Pages

Mar 9, 2013

ጥቃት በየተራ እስከመቼ?

ባለፉት 21 የወያኔ የግዛት አመታት አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጅ ጥቃት፣ ግፍ፣ በደልና እብሪታዊ የመብት ገፈፋ ያልደረሰበት ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ክፍል የለም። ገበሬው፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ የፋብሪካ ሰራተኛና በየዘርፉ የእለት ጉርሱን አሳዶ የሚኖረው ሁሉ የወያኔን የሰቆቃ ግፍ በትር በየተራ አይቶታል፣ እያየውም ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አንጀቱ ለፍቶ ያቋቋማቸው ተቋሞቹ እየፈራረሱ ለወያኔ አገዛዝ እንዲመቹ ሆነው ሲጨፈላለቁም አይተናል።
ወያኔ ይህን ሁሉ ያደረገው “አንዱን በአንዴ” በሚል ስልት ነው። መምህራንን ሲያጠቃ የፋብሪካውን ሰራተኛ ተመልካች ያደርገዋል፤ ገበሬውን ሲያጠቃ ከተሜውን ዝም ይለዋል፤ ከተሜው ላይ ሲዘምት ገበሬው ተመልካች ይሆናል፤ ቤተክርሰቲያን ላይ ሲዘምት ቤተ ሙስሊሙ ይመለከተዋል፤ የቤተ ሙስሊሙ የበደል ተራ ጊዜ ቤተክርስቲያን ተመልካች ትሆናለች። ይህ ወያኔን እስከዛሬ ያደረሰው ስልት ነው።
አራዊታዊው የወያኔ አገዛዝ በተመቸውና ይጠቅመኛል ብሎ በአሰበ ሰአት ሁሉ የውብ ህዝብነት ምልክታችን የሆነውን የባህልና የቋንቋ ስብጥርነታችንን እርስ በርስ ለማናከሻነት ሊጠቀምበትም ሞክሯል፤ በተወሰነ ደረጃ አልሰራላቸውም ማለት ያስቸግራል፡፡
ወያኔዎች ከፋፍሎ መግዛትንና በየተራ ማጥቃትን በኪነ ጥበብ ደረጃ አሳድገነዋል ብለው ያምናሉ። በህዝብ ወገን ያለነውም የዲሞክራሲና የነጻነት ሃይሎች ለዚህ አልተመቸንም ማለት ያስቸግራል፡፡ ይህንን ከፋፍሎ የማጥቃት ግፍ በጋራ ለመመከት ያደረግነው ጥረት ህዝባችን ላይ እየደረሰ ካለው ጥቃት ጋር ቢያንስ የሚመጣጠን አይደለም።
የወያኔ መሪዎች ዛሬ ስልታቸውን በማሻሻል አደገኛ ጭዋታ በቤተ እምነቶቻችን ዙሪያ መጫዎት ጀምረዋል። የቤተክርስቲያን እና የአቢያተ መስጊዶችን አስተዳደር በካድሬዎቻቸው ለመቆጣጠር ከሚያደርጉት ሳይጣናዊ ተግባር በተጨማሪ ህዝቡ ሃይማኖት ለይቶ እንዲባላ ለማድረግ በእጅጉ የሚቀፍ ፕሮፖጋንዳ እያካሄዱ ነው። ፍጹም ምሳሌያዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሲቪል መብት ጥያቄ እንደባዕድ መሳሪያነትና እንደ ሽብርተኝነት ለማሳየት እየሞከረ ይገኛል። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙሉ እጁን በማስገባት የተጀመረውን እርቀ ሰላም በማፍረስ የራሱን እንደራሴ ሰይሟል። ይህም አልበቃ ብሎት ለዘመናት በመከባበር የኖረውን ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን እርስ በርስ ለማጋጨት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።
ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ሀገራችን ወደማትወጣው አደጋ እየተገፋች ነው። ይህንን ወያኔ ያዘጋጀልንን የክፍፍልና ግጭት ድግስ ለመመከት ይበልጥ በአንድነት የምንቆምበት እና የምንታገልበት ግዜ ዛሬ ነው፡፡
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለወያኔ የ”ከፋፍለህ በየተራ ቀጥቀጥ” ፖሊሲ መድሃኒቱ አንድ ሆኖ በአንድነት አሻፈረኝ ብሎ መነሳት መሆኑን ያምናል፡፡ ወያኔ ጉልበቱ የኛ መከፋፈልና ለክፍፍሉ መመቸት መሆኑን ያምናል፡፡ እኛ ስንተባበርና ልዩነታችንን ለመጠቀም የሚያደረገውን ሙከራ ስናከሽፍና አንዱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሁላችንም ነው ብለን የተነሳን እለት ወያኔ የለም።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ወያኔ በፈቃዱ የማይታረም ፋሺስታዊ አምባገነን መሆኑን ከተረዳ ሰንብቷል። በመሆኑም ወያኔን በማስገደድ ወይም በማስወገድ ነጻነታችንን መቀዳጀትና ነጻ ሀገር እንዲኖረን ማድረግ አለብን ብለን እናምናለን። ለዚህ ትግልም ማንኛውንም መሰዋእትነት ለመክፈል ተነስተናል። ነጻነትና ኮርተህ በነጻነት የምትኖርባት ሀገር እንድትኖርህ የምትወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተቀላቀለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ጋምቤላ አሁንም በወያኔ ወራሪ ሠራዊት እየታመሰች መሆኗ ተሰማ


በ1996 ዓም ከ400 በላይ አኝዋኮችን በግፍ የጨፈጨፈዉ የወያኔ ወራሪ ሠራዊትና ልዩ ኃይል ከሰሞኑ በብዛት ወደ ጋምቤላ በመዝመት ሠላማዊ ዜጎችን በተለይ የአካባቢዉን አርሶ አደሮች እየያዘ ማሰርና መግደል መጀመሩን ከአካባቢዉን እየሸሹ ጫካ የገቡ ዜጎች ለኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ስልክ እየደወሉ በሚልኩት ዜና ገለጹ። በተለይ ካለፈዉ አርብ ጀምሮ ፌዴራል ፖሊስ፤ መከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ልዩ ሀይሎች ተቀናጅተዉ በጋራ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ተቃዋሚዎችን ይረዳሉ ወይም ታጣቂዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ ብለዉ የጠረጠሯቸዉን ሠላማዊ ዜጎች ማሰራቸዉንና እራሳቸዉን ለማዳን የሞከሩ ሰዎችን ተኩሰዉ መግደላቸዉን ከአካባባዉ የደረሰን ዜና ጨምሮ ያስረዳል። በአሁኑ ወቅት የወያኔ ወራሪ ሠራዊት በብዛት ወደ ጋምቤላና አካባቢዉ እየዘመተ ሲሆን የአካባቢዉ ህዝብም እራሱን ለማዳን ጫካ እየገባ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የወያኔ ወራሪ ሠራዊት ካለፈዉ ዐርብ ጀምሮ በወሰደዉ የማጥቃት አርምጃ ከአስራ ሁለት በላይ ሠላማዊ ዜጎችን የገደለ ሲሆን ከሟቾቹ ዉስጥ አንድ የአካባቢዉ ተወላጅ የሆነ የአሜሪካ ዜጋ ይገኝበታል። የግንቦት ሰባት ድምጽ ዝግጅት ክፍል የወያኔ ጦር በአካባቢዉ ያደረገዉ ጭፍጨፋ እንደተሰማ በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ ባለስልጣናትን ሰልክ ደዉሎ ሁኔታዉን ለማጣራት ሞክሮ ነበር ፤ ሆኖም የዝግጅት ክፍላችን ያናገረዉ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣን በአካባቢዉ ምንም አይነት ግጭት የለም በማለት በአለም ዙሪያ የተሰራጨዉን እዉነት ለመካድ ሞክሯል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች የጸጥታ ሀይሎች ጋምቤላ አካባቢ የአማጽያንን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በሚል በወሰዱት እርምጃ አንድ የአሜሪካ ዜግነት ያለዉ ሰዉ መገደሉን ለአሜሪካ ኤምባሲ ተናግረዋል።
የአዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ የሆኑት አቶ አባንግ ሜቶ ከኢሳት ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በጋምቤላና በአካባቢዉ ያለዉን ወታደራዊ ዉጥረት ድርጅታቸዉ በቅርብ እንደሚከታተለዉ ተናግረዉ ከሰሞኑ በወያኔ ወታደሮች ተገደለ ስለተባለዉ የአሜሪካ ዜጋ አስፈለገዉን የክትትል መረጃዎች ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መስጠጣቸዉን ተናግዋል። ዜጎችዋ በዉጭ አገር በሚደረጉ ወታደራዊ ግጭቶችና አመጾች ሲገደሉ ወይም ደብዛቸዉ ሲጠፋ ክፍተኛ ክትትል የምታደርገዉ ዩ ኤስ አሜሪካ አሁንም ጋምቤላ ዉስጥ በወያኔ ወታደሮች ተገደለ የተባለዉን ዜጋዋን ጉዳይ መከታተል መጀመሯን ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ የኦባማ አስተዳደር ከአሸባሪዎች ጎን ተሰልፈዉ በሚዋጉ የአሜሪካ ዜጎች ላይ የሚወስደዉን አርምጃ በተመለከት ሾልኮ የወጣዉ መረጃ ኮንግሬሱን ጨምሮ አያሌ አሜሪካኖችን እንዳስቆጣ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ከሰሞኑ ጋምቤላ ዉስጥ የተገደለዉ አሜሪካዊ ጉዳይ ይበልጥ በተሰማና በታወቀ ቁጥር ወያኔ ላይ መዘዝ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ።

Mar 8, 2013

እኛም እንድገመዋ… ርዕዮትን እያሰሩ … ቐሽ ገብሩን ቢዘክሩ… “ሼም” የለም በአገሩ…!?

አቤ ቶኪቻው

ተዓምረኛው ኢቲቪ ለማርች ስምንት የሴቶች ቀን መታሰቢያ አንድ ዶክመንተሪ ፊልም አሳይቶናል። ፊልሙ የዛሬ አመት ተላልፎ እኛም የአቅማችንን አስተያየት ሰጥተንበት ነበር። ታድያ ዛሬም ኢቲቪዬ ፊልሙን ደግሞ አሳይቶናል። ታድያ መድገም ብርቅ ነው እንዴ… እኛም አስተያየታችንን እንድገመዋ!
በመጀመሪያ አበሻ እንደመሆኔ መጠን ጭቆናን “እምቢ” ብለው ፋኖን ለዘመሩ ታጋዮች ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ያለ ሽሙጥ እገልፃለሁ።
ተስፋዬ ገብረ አብ ከተረካቸው ትረካዎች በሙሉ “የቁንድዶ ፈረስ” ትረካ በጣም የመሰጠችኝ ናት። እስቲ ለማስታወስ ልሞክር…
ሐረር አካባቢ፤ የጋሪ ፈረሶች የሚደርስባቸው የስራ ጫና እጅግ በጣም ከባድ ነበር። ከስራ ጫናው እኩል ደግሞ ዱላም አለው። ልክ አሁን አሁን ደሞዛችን አነሰ ብለን “ኡኡ” ስንል “ለአባይ እና ለሌሎች ልማቶች ደግሞ መዋጮ አዋጡ” ተብለን መከራችንን እንደምናየው ማለት ነው። በዚህ ላይ እነዚህ የጋሪ ፈረሶች ስራውና ዱላ የሚደራረብባቸው አንሶ ጌታቸው (አባ ፈርዳው) ቀለባቸውንም በአግባቡ አይሰፍርላቸውም ነበርና ከሰውነት ጎዳና ወጥተው ክስት ጉስቁል አሉ።እኛም እንድገመዋ… ርዕዮትን እያሰሩ … ቐሽ ገብሩን ቢዘክሩ… “ሼም” የለም በአገሩ…!?
ይሄን ግዜ “እምቢኝ” አሉና “ቁንድዶ” ወደተባለ ጫካ ገቡ። ከዛም ባህሪያቸው ተለውጦ እንደፈረስ ሳይሆን እንደ እንደ አውሬ ሆኑ። ማን ወንድ መጥቶ ዳግም ወደዛ የጋሪ ባርነት ይመልሳቸው? ማንም።
ታድያ ፈረሶቹ እዛው ጫካ ውስጥ መሽገው እንዳሻቸው እየበሉ እንዳሻቸው እየቦረቁ አማረባቸው። ወዘናቸውም “ጢም” አለ።
“በአሁኑ ግዜ የሀረር አካባቢ ነዋሪዎች የኦህዴድ አባላትን እስከ መቼ የጋሪ ፈረስ ትሆናላችሁ? አንዳንዴ እንኳን የቁንድዶ ፈረስ ሁኑ እንጂ…! እያሉ ያሽሟጥጧቸዋል።” ብሎናል ተስፋዬ። (ልክ ነኝ አይደል ተስፋዬ…? “ይሄንን እኔ አላልኩም” ካልክ እኔ ለማለት እገደዳለሁ…!(ፈገግታ))
እናም እኔ በበኩሌ የቁንድዶ ፈረስነትን አደንቃለሁ። አላማው ልክ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ በይደር ይቆይ። ነገር ግን በደል ሲበዛ “እምቢ” ማለት ከአባት የወረስነው ነው። ዛሬ የሽብረተኝነት አዋጅ ወጥቶ ሳይከለከል አይቀርም እንጂ አንድ ዘፈን ትዝ ይለኛል…
“ደብቆታል መሰል ሶማ በረሃው
“እምቢ” ያለው ጎበዝ የታል ሽፈራው” የሚል ዘፈን።
በአሁኑ ወቅት፤ ይህንን ዘፈን በይፋ መዝፈን የሚቻል አይመስለኝም። ምክንያቱም በሽብርተኝነት አዋጁ አንድ ግለሰብ፤ በዘፈን በፅሁፍ እና በተለያዩ መንገዶች “ሽብርተኛን” እንኳንስ ሲያበረታታ ተገኝቶ ይቅርና፤ “አበረታቷል” ተብሎ ሲታሰብም “ጉዱ ይፈላል” ይላል። በተጨባጭ እንደምናየው ደግሞ እንኳንስ እምቢ ብለው ሶማ ጫካ ገብተው ይቅርና በከተማው ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸው “አሸባሪ” ስለመሆናቸው መረጃው አለ። ማስረጃው ጠፍቶ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩም እኛም የጨነቀን…! ስለዚህ “ደብቆታል መሰል ሶማ በረሃው እምቢ ያለው ጎበዝ የታል ሽፈራው…” ብሎ ማዜም አይቻልም ማለት ነው።
ለማንኛውም፤ ዘፈኑ ግን “እምቢ” ባይነትን እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙሃን የሀገሬ ሰው እንደሚያደንቅ ያስረዳልኛል። አዎ አንዳንዴም እምቢ ማለት ጥሩ ነው። “እምቢ… እምቢ ለሀገሬ! እምቢ… እምቢ ለክብሪ! እምቢ… ታታታታ” ፉከራው ራሱ ማማሩ።
ስለዚህ ቐሽ ገብሩ፤ አሞራውና ሌሎችም “እምቢ” ባይ ታጋዮች “እምቢ” በማለታቸው አደንቃቸዋለሁ። እንኳንም እምቢ አላችሁ!
ወደ ቐሽ ገብሩ ስንመጣ የዶክመንተሪው አዘጋጆች ልብ ያላሉት ወይም ደግሞ “ምን ታመጣላችሁ” ብለው ችላ ያሉት አንድ ስህተት የፌስ ቡክ ወዳጆቼ አግኝተው ነበር። ልብ በሉልኝ ህውሃት ሆዬ ቐሽ ገብሩን መትረየስ ሲያሸክማት ገና የአስራ ሶስት አመት ልጅ ነበረች። ከፈለጋችሁ አስሉት በአስራ ዘጠኝ ስድሳ አንድ ተወለደች። በአስራ ዘጠኝ ሰባ አራት ወደ ትግል ገባች። ማነው ሂሳብ የሚችል…? በሉ እስቲ አስሉልኝ። ሰባ አራት ሲቀነስ ስድሳ አንድ እኩል ይሆናል፤ አስራ ሶስት። ዘጋቢው ፊልም ሲቀጥልም “…ትግሉን በተቀላቀለች በጥቂት ወራት ውስጥ እጇን ተመታች። እንደዛም ሆና መትረየስ ትሸከም ነበር።” ይላል። ጉድ በል ህውሃት…! አይሉኝም?
በዛ ሰሞን አለም ሲነጋገርበት ከሰነበተባቸው ነገሮች ውስጥ በኡጋንዳ የሚገኘው የሎርድ ሬዚስታንት አርሚ መሪ፤ ጆሴፍ ኮኒ ህፃናትን ጦርነት ውስጥ እየማገደ ነው በሚል ታድኖ ይከሰስ ዘንድ የተጀመረው “ኮኒ ሁለት ሺህ አስራ ሁለት” የሚል እንቅስቃሴ ነው። በአለም አቀፍ ህግ፣ አረ በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ቢሆን ህፃናትን ለጦርነት ማሳተፍ የለየለት ወንጀል ነው። በእግዜሩ ዘንድም ያስጠይቃል።
እና ህውሃት የአስራ ሶስት አመቷን ህፃን ሙሉ “ቐሽ ገብሩ” ን በጦርነት ማሳተፉ ሳያንስ የግፉ ግፍ ደግሞ ለማርች ስምንት የሴቶች መብት ክብረ በዓል ላይ ታሪኳን እንደ ጥሩ ነገር ዘገበልን። እውነቱን ለመናገር ይሄ ትልቅ የወንጀል መረጃ ነው። እንደኔ እምነት ይህንን መረጃ ያጠናከሩ ሰዎች የውስጥ አርበኝነት ስራ እየሰሩ ነው። ይሄ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ገና በርካታ መረጃዎችን ያወጣል። እዝችው ላይ ሙሉ ወይም ቐሽ ገብሩ ገና አስራ ስምንት አመት እንኳ ሳይሞላት አንድ ጎረምሳ በፍቅር ስም አስረግዞ እስከማስወረድ እንድትደርስ እንዳደረጋትም ዶክመንተሪው ይዘግባል። ሰውየው ከሷ ጋር ያሳለፈውን ፍቅርም ሲናገርም በኩራት ነው። እንዴት ነው ነገሩ… እኛ መሀሙድ አህመድ በአንድ ዘፈኑ ላይ “ሸግየዋ ጉብሊቷ… የአስራ አምስት አመቷ እንዴት ነሽ በሉልኝ የምታውቁ ቤቷን” ብሎ ስለዘፈነ አይደል እንዴ ከህፃናት መብት አንፃር ወንጀል ነውና ይቅርታ መጠየቅ አለበት እያልን የምንሟገተው? እንዲህ የባሰውን ነውር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አየነው። ለዚህ ነው አይናችን የተርገበገው…?
ወዳጄ እንዴት ሰነበቱ አይገርምዎትም ይሄ ሁሉ መንደርርደሪያ መሆኑ… ይበሉ ወደ ዋናው ጉዳይ ተያይዘን እናምራ
እናልዎ… ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተለያየ ግዜ የተለያየ ዘጋቢም አወዛጋቢም ፊልሞችን ያቀርብልናል።
በዛ ሳምትን ያየነውም የቐሽ ገብሩ ዶክመንተሪም የዚሁ አካል ነው። እንግዲህ ከላይ ያነሳነውን በቐሽ ገብሩ የተጋለጠውን ህፃናትን ወደ ጦርነት የማሰማራት እና ለአቅመ ህይዋን ያልደረሱ ሴቶችን የማማገጥ ወንጀል እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለሚከታተሉ አካሎች እንተወው እና የፈረደባትን ይቺን ህፃን “እምቢ” እንዳለች ጀግና እንቁጠራት። ቆጠርናት…!
ኢህአዴግ ደርግን ብዙ ግዜ ደርግ በጦርነት የማረካቸውን ታጋዮቼን የማያምኑበትን እንዲናገሩ ያሰቃያቸው ነበር፤ ከዛም እምቢ ሲሉት ያስራቸዋል፤ ይገድላቸዋል። ብሎ ይወቅሳል። ይቀጥልናም ቢሆንም ግን፤ “እንደ አሞራው ሁኑ እንደ ቐሽ ገብሩ ሁኑ ብሎ ይመክረናል። እኛም ምክር የምንሰማ ልባሞች ነንና እሺ ብለን እንደ አሞራው፤ እንደ ቐሽ ገብሩም ለመሆን እንታትራለን ከዛ ውጤቱ ምን ይሆናል አይሉኝም…? ለምን እጠይቅሀለው እያወቅሁት…? አሉኝ እንዴ!?
ሰሞኑን አቶ አንዷለም አራጌ ላይ የሆነውን ነገር ሰምተዋል። አንዷለም አራጌ እንደ አሞራው ሁኑ ከመባሉ በፊትም እንደ አሞራው “እምቢ” ባይ ነበር። ለዛውም ጫካ ሳይገባ ፊት ለፊት እምቢ ብሎ የተጋፈጠ ደፋር የተቃማዊ ፓርቲ አመራር ነው። ምን ዋጋ አለው አንዷለም እንደ አሞራው “እምቢ” ቢልም ኢህአዴግ ደግሞ እንደ ደርግ “እምቢ” ማለት አይቻልም ብሎ አሰረው። ማሰር ብቻ ቢሆን በስንት ጣዕሙ ጎረምሳ አስገብቶ አስደበደበው እንጂ!
ማርች ስምንት የአለም ሴቶች ቀን ነው። በአለም ላይ ያሉ ሴቶች ቀደም ሲል ሲደርስባቸው የነበረ ጭቆና ይብቃ የተባለበት ቀን። ይህ ቀን፤ የህውሃት ሴቶች ቀንም የአንድነት ሴቶች ቀንም፤ የጋዜጠኛ ሴቶች ቀንም፣ የሁሉም ሴቶች ቀን ነው።
ርዕዮት አለሙ አሳሪዎቿ የጠላነውን አብረሽን ከጠላሽ ትለቀቂያለሽ ብለዋት ነበር። ቃል በቃል ሲነገር “ኤልያስ ክፍሌ የተባለው ጋዜጠኛን አሸባሪ ነው መሰስክሪበት እና ትለቀቂያለሽ” ተባለች። እርሷም እኔ “በወንጀለኝነት አላውቀውም” ብላ ድርቅ አለች። እንግዲያስ ብሎ ኢህአዴግም አስራ አራት አመት ፈረደባት። ቐሽ ገብሩን ደርግ የያዛት ግዜ “የህውሃት ሰዎችን ወንጀለኛ ናቸው ብለሽ መስክሪባቸው” አላት እምቢኝ ብላ ድርቅ አለች ሞት ፈረደባት። እንግዲህ ቐሽ ገብሩ እና ርዮት አለሙ አንድ ናቸው “እምቢኝ” ብለዋልና። ደርግ እና ኢህአዴግስ…? የመጣው ይምጣ ደፍሬ ልናገር ነው..! አዎ ደርግ እና ኢህአዴግም አንድ ናቸው። እምቢ ያላቸው ላይ ሁሉ ይፈርዳሉና። በነገራችን ላይ የደርግ ፕሮፖጋንዳ ሰራተኞች ቐሽ ገብሩን ለማናገር መከራቸውን ሲያዩ የነበረውን ያህል የኢህአዴግ ጋዜጠኞችም በተደበቀ ካሜራ ሳይቀር ርዮትን ለማናገር አበሳቸውን ሲያዩ ነበር። ነገር ግን ቐሽ ገብሩም ርዮትም አለሙም ፍንክች የአባ ቢላው ልጅ ብለዋል። ወይ መገጣጠም…! አይሉልኝም?
እና ታድያ የሴቶች ቀን ክብረ በዓል ሲዘከር መንግስት ርዕዮትን አስሮ ስለ ቐሽ ገብሩ ሲተርክ የአራዳ ልጆች ሰሙ። ሰምተውም ጠየቁ “ሼም የለም እንዴ በአገሩ!?” አሉ ዝርዝር ያለው የስራ ሂደት ካለ መልስ ያምጣ…!
በጥቅሉ መንግስት እነ ርዕዮትን፣ እነ እስክንድርን፣ እነ ውብሸትን፣ እነ ሂሩትን፣ እነ አንዷለምን እነ ናትናኤልን፤ ስንቱን ጠርቼ እዘልቀዋለሁ? በጅምላው እምቢ ያሉትን ሁሉ እያሰረ እና እየገረፈ “ደርግ ታጋዮቼን አሰረ፣ ገረፈ፣ ገደለ” ብሎ ዋይ ዋይ ማለት ውሃ የማያነሳ ወቀሳ ነው። መፅሐፉም ይላል “የሌሎችን ጉድፍ ከማየትህ በፊት በአንተ አይን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ተመልከት…”
በመጨረሻም
ያወጋነውን ለፍሬ ይበልልን
አማን ያሰንብተን!

Mar 7, 2013

Watch and share. Two young Ethiopian immigrants physically abused by Arab human traffic smugglers

Watch and share. Two young Ethiopian immigrants physically abused by Arab human traffic smugglers




“ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቆች ሆነዋል” ስማቸው ያልተገለጸ እናት

ከሉሉ ከበደ

ሰሞኑን ከአገር ቤት አንዲት እናት ልጃቸውን ሊጠይቁ መተው ነበር። ልጃቸው የባለቤቴ ጓደኛ ነች።..የኔም ጓደኛ!…እኒህ አናት አንደበተ ርቱእና ተደምጠው የማይጠገቡ ጨዋታ አዋቂ ቀልደኛም ናቸው። ሑሉም ነገር የገባቸው ፍጹም ፖለቲካ አዋቂ ብሩህ እናት ናቸው። ጨዋታቸው ንግግራቸው ሁሉ ይማርካል። ሰማንያ አመት አይሞሉም። ጥንክር ያሉ፤ የነቁ ፍጹም ጤናማ እናት ናቸው።

ወይን ቢጤ ገዛሁና ባለቤቴ ድፎ ዳቦ ጋግራ (እናቶች አዚህ አገር ሲመጡ ድፎ ዳቦ ሲቀርብላቸው ደስ እንደሚላቸው ታውቃለች) እንኳን ደህና መጡ ልንል ሄድን።
ለሁለት ሰአት ያህል አብሬ ስቆይ ከናታችን የገበየሁት ትምህርትና ቁም ነገር በቀላል የሚገመት አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ እየጠላቸው ዛሬ ስልጣን ላይ የተጣበቁት የወያኔ ደናቁርት፤ addis-ababa-2013የኢትዮጵያን ህዝብ ምንም አያውቅም ብለው፤ የሚገምቱትና የሚንቁት፤ወደ ታች ወደ ህብረተሰቡ ዝቅ ብለው፤ስለነሱ አገዛዝ፤ ስለ መልካም አስተዳደር ያለውን ግንዛቤ ቢረዱ ምን ያህል ከህብረተሰቡ ኋላ ኋላ እየሄዱ እንመራሀለን እንደሚሉ በተረዱና ባፈሩ ይበጃቸው ነበር።
እኒህ እናት ድህነትን እኩል ያካፈለን ደርግ ተሻለ ነው ነው የሚሉት፤ “እነዚህ ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቅ ሆነዋል። ደርግ አንዱን ልጅ አንዱን እንጀራ ልጅ አላደረገንም። ቢበድለንም አልለያየንም።”
ጎዳና ላይ ለፈሰሱ ለማኝ ህጻናትና ወላጆች ዘወትር ያለቅሳሉ። ኑሮአቸውን የከተማው ቆሻ ክምር ላይ የመሰረቱ ወላጆችና ልጆች ያስለቅሷቸዋል። “ይሄ ሁሉ ፎቅ ይገነባል። የእያንዳንዱን ፎቅ ባለቤት አስር አስር ልጅ ከጎዳና ወስዶ እንዲያሳድግ ቢያስገድዱት ጽድቅ ነበር። ላለው ሰው ምንም ማለት አይደለም” ይላሉ።
ስለቤተሰብ ስለዘመድ አዝማድ፤ስአየርንብረትና ሌላ ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ወዲያው ነበር ስለ ሀገር ጉዳይ የተነሳው።
“ኑሮ አንዴት ነው?.. እትዬ… አገር ቤት ” አልኩ ።
“…አየ… ልጄ .. ምን ኑሮ እንዴት ነው ትለኛለህ? …ወያኔው እንዴት አደረጋችሁ በለኝ እንጂ? …”
አነጋገራቸው ያስቃል። ሁላችንም ሳቅን። ሳቄን ገታ አደረኩና.. “ወያኔው ምን አደረገ?.. እስቲ ያለውን ነገር ያጫውቱኝ…” አልኩ።
“ከየቱ ጋ እንደምጀምርልህ አላውቅም ልጄ….ያላየነው ታሪክ የለም …በነዚህ ሰዎች ዘመን ያየነው ጉድ ብዙ ነው።”
“ ምን ጉድ አለባቸው?”
“ደግ ጠይቀኸኛል ልጄ…ምን ጉድ አለባቸው አልከኝ? …. ይሔውልህ እኔ ያንተ እናት… ሶስቱንም መንግስት በልቻለሁ።.. አንድ ነገር ልንገርህ ..ጃንሆይን ክፉ …አድሀሪ ስትሉ.. ክፉ መንግስት ስትሉ …ደርግ መጣና ክፉ መንግስት ምን አይነት እንደሆነ አሳየን.. ደርግን ክፉ ስንል ስንጠላ..ስንጠላ..እነዚህ መጡና የባሰ ክፉ መኖሩን አሳዩን..” ድንገት አቁዋረጥኳቸውና…
“የነዚህ ክፋት ምንድንው?”
“ደግ ብለሀል ልጄ… የነዚህ ክፋት.. ደርግ ወንበሬን ቀና ብላችሁ አትዩ ብሎ ነበር ያን ሁሉ ሰው የፈጀው፤…አማራ አላለም፤… ትግሬ አላም። እስላም ክርስትያን አላለም። ደርጉ ይል የነበረው፤ አገራችሁን ጠብቁ፤ ተስማምታችሁ አንድ ሆናችሁ ኑሩ፤ ወንበሬን ግን ቀና ብላችሁ አትዩ…”
ፊቴን ትኩር ብለው እያዩ
“..ያኔ እናንተም በየከተማው ጦርነት ከፈታችሁበት..እሱም ጦርነት ከፈተ…ያሁሉ በልቶ ያልጠገበ ልጅ አለቀ። ቀድሞውንም ያኔ ወይ ጫካ ሂዳችሁ በተዋጋችሁት ደግ… ወይ አርፋችሁ በተቀመጣችሁ… ያንን ሁሉ የልጅ ሬሳ አናይም ነበር..በኢሀፓ ጊዜ…”
“..እነዚህ መጡ …ያገሬ ሰው ተረተ። … ‘ምንሽር ልገዛ ወይፈኔን  ሳስማማ፤መጣ የትግሬ ልጅ በነጠላ ጫማ’… ገና ሲመጡ ጀምሮ የወደዳቸውም የለ… እግዚአብሄር ያመጣውን ፍርጃ መቀበል እንጂ  የሚደረግ የለም… መጡልህና ወንበራችንንም ቀና ብላችሁ እንዳታዩ፤ ለራሳችሁም እንዳትትያዩ… በየዘራችሁ ተበታተኑ አሉ። ለሁሉም በየዘሩ ማህበር አበጀለትና ሁልህም በዚህ ቀንበር ውስጥ ትገባለህ..ግባ አለው።”
“ማን ነው ያለው?’’
“ሟቹ…”
“አልገባም ያለ፤ እነሱን የሞገተ፤ የጥይት እራት ይሆን ጀመር። አንድም ሰው ጠመንጃ አንስቶ የተኮሰባቸው የለም። በያለበት ሰው መግደል ሆነ ስራቸው። አንዱን ካንዱ ማባላት፤ አሉባልታ ውሸት በራዲዮን፤ በቴሌቭዥን ሲነዙ መዋል ሆነ። እንዲህ እንዲህ አድርገው ሰዉን ሁሉ አደናግረው ሲያበቁ፤ አስፈራርተው ሲያበቁ፤… የራሳቸውን ሰው ሁሉ  ቦታቦታውን አስያዙ። ዛሬ ያለነሱ ነጋዴ የለም። ያለ እነሱ የቢሮ አለቃ የለም። ያለነሱ የቀበሌ አለቃ የለም። ያለ እነሱ ፎሊስ የለም። ሰው ሁሉ ሀሞቱ ፈሶ እነሱን እየፈራ መኖር የዟል። ….ወንዱም ሴቱም….ታዲያ ልጄ ደርጉ እንደዚህ ባይተዋር አድርጎናል?” አሉና በንዴት እራሳቸውን እየነቀነቁ ጠየቁኝ።
“ልማቱስ እትየ?…አገሩን አልምተዋል ይባል የለ እንዴ?”
“ሀሰት!.. ሀሰት ልጄ!…አገር ቢለማ፤ አገሬው ሁሉ ከነልጁ ለልመና ጎዳና ላይ ይፈስ ነበር?…ልማቱንስ ቢሆን እነሱ እንጂ ሌላው ሰው የታለ?..የታለ ጉራጌ ባለፎቅ ?..የታለ አማራ?..የታለ ኦሮሞ?….ያ ፎቅ የማነው ስትል… እነሱ….ያፎቅ የማነው ስትል እነሱ…..ልጄ ከየት አመጡት ያሰኛል እኮ? እነሱና አላሙዲ እንጂ ሀብታም አለ እንዴ ዛሬ?..”
“ዛሬ አንድ ሺህ ብር ይዘህ ገበያ ወተህ….. አንዲት ዘንቢል ሞልተህ አትመለስም እኮ!…ልማት ማለት ድህነትና እራብ ነው እንዴ?… ጦሙን የሚያድረው ህዝብ ተቆጥሮ አያልቅም እኮ…. እዚችው አዲስ አበባ…..”
“…ጭራሽ ጥጋባቸው… ቤት ዘግተው፤ ዊስኪ አውርደው ሲጨፍሩ የሚያድሩ እነሱ… ጠግበው በሽጉጥ ሲታኮሱ የሚያድሩ እነሱ… መጠጥ ቤት የፈለጋቸውን ደብድበው አድምተው የሚሄዱ እነሱ….”
“…የኛ ሰፈር መደዳውን ቡና ቤት ነው።…አንድ ቀን ጠዋት ወደ ክፍለ ሀገር አውቶብስ ተራ ልሄድ አስር ሰአት ተነስቼ ታክሲ ስጠብቅ….አንዲቷን ድሀ ጸጉሩዋን ይዞ መሬት ለመሬት እየጎተተ በግንባሯ ያዳፋታል፤ ከቡና ቤት አውጥቶ አስፋልት ላይ ይረግጣታል።..ኡ ኡ እያለች…ገደለኝ እያለች…ሊገላግላት የመጣ ወንድ ጠፋ። ሰው ሁሉ ሰምቶ እንዳልሰማ እየሆነ ብቅ አላለም። በስካር መንፈስ እንኳ እነዚህን ሰዎች የሚደፍር ጠፋ? አልኩና እንባዬን እርግፍ አድርጌ አለቀስኩ። ልጄ ድሮ ሴት ልጅ ድረሱልኝ ብላ ስትጮህ እንዲህ  ነበር እንዴ?..”
“..ወዲያውኑ አንድ ታክሲ ሲበር መጣ… አስቆምኩና ገብቼ… እንዳው ልጄ ይህን ሰውየ እላዩ ላይ ንዳበት!…ንዳበት!…ገደላት እኮ…ንዳበት! አልኩት። ለካንስ ያም ባለታክሲ የነሱ ሰው ኖሯል…አንዳንድ ደግ መቸም አለ…ሽርርር አደረገና መኪናዋን እላዩ ላይ  አቁሞ፤ ወርዶ፤ እንደብራቅ ጮኸበት አልኩህ።ተጯጯሁ..ተጯጯሁ..ተሰዳደቡ፤ተሰዳደቡ..በግርግር እሷ እመር አለችልህና ደሟን እያዘራች ተነስታ አመለጠች…ያም ከባለታክሲው ጋር እየተሰዳደበ ወደ መሄጃየ አቀናን …”
“..ዛሬ አሁን የፈለገ ነገር ቢመጣ የአዲስ አበባ ሰው ቤት ለነሱ አያከራይም….”
“ለምን?” አልኩ።
“ለምን ማለት ደግ..ይኽውልህ ልጄ ቤት ታከራያቸው የለም?…ልቀቁ ስትል አይለቁም፤ …ወደየትም  ሄደህ ከሰህ አታስለቅቃቸውም።…አንዲቷ እንዳደረገችኝ ልንገርህ..”  አሉና ፎቴው ላይ እየተመቻቹ፤ የተደረበላቸውን ብርድ ልብስ ወደላይ እየሰበሰቡ፤ “… እግዚአብሄር ብድሩን ይክፈላቸውና ልጆቼ ቤት ሰሩልኝ ብየህ አልነበር?…”
ውድ አንባቢያን ወደጨዋታችን መጀመሪያ ላይ ልጆቻቸው ቤት እንደሰሩላቸው ነግረውኝ  ነበር። አምስት ልጆች አሏቸው። ሁሉም በየአለሙ ተበትነው ይገኛሉ። ኖርዌይ፤ ጀርመን፤ አሜሪካ፤ካናዳ..እና ሁሉም እንደየአቅሙ አዋቶ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ከየመኝታ ቤት ያላቸው ባለ አንድ ፎቅ ሰርተውላቸው ነበር። እሳቸው አሮጌው ቤት እየኖሩ ይህን ቤት አከራይተው በሚያገኙት ገቢ ስድስት የእህት የወንድም ልጅ ከገጠር አስመጥተው እያስተማሩ ያሳድጋሉ። እናም ልጆቻቸው እንደገና ገንዘብ እንስጥሽ ብለው እንዳይቸገሩ በማለት ለነሱ ያልነገሯቸው፤ ነገር ግን ከቤቱ ኪራይ ቆጥበው ምድር ቤት ባንዱ ክፍል ምግብና መጠጥ ሊነግዱ ሀሳብ አላቸው። ዛሬ ነገ እጀምራለሁ ሲሉ አንዱን ቤት አላከራዩትም ነበር። ኋላ ላይ ግን ለማከራየት ወሰኑ።
“…ቤት ሰሩልኝ ብየህ አልነበር?…ታዲያ ያችን አንዷን የቀረችውን ለአምስት ወርም ቢሆን ላከራይ አልኩልህና….አንዱ ደላላ አንዲቷን ወያኔ ሴት ይዞ መጣ። ቤቱ መንገድ ዳር ነው ለንግድ ይመቻል …አንባሻና ሻይ ቡና ልሸጥ ነው አለችኝ።…..አይ ልጄ እኔም እንዲህ፤ እንዲህ ላደርግ ሀሳብ አለኝ። …ባከራይሽም ለአምስት ለስድስት ወር ነው። ከፍተሽ የምትዘጊው ንግድ ምንም አያደርግልሽም። ሌላ ብትፈልጊ ይሻልሻል አልኳት።”
“…ሞቼ እገኛለሁ። ልቀቂ ባሉኝ ቀን እለቃለሁ። እንደው እትዬ..እትዬ..” አለች።
“ኮሎኔል ወንድም አላት አሉ። እሱ ነው ካገሯ ያስመጣት። ላገሩም እንግዳ ነች። አይ እንግዲህ እለቃለሁ ካለች ትግባ ብየ በሰው ፊት ተዋውለን ገባች።”
“እርግጥ ጎበዝ ሴት ናት። የኛ ሰፈር አላፊ  አግዳሚው ይበዛል። በጠዋት ተነስታ ቄጠማውን ጎዝጉዛ፤ አጫጭሳ፤ ቡናውን አቀራርባ፤ ሞቅ ሞቅ ስታደርገው፤  መንገደኛው ሁሉ ቁርሱን በልቶ ቡናውን ጠጥቶላት ወደየስራው ይሰማራል።”
“..እንዲህ እንዲህ እያለ ያች አምስት ወር ደረሰች። አይ ይች ሰው አሁን እንዲህ ገበያው ደርቶላት ልቀቂ ብላት ትቀየመኝ ይሆን? አልኩልህና እኔው ተጨንቄ አረፍኩት። …እሷም ቤት ልፈልግ አላለች፤ እኔም ትንሽ ትቋቋም ብየ ሶስት ወር ጨመርኩላት። ከዚያ በኋላ ደሞ ሶስት ወር አስቀድሜ ቤት እንድትፈልግ ነገርኳት። እሺ አለች። ወር አለፈ። ሁለተኛውም አለፈ። ሶስተኛው ተገባደደ። እየፈለኩ ነው ትላለች። ወሩ አለቀ። ቤቴን መልቀቅ የፈለገች አትመስልም። …በይ እንግዲህ ካጣሽ እኔው እፈልግልሻለሁ አልኩና ከኔ ቤት ወረድ ብሎ ሌላ አገኘሁላትና በይ በዚህ ወር  መጨረሻ ላይ ቤቱን እፈልገዋለሁ አልኳት። ወሩ ሲሞላ ደህና የነበረችው ሴትዮ ድንገት ተለዋወጠችብኝና አልወጣም ሂጂ ክሰሽ አትለኝ መሰለህ?…አበስኩ ገበርኩ…አልኩና ያዋዋሉንን ሰዎች ጠራሁና ይችን ሽፍታ ገላግሉኝ አልኩ። ጭቅጭቋን ቀጠለች። አንድ አስራ አምስት ቀን ስታምሰን ከረመች አልኩህ…በኋላ አንድ ቀን ጠዋት ወደዚሁ ቤት ስመጣ ሌሊት እቃ ታግዝ ነበር ሲሉኝ አምላክ በሰላም ሊገላግለኝ ነው አልኩና ገብቼ ቤቴን አየዋለሁ….ልጄ አፍርሳዋለች አልኩህ…ግርግዳውን ሁሉ ቧጣ፤ቧጣ ቧጣ…..እንደው ልጄ በምን ይሆን ስትቧጥጠው ያደረችው?…ሸንትራ፤ሸንትራ፤ ግርግዳውን ልጅ ያረሰው መጫወቻ ደጅ አስመስላዋለች። ሽንት ቤቱን ሰባብራ አግማምታ፤ አበስብሳው፤ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ሳትከፍለኝ ኮተቷን ሰብስባ ውልቅ አለች። ክሰሻት አሉኝ። ማን ላይ ነው የምከሳት?…ጭራሽ አሸባሪ ትብየ እኔው ልታሰር?…”
የእናታችን ጨዋታ ፈርጀ ብዙ ነበር። አንዱን ጨርሰው ወደ ሌላው ሲያልፉ አንደበተ ርቱእነታቸውና ለዛቸው አፍ ያስከፍታል።
“..አንድ ጉድ ደሞ ላጫውትህ….ስራ አጥተው ችግርርርር ያላቸው አስር የሚሆኑ የሰፈራችን ወጣቶች ተሰበሰቡልህና ስራ ፈጠሩ። ምንድነው ስራው ብትለኝ…ሆቴል ቤቶች ሞልተዋል ብየሀለሁ ሰፈራችን….ከባለቤቶቹ ጋር ይነጋገሩልህና  በቀን ሶስት ጊዜ ቆሻሻ መድፋት፤ በቀን አንድ ጊዜ ግቢ መጥረግ፤ ይህን ለመስራት ተዋውለው ….ባለ ሆቴሎቹም ሁሉ ደስ ብሏቸው….ሲሰሩ የሚለብሱት ልብስም ገዝተውላቸው…ጋሪም ገዝተውላቸው ስራ ጀመሩ። የሰፈሩ ሰው ሁሉ ደስ አለው። ልጆቹ ገንዘብ አገኙ፤ እናትና አባታቸውን ማልበስ ለራሳቸውም ደህናደህና ነገር መልበስ ጀመሩ። ስራቸውንም እያስፋፉ በቁጥር አስራ አምስት ደርሰው፤ በሰላም ተረጋግተው በመስራት ላይ እንዳሉ፤ ህገ ወጥ ስራ ነው የምትሰሩት አቁሙ ይላቸዋል አንዱ…”
“ማን? “
“እዚያው ቀበሌ ውስጥ ….የምንትስ ሀላፊ ነው ያሉት ትግሬ…”
“ለምን አስቆማቸው?”
“ስራውን ቀበሌው ሊሰራው በእቅድ የያዘው ስለሆነ በቀበሌ ታቅፋችሁ ነው መስራት ያለባችሁ። ቀበሌ ለናንተ ይከፍላል። ግብር ለመንግስት መክፈል አለባችሁ፤ ፍቃድ ያስፈልጋችኋል….አለና አስቆማቸው። ልጆቹም ለምንድነው እኛ የፈጠርነውን ስራ የምንከለከለው ብለው ሲጨቃጨቁ ሁለቱን አስረው፤ የቀሩትን አስፈራርተው በተኗቸው።”
“…ትንሽ ቆየት ይሉልህና… ልጆቹን አደናግረው አስፈራርተው ከበተኗቸው በኋላ ያንኑ ስራ በቀበሌው የማይኖሩ የራሳቸውን ወጣቶች ሰብስበው ….”
“የራሳቸውን ወጣቶች ማለት?” አቋርጨ ጠየኩ።
“ትግሬዎቹን… ሰበሰቡና ከመጀመሪዎቹ ሁለቱን ቀላቅልው ስሩ አሏቸው …እነዚያ ሁለቱ ደሞ ጓደኞቻችን ተባረው እኛ አንሰራም ብለው ትተውላቸው ሄዱ። ባለሆቴሎቹ ቀድሞ የሚያስጠርጉትን ልጆች ሲያጡ፤ ምንድነው  ነገሩ ብለው ቢያጠያይቁ፤ የመጀመሪያዎቹ ልጆች የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው። ባለሆቴሎቹም አደሙ ። ቆሻሻችንን እኛው እንደፋለን እንጂ አናስጠርግም አሉ። የተተኩትን ልጆች ስራ የለንም እያሉ መለሷቸው። ”
“ያ አለቃ ተብየው ቀበሌ ሰዉን ሰብስቦ አሉ… ጸረ ልማት ሀይሎች እያለ ሲሳደብ ከረመ አሉ። ባለ ሆቴሎቹም እንዳደሙ ቀሩ። ሗላ ላይ ሥሰማ በመጀመሪያ ያጸዱላቸው የነበሩትን ልጆች ሁሉንም ተከፋፍለው ቀጠሯቸው አሉ። እነዚያም ጋሪያቸውንና ጓዛቸውን ይዘው ወዴት እንደሄዱ አላውቅም እልሀለሁ …..ልጄ..ወያኔ እንዲህ እያመሰን ነው እልሀለሁ…..” እንደ መተከዝ አይኖቻቸውን ወለሉ ላይ ተክለው ለአፍታ ዝምም አሉ።
ውድ አንባቢያን የህብረተሰብ ደህንነት የሚረጋገጠው፤ እያንዳንዱ ክፍለ ህዝብ ከህዳጣን እስከ ብዙሀን ምልአተ ህዝቡን የገነቡ ብሄረሰቦች ሁሉ እኩል መብትና ነጻነት ሲኖራቸው፤ በሀገራቸው እኩል የባለቤትነት ስሜት ሲኖራቸው፤አንባ ገነንም ይሁን ዲሞክራሲያዊ ..ያለውን መንግስት የኛ ነው ሲሉት፤ በባህላቸው፤ በቋንቋቸው፤ በሀይማኖታቸው፤ የተነሳ ምንም አይነት መገፋት እንደሌለ ሲያረጋግጡ ዜጎች ደህንነት ይሰማቸዋል።
የናታችንን ጨዋታ ለማጫር ይችን ጥያቄ ጣል አደረኩ።
“ወያኔ..ወያኔ ይባላል… ኢህአደግ ነው መባል ያለበት… አይደለም እትየ?”
ከት አሉና ሳቁ ። ሳቃቸው አስቆን ሁላችንም ፍንድት አለን።
“አየህ ልጄ…በቆሎ እሸት ታውቃለህ አይደል?..በቆሎ እሸት..” አሉ እጃቸውን ቀና ቀጥ አድርገው፤ “..በቆሎ እሸት የምትሸለቅቀው ልባሱ አለ። ያ ልባሱ ገለባ ነው። ይጣላል። ዋናው በቆሎው ነው። ፍሬው። እነዚህ ኢህአደግ  ያልካቸው ገለባ ናቸው (ሶስቱን የወያኔ ፍጡራን ድርጅቶች ማለታቸው ነው፡ ኦህዴድ፤ ብአዴን….) ዋናዎቹ ትግሬዎቹ ናቸው። ገባህ ልጄ…”
በአዎንታ ራሴን ነቀነኩ።
“..የአማራው ነን፤ የኦሮሞው ነን፤ ማነው ይሄ ደሞ የበየነ ጴጥሮስ አገር…ብቻ ሁሉም ከነሱ ጋር ያሉት ገለባዎቹ አሽከሮቻቸው ናቸው። ማፈሪያዎች ናቸው፤…..እንዳይመስልህ ልጄ…ጌቶቹ ትግሬዎቹ ናቸው፤….የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም እነዚህ ኢህአደግ ያልካቸው ከምንም አያስጥሉንም……”
ውድ አንባቢያን ያለፈ አንድ አመት አካባቢ አንዲት ሌላ እናት እንዲሁ መተው ለመጠየቅ ሄጄ ዘጠና በመቶ ማለት ይቻላል ተመሳሳይ አይነት ጨዋታ አጫውተውኝ ነበር። ካንድ ሰው ብቻ የተገኘ ኢንፎርሜሽን ለሌላው ማስተላለፍ ያስቸግራል፡፡ ሁለት ይማይተዋወቁ ሰዎች፤ የተለያየ አካባቢ የሚኖሩ፤ በተለያየ ጊዜ አንድ አይነት ነገር ከተናገሩ እውነትነት ያለው ጉዳይ አለ ማለት ነው።
ይህ ስርአት መለወጥ እንዳለበት ዜጎች ይስማማሉ። ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚታሰብ ነገር አልሆነም።  እንዴት ነው እነዚህን ሰዎች ከስልጣን የምናስወግደው ነው ጥያቄው፤ መላ መምታት የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታና ፈንታ ነው። እናታችንን ጠይቄአቸው ነበር።
“ይህንን መንግስት ለመለወጥ ምን ቢደረግ የሚበጅ ይመስሎታል እትየ?”
“መተኮስ….መተኮስ ነዋ!…እነሱ ተኩሰው አይደል ለዚህ የበቁት?…..ግን እኮ ልጄ… ወንዱ ሁሉ ሀሞቱ ፈሰሰ…በጥቁር አህያ ነው አሉ ያስደገሙብን…የሱዳን መተት ቀላል እንዳይመስልህ ልጄ…ሱዳን አልነበረ የሚኖሩት…ያኔ አሉ…. ሲገቡ፤ ሕዝቡ ሁሉ እንዲፈዝላቸው……ወንዱ ሁሉ ወኔው እንዲሰለብ…. በጥቁር አህያ አድርገው አስደግመው ገቡ አሉ። ይኸው ሀያሁለት አመት….አገር መሬቱን ሲሸጡ፤ እስላም ክርስቲያኑን ሲያምሱ፤ ሲገሉ ….ቤት ሲያፈርሱ.. ንብረት ሲቀሙ…ማን ወንድ ሸፍቶ አስደነገጣቸው?…..ሀያ ሁለት አመት…ሀያ ሁለት ዓመት… መተኮስ … መተኮስ ነው ልጄ…”  lkebede10@gmail.com

