወስ የፈጠራ ክስ ለማቅረም መሞከር ከንቱ ልፋት ከመሆን አያልፍም።

እስቲ አጼ ኃይለስላሴ እ.ኤ.አ በ1963 በአሜሪካን አገር ታዋቂ በሆነው የሲቢኤስ ቴሌቪዢን ሚት ዘ ፕሬስ ፕሮግራም ላይ የዛሬዋ ታላቋ አሜሪካ የራሷን ዜጎች በእኩል አይን በማታይበት ወቅት ስለ የቆዳ ቀለም ልዩነት የተናገሩበትን ታሪካዊ ቃለ ምልልስ ቁራጭ ቪዲዮ ይመልከቱ[18]
ይልቅስ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ህጻናትን በማደጎ ስም በመሸጥ እየከበረ ያለው ማነው?? ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በግርድና ስም በየአረብ አገራት እየላከ ገንዘብ እየሰበሰበ እየከበረ ያለው ማነው?? አዎን ስሙን ሲያሳምሩት "ቻይልድ ትራፊኪንግ" ይሉታል ነገር ግን ዘመናዊ የባሪያ ፍንገላ እንጂ ሌላ ስም ሊሰጠው አይገባም። የወያኔ መንግስት በአንድ ህጻን እስክ 30,000 ዶላር ድረስ እየሰበሰበ እንደሚገኝ በ2007 በወጣ አንድ የኤቢሲ ቴለቪዥን ዘገባ መሰረት የመለስ መንግስት በአመት እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር ድረስ ከዚሁ አጸያፊ የህጻናት ንግድ እንደሚያገኝ የተዘገበ ጉዳይ ነው።[19]
አርማጭሆ እና መተማ አካባቢ ያለፈጠረ ታሪክ ይዞ መልከስከሱ ጉዳዩ ሌላ ነው። በአካባቢው ለዘመና ኗሪ የሆኑ የጎንደር ክፍለ ሃገር አማሮችን አፈናቅለው ሲያበቁ ቦታውን ወደትግራይ ከማካለል ጋር የተያያዘ ታሪክ ፍብረካ ወያኔያዊ አጉል ብልጣብልጥነት ከመሆን አያልፍም።
ልብ በሉ በንጉሳውያኑም ሆነ በጨካኙ የመንግስቱ ኃይለማሪያም ዘመን ያልነበረ እና በአሁን የወያኔ አገዛዝ እጅግ እየተስፋፋ የመጣው ለአቅመ አዳም ያለደረሱ የለጋ ህጻናት የወሲብ ብዝበዛ ንግድ እና ማዘዋወር ስለ ህጻናት ጉዳይ የሚቆረቆሩ ግብረሰናይ ድርጅቶችንም ሆነ ኢትዮጵያውያንን እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ ነው። ታዲያ እነዚህ የታሪክ አተላዎች ናቸው በበጎ አሳቢነት እና በቅን ፍላጎት ነጻነት ለማስጠበቅ ፣ አገር ለማሳደግ ፣ ስልጣኔ ለማስፋፋት የለፉ ፣ የተጉ አባቶቻችንን ባልተገራ የባለጌ አፋቸው የሚሰድቡ።[21]





የታሪክ ክህደት ቁጥር 7
<<በ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ አስርት አመታት አብዛኛዎቹ የባሪያ ንግድ ሰለባዎች ከአናሳ ብሔረሰቦች ወይም የስራ እድል ለማግኘት ከሌሎች ክልሎች ከሚጓዙ ህዝቦች የተገኙ ነበሩ። በአገሪቷ ደቡባዊ እና ሰሜን ምዕራብ የተከሰቲት ያልታወቁ ሰብዓዊ ሰቆቃዎች ታሪካዊ ምርመራ ለሚያካሂድ ሰው በርካታ ግፎች ፈልፍሎ እንዲሚወጣ ይታመናል። ከሃምሳ አመታት በላይ ሃገሪቷን በጭካኔ የገዛው የመጨረሻው ንጉሰ ነገስት ኃይለስላሴ ይህ ድርጊቱ ቢያንስ በታሪክ ሳያስጠይቀው አልቀረም።>>[22]

በኢትዮጵያ ታሪክ ዘመናዊ መንግስት የማቋቋም ሙከራ በአጼ ምኒልክ ከተደረገ በኋላ በዘመናዊ መንገድ አገራችንን ለማስተዳደር የበቃ መንግስታዊ መዋቅር እና መተክል ማድረግ የቻሉት አጼ ኃይለስላሴ ነበሩ። አጼ ኃይለስላሴ ለዘመናዊ ትምህርት የሚሰጡት ዋጋ እጅግ ከፍ ያለ ነበር። ስለዚህም ብዙ ኢትዮጵያውያንን በአገር ውስጥም በውጭ አገርም ልከው ዘመናዊ አስተዳደርን በአገር ለማስፋፋት ይህ ነው የማይባል ጥረት አድርገዋል።

አገራችን በዚህ ረገድ መልካም መሰረት ተጥሎ ወደፊት እየተራመደች በነበረችበት ወቅት ቂመኛው የፋሽስት ኢጣሊያ መንግስት ዳግም ኢትዮጵያን በቅኝ ለመያዝ እ.ኤ.አ በ1935 ወረራ ፈጸመ። በወረራው እና በቀጣይም በአምስቱ አመት የጣሊያን አገዛዝ ዘመን ብዙ የተደረጉ ግስጋሴዎች ወደኋላ ተመለሱ። በ1941 ፋሽስት ኢጣሊያ ከኢትዮጵያ ስትባረር አገሪቱ እንደገና ከጦርነት ድቀት አሃዱ ብላ መጀመር ግዴታዋ ነበር።

እ.ኤ.አ ከ1941 እስክ 1974 ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በግርግር ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ለ33 አመታት አገሪቷን ለመገንባት እና ትምህርትን ለማስፋፋት ይህ ነው የማይባል ጥረት አድርገዋል። በዚህ አገር የመገንባቱ ጥረት ንጉሱ በየግዛቱ ያሉ መሳፍንትን ስርዓት ከማስያዝ ይልቅ በማባበል እና በማስታገስ ለመያዝ መሞከራቸው የኋላ ኋላ ለህዝብ ቁጣ ማየል እና ለስርዓቱ መናድ አስተዋጽኦ ማድረጉ አይካድም። ይሁን እንጂ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ በየ አስተዳደር ፊናቸው ለፈጸሙት በደል ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ተጠያቂ ማድረግ አላዋቂነት ከመሆን ያለፈ ትርጉም የለውም። መከሰስ እና መጠየቅ ካለባቸው እሳቸው ባደረጉት ነገር እንጂ ሌሎች በሰሩት አይደለምና።

ቀድሞ ነገር ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ራሳቸውን ከስልጣን ለማውረድ አመጽ ሲደረግባቸው እና በየቀኑ በደጃቸው ሰልፍ ሲወጣባቸው በጣም ሲከፋ አለማቀፍ ህግ በሚፈቅደው መሰረት በውሃ ፣ በአስለቃሽ ጭስ እና በቆመጥ ካልሆነ እርምጃ እንዲወሰድ አልፈቀዱም። በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በጉልበት በስልጣን ጉብ ብለው አልወርድም ያሉት የነ መለስ ቡድን እና ጀሌዎቹ ግን በጠራራ ጸሃይ እንደ ነብዩ አለማየሁ የመሳሰሉ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህጻናትን በአልሞ ተኳሾች አስፈጇቸው። ይህ ብቻም አይደልም: በጋምቤላ ፣ በኦጋዴን ፣ በአዋሳ ፣ በአደባባይ ኢየሱስ ፣ የለየለት ጭፍጨፋ አካሄዱ። በቀጣይነትም በወልቃይት እንዲሁም በኦጋዴን በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊያስጠይቅ በሚያስችል ደረጃ አሁንም ጭፍጨፋው እንደቀጠለ ነው።

የዚህ መጽሃፍ ደራሲ አቶ ብስራት አማረ እራሱ በበረሃ በነበርንበት ወቅት ስንት ህንፍሽፍሽ ሰበብ እና በሌሎችም የፖለቲካ ውሳኔዎች ከላይ ከነመለስ ዘናዊ እና አባይ ጸሃዮ በተሰጡ የግድያ ትዕዛዞች የፈጃቸው የትግራይ ጨቅላ ህጻናት ደም አሁንም ድረስ ይጮሃል። የነኚህ ህጻናት ደም ደመ ከልብ ሆኖም አይቀርም

Apr 4, 2013

ኢህአዴግ የሠላማዊ ሰልፍ መብታችንን ማረሳሳቱ ነው እንዴ? (አያደርገውም!)

ኤልያስ
እኔ የምላችሁ…ኢህአዴግ 9ኛውን የፓርቲውን  ጉባኤ ያካሄደበትን እጅግ የተንቆጠቆጠ “ባለ 7 ኮከብ” (ኮከብ የመስጠት ኮፒራይቱ የራሴ ነው!) የስብሰባ አዳራሽ አይታችሁልኛል? (በኢቴቪ ማለቴ ነው!)  በአካልማ ማን አስደርሷችሁ! (አዳራሹ ከ2ሺ ሰው  በላይ አይችልማ!) ለነገሩ አዳራሹም ቢበቃ ሌላም  የመግቢያ መስፈርት እንደነበረው ሰምቻለሁ። ምንጮቼ እንደነገሩኝ --- “ተራማጅ” ወይም “አብዮተኛ” ያልሆነ  ግለሰብም ሆነ ፓርቲ ---- እንኳንስ በጉባኤው ሊሳተፍ ቀርቶ በአካባቢው ዝር ማለትም አይፈቀድለትም ነበር! (አሉ ነው እንግዲህ) በነገራችሁ ላይ አሁን ባልኩት ጉዳይ ዙርያ ማስረጃም ሆነ መረጃ እንደሌለኝ ከወዲሁ  ለመግለፅ እወዳለሁ (እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር አሉ!) እናላችሁ ---- ኢህአዴግ ከውጭ አገር 13 “እህት  ፓርቲዎች”ን ጋብዞ ከአገር ውስጥ አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ ያልጋበዘው አንዳንዶች እንደሚያስወሩት በ“ንቀት” ወይም “በአገር ውስጥ ምርት ስለማይኮራ”አይደለም ! (የሥጋ ዘመድ እንደሌለው በባዕድ ፓርቲዎች መታጀብ ምኑ ደስ ይላል?) በነገራችሁ ላይ ተጋባዥ የውጭ አገር ፓርቲዎቹ “እህት ፓርቲዎች”የሚል ስያሜ የተሰጣቸው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ እንደሆነ ከሁነኛ የገዢው ፓርቲ ምንጮች “ሁነኛ መረጃ” ማግኘቴን ስነግራችሁ በኩራት ነው፡፡ (የተርብ ካድሬ የፈጠራ ውጤት ነው ተብሏል!) በአሁኑ የኢህአዴግ ጉባኤ ምን እንዳስደሰተኝ ታውቃላችሁ? አንደኛ እንዳለፈው የአዳማ ጉባኤ ኢህአዴግ የሠላማዊ ሰልፍ መብታችንን ማረሳሳቱ ነው እንዴ? (አያደርገውም!)“ጓድ! ጓድ!” የሚል ነገር ብዙም አልሰማሁም (ጥሎብኝ ሶሻሊዝም አይመቸኝም!) ሁለተኛው ያስደሰተኝ ነገር ደግሞ የኢህአዴግ ግንባሮች በነፍስወከፍ (በፉክክር አልወጣኝም!) ያስገነቧቸውን ቄንጠኛ የጉባኤ አዳራሾች መመልከቴ ነው፡፡ (የአዳራሽን ችግር እነ “አንድነት”ፓርቲ ይንገሯችሁ!)አንዱ አሽሟጣጭ ወዳጄ ስለኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ምን እንዳለኝ ልንገራችሁ አይደል---(አደራችሁን ኢህአዴግ እንዳይሰማ!) የዘንድሮ ጉባኤ የተካሄደው “አዳራሽ ከእኔ፤ ጉባኤ ከእናንተ” በሚል መርህ ነው ብሎኝ ቁጭ አለ፡፡ እኔ እንኳን በዚህ አልስማማም፡፡ ለምን መሠላችሁ? የአመራሩን “አድርባይነት”ችግር ያጋለጠውን “ታላቅ ጉባኤ” እኮ ነው አፈር ድሜ ያስበላው! እኔ የምለው ግን --- ጉባኤው በእንግሊዝኛም ሲካሄድ ነበር ልበል --- (የአማርኛው ሳያንስ እንግሊዝኛውንም?)ከሁሉም በላይ ቅር ያሰኘኝን ደግሞ ልንገራችሁ። በጉባኤው ላይ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አባላት መጋበዛቸው አልተመቸኝም፡፡ (ጠንቋይ ቤት ሄጄ ወይም አዋቂ ነግሮኝ ግን አይደለም) ቆይ እስቲ --- የቻይና ፖለቲከኞች ምን ሊፈይዱልን ነው የተጠሩት?የቀድሞው የአገራችን መሪ ጓድ (ኮሎኔል) መንግስቱ ኀይለማርያም ምን እንዳሉ ሰምታችኋል? የአገራችን የረዥም ጊዜ ወዳጅ የነበረችው የሶቭየት ህብረት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሚኻኤል ጎርባቾቭ፤ በ11ኛው ሰዓት ክህደት እንደፈፀሙባቸው በምሬት ተናግረዋል፡፡ (ፖለቲከኛ ወዳጅ የለውም ለማለት ነው!)አንዳንድ እውቅ የፖለቲካ ተንታኞች ስለቻይና ምን ይላሉ መሰላችሁ? “ቻይና የሚያምርባት ቀለበት መንገድ ስትሰራ ብቻ ነው!” በዚህ እንኳን እኔም ራሴ እስማማለሁ፡፡ ለዘመናት ከአንድ ኮሙኒስት ፓርቲ ውጭ የማታውቅ አገር፤ ለኢህአዴግ ምን ልታስተምርብን እንደምትችል መገመት አያቅተንም! (እሱ ለራሱ በቋፍ እኮ ነው!)የእኔን ዋነኛ ስጋት ብነግራችሁ ግን ደስ ይለኛል። ምን አለ በሉኝ --- የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አባላት እንዲህ እግር ካበዙ ስንት ታጋዮች የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበትን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ከንቱ ያደርጉብናል፡፡ እዚህ አገር ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸውን ሲሰሙ በድንጋጤ አፋቸውን መያዛቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፤ ከዚያም “ተራማጅ ፓርቲ በሚመራው ልማታዊ መንግሥት ውስጥ ተቃዋሚዎች ምን ይሰራሉ? ይሄ የተራማጅ ፓርቲ ተፈጥሮም ሆነ መርህ አይደለም” በማለት ኢህአዴግን ይሞልጩታል (የአቋም መግለጫ ሁሉ ሊያወጡ እንደሚችሉ ጠርጥሩ!) እኔ የምላችሁ ግን … ቻይና ውስጥ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን የሚባል ነገር አለ እንዴ? አረ አይመስለኝም!ፓርቲዎችና የምርጫ ፉክክር በሌሉበት አገር ምርጫ ቦርድ ምን ይሠራል? (የሥራ እድል ይፈጥራል ካልተባለ በቀር!)የፓኪስታን ጠ/ሚኒስትር አንድ ወዳጅ አገር ይሄዱና ባቡር ሳይኖር የሃዲድ መስመር ተዘርግቶ ያያሉ፡፡ በዚህ ተገርመውም የአገሪቱን ፕሬዚዳንት “ባቡር በሌለበት ሃዲድ ምን ይሰራላችኋል?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ፕሬዚዳንቱም የዋዛ አልነበሩም “እናንተ አገር የፍትህ ሚኒስቴር አለ አይደለም እንዴ!” በማለት ዝም አሰኟቸው (ፍትህ ሳይኖር ፍትህ ሚ/ር--- ማለታቸው እኮ ነው!) ኢህአዴግ ሁልጊዜ በምን እንደሚያስገርመኝ ታውቃላችሁ? ራሱን ሲወቅስ ለነገ አይልም፡፡ የእሱ ችግር ምን መሰላችሁ? ወቀሳና ቅጣትን አይለይም። ወቅሶ ዝም ነው! (እንኳን ፓርቲ ህፃንም ቅጣት ያስፈልገዋል!) እናም--- “ችግሩን ሸፋፍነን ልናልፍ አይገባም!” ማለት ብቻውን ውጤት አያመጣም ለማለት ያህል ነው !እኔ የምላችሁ… ኢህአዴግ “የአመራሩ ችግር አድርባይነት ነው” ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው?(አንዳንዴ እኮ በወፍ ቋንቋ የሚያወራ ነው የሚመስለው!) በነገራችሁ ላይ አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ በአሉ ግርማ በአንድ የሥነፅሁፍ ሥራው ላይ “ከአድርባይ ብዕር ባዶ ይሻላል” በማለት ፅፏል፡፡ የዘመኑ ደራሲ ደግሞ “ከአድርባይ አመራር ባዶ ፓርቲ ይሻላል” እንደሚል እገምታለሁ (ከሰሞኑ የኢህአዴግ ግምገማ በመነሳት) እናንተ አንባቢዎቼ እንደምታውቁት እስከዛሬ ድረስ በገዢው ፓርቲ የአመራር ጉዳይ ውስጥ ገብቼ “ፈትፍቼ” አላውቅም (ህገመንግሥታዊ መብቴ እንደሆነ ባውቅም!) አሁን ግን የአመራሩ ችግር አድርባይነትና ኪራይ ሰብሳቢነት መሆኑን ከራሱ ከኢህአዴግ ስለሰማሁ መፍትሄ ለመሰንዘር እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ ፈታኝ ወቅት እኮ ዝምታ ከ“ጠላት” እንጂ ከ”ወዳጅ” አይጠበቅም፡፡ (“ወዳጅ” እንጂ “አባል ነኝ” አልወጣኝም!) እናላችሁ… ኢህአዴግ የፓርቲውን አመራር ለውጭ ማኔጅመንት በኮንትራት ቢሰጠው ጥሩ ይመስለኛል፡፡ አሃ… የኢህአዴግ አመራር ችግሮች ያለቅጥ በዙ እኮ! ይሄውላችሁ… በግልፅ እንነጋገር ከተባለ በዘንድሮው የኢህአዴግ ጉባኤ ፓርቲው የሰራው በጐ ነገር አለ ከተባለ፤ ቅድም እንዳልኩት ያስገነባቸው ቄንጠኛ የጉባኤ ብቻ ናቸው፡፡ ችግሩ ግን ምን መሠላችሁ?የጉባኤ አዳራሾች የመልካም አስተዳደር ችግርን ሊፈቱ አይችሉም፡፡ እንኳን የጉባኤ አዳራሾች የመንገድ እና የኮንዶሚኒዬም ግንባታዎችም ለመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄ አይሆኑም፡፡ በጉባኤው ላይ የህወሃት ሊ/መንበር “ልማቱ ሲቀላጠፍ የመልካም አስተዳደር ችግሮችም ይፈታሉ ” በማለት የሰጡት ሃሳብ የተሳሳተ መሆኑን የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ መናገራቸው አስደስቶኛል! (አንጋፋ የብአዴን ታጋይና በመተካካት ሥልጣን ያስረከቡ ግንባር ቀደም ባለሥልጣን መሆናቸው እንዳይዘነጋ!)ኢህአዴግ ራሱን “አድርባይ” ብሎ ሲገመግም ምን ሊል እንደፈለገ አልገባኝም ብያችሁ አልነበር ---- ስለዚህ ምን አደረግሁ መሰላችሁ --- “የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል” ያዘጋጀውን መዝገበ ቃላት አንስቼ ፍቺውን ማፈላለግ ጀመርኩላችሁ (ነገርዬው የአገር ጉዳይ ነዋ!) እናላችሁ እንዲህ ይላል- “አድርባይ አደራ ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን አድርባይ ሆነ ማለት ተስማምቶና መስሎ ኖረ ማለት ነው” ቆይ ግን --- የኢህአዴግ አመራር ከማን ጋር ነው ተስማምቶና መስሎ የኖረው? (እንወቀዋ!) ከተቃዋሚዎች? ከህዝብ? ከኪራይ ሰብሳቢዎች? ወይስ ከ”ሽብርተኛ”? (ይሄኔ ነው መሸሽ!) በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ህላዌ ዮሴፍ ደግሞ “የአመራራችን ቁንጮ የሚጠየቅበት አሰራር አለ ወይ?” ሲሉ መጠየቃቸው የመገረምና የመደነቅ ስሜት ነው የፈጠረብኝ፡፡ ኢህአዴግ ከ20 ዓመት በላይ ሲገዛን የተጠያቂነት ሥርዓት እንኳን አልዘረጋም ማለት ነው? (እንዲያ ከሆነ በመጪው ወር ምርጫ ያገናኘን!) ይቺን “አድርባይ” የምትል የፈረደባት ቃል ፍቺ ስፈልግ አዲስ ሃሳብ ብልጭ አይልልኝ መሰላችሁ … ለኢህአዴግ የአማርኛ ቋንቋ መፍቺያ መዝገበ ቃላት ማዘጋጀት!! እውነቴን ነው… የኑሮ ውድነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሳያንሰን ኑሮአችንን የአማርኛ ቋንቋ ፈተና አደረገብን እኮ! ቆይ እስቲ--“የቀለም ” ማለት ምን ማለት ነው? “ተቸካይ” ማለትስ? “ጥገኝነትስ?” “ኪራይ ሰብሳቢስ?” የሰሞኑ “ተራማጅ”የሚል ቃልስ? (ደርግም ተራማጅ መሆኑን ያውጅ ነበር ብዬ እኮ ነው!) አሁን ለምሳሌ ተቃዋሚዎች ፈፅሞ ሊገባቸው ያልቻለ ኢህአዴግ የሚያዘወትረው አንድ አባባል አለው - “ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤአለሁ” የሚል፡፡ እናላችሁ --- እነዚህንና ሌሎችንም አስቸጋሪ ቃላት ያካተተ መዝገበ ቃላት ለማሰናዳት ስፖንሰር እያፈላለግሁ ነው፡፡ (ምርጥ የቢዝነስ አይዲያ አይመስላችሁም?)አንድ ወዳጅ አለኝ - ተቃዋሚዎችን “ያሳዝኑኛልም ያናድዱኛልም” የሚል (ፈረንጆቹ love - hate relationship የሚሉት ዓይነት መሆኑ መሠለኝ) ይሄ ወዳጄ የኢህአዴግን 9ኛ ጉባኤ እንደ ልብ ሰቃይ ፊልም ቤቱን ቆልፎ በኢቴቪ ሲኮመኩምልኝ ሰነበተና በቀደም ዕለት ስልክ መታልኝ - “ሃሎ” አልኩት፡፡  “እቺ አገር እኮ ዜጐቿን በሁለት ሚዛን ነው የምትሰፍረው!” አለኝ - ተስፋ በቆረጠ የአነጋገር ቃና፡፡ “ምነው… ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?” አልኩት “የኢህአዴግ አድርባይ አመራሮች በተንቆጠቆጠ አዳራሽ ሲሰበሰቡ -- ተቃዋሚዎች አዳራሽ አጥተው በየቤታቸው ይሰበሰባሉ!” (ምህዳሩ ጠቧል ሲባል የት ነበረ?)“ግን እኮ ኢህአዴግም አምኗል!” አልኩት - ዝም ይሻላል ብዬ“ምኑን?” ተገርሞና ተቆጥቶ ጠየቀኝ“የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለበት!”የሚገርም ሳቅ በጆሮዬ እያንቆረቆረልኝ ሳለ ስልኩ ተቋረጠ (እድሜ ለቴሌኮም!)ዝም ብሎ በሸቀ እንጂ ኢህአዴጐችም ቢሆኑ እኮ በአንዴ “ባለ 7 ኮከብ” አዳራሽ ውስጥ አልተንፈላሰሱም፡፡ እስቲ አስቡት… 17 አመት ሙሉ በትግል ላይ ሳሉ የት ነበር ጉባኤያቸውን የሚያካሂዱት? ዛፍ ስር እኮ ነበር (ታሪክ ነው እንዳትሉኝ ብቻ!) ለነገሩ ተቃዋሚዎችም ዛፍ ስር ይሰብሰቡ ቢባል እኮ አያስኬድም (ኢህአዴግ “የትጥቅ ትግል” በኔ ይብቃ ብሏላ!) እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ … በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱ ይመስላችኋል? (የስልጣን ዘመኑ ስንት ነው ካላችሁኝ ግን እንኳን እኔ ባለቤቱም አያውቀውም) እናንተ ግርም ይላል እኮ ---- መልካም አስተዳደር እንደናፈቀን የ22 ዓመት ጐረምሳ አደረስንም አይደል! እግረ መንገዴን አንድ ነገር ጣል ላድርግ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ህገመንግስታዊ መብታችንን ኢህአዴግ ሊያረሳሳን የፈለገ ይመስላልና እንደነቃንበት ለምን አንነግረውም? (በእልህ ሳይሆን በፒስ!) ወይ ይፈቀድ ወይ ይከልከል? (እዚህና እዚያ ማጣቀስ አይቻልም!) እርግጠኛ ነኝ--- ኢህአዴግ ህገመንግስቱ ያጎናፀፈንን መብታችንን መልሶ ይሰጠናል (“አድርባይነት”ቢያስቸግረውም 2 ሚ. ብር እየመዥረጠ ለተቃዋሚዎች የሚለግስ “ቸር ፓርቲ” እኮ ነው!)

Apr 2, 2013

እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው

 ከገለታው ዘለቀ

Eskinder Nega and his Son Nafkot
ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ።
“ኣልሰማህም እንዴ ?”
በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ።
ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ
እስክንድር ነጋ እና ልጁ ናፍቆት
የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። የሁለታችንም ሳቅ ካለቀ በሁዋላ እውነተኛው ስሜት ሲመጣ ደሞ ያስለቅሳችሁዋል። ነገሩ እውነት መሆን ኣለመሆኑን ኣጥብቄ ኣልጠየኩም፣ ለነገሩ ከዚያ ቀን በሁዋላም ከብዙ ሰው ይህንኑ ሰማሁ። ነገሩ በትክክል ሆነም ኣልሆነም ያ ሁሉ ሰው መንግስት እንደዚያ ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ነገሩ መሆኑን ኣለያም ሊሆን መቻሉን ያሳያል። በዚያች ኣገር ምን የማይሆን ኣለና።
በዚህ ስደነቅ ስደመም ደሞ ኣንዴ እንዲህ ሆነላችሁ። እንዲሁ ኣንድ ሻይ ቤት ተቀምጨ ወጪ ወራጁን እማትራለሁ። በመሃል ኣንድ ሰው ሳምሶናይት የሚባለውን ቦርሳ ጠልጠል ኣርጎ ገባና ወዲያ ወዲህ ካየ በሁዋላ የኔን ጠረንጴዛ ተጋርቶ ለመቀመጥ በትህትና ጠየቀኝ። ወንበሩን ሳብኩለት። እንደኔው ሻይ በሎሚ ኣዞ ቁጭ ኣለ። ጥቂት ቆየት ካለ በሁዋላ ያቺን ቦርሳውን ከፈተና ኣንዲት ጋዜጣ ኣውጥቶ ዘረጋጋና ማንበብ ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ሁለት ሰዎች ወደ ሻይ ቤቱ ገቡና ከኛ መቀመጫ ትይዩ ተሰየሙ። ኣንዱ የቀኝ እግሩን ቀጥ ኣርጎ ዘርግቶ ነበር የተቀመጠው። በሁዋላ ኬክ ሊመርጡ ሲነሱ እንደሚያነክስ ሳይ እግሩ ኣርቴፊሻል መሰለኝና ኣለ ኣይደለም ኣሳዘነኝ። የሚጠጣውን እየጠጡ ኬካቸውን እየበሉ ያወካሉ። እኔና ከፊቴ ያለው ሰውየ ግን ጸጥ ብለናል። ትንሽ እንደቆየ ያቺን ጋዜጣውን በሽንጡዋ ሸመለለና ወደ ቦርሳው ከተተ። ደሞ ወዲያው ኣጨበጨበና ሂሳብ ከፈለ።
እኔም እስካሁን ባናወራም ኣብርን ለትንሽ ሰኣትም ቢሆን ባንድ ጠረንጴዛ በልተን ጠጥተናል ዝም ኣይባልም ብየ ነው መሰለኝ ቻው ለማለት ምንም ኣልቀረኝም።በመሃል ያ ያነክሳል ያልኩዋችሁ ሰውየ ድንገት ወደኛ ዞረና
“ምን ኣልክ ኣንተ? ምን ኣልክ? ድገመው እንጂ…… ልብ በሉ… ሰዎች ልብ ኣርጉ.. ምን ኣልክ ኣንተ?…” እያለ ይጮሃል።
ሁላችንም ተደናገጥን። ያ ከኔ ጋር ጠረንጴዛ ተጋርቶ የነበረው ሳምሶናይቱን እንዳንጠለጠለ
“ኸረ እኔ ምንም ኣልወጣኝም ጌታየ ምን ነካዎት” ይላል ኣስር ጊዜ። ከዚያ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየም ኣብሮ ያጫፍራል። በሁዋላ ይሄ ከኔጋር የነበረው ሰው መንጨቅ ብሎ ሲወጣ ሁለቱም ተከተሉትና ጭቅጭቁ ከውጭ ቀጠለ።
ያው መቼም ሃይ ሃይ ማለት ያገር ባህል ነውና ወደ ውጭ ወጥቼ ኸረ እሱ ምንም ኣላለም ፣ ምንም ሲል ኣልሰማሁትም ተረጋጉ እያልኩ ለመምከር መቼም ያቅሜን ሞከርኩ።
ያ የሚያነክሰው እንባው ሁሉ የመጣ ይመስላል። ይገርማል ዋሽቶ የሚያለቅስ ሰው ቢገጥማችሁ ምን ትላላችሁ?
“እንዴት ትሰድበኛለህ……” እያለ ሲሙዋገት ጓደኛውን ጠጋ ብዬ እናገላግላቸው እባክህ ምን ኣለ? ምንም ኣላልም እኮ ኣልኩት።
“የለም የለም እኔ ራሴ ሰማሁት እኮ ወራዳ ነው ሽባ ብሎ ሰደበው እኮ”
ደነገጥኩና መቼ? ብየ ጠየኩ::
ወደዚህኛው ሰውየ ዞሬ ትተዋወቃላችሁ እንዴብዬ ጠየኩ::
“በፍጹም ኣንተዋወቅም ኣለ” ግራ የተጋባው ባለ ሳምሶናይቱ ፈጠን ብሎ
“ሂሳብ ከከፈለ በሁዋላ ድምጹን ከፍ ኣርጎ እኮ ነው የሰደበው”
በውነት ግራ ግብት ኣለኝ። ሁዋላ ላይ ይሄ የሚያናግረኝ ሰው ስልኩን ኣወጣና ኣንድ ሁለት ቁጥሮችን ነካካና ወደዛ ዞር ብሎ ጥቂት ኣወራ መሰለኝ። ወዲያው እንደተመለሰ ኣንድ ፖሊስ መጣና ያንን ባለ ሳምሶናይት “ቅደም ኣለው።”
በዚህ ጊዜ ወደ ፖሊሱ ጠጋ ብዬ ምንም እኮ ኣላለም እኔ እዚህ ነበርኩ
ምንድነው ችግሩ ለማለት ሞከርኩ። ፖሊሱ በግንባሩ ጥሩ ኣርጎ ገረፈና ኣስቆመኝ። ባለ ሳምሶናይቱ እንዲሁ “ምን ኣጠፋሁ” እንዳለ ይነዱት ጀመር። ሁኔታው ገርሞኝ ነበርና ባጭር ርቀት መከተል ጀመርኩ። የሚገርማችሁ ያ ቅድም ቀኝ እግሩን ይጎትት የነበረው “ሽባ” ተብየ ተሰድቢያለሁ የሚለው ሰውየ ኣሁን በግራው ማንከስ መጀመሩን ትኩር ብዬ ኣስተዋልኩና የሆነ ነገር እየሆነ እንደሆነ ገባኝ። ብዙም ሳልርቅ ወደ ሁዋላየ ሂሳቤን ለመክፈል ተመለስኩ። ወደ ሻይ ቤቱ በር ስቃረብ ኣንዱ “ወሰዱት ኣይደል?” ኣለኝ:: ኣዎ ወሰዱት ኣልኩና ግን ምንም ኣለማጥፋቱን ኣስረግጨ ነገርኩት። ጥቂት ኣየኝና “ወንድሜ ተጠንቀቅ ከዚህ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየ የነሱ ጆሮ ነው የተለያየ ልብስ እየለበሰ ሲሰልል ነው የሚውለው ተነቅቶበታል” ኣለኝ። እኔም ወዲያው ጠርጥሬ ስለነበረ ገባኝ። እንግዲህ ያን ሰው በዚህ ርካሽ ስራቸው ኣወናጅለው የሆነ ነገር ኣርገውታል ማለት ነው።
ባለፈው ጊዜ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ከነበሩት መካከል ኣንዱ በኢሳት ቴሌቪዥን ኢንተርቪው ተደርጎለት ሲናገር ልብ ይነካል። ሲቪል እየለበሱ መገናኛ እየያዙ እንዴት የስነ ልቡና ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ገለጸ። ኑሮ ኣይደለም የምንኖረው ኣለ። ያሳዝናል። ሃሳብን መግለጽ ጥቂት ኣስተያየት መሰንዘር በስነ ልቡናና በኣካል የሚያስቀጣ ነገር የሆነባት ሃገር ናት ኢትዮጵያ።
መነሻየኮ ስለ እስክንድር ነጋ ነው። ይህን ያመጣሁት በእንዲህ ባለ ኣገር፣ እስክንድርን የመሰለ ፖሊሲ የሚያመነጭ፣ የሰባዊ መብት እንዲከበር ለማድረግ የሚታገል ሰው ስንት ስነ ልቦናዊ ቅጣት እንደሚቀበል ለመገመት እንዲያስችለን ነው።
እስክንድር የታሰረበትን ምክንያት ኣለም ኣውቆታል። እስክንድር የታሰረው በውስጡ ያለው የእኩልነትና የፍትህ ራእይ እንቅልፍ ኣልሰጥ ስላላቸው ነው። ያንን በገቢ ኣለመመጣጠን የሚሰቃየውን ህዝብ እህል በልቶ እኩልነት ሰፍኖ ማየት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ነው የ እስክንድር ሃጢያቱ።እስክንድር ቅንና ርህሩህ ነው። የጻፋቸው ጽሁፎች ዋቢዎች ናቸው። የሱ ወንጀል መምከሩ፣ ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው። የነ ርእዮት ኣለሙም ወንጀል ይሄው ነው። መናገር፣ መምከራቸው ነው ወንጀላቸው።
ግን እውነት ሊሞት ይችላል። መሞት ብቻ ኣይደለም ሊቀበርም ይችላል። ግን ደሞ እውነት መቃብር ፈንቅሎም የመነሳት ሃይል ኣለው። መንግስት ይህን መረዳት ኣለበት።
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!

Reeyot-Alemu    
መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆች አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤
ከአንድ ወር እስከ አራት ወር ለሚደርስ ጊዜ በወዳጅ ዘመዶቿ እንዳትጎበኝ፤ ደብዳቤ እንዳትልክ እና እንዳትቀበል (ይሄ እንኳ አሁንም ተግባራዊ ተደርጎባታል) የእስር ቤቱን ቤተ መጻህፍት እንዳትጠቀም፣ በእስር ቤቱ በሚደረግ የጋራ ዝግጅት እና መዝናኛ ላይ እንዳትሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ለሚደርስ ጊዜ ለብቻ እስር ትዳረጋለች፡፡
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ያቺ በቃሊቲዊቹ ውቃቢ ትፈቀድ የነበረች አመክሮም ልትከለከል ነው ማለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤልም በእስር ቤቱ እየደረሰበት ያለውን አበሳ በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላትም ቅጥ ያጣውን የእስር ስርዓት ሃይ ለማለት የርሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
ወይ ጣጣ… ብዬ የራሴን አስተያየት በአዲስ መስመር አቀርባለሁ…
እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምነው እንዲህ መካሪ አጣ…? እርሱ እኛን በስንቱ መከራ እንዳልመከረን እርሱን የሚመክረው ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡
እስቲ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እስሩ አንሶ አሳር የሚያበላው ምን ይሁነኝ ብሎ ነው? እንደሰማነው በርካታ የህሊና እስረኞች በታመሙ ጊዜ የሚያክሟቸው የእስር ቤቱ ሀኪሞች “መግደል ነበር አንተን” “መጨረስ ነበር አንቺን” እያሉ ያስፈራራሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ይሄ የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውና ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ መንግስታችን “ባትሪ ሎው” እያለ ይመስለኛል!

የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት?“ከእንግዲህ የቀድሞው መንገድ አይሰራም”

odf


 
ላለፉት አርባ ዓመታት ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ሲታገል የቆየው ኦነግ አመራሮቹ ሲጣሉና ሲታረቁ መስማት የተለመደ ነው። የግለሰብ ጸብ የሚመስለው የድርጅት በሽታ ሲንጠው የቆየው ኦነግ በውል ባይታወቅም ተሰነጣጥቆ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ድርጅት ከሆነም ዓመታት ተቆጥረዋል። ስህተትን ገምግሞ የትግል አቅጣጫና ፕሮግራም ከመቀየር ይልቅ ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ ባለበት ሲረግጥ እድሜውን የፈጀ ድርጅት እንደሆነ ተደርጎም ይወሰዳል።
ስለ ኦነግ ሲነሳ አብዛኞች በመገረም የሚናገሩትና ሚዛን የሚደፋው አስተያየት የሚሰነዘረው በድርጅቱ መከፋፈልና መበጣጠስ ሳይሆን ተለያይተውም አስመራን የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ህጻን እያለ ሻዕቢያ እንዳሻው ይነዳው እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች ከሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ኦነግ አገር ለቆ እንዲወጣ መንገዱን የጠረገው ሻዕቢያ መሆኑንን በቁጭት ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ለስልጣን አዲስ በሆነበት የጨቅላነት ዘመኑ፣ ኦነግ በታሪኩ ያልነበረውን ሰራዊት በመገንባት አስጨንቆት እንደነበር በመጠቆም በወቅቱ አስተያየት የሰጡ ኢህአዴግ በተለይም መለስ በሻዕቢያ በኩል ኦነግን ለመታረቅ አቅርበውት የነበረውን የሽምግልና ጥያቄ ኦነግ እንዳይቀበል ሰሚ ባያገኙም በአጽዕኖት ምክራቸውን ሰጥተው ነበር።
በኦነግ ታጣቂ ሃይሎችና በኢህአዴግ ሰራዊት መካከል እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የጡንቻ  መፈታተን ነበር። ደርግ ሲበታተን ኦነግን የተቀላቀሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አካላት ወያኔን የማዳፋት አቅሙ ነበራቸው። በወቅቱ የንስር ያህል ጉልበትና ሃይል ቢኖራቸውም ራሳቸውን ጫጩት አድርገው ተመለከቱ። አዲስ አበባ ሲገቡ የነበራቸውን የህዝብ ድጋፍ አራግፈው ጣሉት። በስሜት እየተነዱ ከሚወዷቸው ሁሉ ተቀያየሙ። ህወሃት አጋጣሚውን ለቅስቀሳና ለስም ማቆሸሻ ሰራበት። በስተመጨረሻ ኦነግ ሃይሉንና አቅሙን ዘንግቶ በአመራር ችግርና በአቋም ሸውራራነት ሃይሉን በሙሉ ወደ ካምፕ በማስገባት የኢህአዴግን የእርቅ ጥያቄ ተቀበለ። ሰራዊቱን እየነዳ በፈቃደኛት አሳሰራቸው።
በሻዕቢያ አደራዳሪነት ሁርሶ፣ ደዴሳና መስኖ የገባው ሰራዊት “በደባ” ተከቦ ትጥቁን እንዲፈታ ተደረገ። አብጦ የነበረው የኦነግ ጡንቻ በቅጽበት ከሰመ፤ ሰለለ። ኦነግ ሲቆጣጠራቸው የነበሩትን ቦታዎች ለማስተዳደርና በኦህዴድ ለመተካት ኢህአዴግ እንደ እባብ ተሹለክልኮ ዓላማውን አሳካ። ሻዕቢያም በዚሁ ውለታው ኢትዮጵያንና ኢኮኖሚዋን ብሎም የኢትዮጵያን ስነልቦና እንዳሻው እንዲጋልብ ተፈቀደለት። ብዙ አሻጥር ተፈጠረ፤ ተፈጸመም። ደንዳና ቆዳ ያላት ኢትዮጵያና ህዝቧ ተቦጠቦጡ። ተዘረፉ። አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ኤርትራ ቡና ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተሰለፈች። አፈርን።
“አገሬን ከወራሪ አጸዳሁ” በማለት ከበሮ እየመታ ጦርነት አልቋል ብለው እጅ የሰጡ የወገን ወታደሮችን የረሸነው ሻዕቢያ ኢትዮጵያንም ያስተዳድር ጀመር። ዛሬ የሚማልባቸውና “ውርሳቸውን ሳናዛባ እናስጠብቃለን” የሚባልላቸው አቶ መለስ እንደ ባዕድ መሪ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም ለሻዕቢያ አሳልፈው ሰጡ። የሻዕቢያ ታጣቂዎችና ኢትዮጵያ አብልታ ያሳደገቻቸው ጎረቤቶቻችን ሳይቀሩ ናጠጡብን። በየደጃቸው መሳሪያ ወደላይ እየተኮሱ በደስታ ውለታ ባስቀመጠችላቸው አገር ላይ ተሳለቁ። ምስኪኖችን ቤት እያስለቀቁ ወረሱ። የሌላቸውን ሃብትና ንብረት ሰበሰቡ። በኤርትራ ምድር በግፍ ለተረሸኑ የኢትዮጵያ ልጆች ተከራካሪ ጠፋና የሞት ሞት ሞቱ። አገራችን የግፈኞች መፈንጫ እንድትሆን መለስ በበረገዱት በር የገባው ሻዕቢያ ከርሱ ሲጎድል፣ “ልክህን እወቅ” የሚሉ ሲነሱ፣ ስርዓት ያዝ ሲባል ደሙ ተንተከተከና የሃይደር ህጻናትን በጠራራ ጸሃይ በላቸው። ትግራይን ወረረ። ሲሰርቁ ኅብረት የነበራቸው ሲከፋፈሉ ተጣሉና አገር ውርደት ገባው።
ይህንኑ ተከትሎ አገር አልበቃ ብሏቸው የነበሩና ወያኔን ሲያገለግሉ የነበሩ ቅጥረኞች የሰበሰቡትን ሳይበሉ ወደ “ከባርነት ናፅነት” ብለው ድምጻቸውን ወደሰጡላት “እናት አገራቸው ኤርትራ” ተጋዙ። ንብረታቸውን በትነው አገር ለቀው ወጡ። ከነጻነት በኋላ “ታይላንድ ትሆናለች፣ ሲንጋፖር ትሆናለች፤ ሆንግኮንግ ትሆናለች” በተባለላት አገራቸው ለመኖር ተገደዱ። ዳቦ ተሰልፈው ለመግዛት ታደሉ። ኬክ በለመደው፣ ቁርጥ በቆርጠው፣ “ሹካ ባስለመደው” እጃቸው ይድሁበት ገቡ። ወታደር ሆኑ። የሰገዱለትና ቅጥረኛ ሆነው ያገለገሉት ህወሃት መልሶ በረሃ በተናቸው። የሚያሳዝነው ግን ኤርትራዊያን ከየመንደሩ ተለቅመው ወደ አገራቸው ሲሄዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አውቶቡስ ከብበው ደረት እየመቱ ያለቅሱላቸው ነበር። ደብቀው ያስቀሩዋቸውም አሉ። ጨርቃቸውን ጥለው አውቶቡስ እንዳይነሳ በፍቅር አምላክ የተንፈራፈሩ ነበሩ። ሁኔታውን የሚያስታውሱ ድርጊቱን “የሞኝ” ተግባር አድርገው ሲወሰዱት ሌሎች ደግሞ “ክፉ ላደረገብህ ክፉ አትመልስ” የሚለው ግብረገብነት የገባቸው የፈጸሙት የጀግንነት ተግባር ነው በማለት የአዲስአበባ ነዋሪዎችን የመንፈስ ልዕልና ያደንቃሉ፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት ጀምሮ ኦነግ ሻዕቢያን ሲለማመነውና እግሩን ሲልሰው የኖረ ድርጅት ዛሬ ድረስ ተበጣጥሶም እዛው አስመራ አምልኮ ደጅ ይገኛል። ከአመት ዓመት ያለ ለውጥ እዛው ይንፏቀቃል። እንደሚሰማው ከሆነ ወታደሮቹ የሻዕቢያ አግልጋዮች ሆነዋል። አመራሮቹም ቢሆኑ አስመራን ለቀው የመውጣትና እንዳሻቸው የመንቀሳቀስ መብት የላቸውም። በዚህም ይሁን በሌላ መነሻ ኤርትራ በከተሙት የተለያዩ የኦነግ ሃይሎች ላይ ከያቅጣጫው ስሞታ መቅረብ ከጀመረ ሰንብቷል። ኤርትራን ለቀው መውጣት አለባቸው የሚለው የኦሮሞ ልጆች ድምጽም በርክቷል። ጥያቄው አያሌ ፖለቲካዊ ማብራሪያ የሚጠይቅና አማራጭ መፍትሄ የሚያሻው ቢሆንም ኤርትራ ውስጥ አሉ በሚባሉ ታጣቂ ተቃዋሚዎች ያልተማረሩና ያልተሰላቹ ቢኖሩ አፍቃሪ ሻዕቢያዎች ወይም ራሳቸው የሻዕቢያ ሰዎች ወይም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሻዕቢያን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ብቻ ናቸው።
እንግዲህ በዚህ መሃል ነው አስመራን ተሳልመው ከነበሩት የኦነግ አመራሮች መካከል አቶ ሌንጮ ለታ፣ አቶ ዲማ ነገዎና ሌሎች ሰሞኑን አዲስ ዜና ይዘው ብቅ ያሉት። አዲስ ፓርቲ በማቋቋም ድፍረት የተሞላው አቋም በማራመድ “አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” ያሉት። ሃሳቡ መልካም  ቢሆንም እንዴት? የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው። ምክንያቱም በግልጽ “የቀጣዩ ትግል ሜዳ አገር ቤት ነው፤ አገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ተብሏልና!
“የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” ODF የሚባል አዲስ ግንባር መቋቋሙ ከአሜሪካ የሚኖሶታ ጠቅላይግዛት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች እየተወረወሩ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጥርት ያለ መልስ አልተሰጠም። ግንባሩ መመስረቱ ይፋ ከሆነ በኋላ መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) በዚያው ጠቅላይግዛት በሚኒያፖሊስ ከተማ በተካሄደ ስብሰባ አንዳንድ ጉዳዮች ይፋ ሆነዋል።
ከብሪታንያ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። ኢትዮጵያን “ኢምፔሪያሊዝም፣ ቅኝ ገዢና ጠላት” አድርገው በመሳል ጥያቄ የሰነዘሩትን ጨምሮ ስለ ቀጣዩ ትግል ትግበራና ሰለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር በስፋት ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሌንጮ ለታ አስገራሚ መልስ ሰንዝረዋል።
“ያለፈውን በመውቀስ የትም አንደርስም። አሁን ማየትና ማሰብ ያለብን ወደፊት ነው። ሌሎች ወገኖችን አግልለን ብንታገል የትም አንደርስም። ያለፈው የትግል መንገድ ስህተት ነበር” ብለዋል። ስለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር ሲናገሩ “የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ካልተከበረ የኦሮሞ መብት ብቻውን ሊከበር አይችልም” በማለት መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
“ጊዜው ተለውጧል። ጊዜው አዲስ ነው። አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው” በማለት የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ “አገር ቤት እንዴት ገብቶ መታገል ይቻላል?” በሚል ለተነሳው ጥያቄ የሰጡት መልስ አዲሱን ድርጅታቸውንና እርሳቸውን የሚፈትን እንደሆነ ያመላከተ ነው።
ቀጣዩ ትግል ኤርትራ ላይ እንደማይሆን በግልጽ የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ አገር ውስጥ በመግባት ለማደራጀት፣ ለመታገል፣ ለመንቀሳቀስ ይቻል ዘንድ “መንገድ እንፈልጋለን” ብለዋል። ኢህአዴግ በተደጋጋሚ እንደሚለው ለድርድር የሚቀመጡ ወገኖች መጀመሪያ ህገመንግስቱን መቀበልና ህግመንግስቱን አክብሮ ለመስራት መማል አለባቸው። ይህ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም አገር ቤት ለመግባትና ለመታገል እነ አቶ ሌንጮ ቢስማሙ እንኳን ሌላ መሰረታዊ ችግር እንዳለ ከወዲሁ እየተጠቆመ ነው።
በኦሮሞነታቸው በሚያነሱት ጥያቄ እስር ቤት የታጎሩ የኦሮሞ ልጆች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው – በአስር ሺዎች እንደሚቆጠር ይገመታል። በየቦታው ባሉ እስር ቤቶች ዋናው የመግባቢያ ቋንቋ ኦሮሚኛ እስከመሆን የደረሰበት ሁኔታ ነው የሚታየው። ይህ እውነታ ባለበት አቶ ሌንጮ የሚመሩት አዲሱ ድርጅት እንዴት አድርጎ ይታገላል? ወይም ደግሞ አባላቶቹ እስርና እንግልት እንዳያጋጣማቸው ምን ዓይነት ማረጋገጫና መተማማኛ ማግኘት ይቻላል?
“መልሱ ግልጽ ነው” በሚል ይመስላል “የፈለገው ቢመጣ፣ አስፈላጊው ህግን የጠበቀ ትግል ይካሄዳል። አገሪቱ ላይ ያለውን ህዝብ አስሮ ይችል እንደሆነ የሚታይ ይሆናል” የሚል እንደምታ ያለው ምላሽ ነው እየተሰነዘረ ነው ያለው። በሌላ በኩል አገር ቤት ገብቶ መታገል ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ ሲወሰድ አዲሱ ጉዳይ የቀድሞው ሌሎችን ሲያገልና “ልዕልናና ነጻነት ለኦሮሞ ብቻ” በሚል የፖለቲካ ሾፌር ሲደወር የነበረው የትግል ስልት መቀየሩ ነው። በዚህም የተነሳ ይመስላል “ከማናቸውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ መረጋገጥና ለህዝብ እኩልነት ከሚሰሩ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን። የቀድሞው መንገድ አይዋጣም” የሚል ምላሽ የሰጡት።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ “እኔን ተከተል፣ ስትቃወም ከኔ ቀመር አትዛነፍ” የሚለውን አመለካከት ጨምሮ በድፍን የአንድ እንቅስቃሴ እርግጠኛ መነሻ ሳይታወቅ አስቀድሞ “የማብከትና የማበስበስ” ስራ መስራት የተለመደ በመሆኑ ከሁሉም ወገን እርጋታ እንደሚጠበቅ፣ ረጋ ብሎ መመርመር እንደሚያስፈልግ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ላለፉት 20 ዓመታት ኢህአዴግ በብሄር እየለየ በፈጠረው ገደል እየተወረወሩ የሚገቡ ፖለቲከኞች በሰሩት ጥፋት ህዝብ ለከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት ተዳርጓል። ኢህአዴግ የ50 ዓመት የቤት ስራ እንደሰጠ አድርጎ የሚያስበውም እነዚሁ የፖለቲካ መሪዎች የህወሃትን የሳሳ ፖለቲካ መረዳት ባለመቻላቸውና ከዋናው ጠላታቸው ይልቅ እርስ በርስ ለመቧቀስ የፈጠኑ መሆናቸውን በቀላሉ ስለሚያሳዩት ነው።
ከ40 ዓመታት የስህተት ጉዞ በኋላ አገር ቤት በመግባት “ሁሉም ነጻ ካልወጡ ኦሮሞ ብቻውን ነጻ አይወጣም” በሚል የትግል መርህ መነሳት በራሱ አስደሳች እንደሆነ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል በስልክ ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ ተናግረዋል።
“ድንበርና ክልልን ሳይሆን የምንጋራው አብሮነትን ነው” ያሉት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “በዲኤንኤ ምርመራ ጎሳ አይታወቅም። ተመሳሳይ ዲኤንኤ ያላቸው ጎሳዎችም የሉም። ሁሉም ነጻ ካልወጡ ማንም ነጻ እንደማይወጣ መስማት ታላቅ ብስራት ነው” በማለት ከዓመታት ትግልና ውትወታ በኋላ ድርጅታቸው ሲታገልለትና ሲሟገትለት የቆየው ዓላማ የሌሎችም መርህ ሆኖ በማየታቸውና በመስማታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ዓይነቱ መርህ ለዘመናት የቆየው ሥርዓቱም ሆነ አኗኗሩ ቅርብ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አመልክተዋል፡፡ ድርጅታቸው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል የከበረ መመሪያ ላይ ሲሰራ መቆየቱን የገለጹት አቶ ኦባንግ ከዚህ መመሪያ በተጨማሪ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚለው የትግል መርህ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡ ይህንን መፈክር አሁን ደግሞ ኦሮሞ ወገኖቻችን ሲያነሱ መስማት ለድርጅታቸው ታላቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ላይ ማንም ሳይጠራቸው በራሳቸው አነሳሽነት እንደሄዱ ያስታወቁት አቶ ኦባንግ “የኦሮሞ ተወላጆች ስብሰባ ሲቀመጡ የሚነጋገሩት ስለ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝና ውይይቱ ይመለከተኛል። ስለዚህ ተገኘሁ። በደስታ ተቀበሉኝ። በስብሰባው ውስጥ በሰማሁት አዲስ ሃሳብ ተደሰትኩ” ብለዋል።
ላለፉት 20 ዓመታት አንዱ ስለ ሌላው ሲያወራ መኖሩን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ አሁን አንድ ላይ በመሆን ለመመካከርና “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ” ግንባታ በጋራ ለመታገል መወሰን ከልምድ የተገኘ የፖለቲካ ተሃድሶ መሆኑን አስታውቀዋል። አያይዘውም ድሮም ቢሆን ፖለቲከኞች እንጂ ህዝብ አእምሮ ውስጥ ያልነበረ አስተሳሰብ በማቀንቀን ለህወሃት ፖለቲካ ማዳበሪያ የማቅረብ ስራ ሲሰራ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ ሌንጮ ለታ እንጀምረዋለን ያሉት አዲሱ መንገድ ሁሉንም ህዝብና የፖለቲካ ድርጅቶች ማዕከል በማድረግ ለመስራት ወስኖ የተነሳ እንደሆነ ሲያስታውቁ ያሰመሩበት ጉዳይ ቢኖር “ያለፈውን አናስብም። አሁን አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተያይዘው የሚፈጥሯትን አዲስ አገር ማየት ነው፡፡” እርሳቸው እንዳሉት 40 ዓመት ባክኗል። አሁንም መንቃት አግባብ ነው። ነገር ግን ድጋፉም ሆነ ተቃውሞው በተራ የድጋፍና ተቃውሞ ስሜት ሳይሆን ረጋ ብሎ በመመርመር እንደሆነ የሚመክሩ ጥቂቶች አይደሉም።
(ፎቶዎቹን የወሰድነው ከ Hegeree Media channel ቪዲዮ ላይ ነው)

