Pages

Apr 2, 2013

እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው

 ከገለታው ዘለቀ

Eskinder Nega and his Son Nafkot
ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ።
“ኣልሰማህም እንዴ ?”
በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ።
ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ
እስክንድር ነጋ እና ልጁ ናፍቆት
የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። የሁለታችንም ሳቅ ካለቀ በሁዋላ እውነተኛው ስሜት ሲመጣ ደሞ ያስለቅሳችሁዋል። ነገሩ እውነት መሆን ኣለመሆኑን ኣጥብቄ ኣልጠየኩም፣ ለነገሩ ከዚያ ቀን በሁዋላም ከብዙ ሰው ይህንኑ ሰማሁ። ነገሩ በትክክል ሆነም ኣልሆነም ያ ሁሉ ሰው መንግስት እንደዚያ ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ነገሩ መሆኑን ኣለያም ሊሆን መቻሉን ያሳያል። በዚያች ኣገር ምን የማይሆን ኣለና።
በዚህ ስደነቅ ስደመም ደሞ ኣንዴ እንዲህ ሆነላችሁ። እንዲሁ ኣንድ ሻይ ቤት ተቀምጨ ወጪ ወራጁን እማትራለሁ። በመሃል ኣንድ ሰው ሳምሶናይት የሚባለውን ቦርሳ ጠልጠል ኣርጎ ገባና ወዲያ ወዲህ ካየ በሁዋላ የኔን ጠረንጴዛ ተጋርቶ ለመቀመጥ በትህትና ጠየቀኝ። ወንበሩን ሳብኩለት። እንደኔው ሻይ በሎሚ ኣዞ ቁጭ ኣለ። ጥቂት ቆየት ካለ በሁዋላ ያቺን ቦርሳውን ከፈተና ኣንዲት ጋዜጣ ኣውጥቶ ዘረጋጋና ማንበብ ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ሁለት ሰዎች ወደ ሻይ ቤቱ ገቡና ከኛ መቀመጫ ትይዩ ተሰየሙ። ኣንዱ የቀኝ እግሩን ቀጥ ኣርጎ ዘርግቶ ነበር የተቀመጠው። በሁዋላ ኬክ ሊመርጡ ሲነሱ እንደሚያነክስ ሳይ እግሩ ኣርቴፊሻል መሰለኝና ኣለ ኣይደለም ኣሳዘነኝ። የሚጠጣውን እየጠጡ ኬካቸውን እየበሉ ያወካሉ። እኔና ከፊቴ ያለው ሰውየ ግን ጸጥ ብለናል። ትንሽ እንደቆየ ያቺን ጋዜጣውን በሽንጡዋ ሸመለለና ወደ ቦርሳው ከተተ። ደሞ ወዲያው ኣጨበጨበና ሂሳብ ከፈለ።
እኔም እስካሁን ባናወራም ኣብርን ለትንሽ ሰኣትም ቢሆን ባንድ ጠረንጴዛ በልተን ጠጥተናል ዝም ኣይባልም ብየ ነው መሰለኝ ቻው ለማለት ምንም ኣልቀረኝም።በመሃል ያ ያነክሳል ያልኩዋችሁ ሰውየ ድንገት ወደኛ ዞረና
“ምን ኣልክ ኣንተ? ምን ኣልክ? ድገመው እንጂ…… ልብ በሉ… ሰዎች ልብ ኣርጉ.. ምን ኣልክ ኣንተ?…” እያለ ይጮሃል።
ሁላችንም ተደናገጥን። ያ ከኔ ጋር ጠረንጴዛ ተጋርቶ የነበረው ሳምሶናይቱን እንዳንጠለጠለ
“ኸረ እኔ ምንም ኣልወጣኝም ጌታየ ምን ነካዎት” ይላል ኣስር ጊዜ። ከዚያ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየም ኣብሮ ያጫፍራል። በሁዋላ ይሄ ከኔጋር የነበረው ሰው መንጨቅ ብሎ ሲወጣ ሁለቱም ተከተሉትና ጭቅጭቁ ከውጭ ቀጠለ።
ያው መቼም ሃይ ሃይ ማለት ያገር ባህል ነውና ወደ ውጭ ወጥቼ ኸረ እሱ ምንም ኣላለም ፣ ምንም ሲል ኣልሰማሁትም ተረጋጉ እያልኩ ለመምከር መቼም ያቅሜን ሞከርኩ።
ያ የሚያነክሰው እንባው ሁሉ የመጣ ይመስላል። ይገርማል ዋሽቶ የሚያለቅስ ሰው ቢገጥማችሁ ምን ትላላችሁ?
“እንዴት ትሰድበኛለህ……” እያለ ሲሙዋገት ጓደኛውን ጠጋ ብዬ እናገላግላቸው እባክህ ምን ኣለ? ምንም ኣላልም እኮ ኣልኩት።
“የለም የለም እኔ ራሴ ሰማሁት እኮ ወራዳ ነው ሽባ ብሎ ሰደበው እኮ”
ደነገጥኩና መቼ? ብየ ጠየኩ::
ወደዚህኛው ሰውየ ዞሬ ትተዋወቃላችሁ እንዴብዬ ጠየኩ::
“በፍጹም ኣንተዋወቅም ኣለ” ግራ የተጋባው ባለ ሳምሶናይቱ ፈጠን ብሎ
“ሂሳብ ከከፈለ በሁዋላ ድምጹን ከፍ ኣርጎ እኮ ነው የሰደበው”
በውነት ግራ ግብት ኣለኝ። ሁዋላ ላይ ይሄ የሚያናግረኝ ሰው ስልኩን ኣወጣና ኣንድ ሁለት ቁጥሮችን ነካካና ወደዛ ዞር ብሎ ጥቂት ኣወራ መሰለኝ። ወዲያው እንደተመለሰ ኣንድ ፖሊስ መጣና ያንን ባለ ሳምሶናይት “ቅደም ኣለው።”
በዚህ ጊዜ ወደ ፖሊሱ ጠጋ ብዬ ምንም እኮ ኣላለም እኔ እዚህ ነበርኩ
ምንድነው ችግሩ ለማለት ሞከርኩ። ፖሊሱ በግንባሩ ጥሩ ኣርጎ ገረፈና ኣስቆመኝ። ባለ ሳምሶናይቱ እንዲሁ “ምን ኣጠፋሁ” እንዳለ ይነዱት ጀመር። ሁኔታው ገርሞኝ ነበርና ባጭር ርቀት መከተል ጀመርኩ። የሚገርማችሁ ያ ቅድም ቀኝ እግሩን ይጎትት የነበረው “ሽባ” ተብየ ተሰድቢያለሁ የሚለው ሰውየ ኣሁን በግራው ማንከስ መጀመሩን ትኩር ብዬ ኣስተዋልኩና የሆነ ነገር እየሆነ እንደሆነ ገባኝ። ብዙም ሳልርቅ ወደ ሁዋላየ ሂሳቤን ለመክፈል ተመለስኩ። ወደ ሻይ ቤቱ በር ስቃረብ ኣንዱ “ወሰዱት ኣይደል?” ኣለኝ:: ኣዎ ወሰዱት ኣልኩና ግን ምንም ኣለማጥፋቱን ኣስረግጨ ነገርኩት። ጥቂት ኣየኝና “ወንድሜ ተጠንቀቅ ከዚህ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየ የነሱ ጆሮ ነው የተለያየ ልብስ እየለበሰ ሲሰልል ነው የሚውለው ተነቅቶበታል” ኣለኝ። እኔም ወዲያው ጠርጥሬ ስለነበረ ገባኝ። እንግዲህ ያን ሰው በዚህ ርካሽ ስራቸው ኣወናጅለው የሆነ ነገር ኣርገውታል ማለት ነው።
ባለፈው ጊዜ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ከነበሩት መካከል ኣንዱ በኢሳት ቴሌቪዥን ኢንተርቪው ተደርጎለት ሲናገር ልብ ይነካል። ሲቪል እየለበሱ መገናኛ እየያዙ እንዴት የስነ ልቡና ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ገለጸ። ኑሮ ኣይደለም የምንኖረው ኣለ። ያሳዝናል። ሃሳብን መግለጽ ጥቂት ኣስተያየት መሰንዘር በስነ ልቡናና በኣካል የሚያስቀጣ ነገር የሆነባት ሃገር ናት ኢትዮጵያ።
መነሻየኮ ስለ እስክንድር ነጋ ነው። ይህን ያመጣሁት በእንዲህ ባለ ኣገር፣ እስክንድርን የመሰለ ፖሊሲ የሚያመነጭ፣ የሰባዊ መብት እንዲከበር ለማድረግ የሚታገል ሰው ስንት ስነ ልቦናዊ ቅጣት እንደሚቀበል ለመገመት እንዲያስችለን ነው።
እስክንድር የታሰረበትን ምክንያት ኣለም ኣውቆታል። እስክንድር የታሰረው በውስጡ ያለው የእኩልነትና የፍትህ ራእይ እንቅልፍ ኣልሰጥ ስላላቸው ነው። ያንን በገቢ ኣለመመጣጠን የሚሰቃየውን ህዝብ እህል በልቶ እኩልነት ሰፍኖ ማየት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ነው የ እስክንድር ሃጢያቱ።እስክንድር ቅንና ርህሩህ ነው። የጻፋቸው ጽሁፎች ዋቢዎች ናቸው። የሱ ወንጀል መምከሩ፣ ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው። የነ ርእዮት ኣለሙም ወንጀል ይሄው ነው። መናገር፣ መምከራቸው ነው ወንጀላቸው።
ግን እውነት ሊሞት ይችላል። መሞት ብቻ ኣይደለም ሊቀበርም ይችላል። ግን ደሞ እውነት መቃብር ፈንቅሎም የመነሳት ሃይል ኣለው። መንግስት ይህን መረዳት ኣለበት።
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!

Reeyot-Alemu    
መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆች አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤
ከአንድ ወር እስከ አራት ወር ለሚደርስ ጊዜ በወዳጅ ዘመዶቿ እንዳትጎበኝ፤ ደብዳቤ እንዳትልክ እና እንዳትቀበል (ይሄ እንኳ አሁንም ተግባራዊ ተደርጎባታል) የእስር ቤቱን ቤተ መጻህፍት እንዳትጠቀም፣ በእስር ቤቱ በሚደረግ የጋራ ዝግጅት እና መዝናኛ ላይ እንዳትሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ለሚደርስ ጊዜ ለብቻ እስር ትዳረጋለች፡፡
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ያቺ በቃሊቲዊቹ ውቃቢ ትፈቀድ የነበረች አመክሮም ልትከለከል ነው ማለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤልም በእስር ቤቱ እየደረሰበት ያለውን አበሳ በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላትም ቅጥ ያጣውን የእስር ስርዓት ሃይ ለማለት የርሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
ወይ ጣጣ… ብዬ የራሴን አስተያየት በአዲስ መስመር አቀርባለሁ…
እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምነው እንዲህ መካሪ አጣ…? እርሱ እኛን በስንቱ መከራ እንዳልመከረን እርሱን የሚመክረው ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡
እስቲ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እስሩ አንሶ አሳር የሚያበላው ምን ይሁነኝ ብሎ ነው? እንደሰማነው በርካታ የህሊና እስረኞች በታመሙ ጊዜ የሚያክሟቸው የእስር ቤቱ ሀኪሞች “መግደል ነበር አንተን” “መጨረስ ነበር አንቺን” እያሉ ያስፈራራሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ይሄ የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውና ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ መንግስታችን “ባትሪ ሎው” እያለ ይመስለኛል!

የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት?“ከእንግዲህ የቀድሞው መንገድ አይሰራም”

odf


 
ላለፉት አርባ ዓመታት ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ሲታገል የቆየው ኦነግ አመራሮቹ ሲጣሉና ሲታረቁ መስማት የተለመደ ነው። የግለሰብ ጸብ የሚመስለው የድርጅት በሽታ ሲንጠው የቆየው ኦነግ በውል ባይታወቅም ተሰነጣጥቆ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ድርጅት ከሆነም ዓመታት ተቆጥረዋል። ስህተትን ገምግሞ የትግል አቅጣጫና ፕሮግራም ከመቀየር ይልቅ ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ ባለበት ሲረግጥ እድሜውን የፈጀ ድርጅት እንደሆነ ተደርጎም ይወሰዳል።
ስለ ኦነግ ሲነሳ አብዛኞች በመገረም የሚናገሩትና ሚዛን የሚደፋው አስተያየት የሚሰነዘረው በድርጅቱ መከፋፈልና መበጣጠስ ሳይሆን ተለያይተውም አስመራን የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ህጻን እያለ ሻዕቢያ እንዳሻው ይነዳው እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች ከሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ኦነግ አገር ለቆ እንዲወጣ መንገዱን የጠረገው ሻዕቢያ መሆኑንን በቁጭት ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ለስልጣን አዲስ በሆነበት የጨቅላነት ዘመኑ፣ ኦነግ በታሪኩ ያልነበረውን ሰራዊት በመገንባት አስጨንቆት እንደነበር በመጠቆም በወቅቱ አስተያየት የሰጡ ኢህአዴግ በተለይም መለስ በሻዕቢያ በኩል ኦነግን ለመታረቅ አቅርበውት የነበረውን የሽምግልና ጥያቄ ኦነግ እንዳይቀበል ሰሚ ባያገኙም በአጽዕኖት ምክራቸውን ሰጥተው ነበር።
በኦነግ ታጣቂ ሃይሎችና በኢህአዴግ ሰራዊት መካከል እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የጡንቻ  መፈታተን ነበር። ደርግ ሲበታተን ኦነግን የተቀላቀሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አካላት ወያኔን የማዳፋት አቅሙ ነበራቸው። በወቅቱ የንስር ያህል ጉልበትና ሃይል ቢኖራቸውም ራሳቸውን ጫጩት አድርገው ተመለከቱ። አዲስ አበባ ሲገቡ የነበራቸውን የህዝብ ድጋፍ አራግፈው ጣሉት። በስሜት እየተነዱ ከሚወዷቸው ሁሉ ተቀያየሙ። ህወሃት አጋጣሚውን ለቅስቀሳና ለስም ማቆሸሻ ሰራበት። በስተመጨረሻ ኦነግ ሃይሉንና አቅሙን ዘንግቶ በአመራር ችግርና በአቋም ሸውራራነት ሃይሉን በሙሉ ወደ ካምፕ በማስገባት የኢህአዴግን የእርቅ ጥያቄ ተቀበለ። ሰራዊቱን እየነዳ በፈቃደኛት አሳሰራቸው።
በሻዕቢያ አደራዳሪነት ሁርሶ፣ ደዴሳና መስኖ የገባው ሰራዊት “በደባ” ተከቦ ትጥቁን እንዲፈታ ተደረገ። አብጦ የነበረው የኦነግ ጡንቻ በቅጽበት ከሰመ፤ ሰለለ። ኦነግ ሲቆጣጠራቸው የነበሩትን ቦታዎች ለማስተዳደርና በኦህዴድ ለመተካት ኢህአዴግ እንደ እባብ ተሹለክልኮ ዓላማውን አሳካ። ሻዕቢያም በዚሁ ውለታው ኢትዮጵያንና ኢኮኖሚዋን ብሎም የኢትዮጵያን ስነልቦና እንዳሻው እንዲጋልብ ተፈቀደለት። ብዙ አሻጥር ተፈጠረ፤ ተፈጸመም። ደንዳና ቆዳ ያላት ኢትዮጵያና ህዝቧ ተቦጠቦጡ። ተዘረፉ። አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ኤርትራ ቡና ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተሰለፈች። አፈርን።
“አገሬን ከወራሪ አጸዳሁ” በማለት ከበሮ እየመታ ጦርነት አልቋል ብለው እጅ የሰጡ የወገን ወታደሮችን የረሸነው ሻዕቢያ ኢትዮጵያንም ያስተዳድር ጀመር። ዛሬ የሚማልባቸውና “ውርሳቸውን ሳናዛባ እናስጠብቃለን” የሚባልላቸው አቶ መለስ እንደ ባዕድ መሪ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም ለሻዕቢያ አሳልፈው ሰጡ። የሻዕቢያ ታጣቂዎችና ኢትዮጵያ አብልታ ያሳደገቻቸው ጎረቤቶቻችን ሳይቀሩ ናጠጡብን። በየደጃቸው መሳሪያ ወደላይ እየተኮሱ በደስታ ውለታ ባስቀመጠችላቸው አገር ላይ ተሳለቁ። ምስኪኖችን ቤት እያስለቀቁ ወረሱ። የሌላቸውን ሃብትና ንብረት ሰበሰቡ። በኤርትራ ምድር በግፍ ለተረሸኑ የኢትዮጵያ ልጆች ተከራካሪ ጠፋና የሞት ሞት ሞቱ። አገራችን የግፈኞች መፈንጫ እንድትሆን መለስ በበረገዱት በር የገባው ሻዕቢያ ከርሱ ሲጎድል፣ “ልክህን እወቅ” የሚሉ ሲነሱ፣ ስርዓት ያዝ ሲባል ደሙ ተንተከተከና የሃይደር ህጻናትን በጠራራ ጸሃይ በላቸው። ትግራይን ወረረ። ሲሰርቁ ኅብረት የነበራቸው ሲከፋፈሉ ተጣሉና አገር ውርደት ገባው።
ይህንኑ ተከትሎ አገር አልበቃ ብሏቸው የነበሩና ወያኔን ሲያገለግሉ የነበሩ ቅጥረኞች የሰበሰቡትን ሳይበሉ ወደ “ከባርነት ናፅነት” ብለው ድምጻቸውን ወደሰጡላት “እናት አገራቸው ኤርትራ” ተጋዙ። ንብረታቸውን በትነው አገር ለቀው ወጡ። ከነጻነት በኋላ “ታይላንድ ትሆናለች፣ ሲንጋፖር ትሆናለች፤ ሆንግኮንግ ትሆናለች” በተባለላት አገራቸው ለመኖር ተገደዱ። ዳቦ ተሰልፈው ለመግዛት ታደሉ። ኬክ በለመደው፣ ቁርጥ በቆርጠው፣ “ሹካ ባስለመደው” እጃቸው ይድሁበት ገቡ። ወታደር ሆኑ። የሰገዱለትና ቅጥረኛ ሆነው ያገለገሉት ህወሃት መልሶ በረሃ በተናቸው። የሚያሳዝነው ግን ኤርትራዊያን ከየመንደሩ ተለቅመው ወደ አገራቸው ሲሄዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አውቶቡስ ከብበው ደረት እየመቱ ያለቅሱላቸው ነበር። ደብቀው ያስቀሩዋቸውም አሉ። ጨርቃቸውን ጥለው አውቶቡስ እንዳይነሳ በፍቅር አምላክ የተንፈራፈሩ ነበሩ። ሁኔታውን የሚያስታውሱ ድርጊቱን “የሞኝ” ተግባር አድርገው ሲወሰዱት ሌሎች ደግሞ “ክፉ ላደረገብህ ክፉ አትመልስ” የሚለው ግብረገብነት የገባቸው የፈጸሙት የጀግንነት ተግባር ነው በማለት የአዲስአበባ ነዋሪዎችን የመንፈስ ልዕልና ያደንቃሉ፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት ጀምሮ ኦነግ ሻዕቢያን ሲለማመነውና እግሩን ሲልሰው የኖረ ድርጅት ዛሬ ድረስ ተበጣጥሶም እዛው አስመራ አምልኮ ደጅ ይገኛል። ከአመት ዓመት ያለ ለውጥ እዛው ይንፏቀቃል። እንደሚሰማው ከሆነ ወታደሮቹ የሻዕቢያ አግልጋዮች ሆነዋል። አመራሮቹም ቢሆኑ አስመራን ለቀው የመውጣትና እንዳሻቸው የመንቀሳቀስ መብት የላቸውም። በዚህም ይሁን በሌላ መነሻ ኤርትራ በከተሙት የተለያዩ የኦነግ ሃይሎች ላይ ከያቅጣጫው ስሞታ መቅረብ ከጀመረ ሰንብቷል። ኤርትራን ለቀው መውጣት አለባቸው የሚለው የኦሮሞ ልጆች ድምጽም በርክቷል። ጥያቄው አያሌ ፖለቲካዊ ማብራሪያ የሚጠይቅና አማራጭ መፍትሄ የሚያሻው ቢሆንም ኤርትራ ውስጥ አሉ በሚባሉ ታጣቂ ተቃዋሚዎች ያልተማረሩና ያልተሰላቹ ቢኖሩ አፍቃሪ ሻዕቢያዎች ወይም ራሳቸው የሻዕቢያ ሰዎች ወይም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሻዕቢያን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ብቻ ናቸው።
እንግዲህ በዚህ መሃል ነው አስመራን ተሳልመው ከነበሩት የኦነግ አመራሮች መካከል አቶ ሌንጮ ለታ፣ አቶ ዲማ ነገዎና ሌሎች ሰሞኑን አዲስ ዜና ይዘው ብቅ ያሉት። አዲስ ፓርቲ በማቋቋም ድፍረት የተሞላው አቋም በማራመድ “አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” ያሉት። ሃሳቡ መልካም  ቢሆንም እንዴት? የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው። ምክንያቱም በግልጽ “የቀጣዩ ትግል ሜዳ አገር ቤት ነው፤ አገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ተብሏልና!
“የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” ODF የሚባል አዲስ ግንባር መቋቋሙ ከአሜሪካ የሚኖሶታ ጠቅላይግዛት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች እየተወረወሩ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጥርት ያለ መልስ አልተሰጠም። ግንባሩ መመስረቱ ይፋ ከሆነ በኋላ መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) በዚያው ጠቅላይግዛት በሚኒያፖሊስ ከተማ በተካሄደ ስብሰባ አንዳንድ ጉዳዮች ይፋ ሆነዋል።
ከብሪታንያ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። ኢትዮጵያን “ኢምፔሪያሊዝም፣ ቅኝ ገዢና ጠላት” አድርገው በመሳል ጥያቄ የሰነዘሩትን ጨምሮ ስለ ቀጣዩ ትግል ትግበራና ሰለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር በስፋት ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሌንጮ ለታ አስገራሚ መልስ ሰንዝረዋል።
“ያለፈውን በመውቀስ የትም አንደርስም። አሁን ማየትና ማሰብ ያለብን ወደፊት ነው። ሌሎች ወገኖችን አግልለን ብንታገል የትም አንደርስም። ያለፈው የትግል መንገድ ስህተት ነበር” ብለዋል። ስለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር ሲናገሩ “የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ካልተከበረ የኦሮሞ መብት ብቻውን ሊከበር አይችልም” በማለት መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
“ጊዜው ተለውጧል። ጊዜው አዲስ ነው። አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው” በማለት የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ “አገር ቤት እንዴት ገብቶ መታገል ይቻላል?” በሚል ለተነሳው ጥያቄ የሰጡት መልስ አዲሱን ድርጅታቸውንና እርሳቸውን የሚፈትን እንደሆነ ያመላከተ ነው።
ቀጣዩ ትግል ኤርትራ ላይ እንደማይሆን በግልጽ የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ አገር ውስጥ በመግባት ለማደራጀት፣ ለመታገል፣ ለመንቀሳቀስ ይቻል ዘንድ “መንገድ እንፈልጋለን” ብለዋል። ኢህአዴግ በተደጋጋሚ እንደሚለው ለድርድር የሚቀመጡ ወገኖች መጀመሪያ ህገመንግስቱን መቀበልና ህግመንግስቱን አክብሮ ለመስራት መማል አለባቸው። ይህ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም አገር ቤት ለመግባትና ለመታገል እነ አቶ ሌንጮ ቢስማሙ እንኳን ሌላ መሰረታዊ ችግር እንዳለ ከወዲሁ እየተጠቆመ ነው።
በኦሮሞነታቸው በሚያነሱት ጥያቄ እስር ቤት የታጎሩ የኦሮሞ ልጆች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው – በአስር ሺዎች እንደሚቆጠር ይገመታል። በየቦታው ባሉ እስር ቤቶች ዋናው የመግባቢያ ቋንቋ ኦሮሚኛ እስከመሆን የደረሰበት ሁኔታ ነው የሚታየው። ይህ እውነታ ባለበት አቶ ሌንጮ የሚመሩት አዲሱ ድርጅት እንዴት አድርጎ ይታገላል? ወይም ደግሞ አባላቶቹ እስርና እንግልት እንዳያጋጣማቸው ምን ዓይነት ማረጋገጫና መተማማኛ ማግኘት ይቻላል?
“መልሱ ግልጽ ነው” በሚል ይመስላል “የፈለገው ቢመጣ፣ አስፈላጊው ህግን የጠበቀ ትግል ይካሄዳል። አገሪቱ ላይ ያለውን ህዝብ አስሮ ይችል እንደሆነ የሚታይ ይሆናል” የሚል እንደምታ ያለው ምላሽ ነው እየተሰነዘረ ነው ያለው። በሌላ በኩል አገር ቤት ገብቶ መታገል ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ ሲወሰድ አዲሱ ጉዳይ የቀድሞው ሌሎችን ሲያገልና “ልዕልናና ነጻነት ለኦሮሞ ብቻ” በሚል የፖለቲካ ሾፌር ሲደወር የነበረው የትግል ስልት መቀየሩ ነው። በዚህም የተነሳ ይመስላል “ከማናቸውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ መረጋገጥና ለህዝብ እኩልነት ከሚሰሩ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን። የቀድሞው መንገድ አይዋጣም” የሚል ምላሽ የሰጡት።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ “እኔን ተከተል፣ ስትቃወም ከኔ ቀመር አትዛነፍ” የሚለውን አመለካከት ጨምሮ በድፍን የአንድ እንቅስቃሴ እርግጠኛ መነሻ ሳይታወቅ አስቀድሞ “የማብከትና የማበስበስ” ስራ መስራት የተለመደ በመሆኑ ከሁሉም ወገን እርጋታ እንደሚጠበቅ፣ ረጋ ብሎ መመርመር እንደሚያስፈልግ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ላለፉት 20 ዓመታት ኢህአዴግ በብሄር እየለየ በፈጠረው ገደል እየተወረወሩ የሚገቡ ፖለቲከኞች በሰሩት ጥፋት ህዝብ ለከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት ተዳርጓል። ኢህአዴግ የ50 ዓመት የቤት ስራ እንደሰጠ አድርጎ የሚያስበውም እነዚሁ የፖለቲካ መሪዎች የህወሃትን የሳሳ ፖለቲካ መረዳት ባለመቻላቸውና ከዋናው ጠላታቸው ይልቅ እርስ በርስ ለመቧቀስ የፈጠኑ መሆናቸውን በቀላሉ ስለሚያሳዩት ነው።
ከ40 ዓመታት የስህተት ጉዞ በኋላ አገር ቤት በመግባት “ሁሉም ነጻ ካልወጡ ኦሮሞ ብቻውን ነጻ አይወጣም” በሚል የትግል መርህ መነሳት በራሱ አስደሳች እንደሆነ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል በስልክ ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ ተናግረዋል።
“ድንበርና ክልልን ሳይሆን የምንጋራው አብሮነትን ነው” ያሉት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “በዲኤንኤ ምርመራ ጎሳ አይታወቅም። ተመሳሳይ ዲኤንኤ ያላቸው ጎሳዎችም የሉም። ሁሉም ነጻ ካልወጡ ማንም ነጻ እንደማይወጣ መስማት ታላቅ ብስራት ነው” በማለት ከዓመታት ትግልና ውትወታ በኋላ ድርጅታቸው ሲታገልለትና ሲሟገትለት የቆየው ዓላማ የሌሎችም መርህ ሆኖ በማየታቸውና በመስማታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ዓይነቱ መርህ ለዘመናት የቆየው ሥርዓቱም ሆነ አኗኗሩ ቅርብ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አመልክተዋል፡፡ ድርጅታቸው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል የከበረ መመሪያ ላይ ሲሰራ መቆየቱን የገለጹት አቶ ኦባንግ ከዚህ መመሪያ በተጨማሪ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚለው የትግል መርህ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡ ይህንን መፈክር አሁን ደግሞ ኦሮሞ ወገኖቻችን ሲያነሱ መስማት ለድርጅታቸው ታላቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ላይ ማንም ሳይጠራቸው በራሳቸው አነሳሽነት እንደሄዱ ያስታወቁት አቶ ኦባንግ “የኦሮሞ ተወላጆች ስብሰባ ሲቀመጡ የሚነጋገሩት ስለ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝና ውይይቱ ይመለከተኛል። ስለዚህ ተገኘሁ። በደስታ ተቀበሉኝ። በስብሰባው ውስጥ በሰማሁት አዲስ ሃሳብ ተደሰትኩ” ብለዋል።
ላለፉት 20 ዓመታት አንዱ ስለ ሌላው ሲያወራ መኖሩን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ አሁን አንድ ላይ በመሆን ለመመካከርና “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ” ግንባታ በጋራ ለመታገል መወሰን ከልምድ የተገኘ የፖለቲካ ተሃድሶ መሆኑን አስታውቀዋል። አያይዘውም ድሮም ቢሆን ፖለቲከኞች እንጂ ህዝብ አእምሮ ውስጥ ያልነበረ አስተሳሰብ በማቀንቀን ለህወሃት ፖለቲካ ማዳበሪያ የማቅረብ ስራ ሲሰራ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ ሌንጮ ለታ እንጀምረዋለን ያሉት አዲሱ መንገድ ሁሉንም ህዝብና የፖለቲካ ድርጅቶች ማዕከል በማድረግ ለመስራት ወስኖ የተነሳ እንደሆነ ሲያስታውቁ ያሰመሩበት ጉዳይ ቢኖር “ያለፈውን አናስብም። አሁን አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተያይዘው የሚፈጥሯትን አዲስ አገር ማየት ነው፡፡” እርሳቸው እንዳሉት 40 ዓመት ባክኗል። አሁንም መንቃት አግባብ ነው። ነገር ግን ድጋፉም ሆነ ተቃውሞው በተራ የድጋፍና ተቃውሞ ስሜት ሳይሆን ረጋ ብሎ በመመርመር እንደሆነ የሚመክሩ ጥቂቶች አይደሉም።
(ፎቶዎቹን የወሰድነው ከ Hegeree Media channel ቪዲዮ ላይ ነው)

EthiopiaSource: Human Rights Watch World Report 2013, pp 114-120

 
The sudden death in August 2012 of Ethiopia’s long-serving and powerful prime minister, Meles Zenawi, provoked uncertainty over the country’s political transition, both domestically and among Ethiopia’s international partners. Ethiopia’s human rights record has sharply deteriorated, especially over the past few years, and although a new prime minister, Hailemariam Desalegn, took office in September, it remains to be seen whether the government under his leadership will undertake human rights reforms.
Ethiopian authorities continued to severely restrict basic rights of freedom of expression, association, and assembly in 2012. Thirty journalists and opposition members were convicted under the country’s vague Anti-Terrorism Proclamation of 2009.The security forces responded to protests by the Muslim community in Oromia and Addis Ababa, the capital, with arbitrary arrests, detentions, and beatings.
The Ethiopian government continues to implement its “villagization” program: the resettlement of 1.5 million rural villagers in five regions of Ethiopia ostensibly to increase their access to basic services. Many villagers in Gambella region have been forcibly displaced, causing considerable hardship. The government is also forcibly displacing indigenous pastoral communities in Ethiopia’s Lower Omo Valley to make way for state-run sugar plantations.
Freedom of Expression, Association, and Assembly
Since the promulgation in 2009 of the Charities and Societies Proclamation (CSO Law), which regulates nongovernmental organizations, and the AntiTerrorism Proclamation, freedom of expression, assembly, and association have been increasingly restricted in Ethiopia. The effect of these two laws, coupled with the government’s widespread and persistent harassment, threats, and intimidation of civil society activists, journalists, and others who comment on sensitive issues or express views critical of government policy, has been severe.  Ethiopia’s most important human rights groups have been compelled to dramatically scale-down operations or remove human rights activities from their man dates, and an unknown number of organizations have closed entirely. Several of the country’s most experienced and reputable human rights activists have fled the country due to threats. The environment is equally hostile for independent media: more journalists have fled Ethiopia than any other country in the world due to threats and intimidation in the last decade—at least 79, according to the Committee to Protect Journalists (CPJ).
The Anti-Terrorism Proclamation is being used to target perceived opponents, stifle dissent, and silence journalists. In 2012, 30 political activists, opposition party members, and journalists were convicted on vaguely defined terrorism offenses. Eleven journalists have been convicted under the law since 2011.
On January 26, a court in Addis Ababa sentenced both deputy editor Woubshet Taye and columnist Reeyot Alemu of the now-defunct weekly Awramaba Times to 14 years in prison. Reeyot’s sentence was later reduced to five years upon
appeal and most of the charges were dropped.
On July 13, veteran journalist and blogger Eskinder Nega, who won the prestigious PEN America Freedom to Write Award in April, was sentenced to 18 years in prison along with other journalists, opposition party members, and political
activists. Exiled journalists Abiye Teklemariam and Mesfin Negash were sentenced to eight years each in absentia under a provision of the Anti-Terrorism Law that has so far only been used against journalists. Andualem Arage, a member of the registered opposition party Unity for Democracy and Justice (UDJ), was sentenced to life for espionage, “disrupting the constitutional order,” and recruitment and training to commit terrorist acts.
In September, the Ethiopian Federal High Court ordered the property of Eskinder Nega, exiled journalist Abebe Belew, and opposition member Andualem Arage to be confiscated.
On July 20, after the government claimed that reports by the newspaper Feteh on Muslim protests and the prime minister’s health would endanger national security, it seized the entire print run of the paper. On August 24, Feteh’s editor, Temesghen Desalegn was arrested and denied bail. He was released on August 28, and all the charges were withdrawn pending further investigation.
Police on July 20 raided the home of journalist Yesuf Getachew, editor-in-chief of the popular Muslim magazine Yemuslimoche Guday (Muslim Affairs), and arrested him that night. The magazine has not been published since, and at this writing, Yesuf remained in detention.
On December 27, 2011, two Swedish journalists, Martin Schibbye and Johan Persson, were found guilty of supporting a terrorist organization after being arrested while traveling in eastern Ethiopia with the Ogaden National Liberation Front (ONLF), an outlawed armed insurgent group. They were also convicted of entering the country illegally. The court sentenced them to 11 years in prison. On September 10, they were pardoned and released along with more than 1,950 other prisoners as part of Ethiopia’s annual tradition of amnesty to celebrate the Ethiopian New Year.
On several occasions in July, federal police used excessive force, including beatings, to disperse largely Muslim protesters opposing the government’s interference with the country’s Supreme Council of Islamic Affairs. On July 13, police forcibly entered the Awalia mosque in Addis Ababa, smashing windows and firing tear gas inside the mosque. On July 21, they forcibly broke up a sit-in at the mosque. From July 19 to 21, dozens of people were rounded up and 17 prominent leaders were held without charge for over a week. Many of the detainees complained of mistreatment in detention.
Forced Displacement
The Ethiopian government plans to relocate up to 1.5 million people under its “villagization” program, purportedly designed to improve access to basic services by moving people to new villages in Ethiopia’s five lowland regions: Gambella, Benishangul-Gumuz, Afar, Southern Nations Nationalities and Peoples’ Region (SNNPR), and Somali Region.
In Gambella and in the South Omo Valley, forced displacement is taking place without adequate consultation and compensation. In Gambella, Human Rights Watch found that relocations were often forced and that villagers were being moved from fertile to unfertile areas. People sent to the new villages frequently have to clear the land and build their own huts under military supervision, while the promised services (schools, clinics, water pumps) often have not been put in place.
In South Omo, around 200,000 indigenous peoples are being relocated and their land expropriated to make way for state-run sugar plantations. Residents reported being moved by force, seeing their grazing lands flooded or ploughed up, and their access to the Omo River, essential for their survival and way of life, curtailed.
Extrajudicial Executions, Torture and other Abuses in Detention
An Ethiopian government-backed paramilitary force known as the “Liyu Police” executed at least 10 men who were in their custody and killed 9 other villagers in Ethiopia’s Somali Region on March 16 and 17 following a confrontation over an incident in Raqda village, Gashaamo district.
In April, unknown gunmen attacked a commercial farm owned by the Saudi Star company in Gambella that was close to areas that had suffered a high proportion of abuses during the villagization process. In responding to the attack, Ethiopian soldiers went house to house looking for suspected perpetrators and threatening villagers to disclose the whereabouts of the “rebels.” The military arbitrarily arrested many young men and committed torture, rape, and other abuses against scores of villagers while attempting to extract information.
Human Rights Watch continues to document torture at the federal police investigation center known as Maekelawi in Addis Ababa, as well as at regional detention centers and military barracks in Somali Region, Oromia, and Gambella. There is erratic access to legal counsel and insufficient respect for other due process guarantees during detention, pre-trial detention, and trial phases of politically sensitive cases, placing detainees at risk of abuse.
Treatment of Ethiopian Migrant Domestic Workers
The videotaped beating and subsequent suicide on March 14 of Alem Dechasa Desisa, an Ethiopian domestic worker in Lebanon, brought increased scrutiny to the plight of tens of thousands of Ethiopian women working in the Middle East.
Many migrant domestic workers incur heavy debts and face recruitment-related abuses in Ethiopia prior to employment abroad, where they risk a wide range of abuses from long hours of work to slavery-like conditions (see chapters on the
United Arab Emirates, Saudi Arabia, and Lebanon).
Key International Actors
Under Meles Zenawi’s leadership, Ethiopia played an important role in regional affairs: deploying UN peacekeepers to Sudan’s disputed Abyei area, mediating between Sudan and South Sudan, and sending troops into Somalia as part of the international effort to combat al-Shabaab. Ethiopia’s relations with its neighbor Eritrea remain poor following the costly border war of 1998-2000. Eritrea accepted the ruling of an independent boundary commission that awarded it disputed territory; Ethiopia did not.  Ethiopia is an important strategic and security ally for Western governments, and the biggest recipient of development aid in Africa. It now receives approximately US$3.5 billion in long-term development assistance each year. Donor policies do not appear to have been significantly affected by the deteriorating  human rights situation in the country.
The World Bank approved a new Country Partnership Strategy in September that takes little account of the human rights or good governance principles that it and other development agencies say are essential for sustainable development. It also approved a third phase of the Protection of Basic Services program (PBS III) without triggering safeguards on involuntary resettlement and indigenous peoples.