ለዚች አገር የሚገባት እውን ይሄ ነውን !!!!!

yared elias
(nome telemark dagsrud)
ዘረኛው ወያኔ አገዛዝ መንግስት ስልጣን ከያዘበት ግዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ድረስ እየሰራ ያለው ነገር በውነት ከሌላ አገር  ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለመያዝ የመጡ ሰዎች እንጂ እውነት ኢትዮጵያኖች ናቸው ለማለት እያጠራጠረ መጥቷል።
ሃገራችን ኢትዮጵያ አውን በምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል የፖለቲካው ነጸብራቅ መሆኑን ማንም ሊመሰክር ይችላል ለዚሁም አንዱ ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ከሁለት ዓመት በፊት ጋሎፕ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት መሰረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለኑሮ የማይመርጧት ሃገር እንደሆነች ተዘግቧል። ጥናቱ እንዳመለከተው ከሆነ እድሉን ካገኙ፣46 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደውጭ የመውጣት ፍላጎት አላቸው ።ያው ይሄን ያደረገው ?
ይገርማል ግን! ኢትዮጵያዊያንን ከአገራቸው ያውም ወደ አረብ አገራት ያለምንም ማስተማመኛ በዓመት 500 000 ያውም ሳውዲ ዓረቢያ ብቻ  ዲፖርት ያደርጋሉ ያው ዲፖርት ማለት አደለምን ። ከዛማ ስለነሱ ማን ይጠይቃል እንዲህ እያለ የወያኔ ጠባብ ብሄርተኛ ዘረኛው ፓርቲ ለተከታታይ ዓመታት ባለሁለት አሀዝ ኢኮኖሚዊ ዕድገት እንደተመዘገበ፣ ድህነት በገጠርና በከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸነፈ መምጣቱን እየነገረን ይገኛል፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመጨረሻ የትግበራ ዓመት ከድህነት በታች የሚገኙ ዜጎች 22 በመቶ ብቻ እንደሚሆን ተነግሮናል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ በሆኑ ችግሮች ውስጥ ተተብትባ ትገኛለች፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያራምዳቸው ጠርዝ የያዙና ስልጣንን ከሀገር ጥቅም በፊት የሚያስቀድሙ አመለካከቶችና አሰራሮች ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡ አገዛዙ የሚከተላችው ጥራዝ ነጠቅና የዜጎችን ጥቅም ያላማከለ አካሄድ ሀገርን እየጎዳ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ፖሊሲዎች አንዱ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ዘላቂ የሀገርን ጥቅም ባላገናዘበ  መልኩ ለባዕዳን የመስጠት ጉዳይ ነው፡፡መንግስት ራሱ ባቀረበው መረጃ መሠረት ከ380 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች  መሰጠቱን ተገልጿዋል፡፡ የአዲስ አባባን 54 ሺ ሄክታር የቆዳ ስፋት በግምት ውስጥ ስናስገባ፣ ኢህአዴግ  ለውጭ ባለሃብቶች የሰጠው መሬት የመዲናችንን ሰባት እጥፍ በላይ ነው፡፡ መንግስት የፊሊፒንስን ቆዳ  ስፋት የሚያክል መሬት (3 ሚሊየን ሄክታር) ለውጭ ባለሃብቶች ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን  እንደገለፀ ይታወቃል፡፡  በጋንቤላ ክልል ብቻ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለሰፋፊ እርሻ እንደተዘጋጀ መንግስት ገልጸዋል፡፡ ይህ ማለት ከጋንቤላ አጠቃላይ ስፋት 37 በመቶ በላይ መሬት በእርሻ ኢንቨስትመንት ስም ለውጭ ባለሃቶች  ለመስጠት ኢህአዴግ እየሰራ ነው፡፡ ለዚሁ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ ኢህአዴግ በጋንቤላ ሰፊ የሰፈራ ፕሮግራም
 እያካሄደ ይገኛል።
ይቀጥልና ዘረኛው ወያኔ መንግስት ይሄ አስመሳይ በሃሪውን ቀየሮ ለስልጣን መቆያ ይሆነው ዘንድ በሃይማኖት በኩል ዞሮ መጥቶ በተለይ በመላው ኢትዮጵያ መስኪዶች ስፍር ቁጥር የሌለው ህዝብ በአይነቱ የተለየ እና ግዙፍ ተቃውሞ ያደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብም ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ እንግልት በሃይማኖቱ ላይ የሚያደርገውን ግልጽ ጣልቃ ገብነትና እንዲሁም የህዝብ ሙስሊሙ ተወካዮች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን ንቀት የተሞላበት ከፍተኛ ስቃይ እና አምባገነናዊ ተግባር እረ እስከ መቼ ነው የሚጠበቀው ? ምንስ ነው ዝም ያስባለው ብዬ ሳስብ በአንድ ወቅት  አንድ ተናጋሪ ባደረጉት ንግግር ላይ የተናገሩት ነገር ትዝ አለኝ ለካስ ትክክል ነበር ለማለት ወደድኩ  " አገር ቤት ውስጥ ያለው ህዝብ ሁሉንም ነገር ሰለለመደው ለሱ አዲስ ነገር አደለም  የነጻነትን ትንፋሽ የሚባለውን አያውቅም ምክንያቱም አንድ ትልቅ ነገር ሲነሳ ለዛ ለተነሳው ነገር አንድ ሳምንት ሆይ ሆይ ይልና ወዲያው ይለምደዋል" ሌላም እንድህዚሁ አይነት ሲገጥም ለአንድ ወር ያህል ሰው ያለቅሳል ያዝናል ወዲያውም ይለምደዋል ስለዚህ ምንም አይነት ነገር ይፈጠር ነጻነት የምትባለዋን ነገር እንዳለችው ባለችው ነገር ላይ ተላምዶዋት ቍጭ ብሏል ነገር ግን የነጻነት ትንፋሽን የሚያውቀው ያው ወደውጭ አገር ወጥቶ የነጻነትን ትንፋሽ አጣጥሞ ወደ አገር ቤት የሚገባው ሰው ብቻ ነው እንደገባም የህዝቡ የነጻነት ትንፋሹ በትንሽና ጠባብ ብሄርተኛ ዘረኛ ወረኛ መንግስት ታግቶ ሲያይ ምንኛ እንደሚያሳዝን ያሳያል ።
ይህው እንዳየነው ሙስሊሙ ህብረተሰብ በቤታቸው እንኳን ቍጭ ማለት እንዳልቻሉ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ይገኛሉ በአንድ ቴሌቪዠን ለ80_90 ሚልዮን ህዝብ ማስፈራሪያ ይነገረዋል አልፎ ተርፎ የ 1000 አመት ታሪክ ያላቸውን እነዛ ተከባብረው የሚኖሩ አጥር ብቻ የሚለያቸው ሁለቱ ወንድማማቾቹን ሙስሊምና ክርስትያኑን ሊያባሉ ስንት ይዘይዳሉ ። ለነገሩ ነው እንጂ ማን ይሰማቸዋል። ንጹህ የነጻነት ትንፋሽ እንዲተነፍስ እናድርገው ።
እግዚሃብሄር  ኢትዮጵያ ይባርክ!!



Mar 6, 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ

የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።Gambella
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።
አቶ ኡሞት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትም አላቸው። ኢህአዴግ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ አጥብቀው በግልጽ የሚቃወሙ ሰው መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አቶ ኡሞት ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህዝብን የሚያስተባብሩና ለዓመጽ የሚያነሳሱ ናቸው በሚል ኢህአዴግ ቢወነጅላቸውም ውንጀላውን በማስረጃ ማቅረብ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ። ስለተፈጸመው ግፍ የተሞላበት ግድያና ከግድያው በኋላ ስለተከናወነው “አረመኔያዊ የእንስሳ ተግባር” ሲያስረዱ በቁጣ ነው።
በተጠቀሰው ቀን ቤተሰቦቻቸውን ቀበሌያቸው ድረስ በመሄድ በመግረፍና በማስፈራራት ወደ አብሌን ለከበባ በጠቋሚ የመጡት የመከላከያ አባላት ሰዎቹን እንደተመለከቱ ተኩስ ከፈቱ። በድንገት የተከበቡትና ዛፍ ሥር ተቀምጠው የነበሩት አንዳችም ጥያቄ ሳይቀርብላቸው በጥይት የተደበደቡት ሰዎች የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ቢያደርጉም አልሆነም። ተደራጅቶ በሶስት የወታደር ካሚዮን ከባድ መሳሪያ ታጥቆ የመጣው ሰራዊት ጨፈጨፋቸው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደተናገሩት ወዲያው ህይወታቸው ካለፈው ስድስት ንጹሃን መካከል አቶ ኡሞት መሞታቸው ሲታወቅ የሰራዊቱ አባላት አውካኩ፤ በደስታ ጨፈሩ። አስከሬኑንን ጭነው ፉኙዶ ወደሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በመሄድ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ደስታቸውን አበሰሩ።
አስከሬን በመኪና በመጫን ከተማ እየዞሩ ደስታቸውን ገለጹ። በማግስቱ በጋምቤላ ከተማ ስታዲየም አስከሬኑን ህዝብ እንዲመለከተው ታዘዘ። ህዝብ ስታዲየም ተገኝቶ የአቶ ኡሞትን አስከሬን እንዲሳለም፣ ኢንቨስተሮችም ያለስጋት የመሬት ነጠቃቸውንና “ልማታቸውን እንዲቀጥሉ”፣ መሞታቸውን አይቶ ሕዝቡ እንዲያምንና ሞራሉ እንዲጎዳ የተላለፈው ውሳኔ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስተጓጎለ። ለጎልጉል መረጃውን ያስተላለፉ እንዳሉት አቶ ኡሞት አሜሪካዊ መሆናቸው ሲታወቅ ማዕከላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ አስቸኳይ ትዕዛዝ አስተላለፈ። አስከሬኑን ባስቸኳይ እንዲቀብሩ መመሪያ ሰጡ። ሁሉም ነገር በመመሪያው መሰረት ተጠናቀቀ። የአቶ ኡሞት አስከሬን ባልታወቀ ቦታ ተቀበረ። አስከሬኑንን ለማየት በግዳጅ ተሰባሰበው ህዝብም ምንም ነገር ሳይመለከት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ሁኔታውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት የኢህአዴግ ሠራዊት በጎክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች በተለይም ወንዶችን እያሠሩና እያሰቃዩ እንደሆነ ከሥፍራው የደረሰን ዜና ያረጋግጣል፡፡
የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት ጉዳዩን ለአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀና የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን ከስር መሰረቱ ጀምሮ እንደሚመረምረውና እስከ መጨረሻው የመንግሥት አካል እንደሚደርሱ ማረጋገጡ ታውቋል። ኢህአዴግ አቶ ኡሞትን የገደለበትን ምክንያት በማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅበትም አስታውቀዋል። አቶ ኡሞት የሚጠረጠሩበት ድርጊት እንኳን ቢኖር በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ መጠየቅ እየተቻለ እንዲገደሉ መደረጋቸው ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ የሚከራከሩላቸውና ጉዳያቸውን ይፋ ያደረጉት ክፍሎች ይናገራሉ።
በወቅቱ ህይወታቸው ያለፈው ንጹሃንና የደረሱበት ያልታወቀው ሰዎች ስም ዝርዝር ከስፍራው የደረሰን ሲሆን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
  1. ጎጎ ኦቻላ
  2. ቻም ኦቻላ
  3. ዑከች አቻው
  4. አኳይ ኦሞት
  5. ኦሞት ኦባንግ
  6. አጂባ አኳይ
  7. ኦሞት ኡጁሉ ኦጎታ
  8. አንበሳው ኡጁሉ
  9. ቱወል ኦሎክ
  10. ኦችዋል ኦባንግ
  11. ኦዋር ቻም
  12. ኒሙሉ አጎሌ
  13. አብራች ኒሙሉ
  14. አኩኔ ኦሞት
  15. አግዋ ቻም
  16. ኦዋር ኒግዎ አጋክ
  17. ኦሞት ኡዶል (አሜሪካዊው)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውሳኔ ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው ተባለ


በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ 10 የኦሮሞ ተወላጆች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ መደረጋቸውን የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ሊግ አጥብቆ ያወገዘው ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ውሳኔም ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው ብሎታል።
የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከትምርታቸው የታገዱትን ተማሪዎች ፎቶ አስደግፎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገዱት የመጀመሪያ ሴሚስተር ፈተናቸውን አጠናቅቀው የሁለት ሳምንት እረፍት ወስደው ከተመለሱ በሁዋላ ነው ብሏል።
ሊጉ ከውስጥ የደረሱትን መረጃዎች ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው ይህ በግልጽ ፖለቲካዊ የሆነውና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረው ውሳኔ የተላለፈው “ዲሲፕሊን ኮሚቴ” ተብሎ በሚጠራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አካል ሲሆን፤ኮሚቴው ለዚህ ውሳኔ ምክንያት የሆነውም ባለፈው ጥር ወር በኦሮሞና በትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ነው።
በሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች መካከል ግጭቱ ሊፈጠር የቻለውም ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የኦሮሞ ብሄረሰብን አስመልክቶ ተገቢ ያልሆነና ቆስቋሽ ጽሁፍ ጽፈው በመለጠፋቸው ምክንያት እንደሆነ ማረጋገጡን ሊጉ አውስቷል።
ይህን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ በግጭቱ ሳቢያ ከ10 በሚበልጡ ተማሪዎች ላይ የ እስራት፣የግርፋትና የድብደባ እርምጃ መወሰዱን፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የ ኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ ይፋ ማድረጉንም ሊጉ አስታውሷል።
በግጭቱ ምክንያት ከትምህርታቸው እንዲታገዱ የተደረጉት አስሩም ተማሪዎች ኦሮሞዎች መሆናቸውን እና ከመካከላቸው አንዷ ሴት መሆኗን ያመለከተው ሊጉ፤ ሁሉም ለአንድ ወር ያህል ታስረው በዋስ ከተለቀቁ በሁዋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው እንደነበር ጠቅሷል።
ከትምህርታቸው የታገዱት የኦሮሞ ተማሪዎች ከወለጋ ነቀምት የመጣው የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ታደለ ታረቀኝ፣ ከደቡብ ሸዋ ኦሮሚያ የመጣው የ3ኛ ዓመት ተማሪ አበጀ ቱጂ ጫላ፣ የ4ኛ ዓመቱ ተማሪ ገመቹ ደለቶ ዳፎ፣ የ 4ኛ ዓመት ተማሪ መልካሙ ሙሉጌታ፣ የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ፈቃዱ መሰራ፣ የ4ኛ ዓመቷ ሴት ተማሪ አዲስ ጋቴራ ያደሳ፣የ 4ኛ ዓመቱ ተማሪ በቃሉ ስዩም ተሻለ፣ የ3ኛ ዓመቱ ተማሪ ቀጀላ አድማሱ ደሬሳ፣የ 2ኛ ኣመት ተማሪው ኢሳያስ ኢታና እና የ 4ኛ ዓመት ተማሪው አራርሳ ዋቅቶላ ኦልጅራ መሆናቸው ይታወሳል።
ግጭቱን ከቀሰቀሱትም ሆነ በግጭቱ ከተሳተፉት የትግራይ ተወላጆች አንድም ተማሪ ላይ እርምጃ አለመወሰዱ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተብየውን ውሳኔ በግልጽ ፖለቲካዊና ዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ያሳያል ሲል የሰብዓዊ መብት ሊጉ አመልክቷል።
ይህ ውሳኔ ከሰብዓዊ መብት ሊጉ ባሻገር ብዙዎችን ያስገረመ እና ጥቂት በማይባሉም ታዛቢዎች ዘንድ፦ “በ እርግጥም ይህች አገር የማናት?” የሚልን ጥያቄ ያጫረ ሆኗል።

Mar 3, 2013

ተጋዳላይ ማትያስ ሹመት ያዳብር!

click here for pdf
እንዳይነቀሳቀስ አጁን በስንሰለት ጠፍረህ አሰረኸው፡
ሽጉጥክን ደግነህ ተናዘዝ ብትለው፡
በእምነቴ አትምጣ ከፈለክ ያውልህ ደረቴን ለጥይት፡
ከቶ አልበገርም በባዶ ድራማ አድማጭ የለሽ ተረት፡
ሞቴን ከነምነቴ ብሎ በመጽናቱ ግራ የተጋባህ፡
ደንባራ ወያኔ ፊልም መቆራረጥ መቀጣጠል ገባህ፡፡
አንተ አቡ በከር አንድ ጎኔን ሞቀው በጣም አኮራኸኝ ፡
አኩል አልሞቅ አለኝ አንዱ ጎኔ ሳስቶ ክፉኛ በረደኝ ።
እንኳንስ ተከታይ፤ አስተማሪው ካህን መነኩሴው ጳጳሱ፡
ለምነት አልቆም አለ አሳሳችው ነፍሱ።
ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሆኗ ቀረና የእምነት ማህደር፡
ታጋይ ተፈራርቆ ይሾምባት ጀመር።
የሃይማኖት መሪ በግዜር ይመረጣል ተብይ አድጌ፡
አገር በጾም ጸሎት ትጸናለች ሲባል ተምሬ አድጌ፤
ታጋይ ጳጳስ ሲሆን ስተቱ የማን ነው? መልስ አጣሁ ፈልጌ።
በመርዝ በጥይት ወገኑን ጨርሶ የመጣ ሹመኛ ደብሩን ቢረከበው፡
እግዜር የሾመው ነው በሚል አጉል ባህል መስቀል ልሳለም ነው?
ወይስ
አንተ እርኩስ መንፈስ ተጣልቼሃለሁ፡
መስቀልህ ይቅርብኝ ቤቴ ጸልያለሁ፡
ገንዘቤም በኪሴ ለምን ጦርሃለሁ፡
ብዬ ላሳርፈው?
ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የምትሆነው ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው የሃይማኖት መሪ ሲኖራት እንጂ የፖለቲካ ስልጣን በተቆጣጠሩ ባለስልጣናት የሚሾም ካድሬ ቁጥጥር ስር ሆና አደለም ፡ ስለዚህ ለተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ ማስተላለፍ የምፈልገው ምልእክት፡ ስርዓት እሰኪከበር ድረስ ጸሎታችሁን በቤታችሁ ገንዘባችሁን በኪሳችሁ እንድታረጉት እንዲሆን ነው፡ በገዛ ገንዘባችሁ ወያኔን የምታዳብሩበት ምክንያት አይኖርም፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት

Feb 28, 2013

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ

“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ
ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ
ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው
ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት
የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር …
በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው
የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል
የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች
እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው
ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም።
ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል
ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል
በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት
ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።
በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር
ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ
የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ
እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ “እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል” የሚለው የሁሉም ወገን “ዳር ቋሚዎች” ጥያቄ ነው።
“ለጆሮ የሚሰለች ነው፣ እርዳታ መስጠት ታከተን፣ የሚል መልስ የሚሰጡ አጋጥመውኛል። ድርጊቱ ተደጋግሞ ለጆሮ የሚያሰለች
ደረጃ እስኪደርስ እነዚህ ወገኖች የት ነበሩ? ቢያንስ ሌሎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ምን ሰሩ? በውጪ አገር ያለን ወገኖች
የሚረዳውንና የማይረዳውን መለየት የተሳነን ይመስለኛል” በማለት በሚኔሶታ የሚኖሩት ወ/ሮ ሰብለ አስተያየታቸውንና
ተማጽኗቸውን ያሰማሉ።
የካቲት 3፤2005 (2/10/2013) የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ ያሰማው እረፍት የሚነሳ ዜና እስካሁን አልተቋጨም። ሱዳን ሸገራብ
በሚባለው ሰፊ የስደተኞች ጣቢያ ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ጥር 22 ቀን 2005 ዓም ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ከቤታቸው ይወጣሉ። በካምፕ ውስጥ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው በግምት ሰላሳ ሜትር ሳይርቁ
ታፈኑ።
ባለቤታቸው አቶ መልካሙ ባዬ ለቪኦኤ እንደተናገሩት አፋኞቹ ራሻይዳዎች ናቸው። ራሻይዳ የቆዳቸው ቀለም ጠየም ያለ የሱዳን፣

የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ቀደም ሲል ከሶስት እስከ አራት ሺህ ዶላር እየተቀበሉ በደላላ አማካይነት ስደተኞችን
በሲና በረሃ ወደ ግብጽ ያሻግሩ ነበር። እስራኤል በሲና በረሃ ወደ ድንበሯን ዘልቀው የሚገቡበትን የስውር መንገድ ስትዘጋው
ራሻይዳዎቹ የገቢ ምንጫቸው ተዘጋ። ገንዘብ የለመዱት ወንበዴዎች የንግዱ ስልት ቀየሩና ሰው ማፈን ጀመሩ። አፈናውንም
ከሚያካሂዱባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ድንበር አቋርጠው የሚጓዙትን አድፍጠው በመያዝ፣ ስደተኞችን ከስደተኛ ካምፕ አፍኖ
በመውሰድ፣ ከሌሎች አፋኞች ስደተኞችን በአነስተኛ ገንዘብ በመግዛት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት ሜሮን እስጢፋኖስ
ይናገራሉ፡፡
ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ይህንን ዜና ሲሰሙ ደነገጡ። ዜናውን ካሰራጨው የቪኦኤ ዝግጅት ክፍል አድራሻ በመጠየቅ አቶ መልካሙን
አገኟቸው። አቶ መልካሙ በቃለምላልሳቸው ወቅት እንደተናገሩት ሁሉ ለወ/ሮ ሰብለ የደረሰባቸውን ሁሉ አጫወቱ። ወ/ሮ ሰብለ
“የሰማሁት ሁሉ እረፍት ነሳኝ። የማውቃቸውን ሰዎች ማስቸገር ጀመርኩ። ጊዚያዊ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመርኩ። ህይወት ለማትረፍ እየጣርኩ ነው” ሲሉ ጥሪ ያካተተ አስተያየት ሰነዘሩ።
ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው። አፋኞቹ 35 ሺህ ዶላር ካልቀረበላቸው የሰውነት አካል ክፍል ለሚዘርፉት
አራጆች ያስረክቧቸዋል። እዚያ ከደረሱ ድርድር የለም። የሰውነት ክፍላቸው የበለጠ ዋጋ ስለሚያወጣ ሌሎች ወገኖች ላይ
እንደተፈጸመው እርሳቸውም ላይ ይከናወናል።
የ12 እና የ 1 ዓመት ከስምንት ወር ልጅ ያላቸው ወ/ሮ ትዕግስት ባለቤታቸውን በስልክ እንዲያነጋግሩ ይደረጋሉ። ባለቤታቸውም
ይሰቃያሉ። እግራቸውና እግራቸው መካከል ብረት ተደርጎባቸዋል። ይደበደባሉ። ይህ ሁሉ የሚደረገው ባለቤታቸው የተጠየቁትን
ገንዘብ ባስቸኳይ እንዲከፍሉላቸው ለማስጨነቅ ነው። ባለቤታቸው እንደተናገሩት “ምንም አማራጭ የለኝም። የተጠየቀውን ገንዘብ
ማግኘት አልችልም። ልጆቼ ወደፊት ሲጠይቁኝ ለምኜ አቃተኝ ለማለት እየለመንኩ ነው። ባለቤቴ ግን ምንም ማድረግ
እንደማልችል ታውቃለች፤ … ” ብለዋል።
የ 12 ዓመቷ ልጃቸው ሱፊ “እኛንም እንዳይወስዱን ስለምንፈራ ከቤት አንወጣም” በማለት ልብ የሚነካ መልስ ከቪኦኤ ለቀረበላት
ጥያቄ መልስ ሰጥታለች፡፡ “እናቴን አፈኗት” ያለችው ህጻን የበርካታዎችን ልብ እረፍት ነስታለች። ወ/ሮ ሰብለ “እንደዚህ አይነት
አሳዛኝ ሲቃ ተሞላበት ጉዳይ እየሰማን በውጪ ያለን ወገኖች እንዴት 30 ሺህ ዶላር ማዋጣት አቃተን” ሲሉ ይጠይቃሉ። ወ/ሮ
ትዕግስት ጸሃይ ቢተርፉ ለሌሎች በማስተማር ተመሳሳይ ችግር በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እንዳይደርስ የማድረግ ስራ ይሰራል የሚል
እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
በሰብአዊ ተግባርም ሆነ በየትኛውም ዓይነት ማህበር ተመሳሳይ ስራ ተሳትፎ እንደሌላቸው ያስታወቁት ወ/ሮ ገነት፣ ይህን ጉዳይ
የሳቸውን ልብና አእምሮ ዕረፍት ነስቶት ለዚህ ተግባር ራሳቸውን እንደሰጡ ሁሉ፣ ሌሎችም ይህንን ልብ ሰባሪ አደጋ ሌሎች
ወገኖችም ሰምተው ተባባሪ እንዲሆኑ በሚል ለጎልጉል አስተያየት መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ለመንግስት ስለማሳወቃቸው ተጠይቀው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጸሐፊ ስልካቸውን በማፈላለግ ካገኙ በኋላ ማነጋገራቸውን
ይገልጻሉ። በምላሹም “ይልቁኑ አፋኞቹ ስልካችሁን እንዳያውቁ ተጠንቀቁ። እየደወሉ ይጨቀጭቋችሁዋል” የሚል የማስፈራሪያ
ማስጠንቀቂያ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
ቴዲ አፍሮ በፑንት ላንድ ሞት የተፈረደበትን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቀድሞ በመድረስ ህይወቱን እንደታደገው አቶ
መልካሙ አስታውሰው በተመሳሳይ የባለቤታቸውን ህይወት ሊታደግ የሚችል ወገን ሊኖር እንደሚችል ተቁመው ለማንኛውም
“መፍትሔው እግዚአብሔር ዘንድ ነው” የሚል መልዕክት በቪኦኤ በኩል አስተላልፈዋል።
ወ/ሮ ሰብለ በበኩላቸው “ፈቃደኛነቱ ካለ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን” በማለት የጀመሩት የነብስ ማዳን ስራ በቅርብ
ወዳጆቻቸው መደገፉን አስታውቀዋል። አያይዘውም ሩጫው ከጊዜ ጋር መሆኑንን አመልክተዋል።
ገንዘቡ ከተገኘ ለአፋኞቹ እንዴት ይደርሳል? ወ/ሮ ትዕግስትስ እንዴት ነጻ ይሆናሉ? በሚል ወ/ሮ ሰብለ የሰሙት ነገር እንዳለ
ለተጠየቁት፣ ሰዎቹ እስራኤል አገር ወኪል አንዳላቸውና፣ ገንዘቡ ለወኪሎቻቸው ሲገባ ግብጽ ወስደው እንደሚለቋቸው፣ ይህንን
ለማከናወን የሚችሉ ሴት አቶ መልካሙ ማዘጋጀታቸውን እንደነገሯቸው የሴትየዋን ስም በመጥቀስ ተናግረዋል።
“በድብደባና በስቃይ ደክሜያለሁ። አሁን ገንዘቡ ተከፍሎ ቢለቁኝም በረሃውን አቋርጬ ግብጽ የምደርስበት አቅም የለኝም።
እሞታለሁ። አትክሰሩ። እኔ አልተርፍም። የምትችሉ ከሆነ ህይወቴን ይወስዳት ዘንድ ለፈጣሪ ጸልዩ” ይህ ሲና በረሃ ታፍኖ የቆየ
ኤርትራዊ ወጣት ለወንድሞቹ የተናገረው የመጨረሻ ንግግር ነበር። ወንድሞቹ እስራኤል አገር በስደት ሃዘን ተቀመጡ። ከዚያ በኋላ
ስልካቸውን ቀየሩ። ወንድማቸውን በስልክ ድምጽ ነፍሱ ሳይወጣ ሞቱን ተቀበሉ” ሲሉ የሰሙትን ወ/ሮ ሰብለ አጫውተውናል።

በሌላም በኩል በተመሳሳይ ታፍና የነበረች አንድ ወጣት የሚከፈለው ተከፍሎ በቅርቡ ከግብጽ አዲስ አበባ እንደገባች
አመልክተዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሙት የሲና በረሃ አሰቃቂ ስቃይ ሳቢያ የወ/ሮ ትዕግስት ገብሬን ህይወት ለማትረፍ ራሳቸውን ከፊትለፊት
ያቆሙት ወ/ሮ ሰብለ ሊያነጋግራቸው ለሚፈልግ ሁሉ የኢሜል አድራሻቸውን አስታውቀዋል። yegetasew@yahoo.com
ዝግጅት ክፍሉ፦ በተመሳሳይ፣ በተለያዩ ስፍራዎች የሚፈጸሙትን የወገኖቻችንን ስቃይ አስመልክቶ ላልሰሙ ትምህርት ይሆን
ዘንድ ጽሁፍ ለምትልኩልና ወገኖች ሁሉ ቅድሚያ እንደምንሰጥ ለመግለጽ እንወዳለን። በተለይም በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ከ30-
40 ዓመት የኖሩ ስደተኛ ወገኖች ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያዊን ተሳትፎ ምን እንደሚመስል ብትጠቁሙን ጉዳዩን
እንደምናጣራው ከወዲሁ እንገልጻለን።
ወ/ሮ ሰብለና ለተመሳሳይ አላማ የተነሱት እህቶች የሚከተለውን ደብዳቤ ለእምነት ባልደረቦቻቸውና ለቤተክርስቲያን ያቀረቡትን
የተማጽኖና እንቅስቃሴያቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
የካቲት ፲፫/፳፻፬
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈሥ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ የሚያንሱ ከነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ” ማቴ ፳፭ ፥
፴፱
ጉዳዩ፦ በስደት ላይ እያሉ በአጋቾች ለታገቱ እናት ማስፈቻ የሚሆን ገንዘብ ስለማሰባሰብ
የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ በማለት መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያስቀደምን ወደ ጉዳዩ እንገባለን።
ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ በሱዳን አገር ሸገርአብ የስደተኞች ጣቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊት ስደተኛ ሲሆኑ በ01/22/13 ጠዋት ወደ
ቤተክርስቲያን ሲሄዱ በራሻይዳዎች ታግተው በህይወት ለመውጣት ገንዘብ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል።
ባለቤታችው አቶ መልካሙ ባዬ በዛው በሸገርአብ የስደተኞች ጣቢያ ከአንድ ዓመት ከሰባት ወር ህፃን እና ከአስራ ሁለት ዓመት
ታዳጊ ሴት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩ ሲሆኑ የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ምንም አይነት አቅም ስለሌላቸው በ02/10/13/
በተላለፈው የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል የመስታወት ዝግጅት ላይ ወገን ይደርስላቸው ዘንድ ተማጽነዋል ።
/ሙሉ ቃለ-መጠይቁን በዚህአድራሻ ማግኘት ይቻላል?

እኛም ሥማችን ከደብዳቤው መጨረሻ የተዘረዘረው ግለሰቦች ይህንን የተማጽኖ ድምጻቸውን ሰምተን ክርስቲያናዊ እና ወገናዊ
ግዴታችንን ለመወጣት ከአሜሪካ ድምጽ/VOA / ጠይቀን በተሰጠን የስልክ ቁጥር በመደወል አቶ መልካሙን /የታጋቿ ባለቤት /
አነጋግረን በምን ልንረዳቸው እንደምንችል እና አሁን ባለቤታቸው ያሉበትን ሁኔታ በዝርዝር አስረድተውናል።
በእኛ በኩል እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት፦
1. በለንደን የሚገኘውን የAmensity International Sudan Team ስልክ በመደወል በእርግጥም ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ከላይ
በተጠቀሰው ቀን በአጋቾች እንደተወሰዱ በሱዳን ያለው UNHCR እንዳሳወቃቸው ሰምተን ጉዳዩ እውነተኛ እንደሆነ አጣርተናል።
2. በሱዳን ካርቱም ላለው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በአንባሳደሩ ጸሐፊ በኩል ጉዳዩ የሚመለከተው ቆንስላ ክፍል ክትትል እንዲያደርግ
አሳውቀናል።
3. የምናውቃቸውን ሰዎች ቃለ ምልልሱን ሰምተው የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥረት እያደረግን ነው።
4. ተጨማሪ የአየር ሰዓት አግኝተው እርዳታ ይጠይቁ ዘንድ በሸገር ሬድዮ የ‘ታድያስ አዲስ’ አዘጋጅ ከሆነው ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር

ተነጋግረን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ 02/16/13 ሌላ ቃለ-መጠይቅ እንዲደረግላቸው አድርገናል
5. በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የተለያዩ የራድዮ ጣቢያዎች ይህንን አሳዛኝ ነገር ወደ ህዝብ ጆሮ እንዲያደርሱ
እየጠየቅን ነው።
6. በተጠላፊዋ ስም የFacebook ገጽ ከፍተን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በPaypal እርዳታ የሚሰጡበትን መንገድ እያመቻቸን ነው
7. Tewahedo.org. የተባለው የቤተክርስቲያን ድህረ-ገጽ ይህንን አሰቃቂ ነገር በፊት ገፁ እንዲለጥፍ አስፈላጊ መረጃ ልከናል።
8. ለዚሁ አገልግሎት ብቻ የሚውል የባንክ አካውንት ከፍተናል
በአሁኑ ሰዓት ገንዘቡ በፍጥነት መከፈል ካለመቻሉ የተነሳ በወ/ሮ ትዕግስት ላይ በኤሌክትሪክ እና በእሳት መቃጠል፤ ድብደባ፤
ተዘቅዝቆ መታሰር፤ እንዲሁም የሞቱ ሰዎችን አጥንት እያሳዩ የሥነ-ልቦና ጥቃት ማድረስ እና ሌሎችም ኢ- ሰብአዊ ድርጊቶች
እየተፈጸሙባቸው መሆኑን ባለቤታቸውን በስልክ ባገኟቸው ቁጥር ከሚነግሯቸው ነገር ለመረዳት ችለናል።
ይህንንም ደብዳቤ ለመላክ የተገደድነውም በእኛ አቅም የተጠየቀውን 25,000.00 USD ሰብስበን የእኝህን እናት ህይወት
ለማትረፍ የማንችል መሆኑን በማመናችን እና ይህ ገንዘብ ካልተከፈለ ግን አጋቾቹ “ከፍለን ነው የገዛናት ቢያንስ ያንን ለመመለስ
ኩላሊቷን አውጥተን እንሸጣለን ” በማለት በግልጽ በመናገራቸው ይህ አደገኛ ነገር ከመከሰቱ በፊት ህዝበ ክርስቲያኑ የሚችለውን
አድርጎ እኝህን እናት ለልጆቻቸው እንዲያተርፍላቸው በእግዚአብሔር ሥም በመጠየቅ ነው።
በአሁኑ ሰዓት መዋጮ መጠየቅ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው። ጉዳዩ የህይወትና የሞት መሆኑ አስገድዶን እና
ለወገን ደራሽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ተስፋ አድርገን ይህንን ለህዝበ ክርስቲያኑ እንድታስተላልፉልን የተሰደዱት ሁሉ
መከታ በሆነችው በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ሥም በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን። ከሁሉ በላይ ማህበረ ካህናቱም እና
ምዕመኑ እኚህ እናት በህይወት ይወጡ ዘንድ ወለተማርያም እያሉ በፀሎት እንዲያሳስቡላቸው እንጠይቃለን።
ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
እሴተ ህይወት/ኢየሩሳሌም ጸጋዬ/ እህተ ማርያም (አዜብ ሮባ) ሰብለ ወንጌል /ሰብለ ደምሴ/
To wire money:
Seble Demissie Asefa
Swift code for international money wiring :WFBIUS6FFX
Routing number : 121000248
Online or in person transfer in the USA routing number : 019000019.
Account number is 7728584504.
Bank name: Wells Fargo
ስልክ ፡ (612) 636 1266 ስልክ ፡ (651) 366 2310 ስልክ፡ (612) 232 8720
የግርጌ ማስታወሻ፦
የባለቤታቸው አቶ መልካሙ ስልክ ቁጥር 011 249 116 112 170 ሲሆን አስፈላጊውን ጥያቄ ሁሉ ለመመለስ በማናቸውም ሰዐት
ዝግጁ እንደሆኑ ለመግለፅ እወዳለን።

Feb 27, 2013

በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ላይ ብርበራና ዘረፋ በፈጸሙ ፖሊሶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መ.ኢ.አ.ድ ጠየቀ

ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስደንጋጭ በሆነ አሸባሪ ተግባር የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ብርበራና ዝርፊያ በመፈጸሙ ፖሊሶችና ድርጊቱን ባስፈጸሙ የፖሊስ አዛዦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መ.ኢ.አ.ድ/ ጠየቀ፡፡ መ.ኢ.አ.ድ ይህንን የጠየቀው የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሦስት ገጽ መግለጫው ነው፡፡

መግለጫው እንደዘረዘረው ‹‹አገራችን ኢትዮጵያ ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ በኋላ በተቀረጸው ህገ መንግስት አንቀጽ 11 መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ቢልም ለህ.ወ.ሃ.ት መንግስት ግን በተደጋጋሚ በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት የሃይማኖት መሪዎች የህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የፖለቲካ አስፈጻሚ እንዲሆኑ በኃይል ጭምር ሲተገብር ቆይቷል፡፡›› በማለት ይዘረዝራል፡፡ መግለጫው ባለ አራት ነጥብ አማራጭ ነገሮች በማለትም ዘርዝሯል፡፡ መግለጫው በመጨረሻም ‹‹የእስልምና መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የሚለውን ውንጀላ በገለልተኛ አካል ይጣራ፡፡›› ሲልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ፡፡



ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስደንጋጭ በሆነ አሸባሪ ተግባር የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ብርበራና ዝርፊያ በመፈጸሙ ፖሊሶችና ድርጊቱን ባስፈጸሙ የፖሊስ አዛዦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መ.ኢ.አ.ድ/ ጠየቀ፡፡ መ.ኢ.አ.ድ ይህንን የጠየቀው የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሦስት ገጽ መግለጫው ነው፡፡

መግለጫው እንደዘረዘረው ‹‹አገራችን ኢትዮጵያ ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ በኋላ በተቀረጸው ህገ መንግስት አንቀጽ 11 መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ቢልም ለህ.ወ.ሃ.ት መንግስት ግን በተደጋጋሚ በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት የሃይማኖት መሪዎች የህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የፖለቲካ አስፈጻሚ እንዲሆኑ በኃይል ጭምር ሲተገብር ቆይቷል፡፡›› በማለት ይዘረዝራል፡፡ መግለጫው ባለ አራት ነጥብ አማራጭ ነገሮች በማለትም ዘርዝሯል፡፡ መግለጫው በመጨረሻም ‹‹የእስልምና መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የሚለውን ውንጀላ በገለልተኛ አካል ይጣራ፡፡›› ሲልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ፡፡
መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሚዛን ተፈሪ ሙስሊሞች እየታሰሩ ነው


ሚዛን ተፈሪ ሙስሊሞች እየታሰሩ ነው በደቡብ ክልላዊ መንግስት ቤንች ማጂ ዞን ሚዛን ተፈሪ ከተማ ሰሞኑን ሙስሊሞች እየታሰሩ መሆኑን የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳስታውቁት የካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት
ሙስሊሞች የታሰሩ ሲሆን እስካሁንም እስሩ እንደቀጠለ ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም ለዝግጅት ክፍላችን እንዳረጋገጡት በርካታ ሙስሊሞች እየታሰሩ ሲሆን የተሰጠውም ምክ
ንያት አክራሪዎች ናቸው የሚል ነው፡፡ ወደ አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ደውለን ያናገርናቸው ስማቸውን ለመናገር ያልፈለጉ አንድ የስራ ኃላፊ በሰጡን መልስ ‹‹ሦስት ተጠርጣሪዎችን አስረናል፡፡ ምርመራው እየተጣራ ነው፡፡ ተጣርቶ ባላለቀ ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመስጠት እንቸገራለን፡፡›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡
ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Feb 26, 2013

ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት

ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)

tplf rotten apple
25.02.2013
የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱንመመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡
በመሰረቱ ይህ እኩይ ስርዓት(ቡድን) በኢትዮጲያዊነት ላይ ካለው የመረረ ጥላቻ የተነሳ አብረው የመሰረቱትን ግን በኢትዮጲያዊነት ላይ ፅኑ አቋም የነበራቸውን ባልንጀሮቻቸውን ሳይቀር እያስወገዱና እያባረሩ በምግባር የሚመቻቸውን በተለይ በህዝብና በሃገር ላይ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸውን አስከትለው የጥፋት ዘመናቸውን ቀጥለውበታል፡፡
በተለይ የመንግስት ስልጣን ከያዙ በሗላ ከስልጣን በተጨማሪ በገቢ እራሳቸውን ለማጠናከር ከኢትዮጲያ ህዝብ በዘረፉት ሃብትና ንብረት በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ኢፈርት ሃገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የንግዱን መስክ በበላይነት በመያዝ ገቢና ወጪው የማይታወቅ ትልቅ የሃብት ምንጭ በመፍጠር የአገሪቱን የትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ በበላይነት ይዘው ነግሰውበታል፡፡
በተለያየ መስክ ከሚፈፀመው የሰብዓዊ መብት እረገጣ በተጨማሪ የሃገርን ቤሄራዊ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ወይም ገንዘብ የሚይስገኝላቸውን ሁሉ በመዝረፍና በማሸሽ፣ ምስኪኑ ህዝብ በዜግነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ብቻ ሳይሆን በስሙ ተለምኖ የመጣውን ሁሉ በመንጠቅ ብዙሃን በርሃብ በሚሰቃይበት ሃገር ለአራት ለአምስት ትውልድ የሚበቃ ሃብት አሽሽተዋል፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም በፊት በተወሰነ መጠን እራሳቸው ላወጡት ህገ-መንግስት ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ቢያስቸግራቸውም ህጋዊ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩበት ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት መመላለስ የእለት ከእለት ስራቸው ቢሆንም ከአሁን በተሻለ የህትመት ውጤቶች በቁጥርም በይዘትም የተሻሉ ነበሩ፡፡ በሌላም በኩል ይህው እኩይ ስርዓት ህግን ከመሻሩ በፊት የፓርላማ ጀሌዎቹንን ሰብስቦ ሊሽር ባስበው ህግ ላይ ሌላ ህግ ሲያወጣ ታይቷል ለምሳሌ የቀድሞ የህውሃት አባል የነበሩት አቶ ስዬ አብረሃ በተከሰሱበት ወንጀል ህጉ የሚፈቅድላቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት አዲስ ዋስትና የማያሰጥ የፀረ-ሙስና ህግ ማፅደቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ህውሃት በአመለካከትም ይሁን በግል ጥላቻ የራሱን ሰወች ሲበላ ከቻለ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ በማጫረስ አልያም በአደባባይ በደላቸውን እንዲናዘዙ በማስገደድ ከተጠያቂነት እራሱን ሲከላከል መቆየቱ አንድም እራሱን ላለማጋለጥ አልያም በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚፈፅማቸው በደሌች ሰርዞም ደልዞም ህግዊ ለመምሰል የጥር ነበር፡፡
ከምርጫ 1997ዓ.ም በሗላ ያለው በፊት ከነበረው ጋር ማነፃፀር ይከብዳል እጅግ ብዙ እርቀት ወደ ሗላ የመመለስ ያህል ነው ምክንያቱም በዛን ወቅት በተፈጠረው በጣም ጠባብ አጋጣሚ ህዝቡ ለስርዓቱ ይለውን ጥላቻና ለውጥ ፈላጊነቱን እንዲሁም እነሱ በተግባር የማያውቁትን ዴሞክራሲ ህዝቡ ሲዘምርላቸው፣ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከነሱ እንደሚሻል ሲያሳያቸው፣ ይበጁኛል የሃገሬንና የእኔን ህልውና ይጠብቁልኛል፣ ብሩህ የነፃነት ጊዜ ያመጡልኛል ይሆኑኛል ብሎ የሚላቸውን እንደራሴዎቹን ሲመርጥ ለአፍታ ይስተዋልባቸው የነበረው ሰዋዊ ባህሪየቸው ጠፍቶ ጫካ ተወልዶ ጫካ ያደገው አውሬነታቸው ሲመለስ የሚችሉትን ገለው ገሚሱን ወደ ማጎሪያቸው አግዘው ጭልጭል ትል የነበረች ተስፋችንን አደበዘዟት፡፡
ከዚህ በሗላ ያለችው ኢትዮጲያ የግል የህትመት ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በማፈን በሃገራችው በሞያቸው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ፣ ለሃገራችን ክብርና ለህዝቧ ነፃነት የሚሟገቱ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት ወይም በሃገራቸው በነፃነት የመኖር መብት አጥተው የሚሰደዱባት አልያም የነሱ የሆነው በሌሎች ተቀምተው የመከራ ቀንበር ከብዶ በግዞት የሚኖርባት ስትሆን ለኢምንት ባለ ጊዜዎች ግን የምድር ገነት ሆና ያሻቸውን የሚሆኑባት የግል እርስት አድርገዋታል፡፡
ይህ ከላይ ያነሳሁትና ተነግሮ የማያልቀው በህዝብ በሃገር ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ በወያኔ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን የኛም ግፍና በደልን የመሸከም አቅም ወይም እንደ ሰው መብታችንን የማስጠበቅ፣ ህልውናችንን ያለማስደፈር ወይም በውርደት መኖር በቃኝ ብለን ሃላፊነታችንን ሳንወጣ እንዲሁ ከድርጅት ድርጅት ስንላተም፣ ከፓርቲ ፓርቲ ስንከለስ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሳሪያ ሆነን በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት ዘመን እናሻግራለን፡፡
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ ለለውጥ እንዲነሳ በህብረት ከመስራት ይልቅ የነሱን መበታተንና መሰነጣጠቅ አውርተን በድክመታቸው ሳንጠቀም መልሰው ተደራጅተው መብትና ክብራችንን ሲገፉንና ሲፃረሩን እናያለን፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ትተን በሰሞነኛ የወያኔ የጭካኔ ገድል ላይ ቡና እየጠጣን ስናነሳና ስንጥል ከወሬ የዘለለ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ሳንገባና የታደሉት ለሃገራቸውና ለህዝባቸው የሚከፍሉትን መስዋህትነት የሚሰሩትን ታላቅ ስራ ስናፈርስና ስንክብ የዜግነት ግዴታችንን በአግባቡ ሳንወጣ ለገዢዎቻችን መሳሪያ ሆነን በዛ ደሃ ህዝብና ሃገራችን ላይ ቁማር እንጫወታለን፡፡
ነፃነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም የመስዋህቱ አይነት የለያይ እንጂ አነሰም በዛም የነፃነት ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋህትነት ይፈልጋል፡፡ ዶክተር መርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንዳለው “ለውጥ በመንኮራኩር ተጭኖ የሚቀርብ ነገር አይደለም ሊገኝ አይችልም፣ በማያቋርጥ ትግል እንጂ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለነፃነታችን መጣር አለብን ወገብህ ለመጥ ካላለ ጠላትህ ሊጋልብህ አይችልም. . . . . ከልምድ እንዳየነው ጨቋኝ ገዢ ነፃነትን በፈቃደኝነት አይሰጥም በተጨቋኞች መገደድ እንጂ” ይህ ነው እውነቱ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት ከወሬ ያለፈ በተግባር የተፈተን ስራ መስራት ስለምን ተሳነን፣ ስለምን የህይወት መሰዋትነት ለሚከፈልበት የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማገዝ ሰነፍን፣ስለምን ከወያኔ ለምናገኝው ቁራሽ መሬት ብለን የወገኖቻችንን የመከራ ጊዜ እናራዝማለን፣ ቁጥር ስፍር የሌለው ህዝብ በውጪው አለም እየኖረ ስለምን የህዝባችን የመረጃ ምንጭ የሆነው ኢሳት መስራት ያለበትን ያህል እንዲሰራና ህዝባችን እየተራበ መጥገቡን፣ እየከሰረ ማትረፉን፣ እየተቸገረ መበልፀጉን ከሚነግረው የወያኔ ዲስኩር አውጥተን አማራጭና እውነተኛ መረጃ የሚያገኝበትን፣ ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው እያደረገ ያለውን ዘርን ከዘር ሃይማኖት ከሃይማኖት የማጋጨትና የመሳሰሉትን የወያኔን ሴራ ህዝቡ እንዲያቅና በአንድነት ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲነሳ ኢሳትን በመረዳት የዜግነት ግዴታችንን አንወጣም?
በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የሗሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው አስተሳሰብና የሃይል አገዛዝ ተሸብቦ ያልደረሰበት ጫፍ፣ ያላስነባው ህዝብ፣ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፣ ያላፈረሰው አንድነት፣ያላዋረደው የህዝብ ስብእና፣ ያልገባበት የእምነት ተቋም፣ ያልበተነው የሞያ ማህበራት ከከተማ ነዋሪ እስከ ገበሬው አልፎም እስከ አርብቶ አደሩ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም፡፡
በአሁኑ ወቅት አዛዥና ታዛዥ የሌለበት የወያኔ ስርዓት ዘመኑ እያከተመ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች መገንዘብ አይከብድም ህግ ማሰከበር ያለበት መንግስት ላወጣው ህግ መገዛት የማይችልበት ደረጃ ከደረሰ ህልውናው አደጋ ውስጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው ለዚህም መብቱን በወያኔ የተነጠቀው ህዝብ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ እያሳየ የህግ ያለህ ሲል መደመጡ፡ በግምት የሚመራን ስርዓት የመጨረሻው ጠርዝ ላይ መቆሙን አመላካች ነው፡፡
ስለሆነም ኢትዮጲያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማረግ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!
ሞት ለወያኔ!!!

Total Pageviews

Translate