EthiopiaSource: Human Rights Watch World Report 2013, pp 114-120

 
The sudden death in August 2012 of Ethiopia’s long-serving and powerful prime minister, Meles Zenawi, provoked uncertainty over the country’s political transition, both domestically and among Ethiopia’s international partners. Ethiopia’s human rights record has sharply deteriorated, especially over the past few years, and although a new prime minister, Hailemariam Desalegn, took office in September, it remains to be seen whether the government under his leadership will undertake human rights reforms.
Ethiopian authorities continued to severely restrict basic rights of freedom of expression, association, and assembly in 2012. Thirty journalists and opposition members were convicted under the country’s vague Anti-Terrorism Proclamation of 2009.The security forces responded to protests by the Muslim community in Oromia and Addis Ababa, the capital, with arbitrary arrests, detentions, and beatings.
The Ethiopian government continues to implement its “villagization” program: the resettlement of 1.5 million rural villagers in five regions of Ethiopia ostensibly to increase their access to basic services. Many villagers in Gambella region have been forcibly displaced, causing considerable hardship. The government is also forcibly displacing indigenous pastoral communities in Ethiopia’s Lower Omo Valley to make way for state-run sugar plantations.
Freedom of Expression, Association, and Assembly
Since the promulgation in 2009 of the Charities and Societies Proclamation (CSO Law), which regulates nongovernmental organizations, and the AntiTerrorism Proclamation, freedom of expression, assembly, and association have been increasingly restricted in Ethiopia. The effect of these two laws, coupled with the government’s widespread and persistent harassment, threats, and intimidation of civil society activists, journalists, and others who comment on sensitive issues or express views critical of government policy, has been severe.  Ethiopia’s most important human rights groups have been compelled to dramatically scale-down operations or remove human rights activities from their man dates, and an unknown number of organizations have closed entirely. Several of the country’s most experienced and reputable human rights activists have fled the country due to threats. The environment is equally hostile for independent media: more journalists have fled Ethiopia than any other country in the world due to threats and intimidation in the last decade—at least 79, according to the Committee to Protect Journalists (CPJ).
The Anti-Terrorism Proclamation is being used to target perceived opponents, stifle dissent, and silence journalists. In 2012, 30 political activists, opposition party members, and journalists were convicted on vaguely defined terrorism offenses. Eleven journalists have been convicted under the law since 2011.
On January 26, a court in Addis Ababa sentenced both deputy editor Woubshet Taye and columnist Reeyot Alemu of the now-defunct weekly Awramaba Times to 14 years in prison. Reeyot’s sentence was later reduced to five years upon
appeal and most of the charges were dropped.
On July 13, veteran journalist and blogger Eskinder Nega, who won the prestigious PEN America Freedom to Write Award in April, was sentenced to 18 years in prison along with other journalists, opposition party members, and political
activists. Exiled journalists Abiye Teklemariam and Mesfin Negash were sentenced to eight years each in absentia under a provision of the Anti-Terrorism Law that has so far only been used against journalists. Andualem Arage, a member of the registered opposition party Unity for Democracy and Justice (UDJ), was sentenced to life for espionage, “disrupting the constitutional order,” and recruitment and training to commit terrorist acts.
In September, the Ethiopian Federal High Court ordered the property of Eskinder Nega, exiled journalist Abebe Belew, and opposition member Andualem Arage to be confiscated.
On July 20, after the government claimed that reports by the newspaper Feteh on Muslim protests and the prime minister’s health would endanger national security, it seized the entire print run of the paper. On August 24, Feteh’s editor, Temesghen Desalegn was arrested and denied bail. He was released on August 28, and all the charges were withdrawn pending further investigation.
Police on July 20 raided the home of journalist Yesuf Getachew, editor-in-chief of the popular Muslim magazine Yemuslimoche Guday (Muslim Affairs), and arrested him that night. The magazine has not been published since, and at this writing, Yesuf remained in detention.
On December 27, 2011, two Swedish journalists, Martin Schibbye and Johan Persson, were found guilty of supporting a terrorist organization after being arrested while traveling in eastern Ethiopia with the Ogaden National Liberation Front (ONLF), an outlawed armed insurgent group. They were also convicted of entering the country illegally. The court sentenced them to 11 years in prison. On September 10, they were pardoned and released along with more than 1,950 other prisoners as part of Ethiopia’s annual tradition of amnesty to celebrate the Ethiopian New Year.
On several occasions in July, federal police used excessive force, including beatings, to disperse largely Muslim protesters opposing the government’s interference with the country’s Supreme Council of Islamic Affairs. On July 13, police forcibly entered the Awalia mosque in Addis Ababa, smashing windows and firing tear gas inside the mosque. On July 21, they forcibly broke up a sit-in at the mosque. From July 19 to 21, dozens of people were rounded up and 17 prominent leaders were held without charge for over a week. Many of the detainees complained of mistreatment in detention.
Forced Displacement
The Ethiopian government plans to relocate up to 1.5 million people under its “villagization” program, purportedly designed to improve access to basic services by moving people to new villages in Ethiopia’s five lowland regions: Gambella, Benishangul-Gumuz, Afar, Southern Nations Nationalities and Peoples’ Region (SNNPR), and Somali Region.
In Gambella and in the South Omo Valley, forced displacement is taking place without adequate consultation and compensation. In Gambella, Human Rights Watch found that relocations were often forced and that villagers were being moved from fertile to unfertile areas. People sent to the new villages frequently have to clear the land and build their own huts under military supervision, while the promised services (schools, clinics, water pumps) often have not been put in place.
In South Omo, around 200,000 indigenous peoples are being relocated and their land expropriated to make way for state-run sugar plantations. Residents reported being moved by force, seeing their grazing lands flooded or ploughed up, and their access to the Omo River, essential for their survival and way of life, curtailed.
Extrajudicial Executions, Torture and other Abuses in Detention
An Ethiopian government-backed paramilitary force known as the “Liyu Police” executed at least 10 men who were in their custody and killed 9 other villagers in Ethiopia’s Somali Region on March 16 and 17 following a confrontation over an incident in Raqda village, Gashaamo district.
In April, unknown gunmen attacked a commercial farm owned by the Saudi Star company in Gambella that was close to areas that had suffered a high proportion of abuses during the villagization process. In responding to the attack, Ethiopian soldiers went house to house looking for suspected perpetrators and threatening villagers to disclose the whereabouts of the “rebels.” The military arbitrarily arrested many young men and committed torture, rape, and other abuses against scores of villagers while attempting to extract information.
Human Rights Watch continues to document torture at the federal police investigation center known as Maekelawi in Addis Ababa, as well as at regional detention centers and military barracks in Somali Region, Oromia, and Gambella. There is erratic access to legal counsel and insufficient respect for other due process guarantees during detention, pre-trial detention, and trial phases of politically sensitive cases, placing detainees at risk of abuse.
Treatment of Ethiopian Migrant Domestic Workers
The videotaped beating and subsequent suicide on March 14 of Alem Dechasa Desisa, an Ethiopian domestic worker in Lebanon, brought increased scrutiny to the plight of tens of thousands of Ethiopian women working in the Middle East.
Many migrant domestic workers incur heavy debts and face recruitment-related abuses in Ethiopia prior to employment abroad, where they risk a wide range of abuses from long hours of work to slavery-like conditions (see chapters on the
United Arab Emirates, Saudi Arabia, and Lebanon).
Key International Actors
Under Meles Zenawi’s leadership, Ethiopia played an important role in regional affairs: deploying UN peacekeepers to Sudan’s disputed Abyei area, mediating between Sudan and South Sudan, and sending troops into Somalia as part of the international effort to combat al-Shabaab. Ethiopia’s relations with its neighbor Eritrea remain poor following the costly border war of 1998-2000. Eritrea accepted the ruling of an independent boundary commission that awarded it disputed territory; Ethiopia did not.  Ethiopia is an important strategic and security ally for Western governments, and the biggest recipient of development aid in Africa. It now receives approximately US$3.5 billion in long-term development assistance each year. Donor policies do not appear to have been significantly affected by the deteriorating  human rights situation in the country.
The World Bank approved a new Country Partnership Strategy in September that takes little account of the human rights or good governance principles that it and other development agencies say are essential for sustainable development. It also approved a third phase of the Protection of Basic Services program (PBS III) without triggering safeguards on involuntary resettlement and indigenous peoples.

Apr 1, 2013

‹‹…እናትና አባትን የሚለያይ ፖለቲካ…››


ከዘካሪያስ አሳዬ( ኖርዌይ)
እንደሚታወቀው አገራችንን ሊጠብሳት እያዘጋጃት ያለው የ”ጎሳ ፖለቲካ” ደራሲውና ቀማሚው በሞት ቢለዩም
የሚያበርደው አስተዋይ መሪ አልተገኘም እንደውም እርዝራዞቹ የሳቸውን ህራይ እናስቀጥላለን በማለት አብሰውታል፡፡
በማስተዋል ማርከሻውን ለሚቀምሙም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በቂ ጆሮ አልተሰጣቸውም – ጩኸቱ እጅግ
ያደነቁራልና። ከውጪም ከውስጥም የሚረጨው የጎሳና የ”ደም” መርዝ ሳያንስ አሁን ደግሞ በሃይማኖት ተንተርሶ
የተጀመረው አለመግባባት አስደንጋጭ ይዘት እንዳለው አያጠያይቅም። ተወደደም ተጠላም ያስፈራል። ወያኔ/ኢህአዴግ
ባቀናበረው “የድርሰት” ፊልም መነሻ ሳይሆን በበርካታ መረጃዎች የተደገፈ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል።
የሚገርመው ግን እትብታችን በተቀበረችበት በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ፣ ተሰደን ባለንበት አገር ሁለተኛ ዜጋ ! ተሰደን
በምንኖርበት አገር እንኳን የፖለቲካው ሁናቴ የወያኔን የቤት ስራ መቅረፍ ሲገባን እንደውም ያባስነው ይመስለኛል።
የኢህአዴግ/ ወያኔ በብሄር፣ በጎሣ፣ በዘረኝነት የከፋፈላትን አገር መታደግ ሲገባን ዛሬ ደግሞ ተሰደን እራስ በራሳችን
ተከፋፍለን በብሄር የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመን እራስ በራሳችን መሻኮትና ለብሄራችን፣ለዘራችን ነፃነት እንታገላለን ስንል
የወያኔ ስራ ከማስፈፀም ምን ይለያል? ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት አምባገነኑን ስርዓት ጥለን የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን
ባለቤት እናደርጋለን ብለን ካልን ምንድነው ችግራችን? አንድ የማንሆንበት! በእንደዚህ አይነት አካሄዳችን የመቶ አመት
ትግል እንዳያስፈልገን! በብሄር የታመነ ፖለቲካ የትም አያደርስም መጨረሻው ዋጋ ያስከፍላል ኢትዮጵያዊነትን ያልጠበቀ
ትግል ነው ምፃሜውም ያላማረ ነው።በብሄር ብቻ የተደራጀ ፖለቲካ እናትና አባትን የሚለያይ ፖለቲካ ውጤት ነው።
ማንም ሲወለድ ከዚኛው ብሄር ልወለድ ብሎ አልተወለደምና ብሄራችን ውበታችን ነው የመበላለጫ መለኪያ አይደለም!
ደማችን ኢትዮጵያዊነት ነው። ለእኔ ከዘር ቆጠራ እና ከብሔር ነፃ የሆነው የማንነት መገለጫ ኢትዩጵያዊነት ብቻ ነው፡፡
ዛሬ በአገር ቤት ውስጥ ሆነው በኢትዮጵያዊነት ስሜት እየታገሉ ያሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ህዝቡም ዋጋ
እየከፈሉ ባሉበት ወቅት ውጪ ያለው መርዳት፣ ማታገል ሲኖርብን እኛው ውጪ ያለነው ተከፋፈልንና አገራችን ለበይ

ሰጠን! በቃላት ሽኩቻ አንባጓሮ ከፍተን መጣላት ወደድን!
ኢትዮጵያ ውስጥ የሐይማኖት፣ የፖለቲካ፣የጎሳ ችግርች ሲፈጠር እንደ እሳት አደጋ አላርም እየነፉና እየከነፉ መሮጥና
ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ብቻ ግን መሆን የለበትም፡፡መብቴው ማበጀት ያስፈልጋል።መብቴው ደግሞ ልዩነታችንን ወደ
ኋላ ትተን ህዝባችንን መታደግ ነው መሆን ያለበት! ያለበለዚያ ‹‹በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት፣ ይፈራርሳል ‹‹ጅብ የጮኸ
ዕለት…›› እንዳይሆን አንድነታችንም የዘይትና የውሃ አይነት እንዳይሆን ማንም ቢሄድ፣ ማንም ቢመጣ የማይነቃነቅና
መሰረተ ፅኑ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሆኖ እንዲዘልቅ ወደ ታች ወርደን እናጥብቀው፡፡
“ዲሞክራሲ የሚሰራው አውሮፓ ውስጥ ነው፤ የአፍሪካ ባህል የተለየ ነው እንደተባለ፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ
ያለችበትን እንመልከት፡፡ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት አምጥተናል ይላሉ፤ ነገር ግን በትክክል ያመጡት
ጎሰኝነትን ነው፤ሁሉም የተደራጀው በፓርቲ ሳይሆን በጎሳው ወይም በሃይማኖቱ ነው - በሁሉም ቦታ
እንደሚታየው፡፡ በዚህ የተነሳ ዓለም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ጦርነት በአፍሪካ ውስጥ መከሰቱ
አይቀርም ! በኢትዮጵያ ውስጥ አካሄዱም አያምርም ጠንቀቅ ብለን ብንመለከተው ጥሩ ነው አለበለዚያ አደጋው
የከፋ ነው፡፡ አስከፊ ነው የጎሳ ጦርነት!”
ህዝብ ውይይትና ለሚዲያ ፍጆታ ከሆኑት የሰሞኑ ወሬዎች መካከል ሁሉም ለግራ መጋባት የሚዳርጉ ሆነው
አግኝቻቸዋለሁ፡ ፡ አንዳንዱ ግልጽም፣ አስፈላጊም አልነበረም፡፡ ከአደረጃጀት ወሬዎች እንጀምር፡፡ ክላስተር የሚባል ነገር
መጥቷል፡፡ የሥራ ዘርፎችን ቡድኖችን መፍጠርና ተመሳሳይ ሥራዎችን እያሰባሰቡ የማስተባበር፣ የአደረጃጀት አይነት ነው
ፈልሳፊዎቹም ህውሃቶች ናቸው እራሳቸውን ብቻ ለመጥቀም የወጣ አሰራር ነው! መቼም ለህዝብ ሰርተው አያውቁም!
እውነት ነው ፡፡ ስለሁለቱ አዲስ ም/ጠ/ሚኒስትሮችና በድምሩ ሶስት መሆን ተገቢነትና አስፈላጊነት ግራ የተጋባው ዜጋ
ቁጥር ብዙ ነው፡፡ ምሁራን አይስማሙም፤ ተቃዋሚዎች አይደግፉም፡ ፡ የተቀረው ግራ ተጋብቶ መሃል (መስቀለኛ)
መንገድ ላይ ቆሟል፡፡ የተሿሚዎች አመጣጥ ከየትኛውም ብሄር ወይም ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን መሆኑ ፋይዳ
የለውም ብሄሩ ብቻ ሳየሆን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል ።ካለበለዚያ ለእኔ ትርጉም አይሰጠኝም፡፡ ለእኔ ዋናው ጉዳይ
አስፈላጊ ነበር ወይ? የሚለው ነው፡፡ጉልቻው ቢለዋወጥ ለውጥ የለውም! አገሪቱ ራሷ ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትር የሚሸከም
ትከሻ የላትም፡፡
የሌሎች አገሮችን ልምዶች መጠቃቀስ ብቻ አያዋጣም፡፡ እኛ ‹‹እፍ ቢሏት ብን›› በምትል በጣም ዝቅተኛ በጀት (ያውም
ግማሹ ከውጭና ከውስጥ ብድርና እርዳታ ከሚሰበሰብ የምንተዳደር ህዝቦች ነን፡፡ )
በቅርብ ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ቃለ_ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ኤርትራው
መሪ ከኢሳያስ ጋር ለመነጋገር አስመራ ድረስ ለመሄድ መፈለግ በራሱ ግራ የገባ ነገር ነው፡፡አገር ቤት ካሉት የፖለቲካ
ድርጅቶች ጋር ምንም የሚያደራድረን ነገር የለም እያሉ ዲስኩር ሲያረጉም ይሰሙም እንደነበር የሚታወቅ ነው።
ከእነሱ ጋር መታረቅ ለምን ያስፈልገናል? ኢትዮጵያ ለኤርትራ ታስፈልጋታለች፡፡ ኤርትራ ግን ለኢትዮጵያ አታስፈልግም
ማለት ነው? መልሱን ለአንባቢ፡፡ ያው ወደቧ ነው ካላችሁኝ ደግሞ፡ ፡ እሱ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ በእርቅ ስም
መጥተው በለመዱት የበላይነት በተካኑበት እብሪት ሲጨፍሩብን ማየት አንፈልግም፡፡ በገዛ አገራችን የእነሱ መፈንጫ
መሆን አንፈልግም፡ ፡ ያለፈው ይበቃል፡፡ እዛው በጠበላቸው፡፡ አክራሪ (አልቃኢዳ አልሸባብ ወዘተ…) እንዳታስገባብን
ብንታረቅ ይሻላል የሚሉትም ከንቱ ስጋት ነው፡ ፡ የኢሳያስን ጉዳይ ለወያኔ እንጂ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን አያሳስበንም ፡፡
ዛሬ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚኖር ማንኛውም መካከለኛ ገቢ ካለው ዜጋ ይልቅ ተንቀባሮ የሚኖረው የኤርትራ ስደተኛ
ነው፡፡ያግሩ ዜጋማ ሁለተኛ ዜጋ ነው። በእኛ ልጆች ኮታ እነሱ ኮሌጃችን ገብተው ይማራሉ፡፡ እኛ ግን ከእባብ እንቁላል
እርግብ ይፈለፈላል ብለን እንጠብቃለን፡፡ ግራ የገባ ነገር ነው፡፡ ከጎረቤት ጋር ሰላም መፍጠር ተገቢ ቢሆንም ከኤርትራ ጋር
ስላለን ግንኙነት ግን ጊዜ ይፈታዋል ! ኧረ እኛ ማንንም መለየት አልቻንም እኮ ከኢትዮጵያዊነት ደም ይልቅ ሌላ ደም
ይሸታቸዋል ባለስልጣናቱ ተብዬዎች፡፡ የእኛ ችግር ድህነት እንጂ ኤርትራ አይደለችም፡፡ በሁለት ዝሆኖች መካከል ፀብ
ሲፈጠር የሚጎዳው ሳሩ ነው። በተጫረው የድንበር ፀብ ያለቁ ህዝቦቻችንንም እናስታውስ፡፡ መንግስት እያሳየ ያለው ከልክ
ያለፈ ትዕግስት ሊያመጣ የሚችለውን ችግር ከወዲሁ መገመትና መዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡ ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳይገባ
አስቀድሞ መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ በእንቅርት ላይ… እንደሚባለው ማለቂያ ያጣው የወያኔ ግፍ ማለፊው መድረሱ አይቀር!!
ወያኔና ጀሌዎቹ በታላቋ ሀገራችን ኢትዮጽያ ላለፉት 21 ዓመታት የተንሰራፋው የዘር ጥላቻ በማስፈን ነፃ አውጭ ነኝ ባዩ
ቡድን ጠባብ ዓላማውን ለማሳካት ፍቅርን በሰበኩ፤ አንድነትን በመከሩ፤ ስለ እኩሌነት በተናገሩ የዲሞክራሲ ታጋዮችና
ሠላማዊ ዜጎች ላይ ማለቂያ የሌለው ስም በመለጠፍ በእንበለ ፍርድ በየእስር ቤቱ ያጎራቸው ዜጎች ቁጥር ለመጥቀስ

እስኪያዳግት ድረስ በግፍ ላይ ግፍ በበደል ላይ በደል ከመፈጸም ሊታቀብ ይቅርና ጭራሽ እየባሰበት ከመሄድ ሊገታው
የሚችል ሁኔታ ባለመፈጠሩ የጭቆና የብረት ቀንበሩን በሕዝብ ላይ በመጫን ሀገሪቱን በፍጥነት ወደ ታላቅ እስር ቤትነት
ለውጧታል።ኧረ ወገን ምንድን ነው የሚጠበቀው?
በመጨረሻም ወያኔ የዘራውን አይነት የዘር መንፈስ የበላይነትና የበታችነት ስር የሰደደውን የጎሣ ግጭት ማስፋፋት
ልንቃወመው፣ልንታገለውና ልንፋረደው ይገባል። ወያኔ/ህውሃት፣ብአዴን፣ኦህዴድ፣ ደኢሕዴን ወዘተ እያለ እየበታተነ
የዘራው መጥፎ የዘር መንፈስ ሊለያየን ሊበታትነን አይገባም። እናትንና አባትን ሊለያይ የሚችል ፖለቲካ ማለት በብሄር
ተመስርቶ ለብሄሬ ብቻ ነው የምሰራው ካልን ይህ መንፈስ ኢትዮጵያዊነትን አያመላክትም። አባቴ እናቴን ሲያገባት ዘርሽ
ምንድነው ብሎ አላገባትም እኔቴም እንዲሁ ! ኢትዮጵያዊነታቸው በቂ ነው! ዘሩን ለገበሬው እንስጠው! እናትን አባትን
የሚለያይ ፖለቲካ አንስራ !!
ድል በአንድነት ለሚያምኑ ኢትዮጵያውን ሁሉ !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ( edenasaye@yahoo.com)

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ! (ግንቦት 7)

Ginbot 7 press release in Amharic

መግለጫ
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው  ጥላቻና የበቀል ስሜት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ  መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ  መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።
የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ያከበረዉ ወይም የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅሙን ያስጠበቀለት ብሔረሰብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን የወያኔ ዘረኞች የአማራን ህዝብ ከተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ  ነጥለዉ ለማጥቃትና የስነ ልቦና ዘይቤውን ለመስበር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኛ ባለስልጣኖች አማራውን በተከታታይ ሲዘልፉ ቆይተዋል፤አዋርደው  አስረዋል፤ ከአገር እንዲሰደድ አድረገዋል፤ አፈናቅለዋል ገድለዋል።  ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ብቻ አሶሳ፤ በደኖና አርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል።
ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው  ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡና  እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። የወያኔ ባለስልጣኖችና በየአካባቢዉ የኮለኮሏቸዉ ምስለኔዎች አካባቢዉን በግድ እንዲለቅ የተደረገ ህግ አክባሪ ዜጋ የለም፤ የተባረሩት ህግ የጣሱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፣ በማለት አሳፋሪ ድርጊታቸዉን ለመደበቅ ሲሞክሩ ታይተዋል። ሆኖም ከጉራ ፈርዳና ከአካባቢዉ ተፈናቅለዉ ወደ መጣችሁበት አካባቢ ተመለሱ ተብለው በየሜዳው ያለምግብ፣ ውኃና፤መጠለያ የተበተኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ለወገኖቻቸውና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ የድረሱልን ጩኸት ሲያሰሙ መሰንበታቸዉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ።
ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል። ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ተደርገዋል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ቢኖር በገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ዉስጥ  አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዝም ብሎ መመልከቱ ብቻ ሳይሆን ባለፈው አመት ከጉራ ፈርዳ ዘንድሮ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባረሩ እየወጡ ባሉ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ወንጀል ላይ  ተባባሪ መሆኑን አሳይቷል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያደረሰውንና በማድረስ ላይ ያለውን ይህ ነዉ የማይባል ግፍና መከራ ከዚህ ቀደም እንዳደረገዉ ሁሉ አሁንም አጥብቆ ያወግዛል። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ በዚህ በኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የትግል ምእራፍ ውስጥ በደም የተቀባ፣ የቀለመ አኩሪ ታሪክ ያለውን የአማራውን ህዝብ መልሶ መላልሶ የሚያጠቃውና ይህንን ታላቅ ህዝብ ከየቦታዉ የሚያፈናቅለው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከአማራዉ ህዝብ ጋር ብቻ በማያያዝ አገራችንን ለማዳከምና አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ “ምን አገባኝ” ብሎ እንዲመለከት ለማድረግ ባለው እጅግ አደገኛ ዕቅድ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ በጥብቅ ያሳስባል።
ከዚህም በተጨማሪ በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ  ያላችሁ  ወንጀለኞችና ተባባሪዎች፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት   በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።
በአማራው የደረሰው ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያውያን  ዜጎች ጥቃት ነው እንላለን።  ግንቦት ሰባት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበትን ነጻነት የምናስጠብቀው በህብረት ነውና ወያኔ በአሁኑ ግዜ በአማራው ወገናችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ፤ መከራና መፈናቀል በእያንዳንዳችን ላይ እንደደረሰ በመቁጠር ይህንን ግፍ በመፈጸም የማይሰለቸውን ዘረኛ አገዛዝ በተባበረ ህዝባዊ ትግል ከአገራችን ለማስወገድ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል ጥሪ ያስተላልፋል።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
መጋቢት 2005 ዓ. ም

Total Pageviews

Translate