Pages

Jun 4, 2013

ጦር ሃይሎች ውስጥ የተከሰተው የእርስ በእርስ ፍትጊያ ተሟሙቋል

:ከጦር ሃይሎች መኮንኖች የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው የወያኔ ከፍጠኛ የጦር ጄኔራሎች በመንግስታቸው በኩል የቀረበባቸውን ውንጀላ ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ በመግባት እርስ በእርሳቸው እየተፋተጉ መሆኑን ታውቋል::ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተደረገው እና አሁንም በቀጣይነት በመኮንኖች ክበብ ውስጥ በከፍተኛ መኮንኖች እና የጦር መምሪያ ሃላፊዎች ላይ የቀጠለው ግምገማ ውጠቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የሆነውሌ/ጄ. ሳሞራ የኑስ ዋናው አትኩሮ ሲናገር የነበረው በመረጃ ንግድ ላይ የተሰማራችሁ የጦር መኮንኖች ምስጢራችንን አሳልፋችሁ ሸጣችኋል እና ብትጠነቀቁ መልካም ነው ካልሆነ የመጨረሻ እርምጃ እንወስዳለን ሲል ዝቷል::ከመከላከያ ውስጥ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ አላግባብ ጠፍጥቷል የተባለው እና ለወያኔው ምር ቤት የቀረበው የኦዲት ሪፖርት በመኮንኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግብግብ እየፈጠረ ሲሆን ለግምገማው መራዘም ምክንያት መሆኑን ምንጮሹ ለምንልክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::ይህንን ተከትሎ አንዳንድ  የተመረጡ የጦር መኮንኖችን ለመክሰስ የታቀደ ሲሆን አትኩሮት የሚደረግባቸው በሕወሓት ውስጥ በአሁን ወቅት ተከስቶ ያለውን ክፍፍል ተከትለው ከባለስልጣናት በተጻራሪ ወገን ቆመዋል የተባሉ የመለየት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል ምንጮቹ አክለውም ዝርዝር መረጃው በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል::

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate