Pages

Dec 13, 2012

ኢትዮጵያውያን ሚኒሶታ ለህክምና መጥታ ላረፈችው ወጣት ቀብር ማስፈጸሚያ እጃቸውን እንዲዘረጉ ተጠየቀ

ዘ-ሐበሻ)
ከኢትዮጵያ
የህክምና
እድል አግኝታ
በመምጣት ስትከታተል
የነበረችው
ወጣቷ አበሻ
ንጉሴ ከበደ
ትናንት
ዴሴምበር 11
ቀን 2012
አረፈች።
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1985 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተወለደችው አበሻ ንጉሴ ከበደ በሳምባ ካንሰር ላለፉት 2
ዓመታት ስትሰቃይ መቆየቷን ለህዝብ ከተበተነው የሕይወት ታሪኳ ለመረዳት ተችሏል። ኖቬምበር 12 ቀን 2011
ወደ ሚኒሶታ ለህክምና የመጣችው ይህች ወጣት ህክምናዋን አጠናቃ በመልካም ሁኔታ ላይ የነበረች ሲሆን በወቅቱም
ከነበረችበት ሆስፒታል እንድትወጣ ሲደርግ በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በመረባረብ የ እራት ምሽት
በማዘጋጀት ለቤት ክራይ እና በውጭ ሆና የምትታከምበትን ገንዘብ አሰባስበው ነበር። ይህች ወጣትና አስታማሚ እናቷ
እስከ ትናንት ዲሴምበር 11 ቀን 2012 ድረስ በሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን እርዳታ የቆዩ ሲሆን ወጥቷ በማለፏ
ምክንያት ለቀብር ማስፈጸሚያ ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልጋል።
በተለምዶ አንድ ሰው ሲሞት ለቀብር ማስፈጸሚያ ወይም አስከሬኑን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ እስከ $8000
የሚያስፈልግ ሲሆን ይህን ወጪ እናቷ መሸፈን ስለማይችሉ በሚኒሶታም ሆነ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ
ኢትዮጵያውያን የ እርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ተጠይቋል። በዚህም መሠረት በፔይፓል ለመርዳት ለምትፈልጉ
የሚከተለው ሊንክ ላይ ይግቡ። Please Donate
ለበለጠ መረጃ

612-229-7453 or
email us at
biruk012@yahoo.com or
alemhaile6@gmail.com
ሚኒሶታ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለቅሶ ለመድረስ የምትፈልጉ ከሆነ እናቷ በደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ
ሚኒያፖሊስ ስለተቀመጡ እዚያ መሄድ ይቻላል።
አድራሻው፡
4401 Minnehaha Ave. S
Minneapolis, MN 55406
USA
በሚኒሶታ ይሄ ነው የሚባል የመረዳጃ ማህበር ባለመኖሩና የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ የራሳችን አዳራሽ ስለለሌን
በደስታም ሆነ በሃዘን ጊዜ የመሰብሰቢያ ቦታ አለመኖሩ እንደዚህ ያሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ሁሌ እንደምንቸገር
ይታወሳል። መፍትሄው ምን ይሆን??
Abesha Nigussie Kebede was born in 1985
E.C. in Addis Ababa, Ethiopia. Our sister
Abesha Nigussie came to the United States
of America for rare lung cancer treatment
in November 12, 2011. Abesha has been
struggling with this illness for the past two
years. Unfortunately, our sister lost her
battle against this Chronicle disease. She
has been pronounced dead on December 11,
2012 at 8:45pm at Our Lady of Good peace
Council Home 2076 Saint Anthony Avenue
Saint Paul, MN 55116
Now it is our turn to help her mother to go
through this very hard time in any way we
can. So we are kindly asking each and every
one of you to extend your hands to ease the
financial burden on her mother.
If you would like to donate click the “Please
Donate here” button below.
Abesha will always be remembered!!!
May God rest her Soul.
If you would like to pay your condolences in person, please call us
612-501-3648
612-229-7453

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate