Pages

Sep 29, 2013

ማን ነው የሚለየው ይህ ትውልድ ለወያኔ ፍም እሳት ነው !!! የዕለቱ ምርጥ ዘፈን በኖርዌይ ኦስሎ ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ !!!!

በኖርዌይ የሚገኘው ይህ የምትመለከቱት ዌብሳይት ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ የተደረገውን ለግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በ26.09.2013 13:23 ላይ የተለመደውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የነዛበት ሊንክ እና ፕሮግራሙን እንዳይካሄድ ለማድረግ ብዙ የደከመበት ስራ ይህን ይመስል ነበር 
ይቺን ሊንክ ይጫኑ http://www.abesha.no/P%C3%A5-Amharisk/1372
ወያኔ ጥጋብ በወለደው እብሪቱ በማንአለብኝነት የህዝብን መብትና ነጻነት ረግጦ በአፈና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አለኝታየ በሚላቸው የፖሊስ፣ የደህንነትና ወታደራዊ ኃይሎች እስከ መጨረሻው አጠናክር ለመቀጠል የሚችል አድርጎ ያስባል። በዚህም ምክንያት እስካፍንጫው ባስታጠቀው ወታደር ብዛትና በነዋሪው ቁጥር ልክ ህዝብ መሃል ባሰማራው ሰላዮች የተገነባው የፍርሃት ግምብ የሚናድም መስሎ አይታየውም። 
     ሃቁ ግን በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተሰባሰቡ ወጣቶችም ሆኑ መላው አለም ላይ የሚገኙ በተለይም በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች እና ወያኔን በአራቱም የአገራችን ማዕዘናት ለመግጠም ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወያኔ ህዝባችንን ሊያስፈራራ የሚችልበትን ሁሉ በጣጥሰው ለመውጣት ምንም ችግር የሌለባቸው መሆኑን በትላንቱ  በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል  የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ግንባሩን ወክለው የመጡት እንግዳ እና ኢትዮጵያኖቹ በኩራት እና በቁርጠኝነት ተናግረዋል።
      በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው  ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የተገደዱት የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን በገንዘብ ለመርዳት ታስቦ የነበረውን ቀን በኖርዌይ የሚገኙ ጸረ ኢትዮጵያን የወያኔ ደጋፊ ጉጅሌዎች ለተወሰነ ሰዓታት ባደረጉት የተሳሳተ ወይንም ያልተገባ ውሸት በደስታ የተፍነከነኩበት በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያን ቁርጥ ልጆች ድል  ተጠናቋል
Norway G7 fundrise

ትላንት ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ።  በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። በመጨረሻም በኖርዌይ የምንገኝ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የምናስተላልፈው ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው።

፦ ወያኔ ገንብቻለሁ ብሎ የሚኮፈስበትን የፍርሃት ግምብ ደርምሰው ለነጻነታቸው ሲሉ ውድ የህይወት ዋጋ ለመክፈል በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ዙሪያ መሰባሰባቸውን ይፋ ያደረጉ እነዚህ ወጣቶችን በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች  የተነሱለትን ክቡር አላማ ያደንቃል። በዚህም ምክንያት ለነጻነቱ ቀናኢ ለሆነው ለህዝባችን ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ወቅታዊነት ሁሉም እንዲረዳው እና በመላው ዓለም ላይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ  የበኩሉን አሰተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ያሬድ ኤልያስ nome telemark

Sep 24, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ዋነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊና ዘላቂ ጥቅም ጠላት ወያኔ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ይህንን አባባል አንድ ተቃዋሚ ለተቃውሞ ያህል ወይም ስርዓቱን የሚጠላ አንድ ግለሰብ ስርአቱን ስለሚጠላዉ ብቻ እንደተናገረው አድርጎ አቃልሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከአሁኑ ቅጽበት ድረስ በሀገራችን ላይ የፈጸመውን ደባ በቅጡ ያላዩ ሰዎች ይህ አባባል የተጋነነ ይመስላቸው ይሆናል። ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ አገር የቆመችዉ በህዝቦቿ ታላቅነትና እንዲሁም ለታሪካቸው ባሳዩት ክብርና ብርታት ነዉ እንጂ እንደወያኔማ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ከወደቀ ሰንብቷል።
ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።
መገነጣጠል ግብ እንዲሆን በህገ መንግስት ደረጃ አንቀጽ ጽፎ ያስቀመጠው ወያኔ እሱ እንደሚለዉ ለብሔረሰቦች መብት አስቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ አልዘረፍ ካለችን በትነናት ብንሄድስ ከሚል አላማ መሆኑን ሌናጤን ይገባል። ከምር ለብሄረሰቦች መብት በመቆርቆር ቢሆን ኖሮ ከጠመንጃና ከፍጅት በፊት የብሄረሰቦችን መብትና ነጻነት አክብሮ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ይተዋቸዉ ነበር።።
ወያኔ ኢትዮጵያን የሚፈልጋት ለርሱና ለጋሻ ጃግሬዎቹ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሆና ስላገኛት ብቻ ነው። ሀገሪቱን እያለማሁ፣ እያሳደግኩ ነው የሚለው ዲስኩር ለተራ መደለያ እንኳን የማይሆን ውሸት ለተራበው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ያውቀዋል።
የሀገሪቱን ለም መሬት በሄክታር ባንድ ፓኮ ሲጋራ ዋጋ የሚቸረችረው ወያኔ እነዚህ ባእዳን በጎን የሚሰጡትን የሀገራችንን መሬት ዋጋ ኪሱ መክተቱን አረጋግጦ ነው። ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚነዛው የኬሚካል ማዳበሪያ በጥቂት አመታት ውስጥ የሀገሪቱን አፈር ድራሽ እንደሚያጠፋ ወያኔ የአዋቂዎች ምክር ሳይሰማ ስለቀረ አይደለም። በአጥፊ ስራው የቀጠለው መዝረፍ የሚችለዉን ንብረት ካጋበሰና ከዘረፈ በኋላ ነገ ኢትዮጵያ እንደአለ ባድማ ብትሆን ቅንጣት ስለማይሰማዉ ነዉ። ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአገሪቱ ወጣትና የተማረ የሰዉ ኃይል እንደ ጎርፍ ከአገሪቱ እየጎረፈ ሲወጣ ይቆረቆር ነበር። ወያኔ የተማረ ሰው ቢሰደድ፣ ዜጎች ቢራቡና በገዛ አገራቸዉ ቢዋረዱ ጉዳዩ አይደለም። በሰላማዊና ህገመንግስታዊ መንገድ ጥያቄ ያነሳን ዜጋ ሁሉ እንደአውሬ የሚቀጠቅጠውና ወህኒ ቤት የሚያጉረው ይህ በደል ነገ በሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና ላይ የሚያመጣውን መዘዝ አጥቶት አይደለም። የአገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጉዳዩ ስላልሆነ እንጂ።
የኢትዮጵያን ብሄር ቤሄረሰቦች የሚያይዟቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድነት ክሮች እያንቋሸሸና እንደሌሉ እየሰበከ በሚለያዩንን ጥቃቅን ውጭያዊ የቋንቋና የዘር ግንዶች አጉልቶ የሚያሳየን አገራችንንና ህዝቧን እንደ አንድ ሀገር ሳይሆን እንደጊዚያዊ የዝርፊያ ቀጠና ስለሚመለከት ብቻ ነው።
ወያኔና ሎሌዎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላቶቹ ናቸው እያሉ አንዴ የፈረሰችዉ ሶማሊያን፤ ሌላ ጊዜ ወደ ኤርትራና ግብጽ ጣቱን የሚጠነቁሉት አይናችንን ከወያኔ ላይ እንድናነሳ ነዉ እንጂ ከወያኔ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላት የለም። ወያኔ በአካል እኛን ከሚመስሉ ኢትዮጵያውያን መሃል ይውጣ እንጂ፣ በተግባር ከቀን ጅብ ያልተናነሰ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ራሱ የጻፈውን ህግ ሲጥስ ለምን ብለን የምንገረም አለን። ወያኔ ሕግና ሕገ-መንግስት፣ ለአገራቸዉ የሚቆረቆሩ ምሁራንን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ የሚታመን ሰራዊት፣ ለህግ ብቻ የሚሰራ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ዘላቂ ተቋማት እንዳይኖሩን የሚያደርገውና ያሉትንም የሚያፈርሰው ለኢትዮጵያ ብሄራዊና ዘላቂ ጥቅም ምንም ደንታ ስለሌለዉ ነዉመሆኑን የሚዘነጋ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ የዋህ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።
ስለዚህም እንላለን እኛ የግንቦት 7 ልጆችህ ሀገርህ ትውልድ ተሻግራ እንድትቀጥል አንተም የምትኮራባት ዜጋ እንድትሆናት የምትሻ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ሀገርህን ከወያኔ የቀን ጅቦችና ወራሪዎች አድን። አጎንብሰህ ሳይሆን ቀና ብለህ የምትሄድባት ሀገር እንድትኖርህ የምትሻ ሁሉ ለማይቀረው የጀመርነውን የአርበኝነትና የነጻነት ትግል ጉዞ ተቀላቀለን። እኛ የተባበርን እለት አብረን የተነሳንና በቃ ያልን እለት ታሪካዊቷ ሀገራችንና ታላቁ ሕዝባችን ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅማቸው ይከበራል።
አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Sep 19, 2013

ጉዲፈቻ የሰው ልጆች ንግድ ‹‹ከቤተሰቤ ተሰርቄ ነው የተወሰድኩት››

 ታሪኳ ለማ፣ በጉዲፈቻ አሜሪካ የተወሰደችው ጉብል
‹‹ከቤተሰቤ ተሰርቄ ነው የተወሰድኩት››በአሁን ጊዜ በዓለም ላይ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ከሚያስነሳት ጉዳይ አንዱ ጉዲፈቻ ነው፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች አሳዳጊ የሌላቸው ተብለው የሚታሰቡ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ወደ ተለያዩ አገሮች ይሄዳሉ፡፡ ‹‹የተሻለ ሕይወት›› ይኖራቸዋልም በሚል እሳቤ ቤተሰብ ያላቸውን ሕፃናትም ሕገወጥ በሆነ ሰርቆ መስጠት እንዲሁም በደላሎች አማካይነት የሚሠሩ ሥራዎችም እንዳሉበት በርካታ ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሲኤንኤን መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ያወጣው ይህንኑ አስከፊ እውነታ የሚመሰክር ነው፡፡
ታሪኳ ለማ የ19 ዓመት ዕድሜ ያላት ወጣት ናት፡፡ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ነበር ከሁለት ታናናሽ እህቶቿ ጋር ትምህርታቸውን በአሜሪካ እንደሚከታተሉና  ትምህርት በማይኖርበት በማንኛውም የዕረፍት ጊዜ ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ እየመጡ ቤተሰቦቻቸውን እንደሚያዩ ቃል ተገብቶላቸው እናት አገራቸውን የለቀቁት፡፡ 
ዛሬ ማይኒ የምትኖረው ታሪኳ ለማ የኮሌጅ ተማሪ ስትሆን፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ የመሆን ህልም አላት፡፡ በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ ተወስደው ስላለፉት የሕይወት ውጣ ውረድ እንደሚከተለው ተርካዋለች፡፡ 
‹‹የተሸጥኩት አሥራ ሦስት ዓመቴ ላይ ነበር፡፡ ከቤተሰቤ ተሰርቄ የተወሰድኩት፡፡ እኔና እህቶቼን  ለትምህርት ወደ አሜሪካ ሊልከን እንደሚገባ አባቴን ያሳመኑት የአባቴ ጓደኞች ነበሩ፡፡ እኤአ በ2006 በተገባልን የሐሰት ቃል ኪዳን ወላጅ አባቴን አሞኝተው እንድንሄድ ተገደድን፡፡ ይህንን የሚያደርጉት የአባቴ ጓደኞች በሙስና እጃቸው የተጨማለቀና አጭበርባሪ የጉዲፈቻ ወኪል ውስጥ የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ይህም ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ 
‹‹አባቴም ሆነ እኛ ስለ ጉዲፈቻ የምናውቀው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ወላጅ አባታችን የላከን ለትምህርት፣ እኛም ለመማር እንደመጣን ነበር የምናውቀው፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሹን ሆኖ ነበር ያገኘነው፡፡ ዋሽተውናል፤ የዋሹት ግን እኛን ብቻ ሳይሆን በጉዲፈቻ የወሰዱንን አሳዳጊ ቤተሰቦቻችንን ጭምር ነበር፡፡  ያመጣንላችሁ ወላጆቻቸውን በኤድስ ያጡ ሦስት ሕፃናትን ነው፤ ትልቋ ዘጠኝ ዓመቷ ነው ብለው ነበር ሴራውን ያቀነባበሩት፡፡ ይሁንና እውነታው ግን እኔ የአሥራ ሦስት ዓመት ታዳጊ ነበርኩ፡፡ የቤተሰቤም የበኩር ልጅ ነኝ፡፡ ታናሾቼ የአሥራ አንድና የስድስት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ታዳጊዎች ነበሩ፡፡ 
‹‹አዲሶቹ ‹ቤተሰቦቻችን› ስማችንን ቀየሩትና በአፍ መፍቻ ቋንቋችን በአማርኛና በወላይትኛ ማውራት እንደማንችልና ካወራንም ቅጣት እንደሚጠብቀን አስጠነቀቁን፡፡ እናም በስተመጨረሻ አፍ በፈታንበት ቋንቋ መናገር ተሳነን፤ እስከነ አካቴውም ረሳነው፡፡ 
‹‹በጣም ልጅ ነበርኩኝ፡፡ ከዚህ ካለሁበት የእሥር ቤት ሕይወት ጠፍቼ ብወጣ ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ተመልሼ የምገባ ይመስለኝ ነበር፡፡ እነኚህ ቀጣፊዎች ከትውልድ አገሬ፣ ከባህሌና ከቤተሰቤ እንደነጠሉኝ ሳስበው ውስጤ በሐዘንና በምሬት ይሞላል፡፡ 
‹‹ከስምንት ወራት በኋላ ከእህቶቼ ተነጥዬ ወደ ሌላ ቤት እንድጓዝ ተደረግኩኝ፡፡ አዲሱ መኖሪያዬ የተደረገው ከአሳዳጊ እናቴ ቤተሰቦች ጋር ነበር፡፡ ያም ወደ መካከለኛው ምዕራብ ነበር፡፡ እህቶቼን ለመጐብኘት የታደልኩት በጣት ለሚቆጠሩ ጊዜያት ነበር፡፡ አሁን ባለሁበት አገር መኖር ይከብዳል፡፡ ከአገሬ ኢትዮጵያና ከእህቶቼ ተነጥያለሁ፡፡ አጋጣሚዎች ክፉ ቢሆኑብኝም እጅ መስጠት አልፈለግኩም፡፡ ያለኝን አቅም ሁሉ አሰባስቤ ከአገር ውጪ በሚደረግ ጉዲፈቻ ምን ዓይነት ብልሹ አሠራርና የሰው ልጆች ንግድ እየተካሄደ መሆኑን  ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ ወሰንኩ፡፡ 
‹‹ከአገር ውጪ የሚደረግ ጉዲፈቻን የሚያበረታቱ አካላት 151 ሚሊዮን ወላጅ የሌላቸው ታዳጊዎች እንዳሉ ይጠቁማሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱንም ወላጅ ያጡ ሕፃናት 18 ሚሊዮን ብቻ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ከእናት ወይም ከአባት ጋር የሚኖሩ ናቸው፡፡ ይህንንም ወላጅ የሌለው ብሎ መጥራት እጅግ የሚከብድ ነው፡፡ እኔ ወላጅ አልባ አይደለሁም፡፡ በእርግጥ እናቴ ሞታለች፤ ነገር ግን አባት አለኝ፣ እህቶች ወንድሞች እናም ሌሎች የሚወዱኝና የሚናፍቁኝ ቤተሰቦች አሉኝ፡፡ 
‹‹ውሸቱም  ሆነ ማጭበርበሩ ለገንዘብ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ዛሬ ዛሬ ለገንዘብ ሲሉ ወላጅ የሌላቸው ሕፃናት መፍጠር ጀምረዋል፡፡ ለዚህም የገንዘብ ክፍያ አላቸው፡፡ ክፍያውም ከአገር አገር ይለያያል፡፡ ከፍ ዝቅ ይላል፣ ነጭ ሕፃን በጉዲፈቻ ለመውሰድ የሚከፍሉት ክፍያ ከፍ ያለ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የጥቁር ዝቅ ያለ ነው፡፡ ተመልከቱ ምን ያህል አስከፊ ሕይወት እንደሆነ፡፡ 
‹‹ዛሬ ውጣ ውረዶች ጠንካራ አድርገውኛል፡፡ ይህም በሕይወቴ አንድ ጥሩ ነገር እንድሠራ አነሳስቶኛል፡፡ በጉዲፈቻ ዙሪያ የሚሠሩ ተቋማት እየሠሩ ያሉትን ንግድ የሚያጋልጥ መጽሐፍ በመጻፍ ላይ እገኛለሁ፡፡ ወደ አገሬም ለመመለስ የሚበቃኝን ገንዘብ እያጠራቀምኩ ነው፡፡ በቅርቡም ወደ ፍርድ ቤት በመሄድም ትክክለኛ ስሜን ለማግኘት እሞክራለሁ፡፡››

Sep 15, 2013

G7 POPULAR FORCE FUNDRASING EVENT OSLO NORWAY 28 SEPTMBER 2013


Ginbot 7 Popular Force fundraising event in oslo norway September,28, 2013. During this event representatives of the G7PF leadership will be present and the program of the event comprises, discussions, fundraising and entertaining activities Freedom,
justice and democracy to all Ethiopians!

Sep 14, 2013

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

  
ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
  1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
  2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
  3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
  4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
  5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
  6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
  7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
  8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤
  1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
  2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
  3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Sep 9, 2013

የሰው ለሰዉ አስናቀ - 18ሺ ብር ከፈለ!


የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡ አበበ ባልቻ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊሔድ የቻለው ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሸገር ሕንፃ ስር በሚገኘው ዩጎቪያ ክለብ በመዝናናት ላይ ነበር፡፡ በቦታው ለእረፍት ከኖርዌይ የመጣውና በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኖርዌያዊ የሆነው ሐሰን መሐመድና የወንድሙ እጮኛ እየተዝናኑ ነበር፡፡ ከሐሰን ጋር የነበረችው ሴትም አበበ አስናቀን ሆኖ በሚጫወትበት የሰው ለሰው ድራማ ታደንቀው ስለነበር ወደ እሱ በመሄድ አብራው ፎቶ ለመነሳት ትጠይቃለች፡፡ አበበም ፈቃደኛ በመሆን አብሯቸው ይነሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መበሳጨት ይጀምራል፡፡ ከዚያም ወደ ሰዎቹ በመሄድ ከሐሰን ላይ ፎቶ ያነሳበትን አይፎን 5 ይቀበለውና መሬት ላይ በመጣል በእግሩ ይሰባብረዋል፡፡ ከልጁም ጋር ለመደባደብ መተናነቅ ሲጀምር የክለቡ ጠባቂዎች ይገላግሏቸዋል፡፡
ሞባይሉ የተሰበረበት ሐሰን አበበን እንዲሁ ሊለቀው ስላልፈለገ ወደ ሕግ ሊወስደው ሲጥር እሱ ባልጠበቀው ሁኔታ ጠባቂዎቹ አበበን ከቤቱ ያወጡታል፡፡ የአበበን መውጣት ያወቀው ሐሰን ግን ከአበበ ጋር አብሮ ይዝናና የነበረውን አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን በመያዝ “አንተ ስለሆንክ ያስመለጥከኝ አንተን ወደ ሕግ እወስድሃለሁ” በማለት ይዞት አቅራቢያው ወደሚገኝ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ይሄዳሉ፡፡ ጣቢያ ደርሰውም ጉዳዩን ያስረዳሉ፡፡ ስለ ሁኔታ የተጠየቀው ሰለሞንም ድርጊቱ መፈፀሙንና በማግስቱ አበበን እንደሚያቀርበው ተናግሮ የአበበንም ስልክ ለፖሊሶች በመስጠት ይለቀቃል፡፡
በማግስቱም ከሳሾች በንብረት ማጉደል ክስ መስርተው ለአበበ በወኪሉ አማካኝነት መጥሪያ በመስጠት ይመለሳሉ፡፡ አበበም ፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ ሁኔታ መፈፀሙን እንደማያስታወስ ግን ምናልባት በትከሻው ገፍቶት ወድቆ ሊሆን እንደሚችል ይናገራል፡፡ አቃቤ ሕግና ፖሊስም እነ አበበ ጉዳዩን በሰላም እንዲፈቱት በማግባባታቸው አበበ ለሰበረው ሞባይል 18 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እንዲከፍል በመወሰኑ ተያይዘው ወደ ቢሮው በመሄድ ቼክ ፈርሞ ለሐሰን በመስጠቱና ይቅርታ በመጠየቁ ችግሩ ሊፈታ ችሏል፡፡

Sep 4, 2013

በሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደረሰው ወያኔያዊ ጥቃት ተቆጭተናል!!! ወጣቶች መንገዳችሁን እንድትመርምሩ እንመክራለን!!!


ነሐሴ 25 ና 26 ቀን 2005 ዓ. ም. ወያኔ በአብዛኛው በወጣቶች በተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ላይ ያደረሰው ወንበዴያዊ የመብት ጥሰት አሳዝኖናል፤ አስቆጭቶናልም። ይህንን ጥቃት አጥብቀን እንቃወማለን። ከወራት በፊት በይፋ አስታውቀውና ደጋፊዎቻቸውን በይፋ ጠርተው ለሰላማዊ ተቃውሞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ወጣቶችን በቅልብ ኮማንዶዎች ማስደብደብ ተራ የመንደር ወንበዴ እንኳን የማይፈጽመው ወራዳ ተግባር ነው፤ ወያኔ ግን አድርጎታል።
የመፈክር መፃፊያ ቡርሾችና ማርከሮች ካልሆነ በስተቀር ራሳቸውን መከላከያ ዱላ እንኳን ያልያዙ ወጣቶችን በጠመንጃዎች ሰደፍ፣ በጁዶና በካራቴ ተደብድበዋል። ልጃገረዶች ጤንነታቸውን ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን በሚነካ መንገድ እተሰደቡና እየተደበደቡ ጭቃ ውስጥ እንዲከባለሉ ተደርገዋል። ጋጠወጦቹ የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ከወያኔ ሹማምንት ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተላከውን መልዕክት በቃልም በተግባርም አድርሰዋል።
የመልዕክቱ ይዘት ባጭሩ የሚከተለው ነው።
ሞተን አጥንታችንን ከስክሰን ያገኘነው ሥልጣን ትንፋሻችን እያለ ከእጃችን አይወጣም። እንኳንስ በሰላማዊ ትግል የመንግሥት ሥልጣንን ልትይዙ ቀርቶ፤ እኛ ሳንፈቅድላችሁ እደጅም አትወጡም። እንገዛችኋለን!!! እንረግጣችኋለን!!! ሕግ አያግደንም። እኛ ራሳችን ሕግ ነን። ምን ታመጣላችሁ? ምን አቅም አላችሁ?
ይህ መልዕክት ለሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላት በዱላና እርግጫ ታጅቦ ቃል በቃል ተነግሯቸዋል።
ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። ዛሬ ጥያቄው ከመቼውም በላይ አፍጦ መጥቷል። ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ? ፍርዱን ለእናነተ እንተዋለን።
ወያኔ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት የላከው መልክት ለፓርቲው አባላት ብቻ የተላከ አይደለም። መልዕክቱ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ምላሽህ ምንድነው? እስከ መቼ የወያኔን እብሪት እንታገሳለን? ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው?
ግንቦት 7፤ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁለገብ የትግል ስልትን ሲመርጥ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት በማመን ሆኖም ግን ብቻውን የትም እንደማያደርሰን በመገንዘብ ነው። ስለዚህም ሁለቱም የትግል ስልቶች ተደጋግፈው መሄድ አለባቸው ይላል። ግንቦት 7 ይህንን የትግል ስልት የቀየሰው በወያኔ ባህሪ ላይ ተመሥርቶ ነው። የወያኔ ዓይነቱ እብሪተኛ ሥልጣን በያዘበት አገር ሰላማዊ ትግል ከአመጽ ትግል በላይ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ሰላማዊ ትግልና የአመጽ ትግል ውሃና ዘይት ወይም እሳትና ጭድ አይደሉም። እንዲያውም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እና ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ አንዱ ያለሌላኛው ዋጋ የለውም።
ስለሆነም ከደረሰባችሁ ወንበዴያዊ ጥቃት ትምህርት በመውሰድ፤ ወደፊት ደግሞ ከዚህ የባሰ ሊመጣ እንደሚችል በመገንዘብ፤ ሁኔታዎችን መርምራችሁ በግል የስትራቴጂ ለውጥ ለማድረግ የወሰናችሁ ወጣቶች ግንቦት 7ን ማግኘት አይቸግራችሁም። ሆኖም ጊዜ የለም። በወያኔ ዓይን እና በወያኔ ፍርድ ቤት እይታ መብቱን የጠየቀ ሁሉ የግንቦት 7 አባል ነውና የምታጡት ነገር የለም። ዛሬውኑ ወስኑ!!!!
ግንቦት 7፤ በዚሁ እለት ክርስቲያኑንና ሙስሊሙን ኢትዮጵያዊያንን ለማቃቃር ወያኔ የጠራውን ሰልፍ ጥበብ በተሞላበት ስልት ላከሸፈው “የድምፃችን ይሰማ” አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Aug 16, 2013

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!!

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መግለጫ
ነሐሴ 3 2005 ዓ.ም.
በእስልምና እምነት እጅግ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ኢድ አልፈጥር ለ1434ኛ ጊዜ ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ. ም. በመላው ዓለም በደስታ ሲከበር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግን ለዚህ አልታደሉም። በእለቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኢድ ሰላታቸውን ሰግደው ወደ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለድብደባ በሠለጠኑ የወያኔ ወታደሮች አሰቃቂ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ እለት በአዲስ አበባና እና ሌሎች ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁን ሕፃናት የወያኔ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፤ ከዚያ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ወከባ ያመለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ሙስሊሞች በዓሉን ያሳለፉት በወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ በሕመምና በረሀብ እየተሰቃዩ ነው።
ይህ ለምን ሆነ?
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ጥንቃቄ የተሞላበት ተቃውሞ ሲያካሄዱ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። እጅግ ጨዋ በሆነ መንገድ ላቀረቡት የመብት ጥያቄ በታላቁ በዓል ቀን ወያኔ የእንቢታ ምላሹን ወራዳ በሆነ መንገድ ሰጥቷል። ወያኔ ለሰላማዊ ተቃዉሞ ያለውን ንቀት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋዊያንን ጭምር በመደብደብ አሳይቶናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችን ሕመም ይጋራል። በባለጌ የወያኔ ወታደሮች የተገደለየ፣ የተረገጡ፣ በቆመጥ የተደበደቡ፣ የተሰደቡ፣ የተተፋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሕመማቸውን ችለው፤ እልሃቸውን ውጠው ለመረረ ትግል እንዲዘጋጁ ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል በሁላችን ላይ የደረሰ ጥቃት፣ በደል ነው። የሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ የኢትዮጵያዊያን ተበዳዮች ሁሉ ጥያቄ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በወያኔ አገዛዝ ሥር ምላሽ አያገኙም። ስለሆነም ተባብረን ኢትዮጵያችንን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ አውጥተን ሁላችንም የነፃነት አየር የምንተነፍስባት አገር እናድርጋት ዘንድ ዛሬውኑ የጋራ የትግል ጉዞ እንጀምር።
“ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ! እልሃችሁን ውጣችሁ፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር ለሚደረግ ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!” በማለት ግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

Aug 12, 2013

መንግስት አላዋጣ ሲለው ጥሎት የነበረውን ካርታ ዳግም መዘዘው

 
መንግስት አላዋጣ ሲለው ጥሎት የነበረውን ካርታ ዳግም መዘዘው
እውን ይህ ካርታ ይሳካለት ይሆን?

የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መብታችን ይከበር በማለት አሃዱ ብለው ከተነሳንበት ጊዜ አንስቶ በመንግስት አካላቶች በተደጋጋሚ በሚዲያቸው፣በጋዛጣ እንዲሁም በሚያዘጋጁት መፅሄቶች ላይ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት ትግላችንን ለማሸማቀቅ እና ለዘመናት ተቻችለን እና ተከባብረን ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር የመኖር ባህላችንን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ብዙ ሲዳክር ቆይቷል፡፡
ሆኖም ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነው በማለት የክርስቲያን ወገኖቻችንን ድጋፍ ለማግኘት ቢጣጣርም
እውነታውን ግን እየዋለ እና እያደረ ለሁሉም እየተገለጠ በመምጣቱ መንግስት አስቦት የነበረው ኢስላማዊ መንግስት የምትለዋ ካርታ አላዋጣ ብላ ብሎም ኪሳራ ውስጥ ከተተችው፡፡
ሟች ጠ/ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ በመሰናበቻ የፓርላማ ንግግራቸው በኢትዬጲያ ውስጥ የሙስሊሞች ቁጥር ይበልጣል፡፡ መንግስት ያንሳል ማለቱ ስህተት ነወ፡፡ ከሃገሪቱ ካለው ህዝበ ብዛት የሙስሊሙ ቁጥር
ስለሚበልጥ ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን በማለት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው እነዛ ጥቂት ሰለፊዬች በማለት የኢትዬጲያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በሃሰት መዳመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡
የሆኖ ሆኖ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የእምነት ወኪሎቻችንን እኛው እንምረጥ ነው ያልነው አይደለም ሸሪአዊ መንግስት ለመመስረት ማሰብ ይቅርና የሸሪአ ፍርድ ቤታችን እንኳን ይስተካከል ብለን አልጠየቅን በማለት በመላው ሃገሪቱ አንድ አቋም መያዙን ያስተዋለው መንግስት ስቦት የነበረው ካርታ ለጊዜው አላወጣኝም በማለት መልሶ ለመክተት ተገዶ ነበር፡፡ ኮሚቴዎቻችንም ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነበር በማለት ክስ ያቀረበባቸውን በማንሳት ጨዋታውን አክራሪነትን ለማንገስ የሚደረግ ሩጫ በሚል ቀይረውት ነበር፡፡
ህዝበ ሙስሊሙም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመብቱ መከበር ያለውን ቁርጠኝነት እየጨመረ መምጣቱን የተመለከተው መንግስት የውስጥ ሰዎችን ልኮ ትግሉን ለማቀዛቀዝ ሞከረ፡፡አሁንም ዳግም አልሳካ አለው፡፡በሙስሊሙ እና በመንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በዚሁ ሁኔታ መቀጠሉ አብዛሃኛው ማህበረሰብ ችግሩ ምኑ ጋር እንዳለ ለመረዳት አስቻለው፡፡የመንግስት የቅርብ ወዳጅ የሆኑት እነ አሜሪካም እንኳን ሳይቀሩ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አሸባሪዎች እንዲሁም ፅንፈኞች አይደሉም ሲሉ በአንደበታቸው ተደመጡ፡፤
በምስራቅ አፍሪካ የሽብር ስጋት ቀጠና መሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ቢታወቅም በኢትዬጲያ በኩል ግን ከውስጥ አንዳችም ፅንፈኝነት ምልክት አለመታየቱን አለም አቀፍ ድርጅቶች መሰከሩ፡፡
መንግስት በቻለው አቅም አላማውን ለማሳካት የቀደዳቸው በሮች በሙሉ ለመንግስት ሽንፈትን እንጂ ድልን ሊያስገኙለት አልቻለም፡፤በተደጋጋሚ ሙስሊሙን እርስ በእርስ ለመከፋፈል ሱፊ ሰለፊ ብሎ ቁማር ተጫወተ፡፡ አልተሳካም ዞር በል ተባለ፡፡ ቀጠለ ፅንፈኛ አክራሪዎች መጡላችሁ ብሎ ሰበከ፡፡የሚሰማው ጠፋ፡፡ ድራማ ሰርቶ አቀረበ፡፡ሁሉም ህዝብ በተውኔቱ ደካማነት ሳቀበት ብሎም አላገጠበት፡፤አተርፋለው ብሎ ያላሰበው ኪሳራ ውስጥ ከተተው፡፡
በመንግስት በኩል ተሰልፈው የነበሩት አካላትም ጥያቄ አለን በማለት ገሸስ ማለትን አስቀደሙ፡፡ ይህ አልወጥልህ ያለው መንግስት የመጨረሻ የሚለውን ካርድ ለመሳብ ተገደደ፡፡
በደሴ ከተማ ዋና አጋሩን ሼህ ኑሩን አስከወዲያኛው አሰናበታቸው፡፡ሰውየውን በሂወት እያሉ ከጌታቸው ከአላህ ጋርም ከህዝብ ጋርም አጣልቶ ተጠቀመባቸው፡፤ ግብአተ መሬታቸውንም ካፋጠነ ቡሃላም ከፍተኛ ጥቅም ለማጋበስ ሩጫውን ቀጠለ፡፡፡፤
ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ማህበረሰብ ለመለያየት እና ለማጋጨት ሼህ ኑሩ ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሩ፡፤አክራሪዎች ገደሏቸው፡፡ እኔ መንግስት ፅንፈኞች አሉ ስላችሁ አልሰማ አላችሁኝ በማለት ተቋርጦ የነበረውን አስትንፋሱን ለመመለስ መፍጨርጨር ጀመረ፡፡ሼህ ኑሩን ወደ ቀጣዩ አለም አሰናብቷቸው መንግስት ግን የራሱን ቀጣይ የትግል ሜዳ አመቻቸባቸው፡፤
ከሼህ ኑሩ ሞት ቡሃላም ሌላ አንድ ተጨማሪ ካርታ ተመዘዘ፡፡ ባንዲራ(ሰንደቅ አላማ!!!!!!!). ይህን ሰንደቅ አላማ አዋረዱት አለ፡፡ በመቶሺዎች የሚቖጠሩ ሙስሊሞች በተገኙበት ቦታ አንድ ወጣት ልጅ ከአንዋር መስጂድ ጣሪያ ላይ ያገኛትን በዝናብ እና በፀሃይ የተበጣተሰች ባንዲራ ከወደቀችበት በማንሳት አውለበለባት፡፡ይህ ድርጊቱ በኢቲቪ ካሜራ ስር ገባች፡፤በሚዲያም አቀረቧት፡፡
በእርግጥ የባንዲራው ካርታ ቀደም ተብሎ የታሰበባት ጉዳይ ናት፡፡ ከዚህ ቀደም ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኢትዬጲያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዳይታይ ሲደብቁ ተስተውለዋል በማለት መወንጀሉ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ ሁላ ሩጫ ቡሃላ በኑር መስጂድ በተካሄደው አስገራሚ ተቃውሞ ልቡ የደነገጠው መንግስት ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ባንዲራ አቃጠሉ በማለት ድራማ ሰርቶ በሚዲያ አቀረበ፡፡የክርስትና እምነት ተከታዬችን ለመኮርኮር እና በሙስሊሞች ላይ ለማነሳሳት ከፍተኛ ስራ ሰራ፡፡በሁሉም ሚዲያዎቹ ይህን ድራማ በሙስሊሞች ስም ሰርቶ ካራገበ ቡሃላ በፊት መዞት ወደነበረው ካርታ ተንደርድሮ ተመለሰ፡፡
የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ኢስላማዊ መንግትስት ለመመስረት ነው ሲሉ በድጋሚ አወጁ፡፡በኢድ አደባባይ ያን ሁላ ሺህ ህዝብ ደብድበው ጥቂት ሰለፊዬች ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን በማለት ባስነሱት ግርግር እና ሁከት ችግሩ እንደተፈጠረ በመግለፅ ለሚሊዬኖች ሙስሊሞች ንቀታቸውን አሳዩ፡፡
በግብፅ የጠፈጠረውን የፖለቲካ ትኩሳት በመመርኮዝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ከግብፅ እርዳታ እንደሚያገኙ እና ኢስላማዊ መንግስትም ለመመስረት እየሰሩ እንደሚገኙ መስበኩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
በኢድ ሰላት በመላው ሃገሪቱ የተካሄደውን ተቃውሞ ለመግታት ሙሉ ሃይሉን ተጠቅሞ ለማቀዘቀዝ ቢሞክርም ሳይሳካለት የቀረው መንግስት የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊትም ለመሸፋፈን እና ትቶት የነበረውን ካርታ ዳግም በመምዘዝ በሚዲያ በመቅረብ ክርስቲያኖች ሆይ ንቁ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱባችሁ እየታገሉ ነው የሚል እንድምታ ያለው መልዕከት ከጠ/ሚኒሰተሩን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚህ ሁለት ቀናቶች ውስጥ መግለጫቸውን ለሚዲያ ሰተዋል፡፡
ውድ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ሆይ መንግስት እንደ አዲስ የመዘዛት ካርድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ኪሳራን እንጂ ትርፍን እንደማያጋብስለት እሙን ነው፡፡ አዲስ በተጀመረው ፕሮፖጋንዳ ላይ ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር መንግስት ለመፍጠር የፈለገውን እኛን የማጋጨት ስራ ለማክሸፍ ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ቀደም ባዳበርነው ልምድ በመነሳት ይህን ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ለማክሰም ይከብደናል ብዬ አልገምትም፡፡በመሆኑም ሁላችንም በኩላችንን ለክርስቲያን ወገኖቻችን የትግላችንነ እውነታ እና የመንግስትን ቅጥፈት በማጋለጡ ስራ ላይ ለመሳተፍ ቆርጠን መነሳት እንደለብን መልዕክቴን በማቅረብ ሃሳቤን እዚህ ላይ እቋጫውው፡፡

አላህ እውነታውን የምናሳውቅ እና ከሁሉም እምነት ተከታዬች ጋር ኢስላም ባስተማረን መልኩ ተከባብረን የምንኖርባት ሀጋር ያድርግልን፡፡
አቡ ዳውድ ኦስማን ኦስማን
To get more information like this page
https://www.facebook.com/abudawdosman

https://www.facebook.com/abudawdosman

 

 

 

Aug 8, 2013

ፌደራል ፖሊስ በረመዳን ጾም ፍቺ በሙስሊሞች ላይ ድብደባ ፈጸመ

ከመሐመድ
ፖሊስ የኛ አይደለም ሊሆንም አይገባውም፡፡ “ፖሊስ” ለዚህ ጽሁፍ ሲባል “ኢህአዴግ” የተባለ የማፊያዎች ስብስብን
ለመጠበቅ ህዝብን በአደባባይ ሊያሸብር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የደደቦች ስብስብ ነው፡፡ ፖሊስ ደደብ ነው፡፡
ማገናዘቢያውን በኢህአዴግ የሽብር ቡድን የተቀማ ህጻናት ፣ ሃረጋውያን ፣ ነብሰ ጡር ፣ ሴት ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ፣
መንገደኛ መለየት የተሳነው እንሰሳ ነው፡፡ ፖሊስ ክብሪት ነው፡፡ አምጣ የወለደችውን እናቱን ለመደብደብ የማያቅማማ
ቅል ራስ፡፡
ጉዞ በጦር ቀጠና….
ከብሔራዊ …በአዋሽ ወደ ኮሜርስ….. ቱርርር ድጋሚ ወደ አዋሽ ባንክ ፣ በአርቲስቲክ ወደ ብሔራዊ ባንክ ሆም
መዘክር ፣ ታጥሯል መንገዱ ቱርርር ወደ ተገኘው ቅያስ ሰዎች ተደብድበዋል ፣ መስገጃ ፣ ጫማዎች ፣ አማይማ ፣ ኮፊያ
፣ የተፈነከቱ ሰዎች ፣ የተያዙ ወጣቶች ፣ ረጃጅም አጠና የያዙ የባንዳው ውሾች ፣ በፋራረሱት መንደሮች አቆራርጠን
እዚያችው ትንሽ ፈቀቅ ብለን…
አትሩጡ …አትሩጡ… ጥግህን ያዝ!! ጥግጥጉን ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር … የተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች
የሙስሊሙ እስር ቤት ሆነዋል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በብዙ ውሾች መሃል የተያዙ
ወንድሞቼን ተመለከትኩኝ….አንዱ ውሻ ጋረደኝ ሁሉንም ለመቁጠር አልቻልኩም ……..አንድ ..እእ….ሁለት
ተነጥለው ሌላ …ሁለት…. ወዲ…ያ ….ሌሎች የታሰሩ ግን በስንቱ መስሪያ ቤቶች ስንቱ ሙስሊም ታስሯል…!
መስሪያ ቤቶች ባጠቃላይ (ያሲን ኑሩ በሆነው ሲዲው ላይ አጀልህ ከደረሰ ሁሉም ነገር አንተን ለመግደል ሰበቢያ
መሆን ይችላል ብሎን ነበር) ሙስሊሙን ለማሰር አፋቸውን ከፍተው ሲጠብቁን አስተዋልኩ…ናሽናል ጂዎግራፊ ቲቪ
ላይ በብዙ ነብሮች የተከበበችውን ሚዳቋ ትዝ አለችኝ… ከመንጋዋ የተነጠለችውን አንዷን ሚዳቋ ጥቂት የነብር
መንጋ ከበው ሲበሏት ለመን መንጋው አይታደጋትም ስል ጠየኩ…..ዛሬም ከጀምአው እየነጠሉ የሚደበደቡትን
ወንድሞቼን ለመርዳት ሳይሞክሩ ነብስን ለማዳን የሚራወጡት ወንድሞቻቸውን ለመርዳት ከሚናዝኑት ከብዙው
የህዝን መንጋ ጥቂቱን ብቻ አስተዋልኩ…ጥቂት ናቸውና የባንዳው ሰራዊት በቀላሉ አጠቃቸው…. አንድም ባስ አልተሰበረም ፣
አንድም ድንጋይ ሲወረውር የተመለከትኩት ሰው አልነበረም፡፡ በእርግጥ …..መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም ፣ እራሱ ገዳይ እራሱ ከሳሽ ፣ በሃገራችን ሰላም አጣን ፣ መንግስት የለም ወይ ፣ እንትን የህዝብ ነው (ይሄን እኔ አላልኩም) ፣ ኢቴቪ ፣ዛሚ ፣ ፋና፣ መንግስት ፣ ወዘተረፈዎች ሌባ ናቸው ብለናል፡፡ የህዝብን አደራ የበሉ ፣ ከህዝብ አብራክ ወጥተው ህዝብ ላይ ቁልቁል የሚተፋ ወሽካታ አድርባይነታቸውን ነግረናቸዋል፡፡ ጥፋታችን በግፍ
የታሰሩብንን መሪዎቻችንን እንዲፈቱልን መጠየቃችን
ነበር፡፡ በሃይማኖት ጣልቃ አትግቡብን ፣ ህገ
መንግስቱ ካልተተገበረ የወረቀት ነብር ነው ብለን
ብሶታችንን ማሰማታችን …….
በአጠና ተነረትን ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፊት ለፊት
ግንቡ ጥግ ስር እራሱን ስቶ የወደቀው በግምት
እድሜው ወደ ስልሳዎቹ የሚጠጋው አዛውንት መሃል
አናቱ ተበርቅሶ ደሙ እየፈሰሰ ማንም እንዳይረዳው
የባንዳው ሰራዊት ከበው ሞቱን ይጠብቃሉ ፣ ጉዞ ወደ
ጥቁር አንበሳ!! ብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ ፊት ለፊት ያለው የባንዳው ሰራዊት ጣቢያ ፊት ለፊት ባለው ሚዲያን/
የአስባልት አካፋይ ተዘርግፈው የወደቁ ሰዎች ይታዩኛል ፣ አንድ አባት ከሁለት (በግምት የአስራ አራት እና ከአስራ
ስምንት የማይበልጡ) ልጆቹ ጋር አፈር መስለው ሶስቱም በባዶ እግራቸው የሰውዬው ኮት በጭቃ ጨቅይቶ የሴቶቹ
ልብሶች አፈር መስሎና ጸጉራቸው ተንጨባሮ በቢታንያ ክሊኒክ ቅያስ ብቅ አሉ፡፡ የሰራዊቱ ጣብያ በር ላይ ደም ረግጠን
በቅያስ ወደ ሞሃ እድገት በስራ ት/ት ቤት ደረስን፡፡ ከጦር አውድማው ወጥተን መስሎን ጫማችንን ሱሪያችንን ልናነጻ
ቀልባችንን ልናረጋጋ ሊስትሮ ፍለጋ ስንኳትን ከእናቱ ጋር የተለያየ አንድ ከአስራሁለት አመት የማይበልጥ ልጅ አይኖቹ
ወዲያ ወዲህ ሲሉ አይን ለአይን ተገጣጠምን፡፡
እየተቅለሰለሰና እየተርበተበተ “ከእናቴን ጋር ተጠፋፋን ወደ መሳለሚያ 01 መንገዱን አሳዩኝ..” ሲል ልመናውን
አቀረበ፡፡
እናቱ ታየችኝ!! ልክ ብሔራዊ ባንክ ጋር ጥጉን ካሰለፏቸው ሰዎች መካከል አንዲት ነብሰ ጡር ሁለት ልጆቿን ይዛ
ርህራሄ የማያውቁትን እነዚህን የባንዳውን ሰራዊት ያዝኑላት ዘንድ ስትለምናቸው…ሚጣ በሚሯሯጡት ሰዎች ተረግጣ
እሪሪሪ ስትል ከልጇ እኩል የምታነባዋ ብሔራዊ ቲያትር ጋር የየኋት እናት በአይኔ ይዞሩ ጀመር፡፡
“እናትህ ስልክ ይኖራታል..!” የኔ ጥያቄ ነበር ከልጁ ይልቅ የእናቱ ጭንቀት በአይኔ እየዞረ…
“የላትም!”
“ና” በል! ጉዞ በሞሃ ወደ በርበሬ በረንዳ…ከአብነት ፣ ከምራብ ፣ ከተክለሃይማኖትና ከሜክሲኮ ያሚመጡ መንገዶችን
የሚያገናኘው መስቀለኛው መንገድ ላይ ሊስትሮ ስንፈልግ ከተክለሃይማኖት ቱርርር እያሉ አናታችን ላይ ሊወጡ …
ወደ ጭድ ተራ ቱርር…ሃደሬ ሰፈር ውስጥ ውስጡን ሰዎች ይሯሯጣሉ ዞር ስል ልጁ ከአጠገቤ የለም!! የት ገባ!! በቃ
አንድ ሰው ያሳየዋል ብዬ ጥሩውን ጠረጠርኩ!! ከጭድ ተራ ወደ ምናለሽ ተራ ምናለሽ ተራ ጋር የሰላም ቀጠና ነው
ብለን እርግት ፣ ቅዝቅዝ ፣ ትክዝ ፣ ፍዝዝ እንዳልን…ከወደ ሰላም ባልትና አካባቢ ቱርርር ወይ ዛሬ!! ምናለሽ ተራ
ያላትን ቁሶች ኁላ ቆሽ…ኮሽ…ስብር …ብረታብረቶችን ድስጣድስጦችን ፣ ማንኪያዎችን ምናምኖችን ሽክም ይዞ
ቱርርር ….የጭንቅ ቀን አይመሽም!! በሃያሁለት ቀበሌ ወደ ድሬ ህንጻ ሰባተኛ፡፡ አሁን ሰላም ነው፡፡
ስለምን ይሄ ሁላ ውርጅብኝ….አንድም ጠጠር እንኳ ባላነሳ ህዝብ ላይ ግን ለምን!!
የመንግስትን መግለጫ ለማዳመጥ ሞባይሌን አውጥቼ ዛሚን ከፈትኩ …ኤንሶ ኤንሶ…ይላል…ወደ መስተዳድሩ ኤፍ
ኤም….አይኬ ..ጫምባላላ ይላል…ወደ 97.1 የእስፖርት ዝውውር ይዘግባል አንዱን ሃገር በቀል ተጫዋች
ጋብዘው….98.1 የአምስት ሰዓት ዜና ጀመረ…ጆሮዬን ሰክቼ ቀልቤን ሰብስቤ በትካዜ ማድመጥ ጀመርኩ፡፡
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት አቶ እከሌ በአዲስ አበባ እስታዲየም በመገኘት መንግስት ድህነትን
ለመቀነስ በሚያደርገው እርብርብ ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለውን አስተዋጽዎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት
አስገነዘቡ፡፡ የኢድ ሶላትም ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በአዲስ አበባ እስታዲየም በሰላም ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ
ከኢዜአ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል” ብሎ ኩም አደረገኝ፡፡ አሁን አመመኝ፡፡ አሁን ጆሮዬን ጠዘጠዘኝ፡፡ /…./

ሰበር ዜና ! የፌደራል ፕሊስ እርምጃ እየወሰደ ነው !!

ድምፃችን ይሰማ

Ethiopian Muslims Ethiopian Muslims
እስከ አሁን ባለው መረጃ በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤ፣ በደሴ፣ በአዳማ፣…የመንግስት ታጣቂዎች የዒድ ክብረ በዓልን ለመፈጸም የወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ኃይል የተቀላቀለበት ድብደባ ፈጽመዋል፡፡ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሙስሊም ዜጎቹ ያለውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ በዛሬውም በኢድ በዓል ቀን አሳይቷል፡፡


ፖሊስ ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ያሉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሲንደረደር

በፌዴራል ፖሊሶች አረመኔያዊ ድብደባ የተፈጸመባቸው አረጋዊ በነፍስ ውጪ ግቢ ላይ፡፡ እኒህም ግለሰብ አሸባሪ ናቸው? ምስሉ የተነሳው አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ነው፡፡


Aug 6, 2013

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እና የመቀሌያችን መታፈን ከነመፍትሄው! (ግርማ ሞገስ)

voice of millions1
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል። አንድነቶች የኢትዮጵያን ጸረ-ሽብር ህግ ለማሰረዝ የዜጎች ፊርማ በማሰባሰብ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቀድሞውን የግብጽ ፕሬዘዳንት ሞርሲን ከስልጣን የማውረድ እንቅስቃሴ ያስጀመረው ከአስራ አምስት ሚሊዮን በላይ የሚገመተው የግብጾች ፊርማ ከተለያዩ ከተሞች የተሰበሰበው በሶስት ወሮች ነበር። በግብጾች አይን ሲታይ አንድነቶች በሶስት ወሮች አንድ ሚሊዮን ፊርማ ማሰባሰብ አይችሉም ብለን መገመት ያዳግተናል። እርግጥ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ትግል ባህል እና ክህሎት እንደ ግብጾች ብዙ አልዘለቅንም። ይሁን እንጂ ካሰብነው ቁጥር እንደምንደርስ ጥርጥር የለኝም። የአንድነት መሪዎች መታሰር ቢደርስባቸውም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የመጀመሪያው ዘመቻ በጎንደር እና በደሴ ከተሞች ሐምሌ 7 ቀን በስኬት ተፈጽሟል። በጎንደር እና በደሴ ከተሞች የዜጎች ፊርማዎች ተሰብስበዋል።
ባለፈው ሳምንት ደግሞ አንድነቶች የየከተሞች አስተዳዳሪዎች እና የጸጥታ ኃይሎች የሚፈጽሙባቸውን የወከባ፣ የመኪና ጎማ በማስተንፈስ መጓጓዣ የማሳጣት፣ የቢሮክራሲ ጫና፣ የአካል ድብደባ እና እስር የተለመደ ጽዋቸውን በቻይነት እና በሆደ ሰፊነት በመቀበል እሁድ ሐምሌ 28 ቀን ከመቀሌ በስተቀር በወላይታ፣ በጂንካ፣ በአርባምንጭ እና በባህርዳር ሁለተኛውን ዘመቻ በስኬት አጠናቀዋል። ይኽን በውጣ ውረድ የተሞላ ዘመቻ አንድነቶች ሳይታክቱ፣ በትዕግስት፣ በፅናት፣ በአርቆ አስተዋይነት እና በድስፕሊን በታነጸ አኪያሄድ ፈጽመዋል። አንድነቶች “አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡” የሚሉትን መርሃቸውን ምንም ሳይሸራረፍ በተግባር እየፈጸሙት ነው። ከህዝባቸው ጋር ታግለው ህዝባቸውን የመብቱ ባለቤት ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኛነት እያሳያዩን ነው። ሊመሰገኑ ይገባል። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው በአንድ ወገን ፀር-ሽብር ህጉን ለማሰረዝ ሰላማዊ ትግል ዘመቻ ስታደርጉ በሌላ በኩል ደግሞ ከቀድሞው የመገዳደል የፖለቲካ ትግል ባህላችን ወደ ሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ባህል ልታሸጋግሩን ታሪክ እየሰራችሁ ነው። ይኽን ሁሉ የምታደርጉት በአስጨናቂ እና በተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ እንደሆነ ህዝባችሁ ይረዳዋል። የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስበው በአገር ውስጥ እና ካገር ውጭ የሚኖረው ህዝባችሁ ስራችሁን በአክብሮት፣ በአድናቆት እና በኩራት እያስተዋለ ነው። በስራችሁ እና በስኬታችሁ ልትደሰቱ ይገባል። ታሪክ እየሰራችሁ ነው።
በጅንካ፣ በባህርዳር፣ በአርባምንጭ የምትኖሩ ዜጎቻችም ሐምሌ 28 ቀን ባደባባይ ወጥታችሁ፥ “የታሰሩ የፖለቲካ እና የነፃ ጋዜጣ እስረኞች ይፈቱ! መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር! መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም! ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!! የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ! ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!! የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ይከበር!! መብት መጠየቅን ከጸጥታ እና ከልማት ጋር ማያያዝ በአስቸኳይ ይቁም! የፓርቲ አባልነት በፍላጎት መሆን አለበት!!” በማለት የሰብዓዊ መብት ይከበር መልዕክቶች አሰምታችኋል። እነዚህ መልዕክቶቻችሁ እና ጥያቄዎቻችሁ የጅንካ ወይንም የአርባምንጭ ወይንም የባህርዳር ብቻ አይደሉም። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄዎች ናቸው። የአለም ህዝብ ጥያቄዎች ናቸው። የተባበሩት መንግስታትም እንዲከበሩ የሚታገልላቸው መሰረታዊ መብቶች ናቸው። በትናትናው ዕለት በወላይታ የሚኖሩ ዜጎቻችንም ስለአገራቸው አሳሳቢ ጉዳዮች በአደባባይ ተሰባስበው ተወያይተዋል። ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ስለዚህ በጅንካ፣ በአርባምንጭ፣ በባህርዳር እና በወላይታ የምትኖሩ ወንድሞች እና እህቶች በሙሉ ሐምሌ 28 ቀን ባደረጋችሁት የጥሩ ዜጎች ስራ ልትደሰቱ እና ልትኮሩ ይገባል።
በዚሁ ባለፈው ሳምንት ህውሃት በመቀሌ ድምጽ ማጉያ እንዳይሰማ በማድረግ እና አንድነቶችን በማሰር የታቀደው የመቀሌ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እንዳይሳካ አድርጓል። አምባገነኖች ከጠብመንጃ ይልቅ ነፃ ፕሬስ እንደሚፈሩ እናውቃለን። ባለፈው ሳምንት ግን በመቀሌ አምባገነኑ ህውሃት የድምጽ ማጉያ ሲያፍን አስተዋልን። ድምጽ ማጉያ አይገድልም።  ህውሃት ግን ለምን ድምጽ ማጉያ ይፈራል? ድምጽ ማጉያ እንደ ነፃ ፕሬስ ከአንድ ሰው የሚተላለፍን መልዕክት ለብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ እንዲደርስ ያደርጋል። አምባገነን ህውሃት የፈራውም እሱን ነው። ስለዚህ የሰብዓዊ መብት መከበርን አስፈላጊነት የሚቀሰቅስ የድምጽ ማጉያ ከሐምሌ 25 ቀን ጀምሮ በመቀሌ ስራ ላይ እንዳይውል ተደረገ በህውሃት። በተጨማሪ የአንድነቶችን የቅስቀሳ ቁሳቁሶች ህውሃት በአደባባይ በፖሊስ አስነጠቀ። በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እንዲሁም የትግራይ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ ክብሮም ብርሃነ እና አቶ አርአያ ፀጋይን አሰረ።  የመቀሌ ህውሃት አስተዳዳሪ እና የጸጥታ ኃይሎች እነዚኽን እና ሌሎች ማለቂያ የሌላቸው መሰናክሎችን በመፍጠር የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ በመቀሌ እንዳይሳካ አድርጓል። ህውሃት የመቀሌን ህዝብ አሳብ በነፃነት የመግለጽ ህገ-መንግስታዊ መብት ጥሷል። ወንጀል ፈጽሟል።
እንግዲህ ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት የሚሰብኩ ድምጽ ማጉያዎች፣ ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት የሚሰብኩ መኪናዎች፣ ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት እንዲከበር የሚጠይቁ በራሪ ወረቀቶች እሳት እና ጭድ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት በመቀሌ ህውሃት ወለል አድርጎ እንዲታየን አድርጓል። ህውሃት እና ሰብአዊ መብት እሳት እና ጭድ ናቸው። ግን ለምን? ከፍ ብለን እንዳነበብነው ደግሞ አንድነቶች በአንድ ወገን ፀረ-ሽብር ህግ ለማሰረዝ  ሰላማዊ ትግል ዘመቻ ሲያደርጉ እግረመንገዳቸውን በኢትዮጵያ ከቀድሞው የመገዳደል የፖለቲካ ትግል ባህል ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግር መሰረት እየጣሉ ነው። በዚህስ ረገድ ምን ይደረግ? ስለሆነም የዚኽ ጽሑፍ ግብ (1ኛ) ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት ለምን እሳት እና ጭድ ሆኑ? እና (2ኛ) የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግሩ ሳያቋርጥ እንዲዳብር እና በህዝባችን ዘንድ እንዲሰርጽ ምን እናድርግ? ለሚሉትን ሁለት መሰረታዊ (መርህ ነክ) ጥያቄዎች መልስ መስጠት ነው።
(1ኛ) ለምን ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት እሳት እና ጭድ ሆኑ? የመግደል አቅም የሌላቸውን እንደ ድምጽ ማጉያ አይነት ቁሳቁሶችን ህውሃት ለምን ሊፈራ ቻለ? ለሚለው ጥያቄ መልስ እንስጥ።
የመንግስት ስልጣን ከምርጫ ሳጥን ይመነጫል የሚለው የፖለቲካ ትግል ባህል በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚፈጸም ነው። ህውሃት ይኼን የፖለቲካ ባህል ከወሬ ባሻገር አያውቀውም። ባህሉም የለውም። በነፃ ምርጫ እመረጣለሁ ብሎም አያምንም። የመንግስት ስልጣን ከጠብመንጃ አፈሙዝ ይመነጫል የሚለው እርስ በርስ መጨራረስን በይፋ የሚሰብከው ፍልስፍና ነው የህውሃት የፖለቲካ እምነት። ህውሃት ተወልዶ ያደገው ይህን የፖለቲካ እምነት በመከተል እና በመፈጸም ነው። ይኽ የፖለቲካ ፍልስፍና ደግሞ ለስልጣን እንጂ ለሰብዓዊ መብት ዋጋ እንደማይሰጥ ግልጽ ነው። ትጥቅ ትግል እና ሰብዓዊ መብት የተባሉት ሁለት ነገሮች እሳት እና ጭድ ናቸው። ባጭሩ ትጥቅ ትግል እየሰብክ እና እያራመድክ ሰብዓዊ መብት አክባሪ ነኝ አትበለኝ ነው የምልኽ!!!
ህውሃት ሳያቋርጥ ለአስራ ሰባት አመቶች በእርስ በርስ ጦርነት ህዝብ አጫርሶ፣ መንደሮች አፍርሶ እና ህዝብን ለስደት ዳርጎ ለስልጣን የበቃ ድርጅት ነው። እንደሚታወቀው ህውሃት ቲ.አል.ኤፎችን በተኙበት አርዶ፣ ኢ.ዲዩ.ዎችን፣ ኢህአፖችን እና የደርግን ወታደሮች ፈጅቶ ነው እዚህ የደረሰው። በትግራይም ህውሃትን ከተቀላቀሉ ወጣቶች ውስጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ የፈለጉን በአረመኔነት ገድሎ፣ በውስጡም ቢሆን ከአምባገነኖቹ መሪዎቹ የተለየ አሳብ የነበሩዋቸውን አባላቱን እየፈጀ፣ ገበሬውን ስደተኛ እያደረገ፣ የውጭ እርዳታ ለማግኘት ድርቅ እልቂት በአረመኒነት እንዲባባስ እያደረገ ነው ለስልጣን የበቃው። ይህ ሁሉ ተግባሩ ህውሃትን የሰብዓዊ መብት አፍራሽነት የሻምዮንነት ማዕረግ ያስገኝለታል። ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት እሳት እና ጭድ ናቸው።
ህውሃት ስልጣን ላይ ከወጣም ወዲህ አገር አፈረሰ። የባህር በር አሳጣን። የአልቢኒያ እና የሶቪየት ህብረት አምባገነኖች የጻፉትን ቃል በቃል ቀድቶ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር ሞከረ። አልሰራ ሲለው በሽብር በማስተዳደር ላይ ይገኛል። የአገሩን ህዝብ ታሪክ ጠንቅቆ አውቆ፣ ቀደም ብለው የተፈጸሙ ስህተቶችን አስተካክሎ እና እንዳይደገሙ አድርጎ ህዝቡን አቀራርቦ አገር በመምራት ላይ የሚገኝ ቡድን አይደለም።
ስለዚህ ባለፈው ሳምንት ህውሃት በመቀሌ እና በሌሎች ከተሞች የፈጸማቸውን እንቅፋቶች እና ወደፊት ሰላማዊ ትግላችንን ለማራማድ በምናደርገው ጥረቶች ከህውሃት በኩል የሚገጥሙን ፈተናዎች ምንጫቸው ይህ የህውሃት ከሰብዓዊ መብት ማክበር ባህል ጋር እሳት እና ጭድ መሆኑ እንደሆነ መዘንጋት የለበንም። በህገ-መንግስቱ ውስጥ የተዘረዘሩት ሰብዓዊ መብቶችም ቢሆኑ የምዕራቡን አለም ለማጭበርበር እና የገንዘብ እርዳታ ለማግኛ እንጂ አምባገነኑ መለስም ሆነ ዛሬ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው የመኪና ጎማ አስተንፋሽ ወሮበላ ህውሃት ፍጽም አያምንባቸውም። ህውሃት የፖለቲካ ባህሉ መግደል ነው። ስብዕናው የተሟጠጠ ነው። ታሪኩ ደም ነው። ስለዚህ ህውሃት በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ስርዓት መገንባት የሚያስችለው ባህል ፍጹም የለውም። በዚህ ሁሉ ምክንያት ሰብዓዊ መብት የሚቀሰቅስን የድምጽ ማጉያ ህውሃት ቢፈራ ሊገርመን አይገባም።
(2ኛ) የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግሩ ሳያቋርጥ እንዲዳብር እና በህዝባችን ዘንድ እንዲሰርጽ እንዴት እንርዳ? ህውሃት አምባገነን ነው። አምባገነን ይፈራል። ህውሃት በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ አልወጣም። ህጋዊነት እንደሌላቸው ህውሃቶች ብልቦናቸው ያውቁታል። ስለዚህ ከጠበንጃ ይልቅ ህዝባዊ ነፃ መሰባሰብን፣ ህዝባዊ ነፃ ውይይትን እና ህዝባዊ ተሳትፎን ይፈራሉ። ህዝቡ በነፃነት የሚያደርጋቸው ነገሮች አምባገነኖችን ያስደነግጧቸዋል። ያስበረግጓቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላማዊ ትግል ወታደሮች ነን የምንል ሁሉ እነዚህን የአምባገነኖች ሁሉ መለያ መሰረታዊ ጸባዮች ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል። የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግር ቀላል እንደማይሆንም በቅድሚያ ልንገነዘብ እና ልንዘጋጅ ይገባል። የሰላም ትግል ሰራዊት ትግባሮች ድርብርብ ናቸው። ለምሳሌ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ለማኪያሄድ እንኳን አንድነቶች የሰላማዊ ትግልን ባህል ለህዝብ ከማስተዋወቅ በተጨማሪ በየከተማው የሚገኙ የህውሃት አስተዳዳሪዎች እና የፀጥታ ኃይሎችን ሲያግባቡ፣ ሲቻል ሲያላምዱ፣ እንዳይፈሩ እና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንዲያምኑዋቸው ሲጥሩ፣ ወደ ድርድር እንዲመጡ ሲያበረታቱ እና የመሳሰሉትን  ሲያደርጉ አይተናል። እንደ አስፈላጊነቱም የተመጠነ ‘የጀግኖች’ መውጫ በር መስጠት ሊያስፈልግ ይችላል። ይኽ ሁሉ መቼ መደረግ እንዳለበት እና እንደሌለበት እና የትኛው መቅደም እንዳለበት ማወቅ ያስፈልጋል።
የፖለቲካ ትግላችንን ባህል ሽግግር ለማፋጠን ህውሃትን የተጀመረው የፖለቲካ ባህል ሽግግር አካል ማድረግ ለሁላችንም ይጠቅማል። ይኽን ለማድረግ ሰለአምባገነኖች ፀባይ ከፍ ብለን የዘረዘርናቸውን ማወቅ እና ተገቢውን ስራ መስራት ይጠቅማል። የሰላማዊ ትግላችን ግብ ህውሃትን ለመበቀል አይደለም። በፍጹም። የሰላም ትግል ወታደር ግቦች ህዝባችንን ወደ ነፃነት፣ ዲሞክራሲ እና ልማት ማሸጋገር ነው። ይኽን ከስኬት ለማድረስ እራስን በዘመናዊ ሰላማዊ ትግል ንድፈ አሳብ እና አፈጻጸም መቃኘት ያስፈልጋል። እንደትናንቱ በሰላማዊ ትግል መዝገበ-ቃላት ትርጉሙ ብቻ መወሰን በቂ አይደለም። የሰላማዊ ትግል ክህሎታችንን ማዳበር አለብን።
ስለዚህ የመቀሌ አንድነቶች የወሰናችሁት የማፈግፈግ ውሳኔ የሚያመለክተው ብስለታችሁን እንጂ መሸነፋችሁን  አይደለም። በማፈግፈግ የሰላም ትግል ሰራዊትን ለነገ ማቆየት ጠቃሚ ነው። ይኽን አይነቱ  ማፈግፈግ መፍራት አይደለም። የሰላም ትግል ሰራዊት በመቀሌ ያላጠናቀቀው ተጨማሪ ስራ መኖሩን ተገንዝቦ ሰልፉን ወደፊት ማስተላለፉ አኩሪ እርምጃ ነው። አንድነቶች በመቀሌ የደረሰባችሁ ጠንካራ እንቅፋት እና ያደረጋችሁት አይነት ማፈግፈግ እነ ጋንዲም በዘመናቸው ትግላቸውን ወደ አዳዲስ ከተሞች ለማሰራጨት ጥረት ሲያደርጉ ደርሶባቸዋል። አፈግፍገዋልም። አንድነቶች ሰላማዊ ትግላቸውን በመቀሌ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና መስከረም 2006 ዓ. ም. ከመግባቱ በፊት ስኪታማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ጥርጥር የለኝም። ካለፈው ሳምንት አንድ ነገር ተምረናል። በመቀሌ የተሳካ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንደ ጅንካ፣ አርባምንጭ ወይንም ባህርዳር የአንድ እና ሁለት ቀን ቅስቀሳ እንዲሁም የጥቂት አንድነቶች ስምሪት ብቻ በቂ አይደለም። መፍትሄው ዘመቻውን ማጠናከር ነው። ተጠባባቂ ኃይል መመደብ ሊያስፈልግም ይችል ይሆናል። የስለማዊ ትግሉ ነፋስ ከመቀሌ ተነስቶ ወደ አክሱም እና አዲግራትም እንዲነፍስ ማድረግ ይጠቅማል። በመቀሌ የተከማቸውን የህውሃት ኃይል ለመበተን።
በአንድ ወገን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ በመቀሌና በቀሩት ከተሞች እንዲቀጥል ስንታገል በሌላ በኩል  ህውሃት አንድነት ፓርቲን ለመወንጀል እና ክትግል ሜዳ ለማስወጣት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖርም ከወዲሁ መገመት እና መከላከያውን ማዘጋጀት ይኖርብናል። ይኽን ምኞቱን ለማሳካት ህውሃት የተቻለውን በማድረግ ላይ ስለመሆኑ ባለፈው ሳምንት በወላይታ የአንድነት ፓርቲ የዞን አመራር አባል በሆነችውን በወ/ሮ ሀድያ መሀመድ ላይ የፈጸመው ተቋሚ መረጃ ነው። ህውሃት ካለ ምንም ምክንያት ወ/ሮ ሀድያ መሀመድን ካሰረ በኋላ የአንድነት ፓርቲ ህዝበ ሙስሊሙን ለአመፅ ያነሳሳል የሚል ሰነድ እንድትፈርም አግባባት። እምቢ አለች። ከዚያ ህውሃት ሊያስገድዳት ሞከረ። በኢንቢታዋ ጸናች። እስሩ ቀጥሏል። አንድነቶች ህውሃት ሊቀድማችሁ አይገባም። ለምሳሌ በወ/ሮ ሀድያ መሀመድ ላይ የተፈጸመውን በአገር ቤት እና በውጭ የሚኖሩ ዜጎች እንዲሁም ዲፕሎማቶች እንዲያውቁት ሰፊ ዘመቻ ማድረግ ይጠቅማል። ህውሃትን ተአማኒነት ለማሳጣት። ሌላም ይደረግ። ይኽ ፍራቻ አይደለም። ጀግኖች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ነው። አንድነቶች በርቱ!!!
አንባቢዎች ሆይ! አንድነቶች ፀረ-ሽብር ህግን ለማፍረስ እና የፖለቲካ ትግል ባህላችንን ለመቀየር የጀመሩትን ዘመቻ እንቀላቀል። እንርዳቸው! የተጀመረው አዲስ ታሪክ አካል እንሁን!!! የሚከተሉትን በማድረግም በመሰራት ላይ ባለው ታሪክ ማህተማችንን ማስቀመጥ እንችላለን።
ግርማ ሞገስ
ግርማ ሞገስ
እርዳታ፥ በገንዘብ!
እርዳታ፥ በአሳብ!
እርዳታ፥ መረጃዎች በፍጥነት በማሰራጨት!
እርዳታ፥ ፊርማዎች በማሰባሰብ!
እርዳታ፥ እንደገና በገንዘብ!
ድረ ገጻቸው፥ www.andinet.org
(girmamoges1@gmail.com)

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወያኔን እናስወግድ!! ከግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ሐምሌ 28 2005 ዓ.ም


ወያኔ ወገኖቻችንን እየገደለ፤ አገራችንን እና ሕዝቧን በሽብር እያመሰ ነው። ከአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች የወያኔ ሠራዊት ባልታጠቁና ባልተዘጋጁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥይት እያዘነበ ይገኛል። እስካሁን የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ማወቅ ቀርቶ መገመት እንኳን አዳጋች ነው። ሞስሊም ወገኖቻችን፣ በሕጋዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያምኑ ሰላማዊ ታጋዮች፣ ሕፃናትና አዛውንት የጥቃቱ ሰለባ ናቸው።

የወያኔ ግንባር ቀደም የጥቃት ሰለባዎች ሰላማዊነታቸው ለማሳየት እጆቻቸውን አስረው ፍትህ ሲማፀኑ የነበሩ ዜጎች ናቸው። ሕግ የማያውቀው ወያኔን በሕጋዊ መንገድ ታግለን መሠረታዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን ያሉ ወገኖቻችን በግፍ ተግደዋል፤ ተደብድበዋል፤ ተግዘዋል። የምዕራብ አርሲ ከተሞችና መንደሮች በአጋዚ ጦር ተወረዋል። አዲስ አበባም ውስጥ ዋይታ በርክቷል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ ፋሽስታዊ እርምጃ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ሁሉ የተሰማው መሪር ሀዘን ይገልፃል። እንደዚሁም ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ፣ ለተዋከቡ፣ ለተረገጡ፣ ለጅምላ እስር ለተዳረጉ ወገኖቻችን ሁሉ በደረሰባቸው በደል መቆጨቱን ይገልፃል።

ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ የእምነትም ሆነ ሌላ ማናቸውን ነፃነት ሊኖር እንደማይችል የትናትናና የዛሬው ድርጊት አንድ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ወያኔ በሥልጣን መንበር ላይ ውሎ ባደረ መጠን እንዲህ ዓይነቱ መርዶ መስማታችን የማይቀር ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራ እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወደግ አለበት፤ ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሰላማችን ዋስትና የወያኔ መወገድና በምትኩ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መተካት ነው ብሎ ያምናል። ስለሆነም በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን እና መሠረታዊ መብቶቻችን ተከብረውልን መኖር እንድንችል ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠን እንነሳ።

መጽናናት ለተገዱ ወገኖቻችን ቤተሰቦች!!!


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

በኮፈሌ የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ግልጽ አልሆነም በዋቤ መስጊድ ማን ቦንብ አፈነዳ? ለምን?


kofelie


ባለፈው ዓርብ በመላው አገሪቱ አንድ ወጥ የ”ድምጻችን ይሰማ” የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት የወጣውን መርሃ ግብር ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ እስከ ግድያ ሊደርስ የሚችል ርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የሚያመላክት መግለጫ አውጥቶ ነበር። የድምጻችን ይሰማ አመራር መሆናቸውን የሚገልጹት ክፍሎች ፌደራል ፖሊስ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ተቃውሞው እንዲቀር መመሪያ ማስተላለፋቸውን ይናገራሉ። በዋቤ መስጊድ ቦንብ ያፈነዳው ማን ነው? ለምን እንዲፈነዳ ተደረገ?
ፖሊስ በከረሩ ቃላቶችና በማስጠንቀቂያ አጅቦ ባወጣው መግለጫ  ” … አክራሪ ወሃቢ ሰለፊዎች ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረጉ ፖሊስ ለሚወስደው ርምጃ ተገቢውንና የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን” በማለት አስፈራርቶ ነበር። “ምንደኛ፣ ከውጪ በሚላክላቸው ንዋይ ዓይናቸው ታውሮ አርብ በመጣ ቁጥር በተመረጡ መስጊዶች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ …” በማለት በመግለጫው አስቀድሞ እንደፎከከረው በኮፈሌ ብቻ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት መድረሱ ተረጋግጧል።
አስፈላጊውን ድርጊት መርሃ ግብርና የተቃውሞ ደንብ በማስተዋወቅ ከአዲስ አበባ ለአሜሪካ ሬዲዮ መግለጫ የሰጡት አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳሉት አቶ መለስ በህይወት እያሉ በ1997 ተቃዋሚዎች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ከሰጡት ትዕዛዝ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መግለጫ በመተላለፉ ተቃውሞው እንዲቀር ተደርጓል።
ሰላማዊ የተባለውን ተቃውሞ ከማከናወን ቢቆጠቡም ከአርብ የጁምአ ስግድት አስቀድሞ በየቤቱ በመዘዋወርና በሰላማዊ መንገድ የአምልኮ ስርአታቸውን ለመፈጸም ወደ ተለያዩ መስጊዶች ካቀኑ ምዕመናን መካከል ቀላል ቁጥር የሌላቸው ታስረዋል። ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የድምጻችን ይሰማ ተወካይ ካንድ ሺህ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን አመልክተዋል።
ከመንግስትና የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪ ነን ከሚሉት አካላት የሚወጡትን መረጃዎች ሁለት ጽንፍ የያዙ በመሆናቸው በማጣራትና አግባብነት ያለው ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት የዝግጅት ክፍላችን ተቸግሯል። በዚህም የተነሳ የተሟላ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት እንዳለ ሆኖ ባብዛኛው ዘገባችን ከማህበራዊ ገጽ በሚገኙ ዜናዎችና ከመንግስት ድረገጾች እንዲሁም ከአሜሪካ ሬዲዮ ባገኘነው መረጃ የተወሰነ ሆኗል።
በኦፊሴል በማይገለጹ አድራሻዎች፣ በፌስቡክ፣ በተለያዩ የማህበራዊ አምዶችና ድረገጾች በየአቅጣጫው የሚወጡ ዘገባዎች እንዳሉ ሆነው፣ የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ መረጃ የሚሰጠው “ደምጻችን ይሰማ” የማህበራዊ ገጽ በምዕራብ አርሲ ኮፈሌ ልዩ ስሙ ዋቤ በሚባል ቦታ የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በወሰዱት ርምጃ የሟቾችን ብዛት አስራ አንድ እንደደረሰ አስታውቋል። ዘገባው ከሞቱት መካከል አንድ ህጻንና ሴት ይገኙበታል ብሏል።
የሲኤንኤን የአይን ሪፖርተር ደግሞ በተመሳሳይ ቀን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች 25 ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን አስነብቧል። ዜናው ከ1500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ያመለከተ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከል አንድ ህጻን አንደሚገኝ የአይን እማኙን በመግለጽ አመልክቷል።
የአሜሪካ ሬዲዮ ዘጋቢ የአካባቢውን ነዋሪዎች በምንጭነት ጠቅሶ እንደዘገበው ሀምሌ 26 ቀን 2005 ዓ ም የተከሰተው ግጭት መንስዓው በዋቤ መስጊድ ፖሊስ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ተከትሎ ነው። ህዝቡ የፖሊስን ድርጊት እየተቃወመ ሳለ በድንገት ቦምብ መፈንዳቱን ዘገባው አመልክቷል። ቦንቡን ከህዝብ ወገን የሆኑ እንዳላፈነዱትና ቦምቡ እንደፈነዳ ፖሊስ ጥይት በመተኮስ ሰዎችን መግደሉን ያስታወቀው የቪኦኤ ዘጋቢ፣ አስራ ሁለት የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ተናግሯል። የስድስቱን ሟቾች ስም ዝርዝር አስታውቋል። 1ኛ፣ ቱርኬ ሳቶ 2ኛ፣ መሐመድ ሃሰን 3ኛ፣ ሌንጮ 4ኛ፣ ኩርሴ ቱራ 5ኛ፣ ረሺድ ቡርቃ፣ 6ኛ፣ ሳፊ ቴሲሳ በየተራ ዘርዝሯል። ቦንብ ማፈንዳቱ ለምን እንደተፈለገ ዝርዝር መግለጫ አልተሰጠበትም።
በኮፈሌ የደረሰውን አደጋ አስመልክቶ ውስን ሪፖርት ያቀረበውና የመንግስትን አካላትን ለማነጋገር እንዳልቻለ ያመለከተው ይኽው ዘገባ፣ በስተመጨረሻ አገኘሁት ባለው ዘገባ መሰረት የቁስለኞች ቁጥር ሰላሳ አምስት መድረሱን ዘግቧል። መንግሥት ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ከማስታወቁ በስተቀር ተጨማሪ ያለው ነገር የለም። ከዚህ በተቃራኒ “የሙስሊሙ ህብረተሰብ አክራሪዎች የፈጸሙትን ድርጊት ተቃወሙ” የሚል ዜና አሰምቷል።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሻሸመኔ ፖሊስ ዘንድ ደጋግሞ በመደወል የተጣራ መረጃ ማግኘት ባይችልም  የሟቾቹ ቁጥር መንግስት እንዳለው ሶስት ሳይሆን ዘጠኝ እንደሚደርስ ስማቸውን ካልገለጹ የፖሊስ አባል መረጃ አግኝቷል። አባሉ ይህ መረጃ በአርሲ ኮፈሌና አካባቢው ብቻ የደረሰ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አላቸው።
የእንቅስቃሴው መሪ ከሆኑት መካከል የሚጠቀሰው ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በድምጽ ያስተላለፈው ዘገባ ሰዎችን በማነጋገር ጭምር ነበር። በዘገባው የእምነቱ ተከታዮች “ትዕግስታችን አልቋል” ማለታቸውንና “መስጊድ በጥይት ተበሳሳ ድረሱልን” የሚል መልዕክት ለጥንቃቄ በሚመስል መልኩ ማንነታቸውንና አድራሻቸውን ካልገለጹ አስተያየት ሰጪዎች በድምጽ አሰምቷል።
“ኢማሞቻችን አትሰሩ፣ ሐይማኖታችንን ለኛ ተው” በማለት ቅሬታቸውንና ተቃውሟቸውን የሚገልጹትን ለማፈንና ርምጃ ለመውሰድ መንግስት ከፍተኛ በሚባል ደረጃ የአጋዚ፣ የፌደራልና ፖሊስና የኦሮሚያ   አድማ በታኝ ፖሊስ ሃይል ማሰማራቱን ጋዜጠኛ ሳዲቅ ያነጋገራቸው ምስክርነት ሲሰጡ ለማዳመጥ ተችሏል።
በሙስሊም ሰላማዊ ሰላፈኞች ላይ የደረሰውን አደጋ ደምጻችን ይሰማ እንደሚከተለው አቅርቦታል።
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን!በኦሮሚያ አርሲ ዞን የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ!
ትናንት ማለዳ ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ገብተው በሰነዘሩት ጥቃት የሟቾች ቁጥር 11 ደረሰ፡፡ ከሻሸመኔ እስከ ኮፈሌ እና ዶዶላ ድረስ በሚያካልለው በዚህ የመንግስት ወታደሮች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እና የታሰሩ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል፡፡ በእለተ ቅዳሜ ምንም አይነት ተቃውሞም ሆነ መሰል እንቅስቃሰሴዎች በማይካሄድበት እና ባልተካሄደበት እለት የመንግስት ወታደሮች እስከገጠር ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ያለርህራሄ የቀጥታ ጥይት በመጠቀም የአካባቢውን ዜጎች ሲገድሉ ውለዋል፡፡
የመንግስት ቴሌቪዥን በተለመደ መልኩ ‹‹ጂሀድ ሲቀሰቅሱ እርምጃ ተወሰደባቸው›› የሚል ዜና ያሰራጨ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 3 ብቻ መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ መንግስት ቀድሞ በታሰበበት መልኩ በአካባቢው ከፍተኛ የወታደር ሰፈራ በማድረግና በተጠንቀቅ በማስቆም በፌዴራል ፖሊስ፣ አድማ በታኝ እና በወታደሮች በመታጀብ በአካባቢው ሕዝብ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡ አራት ኦራል መኪኖች ላይ የተጫኑ ወታደሮች አካባቢውን በመክበብ መስጂዶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጭምር ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በዚሁም የአካባበውን ታዋቂ የሃይማኖት መምህር፣ አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 10 ደርሷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የራሳቸውን መኪና መስታወት በመሳሪያ ሰደፋቸው በመስበር ‹‹ሕዝቡ ሰበረው›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት የሚያስችል ጥረት ሲያደርጉም ታይተዋል፡፡
መንግስት ምላሽ መስጠት የተሳነውን ሕገ መንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ በጥይት በዚህ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ባለፈው አመት በአርሲ ዞን አሳሳ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ አራት ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአማራ ክልል ገርባ ከተማና በሐረር ኢማን መስጂድ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ በድምሩ ከ13 ሰዎች በላይ ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተቀጥፏል፡፡ መንግስት የገደላቸውን ሰዎች በሙሉ ‹‹ለጂሃድ ሲያነሳሱ ገደልኳቸው›› የሚል ማስተባበያ ሲሰጥ ቢቆይም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አሁንም ይህ የመንግስት ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ቀጥሏል፡፡
አሁንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ተጨማሪ ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክተት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡፡
አላሁ አክበር!
መንግስት በበኩሉ በተቃራኒው “በኦሮሚያ ክልል ኮፈሌ ከተማ አክራሪ ሃይሎች ጉዳት አደረሱ” ሲል ነው ሶስት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ያመነበትን ዜና ያሰራጨው።
በኦሮሚያ ክልል ኮፈሌ ከተማ አክራሪ ኃይሎች ጉዳት አደረሱ
በኦሮሚያ ክልል ኮፈሌ ከተማ ዛሬ አክራሪ ኃይሎች በፈጠሩት ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በሰውህይወትና ንብረት ላይ አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ወረዳ ኮፈሌ ከተማ ውስጥ ዛሬ ሀምሌ 27/2005 አክራሪ ኃይሎች በፈጠሩት ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የሽብር እንቅስቃሴው በፖሊስና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም የኦሮሚያ ፖሊስኮሚሽን ጨምሮ አስታቋል፡፡ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ የእስልምና እምነትን ሽፋን በማድረግ ህዝብን የመከፋፈልና ሰላምን የማደፍረስ አጀንዳ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ አክራሪና ፅንፈኛ ቡድኖች በዛሬው ዕለት ከጧቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በምዕራብ አርሲ ዞን ዋቤ ከተማ የጀመሩት ሁከት ወደ ኮፈሌ ከተማ በመሸጋገሩ ፀጥታ ለማስከበር በተሰማራው የአካባቢው የፖሊስ ኃይልና በሁከቱ ተሳታፊዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሶስት ሰው ህይወት ማለፉና በሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በአክራሪ ቡድኖች ተቀናጅቶ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወናበድና ለሁከት በማነሳሳት ኮፈሌ ከተማ ላይ በዛሬው ዕለት ተቀስቅሶ በሰላም ፈላጊ የአካባቢው ህዝብና በፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ የሁከት ድርጊት አክራሪ ኃይሎች ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም በዚያው ዞን ገደብ አሳሳ ላይ ጁሃድ በማወጅ ሞክረውት ከነበረው የጥፋት እንቅስቃሴ የቀጠለ ነው፡፡
በኮፈሌ ከተማ በዛሬው ዕለት የተቀሰቀሰው የአክራሪ ኃይሎች የሁከት እንቅስቃሴ በሰላም ፈላጊው የአካባቢው ህዝብ ትብብርና በክልሉ ፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም ጽንፈኞች ኃይሎቹ ህገ መንግስቱን በመጻረር የህዝብን ፀጥታ ለማወክና በሰላዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የጀመሩትን እንቅስቃሴ ለማምከንና  የጥፋቱ አቀናባሪና ፈጻሚ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለህግ ለማቅረብ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት  ከመቼውም በላቀ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጾ ሰላም ወዳዱ ህዝብ ከመንግስት ጋር በመሆን አጥፊዎችን በማጋለጥና የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኦሮሚያ ፖሊስ  ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል።
ከመንግስት ወገን ከላይ እንደተገለጸው ቢቀርብም በአካባቢው መረጋጋት እንደሌለና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል። በከባድ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚጓጓዙት ታጣቂ ሃይሎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መግባባት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ በአካባቢው አንጻራዊ መረጋጋት ስለመስፈኑ ከገለልተኛ ወገን የተባለ ነገር የለም። ይልቁኑም ከአያያዝ ጉድለት እየተካረረ የመጣውን የሙስሊሞች ጥያቄና ባገሪቱ እየጠነከረ የመጣውን የጥላቻ ፖለቲካ አገሪቱን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራት ስጋታቸውን የሚገልጹ ተበራክተዋል።
ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረው የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ በግብጽ እንደታየው የአረብ ጸደይ የበርካታውን ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ድጋፍ ያገኘ ባይሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ዘንድ አድማሱን እያሰፋ መሄዱና መንግስትም ከቀን ወደ ቀን የሃይል ርምጃ መምረጡ በአገሪቱ ካለው በርካታ ፖለቲካና የማህበራዊ ችግች ጋር ተዳምሮ አገሪቱን ለከፋ አደጋ እንዳይዳርጋት ስጋት አንዳላቸው የሚገልጹ ክፍሎች “ሁሉም ወገኖች ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡና ችግሩን በሰላም ለመፍታት የሚችሉበት አግባብ ሊፈጠር ይገባል” ብለዋል። የክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ ግልጽ ድጋፍ አለመታየት የድምጻችን ይሰማ ጥያቄዎች (የመጅሊስ አመራር፣ የአህባሽ ጉዳይ፣ …) ሃይማኖታዊ በመሆናቸው ይሁን ወይም ሌላ ምክንያት በግልጽ የታወቀ ባይሆንም በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ኃይላት ሁኔታው ወደ አረብ ጸደይ እንዲቀየር ገና ከጅምሩ ጥሪ ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን በዚህ ሃሳብ ዙሪያ በተከታታይ የሚመለከታቸውንና ያገባናል የሚሉ ዜጎችን አስተያየት እንዲሰጡ በመጋበዝ በእርቅ አስፈላጊነት ላይ ተከታታይ ዘገባ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ያስታውቃል። ከዚህ በፊት በግልጽ እንዳስታወቅነውም አስተያየት ያላቸው ወገኖች በነጻነት ሃሳባቸውን እንዲሰነዝሩ ይጋብዛል። ከጉዳዩ አሳሳቢነትና አገራችንን ከማስቀደም አንጻር ለሚቀርቡ አስተያየቶች ማናቸውንም ገደብ የማናደርግ መሆኑንን ከወዲሁ እናስታውቃለን። ህዝብ ሊያውቅ የሚገባውን ሁሉ ማወቅ ይገባዋል፤ አገር ከሌለ ማንም ሊኖር አይችልም! (Photo: CNNiReport)

Aug 5, 2013

በግብረሰዶም ተጠርጣሪዎች ላይ የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ባለሙያ የምስክርነት ቃል ሰጡ


child-sex-abuse


ሁለት የ10 እና የ11 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የአራተኛና የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የግብረሰዶም ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ ስድስት መምህራን ክስ ላይ፣ ከዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በተጨማሪ አንዲት የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ባለሙያ ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የሙያ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሠረተውን የወንጀል ክስ በማየት ላይ ያለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰባተኛ የወንጀል ችሎት፣ ስማቸው በሚዲያ እንዳይገለጽ የከለከለላቸው የሳይኮሎጂስትና የሳይካትሪ ባለሙያዋ፣ በተጠርጣሪ መምህራን የግብረሰዶም ጥቃት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ሁለት ወንድ ሕፃናት፣ ለሦስት ጊዜያት አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ገልጸዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹንም ሆኑ የጥቃቱ ሰለባ ናቸው የተባሉት ሕፃናትን እንደማያውቋቸው የገለጹት ባለሙያዋ፣ ሕፃናቱን ከአራት ወራት በፊት ቃለ መጠይቅ እንዲያደርጉ ታዘው ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለሙያዋ ከሕፃናቱ ጋር ቃለ መጠይቁን ያደረጉት፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤትና በፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ጠቁመው፣ መጀመሪያ ከእናቶቻቸው ጋር ቀጥለው ደግሞ ሕፃናቱን ለብቻቸው ማነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡
ሕፃናቱን መጀመሪያ ከወላጆቻቸው ጋር ያነጋገሯቸው ስለማያውቋቸው ለመለማመድ መሆኑንና ቀጥለው ለብቻቸው ቤተሰቦቻቸውን ሳይፈሩ እንዲያነጋግሯቸው ማድረጋቸውን የገለጹት ባለሙያዋ፣ በምክር ወይም ድርጊቱን በማስጠናት የተሳሳተ ማስረጃ እንዳይሰጧቸው፣ ቃለ መጠይቁን ያደረጉላቸው እያጫወቱና ዘና እንዲሉ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ጠዋት ቁርሳቸውን ከበሉበት እስከ ማታ ከትምህርት ቤት ተመልሰው ወደ ቤታቸው እስከሚገቡበት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ያደረጉትን አንድ በአንድ እንዲያስረዷቸው በመጠየቅ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ባለሙያዋ የሚፈልጉትን በጨዋታ ዓይነት ተጎጂ የተባሉት ሕፃናት ምንም ሳይፈሩ የጠየቋቸውን ሁሉ በአግባቡ እንደመለሱላቸው አክለዋል፡፡
በተለያዩ ጊዜያትም ያንኑ ጥያቄ ሲጠይቋቸው በተመሳሳይ ሁኔታ ማስረዳታቸውንም አስታውሰዋል፡፡ ሕፃናቱ እንዴት ቀናቱን ሊያስታውሱ እንደሚችሉ ተጠይቀው ባለሙያዋ ሲመልሱ፣ ሕፃናቱ ቀኑን በትክክል ባያስታውሱም ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ በዓል ካለ ወይም በዚያን ጊዜ የማይረሳ ነገር ካለ እሱን በማስታወስ እንዲያስታውሱት ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ከተጠቂዎቹ አንዱ ቀኑን በደንብ አስታውሶ እንደነገራቸው የገለጹት ባለሙያዋ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል ያሏቸውን ሰዎች ስምና ድርጊት እንዳስረዷቸው ተናግረዋል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ሕፃናት ከድርጊቱ በኋላ የሚያሳዩት ባህሪ ካለና የጉዳዩ ባለቤት በሆኑት ሕፃናት ላይ ያዩት የባህሪ ለውጥ ወይም ምልክት ካለ እንዲያስረዱ ተጠይቀው፣ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ሕፃናት አራት ባህሪያትን ያሳያሉ፡፡ ፈሪ፣ ኃይለኛ (ተደባዳቢ)፣ ብቸኛ መሆንን መፈለግና ከፍተኛ የሆነ የወሲብ ፍላጎት የማሳየት ባህሪያት እንደሚያመጡ አስረድተዋል፡፡ ሌላው በትምህርት ላይ የሚያሳዩት ሁኔታ ሲሆን፣ በአንድ ትምህርት ላይ ብቻ ጎበዝ የመሆንና ሌላውን የመጥላት ወይም ፍላጎት ያለማሳየትና ደብተራቸውን ጥሎ የመምጣት ባህሪም እንደሚያመጡ ባለሙያዋ ገልጸዋል፡፡
ተጠቂ ከተባሉት ሁለቱ ሕፃናት አንደኛው የወሲብ ፍላጎት እንዳለውና እሱም እንዳረጋገጠላቸው የገለጹት ባለሙያዋ፣ ይኼ ስሜት ሲመጣበት ከማን ጋር ለማድረግ እንደሚፈልግ ጠይቀውት፣ ከወጣት ወንዶችና እንደ አስተማሪዎች ካሉ ወንዶች ጋር ማድረግ እንደሚፈልግ፣ ወንድ ሕፃናትና ትልቅ ሰው እንደማይፈልግ እንዳስረዳቸው ገልጸዋል፡፡ ይኼንንም ጥያቄ ያቀረቡለት በጥናት ሕፃናት የሚጠቁት በአብዛኛው በሚያውቁትና በቤተሰብ፣ ወይም ዘመድ መሆኑን ስለተረጋገጠ በቤታቸው ውስጥ ወንድሞችና አባት ስለሚኖሩ ከነሱ ጋር ያለውን ሁኔታ ለማወቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ሕፃናት ድርጊቱ እንደተፈጸመባቸው ወዲያውኑ የቤተሰብ እንክብካቤ፣ አማካሪ ዘንድ በመውሰድ የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ፣ ድርጊቱ እንዳልተፈጸመ ሆኖ እንዲሰማቸው ወይም ጥፋቱ የእነሱ እንዳልሆነ እንዲያስቡ ስለሚያደርጋቸው በቀጣይ ከሚደርስባቸው ተፅዕኖ ማዳን እንደሚቻልም ባለሙያዋ አብራርተዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እያደጉ ሲሄዱ እነሱም ወደ ተመሳሳይ ተግባር እንደሚያመሩ፣ ኃይለኞች እንደሚሆኑ፣ ከቤት ወጥተው ተስፋ በመቁረጥ ወደማይሆን ነገር ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም አክለዋል፡፡
መምህራኑ የተጠረጠሩባቸው ሁለቱም ሕፃናት ‹‹ትምህርት አስጠልቶኛል፤ ባልሄድ ደስ ይለኛል፤›› እንዳሏቸው ባለሙያዋ ጠቁመው፣ በጥናትም የተረጋገጠው ሕፃናት ድርጊቱ ከተፈጸመባቸው በኋላ ብቸኝነትን እንደሚመርጡ፣ ፈሪና ኃይለኛ እንደሚሆኑ መረጋገጡንና በእነሱም ላይ ምልክቱ ተግባራዊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች አንደኛው ተጠቂ ብዙ ትምህርት ቤቶችን እንደቀያየረና በሄደባቸው ትምህርት ቤቶች ጥቃቱ እንደደረሰበት በመጥቀስ፣ የድርጊቱን ፈጻሚዎች እንዴት ሊያውቁት እንደሚችሉ ጠይቀውት ከሆነ ባለሙያዋ እንዲያስረዱ ሲጠይቋቸው፣ በተለይ አንደኛው ተጠቂ ከፍተኛ የወሲብ ስሜት ስላለው፣ ተጠግቶ ስለግብረሰዶም እንደሚያወራቸው ነግሯቸዋል፡፡ ስሜታቸው ከፍተኛ ስለሚሆን ተጠቂዎች አንገት ሥር የመሳም፣ የመነካካት፣ በብልት አካባቢ መመልከትና መቀመጥ እንደሚያዘወትሩ ባለሙያዋ አክለው፣ በአንደኛው ሕፃን ላይም ይህንን ምልክት ማየታቸውን አስረድተዋል፡፡
ድርጊቱ በቤተሰብ ቢፈጸም በሌላ ሰው የማሳበብ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበትን አጋጣሚ በሚመለከት ለባለሙያዋ ጥያቄ ቀርቦ፣ ‹‹እውነት ነው፣ አድራጊውን በመፍራት በሌላ ሰው ላይ ያሳብባሉ፤›› ካሉ በኋላ፣ በሁለቱ ሕፃናት ቤተሰብ ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ሲጠየቁ፣ ድርጊቱ የተፈጸመው በትምህርት ቤት ውስጥ መሆኑን ብቻ መናገራቸውን አውስተዋል፡፡
ስድስት መምህራን በአንድ ሕፃን ላይ ተፈራርቀው ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ ልጁ ያለምንም ጉዳት ወደ ጨዋታ የሚሄድበት ሁኔታ ካለ እንዲያስረዱ ባለሙያዋ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ አንዳንድ ጊዜ ሊገጥም እንደሚችል፣ ግን የልጁ ሁኔታ እንደሚወስን ካስረዱ በኋላ፣ ይኼ የአካል ጉዳትን የሚመለከት በመሆኑና እሳቸውም በዚህ ዙሪያ ማብራራት እንደማይችሉ ተናግረው፣ የሕክምና ባለሙያ ማብራሪያ ሊሰጥበት እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሕፃናት ተፅዕኖው አብሯቸው አድጎ ትዳር በሚመሠርቱበት ጊዜ ከፍተኛ ችግር እንደሚያስከትልባቸው ገጠመኛቸውን በማስረዳት አደገኛነቱን ተናግረዋል፡፡
ሕፃናቱ የግብረሰዶም ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው በኋላ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ምርመራ በማድረጋቸው፣ ፍርድ ቤቱ የምርመራ ውጤቱን ተከትሎ በሰጡት ማስረጃ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሆስፒታሎቹ መታዘዛቸው ይታወሳል፡፡ በትዕዛዙ መሠረት ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ‹‹ባለሙያ የለኝም›› ብሎ ምላሽ ሲሰጥ፣ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግን ባለሙያ ሳይልክ በመቅረቱ፣ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲልክ ፍርድ ቤቱ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. የአካዳሚው መምህራን የተጠረጠሩበትን የግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል አስመልክቶ ለመዘገብ በፍርድ ቤቱ የተገኘ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ የሚታየው በዝግ ችሎት መሆኑን ገልጾ እንዲወጣ በማዘዙ ችሎቱን ሊከታተል አልቻለም፡፡
ዘጋቢው በፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ በመዋል መረጃውን ከችሎቱ ታዳሚዎች በማግኘት ውሎውን በተመለከተ ‹‹ጋዜጠኞች ችሎት እንዳይገቡ ተከለከሉ›› በማለት መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ችሎቱ ዝግ የሆነው በሌሎች መዝገቦች እንጂ በግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል የተጠረጠሩትን እንደማያካትት አስታውቆ፣ ችሎቱ በግልጽ መካሄዱን በመግለጽ ማስተካከያ እንዲያደርግ አዟል፡፡ ፍርድ ቤቱ እንደገለጸው፣ ሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ችሎቱ ዝግ እንዲሆን የተደረገው በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ እንደሚገኘው አንዳንድ ክሶች (ጉዳዮች) በዝግ ችሎት መታየት ስላለባቸው፣ የሪፖርተር ዘጋቢ ከችሎት እንዲወጣ የተደረገው በዝግ ችሎት መታየት ለሚገባቸው ጉዳዮች እንጂ፣ በግብረሰዶም ወንጀል ተጠርጥረው ለተከሰሱት ባለመሆኑ፣ ዘገባው ስህተት እንዳለበትና ይኼው እንዲገለጽ በድጋሚ አዟል፡፡
የሪፖርተር ዘጋቢ በዕለቱ ለብይን ተቀጥሮ የነበረውን የግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ለመከታተል በሰዓቱ ችሎቱን ታድሟል፡፡ ችሎቱ በዝግ እንደሚታይ በመግለጽ ታዳሚዎች እንዲወጡ ዳኛዋ ሲያዙ ዘጋቢው ወደኋላ በመቅረት ለፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ መሆኑን በመግለጽ መታደም እንዲችል ሲጠይቅ አልተፈቀደለትም፡፡ ውጭ ቆይቶ በተደጋጋሚ ለመግባት ሲሞክር የችሎት ፖሊሶች ‹‹ዝግ ነው›› በማለት ሊያስገቡት ሳይችል ቀርቷል፡፡ ችሎቱ እስከሚያበቃ እዚያው ቆይቶ ከችሎቱ ታዳሚዎች ባገኘው መረጃ መሠረት ሲዘግብ፣ ችሎቱ ጉዳዩን በዝግ ማየቱን በዘገባው አካቷል፡፡ ዘጋቢው የዕለቱን ችሎት በአግባቡ እንደዘገበ ቢታወቅም፣ ፍርድ ቤቱ መስተካከል እንዳለበት በማዘዙ በድጋሚ ለመዘገብ ተገደናል፡፡
ሌላው ፍርድ ቤቱ እንዲታረም ያዘዘውና ሪፖርተርም ስህተት መሆኑን አምኖ ተስተካክሎ እንዲነበብ አንባቢዎቹን የሚጠይቀው፣ የግብረሰዶም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል በተባሉት ሁለት ወንድ ሕፃናት ዙሪያ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡ የታዘዙትን የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ባለሙያን በሚመለከት ስለተሠራው ዘገባ ነው፡፡
በወቅቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠው የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ሠራተኛ ሆኖ ሳለ፣ የሪፖርተር ዘጋቢ ግን ቀደም ብሎ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በምስክርነት ቆጥሯቸው የነበሩትን የሥነ ልቡና ባለሙያን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በተፈጠረው ስህተትም ፍርድ ቤቱንና አንባብያንን ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)

Aug 4, 2013

ETHIOPIAN REGIME KILLS 25 PEACEFUL PROTESTERS AND ARREST 1,500 CIVILIANS

August 3, 2013 - Ethiopian government forces open fire on unarmed demonstrators throughout the country, killing 25 and injuring dozens more, according to Ethiopian activists who took part in the demonstrations. 

One witness says at least one child was among the the dead. He also stated government security forces arrested over 1,500 protesters on Friday. 

For over a year, Ethiopian Muslims have been holding peaceful protests and mosque sit-ins over the regime's human rights abuses against their community and interference in their religion.
you can see here more

Aug 3, 2013

የመቶ አመት ኢትዮጵያዊ እናት በስደት ለሚኖረው ልጃቸው ስለ ወያኔ አረመኔነት የይድረስ መልዕክት

የመቶ አመት ኢትዮጵያዊ እናት በስደት ለሚኖረው ልጃቸው ስለ ወያኔ አረመኔነት የይድረስ መልዕክት ። እኝህ እናታችን ባሁኑ ስዐት 100 አመት የሆናቸው ሲሆን ይህን መልክት ከተወሰኑ አመታት በፊት በስደት ለሚኖረው ልጃቸው የላኩት መልክት ነው ።

Total Pageviews

Translate