Apr 1, 2013

‹‹…እናትና አባትን የሚለያይ ፖለቲካ…››


ከዘካሪያስ አሳዬ( ኖርዌይ)
እንደሚታወቀው አገራችንን ሊጠብሳት እያዘጋጃት ያለው የ”ጎሳ ፖለቲካ” ደራሲውና ቀማሚው በሞት ቢለዩም
የሚያበርደው አስተዋይ መሪ አልተገኘም እንደውም እርዝራዞቹ የሳቸውን ህራይ እናስቀጥላለን በማለት አብሰውታል፡፡
በማስተዋል ማርከሻውን ለሚቀምሙም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በቂ ጆሮ አልተሰጣቸውም – ጩኸቱ እጅግ
ያደነቁራልና። ከውጪም ከውስጥም የሚረጨው የጎሳና የ”ደም” መርዝ ሳያንስ አሁን ደግሞ በሃይማኖት ተንተርሶ
የተጀመረው አለመግባባት አስደንጋጭ ይዘት እንዳለው አያጠያይቅም። ተወደደም ተጠላም ያስፈራል። ወያኔ/ኢህአዴግ
ባቀናበረው “የድርሰት” ፊልም መነሻ ሳይሆን በበርካታ መረጃዎች የተደገፈ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል።
የሚገርመው ግን እትብታችን በተቀበረችበት በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ፣ ተሰደን ባለንበት አገር ሁለተኛ ዜጋ ! ተሰደን
በምንኖርበት አገር እንኳን የፖለቲካው ሁናቴ የወያኔን የቤት ስራ መቅረፍ ሲገባን እንደውም ያባስነው ይመስለኛል።
የኢህአዴግ/ ወያኔ በብሄር፣ በጎሣ፣ በዘረኝነት የከፋፈላትን አገር መታደግ ሲገባን ዛሬ ደግሞ ተሰደን እራስ በራሳችን
ተከፋፍለን በብሄር የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመን እራስ በራሳችን መሻኮትና ለብሄራችን፣ለዘራችን ነፃነት እንታገላለን ስንል
የወያኔ ስራ ከማስፈፀም ምን ይለያል? ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት አምባገነኑን ስርዓት ጥለን የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን
ባለቤት እናደርጋለን ብለን ካልን ምንድነው ችግራችን? አንድ የማንሆንበት! በእንደዚህ አይነት አካሄዳችን የመቶ አመት
ትግል እንዳያስፈልገን! በብሄር የታመነ ፖለቲካ የትም አያደርስም መጨረሻው ዋጋ ያስከፍላል ኢትዮጵያዊነትን ያልጠበቀ
ትግል ነው ምፃሜውም ያላማረ ነው።በብሄር ብቻ የተደራጀ ፖለቲካ እናትና አባትን የሚለያይ ፖለቲካ ውጤት ነው።
ማንም ሲወለድ ከዚኛው ብሄር ልወለድ ብሎ አልተወለደምና ብሄራችን ውበታችን ነው የመበላለጫ መለኪያ አይደለም!
ደማችን ኢትዮጵያዊነት ነው። ለእኔ ከዘር ቆጠራ እና ከብሔር ነፃ የሆነው የማንነት መገለጫ ኢትዩጵያዊነት ብቻ ነው፡፡
ዛሬ በአገር ቤት ውስጥ ሆነው በኢትዮጵያዊነት ስሜት እየታገሉ ያሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ህዝቡም ዋጋ
እየከፈሉ ባሉበት ወቅት ውጪ ያለው መርዳት፣ ማታገል ሲኖርብን እኛው ውጪ ያለነው ተከፋፈልንና አገራችን ለበይ

ሰጠን! በቃላት ሽኩቻ አንባጓሮ ከፍተን መጣላት ወደድን!
ኢትዮጵያ ውስጥ የሐይማኖት፣ የፖለቲካ፣የጎሳ ችግርች ሲፈጠር እንደ እሳት አደጋ አላርም እየነፉና እየከነፉ መሮጥና
ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ብቻ ግን መሆን የለበትም፡፡መብቴው ማበጀት ያስፈልጋል።መብቴው ደግሞ ልዩነታችንን ወደ
ኋላ ትተን ህዝባችንን መታደግ ነው መሆን ያለበት! ያለበለዚያ ‹‹በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት፣ ይፈራርሳል ‹‹ጅብ የጮኸ
ዕለት…›› እንዳይሆን አንድነታችንም የዘይትና የውሃ አይነት እንዳይሆን ማንም ቢሄድ፣ ማንም ቢመጣ የማይነቃነቅና
መሰረተ ፅኑ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሆኖ እንዲዘልቅ ወደ ታች ወርደን እናጥብቀው፡፡
“ዲሞክራሲ የሚሰራው አውሮፓ ውስጥ ነው፤ የአፍሪካ ባህል የተለየ ነው እንደተባለ፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ
ያለችበትን እንመልከት፡፡ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት አምጥተናል ይላሉ፤ ነገር ግን በትክክል ያመጡት
ጎሰኝነትን ነው፤ሁሉም የተደራጀው በፓርቲ ሳይሆን በጎሳው ወይም በሃይማኖቱ ነው - በሁሉም ቦታ
እንደሚታየው፡፡ በዚህ የተነሳ ዓለም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ጦርነት በአፍሪካ ውስጥ መከሰቱ
አይቀርም ! በኢትዮጵያ ውስጥ አካሄዱም አያምርም ጠንቀቅ ብለን ብንመለከተው ጥሩ ነው አለበለዚያ አደጋው
የከፋ ነው፡፡ አስከፊ ነው የጎሳ ጦርነት!”
ህዝብ ውይይትና ለሚዲያ ፍጆታ ከሆኑት የሰሞኑ ወሬዎች መካከል ሁሉም ለግራ መጋባት የሚዳርጉ ሆነው
አግኝቻቸዋለሁ፡ ፡ አንዳንዱ ግልጽም፣ አስፈላጊም አልነበረም፡፡ ከአደረጃጀት ወሬዎች እንጀምር፡፡ ክላስተር የሚባል ነገር
መጥቷል፡፡ የሥራ ዘርፎችን ቡድኖችን መፍጠርና ተመሳሳይ ሥራዎችን እያሰባሰቡ የማስተባበር፣ የአደረጃጀት አይነት ነው
ፈልሳፊዎቹም ህውሃቶች ናቸው እራሳቸውን ብቻ ለመጥቀም የወጣ አሰራር ነው! መቼም ለህዝብ ሰርተው አያውቁም!
እውነት ነው ፡፡ ስለሁለቱ አዲስ ም/ጠ/ሚኒስትሮችና በድምሩ ሶስት መሆን ተገቢነትና አስፈላጊነት ግራ የተጋባው ዜጋ
ቁጥር ብዙ ነው፡፡ ምሁራን አይስማሙም፤ ተቃዋሚዎች አይደግፉም፡ ፡ የተቀረው ግራ ተጋብቶ መሃል (መስቀለኛ)
መንገድ ላይ ቆሟል፡፡ የተሿሚዎች አመጣጥ ከየትኛውም ብሄር ወይም ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን መሆኑ ፋይዳ
የለውም ብሄሩ ብቻ ሳየሆን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል ።ካለበለዚያ ለእኔ ትርጉም አይሰጠኝም፡፡ ለእኔ ዋናው ጉዳይ
አስፈላጊ ነበር ወይ? የሚለው ነው፡፡ጉልቻው ቢለዋወጥ ለውጥ የለውም! አገሪቱ ራሷ ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትር የሚሸከም
ትከሻ የላትም፡፡
የሌሎች አገሮችን ልምዶች መጠቃቀስ ብቻ አያዋጣም፡፡ እኛ ‹‹እፍ ቢሏት ብን›› በምትል በጣም ዝቅተኛ በጀት (ያውም
ግማሹ ከውጭና ከውስጥ ብድርና እርዳታ ከሚሰበሰብ የምንተዳደር ህዝቦች ነን፡፡ )
በቅርብ ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ቃለ_ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ኤርትራው
መሪ ከኢሳያስ ጋር ለመነጋገር አስመራ ድረስ ለመሄድ መፈለግ በራሱ ግራ የገባ ነገር ነው፡፡አገር ቤት ካሉት የፖለቲካ
ድርጅቶች ጋር ምንም የሚያደራድረን ነገር የለም እያሉ ዲስኩር ሲያረጉም ይሰሙም እንደነበር የሚታወቅ ነው።
ከእነሱ ጋር መታረቅ ለምን ያስፈልገናል? ኢትዮጵያ ለኤርትራ ታስፈልጋታለች፡፡ ኤርትራ ግን ለኢትዮጵያ አታስፈልግም
ማለት ነው? መልሱን ለአንባቢ፡፡ ያው ወደቧ ነው ካላችሁኝ ደግሞ፡ ፡ እሱ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ በእርቅ ስም
መጥተው በለመዱት የበላይነት በተካኑበት እብሪት ሲጨፍሩብን ማየት አንፈልግም፡፡ በገዛ አገራችን የእነሱ መፈንጫ
መሆን አንፈልግም፡ ፡ ያለፈው ይበቃል፡፡ እዛው በጠበላቸው፡፡ አክራሪ (አልቃኢዳ አልሸባብ ወዘተ…) እንዳታስገባብን
ብንታረቅ ይሻላል የሚሉትም ከንቱ ስጋት ነው፡ ፡ የኢሳያስን ጉዳይ ለወያኔ እንጂ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን አያሳስበንም ፡፡
ዛሬ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚኖር ማንኛውም መካከለኛ ገቢ ካለው ዜጋ ይልቅ ተንቀባሮ የሚኖረው የኤርትራ ስደተኛ
ነው፡፡ያግሩ ዜጋማ ሁለተኛ ዜጋ ነው። በእኛ ልጆች ኮታ እነሱ ኮሌጃችን ገብተው ይማራሉ፡፡ እኛ ግን ከእባብ እንቁላል
እርግብ ይፈለፈላል ብለን እንጠብቃለን፡፡ ግራ የገባ ነገር ነው፡፡ ከጎረቤት ጋር ሰላም መፍጠር ተገቢ ቢሆንም ከኤርትራ ጋር
ስላለን ግንኙነት ግን ጊዜ ይፈታዋል ! ኧረ እኛ ማንንም መለየት አልቻንም እኮ ከኢትዮጵያዊነት ደም ይልቅ ሌላ ደም
ይሸታቸዋል ባለስልጣናቱ ተብዬዎች፡፡ የእኛ ችግር ድህነት እንጂ ኤርትራ አይደለችም፡፡ በሁለት ዝሆኖች መካከል ፀብ
ሲፈጠር የሚጎዳው ሳሩ ነው። በተጫረው የድንበር ፀብ ያለቁ ህዝቦቻችንንም እናስታውስ፡፡ መንግስት እያሳየ ያለው ከልክ
ያለፈ ትዕግስት ሊያመጣ የሚችለውን ችግር ከወዲሁ መገመትና መዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡ ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳይገባ
አስቀድሞ መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ በእንቅርት ላይ… እንደሚባለው ማለቂያ ያጣው የወያኔ ግፍ ማለፊው መድረሱ አይቀር!!
ወያኔና ጀሌዎቹ በታላቋ ሀገራችን ኢትዮጽያ ላለፉት 21 ዓመታት የተንሰራፋው የዘር ጥላቻ በማስፈን ነፃ አውጭ ነኝ ባዩ
ቡድን ጠባብ ዓላማውን ለማሳካት ፍቅርን በሰበኩ፤ አንድነትን በመከሩ፤ ስለ እኩሌነት በተናገሩ የዲሞክራሲ ታጋዮችና
ሠላማዊ ዜጎች ላይ ማለቂያ የሌለው ስም በመለጠፍ በእንበለ ፍርድ በየእስር ቤቱ ያጎራቸው ዜጎች ቁጥር ለመጥቀስ

እስኪያዳግት ድረስ በግፍ ላይ ግፍ በበደል ላይ በደል ከመፈጸም ሊታቀብ ይቅርና ጭራሽ እየባሰበት ከመሄድ ሊገታው
የሚችል ሁኔታ ባለመፈጠሩ የጭቆና የብረት ቀንበሩን በሕዝብ ላይ በመጫን ሀገሪቱን በፍጥነት ወደ ታላቅ እስር ቤትነት
ለውጧታል።ኧረ ወገን ምንድን ነው የሚጠበቀው?
በመጨረሻም ወያኔ የዘራውን አይነት የዘር መንፈስ የበላይነትና የበታችነት ስር የሰደደውን የጎሣ ግጭት ማስፋፋት
ልንቃወመው፣ልንታገለውና ልንፋረደው ይገባል። ወያኔ/ህውሃት፣ብአዴን፣ኦህዴድ፣ ደኢሕዴን ወዘተ እያለ እየበታተነ
የዘራው መጥፎ የዘር መንፈስ ሊለያየን ሊበታትነን አይገባም። እናትንና አባትን ሊለያይ የሚችል ፖለቲካ ማለት በብሄር
ተመስርቶ ለብሄሬ ብቻ ነው የምሰራው ካልን ይህ መንፈስ ኢትዮጵያዊነትን አያመላክትም። አባቴ እናቴን ሲያገባት ዘርሽ
ምንድነው ብሎ አላገባትም እኔቴም እንዲሁ ! ኢትዮጵያዊነታቸው በቂ ነው! ዘሩን ለገበሬው እንስጠው! እናትን አባትን
የሚለያይ ፖለቲካ አንስራ !!
ድል በአንድነት ለሚያምኑ ኢትዮጵያውን ሁሉ !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ( edenasaye@yahoo.com)

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ! (ግንቦት 7)

Ginbot 7 press release in Amharic

መግለጫ
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው  ጥላቻና የበቀል ስሜት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ  መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ  መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።
የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ያከበረዉ ወይም የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅሙን ያስጠበቀለት ብሔረሰብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን የወያኔ ዘረኞች የአማራን ህዝብ ከተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ  ነጥለዉ ለማጥቃትና የስነ ልቦና ዘይቤውን ለመስበር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኛ ባለስልጣኖች አማራውን በተከታታይ ሲዘልፉ ቆይተዋል፤አዋርደው  አስረዋል፤ ከአገር እንዲሰደድ አድረገዋል፤ አፈናቅለዋል ገድለዋል።  ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ብቻ አሶሳ፤ በደኖና አርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል።
ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው  ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡና  እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። የወያኔ ባለስልጣኖችና በየአካባቢዉ የኮለኮሏቸዉ ምስለኔዎች አካባቢዉን በግድ እንዲለቅ የተደረገ ህግ አክባሪ ዜጋ የለም፤ የተባረሩት ህግ የጣሱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፣ በማለት አሳፋሪ ድርጊታቸዉን ለመደበቅ ሲሞክሩ ታይተዋል። ሆኖም ከጉራ ፈርዳና ከአካባቢዉ ተፈናቅለዉ ወደ መጣችሁበት አካባቢ ተመለሱ ተብለው በየሜዳው ያለምግብ፣ ውኃና፤መጠለያ የተበተኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ለወገኖቻቸውና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ የድረሱልን ጩኸት ሲያሰሙ መሰንበታቸዉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ።
ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል። ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ተደርገዋል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ቢኖር በገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ዉስጥ  አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዝም ብሎ መመልከቱ ብቻ ሳይሆን ባለፈው አመት ከጉራ ፈርዳ ዘንድሮ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባረሩ እየወጡ ባሉ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ወንጀል ላይ  ተባባሪ መሆኑን አሳይቷል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያደረሰውንና በማድረስ ላይ ያለውን ይህ ነዉ የማይባል ግፍና መከራ ከዚህ ቀደም እንዳደረገዉ ሁሉ አሁንም አጥብቆ ያወግዛል። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ በዚህ በኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የትግል ምእራፍ ውስጥ በደም የተቀባ፣ የቀለመ አኩሪ ታሪክ ያለውን የአማራውን ህዝብ መልሶ መላልሶ የሚያጠቃውና ይህንን ታላቅ ህዝብ ከየቦታዉ የሚያፈናቅለው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከአማራዉ ህዝብ ጋር ብቻ በማያያዝ አገራችንን ለማዳከምና አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ “ምን አገባኝ” ብሎ እንዲመለከት ለማድረግ ባለው እጅግ አደገኛ ዕቅድ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ በጥብቅ ያሳስባል።
ከዚህም በተጨማሪ በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ  ያላችሁ  ወንጀለኞችና ተባባሪዎች፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት   በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።
በአማራው የደረሰው ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያውያን  ዜጎች ጥቃት ነው እንላለን።  ግንቦት ሰባት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበትን ነጻነት የምናስጠብቀው በህብረት ነውና ወያኔ በአሁኑ ግዜ በአማራው ወገናችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ፤ መከራና መፈናቀል በእያንዳንዳችን ላይ እንደደረሰ በመቁጠር ይህንን ግፍ በመፈጸም የማይሰለቸውን ዘረኛ አገዛዝ በተባበረ ህዝባዊ ትግል ከአገራችን ለማስወገድ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል ጥሪ ያስተላልፋል።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
መጋቢት 2005 ዓ. ም

Mar 31, 2013

ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!

“ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን እንታገል”

azebb mesfin

ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው።
በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ የሚያመላክት ንግግር አድርገዋል።
መለስ ደመወዛቸው ስድስት ሺህ ብር እንደሆነ፣ ሁለት ሺህ ብር ሲቆረጥ አራት ሺህ እንደሚቀርና “ይህችኑ ገንዘብ” እየተቀበሉ ላገር ሲሰሩ ያለፉ መሪ መሆናቸውን ያወሱት ባለቤታቸው፣ ለመለስ ዝክረ-መወደስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ይህ መካተት ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
“መለስ ጭንቅላቱን ይዞ ወደዚህች ዓለም መጣ፣ ለዚህች ዓለም፣ አገር፣ ምድር፣ የምታገለግል ሃሳብ አመነጨ” ያሉት ወ/ሮ አዜብ፣ ባለቤታቸው ግለኝነት ሳይፈታተናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን በመርሳት፣ ላገራቸው የለፉና ድህነትን ሲዋጉ ኖረው ያለፉ መሪ መሆናቸው ሊረሳ እንደማይገባው አመልክተዋል። አያይዘውም ሊተኩ የሚችሉ መሪ እንዳልሆኑ በማሳሰብ ዝክረ-መወድሱ ከአቶ መለስ የሕይወት ጉዞ ብዙ ቁምነገሮችን የዘለለና ያልተሟላ ነው ብለውታል፡፡ እንዲሁም መለስ የኢትዮጵያ መሪም ብቻ ሳይሆኑ የአዲስ ራዕይ መጽሄት አዘጋጅ መሆናቸው አለመጠቆሙ አግባብ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የተገኙ የድርጅት አባላት እርስ በርሳቸው ሲለዋወጡ የነበረውን የተከታተሉና በግልጽ ከስርዓቱ ባህርይ በመነሳት ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ እንዳሉት ወ/ሮ አዜብ የቀድሞው ስብዕናቸው አብሯቸው የለም። እንዲያውም በጭንቀት ውስጥ ያሉ ይመስላሉ ብለዋል።
በድርጅቱ አባላት ከላይ እስከታች የባለቤታቸውን ስልጣን ተገን በማድረግ በጣልቃ ገብነታቸውና ከፍተኛ የሚባል ንብረት በማካበት የሚታሙት ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ስም በመደጋገም የሚያነሱት የሚታሙበትን ጉዳይ ለማስረሳት እንደሆነ እርስ በርስ በእረፍት ሰዓት ይወራ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ተናግረዋል።
“ሴትየዋ በግልጽ ስለሚነሳባት ጉዳይ ለምን አትናገርም” በማለት የጠየቁ እንዳሉ፣ ከዚህም በላይ በድርጅቱ ውስጥ ነግሷል የሚባለው ሙስና በግልጽ ለምን አጀንዳ ሆኖ እንደማይቀርብ አባሉ ውስጥ ውስጡን ሲያወራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በትክክለኛው መንግድ ለመታደስና ለመጥራት የሙስና ጉዳይ የድርጅቱ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበት አስተያየት የሰጡም አሉ።
ወ/ሮ አዜብ ይህ ገብቷቸው ይሁን አይሁን ስለ ባለቤታቸው ድህነት ሲናገሩ “እንደሚባለው ሳይሆን እኛ እንኮራበታለን” ማለታቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ስጋት ስለገባቸው የአባሉን ልብ ለማራራት እንደሆነ አድርገው የወሰዱትም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በግልጽ ባያብራሩትም “እንደሚባለው” ብለው በመጥቀስ በይፋ እስከማስተባበል መድረሳቸው በባለቤታቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ራሳቸውም የተረዱት አይመስልም፡፡
አቶ መለስ ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በሚያገኙት መድረክ ስለ ባለቤታቸው ድህነትና ያለ እረፍት ያለፉ መሪ በማድረግ በስፋት የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ፤ ባለቤታቸውን ዴሞክራት መሪ አድርገው ቢስሉም ሪፖርተር በፖለቲካ አምዱ ያስነበበው እውነተኛ ታሪክ የስጋታቸውና የፍርሃታቸው መነሻ እንደሚሆን ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ። ሪፖርተር ወ/ሮ አዜብን በስም ባይጠቅስም፣ “መሐንዲስ አልባው መተካካት” በሚል ርዕስ በጻፈው “(መለስ) በተለያዩ ጊዜያቶች የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ከፖለቲካ ጨዋታ ውጪ ማድረግ ቢችሉም፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ሥልጣን የግላቸው አልነበረም፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ሆነው የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉ ሰውም አልነበሩም፡፡ በወቅቱ የሕወሓት መሰንጠቅን ተከትሎ የድርጅቱ ርዕዮተ ዓለም ቁንጮ (አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም) የወታደራዊ ስትራቴጂ ባለቤት (የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ)፣ የፕሮፓጋንዳ ኃላፊው (የቀድሞ የትግራይ ፕሬዚዳንት አቶ ገብሩ አስራት) እና ሌሎች የድርጅቱ ከ10 በላይ ከፍተኛ አመራሮች መወገድን አስከትሏል፡፡ የእነዚህ የድርጅቱ ወሳኝ ሰዎች መወገድን ተከትሎ በመንግሥትም ሆነ በፓርቲ ሥልጣናቸውን የተደላደለና ምንም የፖለቲካ ተቀናቃኝ የሌላቸው ሰው መሆን የቻሉበት ጊዜ ነበር፡፡ የፈለጉትን ሕግ ማውጣት ያልፈለጉትን የመደቆስ ሥልጣኑም ጉልበቱም ነበራቸው” ሲል ሪፖርተር የጻፈላቸው አቶ መለስን ተገን በማድረግ ወ/ሮ አዜብ በሃብት፣ በጣልቃገብነት፣ በተለያዩ ውሳኔዎች፣ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቆየታቸው በርካታ ወዳጅ ያፈራላቸው ባለመሆኑ የስጋታቸው መጠን ሰፊና ጥልቅ እንደሆነ በስፋት አስተያየት እየተሰጠበት ነው።

የአረብ አገር ተጓዦች ፅንስ በማቋረጥ ለጉዳት እየተጋለጡ ነው!

ሰላም ገረመው
ፒያሳ በሚገኘው ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ክሊኒክ አካባቢ በቋሚነት የሚያንዣብቡት ደላሎች ወደክሊኒኩ የሚያመሩ የመሰሏቸውን ወጣት እንስቶች አያሳልፉም “ክሊኒኩ ተዘግቷል፤ ወዴት ናችሁ?” በማለት በጥያቄ ጣድፋሉ፡፡ ከቀናቸውና የሚያነጋግራቸው ካገኙ የክሊኒኩ ዋና ዶክተር የግሉን ክሊኒክ ስለከፈተ እዛ ልውሠድሽ” በማለት ማግባባት ይጀምራሉ፡፡ አሁንም ከተሳካላቸው (በአብዛኛው ይሳካላቸዋል) አገልግሎት ፈላጊዋን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ የሚካሄድበት ቦታ (መንደር ውስጥ) ይወስዳሉ፡፡ በዚህ ሰዓት ደላሎቹ የሚያሳዩት ትህትናና ሽቁጥቁጥነት ማንኛዋም ሴት ለክፉ አደጋ ወደሚዳርጋት ሥፍራ ይወስዱኛል ብላ እንዳታስብ ያደርጋታል፡፡ ፅንስ ማቋረጥ የሚፈፀምበት ቦታ ከወሰዳት በኋላም ምናልባት በክፍያ ላትስማማ ትችላለች፡፡ ይኼኔ ደላላው መሀል በመግባት ያደራድራል፡፡ ይሄ ደግሞ የደላላውን የኮሚሽን ክፍያ ይጨምርለታል፡፡ ደላላው ሁሉን ደማምሮ ኮሚሽኑን ተቀበለ በኋላ እብስ ይላል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ክፉና ደግ ደግሞ ገባሁ፡፡ ደላላውም ተከትሎኝ ገባ፡፡ የሃኪሙ ጭ ቀለም የተቀባ የሚመስል ጠረጴዛ ለዓይን እንኳን ይዘገንናል፡፡ መሀሉ የተቦረቸፈ ስትሬቸር ግድግዳው ጥግ ይታየኛል፡፡ የእርግዝና ማዳመጫ መሳሪያ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡ በቃ እኒሁ ናቸው የህክምና ቁሳቁሶቹ - ሌላ ነገር የለም፡፡ “ስንት ወርሽ ነው?” ሃኪሙ ጠየቀኝ“አራት ወር ገደማ ይሆነኛል” አልኩት- የውሸቴን መሆኑ ንዳይታወቅብኝ በመጠንቀቅ ችግር የለም እስከ ሠባት ወር እንሠራለን ---- ትንሽ ግን ክፍያው ወደድብሻል” አለኝ ሃኪሙ“እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ---- ጓደኛዬ ነው የሚከፍልልኝ፤ዋጋውን ንገረኝና ገንዘቡን ተቀብዬው እመጣለሁ” “እሺ አራት ወር ከሆነሽ ሠባት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤በመድሃኒት ወይም በማሽን ይሰራልሻል፤ ብሩ ተወደደብኝ ካልሽ ደግሞ በግሉኮስ ላስቲክ ሊሰራልሽ ይችላል” ሲለኝ የእያንዳንዱን ዋጋ እንዲነግረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱም ማብራራቱን ቀጠለ በመድሃኒት ለሚሠራው ነው ሠባት መቶ ብር ያልኩሽ፤ በማሽን ከሆነ ስድስት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤ በግሉኮስ ሶስት መቶ ብር” ከጓደኛዬ ጋር ልምከርበት አልኩትና ሙን አመሥግኜው ወጣሁ፡፡ ከቤቱ እንደወጣን “ቤቱ ደስ አላለኝም” በሚል ሰበብ ወንዱ ሌላ ቦታ እንዲወስደኝ ጠየቅሁት፡ “ችግር የለም” አለኝና መንገዳችንን ቀጠልን - ወደ ሁለተኛው አማራጭ፡፡ ብዙም ሳንደክም ነው የደረስነው፡፡ “በርጌስ ክሊኒክ” የሚል ማስታወቂያ ያለበት የህክምና ተቋም ውስጥ ይዞኝ ገባ - ፈቃዴን ከጠየቀኝ በኋላ፡፡ ክሊኒኩ መጀመሪያ ከገባንበት ቦታ በንፅህና አስር እጅ የተሻለ ነው፡፡ ታካሚዎች ተራ ይጠብቃሉ፡፡ ወንዱ ልክ እንደጓደኛው እጄን ይዞኝ ካርድ ክፍል ሠራተኞች ምልክት ሠጥቷቸው ወደ ሃኪሙ ክፍል ወሰደኝ፡፡ ታዳጊው ደላላ ለክሊኒኩ ቤተኛ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ ይሄኛው እንኳን የክሊኒክም ወግ አለው፡፡ የተራቀቁና ዘመን አመጣሽ ባይሆኑም የተለመዱት የህክምና መሳሪያዎች ይታያሉ፡፡ ዶክተሩ ወንዱን ስላየ ነው መሠለኝ በቀጥታ “ስንት ወርሽ ነው?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “አራት ወሯ ነው፤ ጓደኛዋ አደራ ብሎኝ ነው” ሲል ወንዱ ፈጠን ብሎ መለሰ “እሺ አሁን ትሠሪያለሽ?” የዶክተሩ ጥያቄ ነበር ጋውን እንዲነግረኝ እና ከጓደኛዬ ጋር ተማክሬ “እዚህ ክሊኒክ ግሉኮስ የሚባል ነገር የለም፤ ዋጋው ደግሞ አንድ ሺህ ሠባት መቶ ብር ነው” አለኝ ፍርጥም ብሎ፡፡ ከሃኪሙ ክፍል እንደወጣን ለወንዱ የፍርሃት ስሜት ውስጥ እንደገባሁና እዚህ ክሊኒክ ውስጥ ያሰራች አንዲት ሴት ባገኝ ሁኔታውን ጠይቄያት እንደምደፋፈር ነገርኩት፡፡ እኔ ግን የፈለግሁት ሊያሰሩ የመጡ ሴቶችን ለማነጋገር ነበር፡፡ ወንዱም ያልኩትን ለመፈፀም ለአፍታ እንኳ ሳያመነታ “ተከተይኝ” ብሎ ይዞኝ ሄደ፡፡ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው የሚያቃስቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ባሉ አልጋዎች ላይ በሆዳቸውየተኙም ሴቶች ተመልክቼአለሁ፡፡ ወደ አንዷ ሴት  ጋ አልኩና ጠየቅኋት “ህመሙ ለትንሽ ደቂቃ ነው አትፍሪ” የሚል ማበረታቺያ ሰጠችኝ፡፡ “የስንት ወር ነው ያሰራሽው?” አልኳት፡፡ “እኔ መውለድ ነበር የምፈልገው፤ሆኖም የአረብ አገር ቪዛ መጣልኝና ላስወርድ ፈለግሁኝ፤ ሜሪስቶፕስ ሄጄ ወርሽ ገፍቷል አንሰራም ሲሉኝ ደላላው ወደዚህ አመጣኝ” አለችኝ፡፡ ልጅቱ በነበረችበት ክፍል ውስጥ 18 ሴቶች ነበሩ፡፡ ዘጠኙ ወደ አረብ አገር የሚሔዱ ናቸው፡፡ የዕለቱ ዕለትና በንጋታው የሚበሩ ሴቶችም ነበሩ፡፡ ከክፍሉ ስንወጣ ለደላላው ሀያ ብር ሠጠሁትና ስልኩን ተቀብዬ እንደምደውልለት ነግሬው ተለያየን፡፡ በዚያው ሰሞን በአንድ የዘመድ ለቅሶ ላይ በሜሪስቶፕስ ክሊኒክ ውስጥ የምትሰራ አንዲት ሲስተር አገኘሁና በፅንስ ማቋረጥ ዙሪያ አንዳንድ ነገር ተጨዋወትን፡፡ ሲስተሯ እንደነገረችኝ ወደ ክሊኒኩ ፅንስ ለማቋረጥ ከሚመጡ ሴቶች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ናቸው፡፡ እሷን የሚያስጨንቃት ታዲያ ሦስት ወር ከሆናቸው በኋላ ወደክሊኒኩ መጥተው የሚመልሷቸው ነፍሰጡር ሴቶች ጉዳይ ነው፡፡ ክሊኒኩ ከፀነሱ ሦስት ወር ለሞላቸው እንስቶች አገልግሎት እንደማይሰጥሲ ግራቸው፤ ወደ ህገወጥ ቦታ መሄዳቸው ክፉኛ  ንደሚያሳስባት ትናገራለች፡፡አንዲት ሴት እስከ ሁለት ወር የሚደርስ ፅንስ በመድሀኒት ማቋረጥ ትችላለች፡፡ አንድ ፍሬ ክኒን በመጀመርያው ቀን ትውጥና በሶስተኛው ቀን ደግሞ አራት ፍሬ እንድትውጥ ይደረጋል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ግን መድሃኒቱን አይመርጡም፡፡” ያለችው ሲስተሯ፤ ምክንያቱን ስንጠይቃቸው አረብ አገር ስለሚሄዱ እንደሆነ ይነግሩናል ትላለች፡፡ አንዳንዶቹ ግን ፅንሱ በመጀመሪያ በዋጡት መድሃኒት ብቻ የሚወርድ ስለሚመስላቸው በዛው ይቀራሉ፤ ይሔ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብላለች፡፡ “አንዳንዶቹ እንደውም የሔዱበት አገር ተመርምረው ነፍሠ ጡር መሆናቸው ሲታወቅ ተመልሠው ይመጣሉ፤ይሔም ሌላ ኪሳራ ነው” የምትለው ባለሙያዋ፤ አረብ አገር እሄዳለሁ ብላ ፅንስ ለማቋረጥ የመጣች አንዲት ሴት የገጠማትን አሳዛኝ አደጋ ታስታውሳለች፡፡ “ልጅቷ ወደ አረብ አገር ልትሄድ ስትል ነው ለማስጠረግ የመጣችው፤ ቀኗ በመግፋቱአንሠራምአልናትና ሌላም ቦታ መሄድ እንደሌለባት መክረን ሸኘናት፤ እሷ ግን ባህላዊ ፅንስ የማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ በመሄድ በሠጧት የግሉኮስ ላስቲክ ምክንያት ማህፀኗ በመበሳቱ፤ደሟ ወደ ሆዷ ፈስሶ ህይወቷ አለፈ” ብላለች - ሲስተሯ፡፡ ተዘዋውሬ ባየኋቸው የሜሪስቶፕስ ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ፈላጊዎች ወደአረብ አገር የሚጓዙ ሴቶች መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት በቀን ጥቂት ሴቶችን ብቻ ያስተናግዱ የነበሩ የክሊኒኩ ቅርንጫፎች፤ አሁን ከአቅማቸው በላይ እየሆነባቸው ቀጠሮ እስከ መስጠት ደርሠዋል፡፡ ክሊኒኩን ያጨናነቁት በዋናነት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ቢሆኑም ክሊኒኩ በፊት ከሚሠጠው በማሽን የመጥረግ አገልግሎት በተጨማሪ በመድሀኒት የመጥረግ አገልግሎት  ጀመሩም የተጠቃሚዎቹን ቁጥር እንደጨመረው ሲስተሯ ትናገራለች፡፡ “በመድሃኒት ፅንስ ማቋረጥን ብዙዎች እንደጨዋታ ነው የሚያዩት፤ ምክንያቱም እምብዛም የህመም ስሜት የለውም” የምትለው ጊዜ “በጣም ነው የምወዳችሁ!” እያሉ በመወሻከት ቁርጥ ቀን ሲመጣ “ልጄ ሁሉም ለራሱ ነው!” ብሎ ነገር የለም፡፡ ፀማይ የእውነት ምድር ነው፡፡ መውደድ ንዳይረክስ በቃል አይጠራም፤ በተግባር ነው የሚገለፀው፡፡ እነዚህን ሁሉ በረከቶች አግኝቷል፡፡ ፀማይ ሰላም ነው! በፀማይ ኮረብቶች፣ በፀማይ ሜዳዎች ላይ ቀን ከምሽት ሳይመርጥ ሲንጐራደድ፣ አፉ ውስጥ የቀረች አንዲት ግጥምን እንደ ብሔራዊ መዝሙር ይደጋግማታል፡፡“ፍላጐት ምኞትህ ወደብ ድንበር አለው?ብለህ አትጠይቀኝ ህልሜ አንተን መሆን ነው!ያለ ስም ቅጥያ ግቤ ሰው መሆን ነው፡፡ሰው መሆን! ሰው መሆን! በቃ ነፃ መሆን!ግጥሟ የአንድ ፋርሳዊ ፀሃፊ ነው ብሎ ጓደኛው ነበር በቃሉ ያስጠናው፡፡ ነፃ ሰው የመሆን ስሜቱን በፀማይ አፈር፣ በፀማይ አየር፣ በፀማይ ሰዎች መካከል አግኝቶታል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከኦሞ ወንዝ ጋር የማይደበዝዝ ፍቅር አዳብሮ ነበር፡፡ኦሞን እንደሰው እያዋራ፣ በኦሞ የቅዝቃዜ በረከት ሲረሰርስ፣ በኦሞ ፈሳሽ ውሃ ሲዳሰስ ዘላለማዊ መኖሪያው በኦሞ ዳርቻ እንደሚሆን ወስኖ ነበር፡፡ በሰለሞን ውሳኔ ግን ኦሞ የተስማማ አይመስልም፡፡ እጣውን ኦሞ እራሱ ፅፎ ሰጠው፡፡ እጣ ደግሞ የሚመርጡት ሳይሆን የሚወጣ ነው፡፡ በአንድ ወበቃማ ቀን ሰለሞን ወደ ኦሞ ሲወርድ ለሁለት ወራት ያህል ከውሀው ሲገባ ለወትሮ ሚያገኘውን ደስታ በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ወደ ወንዙ የሚያመራውን ጉብታ ቁልቁል እያቋረጠ ሳለ ግን የድረሱልኝ የሚመስል ድምፅ የሰማ መሰለው፡፡ እየሮጠ ወደ ወንዙ ደረሰ፡፡ ብቅ ጥልቅ የሚል ሰው ታየው፡፡ በውሀው ላለመወሰድ የሚታገል፡፡ዘሎ ከውሀው ገባ፡፡ የውሃውን ሃይል እየታገለ ሰው ወዳየበት አቅጣጫ ተምዘገዘገ፡፡ ያየውን ሰው እጅ እንዳገኘ ሽቅብ ገፋው እና ከውሀው በላይ አደረገው፡፡ በአንድ እጁ እየዋኘ ወደ ወንዙ ዳር ተጠጋ፡፡ ኦሞ እንደለማዳ ፈረስ እሺ ብሎ የሚጋልብለት ይመስል በቀላሉ አቋረጠው፡፡ የተሸከመውን ሰው አውጥቶ ከወንዙ ዳር አስተኛው፡፡ በውሀ ሊወሰድ የነበረው ሰው ግዙፍ ወንድ ነበር - ፈረንጅ! ከአለባበሱ ቱሪስት እንደሆነ ገምቷል፡፡ ከነልብሱ ምን ሊያደርግ ኦሞ ውስጥ እንደገባ ለሰለሞን ሊገባው አልቻለም፡፡“እንደኔ የከተማ ቱማታ ናላውን ያዞረው ይሆናል!” ብሎ እያሰበ ሳለ፣ የፈረንጁን ጩኸት የሰሙ ፀማዮች እየተጠራሩ ከቦታው ደረሱ፡፡ የሰውዬውን ደረት እየተጫኑ ከሆዱ የገባውን ውሀ ሲያስወጡለት ቀስ በቀስ ነፍስ ዘራ፡፡ሰለሞን የሰው ነፍስ ማትረፍ መቻሉ ከፍተኛ ደስታ አጐናፅፎት ነበር፡፡ የፀማዮች ተደጋጋሚ የምስጋና ቃል ሲቸረው በሙሉ ልብ ሲቀበል ቆየ፡፡ ያረፈባት ቤት ፈረንጁን ከውሀ ውስጥ መንጥቆ ያወጣውን ጀግና ለማየት ከአቅራቢያ መንደሮች ጭምር በሚመጡ እንግዶች እስከምሽት ድረስ ተጨናነቀች፡፡ የሰለሞን ዝና በአንድ ምሽት ፀማይን አልፎ ጅንካ ደረሰ፡፡ ከጅንካ ምድር አልፎ አዋሳ ለመድረስ አንድ ቀን አልፈጀበትም፡፡ ከአዋሳ አዲስ አበባ በዚያው ቀን ምሽት ዜናው ተሰራጨ፡፡የጋዜጠኞች ቡድን ካሜራ እና ማይኩን ደቅኖ ጀርመናዊውን ቱሪስት ያዳነውን ጀግና ለማየት ወደ ፀማይ አመራ፡፡ሰለሞን ከከተማ የመጡ ሰዎች ሊያናግሩት እንደሚፈልጉ በብሔረሰቡ አባት ሲነገረው፤ ብዙም ደስ ባይለውም እሳቸውን ላለማስቀየም ወጥቶ መጡትን ሰዎች ማነጋገር ነበረበት፡፡“ለመንደራችን ልዩ ሲሳይ ነው ይዘህ የመጣኸው!... አሁንም ከከተማ ትላልቅ ሰዎች አንተን ለማነጋገር መጥተዋል፡፡ እንደምታየው መንደራችን ብዙም አላደገችም፡፡ አንተ የሰራኸው ስራ መንደራችንን ለማስተዋወቅ ጠቃሚ ነው!” የሚለው ንግግራቸው ይበልጥ አሳማኝ ሆነለት፡፡ ጋዜጠኞቹ ሰለሞንን ሲያዩ አይናቸውን ተጠራጥረው ነበር፡፡ ከመካከላቸው አንዱ፤“ዝነኛው አርቲስት ሰለሞን?” አለ ባለማመን ስሜት ተውጦሰለሞን በአዎንታ እራሱን ነቀነቀ፡፡የፎቶ ካሜራዎች ብልጭታ ከየቦታው ሲተኮስበት፣ የካሜራዎች እይታ እሱ ላይ ሲያነጣጥርበት አንድ ነገር ገባው፡፡ ዝነኝነት ምርጫው ባይሆንም እጣው ነበረ፡፡ ቢሸሽ የማያመልጠው! እንደ ጥላ!ዝነኛው ከገፅ 17 የዞረየምትቀበለው እንስቷ ብቻ ናት፡፡በዚህ ዓይነቱ የድለላ ስራ ላይ የተሠማራው የ16 አመቱ ታዳጊ ወንዱ (ጩቤ በሚል ቅፅል ስሙ ይበልጥ ይታወቃል) በቀን ከ8-10 የሚደርሱ ወጣት እንስቶችን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ ወደሚፈፀምባቸው ሥፍራዎች እንደሚወስድ ይናገራል፡፡ ወንዱ እንደሌሎች ደላሎች “ክሊኒኩ ተዘግቷል” አይልም፡፡ በክሊኒኩ ሲሰሩ የነበሩ ዕውቅ ዶክተሮች የራሳቸውን ክሊኒክ ከፍተው መውጣታቸውንና አሁን ያሉት ተማሪዎች (ተለማማጅ ሃኪሞች) ስለሆኑ “እንዳያበላሿችሁ” በሚል እያስፈራራ ጭምር ነው ሴቶችን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ወደሚሰጡባቸው ሥፍራዎች አግባብቶ የሚወስደው፡፡ይሄ ደላላ አንደበቱን አምነው የተከተሉትን ተላላ ሴቶች፤ እሪ በከንቱ አካባቢ ወደሚገኝ ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ የሚካሄድበት ሥፍራ ይወስዳቸዋል፡፡ እኔ ወደዚህ ሥፍራ ልሄድ የቻልኩት ሜሪስቶፕስ አካባቢ ወንዱን አግኝቼው የአራት ወር ነፍሠጡር መሆኔን ከነገርኩት በኋላ ነው፡፡ እሪበከንቱ አካባቢ ስደርስ ግን አንድም ክሊኒክ የሚመስል ነገር አላገኘሁም፡፡ ሆኖም ደላላው ይሄ ዓይነቱ ጥያቄ ከእንስቶቹ ከመምጣቱ በፊት እያዋከበ በጭቃ የተሠራ ቤት ውስጥ ይዟቸው ዘው ይላል፡፡ ቤቱ ለእንስቶቹ እንጂ ወንዱን ለመሰሉ ደላሎች አዲስ አይደለም፡፡ በዚህ ቤት ውስጥ አንዲት ካርድ የምትሰጥ ሴት፣ አንድ ሃኪምና የፅንስ ማቋረጡን የሚሰራ “ባለሙያ” መኖራቸውን አይቼአለሁ፡፡ ቤቷ አንዲት ክፍል ብትሆንም በአቡጀዲ ጨርቅ ሦስት ቦታ ተከፋፍላለች - ሦስት ክፍሎች ለመፍጠር፡፡ ወደዚህች ቤት እንደገባን በወንዱ መሪነት ለካርድ ሀያ ብር ከፍዬ ከተደረደሩት ወንበሮች በአንደኛው ላይ ተቀመጥን፡፡ ከጎኔ ሁለት የምኒሊክ ት/ቤት ዩኒፎርም የለበሱ ወጣት እንስቶች ተቀምጠው ነበር፡፡ ጠጋ ብዬ ለምን እንደመጡ ጠየቅኋቸው፡፡ ጓደኛቸው አርግዛ ለማስወረድ ይዘዋት እንደመጡና ሃኪሙን ልታነጋግር ወደውስጥ እንደገባች ነገሩኝ፡፡ “አያስፈራም?” ስል ጠየቅኋቸው፡፡ እንደማያስፈራ ከነገሩኝ በኋላ የተለያዩ አማራጮች እንዳሉና አንዱን መምረጥ እንዳለብኝ ምክር ቢጤ ለገሱኝ፡፡ ወዲያው ጓደኛቸው ሃኪሙን አናግራ በመውጣቷ በተራዬ እኔደግሞ ገባሁ፡፡ ደላላውም ተከትሎኝ ገባ፡፡ የሃኪሙ ነጭ ቀለም የተቀባ የሚመስል ጠረጴዛ ለዓይን እንኳን ይዘገንናል፡፡ መሀሉ የተቦረቸፈ ስትሬቸር ግድግዳው ጥግ ይታየኛል፡፡ የእርግዝና ማዳመጫ መሳሪያ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡ በቃ እኒሁ ናቸው የህክምና ቁሳቁሶቹ - ሌላ ነገር የለም፡፡ “ስንት ወርሽ ነው?” ሃኪሙ ጠየቀኝ“አራት ወር ገደማ ይሆነኛል” አልኩት- የውሸቴን መሆኑ እንዳይታወቅብኝ በመጠንቀቅ “ችግር የለም እስከ ሠባት ወር እንሠራለን ---- ትንሽ ግን ክፍያው ይወደድብሻል” አለኝ ሃኪሙ “እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ---- ጓደኛዬ ነው የሚከፍልልኝ፤ዋጋውን ንገረኝና ገንዘቡን ተቀብዬው እመጣለሁ” 
“እሺ አራት ወር ከሆነሽ ሠባት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤በመድሃኒት ወይም በማሽን ይሰራልሻል፤ ብሩ ተወደደብኝ ካልሽ ደግሞ በግሉኮስ ላስቲክ ሊሰራልሽ ይችላል” ሲለኝ የእያንዳንዱን ዋጋ 
እንዲነግረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱም ማብራራቱን ቀጠለ “በመድሃኒት ለሚሠራው ነው ሠባት መቶ ብር ያልኩሽ፤ በማሽን ከሆነ ስድስት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤ በግሉኮስ ሶስት መቶ ብር” ከጓደኛዬ ጋር ልምከርበት አልኩትና ሃኪሙን አመሥግኜው ወጣሁ፡፡ ከቤቱ እንደወጣን “ቤቱ ደስ አላለኝም” በሚል ሰበብ ወንዱ ሌላ ቦታ እንዲወስደኝ ጠየቅሁት፡፡ “ችግር የለም” አለኝና መንገዳችንን ቀጠልን - ወደ ሁለተኛው አማራጭ፡፡ ብዙም ሳንደክም ነው የደረስነው፡፡ “በርጌስ ክሊኒክ” የሚል ማስታወቂያ ያለበት የህክምና ተቋም ውስጥ ይዞኝ ገባ - ፈቃዴን ጠየቀኝ በኋላ፡፡ ክሊኒኩ መጀመሪያ ከገባንበት ቦታ በንፅህና አስር እጅ የተሻለ ነው፡፡ ታካሚዎች ተራ ይጠብቃሉ፡፡ ወንዱ ልክ እንደጓደኛው እጄን ይዞኝ ለካርድ ክፍል ሠራተኞች ምልክት ሠጥቷቸው ወደ ኪሙ ክፍል ወሰደኝ፡፡ ታዳጊው ደላላ ለክሊኒኩ ቤተኛ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ ይሄኛው እንኳን የክሊኒክም ወግ አለው፡፡ የተራቀቁና ዘመን አመጣሽ ባይሆኑም የተለመዱት የህክምና መሳሪያዎች ይታያሉ፡፡ ዶክተሩ ወንዱን ስላየ ነው መሠለኝ በቀጥታ “ስንት ወርሽ ነው?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “አራት ወሯ ነው፤ ጓደኛዋ አደራ ብሎኝ ነው” ሲል ወንዱ ፈጠን ብሎ መለሰ እሺ አሁን ትሠሪያለሽ?” የዶክተሩ ጥያቄ ነበርዋጋውን እንዲነግረኝ እና ከጓደኛዬ ጋር ተማክሬ እንደምወስን ገለፅኩለት፡፡ “እዚህ ክሊኒክ ግሉኮስ የሚባል ነገር የለም፤ ዋጋው ደግሞ አንድ ሺህ ሠባት መቶ ብር ነው” አለኝ ፍርጥም ብሎ፡፡ ከሃኪሙ ክፍል እንደወጣን ለወንዱ የፍርሃት ስሜት ውስጥ እንደገባሁና እዚህ ክሊኒክ ውስጥ ያሰራች አንዲት ሴት ባገኝ ሁኔታውን ጠይቄያት እንደምደፋፈር ነገርኩት፡፡ እኔ ግን የፈለግሁት ሊያሰሩ የመጡ ሴቶችን ለማነጋገር ነበር፡፡ ወንዱም ያልኩትን ለመፈፀም ለአፍታ እንኳ ሳያመነታ “ተከተይኝ” ብሎ ይዞኝ ሄደ፡፡ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው የሚያቃስቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ባሉ አልጋዎች ላይ በሆዳቸው የተኙም ሴቶች ተመልክቼአለሁ፡፡ ወደ አንዷ ሴት ጠጋ አልኩና ጠየቅኋት “ህመሙ ለትንሽ ደቂቃ ነው አትፍሪ” የሚል ማበረታቺያ ሰጠችኝ፡፡ “የስንት ወር ነው ያሰራሽው?” አልኳት፡፡ “እኔ መውለድ ነበር የምፈልገው፤ሆኖም የአረብ አገር ቪዛ መጣልኝና ላስወርድ ፈለግሁኝ፤ ሜሪስቶፕስ  ጄ ወርሽ ገፍቷል አንሰራም ሲሉኝ ደላላው ወደዚህ አመጣኝ” አለችኝ፡፡ ልጅቱ በነበረችበት ክፍል ውስጥ 18 ሴቶች ነበሩ፡፡ ዘጠኙ ወደ አረብ አገር የሚሔዱ ናቸው፡፡ የዕለቱ ዕለትና በንጋታው የሚበሩ ሴቶችም ነበሩ፡፡ ከክፍሉ ስንወጣ ለደላላው ሀያ ብር ሠጠሁትና ስልኩን ተቀብዬ እንደምደውልለት ነግሬው ተለያየን፡፡ በዚያው ሰሞን በአንድ የዘመድ ለቅሶ ላይ በሜሪስቶፕስ ክሊኒክ ውስጥ የምትሰራ አንዲት  ስተር አገኘሁና በፅንስ ማቋረጥ ዙሪያ አንዳንድ ነገር ተጨዋወትን፡፡ ሲስተሯ እንደነገረችኝ ወደ ክሊኒኩ ፅንስ ለማቋረጥ ከሚመጡ ሴቶች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ናቸው፡፡ እሷን የሚያስጨንቃት ታዲያ ሦስት ወር ከሆናቸው በኋላ ወደክሊኒኩ መጥተው የሚመልሷቸው ነፍሰጡር ሴቶች ጉዳይ ነው፡፡ ክሊኒኩ ከፀነሱ ሦስት ወር ለሞላቸው እንስቶች አገልግሎት እንደማይሰጥ ሲነግራቸው፤ ወደ ህገወጥ ቦታ መሄዳቸው ክፉኛ እንደሚያሳስባት ትናገራለች፡፡ “አንዲት ሴት እስከ ሁለት ወር የሚደርስ ፅንስ በመድሀኒት ማቋረጥ ትችላለች፡፡ አንድ ፍሬ ክኒን በመጀመርያው ቀን ትውጥና በሶስተኛው ቀን ደግሞ አራት ፍሬ እንድትውጥ ይደረጋል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ግን መድሃኒቱን አይመርጡም፡፡” ያለችው ሲስተሯ፤ ምክንያቱን ስንጠይቃቸው አረብ አገር ስለሚሄዱ እንደሆነ ይነግሩናል ትላለች፡፡ አንዳንዶቹ ግን ፅንሱ በመጀመሪያ በዋጡት መድሃኒት ብቻ የሚወርድ ስለሚመስላቸው በዛው ይቀራሉ፤ ይሔ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብላለች፡፡ “አንዳንዶቹ እንደውም የሔዱበት አገር ተመርምረው ነፍሠ ጡር መሆናቸው ሲታወቅ ተመልሠው ይመጣሉ፤ይሔም ሌላ ኪሳራ ነው” የምትለው ባለሙያዋ፤ አረብ አገር እሄዳለሁ ብላ ፅንስ ለማቋረጥ የመጣች አንዲት ሴት የገጠማትን አሳዛኝ አደጋ ታስታውሳለች፡፡ “ልጅቷ ወደ አረብ አገር ልትሄድ ስትል ነው ለማስጠረግ የመጣችው፤ ኗ በመግፋቱ አንሠራም አልናትና ሌላም ቦታ መሄድ እንደሌለባት መክረን ሸኘናት፤ እሷ ግን ባህላዊ ፅንስ የማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ በመሄድ በሠጧት የግሉኮስ ላስቲክ ምክንያት ማህፀኗ በመበሳቱ፤ደሟ ወደ ሆዷ ፈስሶ ህይወቷ አለፈ” ብላለች - ሲስተሯ፡፡ ተዘዋውሬ ባየኋቸው የሜሪስቶፕስ ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ፈላጊዎች ወደአረብ አገር የሚጓዙ ሴቶች መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት በቀን ጥቂት ሴቶችን ብቻ ያስተናግዱ የነበሩ የክሊኒኩ ቅርንጫፎች፤ አሁን ከአቅማቸው በላይ እየሆነባቸው ቀጠሮ እስከ መስጠት ደርሠዋል፡፡ ክሊኒኩን ያጨናነቁት በዋናነት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ቢሆኑም ክሊኒኩ በፊት ከሚሠጠው በማሽን የመጥረግ አገልግሎት በተጨማሪ በመድሀኒት የመጥረግ አገልግሎት መጀመሩም የተጠቃሚዎቹን ቁጥር እንደጨመረው ሲስተሯ ትናገራለች፡፡ “በመድሃኒት ፅንስ ማቋረጥን ብዙዎች እንደጨዋታ ነው የሚያዩት፤ ምክንያቱም እምብዛም የህመም ስሜት የለውም” የምትለውባለሙያዋ፤ ዋናው ነገር ሴቶች ፅንስ ለማቋረጥ ብለው በየመንደሩ በመሄድ ህይወታቸውን ለአደጋ ከማጋለጥ መቆጠባቸው ነው፤ ማናቸውንም ጉዳዮች የህክምና ባለሙያዎች በማማከር ቢፈፅሙት ራሳቸውን ከሞት አደጋና ከጤና እክሎች ሊጠብቁ ይችላሉ ስትል ትመክራለች፡፡ በአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ዶክተር ገላኔ ሌሊሳ ሲናገሩ፤ ማንኛውም ህክምና በትክክለኛ ባለሙያ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፣ የእርግዝናው እድሜ እየገፋ በመ ቁጥር አደጋዎቹም እየከበዱ እንደሚሄዱ ያስረዳሉ፡፡ አንዲት ሴት በመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ሳምንት የምታደርገው ውርጃዎች ትንሽም ቦሆን ችግር አላቸው ምንኛውም ሴት እስከ ስምንት ሳምንት ያልሞላው ጽንስ አንዳንዴ በተፈጥሮም የሚቋረጥበት አጋጣሚ ይኖራል፤ በህክምናም ሊቋረጥ ይችላል የሚሉት ዶ/ር ገላኔ፤ ይሄ የተለየ ችግር ያመጣል ተብሎ አይታሰብም ብለዋል፡፡ አንዲት ሴት ፅንሷ ከተቋረጠ በኋላ እረፍት ሳታደርግ ለጉዞ ብትነሳ ወይም ወደ ስራ ብትገባ ችግር ያጋጥማታል ማለት አይደለም ያሉት ዶ/ር ገላኔ፣ ነገር ግን ማንኛውም ህክምና ሁሌም ክትትል ያስፈልገዋል፤ ህክምናው ትክክለኛ ውጤት ማስገኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ከህክምና በኋላ፣ እንደተጠበቀው ፅንሱ ሳይቋረጥ ቢቀር በጣም አስጊ ስለሚሆን ክትትል ማድረግ ይኖርባታል ብለዋል ዶ/ር ገላኔ፡፡ የፅንስ ማቋረጥ ህክምና በሁለት መንገድ እንደሚካሄድ ዶ/ር ገላኔ ጠቅሰው፣ አስር ሳምንት ያልሞላው ጽንስ በመድሀኒት ሊቋረጥ ይችላል፤ የፅንሱ እድሜ ከዚህ በላይ ከሆነ ግን የግድ መጠረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ከሁለቱ ዘዴዎች መካከል በመድሃኒት ጽንስ የማቋረጥ ዘዴ ተመራጭ ነው፣ ምክንያቱም ከማህፀን ጋር ምንም ንክኪ ስለሌለው የማህፀን መኮማተርን አያስከትልም፡፡ ስለዚህ ያልተፈለገ እርግዝና ሲከሰት ጊዜው ሳያልፍ ወደ ትክክለኛው የህክምና ባለሙያ መሄድ ያስፈልጋል ሲሉ ዶ/ር ገላኔ ይመክራሉ፡፡ 

Mar 29, 2013

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?

(ምንጭ፡ ፍኖተ ነጻነት)

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡
ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡ ሀገራችንን የባህር በር ማሳጣትን ጨምሮ ሀገራዊ ስሜትን አንኳሶ ጠባብ የብሔር ስሜት እንዲንሰራፋ አድርጓል፣ ታሪክን ለስልጣኑ መደላድል ሲል በራሱ መንገድ የሚያዘጋጀው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያን ጠፍጥፎ እንደሰራት ሁሉ ደርግን ለመጣል ካደረገው ትግል ውጪ ያለውን የአርበኞች ተጋድሎ እውቅና ሲሰጥ አይታይም፡፡
መንግስት ለፋሽስቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተገነባውን ሀውልት በመቃወም የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ሳያንስ ግራዚያኒን ለማውገዝ የወጡ ዜጎችን በመደብደብና በማንገላታት ማሰሩ አሳፍሮናል፡፡ ለዜጎቻቸው እና ለሚመሯት ሀገር ክብር የማይሰጡ ይልቁንም የጦር ወንጀለኛና ፋሺስትን ለመቃወም የወጣን ዜጋ ማሰርራቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወገንተኝነታቸው ለዜጎቻቸው ነው ወይስ ለፋሺስት? የሚል ዘግናኝ ጥያቄ እንድንሰነዝር ያስገድደናል፡፡
በሰልፉ ላይ የተገኙት ሀገር ወዳድ ዜጎች በማን አለብኝነት ሲታሰሩ ድባደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የታሳሪዎቹን የኢሜይልና የማህበራዊ ገፅ የይለፍ ቃል (password) በግዳጅ የሚቀበሉ የደህንነት ሀይሎች ተልከውባቸዋል፡፡ ይህን ቅጥ ያጣ አንባገነናዊ ድርጊት የፈፀመው ወይም እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጠው አካል ማንነት ተጣርቶ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ በየምክንያቱ ዜጎችን ማሰር የለመደው አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ምን ያክል ኢትዮጵያዊነትን እየተዋጋ እንዳለም የሚያሳይ ድርጊት ነው፡፡ መሰረቱ ዜጎች በማንኛውም ጉዳይ ላይ የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ሰልፍ ማድረግ እንደሚችሉ ህገመንግስቱ ደንግጓል፡፡ ይህን መብት ዜጎች እንዳይጠቀሙ ያፈነው መንግስት፣ ኢህአዴግን የሚደግፉ አልያም በራሱ ከተጠሩ ሰልፎች ውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ በአሰራር ከልክሏል፡፡ ይህ የመብት ረገጣ ከመሆኑም በላይ በዜጎች መካከል 1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ዜግነትን ያስቀመጠ ነው፡፡
የኢህአዴግን ባናውቅም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዢዎች የተዋረደ ስነልቦና የለንም፡፡ ሆኖም የግል ጥቅማቸውን ለማደላደል ሲሉ ለቅኝ ገዢ ጠላቶቻችን ያደሩ ባንዳዎች እንደነበሩ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ ሸክፎታል፡፡ ይህን አሳፋሪ ተግባር በጣሊያን ወረራ ወቅት የፈፀሙ ኢትዮጵያውያን ለልጅ ልጆቻቸው የሚያስተላልፉት አንገት ቀና የሚያደርግ ታሪክ አይኖርም፡፡
በዚህም ዘመን ተመሳሳይ ክህደት የሚፈፅሙ አካላት መኖራቸው አይጠረጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት በይፋ ለጦር ወንጀለኛውና ለፋሺሽቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን ሀውልት በይፋ ካለማውገዝ ባለፈ ለተቃውሞ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በግፍ የማሰሩን ምክንያት ስንመረምር አንድ መራራ እውነት እንረዳለን፤ ይኸውም ጣሊያን ለኢህአዴግ መንግስት ዋንኛዋ ለጋሽ ሀገር መሆኗ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ መንግስት ተግባር በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያዊነት ላይ ከፈፀማቸው ክህደቶች እኩል በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

ነገን የተሻለ ቀን ለማድረግ፤ ዛሬ ነው መነሳት፤ ይድረስ ለሀገሬ ወጣቶች

ሉሉ ከበደ
ከዘር ማንነታችን በፊት ሰብአዊ ሰውነታችን፤ ከጎጠኝነታችን በፊት ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከሸፍጥ፤ ከተንኮል፤ ከመሰሪነታንችን በፊት ቅንነታችን፤ ከፍርሀታችን በፊት ድፍረታችን፤ እርስEthiopian flag, Green, yellow and red በርስ ከመጠራጠራችን በፊት መተማመናችን፤ ከመፍረክረካችን በፊት በጽናት መቆማችን፤ ከልዩነታችን በፊት አንድነታችን፤ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ከከተተበት መቀመቅ ውስጥ የሚያወጣን ብቸኛ መፍትሄ ከላይ የደረደርኩት ነገር ብቻ የመስለኛል።
ነጻ አውጭ ነን የሚሉ የዘር ፖለቲከኞች፤  ህዝብ መክሮ ዘክሮ ከዚህ ዘር ነጥሉን፤ ከዚያ ዘር ነጥሉን፤ ነጻ አውጡን፤ ብሎ ባይመርጣቸውም፤  በስራቸው ለማሰባሰብ ለፈለጉት ህዝብ ታሪክ እየፈጠሩ መስበካቸው እንዳለ ሆኖ፤  እንዲዋጋላቸው፤ እንዲታገልላቸው ሲያደርጉም የዚያኑ ያህል የውሸት ተስፋ እየመገቡም ነው። ለምሳሌ በትግሉ ዘመን የሻእቢያ ካድሬዎችና ፕሮፓጋንዳ ሰራተኞች ዘወትር ህዝቡን ሲሰብኩ፤ ኤርትራ ነጻነቷን ስታገኝ እያንዳንዱ ኤርትራዊ ዜጋ ምንም ስራ ሳይሰራ ከወደቦች በሚገኝ ገቢ ብቻ በቀን ከሰላሳ እስከ አርባ ብር ገቢ ይኖረዋል እያሉ ይሰብኩ ነበር።  ከነጻነት በኋላ ኤርትራ የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፑር ትሆናለች ይሉ ነበር። እነሆ ነጻነቱ ሀያ ሁለት አመታትን አስቆጠረ፤ የኤርትራ ህዝብ በቀን ሰላሳ ብር በነፍስ ወከፍ እየታደለው ነው? ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን የሚሉትን ሰዎች ብትሰሟቸው ወርቁ፤ ቡናው፤ ማእድኑ የብቻቸው እንደሚሆንና ከነጻነት በኋላ እንደሚበለጽጉ ነው የሚቀባዥሩት። ኦጋዴንን ነጻ እናወጣለን የሚሉትን ሶማሌዎች ብትሰሟቸው ጋዙ፤ ነዳጁ የብቻችን ይሆናል ከነጻነት በኋላ እያንዳንዱ ሰው ይበለጽጋል ነው የሚሉት። የብቻ ተጠቃሚነት ቅዥት፤ ስግብግብነት፤ ራስ ወዳድነት፤ በነጻነት ስም የቡድን ጥቅም የስልጣን ምኞት ቅዥት።
አንድ ህዝብ አንድ ቋንቋ ስለተናገረ፤ አንድ ባህል ስለተጋራ፤ ባንድ አካባቢ ስለኖረ፤ ምንጊዜም አብሮ በሰላም ይኖራል ማለት አይደለም። ርእዮተ አለም፤ ሀይማኖት፤ ጥቅም፤ ስልጣን፤ ንኡስ ነገድ፤ የአካባቢ ልዩነት፤ በሰው ልጆች መካከል ግጭትና አለመግባባትን፤ ብሎም ጦርነትና ፍጅትን ለመፍጠርም ሆነ ለማስነሳት በቂ ሀይል አላቸው። ሶማሌዎች አንድ ቋንቋ፤ አንድ ባህል፤ አንድ መልካምድር የሚጋሩ ናቸው።ለምንድነው አብረው መኖር ተስኖአቸው መንግስት አልባ ሆነው የቀሩት?
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም “አቡሸማኔው ትውልድ” በሚለው የእንግሊዝኛ ጽሁፋቸው ውስጥ እንዳስቀመጡት “…ከኢትዮጵያ ህዝብ አርባ አንድ ሚሊዮን የሚሆነው እድሜው ከአስራ ስምንት አመት  በታች እንደሚሆን ይገመታል። ካጠቃላዩ ህዝብ ከግማሽ በላይ ማለት ነው። ዩኒሴፍ የተባለው የህጻናት መርጃ ድርጅት እንደሚገምተው ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናቶቻችንን ከግማሽ በላይ የሚገላቸው የምግብ እጦት ነው። ኢትዮጵያ አምስት ሚሊዮን የሚገመቱ ወላጅ አልባ ህጻናት አሏት። 800 000 ያክሉ ወላጆቻቸውን ያጡት በኤድስ በሽታ ምክንያት እንደሚሆን ይገመታል። በከተሞች አካባቢ የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር 70 በመቶ በላይ መድረሱ ይገመታል። በ2011 የወጣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው 77.8 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ወጣት ኑሮን የሚገፋው በቀን ከሁለት የአሜሪካን ዶላር ባነሰ የገንዘብ አቅም ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ስራ ለማግኘት፤ ለመኖር ሲሉ፤ ራሳቸውን ለመሸጥ ይገደዳሉ። በ 2010 የወጣ የአሜሪካ መንግስት የሰባዊ መብት ሪፖርት እንዳመለከተው የኢህአደግ ድርጅት አባል ያልሆነ ወጣት ስራ ለማግኘት ከቀበሌ የድጋፍ ደብዳቤ አያገኝም። ትምህርት ለመማር፤ ስራ ለመቀጠር፤ በግል ስራ ለመሰማራት የፓርቲ አባልነት መስፈርት ሆኖ ተቀምጧል።…..”
ታዲያ ለዚህ ትውልድ እየመሸ ነው እየነጋ? ለዚህች አገር እየመሸ ነው እየነጋ ? የጥቂት ህውሀት መሪዎችና ቅጥረኞቻቸው ህይወትና እድል እየለመለመና እያማረ ሲሄድ፤ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት እየጨለመና እያሽቆለቆለ ሲሄድ፤ የመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች የነገ ህይወት ጸሊም ተስፋ ተጋርዶበት፤ አስፈሪውን መጪ ጊዜ ሁላችንም እያየነው ተነስተን አንድ ነገር ማድረግ የተሳነን ለምን ይሆን?
በሚሊዮኖች ለሚቆጠረው ወጣት ትውልድ በዚህ ዘረኛ ገዢ ቡድን ምክንያት ህይወት ጭለማ ከሆነችበት፤ የተፈጥሮ መብቱን፤ የዜግነት መብቱን በጥቂት ማፊያ ቡድን ካስነጠቀ፤ የወደፊት ህይወቱን፤ እድሉን፤ የጋራ ሀገሩን ለዚህ አጥፍቶ ጠፊ የዘረኞች ቡድን መቆመሪያ አሳልፎ ከሰጠ፤ ይህ ወጣት እንዴት ለሀገሩና ለወገኑ መድህን ሊሆን ይችላል? ወጣትነት ለውጥ ፈላጊነት ነው። ወጣትነት አዲስ ነገር ናፋቂነት ነው። ወጣትነት የሀገር ተረካቢ ባላደራነት ነው።
በ1998 እኤአ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመንግስታቸው ጋር ከፍተኛ ግጭት የፈጠሩበትና ከፖሊስ ጋር አደባባይ የተፋለሙበትን አንድ አጋጣሚ ላንሳ፤ በዚያን ጊዜ የነበረው የሞይ መንግስት የሆነ መሬት ለኢንቨስተሮች በሊዝ ሊሸጥ ይስማማል። ወዲያው ጉዳዩ ለህዝብ ውይይት ይፋ እንደተደረገ፤ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከየተቋሙ በቁጣ ተፈንቅለው ድርጊቱን ለመቃወም ያልተፈቀደ ሰልፍ ይወጣሉ። የተማሪዎቹ ቁጣ ሊሸጥ የታሰበው መሬት በደን የተሸፈነና ለአራዊትም መኖሪያ ለተፈጥሮውም ጥበቃ ሀገሪቱን የሚጠቅማት በመሆኑ፤ “ሀገራችንን ነገ የምንረከብ እኛ ስለሆን፤ ይህ መንግስት ሀላፊነት የጎደለው ስራ እንዲሰራ አንፈቅድም፤ ለም መሬታችን ለማይረባ የባእድ ኢንቨስትመንት አይሸጥም” በማለት አደባባይ ወተው ከመንግስታቸው ጋር ግብግብ ገጠሙ። ህዝቡም ከያቅጣው ደገፋቸው። መንግስት አቋሙን ቀይሮ ሌላ አማራጭ ለመፈለግ ተገደደ።
ድፍን ኢትዮጵያ እለት በእለት ሲቸበቸብ የኛ ተማሪዎች በዘር ተቧድነው በድንጋይ ይደባደባሉ። ወያኔ መላውን የሀገራችንን ምድር ከየትም አለም እየጠራ፤ ስለአጭር ጊዜም ሆነ ስለረጅም ጊዜ ጉዳቱ ምንም አይነት ጥናትና የህዝብ ውይይት ሳያደርግ በርካሽ ምድራችንን መሸጡን ቀጥሏል። ከሰላሳ አምስት በላይ ከሚሆኑ አገሮች ለሚመጡ ወይም ለመጡ 8000 በላይ ባለሀብቶች የንግድ እርሻ ፍቃድ አድሏል። መሬቱ ለባለሀብቶቹ ሲሰጣቸው፤ ዜጎች ከቀያቸው በሀይል እንዲወጡ፤ መኖሪያቸው እየፈረሰና ልጆቻቸው ደጅ እየተበተኑ፤ እንዲፈናቀሉ እየተደረገ፤ እንቢ ካሉ እየታሰሩ፤ እየተገረፉና እየተገደሉ ነው። በቅርቡ 150 የሚሆኑ የሰሬ ብሄረሰብ ወገኖቻችን በወያኔ ሚሊሺያ ተጨፍጭፈው መሬቱ ለባእዳን ባለሀብቶች ጸድቶላቸዋል።  በሚቀጥሉት አስርና አስራአምስት አመታት ውስጥ ወያኔ ስልጣን ላይ ከቆየ ለራሳችን ፍጥነቱን የማንቆጣጠረው የህዝብ ብዛታችን ሲፈነዳ፤ መሬታችን ሁሉ በባእዳን እጅ ገብቶ የምናርሳት ኩርማን መሬት ቀርቶ፤ መቆሚያ መቀምጫ እንደምናጣ ለመተንበይ ነብይ መሆን አያስፈልግም። ለመኖር ስንል ሀገራችንን ከወረራት አለም ጋር ጦርነት መግጠማችን የማይቀር ነገር ነው። ወያኔ በመርዝ እንዲያልቁ ካላደረጋቸው የህዝባችን ብቻ ሳይሆን የቤት እንስሳቶቻችንም ቁጥር ያድጋል፤ ወደፊት የሚሰማሩበትም ቦታ ይጠፋል። ዛሬ ወያኔ ብቻ ነው ዋናው ገዳያችን። ያኔ ግን እርሻቸውንና ሀብታቸውን ንብረታቸውን የሚጠብቁት የአለም ሀብታሞች ወታደሮቻቸውን ልከው ያግዙታል። በደንብ እንገደላለን።
ያሁሉ ከመምጣቱ በፊት፤ ኢትዮጵያዊው ወጣት ትውልድ ዛሬ ላይ ቆሞ እየተጓዘበት እየቀረበው የመጣውን ጨለማ ጊዜ መመልከት ከቻለ፤ ፈጥኖ መነሳትና ህብረተሰቡን አስከትሎ የወያኔን መንግስት ማስወገድና ሀገሪቱን ማዳን መጪውን የጨለመ ተስፋ ወደ  ብርሀን መለወጥ አለበት። በዘር ተከፋፍሎ መናቆሩን ከቀጠለ፤ እርስ በርሱ ሲባላ ወያኔና የባእድ ሽርካዎቹ ቅርጥፍ አድርገው በልተውት ምድሪቷን ያለስጋት ይኖሩባታል።
አቶ አስገደ ገብረስላሴ “መለስ ከደደቢት እስከ ህልፈት” በሚለው የጽሁፍ ስራቸው ውስጥ እንዳስቀመጡት፤  “….የሀገራችን መሪዎች ልጆችና ዘርማንዘራቸው በመንግስት ባጀት ያለ አንዳች የትምህርት ውድድር በቻይና፤ በአሜሪካ፤ በአውሮፓ፤ በደቡብ ኮርያ፤ ከፍተኛ ትምህርት በሚማሩበት፤ ፍትሀዊ የሆነ የሀገር ሀብት ክፍፍል በሌለበት፤ የሀገራችን ሀብት በህውሀትና ግብረአብሮቻቸው በባለቤትነት በተያዘበት፤ ህዝብ መጠለያ የማግኘት መብት ባጣበት፡ህብረተሰብ በሙሉ በግድ የህውሀት ኢህአደግ አባል ካልሆነ የማይኖርበት ሀገር ሆና እያለች፤ የትምህርት ነጻነት በሌለበት፤ የትምህርት ተቋማት ሁሉ የህውሀት ኢህአደግ አባላት መመልመያና ማደራጃ  በሆነበት፤ የሴፍቲ ኔት፤ የድርቅ፤ ማናቸውም እርዳታ ሁሉ ለህውሀት አባላትና ደጋፊዎች ብቻ የሚሰጥበት፤…ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሁለተኛ ዜጋ የሆኑበት ሁኔታ እያለ መለስ እንዴት ዲሞክራሲያዊና ተራማጅ ሊባል ይችላል?….”
ዛሬ ስልጣን ላይ ተጣብቀው ሞት ነው የሚያስለቅቀን የሚሉት የትግራይ ናዚዎች ስልጣኑን ላለመልቀቅ ሲሉ የኢትዮጵያን ህዝብ እየገፉ የሚወስዱበት መቀመቅ አሁን ካለንበት ከደረስንበት ቦታ ላይ ቆመን የነገውን ስንመለከተው ወለል ብሎ የሚታይና የተለያዩ መድረሻዎችም ያለው ነው።
አንድ ሁለት እውነታ ላንሳ። ሩዋንዳ ውስጥ ሶስት ዘሮች አሉ። ሁቱ፤ ቱትሲና ቱዋይ ። እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1919 አም ጀርምኖችን ተክተው የበልጅየም ቅኝ ገዢዎች ሩዋንዳን ተቆጣጠሩ። ከሌሎች የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጋር ሲነጻጸሩ ቤልጅየሞች እጅግ ጨካኝና ግፈኛ ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው ይነገራል። ስለተቆጣጠሩት አገር ህዝብ ምንም አይነት ደግነት የላቸውም። ላገሩ የተፈጥሮ ሀብት፤ ለህዝቡ ባህል፤ ለመሬቱ … ወዘተ። ዋናው እስትራቴጂያቸው ከህዝቡም ከመሬቱም ማናቸውንም ጠቃሚ ነው ብለው ያመኑትን አገራቸው ቤልጅየምን የሚገነቡበትን ሀብት መቦጥቦጥና ወደሀገራቸው ማሻገር ብቻ ነበር። ልክ  ያለፈ ሀያ ሁለት አመታት ጀምሮ ወያኔ  እያደረገ እንዳለው ሁሉንም ነገር ለትግራይና ወደትግራይ ክልል ማለት ነው። ቤልጂየሞች እንደመጡ ጀምሮ የነዋሪዎቹን የዘር ግንድ ልዩነት ሲያጠኑ ቆይተው በ1933 ላይ ሁቱ የትኛው ቱትሲ፤ ትዋይ አውቀው ሲጨርሱ፤ ሁሉም በየብሄረሰቡ መታወቂያ እንዲሰራለት፤ ሩዋንዳዊ ነኝ ሳይሆን የተለጠፈለትን የዘር አይነት እንዲጠራ ተደረገ። አሁን የኛ ቅኝ ገዥዎች ጀግኖቹ የትግራይ ፍልፈሎች እንዳደርጉን ማለት ነው። ሁቱዎች ብዙሀን ናቸው። ቱትሲዎች ሀዳጣን ናቸው 15%። የኛ ትግሬዎች እንዲያውም ከዚያ ያነሱ ናቸው 5%።  አምስት እጅ የምለው አጠቃላዩን የትግራይ ህዝብ እንጂ በጦር ሀይል አገሪቱን ተቆጣጥረው በመግዛት ላይ ያሉትን ጥቂቱን የህውሀት መሪዎች አይደለም። በማናቸውም ጽሁፌ ውስጥ እማወራው የትግራይን አርሶ አደርና ሰራተኛ ህዝብ አይመለከትም። ህዝቡ ለራሱ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ  በከፋ መልኩ ታፍኖ ተረግጦ የሚኖር ነው።  ቤልጂየሞች የከፋፍሎ መግዛቱን ሂደት ሲያስተካክሉ ቱትሲዎችን ቀድሞውንም የሀገር ባላባት ሆነው ራሳቸውን ከፍ አድርገው ይኖሩ የነበሩትን አቀፉና ብዙሀኑን ሁቱዎችን ገሸሽ አደረጉጓቸው። የወያኔ ገዢዎቻችን ትግሬን አቀፉ፤ የቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ አርባ ክንድ አራቁት።  የመንደር፤ የጎሳ፤ የአካባቢ መሪ ተብለው ህዝቡ የሚያውቃቸውን የሚቀበላቸውን በሙሉ ቤልጂየሞች እያባረሩ በምትካቸው በታማኝነት የሚመለምሏቸውን ሀዳጣን ቱትሲዎችን አስቀመጡ። ወያኔ በሀገራችን እያደረገ እንዳለው ማለት ነው።
የትምህርት እድሉን፤ የመንግስቱን ስራ ሀላፊነትና ተቆጣጣሪነት፤ በማናቸውም መስክ በጥቅማጥቅሙም “በዝምበለው ይውሰድ” ንቅዘቱም የበላይነቱን ለቱትሲዎቹ ሰጧቸው። የወያኔ ገዢ ቡድን ከትግራይ የሚመለምላቸውን ሁሉ በማናቸውም የኢትዮጵያ ክፍል የበላይ እንዳደረገው፤ ቤልጅየሞችም ቱትሲዎችን አጠናከሩ። ቤልጂየሞች ከሌላው ወገን ለሆዱ የተገዛውንና ከተጠቀመ  ለጥፋት ስራቸው ሁሉ ፍጹም ተባባሪ ለመሆን የቆረጠውን ትንሽ ትንሽ እያላሱ፤ የገዛ ወገኑን መቀጥቀጥ የሚችል መዶሻና ድንጋይ አደረጉት። አሁን በየክልሉ ወያኔ በአምሳሉ የፈጠራቸው የአማራ፤ የኦሮሞ፤ የሀረሪ፤ የሶማሌ፤….ወዘተ አይነት ደደቦችና ጅቦች።
ታዲያ ብዙሀኑን የሩዋንዳ ህዝብ ሁቱዎችንና ቱዋዮችን ያስከፋቸውና ለበቀል ያነሳሳቸው ነገር፤ ህዳጣኑ ቱትሲዎች የቅኝ ገዚዎችን ከለላና ድጋፍ በማግኘታቸው ብቻ ከሌሎች ወገኖቻቸው ተለይተው ተጠቃሚ በመሆናቸው ብቻ፤ ከቅኝ ገዢዎቹ ብሰው ወገኖቻቸውን የሚረግጡ፤ የሚገፉ፤ የሚጨቁኑ ሆኑ። አሁን በሀገራችን ህውሀት ስር ተለጥፈው የሚጥሉላቸው ቅንጥብጣቢ ብሶባቸው፤ ሆዳቸው ስለሞላ ብቻ ህሊናቸው ታውሮ፤ በወያኔ ትእዛዝ የገዛ ወገናቸውን የሚገሉ፤ የሚያፈናቅሉ ኢትዮጵያውያንን አይነት ማለት ነው።
በ1950 ዎቹ ቱትሰዎችንና ቅኝ ገዢዎቹን የሚያጣላ ሁነት ተከሰተ። በመላው አፍሪካ የተነሳው የነጻነት እንቅስቃሴና፤ አንዳንድ ተደማጭ የሀይማኖት አባቶች ስለነጻነት ህዝቡን ማነሳሳታቸው፤ ቱትሲዎች በቤልጂየሞች ላይ የእንቢታና የመነሳሳት፤ የነጻነት ጥያቄም አነሱ። በዚህን ጊዜ ለሩዋንዳ ነጻነት የሚንቀሳቀስ የሁቱዎች ፓርቲ ነበር። ቤልጂየሞች ገልበጥ አሉና እሳትን በሳት እንዲሉ ቀድሞ  በእንክብካቤ ይዘው ከፍከፍ ያደረጓቸውን ቱትሲዎች ማግለልና የሁቱዎቹን ንቅናቄ መደገፍ ጀመሩ።
በሁቱና ቱትሲ ወንድማማቾች መካከል ይህ መጨካከን ይህ መገፋት፤  በተለያየ ጊዚ ብዙ ደም ያፋሰሰ ግጭት አስነስቶ በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ የሀገሪቱ ተወላጆች እልቂት መክንያት ሆነ። 1961 ከነጻነት በሁዋላ ሁቱዎች እንደገና በቤልጂየሞች ድጋፍ ስልጣኑን ተቆጣጠሩ። የበቀል አዙሪቱ ቀጠለ። በጋራ ሀገራቸው ስልጣኑን ተጋርተው በሰላም ሀገራቸውን ማስተዳደሩ ተስኗቸው በስልጣንና በጥቅም ህሊናቸው ታውሮ እንደሰው ማሰብ ተስኗቸው እንደ አውሬ ሁነው እንደገና ሁቱዎች ደሞ በተራቸው ቱትሲዎችን ያሳድዱ ይጨቁኑ ጀመር። ቱትሲዎች ሽሽት ወደየጎረቤት አገራት መበተን ጀመሩ። ከ1961 እስከ 1964 ብቻ ቱትሲዎች አስር ጊዜ ከጎረቤት አገር እየተንደረደሩ ሁቱዎችን ለማጠጥቃትና ወደ ስልጣን ለመመለስ ሞክረዋል። ይህ ሙከራ ደግሞ በሀገር ውስጥ የቀሩ ቱትሲዎች በበቀል እንዲጨፈጨፉ ምክንያት ሆነ። እንዲህ እንዲህ እያለ ቅኝ ገዢዎች ስራ ላይ ያዋሉት እየከፋፍሉ እያጋጩ መግዛት የህብረተሰቡ ቋሚ በሽታ ሆኖ አረፈው።
እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1994 በሁቱዎች የበላይነት የሚመራው የሩዋንዳ መንግስት በቱትሲ አማጽያን መሪው ሲገደል፤ በቱትሲዎች ላይ ያንቀሳቀሰው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ቀድሞውንም የታለመ የታቀደ ነበር። ለረጅም ጊዜ በሀገሪቱ ሬዲዮና ጋዜጦች ሁቱዎችን ኢላማ ያደረገ የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በይፋ ይነዛ ነበር። “ሁቱዎች ከዚች ምድር ተጠራርገው ካልጠፉ ሩዋንዳ ሰላም አይኖራትም” ይሉ ነበር። ህውሀት በአማራው ህዝብ ላይ አሁንም በተለይ በትግራይ ክልል የማያቋርጥ የሬዲዮና የህትመት ፕሮፓጋንዳ፤ የዘር ጥላቻ ትምህርት ይሰጣል። እርግጥ ኢትዮጵያ በሽፍቶች የተያዘች ሀገር በመሆኗ ህግ የለምና ነው እንጂ ይህ የህውሀት ቀንደኛ መሪዎች በህዝቡ ውስጥ የሚረጩት መርዝ እድሜልክ ወህኒ መቀመቅ እንዲያርፉ የሚያደርጋቸው ነበር። ደጉ ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ ከነሱ የቀደመ በመሆኑ የሚፈልጉትን የሚያስቡትን ነገር አያደርግላቸውም።
ወያኔ በህብረተሰቡ ውስጥ እያበረታታና እያስፋፋ ያለው እስከዛሬም ያከናወነው ዘርን ከዘር ሀይማኖትን ከሀይማኖት የማጋጨት ስራና እስትራቴጂ ባይዝለትም ተስፋ ይቆርጣል ማለት አይደለም። ተስፋውንና እስትንፋሱን የሚቆርጠው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ተነስቶ ጉሮሮውን ያነቀ እለት ብቻ ነው። በሰላማዊ አመጽም በሉት እሱ በሚያውቀውና በሚገባው አይነት። ለዚህም ተግባር ፊት አውራሪ መሆን ያለበት የኢትዮጵያ ወጣት ዛሬ ነገ ሳይል ሁሉም ወደተመቸው የትግል ስልት ተካቶ ህብረተሰቡን በመምራት ለውጥ ማምጣት ግድ ይለዋል።
የደቡብ አፍሪካውን አፓርታይድ ታሪክ ላንሳ። በአስራሰባተኛው ክፍለ ዘመን በደቾችና በእንግሊዞች የቅኝ አገዛዝ ስር  በነበሩበት ወቅት፤ በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ከፋፍሎ የመግዛት ስልት፤ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር ከ1948 ጀምሮ አፓርታይድ የመንግስቱ ይፋ ፖሊሲ ሆኖ በህግ ተደነገገ። ህዝቡ አንገዛም በማለቱ ህዳጣኑ ነጮች (ከእንግሊዞችና ደቾች ተዳቅለው እዚያው የተራቡ)፤ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ በዘሩ እየተለየ የሚሰባሰብበት ክልል አዘጋጁ። የሀገሪቱን ዜጎች በአራት መደቧቸው። ነጮች፤ ጥቁሮች፤ ክልሶች፤ አና እስያውያን። ባንቱስታን በሚል የሚታወቁ አስር ትንንሽ አካባቢዎችን ከፋፍለው 75% ለሚሆነው ጥቁር ህዝብ፤ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ስፋት 13% በሚሆን ክልል ውስጥ አጎሩት። ሀይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ወደየ ክልላቸው እንዲሰባሰቡ ተደረገ። አሁን ወያኔ በአማራው ህዝብ ላይ እያንቀሳቀሰ ያለው ንብረት እያስቀማ ወደ ክልላቸው እንዲባረሩ የማሳደድ እርምጃ፤ አፓርታይድ ያደርገው የነበረ፤ ሁሉንም ወደከለለት አካባቢ የማካተት ስራ አይነት ነው።  ከህዳጣኑ ነጮች በስተቀር ማናቸው ወገን የፖለቲካ ውክልናም ሆነ ተሳትፎ በኢኮኖሚ በህግ እኩልነት እንደማይኖረው ደነገጉ። ባንቱስታንስ በሚል ለጥቁሮቹ የተከፋፈሉ የጎሳ አካባቢዎችን ከከለሉላቸው በኋላ የደቡብ አፍሪካ ዜጋ መሆናቸው ተሰርዞ፤ የየንኡስ ነገዳቸው አባልና ክልል ዜጋ የመሆን መብት ብቻ ሰጧቸው። ነጮቹ ይህንንም ያደረጉት ጥቁሮች፤ ራሳቸውን የደቡብ አፍሪካ፤ የገዛ አገራቸው ዜጋ አድርገው  መቁጠር እንዲያቆሙ፤ ብሎም የፖለቲካ ተሳትፎና እኩልነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ ነበር። የህዳጣኑን ነጮች የበላይነት የበለጠ ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ ነበር።
ወያኔ ስልጣኑን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ  “ዜግነት” የሚለውን ቃል “ብሄረሰብ” በሚለው የጥፋት ቋንቋው የለወጠበት ዋና ምክንያት፤ የኢትዮጵያዊነት እምነትና አስትሳሰብ በሂደት ከህዝቡ ውስጥ ይጠፋል በሚል ከንቱ ምኞት ነው። የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ እንዳደረገው፤ ኢትዮጵያውያንም ኢትዮጵያዊነታቸው ተሰርዞ ማንነታቸው በየጎጣቸው ተወስኖ ይቀራል የሚል መለስ ስብሀት የፈጠሩት ከንቱ ራእይ አለ። ይሁንና እነሱ ይጠፋሉ እንጂ የኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብር ከእውነተኛ ኢትዮጵያውያን ደምና ስጋ ውስጥ አይጠፋም። የሚኒሊክን ሀውልትም ቢያፈርሱት፤ የአቡነጴጥሮስንም ሀውልት ቢያፈርሱት፤ የአሉላ አባነጋንም ሀውልት፤ ቢንዱት፤ ስድስት ኪሎ የቆመውን የሰማእታት ሀውልት አፍርሰው ጣሊያንንም ቢያስደስቱት፤ ለሺዎች ዘመናት በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ የተገነባችውን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከቶም ከቶ ከዜጎች ልብ ውስጥ ሊያፈርሱት አውጥተው ሊጥሉት አይችሉም። ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንደተባለው ዛሬ ክፉ ቀን ለወያኔ መሪዎች አድልቷልና እስከምናጠፋቸው ታሪካችንን መለያ ቅርሶቻችንን ማጥፋታቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ። በህውሀት ማቃብር ላይ መልሰን ብንገነባቸውም።
የደቡብ አፍሪካ ህዳጣን ነጭ ገዢዎች ያኔ ነጮችና ጥቁር ልጆች አብረው ትምህርት ገበታ ላይ እንዳይቀመጡ አደረጉ። አገልግሎት መስጫ ተቋማት፤ ህክምናና የመዝናኛ ስፍራዎች ሳይቀር ዝቅ ባለ ደረጃ ለብቻቸው ሰሩላቸው።  የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች የነሱ ወዳልሆ ክልል ለመጓዝ የይለፍ ወረቀትና የዘር መለያ መታወቂያ የግድ አስፈላጊ ሆነ….  ለጥቁሮቹ ብቻ።ያ ከሌለ ከክልሉ ወደሌሎች ክልል ለመዝለቅ የሞከረ ጥቁር እስርና ቅጣት የሚጠብቀው ሆነ።
አሁን ኢትዮጵያውያን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል። በተለይ አማራና ኦሮሞ የሚተኮርባቸው ሲሆን፤ የሌላ ክልል ዜጎችም ቢሆኑ ወደ አፋር ክልል ወደ ሶማሌ ክልል ወደ ትግራይ ክልል ሄዶ እንደልቡ በነጻ መንቀሳቀስ አይችልም። የአካባቢው ፖሊሶች በስነስራት እንግዳ የሆነባቸውን ሰው አስቁመው ዘሩን፤ አድራሻውን፤ ከየት እንደመጣ ለምን እንደመጣ ይጠይቃሉ። የሚነጠቅ ነገር እንዳለው ካረጋገጡም ያለምንም ምክንያት አስረው ገርፈው፤ አሰቃይተው፤ የያዘውን ነገር ነጥቀው፤ ቢፈልጉ ይለቁታል፤ ወያኔን ማስደሰት ከፈለጉም አንድ አሸባሪ ሊያፈነዳ ሲል ያዝን ብለው ንጹሁን ዜጋ አሳልፈው ይሰጡታል። ያ መከረኛ ወያኔ እጅ ከገባ  በኋላ ደግሞ እንደሁኔታው ታይቶ የሆነ ትያትር ይሰራበትና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ይውላል። የአማራ ክልል ታርጋ ያለው መኪና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከተገኘ፤ ፖሊሶች አስቁመው ወዴት እንደሚሄድ ምን እንደሚፈልግ ይጠይቃሉ። ታዲያ አፓርታይድ ከዚህ የተለየ ምን አደረገ?
የደቡብ አፍሪካው የዘረኞች መንግስት፤ ያን ሁሉ ሽንሸናና አፈና፤ ያን ሁሉ ግድያና እስራት ሰብአዊ መብት ረገጣ፤ ያን ሁሉ የመከፋፈል ስልት እየተጠቀመ፤ የደቡብ አፍሪካን ወጣቶች አንድ ሆነው አምርረው አፓርታይድን ታግለው ከማሸነፍና መሪያቸው ማንዴላን ከማስፈታትና ነጻነታቸውን ከመቀዳጀት አልገታቸውም። ልዩነታችን የኛ ዘረኞች አገር በቀል መሆናቸው፤ እነዛኛዎቹ መጤ መሆናቸው፤ የነዛ ወጣቶች በእንድነት ጸንተው እስከመጨረሻው መታገላቸውና የኛ ወጣቶች ደሞ ለራሳቸው የዘረኞቹ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነው፤ እርስ በራሳቸው በድንጋይ መደባደባቸው ነው…… የጋራ ጠላታቸውን ትተው።
የሆነው ሆኖ ኒልሰን ማንዴላ ከተናገራቸውና ለደቡብ አፍሪካ ወጣቶች ጽናትና ብርታት ከሆናቸው ቁም ነገዎች ጥቂቱን ለወጣቶቻችን ልጥቀስና ዛሬ ነገ ሳትሉ አንድ ሁናችሁ አሁኑኑ ተነቃነቁ ልበል…
“ድፍረት ማለት ፍርሀት በሰው ልብ ውስጥ የለም ማለት አለመሆኑን ተምሬአለሁ፤ የራስን ፍርሀት ማሸነፍ እንጂ፤ ጀግና ማለት የማይፈራ ማለት አይደለም፤ ፍርሀቱን አሸንፎ ያሰበውን የሚያደርግ እንጂ!!!””
“በየትኛውም አቅጣጫ ቢሄዱ ወደ ነጻነት የሚደረግ ጉዞ ቀላል አይደለም። ወደምንመኘው ተራራ አናት ላይ ከመድረሳችን በፊት፤ ብዙዎቻችን ደግመን ደጋግመን ሞት ጥላውን በሚያጠላበት ሸለቆ ውስጥ ማለፍ አለብን”
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!
ሞት ለወያኔ!
lkebede10@gmail.com

Freedom For Ethiopian Women & Childern: Tamagn With ESAT Europe Journalists

Freedom For Ethiopian Women & Childern: Tamagn With ESAT Europe Journalists

Mar 28, 2013

ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀዋል


 መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:- ከ3 እስከ 4 ሺ የሚሆኑ ከቤንሻcccጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ከመስተዳድሩ ፊት ለፊት ባለ ሜዳ ላይ ያለምንም መጠለያ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። ከከተማው ነዋሪዎች ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ተፈናቃዮቹ ቀን በጸሀይ፣  ሌሊት በብርድ እየተሰቃዩ ነው። እጅግ በርካታ ህጻናትና ሴቶች ከተፈናቀሉት መካከል ይገኙበታል። ተፈናቃዮች ከአካባቢያቸው ይዘውት የመጡትን ዱቄት እየጋገሩ በበመገብ ላይ መሆናቸውም ታውቋል። እስካሁን ድረስ ተፈናቃዮችን ቀርቦ ያነጋገራቸው ባለስልጣን አለመኖሩንም ለማወቅ ተችሎአል። ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ 60 የአማራ ተወላጆችን  ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ 59 ሰዎች መሞታቸውን እንዲሁም ትናንት ሁለት ህጻናት በአይሲዙ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ታፍነው መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

መንግስት ለአባይ ግድብ ግንባታ ከህዝብ ለመሰብሰብ ያወጣውን እቅድ ሳይተወው አይቀርም ተባለ

 መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የአባይ ግድብን በሕዝብ ተሳትፎ ለመገንባት ባቀደው መሰረት ከመንግስት ሰራተኞች፣ባለሃብቶች፣አርሶአደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እያካሄደ ያለውን የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ዘንድሮም ለመቀጠልም አቅዶ ቢንቀሳቀስም ከህዝቡ የታሰበውን ያህል ምላሽ ባለመገኘቱ ለማቋረጥ ሳይገደድ እንደማይቀር ምንጮቻችን ገለጡ። የአባይ ግድብ ከተጀመረ በኋላ በተለይ ባለፈው ዓመት የመንግስት ሰራተኞች ሳይወዱ በግድ የአንድ ወር እና ከዚያ በላይ ደመወዛቸውን በአንድ ዓመት ከፍለው ለመጨረስ ቃል እንዲገቡ በማድረግ ገንዘብ ለማሰባሰብ መሞከሩ የሚታወስ ሲሆን፣  መዋጮው ስጦታ መሆኑ ቀርቶ በቦንድ ግዥ እንደሚያዝ፣ይህም የቁጠባ ባህልን ለማበረታታት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት ዘንድሮም መዋጮ ለማሰባሰብ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ምላ ሹ ጥሩ ባለመሆኑ ምክንያት ለማቋረጥ ሳይገደድ አይቀርም። ለዚህ አንዱና ዋንኛው ምክንያት ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ ደመወዝተኛው በገቢው ለመተዳደር ያለመቻል ሲሆን በተጨማሪም ለፕሮጀክቱ ከሕዝብ በመዋጮ መልክ የሚሰበሰበው ገንዘብ በምን መልኩ ስራ ላይ እየዋለ እንደሆነ፣ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ግልጽ መረጃ አለመኖሩ በሕዝብ ውስጥ ጥርጣሬን ፈጥሯል፡፡  ሌላው ቀርቶ ስንት ብር እንደተዋጣ እንኳን መንግስት ተከታታይነት ያለው በቂ መረጃ እየሰጠ አለመሆኑ የበርካታ ወገኖችን ቅሬታ አስከትሏል፡፡ ለግድቡ ገንዘብ ለመስጠት ቃል የገቡ ሼህ አላሙዲንን ጨምሮ በርካታ ባለሃብቶችም ገንዘቡን በወቅቱ ገቢ አለማድረጋቸው በእነአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና አቶ በረከት ስምኦን የሚመራውን የአባይ ግድብ ብሔራዊ ም/ቤትና አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናትን ማበሳጨቱ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት ሁለተኛ ዓመት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡ ከነዚህ ዝግጅቶች መካክል የስነጹሑፍ ፣የስዕል፣የሙዚቃ ዝግጅቶች፣ልዩ ልዩ የአትሌቲክ ውድድሮች፣በተዋናዮችና በድምጻዊያን መካከል መጋቢት 21 በሚካሄድ የእግር ኳስ ውድድር እንዲሁም ግንባታው በሚካሄድበት ቦታ መጋቢት 24 ቀን በሚካሄድ በዓል እንደሚከበር የወጣው መርሃግብር ያሳያል፡፡ ግድቡ በአሁኑ ወቅት 18 በመቶ ስራው መጠናቀቁ በመገለጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን በስራው ላይ በህወሃት የቀድሞ ታጋዮች የሚመራውና ከተመሰረተ የሁለት ዓመት ዕድሜ ብቻ ያለው የብረታብረት ኮርፖሬሽንን ጨምሮ የኢህአዴግ ኢንዶውመንት ድርጅት የሆነው መስፍን ኢንዱስትሪያል በልዩ ድጋፍ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ያለው ስራ እንዲያንቀሳቅሱ እየተደረገ ነው፡፡፡ የወ/ሮ አዜብ የእህት ልጅ በሆኑት በወ/ሮ አቲኮ ስዩም አምባየ የሚመራው ኦርቺድ ድርጅትም በግድቡ ስራ ከሳሊኒ በመቀጠል ከፍተኛ ገንዘብ በማግበስበስ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።ግድቡ በተፋሰሰ አገራት በተለይም በግብጽና ሱዳን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የማያስከትል መሆኑን ለማረጋገጥ የተቋቋመውና በስራ ላይ የሚገኘው የዓለምአቀፍ የኤክስፐርቶች ቡድን በግንቦት ወር 2005 የመጀመሪያ የጥናት ሪፖርቱን ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ምናልባት የጥናቱ ግኝት እነ ግብጽን የማይጠቅም ከሆነ የግድቡ ግንባታ የመቀጠሉ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚወድቅ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ግን ጥናቱ ግድቡ በተለይ የኢንቫይሮመንት ተጽዕኖ እንደማያስከትል ማረጋገጫ ይሰጥልኛል ብሎ ተስፋ ያደረገ ሲሆን ይህ ባይሆንም እንኳን ግድቡን ከመገንባት የሚያግደኝ የለም እያለ ነው፡፡

Total Pageviews

Translate