የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር።
አቶ ኦባንግ ሜቶና የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ፣ ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር አራት፣ ከአዲስ አበባ ሰባት ጠበቆች በመሆን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የስካይፕ ውይይት ለመጀመር ተዘጋጅተው ነበር። የጋራ ንቅናቄው እንዳስታወቀው ውይይቱ ሲጀመር ድምጽ መስማት አልተቻለም።
በዚሁ ሳቢያ ውይይቱ መቋረጡን ያስታወቀው አኢጋን ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር ጋር በመነጋገር ሰኞ ቀን በውል በማይገለጽ ሰዓት በሌላ መልኩ ውይይቱን ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን አመልክቷል። የአሜሪካ ህግ ባለሙያዎች ማህበር ኢህአዴግ ያለ አግባብ አስሮ የሚያሰቃያቸውን ዜጎች ጉዳይ አደባባይ ለማውጣትና አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ይቻለው ዘንድ
http://www.goolgule.com/aba-and-smne/ መግለጻችን ይታወሳል። በዜናው አሁን የተጀመረው ስራ የስምምነቱ መጀመሪያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment