Pages

Apr 11, 2013

(ሰበር ዜና) ሲአን የፊታችን እሁድ ከሚደረገው ምርጫ

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባ የድሬዳዋ የክልል የአካባቢ
ምርጫ ለማሳተፍ ተመዝግቦ በዝግጅት ላይ የሚገኘው
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ የሚደርስበትን ጫና
ከምርጫው ለመውጣት መገደዱን አስታወቀ። ኢሕ
አዴግ ብቻውን በሚወዳደርበት የአካባቢና የከተማ
ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ የፊታችን እሁድ
እንዲሁም በሳምንቱ ሚያዚያ 13 የሚካሄድ ሲሆን
የሲአን ከምርጫው መውጣት ለገዢው መንግስት
የፖለቲካ ኪሣራ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ለዘ-
ሐበሻ ተናግረዋል።
ፓርቲውም በደረሰበት በደልና ጫና የተነሳ የመጨረሻ
እርምጃ ለመውሰድ መቃረቡን ሲገልጽ የከረመው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የፊታችን እሁድ የሚካሄደውን ምርጫ
በተመለከተ የሚደርስባቸውን ጫና መታገስ የማይችሉበት ደረጃ በመድረሱ ከምርቻው ሊወጣ ተገዷል። ሲአን “እጩ
ተወዳዳሪዎቻችን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ እንዲሁም የተለያዩ በደል እንደሚፈፀምባቸው”
ሲገልጽ ቆይቶ ገዢው መንግስትም ይህን እንዲያስቆም ቢተይቅም ይህ የማሰር እና የማንገላታት ተግባር ጨምሮ
በመቀጠሉ ፓርቲው ራሱን ከምርጫ እንዳገለለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።
በዘንድሮው የአካባቢና የከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ ዋና ዋናዎቹ ከ30 በላይ የሚሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች
አንሳተፍም በሚለው አቋማቸው በመጽናታቸው ኢሕ አዴግና ተለጣፊዎቹ ፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ /ኢራፓ/
፣ የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲ ሃይሎች ግንባር /ኢፍዴሃግ/ እና ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አንዲሁም አንድ
ተወዳዳሪን የመደበው ኢዴፓ ይሳተፋሉ ቢባልም ዋና ዋና ተቃዋሚዎች ቦይኮት ባደረጉት የዚህ ምርጫ በኢሕአዴግ
አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ከወዲሁ የታወቀ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate