Pages

Dec 12, 2012

የመድረክ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዲያስፖራው እርስዎን ለምን አይወድም? በሚል በሃገር ቤት በሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ ለቀረበላቸው

የመድረክ
ከፍተኛ
አመራር
የሆኑት
ፕሮፌሰር በየነ
ጴጥሮስ
ዲያስፖራው
እርስዎን
ለምን
አይወድም?
በሚል በሃገር
ቤት
በሚታተመው
ሰንደቅ ጋዜጣ
ለቀረበላቸው
ጥያቄ “ዲያስፖራው 50 ዶላር ከፍሎ በዛች 50 ዶላር መንግስት ለምን አትገለብጡም ይላል” ሲሉ ምላሽ ሰጡ።
ፕሮፌሰር በየነ ለሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት አብዛኛው ምላሽ አነጋጋሪ ነው። ያንብቡትና የ እርስዎን አስተያየት ያካፍሉን።
በነገራችን ላይ ሚኒሶታን ጨምሮ ለወራት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የከረሙት ፕ/ር በየነ አንድም ህዝባዊ ስብሰባ
ከሕዝብ ጋር አላደረጉም። የየከተማው የመድረክ የድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮችም ከሕዝብ ጋር እንዲነጋገሩ ሁኔታዎችን
እንዳላመቻቹላቸው ልብ ይሏል።
በዘሪሁን ሙሉጌታ
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የአራት ፓርቲዎች “ግንባር” የሆነው የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው። ፕሮፌሰር በየነ
የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ቢሆኑም ከ2002ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ በኋላ የሚዲያ ተደራሽነታቸው ቀንሷል። በተለይ
ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እሳቸውን በተመለከተ ከተፃፉ ፅሁፎች ጋር በተያያዘ በመጠኑ ሻክሮ ቆይቶ
ነበር። ያም ሆኖ የተከሰቱ ችግሮችን በመተውና ለአንባቢዎቻችን ክብር በመስጠት ለቃለ-ምልልስ ተባብረውናል።
ለዚህም የፕሮፌሰር በየነ ተነሳሽነትና አርቆ አሳቢነት ሰንደቅ ጋዜጣ ትልቅ ክብርና እውቅና ትሰጣለች።
ባልደረባችን ዘሪሁን ሙሉጌታ በወቅታዊ የሀገሪቱ ፖለቲካ እና በተያያዥ ጉዳዮች ከፕሮፌሰር በየነ ጋር አራት ኪሎ
በሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ፋክልቲ ፅ/ቤታቸው አግኝቶ ከአንድ ሰዓት በላይ ቆይታ አድርጓል።
የቆይታቸውም ውጤት የሚከተለውን ይመስላል።
ሰንደቅ፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ ጊዜ በሚዲያ አይታዩም ምክንያቱ ምንድነው
ፕሮፌሰር በየነ፡- ሚዲያው እኔ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንዲያስተዋውቀኝ ወይም (promote) እንዲያደርገኝ ወይም
ያልተሟላ አጀንዳ ያለኝ ሰው አይደለሁም። ሊያናግረኝ የፈለገ ሚዲያ መጥቶ ያባረርኩት ሚዲያ የለም። ከዚህ ባለፈ
ግን በግድ ስሙኝ ብዬ የሚዲያዎቹን በር እያንኳኳሁ ቃለ-መጠይቅ አድርጉኝ የምል ሰው አይደለሁም። ስለዚህ
ከሚዲያ ሆን ብዬ የጠፋሁበት ምክንያት የለም። ምንአልባት የጠፋሁ የሚያስመስለው ከሰኔ ወር መጨረሻ አንስቶ
እስከ መስከረም መግቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ አልነበርኩም በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታመሙ፣ ሞቱ፣ አሉ፣ የሉም
በሚባልበትና በኋላም በለቅሶው ጊዜ እዚህ ሀገር አልነበርኩም። ለዚህ ነው ከሚዲያው ላልታይ የቻልኩት።
ሰንደቅ፡- በነገራችን ላይ ቢዘገይም በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ምን ተሰማዎት
ፕሮፌሰር በየነ፡- እንደማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሲሞቱ ማዘን ያለ ነው። መቼም በጦር ሜዳ ለመሞት እኔ ልቅደም፣
እኔ ልቅደም ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰብአዊ ፍጡር ተፈጥሮአዊ ሞት ሲሞት የሚደሰትበት ወይም የሚፈነድቅበት
ሁኔታ አይኖርም። እና እኔም እንደማንኛውም ዜጋ አዝኛለሁ። በተለይ በሽግግሩ ቻርተር ጊዜ አንስቶ ከማንኛው
የተቀዋሚ ፓርቲ አመራር በበለጠ የማወቃቸው ሰው ናቸው። ብዙ ጊዜ ፊት ለፊት ተነጋግረን እናውቃለን። ስለዚህ
የአካሄድና የአላማ ልዩነት ቢኖረንም የእሳቸውን ህልፈተ- ሕይወት እየተመኘሁና እየፀለይኩ የነበርኩ ሰው
አይደለሁም። 57 ዓመት አፍላ ዕድሜ ነበር ብዙ ቢቆዩ ጥሩ ነበር።
ሰንደቅ፡- ድንገት “መለስ ሞቱ” ሲባል ደንግጠው ነበር? በቀጣይስ ሀገሪቱ ምን ትሆናለች ሲሉ አሰቡ
ፕሮፌሰር በየነ፡- እንደማንኛውም ሰው የሚያስደነግጥ ነገር ሊኖር ይችላል። ሀገሪቱ ምን ትሆናለች ለሚለው
ኢህአዴጎች የተፈጠረውን ክፍተት ተሰካክተውም ቢሆን እሳቸው የቀየሱትን መስመር ተከትለው እንደሚሄዱ እምነቱ
ነበረኝ። ከዚህ ውጪ የፖለቲካ ክፍተት (Political Vacuum) ይፈጠራል የሚል ነገር በአዕምሮዬ አልነበረም።
ለዚህ ደግሞ የኢህአዴግን ፖለቲካ ስለማውቀው ነው። አቶ መለስ አብዛኛውን የቤት ሥራ ሰርተውታል። በላመ መሬት
ላይ የተዘራውን መሰብሰብ አዳጋች አይሆንም። “ፈለጋቸውን እንከተላለን” እያሉ እየተሽቀደዳደሙ ያሉትስ ለዚሁ
አይደል? ማን ለመለስ ባለሙዋል ይሆናል እያሉ ሽሚያ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው። የእኔም ግምት ይሄው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን ለዚሁ ዓላማ እንዳዘጋጁዋቸውም አውቅ ነበር። ነገር ግን ኢህአዴግ እሳቸው (አቶ
መለስ) ካስቀመጡት መስመር ከወጣ ገን ቀውጢን መጥራት ነው። ሕገ-መንግስቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሌሉ
ምክትሉ ተክቶ ይሰራል ስለሚል በዛው ቀጥለዋል። ከሕገ-መንግስቱም ባሻገር የአቶ መለስን ኀሳብ እንደወረደ
ከማስቀጠል ሌላ አማራጭ ያላቸው አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- አቶ መለስ አቶ ኃይለማርያም ተተኪአቸው እንዲሆኑ የፈለጉበትን ፖለቲካዊ እንደምታ ሊገልፁልኝ ይችላሉ
ፕሮፌሰር በየነ፡- መቼም የሰውዬውን አዕምሮ ጨርሶ ማንበብ አይቻልም። አቶ መለስ ግን አቶ ኃይለማርያም
የዓይናቸው ቀለም ስላማራቸው ብቻ ለሹመት አጭተዋቸዋል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል። በእኔ ግምት አቶ ኃይለማርያም
በጣም ውስብስብ በሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያደጉ አይደሉም። እሳቸው የቀለም ሰው ናቸው። እኛ በተማሪ
እንቅስቃሴ ያሳለፍነውን የማርክሲዝም፣ ሌኒኒዝምና የተራማጅ ፖለቲካ አቀንቃኝ አይመስሉኝም። ስለዚህ አቶ
ኃይለማርያም በአቶ መለስ ዙሪያ ካሉት በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ አልፈን መጥተናል ከሚሉት፣ በርዕዮተ ዓለሙም ግትር
ከሆኑት ታጋዮች የተሻለ አዳማጭ ይሆናሉ፣ የተማሩም በመሆኑ ለሚሰጣቸው አዳዲስ ኀሳቦችና ቀና አመለካከት
ይኖራቸዋል ብሎ መገመት ይቻላል። ነገር ግን የተከበቡት “ከማን አንሼ” በሚሉ የህወሓት ታጋዮች ነው። “ማንም
ከማን አባቱ ይበልጣል” የሚል አባባል ታጋይ ነበርን ከሚሉ ሰዎች ይታያል። እና አቶ መለስ በቀላሉ ከማይወርፍ ሰው
ጋር መስራት መርጠው ሊሆን ይችላል። ኃይለማርያምን ለስልጣን ያጩአቸው የፖለቲካ ድርቅና በሚያራምዱና ታጋይ
ነን በሚሉ ኃይሎች ተሰላችተውም ሊሆን ይችላል አቶ ኃይለማርያምን ከፊት ያመጣቸው በእርግጥ ይሄንን ስል ልሳሳት
እችላለሁ። ነገር ግን እንደ አንድ ታሳቢ ሊወሰድ ይችላል።
ሰንደቅ፡- አቶ ኃይለማርያም የተሰጣቸውን ከማስፈፀም ባለፈ ግልፅ የፖለቲካ ስልጣን የላቸውም የሚሉ ትችቶች
ሲሰጡ ይታያል። እርስዎም ይሄንን ትችት ይጋራሉ
ፕሮፌሰር በየነ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ከጅምሩ አስፈፃሚ ነው። አቶ መለስ ግን ከአስፈፃሚነት አልፈው ብዙ ነገር
ተቆጣጥረው ነበር። አሁንም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሳቸው ይህኑ ማለት ነው? ኢህአዴጎች ደጋግመው
እንዳሉት አመራራቸው ቡድናዊ አመራር ብለው ነበር። አሁን ግን የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ አቶ መለስ ነበሩ
ብለውናል። ከትንሿ ተራ ሰነድ እስከ ትልቁ ዓላማ የነደፉት አቶ መለስ ናቸው ብለውናል።
የትብብር አመራር ሲሉ አንድ ነገር ሁሌ ትዝ ይለኛል። በሽግግሩ መንግስት ጊዜ እኔ የትምህርት ሚኒስትር በነበርኩበት
ጊዜ አንድ የአቶ መለስ ዋርድያ (ጠባቂ) ያለኝ ነገር እስከአሁን ድረስ አልዘነጋውም። እኔ ወደ እሳቸው ቢሮ ስሄድ
“ወዴት ነው የምትሄደው?” አለኝ። ወደ ክቡር ፕሬዝዳንት መለስ ጋር ነው (በዛን ጊዜ ፕሬዝዳንት ነበሩ) “ለምንድ
ነው?” ሲለኝ ቀጠሮ አለኝ አልኩት። በእውነቱ በወቅቱ እኔ ወደውጪ ሀገር ለመሄድ ተልዕኮ ስለነበረኝ ከእሳቸው ጋር
አንዳንድ ኀሳቦች ለመለዋወጥ ነበር። እና ያ ዋርድያ “ቁም” አለና ስማቸውን መጣራት ጀመረ። እንዴ … “አንተ
“የሀገርን መሪ እንዴት በራፍ ላይ ሆነህ ትጣራለህ” አልኩት። “እሱም ቢሆን የተሰጠውን ስራ ይሰራል፤ እኔም
የተሰጠኝን ኃላፊነት እወጣለሁ” አለኝ። በዛ ጊዜ እውነትም የጋራ አመራር አለ ይሆን? በሚል ለማስመሰል ይሞከራል።
ሁሉም የየራሱን የስራ ድርሻ በመወጣት እኩል ይመስለን ነበር። በተማረውም ሆነ ባልተማረው ታጋይ መካከል
የእኩልነት ምልክቶች ያሉ ይመስል ነበር። አሁን ግን በእሳቸው ስም ብቻ ሲማል ስናይ በሚባለውና በሚሰራው
መካከል ልዩነት መኖሩን ያመለክታል።
የሆነ ሆኖ አቶ ኃይለማርያምን ስልጣን ይኖራቸዋል ላልከኝ መቼም የስልጣን ክፍፍል አለ ይባል የለ? የተሰጣቸውን
የስልጣን ድርሻ ይጠቀሙበታል ብለን እንገምታለን። ይህ ሲባል ግን ጥርጣሬ ሊኖር ይችላል። የህወሓት ካድሬዎች
የጠቅላይ ሚኒስትሩን መስመር ለማዝለቅ ሲሉ ከዚህ መስመር እንዳይወጡ ከበው ይከላከሉዋቸዋል ብሎ መገመትም
ይቻላል።
ሰንደቅ፡- ከሰሞኑ ተጨማሪ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሹመዋል፤ ይሄንንስ እንዴት ያዩታል
ፕሮፌሰር በየነ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የመሾማቸው ምስጢር
በህወሓት ካድሬዎች የመከበባቸው ምስጢር ሊሆን ይችላል። አቶ ኃይለማርያም የሁለቱን ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትሮች ሲያሾሙ በሕገ-መንግስቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራና ተግባራት መካከል የእኔ ድርሻ ያሉት አንድ
ሦስቱን ብቻ ነው። የቀረውን ደግሞ በክላስተር ነው … በምናምን ብለው አሳልፈው ሰጥተዋል። ይህም ማለት ጠቅላይ
ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብቻቸውን ሲሰሩት የነበረውን ስራ ለአራት ተካፍለውታል። ይህም ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ነው።
ከዚህ ቀደም የቀድሞ የፓርላማ አባል በነበርኩበት ዘመን ይህ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ተቃውመናል። ሹመቱ
ኢህአዴግ በራሱ ተነሳሽነትና በማንአለብኝነት የሚሰጠው በመሆኑ “በሕግ አምላክ” ስንል ተቃውመናል።
ሕገ-መንግስቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒሰትር ነው የሚለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ነገር ቢሆኑ፤ ‘‘ተክተው ይሰራሉ’’
ሳይሆን ‘‘ተክቶ ይሰራል’’ ነው የሚለው። ይህም ከሕገ-መንግስቱ አንፃር አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሾም
ያመለክታል “ሕገ-መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው። ማንኛውም ሕግና ልማዳዊ አሰራር፣ እንዲሁም የመንግስት
አካል ወይም የባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት የለውም” በሕገ-መንግስቱ
አንቀፅ ዘጠኝ ንዑስ አንቀፅ አንድ ላይ ሰፍሮ ይገኛል። በንዑስ አንቀፅ ሦስት ደግሞ ከዚህ ሕገ-መንግስት ከተደነገገው
ውጩ በማንኛውም አኳሃን የመንግስት ስልጣን መያዝ የተከለከለ ነው ይላል። በተጨማሪም በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ
75 ላይ ስለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በሚዘረዝረው ድንጋጌ ላይ “ሚኒስትር” እንጂ “ሚኒስትሮቹ” በሚል
ብዙሕነትን አያሳይም። ለምሳሌ በዚሁ አንቀፅ “ሀ” ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው
የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል ይላል እንጂ “ያከናውናሉ” አይልም በ“ለ” ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሰራሉ
አይልም። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ይላል እንጂ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ
አይልም። ሌላው በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 36 ላይ የሚኒስትሮችና ምክር ቤት ማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ምክትል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሮች በሕግ በሚወሰነው መሠረት ሌሎች የሚገኙበት ምክር ቤት ነው ይላል። ስለዚህ ሕገ-
መንግስቱ ተጥሷል። የሚገርመው “በሚኒስትር ማዕረግ” እያሉ ፓርላማው ያላፀደቀላቸው ከአራት በላይ ሰዎች አሉ።
“ሚኒስትር” ብለው ወደ ፓርላማው አያመጡም። ይሄ ደግሞ ኢ-ህገመንግስታዊነት ነው። አሁንም ይሄ ሁሉ የምክትል
ጠቅላይ ሚኒስትር ጋጋታ ምን የሚሉት ነገር ነው? እነዚህ የተሾሙት ሰዎች በሕገ-መንግስቱ መሠረት ተጠያቂ ናቸው?
እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም አንድ ነገር ቢሆኑስ ማን ነው የሚተካቸው? ሦስቱም በአንድ ጊዜ ጠቅላይ
ሚኒስትር ሊሆኑ ነው ወይስ ምንድነው? ሕገ-መንግስቱ በአማርኛ ነው የተፃፈው “ነው” እና “ናቸው” ‘‘ሚኒስትሮች’’
እና ‘‘ሚኒስትሩን’’ አናውቅም እንዴ?
ሰንደቅ፡- ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመበት ምክኒያት ስራን ለማከፋፈልና ለማፋጠን ነው ተብሏል።
በሌላ ወገን ደግሞ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ስልጣንን የማጋራት ይመስላልና የእርስዎስ ኀሳብ ምንድ ነው
ፕሮፌሰር በየነ፡- ገዢው ፓርቲ የሰከነና የበሰለ ቢሆን በአደባባይ እንደሚናገሩት እምነት ኖሮአቸው በጠቅላይ
ሚኒስትርነት ያስቀመጡትን ሰው ማገዝ ነበረባቸው። አሁን ግን ስልጣንን በኮታ የተከፋፈሉት ነው የሚመስለው።
ከተማው ውስጥ፤ ስልጣን ለአማራ፣ ለትግሬ፣ ለኦሮሞና ለደቡብ እያለ እንደሚያወራው ነው እነሱም የተከፋፈሉት።
ሰው እንኳ የሚያወራው ጊዜ ለማሳለፊያ ቢሆንም፤ እነሱም ወሬውን ሰምተውና ተከትለው ለወሬው ምላሽ የሰጡ ነው
የሚመስለው። ይሄ ደግሞ በጣም የሚያሳፍር ነው። ሰውዬውን (አቶ ኃይለማርያም) በተለየ ሁኔታ መደገፍ ሲገባቸው
ስልጣንን እንደ ፀበል ነው የተራጩት “ክላስተር” የሚል ነገር ደንቅረው ተራው ሰው የማይገባውን ነገር እየከተቱ
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማአት ያዥጎደጎዱት በመካከላቸው መተማመን ባለመኖሩ ነው። ይሄ ደግሞ በኢህአዴግ
አመራር ውስጥ መተማመን የለም የሚለውን ስነ-ልቦና የሚያሰርፅ ነው።
ሌላው “ታላቁ መሪ” በሚል የተጀመረው ነገር ነው። ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን የራስዎት ሰው
ይሁኑ ብያለሁ። አሁን ግን በቻይና ፖለቲካ የቀረውን የመሪን ተክለሰብዕና የመገንባትን ጉደይ በሰፊው ተያየዘውታል።
በዕርግጥ አቶ መለስ እያሉ በ2002ቱ ምርጫ ወቅት እኛ ለምርጫ ቅስቀሳ እንዳየነው፤ ምስላቸው ደቡብ ኦሞ ድረስ
ጫቃ ላይ ሁሉ ተሰቅሎ ነበር። እሳቸው ይወዳደሩ የነበረው እዛ ሰሜን አድዋ ሆኖ እያለ ደቡብ ኦሞ ምስላቸው
በየጫካውና በእየሾሁ ላይ በዛፍ ግንድ ላይ ሳይቀር ተሰቅሎ ነበር። እኛ አድዋ ላይ ምስላችንን ብንሰቅል ግን ሕገ-ወጥ
ብለው ያስሩን ነበር። አሁን ደግሞ ለይቶለታል። ቻይናዎች የማኦሴቱንግን የግል አምልኮ እራሳቸው በኮሚኒስት ፓርቲ
ውስጥ የታገሉት በእኛ ግን “ኸረ አበዛችሁት” የሚል ነው የጠፋው። አንድ ሰሞን አቶ ስብሃት ነጋ አቶ መለስ በህይወት
አሉ ወይስ የሉም ሲባል “አቶ መለስ በግለሰብነት ቢኖርም ባይኖርም ፓርቲው ይቀጥላል” ያሉትን አሁን መድገም
አቅቷቸዋል። አሁን “ታላቁ መሪ” የሚለው ጫጫታ ሲበዛባቸው አስተያየት መስጠት አቁመዋል። ዞሮ ዞሮ ይሄ ጠቃሚ
እንዳልሆነ የዓለም ታሪክ ያሳያል። ከቻይናም ይሄንንም ሊማሩ በተገባ ነበር።
ኢህአዴጎች በራሳቸው ስለማይተማመኑ ሁሉም ነገር በአቶ መለስ ዙሪያ ያደረጉት የፖለቲካ መስመሩን በመንደፉ፣
ለውይይት የሚበቃ ሰነድ በማዘጋጀቱም ሆነ በሌላ በልማት ዙሪያ እራሳቸውን ያላዘጋጁ መሆኑን ያሳያል። ፈረንጆቹ
እንደሚሉት የቀሩት ኢህአዴጎች Foot Soldier ወይም ለመሰማራት የተዘጋጁ እንጂ የሚያስቡ የሚያጠኑ ወይም
የሚመራመሩ አልነበሩም ማለት ነው። በተቀደደ ቦይ የመፍሰስ ነገር ነው።
ሰንደቅ፡- ቀድሞ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ህልፈት በኋላ በቀጣይ ዓመታት በኢህአዴግ ውስጥ የኀሳብ ልዩነት
ተፈጥሮ በኬኒያ እንደታየው ሁለት ተቀናቃኝ ኃይል ሊፈጠር እንደሚችል የሚገምቱ ወገኖች አሉ፤ ይህ አካሄድ
በኢህአዴግ ውስጥ ምን ያህል ርቀት ይጓዛል
ፕሮፌሰር በየነ፡- የኬኒያን ምሳሌ እንዴት ታመጣለህ? ኢህአዴግ እኮ መነሻው እንደ አለሎ ድንጋይ የጠጠረ
ከማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦሴቱንግ የወጣ ቡድን ነው። የእነ መለስ የርዕዮተ ዓለም መተክላቸውና ያደጉበት ጠጣር
አቋም አላቸው። የኬኒያ ግን ፖለቲከኞች ገንዘብ ሲያገኙ እኔ ከእገሌ እለያለሁ የሚሉ ገራገር ፖለቲከኞች ናቸው።
ገንዘብ ሲያገኙ እኔ ከእገሌ አለያለሁ የሚሉ እንጂ ጠጣር አይደሉም። ኢህአዴግ እኔ ያልኩት ካልሆነ በመቃብሬ ላይ
የሚል ኃይል ነው። ኢህአዴግ ግትር ነው አይታጠፍም። አጥፈዋለሁ ብትል ይሰበር ይሆናል እንጂ አይታጠፍም።
ፈረንጅንም እንዴት ማታለል እንደሚችሉ ተክነውበታል። እኛ እኮ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር አለ ለማለት’ኮ
ተቸግረናል።
ሰንደቅ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕልፈትና ያንንም ተከትሎ በመጣው ፖለቲካዊ ሁኔታ ተቃዋሚዎች ተጠቃሚ
የሚሆኑበት ዕድል አለ
ፕሮፌሰር በየነ፡- በሰው ህይወት ውስጥ ለውጥ እንደሚመጣ ባላሰብክበት ጊዜ ሁሉ በፖለቲካ ህይወት ውስጥም
ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ። በምን አጋጣሚና ሁኔታ የሚለው ቁርጥ አድርጎ መተንበይ አስቸጋሪ ቢሆንም ተቃዋሚ
ድርጅቶች አደረጃጀታቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው።
ሰንደቅ፡- ተቃዋሚዎች ባለፉት 21 አመታት ኢህአዴግን አልቻላችሁትም እኮ?
ፕሮፌሰር በየነ፡- እያስጨረስናቸው ነው። ማለቴ ሁልጊዜ ምርጫ ሲሉ ሂደቱን እናግዛለን በማለት የተቃዋሚ ካምፕ
በተለይ ሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሰው እንደሁኔታው የሚቀያየር ነው። በአንድ ሁኔታ ተስፋ ቆርጦ ቤቱ የሚገባ
አይደለም። ይሄንን ስርዓት እስከተቻለ ድረስ እየተነቀነቀ መቆየት አለበት። ተቃዋሚ ዝም ብሎ ስልጣን መያዝ ብቻ
አይደለም። በሂደት ሕዝብ ያነቃል ያስተምራል ያለውንም ስርዓት ያጋልጣል።
ሰንደቅ፡- ሃያ አንድ አመት ሕዝብን ለማንቃትና ለማስተማር በቂ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ’ኮ?
ፕሮፌሰር በየነ፡- በእኔ እምነት ትእግስት የሚያሳጣን ምክንያት የለም። ሌላ ቀርቶ በዲሞክራሲ አምስት መቶ አመት
ሞልቶአቸዋል በሚባሉ አገሮች እንኳ 40 እና 50 አመት ከታገሉ በኋላ ወደ ስልጣን የመጡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች
አሉ። ለምሳሌ የሜክሲኮ ፓርቲ 70 አመት ሙሉ አንደ ፓርቲ ነው ሲገዛ የኖረው። በዚህ ጊዜ ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች
የሉም ማለት አይደለም። ፈረንሳይ ሀገር ሶሻሊስት ፓርቲ ከ40 አመት በኋላ ነው ስልጣን ላይ የወጣው። የፖለቲካ
ስርዓቱ እንደኛ ሀገር ፅንፍ የረገጠ በማይሆንበት ሁኔታ ስልጣን ላይ ባይወጡም በሂደት ልዩነት ያመጣሉ።
ሰንደቅ፡- ይሁን እንጂ የፖለቲካ ስርዓቱ አልተስተካከለም እያላችሁ ባለበት ሁኔታ አሁን ካለው ትግል ይልቅ እጅን
አጣጥፎ መቀመጥ ይሻላል የሚሉ አሉ። እናንተም ቢሆን በከንቱ ከምትደክሙ አርፋችሁ ብታስተምሩ ይሻላል የሚል
ክርክር አለ?
ፕሮፌሰር በየነ፡- የለም… የለም… አሁን ለምሳሌ በጃፓን እንኳ ሶሻሊስት ፓርቲ ነበር። ስልጣን ላይ ወጥቶ የማያውቅ
ነገር ግን ሁልጊዜ ፓርላማ ውስጥ ይገባል። በገዥው ፓርቲ ላይ ውጥረት ይፈጥራል። እንዲህ እያለ ሕዝቡ ችግር ላይ
እንዳይወድቅ እየተከታተለ የሚቀጥል ፓርቲ አለ። የእኛ ሀገር ከዚህ ለየት የሚልበት ገዥው ፓርቲ ጨርሶ ለማዳመጥ
ፈቃደኛነቱ የሌለው መሆኑ፣ ጠርዝ የረገጠ አመለካከት የሚከተል በመሆኑ ነው። ክፋት፣ ቂም በቀለኛ እና ጨካኝ
በመሆኑ ነው።
ሰንደቅ፡- በእናንተ በኩል ችግር አለ። ሕዝብ ማደራጀት አልቻላችሁም የሚል ኀሳብ አለ። ሕዝብ ሳትይዙ ገዥውን
ፓርቲ ማንበርከክ አትችሉም እየተባለ ነው?
ፕሮፌሰር በየነ፡- ሕዝቡን ከዚህ በላይ እንዴት እንያዝ? ሕዝብ ላለመያዛችን ምን ማስረጃ አለ? ኢህአዴግ ሕዝብ
አልያዙም ብሎ ካሰበ ለምነ የምርጫውን መድረክ ክፍት እያደርግም? ሕዝቡን ለምን አንድ ለአምስት አደራጅቶ ድምፅ
እንዲሰጡት ያደርጋል? እኛ ሕዝብ የመያዝ ጉዳይ ችግራችን አይደለም። የማያውቁ ሰዎች ግን ሕዝብ አልያዙም ብለው
ሊያወሩ ይችላሉ። ተቃዋሚዎች ደካማ ናቸው ይሉናል። ደካማ ከሆንን ኢህአዴግ ለምን ይፈራናል? ስጋቱስ ከየት
መጣ? በ1997 ትንሽ በሩ ገርበብ ሲደረግ ሮጠን ስንገባ ኢህአዴግ ደነገጠ። እና ተቃዋሚዎች ደካማ ናቸው የሚለው
አልባሌ ወሬ ነው።
ሰንደቅ፡- መድረክ ከእነችግሩም ቢሆን ለምን የስነ ምግባር ደንቡን በመፈረም የተዘጋውን የድርድር በር አይከፍትም?
ፕሮፌሰር በየነ፡- የእነሱን እልህ ለመወጣት ብለን በሚሆነውም በማይሆነውም ይፈረማል እንዴ? እነ በረከት
እንደሚያውቁት ድርጅቴን በመምራት ብዙ ጊዜ ተፈራርመናል። ነገር ግን ፊርማው ከተፈረመበት ወረቀት ዋጋ የሌለው
ነገር እየሆነብን ነው የተቸገርነው። አቶ በረከት እንደ ሀገር መሪ በቁም ነገር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል። በየነን
አንበርክኬ አስፈረምኩት ማለት ምን ዋጋ አለው። አቶ በረከት በመፅሐፋቸው ላይ ‘‘አቶ መለስ ይሄንንማ እነ በየነ እሺ
ብለው አይፈርሙም’’ እያሉኝ እንደምንም እጃቸውን ጠምዝዤ አስፈረምኩ ማለታቸው ነውረኝነት ነው። በ1997
ቀውጢ ወቅት ሰላም ፍለጋ ላይ በነበርንበት ወቅት፤ አመፀኛ ከምትሏቸው ጋር እነርሱም ስላሉ ሳይሆን ምንም አይነት
ድርጅታዊ ቁርኝት የለንም ብለን ፈርመን ነበር። ያ ደግሞ የእውነታችን ነው። እኛ በነውጥና ጉልበት ለውጥ ላምጣ
ከሚለው አካል ጋር ውል የለንም። አሁንም የለንም። ይሄንን ይዘው እጃቸውን ጠምዝዤ አስፈረምኩ አሉ። አቶ በረከት
ገና በረቂቅ ላይ ለመነጋገር የተቀመጠውን ነገርና በመጨረሻ ይሄ ይግባ ይሄ ይውጣ ብለን የፈረምነውን ሳይለዩ
በመፃፋቸው ነው የፃፉት። ይሄ ደግሞ በጣም የሚያሳፍር ነው። የሀገር መሪ ሆነው የመንደር ልጆች አይነት ሽወዳ
መውረድ ደረጃችንን አይመጥንም።
የስነ ምግባር ደንቡ በተመለከተም አንደኛ ሕግ አድርገውታል። ሕግ አክባሪ ድርጅቶች ስለሆነ እናከብራለን።
ኢህአዴጐች የተባሉት (የተሸወዱት) የስነ ምግባር ደንቡን ወስደው በፓርላማቸው ሕግ ማድረጋቸው ነው። ሕግ
ባያደርጉ ኖሮ አሁን የሚሉትን ነገር ማንሳት ይችሉ ነበር። ነገር ግን አሁን ሕግ ሆኗል። የቀረው ነገር የእነበረከት እልህ
ነው። እና የበረከትን እልህ ለማርካት ስል ሄጄ ተንበርክኬ አልፈርምም። ይሄንን ዕድል ዕድሜ ልክ አያገኙትም። ምን
ሊያደርግልን?
ሰንደቅ፡- ኢህአዴግ የአመራር መተካካት ሲያደርግ በተቃዋሚ ጎራ በተለይም የእርሶ ፓርቲ እርሶዎን በሌላ አመራር
መተካት አልቻለም የሚል ወቀሳ ሲቀርብብዎ ይደመጣልና ስለዚህ ምን ይላሉ?
ፕሮፌሰር በየነ፡- እኔ የድንጋይ ዳቦ ዘመን ሰው አይደለሁም። 60 ገብቼአለሁ። ነገር ግን የስራ ፈት ወሬ ነው። አቶ
መለስም የተፈጥሮ ሞት ስለወሰዳቸው አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አየን እንጂ ምኑን ነው የተተካኩት። ማን በማን ነው
የተተካው? የመለመሏቸው ካድሬዎች ገና ወጣቶች ናቸው። የቀሩት ደግሞ አንጋሽ (king maker) ሆነው ከበው
ነው ያሉት። አሁን አንጋሾቹ ባለሙሉ ስልጣን ሆነው፣ የሀገሩን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው ማንን ነው የተኩት? ይህን ወሬ
የሚያስወሩት ኢህአዴግን ጠንቅቀው የሚያውቁትን የተቃዋሚ አመራሮች በምላሳቸው በመተንኮስ ካባረሩ በኋላ
የቀረውን በልምጭ እንነዳዋለን የሚል ፍላጎት ስላላቸው ነው። እኛ ከተማሪ ንቅናቄ ጀምሮ የህወሓት አባላት እነማን
እንደሆኑ እናውቃለን። እና ተቃዋሚውን በልምጭ እንነዳዋለን ብለው ነው ይሄንን የሚያስጮሁት። ይሄ ነገር ከሆነ
ቦታ ቱስ ያደርጉና እንደ ቄንጥ ‘‘መተካካት’’ እያሉ እንደ ባዶ በርሜል ይጮሃሉ። የእኛ ችግር የዕድሜ አይደለም እስቲ
የፖለቲካ ምህዳሩን ክፍት ያድርጉና የሚዳደር ወጣት እንጣ? በተማሪ እንቅስቃሴ ያለፈው ትውልድ የሚከበር ነው።
በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በርካታ ታሪክ የፈፀመ ትውልድ ነው። እስካሁንም ድረስ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለ
ወገን ነው እንጂ እንደማንም ዝም ብሎ ሆዳም አይደለም። ፎቅ እየካበ ሀብት እያካበተ የተቀመጠ አይደለም። ያ
ትውልድ አድር ባይ አይደለም። ገንዘብ የለመደ፣ አየር ባየር ነጋዴ ሳይሆን ሕይወቱንና ጊዜውን ለትግል የሰው ናቸው።
እና ‘‘መተካካት’’ እያሉ የእኛን ስም መስማት የመይፈልጉ ከሆነ እኛ ምን እናድርጋቸው ታዲያ?
ሰንደቅ፡- በአብዛኛ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራ) እርሶዎን የማይወዱዎት ለምን ይሆን?
ፕሮፌሰር በየነ፡- በመጀመሪያ ዲያስፖራውን አንተ ማወቅ አለብህ። ዲያስፖራውን ካላወቅክ ለምንድነው የሚለው
አይገባህም። እኔ በእርግጥ የራሴ ሰው ነኝ። አንዳንዶቹ የድርጅቶችን ነፃነት የሚጋፉ ናቸው። አንድ ስብሰባ ላይ መጥቶ
50 ዶላር ከፍሎ በዛች 50 ዶላር መንግስት ለምን አትገለብጡም ይላል። ያለው ኢህአዴግ ደግሞ የማይፈለጥ አለት
ነው። ዛሬ የተቃዋሚ አባል መሆን ፈተና ነው። ነገሩ የሂደት ጉዳይ ነው። ባለን አቅም ነው የምንገፋው። ቤቱን ሸጦ
ተቃዋሚ ፓርቲ እያንቀሳቀሰ ያለ የፓርቲ አመራር በመሀከላችን አለ።
ሰንደቅ፡- በተጨባጭ ቤቱን የሸጠ ሰው አለ?
ፕሮፌሰር በየነ፡- ይሄን በእርግጥ ግለሰቡ ሊናገረው ይችላል። ቢያንስ እኔ ስለማውቅ ነው። ቤታችሁ አትገቡም ወይ
ከምንባላውስጥ ቤት የሌላቸውን ስለማውቅ ነው። እና ወደ ዲያስፖራው ስመለስ ጯሂውን ከሰከነው መለየት
ያስፈልጋል። እና እኔ የጯሂው ዲያስፖራ ተላላኪ መሆን አልችልም። ነገር ግን ተባብሬ መስራት ግን እፈልጋለሁ። እና
አንተም የጯሂውን ድምፅ ነው የሰማኸው። ብዙ ግን የሰከኑ ኢትዮጵያውያን አሉ። ይሄ የፖለቲካ መልከኛ መሆን
የሚፈልገውን ጯሂውን ዲያስፖራ መተው ነው።
ሰንደቅ፡- ባለፉት 21 አመታት ብዙ ሰው ሲታሰር እርሶዎና ዶ/ር መረራ ታስረው አያውቁም የሚል ይባላልና…?
ፕሮፌሰር በየነ፡- እኛ በግ ነን እንዴ ኢህአዴግ በፈለገ ጊዜ የሚያስረን? ይሄ ደግሞ ካልተዋጠላቸው ሄደው ኢህአዴግን
ይጠይቁት። ኢህአዴግ ለእኛ የሚላላኩትን ታጋይ ልጆቻችንን እያሰረ አይደለም እንዴ? ይሄ ሁሉ አላዋቂነት ነው።
ሕዝብ ስላገለገልን መታሰር ያለብን አይመስለኝም።

Dec 11, 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Dec. 11 2012 Ethiopia

ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ: የሕሊና እስረኞቹ በቀለ ገርባ እና ኦልባና ሌሊሳ እንዲፈቱ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀ...

ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ: የሕሊና እስረኞቹ በቀለ ገርባ እና ኦልባና ሌሊሳ እንዲፈቱ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀ...: የሕሊና እስረኞቹ በቀለ ገርባ እና ኦልባና ሌሊሳ እንዲፈቱ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን በየፌስቡካቸው እያስቀመጡት ነው። (zehabesha.com) (ዘ-ሐበሻ) የመንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ...

የሕሊና እስረኞቹ በቀለ ገርባ እና ኦልባና ሌሊሳ እንዲፈቱ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን በየፌስቡካቸው እያስቀመጡት ነው። (zehabesha.com)

የሕሊና እስረኞቹ በቀለ ገርባ እና
ኦልባና ሌሊሳ እንዲፈቱ
የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ነው።
በርካታ ኢትዮጵያውያን
በየፌስቡካቸው እያስቀመጡት
ነው። (zehabesha.com)
(ዘ-ሐበሻ) የመንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል በተከሰሱት በአቶ በቀለ ገርባ የክስ
መዝገብ ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ፍርድ መስጠቱን የዘ-ሐበሻ የዜና ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አመለከቱ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪው አንደኛ ተከሳሽ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ኦልባና ለሊሳ ፣ ወልቤካ ለሚ ፣ አደም ቡሳ ፣ ሀዋ ዋቆ ፣ መሀመድ ሙሉ ፣ ደረጀ ከተማ ፣ አዲሱ ሞክሬና ገልገሎ
ጉፋ የቀረበባቸው ክስ “የኦሮሚያ ክልልን ከፌዴሬሽኑ ለመገንጠል ፣ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል በመሆንና ኬኒያ ድረስ በመሄድ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ” የሚሉ መሆናቸውን
የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቱ አስቀድሞ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ የተለያዩ የፍርድ ማቅለያዎችን ማቅረባቸውን ዘግበዋል።
በዚህም መሠረት በመንግስት አቃቤ ሕጎች “የአሸባሪነት ክስ” በቀረበባቸው ላይ አንድም ጊዜ በነጻ ፈትቶ የማያውቀው በሚል የሚተቸው ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የሰጠው ፍርድ
የሚከተለው ነው።
1ኛ. አቶ በቀለ ገርባ – በ8 ዓመት እሥር
2ኛ. ኦልባና ለሊሳ – በ13 ዓመት እስር
3ኛ. ወልቤካ ለሚ – በ7 ዓመት እስር
4ኛ. አደም ቡሳ – በ3 ዓመት እስር፣
5ኛ. ሀዋ ዋቆ – በ8 ዓመት፣
6ኛ. መሀመድ ሙሉ- በ 10 ዓመት እስር
7ኛ. ደረጀ ከተማ – በ8 ዓመት እስር፣
8ኛ. አዲሱ ሞክሬ – በ10 ዓመት እስር
9ኛ ገልገሎ ጉፋ – በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ ከሁለት እስከ አራት ዓመት ለሚደርስ ጊዜም ህዝባዊ መብታቸው ፍርድ ቤቱ መሻሩም ታውቋል።
በቀለ ገርባ በተለይ ከአቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኋላ የኦፌዴን ፓርቲን ጥሩ ተፎካካሪ ያደርገዋል ተብሎ የሚጠበቅ መምህር ነበር ሲሉ የሚያውቁት ይናገራሉ።
መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተደብቆ ተገኘ በተባለው መትረየስ እና ባዶ ሠንሰለት ምክንያት “የተንኮል ድርጊቶችን ግዙፍ በሆነ ዓይነት ማሰናዳት ወንጀል” በሚል ክስ ጭምር የተከሰሱት 9ኛው
ተከሳሽ ገልገሎ ጉፋ ከ1984 እስከ 2002 ዓ.ም የኦነግ አመራር አካል የነበሩ ሲሆን በ2002 ዓ.ም ግን ከሌሎች ከኦነግ አባላት ጋር ሆነው እጃቸውን ለመንግሥት ሲሰጡም የኦነግን ዓላማ
ኮንነው ሃገር ቤት የገቡ መሆናቸው ይታወሳል።

ዛሬ Mitu Abebe የምትባል እህታችን “ዱባይ ውስጥ ከ38ኛ ፎቅ ላይ ወርውረዋት ህይወቷ ላለፈው እህታችን ለቤተሰቧ መጽናናትን እንመኛለን ጓደኞቿ” ብላ በዚሁ በፌስ ቡክ ግድግዳ ላይ የለጠፈችውን የሟች ፎቶና የሐዘን መግለጫ ተመልክቼ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ወገን ኧረ መጨረሻችን ምንድን ነው????????????????

ዛሬ Mitu Abebe የምትባል እህታችን “ዱባይ ውስጥ ከ38ኛ ፎቅ ላይ ወርውረዋት ህይወቷ ላለፈው እህታችን ለቤተሰቧ መጽናናትን እንመኛለን ጓደኞቿ” ብላ በዚሁ በፌስ ቡክ ግድግዳ ላይ የለጠፈችውን የሟች ፎቶና የሐዘን መግለጫ ተመልክቼ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ወገን ኧረ መጨረሻችን ምንድን ነው????????????????

ዋ! ለኔ!
ዋይ! ዋይ! ልበልልሽ፣ እስኪ ደረት ልድቃ፤
የእኔም ተራ ደርሶ፣ መኖሬ እስኪያበቃ፤
ለምዷል እምባም ይርገፍ፣ ሙሾዬም ይደርደር
ዛሬም እንደ ትናንት፣ እ’ቴ ወጥታ ስትቀር፡፡

በዛ በበረሃ በዛ በሃሩሩ፣ ያ ሁል መንከራተት፤
ቢያልፍልኝ ብላ እንጂ፣ መች ለዚህ ነበረ፣ በሰው ጐዳና ላይ፣ ተደፍቶ ለመቅረት፡፡

ዋይ! ዋይ!
ማንም በሌለበት፣ ለሷ ተቆርቋሪ፤
እውነት በሌለበት፣ በደሏን መስካሪ፤
አዛኝ በሌለበት፣ አንስቶ ቀባሪ፤
ምነዋ ፈጣሪ!
እንዲህ እንባ ነጥፎ፤
በዳይ በግፍ ገዝፎ፤
ያንተው የእጅህ ስራ፣ እንደ ቅጠል ‘ረግፎ፤
ምነዋ ፈጣሪ! ኢትዮጵያን ዝም አልካት፤
በልጅ ሞት ስትከስል፣ ስታር እያየሃት?????????

Dec 10, 2012

‹‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው›› ዳዊት ከበደ (የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር)

‹‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው›› ዳዊት ከበደ (የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር)
Submitted by Admin on Mon, 12/10/2012 - 11:49

‹‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው››
ዳዊት ከበደ
የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር

በ97 ዓ/ም. በሀገራችን ተከስቶ በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ሣቢያ ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት እስር በኋላ በሂደት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን በየካቲት ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. አቋቁሞ ማሳተም ጀመረ፡፡ የሲፒጄ የ2ዐ1ዐ የኘሬስ ነፃነት ዓለም አቀፍ ተሸላሚ የነበረው - ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ፡፡ ህዳር 9 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም. ግን “ይቅርታዬ ተነስቶ እንድታሠር በመወሰኑ ከፍትህ ሚኒስቴር አስተማማኝ ምንጭ መረጃ አገኘሁ” በማለት ከሀገሩ ወደ አሜሪካ መሰደዱ ይታወሳል፡፡
ኤልያስ ገብሩም ለቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ በማንሣት ተከታዩን ቃለ-ምልልስ አድርጓል፡፡

አድዋ እንደተወለድክ አውቃለሁ፤ እስቲ ስለትውልድህና ስለልጅነት ህይወትህ ጠቅለል አርገህ ንገረኝ፡፡ አድዋ በመወለድህስ ምን ይሰማሀል?

በቅድሚያ እድሉን ስለሰጣችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ያው የተወለድኩት አድዋ
ነው፡፡ ያደግኩት ደግሞ አዲስ አበባ፡፡ አንዳንድ ሰዎች አድዋ መወለዳቸውን ብቻ እንደ ትልቅ ስኬት አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ እኔ ግን አይታየኝም፡፡ ሰው ፈልጎ ባመጣው ነገር ነው መኩራት ያለበት፡፡ እውነትም ፈልጌና መርጬ አድዋ ብወለድ ኖሮ እንደ ስኬት እቆጥረው ነበር፡፡ በተረፈ ከተወለድኩ በኋላ ነው የት እንደተወለድኩ ያወቅኩት፡፡ ስለዚህ አጋጣሚ እኔ የተወለድኩበት አካባቢ የተወለዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት ስለመሩ የዚህ ኩራቱ አይታየኝም፡፡ ከዛ ይልቅ መኩራት ያለብኝ አድዋ ላይ በተሰራው የጥቁር ህዝቦች ታላቅ ታሪክ ነው፡፡ ያ ታሪክ ደግሞ በሌላ የኢትዮጵያ ክፍልም ብወለድ ኖሮ ኩራቱ እኩል ነው የሚሰማኝ፡፡

ጋዜጠኝነትን መቼ ጀመርከው? ወደዚህ ሙያ እንድትገባስ ምክንያት የሆነህ ምንድነው?

ጋዜጠኝነትን መቼ እንደጀመርኩት ከመናገር ይልቅ፤ ለሙያው ትኩረት መስጠት የጀመርኩት ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ መናገሩ ይሻላል፡፡ የጋዜጠኝነት ፍቅር በውስጤ ማደር የጀመረው ገና የአራት አመት ልጅ እያለሁ ጀምሮ ነው፡፡ በወቅቱ ምንም የማውቀው ነገር ባይኖርም አባቴ አንድ አነስተኛ ሬዲዮ ይዞ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተመስጦ ሲሰማ በጣም ይገርመኝ ነበር፡፡ እና አስታውሳለሁ፡- በወቅቱ ለእኔ በጣም አስገራሚ የነበረው ‹‹እንዴት ነው የሰው ልጅ በእንደዚህ አይነት ትንሽዬ ነገር ውስጥ ሆኖ (ሬዲዮውን እያየሁ ማለት ነው) ሊያወራ የሚችለው›› የሚለው ነገር ነበር፡፡ ደግሞም በነገሩ ተገርሜ ዝም አልልም" አባቴንም እጠይቀው ነበር፡፡ ታዲያ ሁሌ እሱ በተመስጦ ሲሰማ እኔ ደግሞ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ደጋግሜ እየጠየኩ ሳስቸግረው አንድ ቀን ‹‹ስማ ጋዜጠኞች ናቸው፤ የሚያወሩት እዚህ ውስጥ ገብተው ሳይሆን ሌላ ቦታ ሆነው ነው፡፡ ስለዚህ እንደነሱ መሆን ከፈለክ ትምህርትህን ጠንክረህ ተማር!›› አለኝ፡፡

ከዛ በኋላ በትምህርት ቤት ግጥም ማንበብ፣ የተለያዩ ክበባት ውስጥ መግባት፣ ሚኒ ሚዲያ መሳተፍ ጀመርኩ፡፡ 12ኛ ክፍል ጨርሼ የማትሪክ ውጤት እስኪመጣልኝ ድረስ ባለው የክረምት ወር ከአዲስ አበባ ማስታወቂያ ቢሮ የሦስት ወር የጋዜጠኝነት ስልጠና ወሰድኩ፤ እግረመንገዴንም በአንዳንድ ጋዜጦችና መጽሄቶች ጽሁፍ እንዲወጣልኝ መስጠት ጀመርኩ፡፡ ከዚህ በኋላ የማትሪክ ውጤት መጣ፡፡ የመጣው የማትሪክ ውጤት በመንግስት የትምህርት ተቋም ሊያስገባኝ የሚችል ቢሆንም እኔ ግን ሁሌ የማስበው ጋዜጠኝነት ብቻ ስለነበረ በወቅቱ የጋዜጠኝነት ትምህርት የሚሰጠውን ዩኒቲ ኮሌጅ መርጬ ገባሁ፡፡ እና በዚህ መልኩ ነው ወደ ሙያው የገባሁት፡፡



በጋዜጠኝነት ህይወትህ ውስጥ የገጠመህን ፈተናና ውጣ ውረድ ብትገልጽልን? (ከሐዳር ጋዜጣ ጀምሮ እስከ ፊኒክስ - አሪዞና ድረስ የነበረህን ጉዞ ብትነግረን)

እንግዲህ ፈተና ሲባል ከትልቁ ነው መጀመር ያለብኝ፡፡ እኔ መጀመሪያ ያጋጠመኝ ፈተና ትልቁ ፈተና ነው፡፡ እስኪ አስበው በአንድ የክስ መዝገብ ውስጥ በስድስት የተለያዩ ክሶች መከሰስ ብቻ ሳይሆን" የእያንዳንዱ ክስ ቅጣት ደግሞ እድሜ-ልክ እና ሞት የሚያስፈርድ ሲሆን ምን አይነት ፈተና ብለህ ትጠራዋለህ? የ1997ቱን ፈተና ዱብ እዳ ከማለት ውጪ ምን ትለዋለህ፡፡ ደግሞም ከዛ በፊት ታስሬ አላውቅም፡፡ አንዳንዴ ፕሬስን የመሰለ ተቋም በአንድ አገር ሊኖረው የሚገባው ሚና እጅግ በጣም ትልቅ ቢሆንም" ይህ አይነቱ ተቋም ድምጥማጡ እንዲጠፋ የሚያደርግ ፍጹማዊ ስልጣን በጣም ጥቂት በሆኑ ግለሰቦች እጅ ውስጥ ገብቶ እንዳሻቸው ሲጫወቱበት ታያለህ፡፡ ሙያውና ሙያተኛው የሚተዳደርበት ህግን የሚያረቁት እነሱ፣ ሙያተኛም ተሰብስቦ እስር ቤት እንዲገባና በሞት እንዲቀጣ አቃቤ ህግ ሆነው የሚከራከሩት እነሱ፣ የአለም የፕሬስ ቀን በተከበረ ቁጥርም ይሁን በተለያዩ ኮንፈረንሶች ተገኝተው ‹‹የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ያላቸው የኤዲቶሪያል ነጻነት ለአለም ሁሉ ምሳሌና ትምህርት ይሆናል›› የሚል ስብከት የሚሰብኩትም እነሱ ናቸው፡፡ አየህ ኢንዱስትሪው ኃላፊነት እንዲሰማው ለማድረግ ሁሉንም የሚያስማማ ግልጽ የሆነ ተቋማዊ አደረጃጀትና ሁሉም በእኩል የሚስተናገዱበት ጽኑ መሰረት ያለው የህግ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡ አለበለዚያ ግለሰቦች እንዳሻቸው በታማኝነት አሊያም በቂም በቀል ውሳኔ የሚያስተላልፉበት፤ በየጀበና ቤቱ ማን ፍቃድ ሊነጠቅ እንደሚገባ፣ ማን መባረር እንዳለበት የሚወስኑበት አገር ነው ያለን፤ ያሳዝናል፡፡

ጥያቄውን በትክክል አልመለስክልንም?

ያው ስለውጣ-ውረድ ነው እየጠየቅከኝ ያለኸው፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ አሪዞና ድረስ ያለውን መንገድና ውጣ-ውረድ መዘርዘር አቅቶኝ አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ ውጣ-ውረድ እና እንቅፋት በስተጀርባ ያለው መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ ነው መታወቅ ያለበት፡፡ አውራምባ ውስጥ ዘገባዎችን ሚዛናዊ ለማድረግ ምን ያህል ርቀት ስንጓዝ እንደነበር ታውቃለህ፡፡ ያንን እያደረግን ግን የግል ጥላቻ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ያላቸው ‹‹ስልጣን›› ደግሞ የግል ጥላቻቸውን ለማራመድ ምቹ ነበር፡፡ እናም ያላቸውን ኔትወርክ ተጠቅመው ሳንወድ በግዳችን ከጨዋታው እንድንወጣ አደረጉን፡፡ ከኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እስከ ፍትህ ሚኒስቴር፤ በጉዳይ ፈጻሚነት ከሚያገለግሏቸው የግል ሬዲዮኖች፤ እስከ መንግስታዊው አዲስ ዘመን ድረስ ተረባርበው ስራቸውን ሰሩ፡፡ ከዛ ደግሞ ክራቫታቸውን አሳምረው በኪሳራ እንደዘጋነው ሊሰብኩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ ወጡ፡፡ ስለዚህ የውጣ-ውረዱ ማጠንጠኛ እዚህ ላይ ነው ያለው፡፡

አሁን ባለህበት አገር አሜሪካ ኑሮን እንዴት እየገፋኸው ( እየመራኸው) ነው? ለመሆኑ ምግብ ታበስላለህ?

ማንም እንደሚያውቀው ተገድጄ ነው የወጣሁት፡፡ በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው፡፡ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ወዳጆቻችን እንደሚሉት ሰው የሚሰደደው የተሻለ ኑሮ ለመኖር ነው፡፡ እኔ ያየሁት የተሻለ ኑሮ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ከሙያዬ ውጪ ሌላ ስራ እንኳን መስራት አልፈልግም፡፡ በመንፈስ ደረጃ ስደትም ሌላ እስር ቤት ነው፡፡ እንደምታውቀው ከአገሬ የወጣሁት በ 2004 ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ሁኔታዎች ይሻሻላሉ በሚል ተስፋ እስከ መጋቢት ድረስ የ‹‹አሳይለም›› (የጥገኝነት) ጥያቄዬን አላቀረብኩም ነበር፡፡ በኋላ ግን የግድ የሚዲያ ስራውን ስደት ላይ ሆኜ መቀጠል ስለነበረብኝ ህጋዊ የሆነ ማዕቀፍ ውስጥ ለመግባት ‹‹አሳይለም››(ጥገኝነት) ከመጠየቅ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ ስደት ካከበድከው ይከብዳል" ካቀለልከውም ይቀላል፡፡ ምግብ አበስላለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ሲሰለቸኝ ውጭ እመገባለሁ፡፡

እንደሚታወቀው አሁን ድረ-ገፅ አቋቁመሃል፤ ስራው አንዴት ነው? (ከጋዜጣ ስራ የሚለይበት ነገርስ ምንድን ነው?)

የድረ-ገጽ ስራ ከጋዜጣ ይለያል፡፡ ጋዜጣ በሳምንት አንዴ ነው የሚታተመው፡፡ ድረ-ገጽ ግን በየሰዓቱ የሚፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችን እየተከታተልክ ማቅረብ የግድ ይላል፡፡ ሌላ ዌብ ሳይት ቀድሞ ሳያወጣው የመጀመሪያ ለመሆን የምታደርገው ትንቅንቅ ደስ ይላል፡፡ ለምሳሌ ከዌብሳይቶች መካከል የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ህልፈት፤ የአቶ መለስን ዜና እረፍት (ከኢቲቪ ቀጥሎ) ቀድሞ ያወጣው ዌብሳይት አውራምባ ነው፡፡ ለምሳሌ ኦባማ በድጋሚ ተመረጡ ተብሎ በቀጥታ (ላይቭ) ሲነገር በ1 ደቂቃ ከ 15 ሴኮንድ ውስጥ ዜናውን ፖስት በማድረግ አውራምባ የመጀመሪያው ነው፡፡ የእድል ጉዳይ ሆኖ የአውራምባ ድረ-ገጽ በተመረቀ በሁለት ወር ውስጥ ነው ከፍተኛ ጎብኝ ካላቸው አንጋፋ ድረ-ገጾች መካከል አንዱ ለመሆን የበቃው፡፡ የዳያስፖራ የፖለቲካ ሙቀት ከምትገምተው በላይ ነው፡፡ ነገሮችን በኃላፊነት መንፈስ መርምረህ ገለልተኛ የሆኑ አቋሞችና አመለካከቶችን መያዝ ካልቻልክ ፈታኝ ነው፡፡ ልክ አገርቤት ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ መዘገብ የለብህም›› የሚሉ አምባገነኖች እንዳሉ ሁሉ፤ እዚህም በተመሳሳይ መልኩ እኛ የምንፈልገው ነገር ብቻ ነው መቅረብ ያለበት የሚሉ ‹‹የዳያስፖራ ሽመልስ ከማሎች›› አሉ፡፡ ልክ አገር ቤት ጸያፍ ስድብ የሚሳደቡ የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤቶች እንዳሉ ሁሉ እዚህም በመልክም በተግባርም እነሱን የሚመስሉ በሌላ ጽንፍ የተሰለፉ የፓልቶክ አድሚኖች አሉ፡፡ ይገርምሀል እንዲሁ ፈርዶብን የአምባገነንነት ችግር የትም ቦታ ነው የሚያጋጥመን፡፡ እጅ ላለመስጠት ቁርጠኛ መሆን ግን ግድ ይላል፡፡

ከዲሲ ወደ ኦሪዞና ግዛት ለምን ሄድክ? (ብዙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት መራቁ ለስራህ ጥሩ ነው?)

አዎ! ዲሲ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ የብዙ ፖለቲከኞችና ቲፎዞዎቻቸው መፈንጫ፤ የብዙ ፍላጎቶች መናኸሪያም ነው፡፡ ብዙ ዝግጅቶች፣ በርካታ ሰላማዊ ሰልፎችና ኮንፈረንሶችም ይከናወንበታል፡፡ ይህ ማለት ግን አገር ቤት ለሚደረገው ትግል አሊያም እንዲመጣ ለምንፈልገው ፖለቲካዊ መቻቻል የሚኖረው ፋይዳ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጽንፍ የያዘ የፖለቲካ አማራጭ አሉታዊ እንጂ አዎንታዊ ውጤት የለውም፡፡ ገና ለገና ነጻነት ያለበት አገር ላይ ነው ያለነው ተብሎ የሚደረገው ልቅ የሆነ የመጠፋፋት ዘመቻ፤ ገና በዳዴ ላይ ላለው የፖለቲካ ባህላችን መራዥ የሆነ ሚና ነው የሚኖረው፡፡
ስለዚህ ከዲሲ ወደ አሪዞና የመጣሁበት ዋናው ምክንያት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እዚሁ አሪዞና ስቴት ዪኒቨርስቲ ትምህርቴን ለመቀጠል አንዳንድ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች እያሟላሁ ነው፡፡

የዳያስፖራውን ኑሮ፣ ማህበራዊ-ህይወትና፣ ፖለቲካ እንዴት ተመለከትከው? በተለይ ፖለቲካ አራማጆቹ የፅንፈኝነት ደረጃቸውን እንዴት ትገልጸዋለህ? የዳያስፖራ ፖለቲካ ሲባል ሚዲያዎቹንም ይመለከታልና አያይዘህ ብትመልስልኝ፡-

እንደው አለመታደል ሆኖ የፖለቲካ ባህላችን ከ1960ዎቹ ጀምሮ የጽንፍ ፖለቲካ ነው፡፡ የኢህአዴግ ደጋፊዎችም ሆኑ ተቃዋሚዎች በእኩል ደረጃ ሁለት ጫፍ ይዘው ነው ሲጠዛጠዙ የምታያቸው፡፡ ፍልሚያው ደግሞ በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል ብቻ የሚቆምም አይደለም፡፡ አንዱ ተቃዋሚ ሌላውን በወያኔነት ለመፈረጅ ያለው ጥድፊያ ብዙ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ <የአንድን ሰው የፖለቲካ አቋም ለመፈረጅ ብሄሩን ጠንቅቀህ ማወቅ በቂ ነው> ባዬች ብዙ አሉ፡፡ አንዳንዴ አገር ቤት ያለው እንዴት አይነት ስልጡን ህዝብ ነው ትላለህ፡፡ ሁለቱም ወገን ጋር የምትመለከተው ‹‹እኔ ጋ ካልሆንክ ጠላቴ ነህ›› አይነት አጥፊ ድምዳሜ ነው፡፡
ሚዲያዎቹም የዚህ አይነቱ አሰላለፍ ሰለባዎች ናቸው፡፡ በተለይ እዚህ የምታየው አስቀያሚ ነገር የፖለቲካ ልዩነትን የብሄር ካባ አልብሶ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ያለው ሩጫ ተአምር ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ‹‹ጸባችን ከስርዓቱ ጋር ነው" ከትግራይ ህዝብ ጋ አይደለም›› ሲል ትሰማውና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ‹‹አጼ ዮሐንስም እኮ ለአካባቢያቸው ተወላጆች ነበር ስልጣን የሚሰጡት፤ እነ ብርሀነ መስቀልና እነ ተስፋዬ ደበሳይም ለትግራይ የበላይነት ነው ሲታገሉ የኖሩት›› ሲሉ ትሰማቸዋለህ፡፡ ይህ አይነቱ አባባል ‹‹ጸባችን ከህዝቡ ጋር ሳይሆን ከስርአቱ ጋር ነው ለሚለው ፕሮፖጋንዳ እንዴት ግብአት ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይሆንልህም፡፡
እንደሚገባኝ ከሆነ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ስትራተጂ ተግባራዊ እንዲሆን የተፈለገው ‹‹ህወሃት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ደርግና አማራ አንድ እንደሆኑ አድርጎ ይቀሰቅስ ነበር፤ እናም በዚህ መንገድ ውጤታማ መሆን ችሏል›› በሚል የተሳሳተ ስሌት ምክንያት ይመስለኛል፡፡ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ቀመር በ2012 ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር ግን ምንኛ ኋላ ቀር አካሄድ እንደሆነ ለመገንዘብ ዝግጁነቱ የለም፡፡ አንዳንዴ ከአንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎች ጋር ሳወራ ‹‹የትግራይ ተወላጆች የጸረ ኢህአዴግ ትግሉን የማይቀላቀሉት ለምንድነው›› የሚል የቁጭት ጥያቄ ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡ ነገር ግን ደግሞ እነ ስዬና እነ ገብሩ አስራት አይነት ሰዎች ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጥተው ‹‹ተባብረን አንድ ነገር እናድርግ›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የተቃዋሚው ምላሽ ‹‹እናንተም ያው ወያኔዎች ናችሁ›› የሚል ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ‹‹ታዲያ እሺ ምን ይደረግ ስትል›› ደግሞ መልስ የለም፡፡

አሁን አቶ መለስ በህይወት የሉም፤ ወደአገርህ ለምን አትመለስም?

ችግሩ እኮ በአቶ መለስ መኖርና አለመኖር የሚፈታ አይደለም፡፡ ከሆነም እናየዋለን፡፡ አውራምባን የማዘጋቱና እኔን የማባረሩ የቤት ስራ የተሰራው ቀደም ብዬ እንደገለጽኩልህ ይህ አይነቱን ሴራ እንዲያከናውን በተመደበው ቡድን አማካኝነት ነው፡፡ ይህ ቡድን የሚያቀርበው ሪፖርት ደግሞ ከእንደኛ አይነቱ ምስኪን ዜጋ የበለጠ በአቶ መለስ ዘንድ አቅምና ተሰሚነት የነበረው ነው፡፡ አሁንም እንዳለው ይሰማኛል፡፡ ለዚሁ ተብሎ የተዋቀረ የጥፋት ቡድን ነውና፡፡

የአቶ መለስን ህልፈት ስትሰማ ምን ተሰማህ? በቀብራቸው ቀን ተገኝተው ሱዛን ራይስ ተናግረው ነበር፤ ንግግሩን እንዴት አየኸው?

በአቶ መለስ ህልፈት አዝኛለሁ፡፡ ለምን አዘንክ የሚለኝ ሰው ካለ በሱም ጭምር አዝናለሁ፡፡ አቶ በረከት ስምኦን ህልፈታቸውን በተመለከተ በይፋ ሲናገሩ ‹‹21 ዓመት ሙሉ ያለ እረፍት ሲሰሩ..ወዘተ›› ብለዋል፡፡ አዎ! በረከት ያሉት እውነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአገር ቤትና በውጭ መለስን የሚተካ ሰው አጥታ አንድ ሰው እሰኪሞት ድረስ እንዲመራት ሲደረግ ያሳዝናል፡፡ አቶ መለስ ምንም ጥያቄ የለውም አዋቂ ናቸው፡፡ እንኳን አቶ መለስ አልበርት አንስታይንም 21 ዓመት ሙሉ አንድን አገር በብቃት መምራት አይችልም፡፡ አሜሪካዊያን ከስምንት አመት በላይ አንድ ሰው እንዲመራቸው የማይፈልጉት ለምንድነው? በቃ አንድ ሰው በሙሉ አቅምና ኃይል (ፓሽን) ውጤታማ (ፐሮዳክቲቭ) ሆኖ አገርን መምራት የሚችለው ለትንሽ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ወደ ኢህአዴግ ስንመጣ ለፖለቲካ መቻቻል በሩ ዝግ ነው፡፡ እሱ ብቻ ነው ለአገር የሚያስበው" ሌላው አገር አጥፊ ነው፡፡ ይህ የተሳሳተ የፖለቲካ ባህላችን ለጤናችን እንኳን ተገቢውን ጊዜ እንዳንሰጥ እያደረገን ነው፡፡ መለስ ብዙ ሰው አልቅሶ እንደቀበራቸው አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ሰው ግን አልቅሶ አልቀበራቸውም፡፡ ያ ግን እንዲሆን ማድረግ ይችሉ ነበር" እድልም ነበራቸው፡፡
የሱዛን ራይስን ንግግር በተመለከተ በወቅቱ አንድ አርቲክል ጽፌ ነበር፡፡ መለስ ሱዛን ራይስ እንደገለጽዋቸው አይነት ሰው ቢሆኑ ኖሮ በሱዛን ራይስ አገር ላይ በጥገኝነት ተቀምጨ የሱዛን ራይስን ንግግር በቴሌቭዥን አልመለከተውም ነበር፡፡ መቅረጸ-ድምጼን ይዤ መስቀል አደባባይ ሆኜ ነበር የምመለከታቸው፡፡ እውነትም መለስ ‹ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው መሪ> <<ወርልድ ክላስ ሊደር›› ቢሆኑ ኖሮ እኔም እስክንድርም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተገኝተን አልቅሰን እንሸኛቸው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ ለምን አልሆነም? ካልከኝ መለስ ሱዛን እንደገለጽዋቸው አይነት አይደሉማ! አንዳንድ ወገኖች እዚሁ ሆነህ የሚከፈለውን ሁሉ መስዕዋትነት መክፈል እንደነበረብህ ይገልጻሉ፡፡ ምን ትላለህ ስለዚህ ጉዳይ? በመጀመሪያ ጥያቄውን አታድበስብሰው! ‹‹እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች በበቂ ሁኔታ አልታሰሩም" የእነ እስክንድር መታሰር በቂ ስላልሆነ አንተም መጨመር ነበረብህ›› ማለት ነው ጥያቄው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ 80 ሚሊዮን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ቀላሉን ጥያቄ ከመጠየቅ ከባዱንም ኃላፊነት ቢጋሩ መልካም ነው፡፡ ሌላው እንዲታሰር የምንጓጓውን ያህል የታሰሩትን ለማስፈታት ምን ጥረት አድርገናል ለመሆኑ? እስከ መቼ ነው ዋጋ የሚከፍሉልንን ሰዎች በመብራት እየፈለግን የምንኖረው? ሁሌ ተመሳሳይ ሰዎች ብቻ እየታሰሩ በይቅርታ እየወጡ እንደገና እየታሰሩ እንዲኖሩልን የምንፈልገውስ እስከመቼ ነው? ለእንደዚህ አይነቱ ነገር ዝግጁ ካልሆንን እንዲታሰሩ የምንፈልጋቸው ሰዎች ታስረው ነው የሚቀሩት፡፡ ለታሰሩ ሰዎች አንድ ነገር ማድረግ የማንችል ከሆነና ‹‹እከሌ ለምን ታስሮ አልቀረም›› ለማለት ከሆነ እንቅልፍ የምናጣው፤ ጭካኔአችን የሰው ልጅ ሳይሆን የእንስሳ ጭካኔ ነው፡፡ እኔ በግሌ ለእንደ ተመስገን አይነቱ አክብሮት አለኝ፡፡ ተመስገን ሁለት አመት ታስሮ በይቅርታ ቢፈታና ከዛ በኋላ ‹‹ይቅርታህ ሊነሳ ነው›› የሚል መረጃ ቢደርሰው እና አገር ጥሎ ቢወጣ ‹‹ተመስገን ለምን አልታሰረም›› ብዬ አገር ይያዝልኝ አልልም፡፡ አዲስ መፅሐፍ እየፃፍክ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ መቼ እንጠብቀው? ምንስ ነገሮችን አካቷል? መጽሐፉን ጽፌ የጨረስኩት ባለፈው ነሐሴ ነው፡፡ ነገር ግን ከጠ/ሚኒስትሩ ህልፈት ጋር በተያያዘ ያኔ የነበረው የፖለቲካ ድባብ መጽሀፉን ገበያ ላይ ለማዋል አስቸጋሪ ስለሆነ ከማቆየት ውጪ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ አሁን ሁኔታዎች ስለተረጋጉ ከዛ በኋላ የተፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችንም ጭምር አካትቼ እንደ አዲስ ለመከለስ ተገድጃለሁ፡፡ አሁን እያለቀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ በሁለት ወር ውስጥ ይፋ ይሆናል፡፡ ይዘቱን በተመለከተ፡- አጠቃላይ ፕሬሱ ያለፈበትን ውጣ-ውረድ ከራሴ ልምድ ጋር በማዛመድ እቃኘዋለሁ፡፡ ከፕሬስ ነጻነት አንጻር የአቶ መለስ ሚና ምን እንደነበረም ትዝብቴን አሰፍራለሁ፡፡ እንዴት ከአገር እንደወጣሁ፣ የነበሩት ፈታኝ ሁኔታዎች ምን ይመስሉ እንደነበር ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ከሀገር ከወጣህ በኋላ የተጻፉ መፅሀፍትን እንዴት አየሃቸው? እኔ ከተሰደድኩ በኋላ የወጡት መጽሐፎች የአቶ በረከት ስምኦን (በወቅቱ ሪቪው ሰርቼበታለሁ)፤ የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያምና የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከዚሁ ከዳያስፖራ፤ የተመስገን ደሳለኝና የወሰንሰገድ ገብረኪዳንን አንብቤአቸዋለሁ፡፡ ሌላ ስለ አዲስ አበባ የዝሙት ህይወት እና የመሳሰሉት ነገሮች የሚተርክ መጽሐፍ ደግሞ ‹‹የአውራምባ ታይምስ ሎጎ ተለጥፎበት ወጥቷል›› የሚል ነገር ሰምቻለሁ፤አላየሁትም፡፡ እንደዚህ አይነት ይዘት ባለው መጽሐፍ ላይ የአውራምባን ሎጎ ማስቀመጥ ለምን እንዳስፈለገ እስከ ዛሬ ድረስ አልገባኝም፡፡ እስኪ አጣራለሁ፡፡ እስቲ ደግሞ በቅርቡ ባለህበት አሜሪካ ስለተካሄደው ምርጫ ትንሽ በለን፡፡ ከአገራችን ምርጫ ጋር ስታስተያየው (ማነፃፀሩ አዳጋች ቢሆንም) እንደ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኝነትህ ምን ተሰማህ? በነበርክበት ኦሪዞና ግዛትስ የነበረው የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል? የአሜሪካ ምርጫን በደንብ ተከታትየዋለሁ፡፡ ኦባማ በድጋሚ መመረጡ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን አስደስቷል፡፡ ሁሌም የአሜሪካ ምርጫ ስትከታተል የሚያስቀናህ ነገር በእጩዎቹ መካከል ያለው መከባበር ነው፡፡ በተለይ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ አንዱ ለሌላው የሚያስተላልፈው የእንኳን ደስ ያለህ መግለጫ ደስ ይላል፡፡ በተለይ ሚዲያዎቹ ያላቸው ነጻነት ይገርምሀል፡፡ ‹‹ሲ ኤን ኤን›› እና ‹‹ፎክስ››ን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች በራሳቸው መንገድ የተለያዩ መረጃዎችን መሰረት አድርገው ማን እንዳሸነፈ አስቀድመው ይፋ ያደርጋሉ፡፡ እኛ አገር ግን ምርጫ ቦርድ ይፋ ከማድረጉ በፊት እንዲህ አይነቱን የሚዲያ ትንበያ ይፋ ማድረግ አይፈቀድም፡፡ በእርግጥ በአገራችን እንዲህ አይነቱን ትንበያ ለመስራት የቴክኖሎጂ እጥረትና የአቅም ውሱንነት ቢኖርም በጊዜ ሂደት ግን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ በአዋጅ መከልከሉ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ እኔ ያለሁበት አሪዞና ‹‹ሬድ ስቴት›› ነው፡፡ ማለትም ሪፐብሊካኖች ናቸው ሁሌ የሚያሸንፉት፡፡ ለምሳሌ ከአራት አመት በፊት ከኦባማ ጋር የቀረቡት ጆ ማኬይን የዚህ አካባቢ ሰው ናቸው፡፡ አዲሱ የአቶ ኃ/ማርያም አስተዳደር በፕሬስ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ያመጣል ብለህ ትጠብቃለህ? እኔ ሁሌም ተስፈኛ ነኝ፡፡ አቶ ኃይለማሪያም እዚህ ለተባበሩት መንግስታት ስብሰባ የመጡ ጊዜ ለእንግሊዝኛው ቪ ኦ ኤ የሰጡትን ቃለምልልስ ሰምቼዋለሁ፡፡ ፓርላማም ላይ የተናገሩት ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ ትንሽ ራሳቸውን መሆን የቻሉ አይመስለኝም፡፡ ፓርላማ ላይ ከእጅ እንቅስቃሴያቸው ጀምሮ አነጋገራቸው፣ በምላሾቻቸው ላይ የሰነዘሯቸው ማስጠንቀቂያዎችና ዘለፋዎች ተገቢ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ተስፈኛ ነኝ፡፡ ከ38 ዓመት በኋላ እምነት ያለው ሰው ወደ መሪነት ቦታ መምጣቱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር ይርዳቸው! ከኢትዮጵያ በመሰደድህ ምን ያጣኸው ነገር አለ? (የሚቆጭህ፣ የሚናፍቅህ፣ የሚፀፅትህ ነገር አለ?) ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ስደት ላይ ስትሆን ቁጭት፣ ናፍቆትና ጸጸት ሁሌም ይኖራል፡፡ እኔ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አድርጌአለሁ፡፡ ባልወጣና ባልሰደድ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ታረገዋለህ" ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ህይወት መቀጠል አለበት፡፡ የባልደረባህ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከስዊድን ጋዜጠኞች ጋር በይቅርታ ያለመፈታት ጉዳይን እንዴት አየኸው? የውብሸት ጉዳይ ብሄራዊ ክብርን የሚፈታተን ነገር ነው፡፡ ከስዊድኖቹ ጋር እንደሚፈታ ሙሉ እምነት ነበረኝ፡፡ እኩል ነው የይቅርታ ሰነዱን የፈረመው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ ጋር ተነጋግሬአለሁ፡፡ አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡኝም እንጂ፡፡ አለም አቀፉ ሚዲያ የሚጮኸው ለስዊድኖቹ ስለነበር የኢትዮጵያ የይቅርታ ህግ ከኢትዮጵያዊያን ይልቅ የውጭ ዜጎችን ተጠቃሚ ሊያደርግ ግድ ነበር፡፡ ትንሽ ግራ የሚያጋባው ውብሸትም ስዊድናዊያኑም ሲታሰሩ አቶ መለስ የነጭ እና የጥቁር ደም እኩል ነው ብለው ነበር በፓርላማ፡፡ ተመርጠው ሲፈቱ ግን እኩል እንዳልሆነ አረጋግጠናል፡፡ ለዚህም ነው ስዊድኖቹ በተፈቱ በማግስቱ ‹‹አድሏዊውና አሳፋሪው ይቅርታ›› ብዬ አርቲክል ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ ለነገሩ ውብሸት የተበደለው ባሰሩት ሰዎች ብቻ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ባይሆንልኝም አገር ቤትም ውጭም ያለው ሚዲያ ሆን ብሎ ረስቶታል፡፡ ከታሰረበት ጉዳይ ቀጥተኛ የሆነ ትስስር አላቸው የሚባሉ ዌብሳይቶች እንኳን አንድ ነገር ትንፍሽ ለማለት አልፈቀዱም፡፡ በሌላ በኩል አገር ቤት ያሉ ሚዲያዎችም እንደዛው፡፡ አንድ የሚዲያ ተቋም የራሱን ባልደረባ ብቻ እየመረጠ ማግዘፍና ማጀገን የለበትም፡፡ እስርቤት ስለነበርኩ የሚዲያ ሽፋን ስታገኝና ሳታገኝ የሚሰማህ ብርታት እኩል እንዳልሆነ አውቀዋለሁ፡፡ በቅርቡ የተካፈልክበት ስብሰባ በ (National Endowment for Democracy) የተዘጋጀው ላይ ፅሁፍ አቅርበህ ነበር? ስለስብሰባው ምንነትና ዓላማ ብታብራራልን? ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የአሜሪካዊያን አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም ነው፡፡ የፌሎውሽፕ ፕሮግራምም ይሰጣል፡፡ እንደምታወቀው ወ/ሪት ብርቱካን ለአንድ አመት ገደማ የቆየችው በዚሁ ተቋም ውስጥ ነው፡፡ ይህ ተቋም ባለፈው ጥቅምት "Toward a Democratic Ethiopia" በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚል አለምአቀፍ ኮንፈረንስ አካሂዶ ነበር፡፡ ውይይቱ በሦስት ፓነል የተከፋፈለ ነው፡- የመጀመሪያው የፕሬስ ነጻነትና የሲቪክ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወጡት አዋጆች ምን ተጽእኖ አላቸው በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ እኔ (በፕሬስ ነጻነት)፣ ወ/ሮ ማህደር ጳውሎስ (በሲቪክ ድርጅቶች) እንዲሁም የሂዩማን ራይትስ ዎች የዋሺንግተን ዲሲ ተጠሪ ሳራ ሞርጋን (በአዋጆቹ ዙሪያ) ጥናታዊ ጽሁፎቻችንን አቅርበናል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ ምን እንደሚመስል አምባሳደር ዴቪድ ሺን እና ፕ/ር ቴሬንስ ሊዮንስ በመጨረሻ ደግሞ የስቴት ዲፓርትመት አሲስታንት ሴክሬታሪ እንዲሁም ሌላው የዩኤስ ኮንግረስ ተወካይ በተከታታይ ጽሁፎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ከኛ ከጽሁፍ አቅራቢዎቹ ውጪ በዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ ስዬ አብርሀ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም በዋሺንግተን ዲ.ሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ የስብሰባው ታዳሚዎች ሆነው ፕሮግራሙን ተከታትለዋል፡፡ አንተ ያቀረብከው ይዘቱ ምን ይመስላል፤ የኤምባሲው ተወካይስ ማን ናቸው? ምንስ አሉ? እኔ ያቀረብኩት አጠቃላይ ሚዲያው አሁን ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከስብሰባው ከሁለት ሳምንት በፊት በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመናገር ነጻነትን በተመለከተ በጣም ድንቅ የሆነ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ እኔ ለንግግሬ መነሻ ያደረኩት ኦባማ ያደረጉትን ንግግር በማስታወስ ነው፡፡ ኦባማ ያሉት ‹‹ሰዎች በሚያራምዱት አመለካከት ምክንያት እስር ቤት መግባት የለባቸውም፡፡ እዚህ አሜሪካ በርካታ ፕሬሶች እኔን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ፡፡ እኔ የአሜሪካ ፕሬዚደንትና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነኝ ብዬ ግን ምንም የማረገው ነገር የለም፡፡ እንደውም በህገ መንግስታችን የተረጋገጠውን መብት ተግባራዊ በማድረጋቸው ይበልጥ ደስ ነው የሚለኝ›› ነበር ያሉት ኦባማ፡፡ ይህንን መነሻ አድርጌ የእስክንድርን፣ የርዕዮትንና የውብሸትን ሁኔታ በንጽጽር ለማስቀመጥ ሞክሬአለሁ፡፡ ያው አምባሳደር ዴቪድ ሼን ሁሌም …ዴሞክራሲ እኮ ሂደት ነው ምናምን የሚሉት ነገር አለ…እኔ ደግሞ ‹‹አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ እርስዎ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እያሉ ስንት ጋዜጦች ነበሩ? አሁንስ ስንት አሉ? ሂደት ማለት ይሄ ነው? ሂደት ማለት እንደዚህ ከሆነ፤ ወደተሳሳተ አቅጣጫ የሚወስድ ሂደት ላይ ነው ያለነው፤ ‹‹እኤአ እዚሁ በዋሺንግተን ዲሲ ተገናኝተን ስናወራ ቢያንስ እኮ እነ አውራምባ ይታተማሉ ብለው ተከራክረውኝ ነበር፤ ዛሬ ግን እነ አውራምባም አይታተሙም፡፡ ይኼ ነው ሂደት? ባለፈው አመት የእርስዎ ዌብሳይት ሳይቀር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተዘጋ ነግረውኝ ነበር" እንዴት ነው ይህንን ማስታረቅ የሚቻለው?›› አልኳቸው፡፡ በጣም የሚያስቀው ነገር ዌብሳይታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘግቶ እንደነበረና ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር ተነጋግረው እንዳስከፈቱት ነገሩኝ፡፡ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ አቶ ዋሕድ በላይ ናቸው የተገኙት፡፡ አጋጣሚ የእኔ ጽሁፍ ቀርቦ ቤቱ ለጥያቄና መልስ ክፍት ሲሆን አቶ ዋሕድ ተነስተው የኔ ጽሁፍ የደርግ አመለካከት እንደሚንጸባረቅበት ተናገሩ፡፡ እኔ ደግሞ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ የዘጠኝ አመት ልጅ እንደነበርኩ ተናግሬ በአዳራሹ የነበሩ ታዳሚዎችን ትንሽ ፈገግ አሰኘኋቸው፡፡ በነገራችን ላይ ከዛ በኋላ ከአቶ ዋህድ ጋር አድራሻ ተለዋውጠን ኢንተርቪው ሁሉ እንደሚሰጡኝ ቃል ገብተውልኛል፡፡ አገሬ መጥቼ ተወዳጇን አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዳግም አሳትማለሁ ብለህ ታስባለህ? ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሌላው ቢቀር ቢያንስ ዌብሳይቴን ኢትዮጵያ ሆኜ ብሰራው እንዴት ደስ ይለኛል መሰለህ፡፡ ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር እንደዛ አይነት ሆደ ሰፊነት ኢህአዴግ ጋ የለም፡፡ ይገርምሃል ዌብሳይቱ የተመረቀው ሜይ 05/2012 እንግዶች በተገኙበት በዋሺንግተን ዲ.ሲ ነው፡፡ በተጠቀሰው ቀን ተመርቆ በማግስቱ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘግቷል፡፡ ‹‹አውራምባ ታይምስ በኪሳራ ነው የተዘጋው፤ እኛ ጫና አላሳደርንም›› ያሉት ኃላፊዎች የአውራምባ ዌብሳይትን ግን ከ24 ሰዓታት በላይ ሊታገሱት አልፈቀዱም፡፡ ቢያንስ ይዘቱ ምን ይመስላል? ተብሎ እንኳን ዳሰሳ ለማድረግ አይሞከርም? እና እንዲህ እንዲህ አይነቱን ስመለከት ትንሽ ተስፋዬን ያደበዝዘዋል፡፡ ግን ይሁን እስኪ…………..


Dec 8, 2012

ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ከካሳንቺስ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ እንደወትሮው የትራፊክ እንቅስቃሴ አጨናንቆታል፡፡ በተጨናነቀው በዚህ መንገድ ላይ ግን አንድ ሃችፓክ መኪና በአየር ላይ የሚበር በሚመስል ሁኔታ ይከንፋል፡፡ ከፊት ለፊቱ ባሉ መኪናዎች መንገድ የተዘጋበት የዚህ መኪና አሽከርካሪ ልክ ዮርዳኖስ ሆቴል ደጃፍ ጋር ሲደርስ ‹‹በአሳልፉኝ›› ምልክት በክላክስ አካባቢውን ያውከዋል፡፡

አስገራሚው እና አነጋጋሪው ፍጻሜ-18 ጥይት ለምን?

ጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ.ም
ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ከካሳንቺስ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ እንደወትሮው የትራፊክ እንቅስቃሴ አጨናንቆታል፡፡ በተጨናነቀው በዚህ መንገድ ላይ ግን አንድ ሃችፓክ መኪና በአየር ላይ የሚበር በሚመስል ሁኔታ ይከንፋል፡፡ ከፊት ለፊቱ ባሉ መኪናዎች መንገድ የተዘጋበት የዚህ መኪና አሽከርካሪ ልክ ዮርዳኖስ ሆቴል ደጃፍ ጋር ሲደርስ ‹‹በአሳልፉኝ›› ምልክት በክላክስ አካባቢውን ያውከዋል፡፡
የክላክስ ድምፁ በተደጋጋሚ የተነፋላት ከፊት ለፊቱ ያለችው በተለምዶ ወያኔ ዲኤክስ መኪና አሽከርካሪ ክላክሱ ለእሷ የተነፋ አልመሰላትም ነበር፡፡ ወላጅ እናቷን ጭና ወደ ኦሎምፒያ አቅጣጫ መብራቱን ለመሻገር ጥረት ታደርግ የነበረችው አሽከርካሪ ከኋላዋ ያለውን ሰው ማንነት ለማረጋገጥ በመኪናዋ የጎን መስታወት ስፖኪዮ ስትመለከት በፍ/ቤት በፍቺ ወረቀት የተለየችው የሁለት ልጆቿ አባት መሆኑን ተመልክታለች፡፡
የቀድሞው ባለቤቷ የክላክስ ጩኸትና በተደጋጋሚ በእጅ ምልክት እንድትቆም የሚያሳያት ዛቻን ያላማራት ሚስት የመንገዱን መብራት በፍጥነት አቋርጣ ወደ ኦሎምፒያ ደንበል አቅጣጫ ሽቅብ መንዳት ትጀምራለች፡፡ ከኋላዋ እየተከታተላት ያለው አሽከርካሪም የመጨረሻ ፍጥነቱን ጨምሮ ይከተላታል፡፡ አጠገቧ ያሉት እናት ወ/ሮ ተናኜ ሀ/ማርያም ባሏ ምን እንደፈለገ ቆማ እንድታናግረው አለበለዚያም የፀጥታ ሀይሎች ወዳሉበት እንድትነዳ ሲጠይቋት የሁኔታውን አስፈሪነት በመረዳት ሁለተኛውን አማራጭ ነበር የመረጠችው፡፡ እናም ወደ ደንበል የሚወስደውን መንገድ በፍጥነት ነድታ አዲስ እየተሰራ ያለው አደባባይ ጋር ስትደርስ በአይኗ ግራና ቀኝ ፖሊሶችን ፍለጋ አማተረች፡፡
በወቅቱ በአካባቢው ላይ የትራፊክ ፖሊሶችና ሌሎች የፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሠራተኞ ነበሩ፡፡ ሚስት አደባባዩን እንደተሻገረች ላፓራዚያን ካፌ ፊት ለፊት ከመድረሷ በፊት ከኋላ የሚከተላት የባሏ መኪና ሲጋልብ አጠገቧ ይደርሳል፡፡ አመጣጡ ያላማራት ሚስት መኪናዋን ካርቱም ሬስቶራንት ፊት ለፊት ባለበት ሁኔታ አቁማ በመውረድ ወደ ፀጥታ ሠራተኞች ለመሮጥ በመወሰን መኪናዋን ታቆማለች፡፡
የአደጋ መከላከያ ቀበቶዋን በፍጥነት ፈትታ ልትወርድ ስትል ግን መኪናው በበሯ አጠገብ ሲጢጥ ብሎ በማቆም አሽከርካሪው ወደ እሷ መጣ፡፡ በሯ በመኪናው መዘጋቱን የተመለከተችው ሚስት በሌላኛው የፊት በር በፍጥነት ወጥታ ለማምለጥ ጥረት እያደረገች ሳለ ረዥም ክላሺንኮቭ ጠመንጃውን እያቀባበለ ወደ እሷ የተጠጋው አሽከርካሪ በቀጥታ በመተኮስ በ18 ጥይት የሁለት ልጆቹን እናት ባለችበት ጣላት፡፡ ከተኮሳቸው ጥይቶች መሀከል ወላጅ እናቷን ሶስት ጥይት አግኝቷቸዋል፡፡ ሁኔታውን በስፍራው ሆነው ሲከታተሉ የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለፁት ከሆነ ያለምንም ንግግር ይህንን አስከፊ ድርጊት የፈፀመው ሰው በቀረው ጥይት ራሱን ለማጥፋት ወደርሱ ለመተኮስ ቢሞክርም ጠመንጃው ጥይቱን ጨርሶ ስለነበር መሞት አልቻለም፡፡ ይህ ከሁለት እስከ ሶስት ደቂቃ የፈጀውን ትዕይንት ለማስቆም ጊዜ ያጡት በአካባቢው የነበሩት የፀጥታ ሠራተኞች የድርጊቱን ፈፃሚ ዋና ተዋናይ በቁጥጥር ስር አድርገው ተጎጂዎቹን ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ወዲያ ወዲህ ቢሉም ሚስት ወ/ሮ ፍሬህይወት ታደሠ ሰውነቷ ላይ ባረፉት 18 ጥይቶች ሳቢያ እስከወዲያኛው ያሸለበችው እዚያው መኪና ውስጥ ነበር፡፡
በስፍራው ሆኖ ድርጊቱን ሲከታተል የነበረውና ጫጫታው መሀል ሆኖ ስልክ የደወለልኝ ወዳጄ አርቲስት ሙሉቀን ተሾመ (የቴዲ ተሾመ ታናሽ ወንድም) የድርጊቱን ሁኔታ በሀይለቃል መግለፅ ቢችልም በወቅቱ ከዚህ የበለጠ ሁኔታውን ሊያብራራልኝ አልቻለም ነበር፡፡ የአልመንሱር ጄኔራል ትሬዲንግ ባለቤት አቶ መንሱር ጀማል ግን ድርጊቱን በሞባይሉ ፎቶ ማንሳት ችሎ ነበር፡፡
18 ጥይት ለምን?
የሁለት ልጆቹን እናት ወ/ሮ ፍሬህይወት ታደሰን በአስከፊ ሁኔታ በጥይት ደብድቦ በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው አቶ ወንድወሰን ይልማና ባለቤቱ ወ/ሮ ፍሬህይወት ትዳር መስርተው የሚኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ፡፡ መስከረም 27 ቀን 1999 ዓ.ም የተፈፀመው የሁለቱ ጥንዶች የሠርግ ሥነ ሥርዓት እጅግ የደመቀ፣ የተለየና በከተማው በወቅቱ ትልቅ መነጋገሪያ የነበረ ሠርግ ነበር፡፡ (ስለ ሰርግ ሥርዓቱ ወደኋላ ላይ እመለስበታለሁ)
ወንድወሰንና ፍሬህይወት ከ1999 እስከ 2004 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ‹‹አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ›› እየተባባሉ በአንድ ጎጆ ውስጥ ኖረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥም የአራት ዓመት ሴት ልጅና የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ወንድ ልጅ አፍርተዋል፡፡ ወንድወሰን በተፈጥሮው ቁጡ፣ ግትርና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ ከዚሁ ባህሪው ጋር በተያያዘም ከፍሬህይወት ጋር በተደጋጋሚ ይጋጫሉ፣ ሀሳቧን ስለሚጫናትም ለጠብ ይዳረጋሉ፡፡ አለፍ ሲልም ወንድወሰን ቡጢ እስከመሰናዘር ደርሶ በገላጋይ የተለያዩበት ጊዜ አለ፡፡
ከሁለተኛው ወንድ ልጅ መወለድ በኋላ አለመግባባታቸው እየተካረረ መምጣቱን የሚናገሩት ለጥንዶቹ ቅርበት ያላቸው ወገኖች የጠባቸው ትክክለኛ ምክንያት ይህ ነው ብለው ለመናገር ቢቸገሩም ፍሬህይወት ቀደም ሲል ትሰራበት ከነበረበት ክሊንተን ፋውንዴሽን መ/ቤት ለቃ የግል ሥራ ብሰራ ይሻለኛል ማለቷ ጠባቸውን ከቤተ ዘመድ ጉባኤና ሽማግሌዎች እጅ አውጥቶ ወደ ፍ/ቤት እንዲያመራ አድርጎታል ይላሉ፡፡
“የፍቺ ይፅደቅልኝ” ክስ መስርታ ወደ ፍ/ቤት ያመራችው ፍሬህይወት ‹‹ሁለት ልጆቼን ለማሳደግ አላንስም›› በማለት ፍቺው እንዲፀድቅላት ብቻ ወደ ፍ/ቤት ማምራቷ ወንድወሰንን አላስደሰተውም ሁለት ልጆች መውለዳቸውን የተረዳው ፍ/ቤትም ለልጆቻቸው ሲሉ አለመግባባታቸውን በሰላም እንዲፈቱ የማንሰላሰያ ጊዜ በተደጋጋሚ በመስጠት በቀጠሮ ቢያቆያቸውም መስማማት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ፍቺው በፍ/ቤት ሲፀድቅ ወንድወሰን ለጊዜው ደስተኛ መስሎ ታይቷል፡፡ የልጆቻቸውን ጉዳይ በተመለከተ ብይን የሰጠው ፍ/ቤቱ ‹‹ልጆቹ ከእናታቸው ጋር እንዲሆኑና በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ መጥቶ በመውሰድ አጫውቷቸው እንዲመልስ›› በተወሰነው መሠረት ይህንኑ ድርጊቱ ሰላማዊና ቤተሰባዊ በሆነ መልኩ ላለፈው አንድ ዓመት ወንድወሰን ተግብሮታል፡፡
የፍቼው እንግዳ
ሐምሌ 7 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ከፍቼ የመጣ አንድ እንግዳ አዲሱ ገበያ አካባቢ ከፅዮን ሆቴል በታች ባለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ
በጥቁር ላስቲክ የተጠቀለለ ዕቃ ጀርባው ስር ሸጉጦ አስር ጊዜ ሰዓቱን ይመለከታል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ የአሁኑ ተጠርጣሪ ወንድወሰን ካፌው በር ላይ መኪናውን በማቆም ወደ ግለሰቡ ስልክ ይደውላል፡፡ ስልኩ በካፌው በረንዳ ላይ ወዳለው ሰው ሲጠራና ስልኩ ሲነሳ በአካል የማይተዋወቁት ተቀጣጣሪዎች ይተያያሉ፡፡ ወዲያው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ እንግዳው ዕቃውን ይዞ ወንድወሰን መኪና ውስጥ መግባታቸውን ሁኔታውን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ ምንጮች ይናገራሉ፡፡
መኪናው ውስጥ የገቡት ወንድወሰንና የፍቼው ሰው ጥቂት ደቂቃዎች ከተነጋገሩ በኋላ ‹‹ሌባ በተደጋጋሚ ግቢህ ውስጥ እየገባ እንዳስቸገረህ የነገረኝ ጓደኛዬ ስልክህን ሰጥቶኝ ደውልለት ስላለኝ ነው የመጣሁት›› አለው የፍቼው ሰው፡፡ ‹‹ዕቃውስ?›› የወንድወሰን ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹ይዤዋለሁ›› በማለት በጥቁር ላስቲክ የተጠቀለለውን ክላሽንኮቭ አውጥቶ ሰጠው፡፡
ስጋት ጥርጣሬና ተስፋ በወንድወሰን ፊት ላይ ይነበብ ነበር ይላሉ ምንጮቻችን፡፡ ወንድወሰን ጊዜ
ሠርጋቸው
ሳያጠፋ በደላላው በኩል የተነገረውን 25 ሺህ ብር ከመኪናው የኋላ ወንበር ስር አንስቶ ለፍቼው ሰው ሰጠው፡፡ የፍቼው ሰው ብሩን መቁጠር ሳያስፈልገው ገለጥ አድርጎ ከተመለከተ በኋላ ከመኪናው ወረደ፡፡ ‹‹በተደጋጋሚ ሌባ ግቢዬ እየገባ አስቸገረኝ›› ያለው ወንድወሰን መሳሪያውን ይዞ በግቢ ሌባ የመሰላት የልጆቹ እናት ላይ ለመሞከር የሚያስችለውን አመቺ ጊዜና ቦታ እያንሰላሰለ ቁል ቁል ወደ ፒያሳ አቅጣጫ ተፈተለከ፡፡
መስከረም 27 ቀን 1999 ዓ.ም በተከናወነው የአቶ ወንድወሰን ይልማና የወ/ሮ ፍሬህይወት
ታደሰ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ቁም ነገር መፅሔት የመገኘት ዕድል ገጥሟት ነበር፡፡ በወቅቱ ለ3 ዓመታት ያህል የዘለቀውን የፍቅር ግንኙነታቸውን በጋብቻ ለመቋጨት የወጠኑት ወንድወሰንና ፍሬህይወት ወደ ትዳር ሲገቡ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ጠርተው የደስታቸው ተካፋይ የሚያደርጉበትን የሠርግ ዝግጅት በምን መልኩ እና እንዴት ማከናወን እንዳለባቸው ሲያወጡና ሲያወርዱ ነበር የከረሙት፡፡ በተለይ ወንድወሰን ጋብቻው እስከዛሬ ድረስ ከተደረጉት ሠርጎች ሁሉ ለየት ያለ እንዲሆን አጥብቆ ነው ያሰበበት ‹‹ፍላጎቴ ከሌሎች ሰዎች ለየት ብዬ እንድታይ አይደለም›› የሚለው ወንድወሰን ‹‹ይልቁንም የአሁኑ ትውልድ ራሱን ሆኖ በራሱ ባህልና ትውፊት የመድመቅ ችግር ስለሚታይበት ኢትዮጵያዊ ባህልና ወግን የተከተለ ሠርግ በማድረግ ራሴን ሆኜ ለመገኘት ነው›› ብሏል በወቅቱ ለቁም ነገር መፅሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ፡፡
ወንድወሰን በከተማችን ከታዩት የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች ሁሉ የተለየ ከውጥኑ ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ባህልና ወግን የተከተለ ታሪካዊ አሻራ ያለው ሠርግ ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ ፍሬህይወት ምንም እንኳን መጨረሻ ላይ በሃሳቡ ተስማምታ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ብትጀምርም ‹‹ሠርጋችን ምንም አይነት ዘመናዊ ነገር የማይገባበት በባህል ተጀምሮ በባህል የሚያልቅ መሆን አለበት›› በሚለው የወንድወሰን ሀሳብ አልተስማማችም ነበር፡፡ ከውይይት ይልቅ የወሳኝነት ባህሪ ያለው ወንድወሰን ግን ከስምምነታቸው በፊት አንዳንድ ወሳኝ ነገሮችን ይዞ የሰርግ ስነ ሥርዓቱን ጀምሮ ነበር፡፡
የጥሪ ካርድ
በዚሁ መሠረት ወንድወሰን ለዘመን አመጣሽ የሠርግ ዝግጅቶች ቦታ አልሰጠም፡፡ የሠርግ ካርዱን በማተሚያ ቤት ከማሳተም ይልቅ በብራና ላይ በቁም ፅሁፍ ተፃፈ፡፡ ይህንኑ የጥሪ ካርድ በፖስታ ውስጥ ጨምሮ ለእድምተኞች ከመስጠት ይልቅ ብራናው ተጠቅልሎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ጠፈር ሸብ የተደረገ ነበር፡፡ የጥሪ ካርዱን በብራና ላይ ለማፃፍ ሀሳቡን ያፈለቀው ወንድወሰን ቢሆንም ዲዛይኑን በመስራት በኩል የኮምፒውተር እውቀት ያላት ባለቤቱ አግዛዋለች፡፡
አልባሳት
‹‹ሠርግ ያለዘመናዊ ቬሎ የማይታሰብ ሊመስለን ይችላል›› የሚለው ወንድወሰን የባለቤቱን መሞሸሪያ ቬሎ በሀገር ውስጥ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሰራ አድርጓል፡፡ የባለቤቱ ልብስ ብቻ ሳይሆን የእሱም ሆነ የወንዶቹና የሴቶቹ ሚዜዎች አልባሳትና መጫሚያ ሁሉ የእጅ ጥበብ ውጤቶች ነው የተደረጉት፡፡
ጌጣጌጦች
የመዋቢያ ጌጣጌጦችም በተቻለ መጠን ባህላዊ እንዲሆኑ ተወጥኗል፡፡ የሙሽሪት የእጅና የአንገት፣ የጆሮና በፀጉር ላይ የሚሰኩት ጌጣጌጦች በሙሉ ጨሌዎችና ከቀንድ የተሰሩ ነበሩ፡፡ የሙሽሮቹ መቀመጫ ወንበር ከጠፈር የተሰራ፣ የእግራቸው ማረፊያም ምንጣፍ አጎዛ፣ በዙሪያቸው ያለው ዲኮር በሙሉ በሀገር ባህል ጥበብ የተሰራ ነበር፡
ምግብና መጠጥ
ከላይ ከቀረበው እቅድ አንፃር ምግብ ባህላዊ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ ሠርጉ የፈረንጅ ምግቦች እንዳይቀርቡበት ብቻ ሳይሆን አቀራረቡም ባህላዊ እንዲሆን ተፈልጓል፡፡ በዚሁ መሰረት የክትፎ አይነቶች ከነማባያቸው አይብና ጎመን ጋር ሲቀርቡ መመገቢያ ዕቃዎቹም ከቀንድና ከሸክላ የተሰሩ ሆነዋል፡፡ መጠጡም ውስኪንና ሻምፓኝን በማስወገድ ጠላና ብርዝ ነበር በብርሌ የቀረበው፡፡ በኬክ ፋንታም ሻኛ ድፎ ተቆርሷል፡፡
አጃቢዎች
ይህ ሁሉ ባህላዊ ነገር ተዘጋጅቶ አጃቢዎች ሙሽሮቹን በመርቸዲስ እንደማይሄዱ መገመት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ወንድወሰን አስቀድሞ በባልደራስ ስር ያሉ የቤተ መንግስት ፈረሶችን ከነሠረገላቸው ለመከራየት ተነጋግሮ ስለነበር በዕለቱ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሽር ብለዋል፡፡ ከሙሽሮቹ ፊት ለፊት ነጋሪት የሚጎስሙ ወጣቶች በጥንታዊው የባህል አልበሳት ደምቀው ነበር፡፡ ከፈረሰኞቹ ፊት ደግሞ እምቢልታ የሚነፉ ሻምላና ምንሽር የታጠቁ አባቶች፣ በርኖስ የደረቡ ጭንቅላታቸው ላይ አንፋሮ አድርገው ዝናር በታጠቁ ወጣቶች ታጅበው ነበር ከአራት ኪሎ ወደ ካሳንቺስ ሲያመሩም በየመንገዱ ያለ ህዝብ ግራና ቀኝ ቆሞ በአድናቆት አጅቧቸዋል፡፡
እንግዶች
ሁሉም ነገር ባህላዊ በሆነበት በዚህ ሠርግ ስነ ስርዓት ላይም እንግዶች የራሳቸውን የባህል አልባሳት ለብሰው እንዲገኙ ነበር የወንድወሰን ፍላጎት ‹‹የባህል ልብስ ያልለበሰ እድምተኛ ወደ ሠርጉ አዳራሽ መግባት የለበትም›› የሚል አቋም ይዞ የነበረው ወንድወሰን ዝግጅቱ ሠርግ በመሆኑ እድምተኞችን ማስገደድ ተገቢ እንዳልሆነ በሙሽሪት ቤተሰቦች በኩል ተቃውሞ እስኪመጣበት ድረስ በአቋሙ ገፍቶበት ነበር፡፡ ያም ሆኖ እድምተኞች የፈለጉትን ልብስ ለብሰው እንዲመጡ ወንድወሰን በሀሳቡ ቢስማማም የጥሪ ካርዱን ሲልክ ግን የባህል ልብስ ለብሰው እንዲመጡ የሚጠይቅ መልዕክት አብሮ ከመላክ አልቦዘነም ነበር፡፡ በዚሁ መሠረትም ከቅርብ ዘመዶቻቸውና ወዳጆቻቸው በተጨማሪ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ውስጥ የሆኑ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የጣልያንና የጃፓን የባህል አታሼዎች የሠርግ ሥነ ሥርዓቱን ተከታትለዋል፡፡
የሠርግ ሥነ ሥርዓትን በክብር እንግዳ ፊት ማከናወን የተለመደ አይደለም፡፡ ወንድወሰን ግን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑትን ወ/ሮ ታደለች ዳለቾን የባህል ልብስ እንዲለብሱ ከሚያሳስብ መልዕክት ጋር ጋብዟቸው ስለነበር በሀገር ባህል ልብስ ደምቀው በሠርጉ ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ተመልክተናል፡፡
ወንድወሰን ማነው?
አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው የ43 ዓመቱ ወንድወሰን ይልማ በቤተሰብ ግጭት ሳቢያ ከወላጆቹ የተለየው ገና የ7 ዓመት ልጅ ሆኖ ነው፡፡ በዚህ ሳቢያም ክፍለሀገር ዘመዶቹ ጋር ነው ለረዥም ዓመታት የኖረው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ የቴክኒክና ሙያ የተማረው ወንድወሰን የራሱን አነስተኛ የብሎኬትና የሸክላ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከፍቶ ትዳር እስከመሰረተበት ጊዜ ድረስ ድርጅቱን በበላይነት መርቷል፡፡
ፍሬህይወትስ?
ያለፈው መስከረም 2 ቀን 2005 ዓ.ም የ29ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ያከበረችው ፍሬህይወት ተወልዳ ያደገችው እዚሁ አዲስ አበባ ፤ነው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በጀኔራል ዊንጌት ት/ቤት ያጠናቀቀችው ፍሬህይወት ከዊንጌት የ10 ሲደመር 3 ዲፕሎማ ተቀብላለች፡፡ ከዚያም በሲፒዩ ኮሌጅ እየተማረች የማትሪክ ውጤቷ ስለተሻሻለላት በማይክሮሊንክ ኢንፎርሜሽን ኮሌጅ ገብታ በማኔጅመነት ኢንፎርሜሽን ሲስተም በዲግሪ ተመርቃለች፡፡
ፍሬህይወት ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን፣ ኋላም በብራዘርስ ፉድ ኮምፕሌክስና በሰላም የጉዞ ወኪል ውስጥ በፀሐፊነትና በዲዛይነርነት የሰራች ሲሆን ለሞቷ ምክንያት የሆነውን የግል ሱቋን ከመክፈቷ በፊት በክሊንተን ፋውንዴሽን ውስጥ አገልግላለች፡፡
እንዴት ተዋወቁ?
ትውውቃቸው በአጋጣሚ ነው፡፡ አጋጣሚውን የፈጠረው ደግሞ ወንድወሰን ነው፡፡ ወቅቱ ደግሞ 1996 ዓ.ም፤ ወንድወሰን በግል የብሎኬትና የሸክላ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ውስጥ ጎንበስ ቀና ሲል የወገብ ህመም ያጋጥመዋል፡፡ ህክምና ለማግኘት ደግሞ ቦሌ ድልድይ አካባቢ ወደሚገኘው ቦሌ ካይሮ ፕላስቲክ ክሊኒክ ያመራል፡፡
ገና ወደህንፃው የእንግዳ መቀበያ ሲገባ ከአንዲት ብስል ቀይ ቆንጆ ልጅ ላይ አይኑ ያርፋል፡፡ ልጅቱን ተከትሎ ሲሄድ ሊፍት ያለበት ቦታ ትቆማለች፤ ሊፍቱ ሲመጣና ስትገባ እሱም ይገባል፡፡ ክሊኒኩ ያለበትን ፎቅ ሲጠይቃት 6ኛ ፎቅ ላይ እንደሆነ በመንገር 2ኛ ፎቅ ላይ ጥላው ትወርዳለች፡፡
ወንድወሰን ክሊኒክ ገብቶ ካርድ አውጥቶ ታክሞ ከጨረሰ በኋላ በቀጥታ ወደ ቤቱ አላመራም፡፡ ልጅቱን ፍለጋ ወደ 2ኛ ፎቅ እንጂ፡፡ ግን ልጅቱን በስምም ሆነ የምትሰራበትን መ/ቤት ባለማወቁ ወደ እንግዳ መቀበያው ወርዶ ለእንግዳ ተቀባዩ አድራሻውን እንድትሰጥለት አደራ ሰጥቶ ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡ በህንፃው ውስጥ ካሉት መ/ቤቶች መሀከል በሰላም የጉዞ ወኪል ውስጥ የምትሰራው ፍሬህይወት የስልክ አድራሻው ከደረሳት ከቀናት በኋላ ስልክ ትደውልለታለች፡፡ ‹‹የመ/ቤቴ የሥራ ባህሪ ከብዙ ደንበኞች ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ከደንበኞቻችን አንዱ ይሆናል ብዬ ነበር የደወልኩለት›› ብላለች በወቅቱ ለቁም ነገር መፅሄት በሰጠችው ቃለ ምልልስ፡፡ ወንድወሰን ግን ስትደውልለት ምን ሊላት እንደሚችል አስቀድሞ ተዘጋጅቶበት ስለነበር ተገናኝተው እንዲነጋገሩ በመጠየቅ ይቀጣጠራሉ፡፡ ተገናኝተው ሲነጋገሩ ይግባባሉ፤ ውሎ ሲያድር በፍቅር ይወድቃሉ፡፡
ሁሌም በንግግሩ መሀል የእግዚአብሔርን ስም ሳይጠራ ቆይቶ የማያውቀው ወንድወሰን ስለ እያንዳንዱ ነገር መተቸትና ከሥር መሰረቱ ጀምሮ ማብራራት የሚወድ ሰው ነው፡፡ ‹‹አፉ ጤፍ ይቆላል›› ይላሉ የቅርብ ጓደኞቹ የንግግር ችሎታውን ሲገልፁ፡፡ ወንድወሰን ከመደበኛ ሥራው ውጪ በሥነ መለኮት ትምህርት የተመረቀ ሲሆነስ ሁለቱም የፕሮቴስታን ሀይማኖት /ሙሉ ወንጌል?/ ተከታይ ናቸው፡፡
የአስገራሚው ሠርግ መጨረሻ
ከፍቼ ወደ አዲስ አበባ በአህያ ከአጠና ጋር ተጭኖ የገባው መሳሪያ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በወንድወሰን እጅ ሲፈታታና ሲገጣጠም፣ ሲወለወልና ሲሞከር ከርሟል፡፡ ከፍ/ቤቱ ውሳኔ በኋላ በተደጋጋሚ ‹‹የእገድልሻለሁ›› ዛቻ ያደርግባት የነበረችው ፍሬህይወት ጉዳዩን በቀላሉ ባለማየት ለቤተዘመድ ጉባኤና ለሽማግሌዎች ብታሳውቅም የዛቻውን እውነተኛነት ለማስረዳት ባለመቻሏ ተቀባይነት ሳታገኝ ቆይታለች፡፡ ነገሩ እጅግ እየተደጋገመና እየበዛ ሲመጣ ግን ወደ ህግ ለመሄድ ተገዳለች፡፡ ‹‹ለህይወቴ ያሰጋኛል›› በማለትም ፖሊስ ጣቢያ ማስመዝገቧን ቤተሰቦቿ ይናገራሉ፡፡
የወንድወሰን ዛቻ ነፍስ ዘርቶ ከፍቼ ባገኘው ‹‹የሌባ መከላከያ መሣሪያ›› ሞራል አግኝቶ የሁለት ልጆቹን እናት ለመቅጠፍ ማሴር የጀመረው ግን ጥቅምት ከገባ ጀምሮ መሆኑን የሟች ቤተሰቦች ያስታውሳሉ፡፡ ዘወትር ቅዳሜ ቅዳሜ ከካሳንቺስ መናኽሪያ አካባቢ ከሚገኘው የወላጆቿ ቤት እየመጣ ልጆቿን ወስዶ በማዝናናት የሚመልሰው ወንድወሰን ጥቅምት ከገባ በኋላ ግን መጥቶ ልጆቹን አልወሰደም፡፡ በሁለተኛው ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን ጠዋት ግን ወደ መናኽሪያ ያመራው ልጆቹን ፍለጋ ሳይሆን እናታቸውን ፍለጋ ነበር ተብሏል፡፡
እናም ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ከቤት በመውጣት ደምበል አካባቢ ወደሚገኘው ሱቋ እናቷን ጭና ስታመራ ከኋላዋ መኪናውን አስነስቶ መከተል ጀመረ. . . . .የሆነውም ሆነ

ኢሳት ዜና:-የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ እንዲከበር እንዲታገል ጥሪ አደረጉ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሕዝብና ለመንግስት ጥሪ አደረጉ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ እንዲከበር እንዲታገል ጥሪ አደረጉ።

ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ አርብ ህዳር 28 ቀን ከኢሳት ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ኢህአዴግ ከጥቂት አመታት ወዲህ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ የሚጠራው ህዳር 29 ቀን፤ በዋንኛነት ሕገመንግስቱ የጸደቀበት ቀን እንደሆነ በማስታወስ፤ ኢህአዴግ ቆም ብሎ በማሰብ የህገ መንግስቱን የሰብአዊ መብት አንቀጾች እንዲያከብርና እንዲያስከብር አሳስበዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሕገ መንግስቱ በሚረቀቅበትም ግዜ ይሁን በሚጸድቅበት ግዜ ስህተቶች እንደተሰሩ አስታውሰው፤ ህገ መንግስት የማይለወጥ የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል ስላልሆነ፤ ኢህአዴግ ህገመንግስቱን እንዲያሻሽልም ጠይቀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት፤ የገዢውን ፓርቲ የአምባገነንት ባህርይ በመተንተን፤ ገዢው ፓርቲ “ተገዶ እንጂ በልመናና በመለማመጥ በፈቃደኝነት በህዝብ የሚፈለገውን ለውጥ እንደማያመጣ” ገልጸው የጻፉትና ህዝቡም የተበታተነ ብሶቱንና ምሬቱን ወደአመጽና እምቢተኝነት መለወጥ እንዳልቻለ የተቹት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሀሳባቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ውይይት አብራርተዋል።

ከህዝቡ ምሬት ወደ አመጽ ያለማደግ ሁኔታ ጋር በተያያዘም ምክንያቱ የተለያዩ እንደሆነ ገልጸው፤ በተለይም ከምርጫ 97 በፊትም በሁዋላም ኢህአዴግ በህዝቡ ላይ ባደረሰው የጭካኔ ጥቃት ምክንያት በህዝቡ ላይ የፍርሀት ድባብ ሰፍኖ እንደሆነ ተናግረው፤ ህዝቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይጠብቅ፤ መብቱን ለማስከበር መስራት አለበት ብለዋል።

ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በሬድዮ ፕሮግራማችና ላይ ይከታተሉት።

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ረቡእ ሕዳር 26፡ 2005 የተጀመረው ስብሰባ በዛሬው እለት ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ እንደዋለ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።

የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላምና አንድነት ጉባኤ እንደቀጠለ ነው

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ረቡእ ሕዳር 26፡ 2005 የተጀመረው ስብሰባ በዛሬው እለት ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ እንደዋለ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።

ስብሰባው እስከእሁድ ፕሮግራም የተያዘለት ቢሆንም፤ ምናልባት ከእሁድ በፊት በዛሬው እለት ውጤቱ ሊታወቅ ይችላል ሲሉ አንዳንድ ምንጮች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያው ልኡካን ዳላስ በደረሱበት እለት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለፓትሪያርክ መርቆሬዎስ የጻፉትን ደብዳቤ ተከትሎ የተፈጠሩ ሁኔታዎች ትኩረትንና ውይይትን ጋብዘዋል።

ፕሬዚዳንቱ፤ ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ወደመንበራቸው አንዲመለሱ የጋበዙበትን ደብዳቤ አንስተው፤ በምትኩ አገርቤት ገብተው እንደማንኛውም ጳጳስ ለምርጫ መወዳደር ይችላሉ በሚል ደብዳቤ እንደሚለወጥ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ለአሜሪካን ድምጽ ተናግረዋል።

ከሀገር ቤት በመጡትና በውጪ በሚገኙት አባቶች መካከል ሰላማዊ በመሆነና በመግባባት መንፈስ በቀጠለው በዚህ ስብሰባ፤ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው በተነሱበት ሂደት ላይ መወያየታቸው ታውቋል።

አሁን እርሳቸው ወደሀገር ቤት እንዴት ይመለሱ በሚለው ሁኔታ ላይ እየመከሩም እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ኢሳት ዜና:-የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል።

በጂዳ የብአዴን ዝግጅት ላይ የተገኙ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተባረሩ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል።

ዛሬ በተጠራው የብአዴን ዝግጅት ላይ የተቃውሞ ድምጻችን እናሰማለን በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወረቀት በህቡዕ የበተኑ ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ እንዳያካሂዱ በሚል ፍራቻ ጥሪ የተደረገላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከስብሰባው ውስጥ እየተጠሩ እንዲባረሩ መደረጉን ነዋሪዎች ለነቢዩ ሲራክ ገልጸውለታል።

ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ መታዎቂያ አሳዩ የሚል ምክንያት ለመስጠት የተሞከረ ቢሆንም፤ መታወቂያ ይዘው የተጠረጠሩና የተፈሩ አንዳንድ ነዋሪዎችም ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ እንደተደረጉ ታውቋል፡፡

የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በባንዴራ አጅበው ከኮታቸው ላይ የለጠፉ የብአዴን አባላት ነዋሪዎችን በጥርጣሬ አንዳይገቡ ሲከለከሉና የፈለጓቸውን እየመረጡ ሲያስገቡ እንደታዘበ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ዘግቧል።

ከመግቢያው በር ያሉትን የሳውዲ ልዩ ኮማንዶ ወታደሮችን ያናገረው ነቢዩ ሲራክ፤ ”የቆንስሉ ሃላፊዎች ማንም እንዳይገባ ከልክሉ ብለውናል” በማለት እንዳስረዱትና ነዋሪውን በማግባባት ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ሲማጸኑ እንደተመከተም ገልጿል።

የብአዴን አባላት እገዳው የተደረገው በጸጥታ ምክንያት እንደሆነና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተጠረጠሩና የማይታወቁ ሰወች እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን ገልጸዋል።

አንዳንድ የብአዴን አባላት በጥሪ የመጡትንም እያንጓጠጡ ያስወጧቸው ሲሆን፤ ስብሰባው ያለወትሮው በጊዜ ሲጠናቀቅ ከስብሰባው የወጡ አንዳንድ ሰዎች ሲገቡ ችግር እንደገጠማቸውና በስብሰባው ላይ ምንም አይነት ፎቶም ሆነ ቪዲዮ እንዳይነሳ ቁጥጥር መደረጉንና ስብሰባው በተቃውሞና ፍራቻ ሲናጥ ማምሸቱን እንደገለጹለት ነቢዩ ሲራክ ከጂዳ ገልጿል።

በአንዋር መስጊድ ዛሬም የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋቡ

በአንዋር መስጊድ ዛሬም የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋቡ

ኢሳት ዜና:-በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እስላም ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአንዋር መስገድ በመገኘት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ አምርረው ተቃውመዋል።

ምእመናኑ 27 ቁጥር የተጻፈበት ወረቀት በማውለብለብ ” አንቀጹ ይከበር፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ አሸባሪዎች አይደለንም” በማለት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተሰምቷል።

ምእመናኑ 27 ቁጥር በመያዝ ተቃውሞአቸውን ያስተጋቡት በህገመንግስቱ በአንቀጽ 27 ላይ የተደነነገገው የሀይማኖት እኩልነት መብት ይከበር በማለት ነው።

አዲሱ መንግስት የመለስ መንግስት ይከተለው የነበረውን ችግሮችን በሀይል የመፍታት ዘዴ መከተሉ፣ ከኢትዮጵያውያን አልፎ በጸረ ሽብር ትግሉ ወዳጅ ተደርጋ የምትታየዋን አሜሪካ ሳይቀር እያሳሰበ የመጣ ጉዳይ ሆኗል።

በእስር ላይ በሚገኙት የኮሚቴ አባላት ላይ የሚታየው የተንዛዛ የፍርድ ሄደትና በአባላኦቹ ላይ በእስር ቤት የፈጸመው አሰቃቂ እርምጃ ምእመኑን ማበሳጨቱን ወኪላችን ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

Dec 7, 2012

ESAT Daliy News Amsterdam Dec 07 2012 Ethiopia

ዘረኝነት ማንን ጠቀመ ከያሬድ ኤሊያስ

የህይወት ታሪክ
መለስ ዜናዊ
አቶ መለስ በታሪክ የመጀመሪያው በምስራቅ አፍሪካ የዘረኛ አፓርታይድ አገዛዝ አቀንቃኝ የነበሩ ከቀድሞውን ጀምሮ በግርግር በወረሱት ህወአት ተብዪ ሽቃጭ እና ረቃጭ ድርጅት ያለምንም ጦር ሜዳ ጀብዱ ወይንም ችሎታ ፊደል በመቊጠር ብቻ ሊቀመንበር እንደሆኑ እናውቅ ነበር።
1፦ ኤርትራን ከተቀረው ኢትዮጵያ ግዛት እንድትገነጠል አስተምረው ያለፉ።
2፦ ያለምንም ማመንታት የኢትዮጵያን ህዝብ አስንቆ ብሎም አማራ የተባለውን ብሄር እንደነሱ አጠራር (አድጊ)መጥፋት አለበት ብለው አስተምረው ያለፉ።
3፦የ97ቱን የኢትዮጵያ ቊጣን በሰው ውስጥ መቼም ሊበርድ የማይችል እሳትን አቀጣጥለው እሳቸው ወደማየቀረው ህየወት የሄዱ።
4፦የጋምቤላ አኙዋክ ህዘብ በግፍ ያስጨረሱ እረ ስንቱ ብቻ።

Dec 6, 2012

ወያኔን የዉጭ ምንዛሪ የለዉም – ዶላር አበድሩኝ ይለናል


አቶ መለስ ስልጣን ከጨበጡ ጀምሮ ወደ 36 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን እርዳታ ከምዕራባዉያን አገሮች አገዛዛቸዉ አግኝቷል። የሕዝቡ ኑሮ ግን አልተሻሻለም። ባሰ እንጂ። ዶላሩ ወዴት ሄደ ? እግዜር ይወቀዉ።

አሁንም ወደ አምስት ሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ለረሃብና ለእልቂት ተጋልጧል። አንድ ኩንታል ጤፍ 1500 ብር ሲሸጥ በደርግ ጊዜ 10 ዳቦ የሚገዛው አሁን አንድ ዳቦ ብቻ ነዉ የሚገዛዉ። ኑሮ እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ ዉስጥ ዉስጡን የሚያልቁት ወገኖቻችን ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አከባበር ነቀፉ

ኢሳት ዜና:- ኢሳት ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦች በአል አከባበር የይምሰል ነው በማለት ተችተዋል። የተረፈች ልጅ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስድስት ኪሎ ግቢ ተማሪ እንደተናገረው ኢትዮጵያ በጥቂቶች የምትገዛ ፣ አብዛኛው ህዝብ የበይ ተመልካች የሆነባት አገር ናት ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብሄሮች መብት አለመከበሩ በግልጽ የሚታየው በስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ነው የሚለው ተማሪ፣ ተማሪዎች እርስ በዘር በመከፋፈላቸው ለመገናኘትና በአንድ አገር ጥላ ስር ለመቆም እየከበደ መምጣቱን ተናግሯል ።

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ኢህአዴግ ያስገኘው የብሄር ብሄረሰቦች መብት ውጤት ተደርጎ እየታየነው ምን አስተያየት አለህ ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ፣ ሀይለማርያም ማለት ” የራሺያው ሜድቬደቭ ነው፣ ስልጣን የለውም ለምልክት የተቀመጠ ነው” በማለት መልሷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተንሰራፋው ዘረኝነት ተማሪዎች ለአገራቸው ጉዳይ በአንድነት እንዳይቆሙና እንዳይታገሉ እንዳደረጋቸው ተማሪው ገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዛሬው እለት በአዋሳ ዩኒቨርስቲ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ያከበረ ወጣት እንደገለጠው በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄረሰቦች መብት ተከብሮአል ብሎ እንደማያስብ ገልጿል።

የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ በበኩሉ ህገመንግስቱ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት መከበር እንደሚደነግግ ገልጾ፣ ይሁን እንጅ በህገመንግስቱ ውስጥ የሰፈሩት መብቶች ባለመከበራቸው የብሄሮች መብት ተከብሯል ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጿል።

ክልሎች ራሳቸውን እያስተዳደሩ ነው ብሎ እንደማያምን የገለጠው ወጣት ዳዊት፣ በብሄር ደረጃ መብቱ የተከበረለት ብሄር አለመኖሩን ይሁን እንጅ የገዢው ፓርቲ ሰዎች የሰዎችን መብት እስከ መድፈር የሚደርስ መብት እንደተከበረላቸው ገልጿል( 7፡08-7፡35)። በብሄሮች ጥያቄ ላይ ያቀናበርነውን በነገው እለት በትኩረት ዝግጅት ላይ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በመያዝ በአሉን እንዲያከብሩ እየተገደዱ መሆኑን ርእሰ መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ርእሰ መምህር ” ትምህርት ቤቶች የኢህአዴግ የፖለቲካ ትምህርት ቤት ሆነዋል” ሲል ገልጿል።

ተማሪዎች ሳምንቱን ሙሉ በአል አክብሩ በመባላቸው የትምህርት ሂደቱ እየተስተጓጓለ መምጣቱን መምህሩ ገልጿል።

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎችን ጉዳይ ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ

ኢሳት ዜና:- 16ኛው ወንጀል ችሎት የኮሚቴ አባላቱ ጠበቆች ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ ነበረ ቢሆንም፣ ቀጠሮውን ለታህሳስ 8 ፣ 2005 ኣም ለማሸጋጋር ወስኗል።

ዳኞች ለጠበቆችና አቃቢ ህጎች፣ የተከሳሾች ቁጥር ብዙ በመሆኑ ሁሉንም ተመልክተን ለመወሰን አልቻልንም በማለት እንደነገሯቸው ታውቋል። ዳኞቹ እስረኞቹ ችሎት እንዳይቀረቡ የተደረገው ለደህንነታቸው ሲባል ነው በማለት መናገራቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ አባላት ዛሬም ችሎቱን ለመከታተል የመጡትን ሙስሊሞች በአይነ ቁራኛ ሲከታተሉ መዋላቸው ታውቋል።
__________

በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸው

ኢሳት ዜና:- በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል። መንግስት መምህራንን በመሰብሰብ ለማወያየት ሙከራ አድርጓል።

መንግስት የችግሩን ምንጭ ፈልጎ እንደማግኘትና መፍትሄ እንደመፈለግ በመምህራን ላይ ማሳበብን መርጧል። የመንግስት አቋም መምህራን ወደ አረብ አገራት ስለሚደረገው ስደት በቂ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለተማሪዎች አልሰጡም የሚል ሲሆን፣ የመምህራን አቋም ደግሞ ” ተማሪዎች የሚሰደዱት ተስፋ በማጣታቸው ነው” የሚል ነው ።

እድሉ ቢገኝ ከአገሪቱ ህዝብ 40 በመቶው አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ፍላጎት እንዳለው በውጭ አገር የተደረገ አንድ ጥናት ከአመት በፊት ማመላከቱ ይታወሳል።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን በየመን የባህር ሰላጤ እንዲሁም በሰሀራ በረሀ የውሀ ሽታ ሆነው መቅረታቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።

በባህርዳር በመቶዎች የሚቆጠሩ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ተይዘው አንድ ካምፕ ውስጥ ታጎሩ

ኢሳት ዜና:- ለኢሳት ከባህርዳር የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር ይለምኑ የነበሩ ሰዎች ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ተሰብስበው ጅንአድ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ እንዲጠራቀሙ ተደርጓል። ጎስቋሎቹ የተያዙት በባህርዳር የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል ውበት ይቀንሳሉ፣ ለከተማዋም መጠፎ ምስል ይፈጥራሉ በሚል ምክንያት ነው። እንደ ፈለጉ የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲታጎሩ የተደረጉት ጎስቋሎች፣ በአሁኑ ጊዜ በቂ ምግብና ውሀ ያግኙ አያግኙ የታወቀ ነገር የለም። ከታጎሩት መካከል አሮጊቶችና ህጻናት እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሎአል።

በተመሳሳይ ዜናም በከተማ ውስጥ በድለላ ስራና በወያላነት የሚሰሩ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ወጣቶቹ በአሉን ለማክበር ወደ አካባቢው የሚሄዱትን እንግዶች ሊያውኩ ይችላሉ በሚል ምክንያት ነው የሚታሰሩት። ባለፉት ሶስት ቀናት እስርን በመሸሽ በርካታ ወጣቶች መደበቃቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየቱን የጠየቅነው ወጣት እንዳለው “ ጎስቋሎችን በመደበቅ ፣ ለማኝ ጠፍቷል እያሉ ራስን ማታለል አይቻልም፣ የልመና ምንጩን ካላደረቅነው፣ ለማኞቹ ነገ ሲለቀቁ ተመልሰው ከተማዋን ማጣበባቸው አይቀርም።” ሲል አስተያትን ሰጥቷል።

President Girma's Letter to Abune merkorios

ESAT Daliy News Amsterdam Dec 06 2012 Ethiopia

ድሮ ድሮ በጣራ ላይ የሚገባው ዝናብ ነበር እንዳይገባ ደግሞ ድንጋይ ነበር የሚቀመጠው እሱን ለማዳን አሁን ደግሞ ኢሳት እውነት ይዞ ሲመጣ በዲሽ ወያኔ በምን ይከላከለው ለማንኛውም ወያኔ 1 ለ 0 እየተመራ መሆኑን እንዳይረሳ

ድሮ ድሮ በጣራ ላይ የሚገባው ዝናብ ነበር እንዳይገባ ደግሞ ድንጋይ ነበር የሚቀመጠው እሱን ለማዳን አሁን ደግሞ ኢሳት እውነት ይዞ ሲመጣ በዲሽ ወያኔ በምን ይከላከለው ለማንኛውም ወያኔ 1 ለ 0 እየተመራ መሆኑን እንዳይረሳ


ይሄ ሰዉዪ ለትግራይ ህዝብና ለወያ ኔ ደጋፊዎች አዉርሶ የሞተዉ ታሪክ ቢኖር፤[ስድብ===++++100000000000000]ግዜ ፤ዘረኝነት፤በቀል፤ደም ማፍሰስ፤ዉሸት እና ሃገርንና ሃይማኖትን መከፋፈል ይሀ ታዲያ የምን መንፈስ ነው???????

ይሄ ሰዉዪ ለትግራይ ህዝብና ለወያ ኔ ደጋፊዎች አዉርሶ የሞተዉ ታሪክ ቢኖር፤[ስድብ===++++100000000000000]ግዜ ፤ዘረኝነት፤በቀል፤ደም ማፍሰስ፤ዉሸት እና ሃገርንና ሃይማኖትን መከፋፈል ይሀ ታዲያ የምን መንፈስ ነው???????

በሚያሳፍር ሁኔታ ደብዳቤውን የፃፍኩት በስህተት ነው በማለት


ሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ ፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ::


ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ የፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ::

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ ገብቶል በማለት ያነሱት ተቃውሞ አመት ማስቆጠሩን ያስታወሰው የፊርማ ማሰባሰብ መግለጫ በአሰሳ አርሲና በገርባ በመንግስት ታጣቂዎች 7 ሰዎች መገደላቸውን ፡በረካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ሌሎች መሰደዳቸውን በመግለጽ የተባበሩት መንግስታት የሀይማኖት ነጻነት ቢሮ የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ እንዲጽፍ በመጠየቅ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል::

ኢትዮጵያ የአለም አቀፉን የሰብአዊ መብትና የሲቪልና የፖለቲካ መብቶችን ለማክበር ተስማምታ የፈረመች አገር መሆኖን ያስታወቀውና የፊርማ ማሰባሰቡን የጠየቀው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመጅሊስ አባሉን በመስኪድ እመርጣለሁ እያለ መንግስት በቀበሌ አስመርጧል ካለ በሆላ ይህም በሀይማኖት ጣልቃ መግባት በመሆኑ መንግስት ከተግባሩ እንዲታቀብና የሀይማኖት ነጻነት እንዲያከብር የተባበሩት መንግስታትን ለመጠየቅ ማ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎል::

ኢሳት ዜና:-ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ሴኔትና በፕሬዚዳንቱ ካልጸደቀ በስተቀር ተግባራዊ እንደማይሆን ታውቆል::

የዩናይትድ ስቴት ፓርላማ አመታዊው የዲቪ ሎተሪ እጣ እንዲቆም አርብ እለት ባካሄደው ስብሰባ ገለጠ

ኢሳት ዜና:-ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ሴኔትና በፕሬዚዳንቱ ካልጸደቀ በስተቀር ተግባራዊ እንደማይሆን ታውቆል::

በሪፐብሊካን አነሳሽነት ለፓርላማ እንደቀረበ በተገለጠው የዲቪ ሎተሪ ይቁም ጥያቄ ከ245 የፓርላማ አባል የ 139ኙን ድምጽ በማግኘት ነው ያለፈው::

በሀገሪቱ ስደተኞችን ለመግታት በሚለው የሪፐብሊካን አንዱ ስትራቴጂ እንደሆነ በሚነገርለት የዲቪሎተሪ ይቁም ሀሳብ በተለዋጭ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንጂነሪን ፡ በቴክኖሎጂና በሳይንስ ለተማሩ የውጭ ሰዎች ቪዛው ይሰጣል ነው የተባለም::

በዲሞክራቶች አይደገፍም የተባለው ይህ እቅድ ለ ሊካን ታላቅ ፈተና ይሆንባቸዋል ተብሎል::

በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀርቦ የጸደቀው የዲቪ ሎተሪ ይቁም እቅድ በሴኔቱ ጸድቆ በፕሬዚዳንቱ ከተፈረመ ተቀባይነት እንደሚያገኝ የታወቀ ሲሆን ከሴኔት ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል የሚል አስተያየት ከወዲሁ እየተሰነዘረ ነው::

ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ: በህይወታቸው እንዲህ ያለ ማጭበርበር አጭበርብረው አያውቁም። እንደምንም ብለው የ...

ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ: በህይወታቸው እንዲህ ያለ ማጭበርበር አጭበርብረው አያውቁም። እንደምንም ብለው የ...: የርሳቸው ነፍስ… (አጭር ልቦለድ) center;"> በህይወታቸው እንዲህ ያለ ማጭበርበር አጭበርብረው አያውቁም። እንደምንም ብለው የሰማይ ቤት ጥብቃ ሰራተኞችን፤ አሳምነው ወደ ምድር ተመልሰው መጡ። በርቀት ሲመለከቷቸው የ...

በህይወታቸው እንዲህ ያለ ማጭበርበር አጭበርብረው አያውቁም። እንደምንም ብለው የሰማይ ቤት ጥብቃ ሰራተኞችን፤ አሳምነው ወደ ምድር ተመልሰው መጡ። በርቀት ሲመለከቷቸው የነበሩ ኢትዮጵያዊ ነፍሶች፤ “ድሮም ሰውዬው የማሳመን እና የማሳመም ችሎታቸው እኮ ቀላል አይደለም” እያሉ አደነቋቸው።

የርሳቸው ነፍስ… (አጭር ልቦለድ)
center;">
በህይወታቸው እንዲህ ያለ ማጭበርበር አጭበርብረው አያውቁም። እንደምንም ብለው የሰማይ ቤት ጥብቃ ሰራተኞችን፤ አሳምነው ወደ ምድር ተመልሰው መጡ። በርቀት ሲመለከቷቸው የነበሩ ኢትዮጵያዊ ነፍሶች፤ “ድሮም ሰውዬው የማሳመን እና የማሳመም ችሎታቸው እኮ ቀላል አይደለም” እያሉ አደነቋቸው።

ከሰማየ ሰማያት ወደ ምድር ሲመጡ መጀመሪያ በቀጥታ የሄዱት የብራሰልሱ ሃኪማቸው ዘንድ ነበር። አገኙት። ሊጨብጡት እጃቸውን መዘርጋት ፈልገው፤ ለካስ እጅ የላቸውም። ለካስ መላ ስጋቸው ግባ ተመሬት ተብሏል።

“የምረዳዎት አለ…?” አላቸው ዶክተሩ ማን እንደሆኑም እንደረሳቸው የገባቸው ይሄኔ ነበር። “በቃ ሰዉ በራዬን ካላየ አያውቀኝም ማለት ነው…?” ሲሉ እያንሰላሰሉ፤ “ከዚህ በፊት አንተ ዘንድ ታክሜ ሞቼ ነበር። አሁን በስንት ትግል መሰለህ ከሰማይ ቤት የመጣሁት፤ እባክህን የመጨረሻ እድል ሞክርልኝ እና ከህመሜ አድነኝ…!” አሉት። ሃኪሙ ግር እያለው። “ስጋዎን እኮ አልያዙትም” አላቸው…! ይሄኔ “ስጋቸው የት እንዳለ ማሰብ ጀመሩ…

ይህንን እያሰቡ ወደ ቴሌቪዥኑ ዘወር ሲሉ እርሳቸውን “የተኩዋቸው” አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ተመለከቱ። መጀመሪያ “ውይ ይሄንን ሰውዬ ጠቅላይ ሚኒስትር አደረጉት ማለት ነው…?” ብለው ደነገጡ። ወድያውም ታዛዥነታቸውን አይተው ምክትል ሲያደርጓቸው ስተት እንደሰሩ ገባቸው። ያልገባቸው አሁን አቶ ሃይለማሪያም ከአልጀዚራ ጋር እያደረጉ ያለው ቃለ ምልልስ ነው፤

“ወደ አስመራ ሄጄ መደራደር እፈልጋለሁ። መለስም ከሃምሳ ጊዜ በላይ ወደ አስመራ ተመላልሶ ለመታረቅ ሙከራ አድርጓል…” ጆሯቸውን ማመን አቃታቸው። ድሮስ የተቀበረ ጆሮ ምኑ ይታመናል!? “እንደውም ስሜ አያምርም፤ ይሄ ሰውዬ ጭራሽ ሊያስጠምደኝ ሃምሳ ጊዜ ተመላልሷል ይላል እንዴ…! ወይ አነ ግዲ…” ብለው ተበሳጩ ይሄኔ አንድ ወደላይ ቢያስተኩሶ ወይ ደግሞ ራሳቸው አንድ ሮዝማን ቢለኩሱ ደስ ይላቸው ነበር። ነገር ግን ድሮ እንጂ አሁን ምንም የላቸውም እና ራሳቸውን ወደ አዲሳባ ተኮሱ…!

አዲሳባ ሲደርሱ ከተማው በሙሉ በርሳቸው ምስል ተዥጎርጉሯል። ግራ ገባቸው፤ “አልሞትኩም እንዴ…!?” ብለውም አሰቡ። ግን ሞተዋል። ባይሞቱ ኖሮ ስጋ በላያቸው ላይ ይኖር ነበር። ስጋዬን አገኘው ይሆን…? ራሳቸውን ጠየቁ… “የት ይሆን የቀበሩኝ…!? መቼም ቤተክርስቲያን እሺ ብለው አይቀብሩኝም…” አሉ ሰማይ ቤት የተከሰሱባቸው በክርስቲያኖች ላይ የሰሩት ሸፍጦች ቁልጭ ብለው ታዩዋቸው…! መስጂድም አይቀብሩኝም አሉ… አሁንም የሰማይ ቤቱ የክስ ቻርጅ ትዝ እያላቸው። ጫካ ወርውረውኝ ይሆን…? ብለው አስበው ሳይጨርሱ “ምናልባት ቤተ መንግስቱ ውስጥ ተቀብሬ ይሆናል…” ሲሉ ገመቱ እና ወደዛው ገሰገሱ!

ቤተ መንግስት ከመድረሳቸው በፊት ፓርላማ አካባቢ አባላቱን በርከትከት ብለው ተመለከቷቸው። ይሄኔ የፓርላማ ስብሰባው ትዝ አላቸው ቁጣቸው ራሳቸውን አስደነገጣቸው፤ ቀልዳቸም አሳቃቸው። “ኮሚክ እኮ ነበርኩ” ብለው በሆዳቸው ሊያስቡ ሲቃጡ… (ለካስ ሆዳቸው የለም!)

ፓርላማው አካባቢ የሚያዩዋቸው አባላት በሙሉ እርሳቸውን ነው የሚመስሉት። ግር አላቸው፤ እንዴት ነው ነገሩ…! ቆይ ቆይ… ብለው የተለያዩ ባለስልጣናት ቢሮ ሄደው ጎብኘት ጎብኘት ማድረግ አሰኛቸው… ሁሉም ባለስልጣናት እርሳቸውን የሚመስል ነገር በላያቸው ላይ ለጥፈዋል።

የት ነው የተቀበርኩት…? ብለው ሲጨነቁ፤ ለካስ አልቀበሯቸውም። ስጋቸውን ቆራርጠው ተከፋፍለው ሁሉም ባለስልጣኖች እርሳቸውን ለመመስል እያሰፉ ለብሰውታል። “ወይ አነ ግዲ…” በጣም አዘኑ…!

ሀሳባቸው ስጋቸውን ካለበት አውጥተው ብራሰልስ ወስደው ሀኪሙን እባክህ ድጋሚ ገጣጥምና ሞክረኝ… ብለው ሊለምኑት ነበር። ነገር ግን በየት በኩል… ያመኗቸው ባለስልጣናት ተከፋፍለው ስጋቸውን ለብሰውታል። ምናለ የራሳቸውን ስጋ ቢለብሱ!? ሲሉ በጣም ተበሳጩባቸው!

ባለስልጣናቱን ሰብስበው ሊጮሁባቸው ፈለጉ ግን በምን አፍ… “አፌ ማን ጋ ይሆን…” ብለው እያሰቡ እያለ… አንዳች ነገር ወደላይ ሲጎትታቸው ታወቃቸው። የሰማይ ቤቱ ጥበቃ ክፍል ባልደረባ ነው። ጎትቶ ከመጡበት የሰማይ ክፍል ሲያደርሳቸው ኢትዮጵያውያን ነፍሶች አንድ ተረት በዜማ አሉላቸው

“ዶሮ በረጅሙ ሲያሰሯት የለቀቋት መሰላት!

Dec 4, 2012


Petitioning UN Special Rapporteur on Freedom of Religion UN Special Rapporteur on Freedom of Religion: Stop Government Intolerance of Islam in Ethiopia

Petitioning UN Special Rapporteur on Freedom of Religion
UN Special Rapporteur on Freedom of Religion: Stop Government Intolerance of Islam in Ethiopia

Muslims in Ethiopia have been, for more than a year now, holding protests at mosques around the country against what is perceived as government interference in religious affairs. The protesters are demanding that the current members of the Islamic Affairs Supreme Council (Majlis) be replaced by elected representatives and that elections for Majlis representatives be held in mosques rather than in the Kebeles. Some members of the Muslim community accuse the Ethiopian Government of controlling the Majlis and sponsoring the propagation of Al-Ahbash, a little known sect of Islam. The Ethiopian Government, on the other hand, accuses the protesters of being led by extremists who want to establish an Islamic state in place of the current secular multination federation. The Ethiopian Government has responded against some protests in 2012 with deadly force, most recently in Assassa in April and Gerba in October, resulting in the death of at least seven protesters, a large number of injuries, and the imprisonment of a number of protesters on terrorism charges.

Since Ethiopia is a state party to the Universal Declaration on Human Rights and the International Convention on Civil and Political Rights, in this petition, we, in earnest, implore the UN Special Rapporteur on Freedom of Religion to issue allegation or urgent appeal letters demanding the Government of Ethiopia to end the ongoing violations.

You can sign the petition by clicking here.

Thanks!
The team

ESAT DC Daily News 3 December 2012

HELP ESAT ESAT ESAT ESAT

This video, shown at the 2012 PEN American Center Literary Gala in New York City on May 1, 2012, introduces jailed Ethiopian journalist and dissident blogger Eskinder Nega, recipient of the 2011 PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award. Take Action for Eskinder now by visiting www.pen.org/eskinder

BREAKING NEWS JIMMA UNIVERSITY DEC 3 ESAT TV

Dec 3, 2012

በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራ
ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነባበቱልኝ…!?

ይቺ ጨወታ ለአዲሳባዋ ፍትህ (አዲስ ታይምስ) ተልካ ነበር። ታድያ እርስዎስ ለምን ታመልጥዎታለች!?

ዛሬም ወደ ኬኒያ ይዤዎት ልሄድ ነው። “አረ አንከራተትከን!” ብለው ቅር እንዳይሰኙብኝ ጥሩ ጥሩ ጨዋታዎች ስላሉ እንዳያመልጥዎ ብዬ ነው።

ኬኒያ ዘልቀን ከመግባታችን በፊት ስለ ሀገራችን ጉዳይ አንድ አስተያየት ለመስጠት ተነሳሽነቱ አለኝ። እኔ የምለው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርስ ነው የሚለው ነገር የምር ነው ማለት ነው። መንግስታችን መቼም ማፍረስ ብርቁ አይደለም። እውነቴን ነው የምለው ላለፉት ከሃያ የሚበልጡ አመታት በሳቅ ሲያፈርሰን አይደል እንዴ የከረመው…!? አሁን ደግሞ ሀውልታችንን ሊያፈርስው መሆኑን ስንሰማ ባለፈው ጊዜ ልምዱ ነው ወይስ አዲስ ስልጠና ወስዶ ነው ብዬ ጠይቄያለሁ!

ሎሬት “ኦቦ” ፀጋዬ ገብረ መድን ጉዱን አላየ ያኔ በርሱ ጉርምስና ዘመን አንድ ጀብራሬ ሀውልቱ ጥግ ሽንቱን እየሸና “አንተ ድንጋይ እሸናብሃልሁ… ጓደኞችህ የተባሉትን እሺ ብለው በማርቸዲስ ሲንፈላሰሱ አንተ ይኸው እምቢ ብለህ ድንጋይ ሆነህ ቀረህ! እሸናብሃለሁ” ሲለው ከጀብራሬው ጋር “ድንጋይ አይደለም አትሸናበትም” እያለ እንዳልተፋለመ፤ አሁን የባሰባቸው ጀብራሬዎች ሀውልቱን ሊያፈርሱት መሆኑን ቢሰማ ቢኖርም በብስጭት መሞቱ አይቀርም ነበር። አንድ የፌስ ቡክ ወዳጃችን “ፀጋዬ ይቺን ሰዓት” ስትል ሸጋ ግጥም ገጥማ ተመልግቻለሁ… እኔም አቅም አጥቼ እንጂ ይሄንን ሳይ ግጥም ብቻ ሳይሆን ቡጢም ብጋጠም ደስታዬ ነበር… ግን ፈራሁ…! እሸሸግበት ጥግ አጣሁ! እፀናበት ልብ አጣሁ… “ባከሽ እመብርሃን ይብቃሽ፣ ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ… ፅናት ስጪኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ፣ ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን የእርሷን ሞት እኔ እንድሞታት፣ ገላዋ ገላዬ እንዲሆን።… አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ እፀናበት ልብ አጣሁ።…” ብለው ለሀገራቸው የተሰዉ አባት ሀውልት ሲፈርስ ማየት እውነትም ግጥም ብቻ ሳይሆን ቡጢም ያጋጥማል….!

ኢህአዴግ ግን የሚገርመኝ መመስገን ለምን እንደማይፈለግ “ጎሽ አበጃችሁ” መባልን ለምን እንደሚፀየፍ ነው። የባቡር ግንባታ ስራ መጀመር እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ሆኖ ሳለ የማይነኩትን ከመንካት ትንሽ ዘወር አድርጎ ድምፁን ሳያሰማ መስራት ሲችል ግረግር መፍጠር በጣም ያስደስተዋል። ድሮስ በግርግር የገባ ምን መላ አለው እንዳይሉ… ካሉም ይበሉ።

የኔ ነገር ኬኒያን ደጅ አቁሜ የሀገር ወሬ ላይ ተጠመድኩኝ አይደል ይቅርታ ኬኒያዬ… በነገራችን ላይ ኬኒያ በከተማዋ ውስጥ ዘመናዊ ባቡር መጠቀም እንደጀመረች መቼለታ በኢቲቪ ሰምቻለሁ። እርስዎም ወይ ከእኔ ወይ ከኢቲቪ ሳይሰሙት አይቀሩም… ለባቡሩ ስትል ሀውልት ማፍረሷን ግን አልሰማሁም…

ሌላ በነገራችን ላይ ከአቡኑ ሀውልት ጋር የተያያዘ የዚሁ ቀጣይ የሚመስል ጨዋታ በኢሳት ድረ ገፅ ላይ ታገኙታላችሁ።

እንቀጥል… በኬኒያ የስደት “ኬዝ”…

“ኬዝ” ይህንን ቃል በዚህ መልኩ ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቅበሁት “ምን አለኝ ሀገሬ” ብዬ ስደት ከወጣሁ በኋላ ነው። ቆይ ቆይ… እዚች ጋ አንዲት ጨዋታ መጣች… አንድ ወዳጃችን ነው። በሀገሩ ጉዳይ ምርር ብሎት መታወቂያው ላይ ዜግነት ኢትዮጵያዊ ተብሎ ተፅፎ ሳለ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየቱን እያማረረ ወደ ቤቱ ገባ። ቤቱ ሲገባ የደላው ቴሌቪዥን የአንድ መምህርን ሙዚቃ ከጭፈራ ጋር አዋህዶ እያቀረበ ነው። ጌቴ አንለይ ይባላል ዘፋኙ። (በነገራችን ላይ ጌቴ ድሮ መምህር ነበር። ከዛ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ አንድ ግጥም ፃፉ። ግጥሙ እንዲህ ይላል። “ሩጥልኝ ልጄ ዝፈንልኝ ልጄ መማር ለኔም አልበጄ!” አሉ። ይመስለኛል ይህንን ግጥም ጌቴ አነበበው እናም መምህርነቱን ትቶ ሙዚቀኛ ሆነ… “መሰለኝ” ካሉ የፈለጉትን ማውራት ይቻላል። መሰለኝ ነው ያልኩት!)

እናልዎ ይህ ወዳጃችን የጌቴ አንለይን “ምን አለኝ ሀገሬ!” ሙዚቃ ሲሰማ፤ ቀን በዋለበት የደረሰበት በደል፣ ሁሌም እንደ ሁለተኛ ዜጋ የመቆጠሩ ነገር ክንክን አድርጎት “ለ”ን አጥብቆ “ምን አለኝ ሀገሬ… ምን አለኝ ሀገሬ…?” እያለ መዝፈን ጀመረ። እንዳይፈርዱበት ወዳጄ ሰዎች በሀገራቸው ጉዳይ እጅግ ተስፋ ሲቆርጡ ብዙ ጥያቄ ይጠይቃሉና አይፍረዱ። በዛን ሰሞን ወዳጃችን ዳዊት ከበደ እና መስፍን ነጋሽ “እውነት ግን ይሄ ሀገር የማነው?” ብለው እንደጠየቁት ማለት ነው። እነ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ እነ ሚሚ ስብሐቱ፣ እነ ጋሽ በረከት ሰሞን ለሁሉም የምትበቃዋን ሀገር እንደ ገብጋባ ህፃን ምግብ በልቶም እንደማያውቅ፤ ሀገሪቷን በሙሉ ዝግን አድርገው ይዘው፤ ምን ዝግን አድርገው ብቻ… በሁለት ጉንጫቸው ጎስጉሰዋት (በርግጥ ይሄም ተጋኗል!) ብቻ ግን በጥቅሉ “ሀገሪቱ የኛ ብቻ ናት” ብለው ቢያስቸግሩ ግዜ ነው፤ መስፍኔ እና ዴቭ “እውነት ይቺ ሀገር የማናት?” ብለው መጠየቃቸው። በነገራችን ላይ መልሱ “ሀ” ነው። “ሀ” ምን መሰልዎ? “ሀገሩ የሁላችንም ነው። የእነሱም የእኛም!” ይህንን መለስ በተሰደድኩ በሳምንቱ ተመስገን ደሳለኝ ነግሮኝ ነበር። ያኔም በሆዴ “ቀድመህ አትናገርም ነበር” ስል አጉረምርሜያለሁ… እዚችግ ሳቅ ይግባልኝ…

ይቅርታ ወዳጄ ዋና ጨዋታዬን አልረሳሁትም። ድጋሚ አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ። እና ኬኒያችን ሹልክ ብለን እንገባለን።

በኬኒያ “ኬዝ” እንጀራ ነው። በርካታ የሀገሬ ሰው “ምን አለኝ ሀገሬ? ምን ቀረኝ ሀገሬ?” ብሎ ይሰደዳል። በአስቸጋሪ በርሃ ውስጥ፣ ህይወቱን ለአደጋ አጋልጦ ይወጣል። አሁን ስለ ስቃዩ የምናወራበት ገፅ ላይ አይደለንም። እና ውጣ ውረዱን አልፎ እዚህ ደርሷል አሉ፤ “አንኳኩ ይከፈትላችኋል ስትገቡ ሌላ በር ይጠብቃችኋል!” እንዳለው በውቀቱ ስዩም፤ ያንን ሁሉ አልፎ እዚህ ደግሞ ሌላ ውጣ ውረድ ይጠብቀዋል። ወደ ሌላ ሀገር ለመዛወርም ሆነ በተሰደደበት ሀገር ላይ ተረጋግቶ ለመቀመጥ አንደ ወሳኝ ነገር አለ “ኬዝ” ይባላል። ጥገኝነት የመጠየቂያ አሳማኝ ምክንያት!

እንግዲህ አሁን የምናወራው “እዛ ቁጭ ብዬ ርሃብ ከምሞት ወጥቼ የመጣው ይምጣ!” ብሎ ስለተሰደደው “የኢኮኖሚ ስደተኛ” ነው ማለት ነው። ልብ አድርጉልኝ! ስደተኞችን ተቀብሎ የሚያስተናግደው ድርጅት ደግሞ “የኢኮኖሚ ስደተኛ” ከሆኑ ወደተሻለ ሀገር ለማዛወር ፈቃደኛ አይደለም። እንኳንስ ወደሌላ ሀገር ሊያሸጋግር ይቅርና በተሰደደበት ሀገርም ለመኖር የሚያስችል እውቅና አይሰጥም። እና ምን ይሻላል? የሚሻለውማ “ኬዝን” ማሳመር ነው። “ኬዝ” ከየት ይመጣል? ካሉኝ… አያስቡ… ቀልቦን አሰባስበው ይከተሉኝማ…

“ኬዝ” ልክ እንደማንኛውም ሸቀጥ ይገዛል፣ ተገዝቶም ይለቀማል፣ ተለቅሞም ይበጠራል፣ ተበጥሮም ይፈጫል፣ ተፈጭቶም ይቦካል፣ ተቦክቶም ይጋገራል! ይህንን የሚያከናውኑ ደግሞ ጥሩ ጥሩ “ኬዝ” ጋጋሪ ባለሞያዎች አሉ። ስለ ባለሞያዎቹ ሌላ ጊዜ በስፋት እናወራለን። ለአሁን ግን ከአንዳንድ ባለኬዞች ጋር የተጨዋወትኩትን እንካችሁ

አንድ

ማርዬ ትባላለች። የመጣችው ከጎንደር ነው።፡ቆንጆ ናት። ንግግሯ ላይ የዋህነቷ ተንኮል አለማወቋ፣ በጥቅሉ ጨዋነቷ ይነበባል። ዘመዶቿ ካናዳ ነዋሪ ናቸው። ታድያ እሷስ ለምን ይቅርባት? ልትሄድ ሻንጣዋን ሸክፋ መሸጋገሪያው ሀገር ላይ ደርሳለች። አገኘኋት… “ከሀገርሽ ለምን ወጣሽ?” አልኳት። “ዋ…የኬዜን ልንገርህ ወይስ የእውነቱን…?” ብላ ሳቀች። በነገራችን “ዋ!” የምትለውን የአግርሞት ቃል ትግሬዎች ይሏታል። ጎጃሜዎች ይሏታል። ጎንደሬዎችም አይምሯትም። ልብ ብለን ብንመረምር የተጣመርንበት ብዙ ነገር አለ። እስቲ… “ኬዝሽ” ምንድነው? አልኳት። “አረ ተወኝ! የኔስ ይቅር ይበለኝ…!” ብትለኝ ጭራሽ አጓጓችኝ። እስቲ ንገሪኝ… “ቄሱን አባቴን… አርበኛ ግንባር ተዋጊ ነው ብዬ…” እሺ…

በጎንደር አካባቢ በተለይም በታች አርማጭሆ አርበኛ ግንባር እንደሚንቀሳቀስ እኔም አውቃለሁኝ። ግንባሩ ከኢህአዴግ ጋር ትግል ከገጠመ ቆይቷል።

ታድያ የጎንደሯ ማርዬ፤ በስደት ያረፈችበት ኬኒያ ወደ ዘመዶቿ እንዲቀላቅላት “ወደ ጎንደር መመለስ አልችልም” ብላ ስትናገር አበቷ የአርበኛ ግንባር አባል እንደነበሩ፣ ከዛም በአንዱ ውጊያ እንደተማረኩ፣ ከዛም መንግስት የት እንዳደረሳቸው እንደማታውቅ፣ ከዛም አልፎ ጨካኙ መንግስት፣ እርኩሱ መንግስት እነርሱን፤ ልጆቻቸውን ማደን ሲጀምር እንደወጣች የሚያስረዳ “ኬዝ” ተጋግሮላታል።

ማርዬ ይቺን በደንብ አጥንታ ኢንተርቪው ያደረገች ጊዜ ስትናገር ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች እንደነበር ነገረችኝ። ምን ሆነሽ አለቀስሽ? ብላት “እንጃ አባቴን… ሀጥያቴ ይሆናላ! የውሸቴ ብዛት…!” አለችኝ። ማርዬን ስደተኞችን የሚቀበለው ድርጅትም ማልቀሷን ሲያይ ሆዱ ተንቦጫቦጨበት ከዛም አምኖ ተቀብላት። እናም በዛ ሰሞኑ ካናዳ ልትሄድ ጥቂት ቀርቷት ነበር። ካናዳ ስትገባ መጀመሪያ የምታደረገው ነገር ምን መሰልዎ… “ቄሱን አባቴን ጦረኛ በማለቴ ንስሀ እገባለሁ” ብላኛለች።

ሁለት

ከሀብቶም ጋር የተዋወቅነው አንድ “ኬዝ ጋጋሪ” ወዳጄ ጋር መጥቶ ነበር። ሀብቶም ገብረ ክርስቶስ ገብረ ማርያም ይባላል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኖር ወደ ሌላ ሀገር እየሄዱ መሞት ይሻላል።” ይላል። የሀገር ቤት ኑሮ ሮሮ ሆኗል የሚለው ሀብቶም። ከመሀል አዲሳባ ነው ውልቅ ብሎ የወጣው። ስራ አጥነቱ አሰቃየኝ ከዛ በዚህ በኩል “ላጥ ማለት” ይሻላል ብዬ መጣሁ ብሎኛል።

ሀብቶም እዚህ እንደገባ በርካታ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወዳጆች ነበሩት። ታድያ እነዚህ ኦሮሞ እና ኦሮምኛ ተናጋሪ ወዳጆቹ በሙሉ ኬዛቸውን የሰሩት “ኦነግ” ነን ብለው ነበር። ታድያ እርሱስ ለምን ከጓደኞቹ ይለያል “ኦነግ” ነኝ ብሎ “ኬዝ” አስጋገረ። ይህንን “ኬዙን” ያየለት ወዳጄ የሀብቶም “ኦነግ” መባል አስደነቀው። ከዛም ይሔ ኬዝ መታደስ አለበት ብሎ ይህው ጥገና ያዘ። ሀብቶም በጓደኞቼ “ኦነግ” ነኝ ቢልም ድርጅቱ በሚያደርገው ማውጣጫ “ሪጀክት” የመባል እድሉ ሰፊ ነው። ፈረንጆቹ ስምህን ሁሉ አይተው ከየት አካባቢ እንደመጣህ መገመት ጀምረዋል ብሎኛል የ”ኬዝ” ባለሞያው ወዳጄ።

ሶስት

በልዩ እንደ አብዛኛው ስደተኛ “የኢኮኖሚ ስደኛ” ናት! “ቢያልፍልኝ ብዬ ነው ስወጣ ከሀገሬ…” ብላ የተሰደደች። ነገር ግን እዚህ ሀገር ለመኖር ወይም በወጉ ወደሌላ የተሻለ ሀገር ለመሸኘት ጥሩ አሳማኝ “ኬዝ” ያስፈልጋታል። ለኬዝ ጋጋሪዎች የሚከፈለውን እስከ መቶ ዶላር የሚደርስ ክፍያ መክፈል አቅም የላትም። ስለዚህ ራሷ ማሰብ አለባት ማለት ነው። በአንድ ወቅት ከቶጎዎች ጋር ኖራ የምታውቀው በልዩ አንድ ዘዴ መጣላት። ያኔ አብረዋት የነበሩት ቶጎዎች ከሀገራቸው የተሰደዱት “ቡዳ ናችሁ” ብሎ ማህበረሰቡ ስላገለላቸው ነበር። “…አሃ” አለች በልዩ ኬዟንም ጋገረችው። መጀመሪያ ስሟን ቀየረች፤ “የመጣሁት ከቶጎ ነው።” አለች። “ወደ ሀገርሽ መመለስ የማትችይበት ምክንያት ምንድነው?” አሏት። ፈቃጅ፤ ከልካዮቹ። ፈረንጆቹ። እሷም “ቡዳ ነኝ!” አለቻቸው። “ስለዚህ ያስወጣኝ ማህበረሰብ ዘንድ ድጋሚ ብቀላቀል ይገሉኛል። አለች።

አይደነቁ ወዳጄ በስደት ሀገር ተደላድሎ ለመቀመጥ ወይም ወደሌላ የሚደላ ሀገር ለመዛወር በርካቶች ያልሆኑትን ነን ብለው ሲናገሩ መስማት እዚህ የተለመደ ነው። አለበለዛ የስደተኞች ጉዳይን በሚመለከቱት “ሪጀክት” መባል ይመጣል። አንዳንዶቹ “ኬዞች” እጅግ በጣም ከሞራል በታች ናቸው…

አራት አምስት ስድስት…

በአንድ ወቅት ከሱማሌ የሚሰደዱ ዜጎች “ሂጃባቸውን” ፈተው “ክርስቲያን ስለሆንኩ ከሀገር አባረሩኝ” የሚል “ኬዝ” ይሰሩ ነበር። አሁን አሁን ደግሞ ከኤርትራ የሚሰደዱ ብዙዎቹ “ጴንጤ” ስለሆንኩ ወይም “ጆቭሃ” ስለሆንኩ ከሀገር ተናረርኩ ብሎ ማለት አሪፍ ኬዝ እየሆነ ነው። ምክንያቱም ኢሳያስ ነፍሴ በተለይ ጴንጤ እና ጆብሀዎችን ጠምደው ይዘዋቸዋል እና ነው።

በጣም ካስገረሙኝ ኬዞች ውስጥ “ግበረ ሰዶማዊ” ስለሆንኩ ከሀገር አስወጡኝ ተመልሼ ብሄድም ይገሉኛል። ብሎ የተሰራው “ኬዝ” ነው። ልብ አድርጉ አንድ ሰው የሌለበትን ያልሆነውን በራሱ ላይ ለጥፎ “ብቻ ወደ ሀገሬ አትመልሱኝ!” የሚለው ሀገሩ ምን ያህል አላስኖር ብትለው ነው? አቤቱ የምንዘምርላት ብቻ ሳይሆን የምንኖርባት አገር ስጠን ብሎ መፀለይ ይሄኔ ነው።

እስቲ ወዳጄ ለዛሬ በዚሁ ይብቃን እና ለሚቀጥለው ሞራላችንን አስባስበን እና ቤት ያፈራውን እንድናወጋ ያድርገን!

አማን ያሰንብተን!

Today it is hard to be a jornalist in Ethiopia coze it will cost a freedom,things like this getting worse and worse! For Ethiopian Governement being a jornalist and exposig the fact that exist is equally seen as an oposition party for the govnt or a triorist for a country! what a shame for the govnt that call it self a democratic party!!!!!

የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።

ተፋላሚዎቹ ያልተገነዘቡዋቸው አንዳንድ ጉዳዮች ይታዩኛል፤ አንደኛ እስልምና በጎሣ የታጠረ ባለመሆኑ ከወያኔ/ኢሕአዴግ የአመራር መሠረት ጋር የመቃወም ዝንባሌ ያሳያል፤ እስልምና አብዛኛዎቹን፣ በተለይም ትልልቅ የሚባሉትን ጎሣዎች ሁሉ በተለያየ ደረጃ የሚያቅፍ ነው፤ ስለዚህም አንዳንዶች የእስልምና መሪዎች ሌሎች (ማለት – ክርስቲያኑ) አልተቀላቀሉንም እያሉ የሚያላዝኑበትን ቆም ብለው መመርመር ያሻቸዋል፤ ክርስቲያኑ በተለይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ያሉበትን ሁኔታ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል፤ እስላሞች ገና ቀደም ብለው ከብዙ ዓመታት በፊት በተደረገ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹እስላሞች በጎሣ አይከፋፈሉም›› በማለት የገለጹትን ቁም-ነገር አገዛዙ የረሳው ወይም እስላሞቹ ረስተውታል ብሎ ያሰበ ይመስላል፤ አለዚያ እንዲህ ያለ የከረረ እልህ ውስጥ የገባበትን ምክንያት ለመረዳት ያዳግታል፤ ይቺ ባቄላ ያደገች እንደሆን የሚያሰኝ ነገር ለብዙዎች ሰዎች ምንም አልታየም፤ በጉልበት የማይጨፈለቅ ምንም ነገር የለም ከሚል እምነት ተነሥተው ከሆነ ስሕተቱ እየታየ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የእስላሙ ኅብረተሰብ ገና በጠዋቱ በጎሣ የመከፋፈሉን አመራር እንደማይቀበለው በማያጠራጥር መንገድ የገለጠ ይመስለኛል፤ ነገር ግን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች የጎሣ ትግላቸውን ወደቤተ እግዚአብሔር አምጥተው የተከፋፈሉና የተዘጉም ቤተ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ይህ የሚያሳፍር ነው፤ ቤተ መስጊዶች እዚህ ደረጃ አልወረዱም፤ እስልምና በጎሣ አይቀደድም፤ እስላሞች ሁሉ የአላህ ልጆች ናቸው፤ በቤተ መስጊድ የሚሰበሰበው ሁሉ በአላህ ልጅነቱ ነው፤ ስለዚህም በመሀከላቸው ልዩነት የለም፤ ይህ የእስላሞች አቅዋም ሃያ ዓመት ተፈተነ፤ የማይበገር ሆነ፤ ስለዚህም ከጎሣ አስተሳሰብ ወጥቶ ሌላ ቀዳዳ መፈለግ ግዴታ ሆነ፤ አል-ሀበሽ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።

እስቲ ጉዳዩ ለሁላችንም ግልጽ እንዲሆንልን ወደክርስትና ዞረን እንየው፤ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከነገ ጀምሮ የሉተራን ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተከተሉ ቢባል አንደኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን (ካለች) ምን ትላለች? ሁለተኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ምን ይላሉ? ሦስተኛ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 ‹‹መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤›› የሚለው በጤና አለ ወይ? ብሎ መጠየቅ የማይቀር ይሆናል፤ መልሶቹስ ምን ይሆናሉ?

ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ስዒረ ሊቀ ጳጳስ እንደተደረገ አሁን ታወቀ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱም፣ ምእመናኑም፣ ማንም ምንም ያለ የለም፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ሊቀ ጳጳስ የሻረው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ዛሬ እግዚአብሔር ተገለጠልኝ በማለት ሊቀ ጳጳስዋን የሻረባትን ቤተ ክርስቲያን ትቶ ወደሌላ ተገልብጦአል፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በነበረበት ጊዜ የሠራውን ኃጢአት ዛሬ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባል ሆኖ እውነቱን ገልጦልናል፤ ታምራት ላይኔ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ከለቀቀ በኋላ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት መረዳቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚያሳፍር ነው፤ ከዚያም በላይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አሁንም እውነቱን አላወጣችም፤ አንድም ለሹመት ያኮበኮበ ጳጳስ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት አምኖና ተቀብሎ እውነቱን ለመናገር የደፈረ አልተሰማም፤ ጴጥሮሳዊነት ከጴጥሮስ ጋር ተቀብሮአል አንበል? ይበልጥ ያሳፍራል፡፡

የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ለንጽጽር አመጣሁ እንጂ ዋናው ነገሬ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ነው፤ ድርቅና ቁልጭ ያለው እውነት እስልምና አስፈላጊውን መስዋእት ከፍሎ በሰላማዊ መንገድ ጎሠኛነትን ተቃወመ፤ ተቋቋመ፤ አሁን ደግሞ አንደኛ በእስልምና ምእመናን ላይ እንዲጫን የታቀደውን አዲስ የእስልምና ዓይነት አንቀበልም በማለትና ሁለተኛም የእስልምና ካህናትን የምንመርጠው ራሳችን ምእመናኑ ነን፤ ሦስተኛም የእስልምና ካህናቱ ምርጫ የሚካሄደው በመንፈሳዊ ቦታ በቤተ መስጊድ ነው እንጂ በፖሊቲካ ቦታ በቀበሌ አይደረግም አሉ፤ በጎሣ አንከፋፈልም ብለው ጥንካሬያቸውን ያሳዩትን እስላሞች በሃይማኖት ለመከፋፈልና ካህናቶቻቸውን ራሳቸው በየመስጊዳቸው እንዳይመርጡ መከልከል በግልጽ ሕገ መንግሥቱን መዳፈር ነው።

ሁለተኛው ቁም-ነገር አገዛዙ በየቀበሌው ያካሄደው ከሕዝብ ፈቃድ ውጭ ለሆነ ምርጫ እስላሙ ኅብረተሰብ የሰጠው ሰላማዊ መልስ የማያዳግምና የሚያስደንቅ ነው፤ በአገዛዙ ስልት በተመረጡት ሰዎች በሚተዳደሩ ቤተ መስጊዶች ውስጥ አንሰግድም በማለት መስጊዶቹን ባዶ ማድረጋቸው አገዛዙን ራቁቱን አቁሞ ስሐተቱን ያጋለጠው እውነተኛ ሰላማዊ ትግል ነው፤ በቅርቡ ሦስት የአፍሪካ፣ አንድ የእስያ፣ ሁለት ዓለም-አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ኃይለ ማርያም ኢትዮጵያ ለዓለም-አቀፍ ሕጎች የገባችውን ቃል ኪዳኖች ሁሉ እንድትጠብቅ ከመቼውም የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለባት የሚገልጽ ረጅም ደብዳቤ ተልኮላቸዋል፤ ለመብቶቻቸው የቆሙ ሁሉ፣ ጋዜጠኞችም ይሁኑ የሃይማኖት ሰዎች በሽብርተኛነት እየተከሰሱና እየተፈረደባቸው ወህኒ ቤት በመግባታቸው ፍርድ ቤቱንም ወህኒ ቤቱንም ጎብኝተው የሄዱት የስዊድን ጋዜጠኞች በሚያሳፍር ሁኔታ ለዓለም አጋልጠውታል።

የቤቴ መቃጠል ለትኋኑ በጀኝ ያለው ቂል ሰው ነው፤ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ያለው ሰው ሰነፍ ነው፤ ቂልነትም፣ ስንፍናም ለመሪዎች አይበጅምና እግዚአብሔር በጎ መንፈሱን ያሳድርባቸው፤ ያሳድርብን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ወታደራዊ



በሰሜን ጎንደር መተማ ልዩ ስሙ ዘባጭ ባህር በተሰኘ ስፍራ ህዳር 20-2005 ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ቅጥረኛ ጋር የኢትዮጵያ ሕዝብ
አርበኞች ግንባር አገር አድን ሰራዊት ባካሄደው ውጊያ 13 /አስራ ሶስት/ የእብሪተኛው ቡድን ታጣቂዎች በመግደልና 17 /አስራ ሰባት/ በማቁሰል እንዲሁም ተተኳሽ መሳሪያዎችን በመማረክ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።
በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የወያኔው ታጣቂ ኃይል ተጨማሪ ሰራዊት በአካባቢው ያዘመተ ሲሆን፡ አርበኛው ሰሞኑን በተከታታይ እየወሰደ የሚገኘው ድንገተኛ ወታደራዊ ማጥቃት እርምጃ የህዝቡን ትኩረት ከመሳቡም ባሻገር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የፀረ-ወያኔ ትግል መነሳሳት አብይ ሚና እየተጫወተ መሆኑን በርካቶች እየገለጹ መሆኑም እየተገለጸ ነው።

የፖለቲካ ትግል የመጨረሻ አማራጭ የሆነው የትጥቅ ትግልን መፍትሄ አድርጎ ለአመታት ያህል የጊዜ፣ የእውቀት፣ የጉልበት ብሎም የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ከጎጠኛውና መሰሪው ኃይል የመከላከል አኩሪ ጥረቱን ዛሬም እንደ ትላንቱ ሳያሰልስ የሚገፋበት መሆኑን አስታውቋል።

ሰራዊቱ የተለመደውን ጀብድ በፈፀመበት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የግንባሩን ሰራዊት እየተቀላቀሉ መሆኑን የገለጸው የድርጅቱ ወታደራዊ መምሪያ ግንባሩ በተከታታይ የወሰደውንና እየወሰደ የሚገኘውን ወታደራዊ ማጥቃት የመላውን ኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ለሁለንተናዊ የአርበኝነት ትግሉ የተቻለውን በማበርከት ከስርዓት ለውጡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አገር ለመገንባት መነሳት ይገባዋል የሚለውን መልዕክት ያስተላለፋል።

የወያኔ ፓርላማ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ራሱ ያጸደቀውን የይስሙላ ህገ መንግስት በመጣስ ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሮችንና የውጭ ጉዳይ ሚንስትርን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ሚንስትሮችን በመሾም ቀሪው ባለበት እንደሚረግጥ ከሃይለማሪያም ደሳለኝ የቀረበለትን ተቀብሎ አጽድቋል።


ወያኔ በመተካካት ሰበብ ራሱ ያጸደቀውን ህገ መንግስት ጣሰ


ይኸነው አንተሁነኝ
ታህሳስ 1 2012

የወያኔ ፓርላማ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ራሱ ያጸደቀውን የይስሙላ ህገ መንግስት በመጣስ ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሮችንና የውጭ ጉዳይ ሚንስትርን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ሚንስትሮችን በመሾም ቀሪው ባለበት እንደሚረግጥ ከሃይለማሪያም ደሳለኝ የቀረበለትን ተቀብሎ አጽድቋል።

ይህን የህወሃቶች ጊዜ የወሰደ፣ ጥንቃቄ የተሞላበትና የተጠና ሹመት በተመለከተ ገና ያኔ የዘረኛው መለስ ዜናዊ ግብኣተ መሬት ይቅርና በወያኔዎችና የቅርብ ዘመዶች በሚስጥር የተያዘው ገሃድ ሞቱ በይፋ ሳይገለጽ፤ የነበረከት የለቅሶ ሀገር አቀፍ ወጥ ሙሾና ረገዳ ተደርሶ ሳይመረቅ ፤ ዘማሪያን በመዝሙራቸው፣ ደራሲያን በግጥሞቻቸው፣ ዘፋኞች በዘፈኖቻቸውና ተዋኒያንም በትእይንታቸው ”ባለ ራዕዩ መሪ” እያሉ ከመዘባረቃቸው በፊት፤ አዜብ መስፍን የምርጫ ቅስቀሳ እንደሆነ ባሳበቀባት ንግግሯ ”የመለስ ራዕይ እስካልተበረዘና እስካልተከለሰ ድረስ … ወዘተ ወዘተ ከማለቷ እጅግ በፊትና የጠቅላዩን መሞት ያወቁ ሁሉም ወያኔዎች በድብቅ እህህ በሚሉበት ወቅት ሳይቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ ካንድ በላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሊኖር እንደሚችል ያውቅ ነበር።

አንዳንድ ልበ ብርሃን የማሕበረሰባችን አባላት ያህን ጉዳይ እንዲያውም ሲበዛ ወደ ሗላ ጎትተው ጨካኙ መለስ ከመታመሙ በፊት ከሚቀጥለው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሗላ ሊተገብራቸው ካሰባቸው የተነቃቁ የወያኔ አባላትን ማደንዘዣ እና በወያኔ ውስጥ እየታየ ያለውን የህወሃት የበላይነት ይብቃ ማጉረምረም ማስተንፈሻ ዘዴዎች ውስጥ እንዳንዱ የሚጠቅሱት አልጠፉም፤ የሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሮችን ሹመት ጉዳይ ፤ ጨካኙ መለስ በጨካኙ ሞት ተወሰደና እስከ ዛሬ ተጓተተ እንጅ።

የሕዝብ ዓይን ያየውን በዚህ መልኩ ይናገር እንጅ እንዲህ እንዳሁኑ ህግ ተጥሶ በጠራራ ፀሐይ ያለ ምንም ማስተባበያ ሹመቱ ያሰጣል ብሎ አልጠበቀም ነበር። ይልቅስ ከዚያ በፊት የወያኔ ማለዘቢያ ንግግሮችና ማስታረቂያ ወይም ግራማጋቢያ መመሪያዎች ካልሆነም ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ የሆነው ወያኔ የግል ንብረቱ በሆነው ፓርላማ አማካኝነት አንቀጽ 75ን ሞረድ የደርጋታል የሚል ግምት ነበር፤ በነበር ቀረ እንጅ። ከዚህ ይልቅ በጊዜው የተመረጠው የሕዝብን ከመሬት ጠብ የማይል ንግግር፤ ”የነቶኔ ሃሳብ ነው፣ ያሸባሪዎች መላምት ነው፣ እንትና እና እንትና የሚባሉ ንቅናቄዎች በዚህ መልኩ ያሻቸውን ቢያወሩ እኛ ግን ከባለራዕዩ ራእዮች ጋር ሳንበረዝና ሳንከለስ ቀጥለናል” እየተባለ እንደተለመደው በሕዝብ ላይ ተሾፈ። ዛሬ የሆነው ግን የህዝብ አይን ያየውና የተናገረው ሆነ።

ዛሬ ህዝባችንን ያንገበገበው ወያኔ የራሱን ህገ መንግስት አንቀጽ 75ን በመጣስ ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር መሾሙ አይደለም፤ምክንያቱም ህግ መጣስ ለወያኔ የዕለት ተዕለት ተግባሩ ስለሆነ፤ ከዚያ ይልቅ መተካካት በሚል ሰበብ የህወሃት የበላይነት እንደገና መንገሱ እንጅ። ሃይለማሪያም ደሳለኝ አሁን በዋናነት ካቀረበው ሹመት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ሁለቱ በህወሃት ከመያዛቸው አንጻር ሲታይ ሰውየው በራሱ ላይ የቅርብ አለቃና ተከታታይ በመተካካት ስም ለማስቀመጥ እንደተገደደ ያሳይል። የብሄርን ተዋጽኦ ለማሟላት በሚል ከሌሎች ብሄሮች የተሰየሙትም ቢሆኑ ወይም ቀድመው የደነዘዙ አልያም በህወሃት ሰዎች እንዳሻ የሚሽከረከሩና ቦታው ስም እንዲሰጠው ብቻ ሹመቱ የተሰጣቸው ናቸው።

ይችን ”መተካካት” የምትባል ቃልና ውጤቷን በደንብ ያስተዋሉ አንዳንድ ሰዎች እጅግ ወደ ሗላ ተመልሰው የወያኔን የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን በማስታወስ በጊዜው ወያኔዎች ” በሁሉም መልኩ ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች” በሚል ሰበብ የቀበሌ ቴሌቪዥንና የእድር ድስትና ማንኪያ ሳይቀር ወደ ትግራይ ማጓጓዛቸው አይረሳም፤ ምንም እንኳ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ ዝርፊያ ስም እንጅ ምንም ያልደረሰውና ተጠቃሚ እንዳልነበር የሚታወቅ ቢሆንም።

ወያኔ በየጊዜው በሚያወጣቸው እንደመተካካት ያሉ ዘዴዎች በሽፋን ህወሃቶች ያሻቸውን ሲያደርጉና የፈለጉትንም ሲከውኑ ኖረዋል። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች በሚል ሰበብ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጥሬ እቃ፣ የሰው ሃይል፣ የኢንቨስትመንት አቅም፣ የትምህርት ተቋማትና ሌሎች ግንባታዎችን ወደ ትግራይ በማዞር ትልቅ የሙስና መረብ ገንብተውበታል፤ ጥቂት የማይባሉትም ከታጋይነት ይልቅ ባንድ ጊዜ ወደ ታዋቂ ነጋዴነት እና ኢነቨስተርነት ተቀይረውበታል። የትግራይ ሰፊ ሕዝብ ግን ልክ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ”ሽህ ቢታለብ ያው በገሌ…” አለች የምትባለውን የድመቷን ተረት እየተረተ የስቃይ ዘመኑን ይገፋል።

እንዲህ እንደዛሬው የያኔው የወያኔ ፓርላማም ያችኑ የተለመደች ”ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች” የምትለዋን ነጠላ ዜማ በማዜም ከፍ ያለ በጀት ለክልሉ በመመደብ ሙሰኛ ወያኔዎችን አበረታቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በጊዜው የነበሩት ጥቂጥ የህትመት ውጤቶች፤ በእርግጥ ቁጥራቸው ካዛሬው ይበልጥ ነበር፤ ”ትግራይ እስክትለማ ሌላው ሀገር ይድማ” የሚል ጽሁፍ በማስነበባቸው ብዙ መተረማመስ እንደተፈጠረና ከፍ ዝቅ እንደተደረጉ አይዘነጋም።

ሌላው እንደ መተካካት ያለና በሀገራችን ጉድ የታየበትና ታምር የተሰራበት አሁንም እየተሰራበት ያለ ደግሞ ”መድብለ ፓርቲና አውራ ፓርቲ” የሚለው ነው። ወያኔ በሀገራችን መድብለ ፓርቲ ስርአትን እስፍኛለሁ በማለቱ ከዓለም ዙሪያ ከሚጎርፍለት የዲፕሎማሲ ችሮታ በተጨማሪ የትምህርትና የአቅም ግንባታ እገዛ፣ የአቅርቦትና የቴክኖሎጅ ሽግግር እርዳታ እንዲሁም በገንዘብ አገሪቱ አይታው የማታውቀውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እርዳታ በየዓመቱ ወያኔ ሲያፍስ ቆይቷል፤ ምንም እንኳ አንቱ የተባሉ ዓለማቀፍ ተቋማት የሚበዛው የአይነትም ሆነ የገንዘብ እገዛ በወያኔ ባለስልጣናት አማካኝነት ተዘርፎ በውጭ ባንኮች በግል ሃብትነት የተቀመጠ መሆኑን ያጋለጡ ቢሆንም። ይሁንና ይህን ሁሉ ችሮታና ጥቅማጥቅም ያስገኘው መድብለ ፓርቲ ተሽከርክሮና ለዘብ ብሎ ”የአውራ ፓርቲ ስርአት” በመባል አውራ ነኝ ባዩ ወያኔ ህወሃት ተቃዋሚ ነን የሚሉትን ፓርቲዎች ይቅርና የኔ ናቸው በሚላቸውም በብአዴን፣ በደህዴን እና በኦህዴድም ላይ አውራ ሆኖ ባውራ ፓርቲ ስም እገዛውንም፣ የትምህርት እድሉንም፣ ስልጣኑንም፣ ኢንቨስትመንቱንም፣ ንግዱንም፣ ሙስናውንም፣ የመንግስትም ሆነ መንግሳታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንም፣ እድሩንም፣ ፎረሙንም፣ ማህበሩንም፣ እቁቡንም ጠቅልሎ ይዞ ያሻውን እያደረገ ቀጥሏል።

የወያኔ ህግ አልበኝነትና ሃይ ባይ ማጣት በመተካካት ሰበብ በሚፈጸም ህግወጥነት እና ቅድሚያ ለተጎዱ አካባቢዎች በሚል የሃብት ሽግግር ብቻ የሚቆም አልሆነም። ይህን ሁሉ ካደረገና ሁሉንም ነገር ዝብርቅርቁን ካወጣም በሗላ ቢሆን ሀገሪቱን የሚመራት ማን መሆኑ ለመለየት እስከሚቸግር ድረስ የሟቹ የጎጠኛው መለስ ዜናዊ የተለያዩ ፎቶ ግራፎች የሀገሪቱን ህንጻዎች እስከ ዛሬም ድረስ ሸፍነው መታየታቸውና ስሙም ለሀገሩም ሆነ ለሕዝቡ መልካም እንዳደረገ መሪ በወያኔ ጋዜጦች፣ ራዲዮዎችና ቴሌቪዥኖች ክህዝባችን ህሊና እንዳይጠፋ ይመስላል ጠዋት ማታ እንደ ፈረንጅ ቅመም በየዜናው አላግባብ እየተደነጎረ ከመገኘቱም በተጨማሪ፤ የባስ ብሎ የወያኔ ቃል አቀባይ አንባሳደር ዲና ሙፍቲ ከቪኦኤ የእንግሊዝኛው ክፍል ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ”በፓርላማ የመለስ መቀመጫ ቦታ ክፍት ነው ለምንድን ነው” ተብሎ ለተጠየቀው ጥጣቄ ሲመልስ ”ለባራዕዩ መሪያችን ክብር ለመስጠት ነው” ማለቱ ዘላለማዊ መሪ ተብለው በልጃቸውና በልጅ ልጃቸው ዘመን ሰይቀር ሰሜን ኮሪያን እየመሩ እንደሚገኙት የሰሜን ኮሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኪም ኢል ሱንግ እኛስ አገር ”ለባለ ራዕዩ መሪ ክብር ለመስጠት” በሚል ስበብ አሁንም ሀገራችን በሙት እየተመራች ስላለመሆኗ ምን ማረጋገጫ አለ። መቼም ሃይለማሪም ደሳለኝስ የት ሄደና ብላችሁ ስድስት ወር እንዳታስቁኝ።

ይህን ሁሉ ጉድና መከራ፣ ስቃይና ግፍ፣ ህግ አልበኝነትና የወያኔን ሁሉ የኔና በኔ ባይነትን ተሸክሞ እየተጓዘ ያለው የሀገራችን ሕዝብ በቃኝ ብሎ በመነሳት በወያኔ የግፍና የከፋፍለህ ግዛ አገዛዝ ላይ ማሳየት የጀመረውን በብሔርም ሆነ በሃይማኖት አነድነትን የማጠናከርና ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር እያደረገ ያለውንም ሁሉን አቀፍ ትብብር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀጠልና ወያኔን የማስወገድ ብቃቱን ለዓለም የበለጠ አጠናክሮ በማሳየት ከሌሎች አህጉር አቀፍም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ሆነ ሀገሮች እገዛን ሊያገኝ ይችላል። ከዚህ ውጭ ግን ”ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም” እንደሚባለው እጅን አጣጥፎ በመቀመጥ ለራስ ችግርና መከራ ዓለም አቀፍ እገዛንም ሆነ መለኮታዊ መፍትሄን መጠበቅ የሕዝባችንን ስቃይ የበለጠ ከማስፋቱም በላይ ሀገራችንንም ከዓለም ካርታ ላይ ሊያስፍቃት ይችላል። ስለዚህም የህን ትሪካዊ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ጊዜው ዛሬ ነው፤ አሁን።

EPRP: Save Ethiopian Refugees in Norway!! Now!! (Ethiopia)

Dec 2, 2012

ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ ቀርቦበት የነበረው ክስ እንደገነ ተቀሰቀሰ፤


የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ እንደገና ተቀሰቀሰ

ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ ቀርቦበት የነበረው ክስ እንደገነ ተቀሰቀሰ፤

ትላንት ሃሙስ ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ወደ ጋዜጣው ቢሮ የፍርድ ቤት መጥሪያ ይዘው የመጡት የፖሊስ አባላት ጋዜጠኛ ተመስገን ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑ ተነግሯቸው ተመልሰዋል ።

ዓርብ ህዳር 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰሃት በኋላ የፌዴራል ፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ተኛ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን በሌለበት ችሎት የሰየመ ሲሆን የፍርድ ቤት መጥሪያ ለጋዜጠኛው ሊያደርሱ የሄዱት ፖሊሶች በጊዜው ሊያገኙት አለመቻላቸውንና ለሥራ ባልደረቦቹ ግን መንገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የዋስትና መብት የነፈጉት ዳኛ መጥሪያው እንዳልደረሰው ካረጋገጡ በኋላ ዐቃቤ- ሕግን የውሳኔ አስተያየት የጠየቁ ሲሆን ዐቃቤ- ሕግ በበኩሉ በቀጣይ እንዲቀርቡልኝ ማዘዣ ይጣፍልኝና አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል፡፡

የችሎቱ ዳኛ በበኩላቸው የፍርድ ቤት መጥሪያ ለፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እና ለድርጅቱ ጠበቃ እንዲደርስ ማዘዣ እንዲወጣ አዘው ቀጣይ ቀጠሮውንም ለታህሳስ 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጊዜ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከጤናው ጋር በተያያዘ ወደ አዋሳ መጓዙን ተከትሎ መጥሪያ እንደደረሰው ለኢሳት ገልጿል።

የፕሬስ አፈናው በአቶ ሀይለማርያም የስልጣን ዘመንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአዲስ ታይምስ መጽሄት ላይ ሲሰራ የገጠመውን ችግር በመዘርዝር ገልጿል

ተመስገን ፍትህ ጋዜጣን ሲያሳትም በነበረበት ወቅት ከ39 ባላነሱ እንያንዳንዳቸው ከ106 በላይ ዝርዝር ክሶችን በያዙ ወንጀሎች መከሰሱ ይታወቃል።

ከታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር በፕሬስና በወቅታዊ የአገራች ፖለቲካ ዙሪያ ያደረግነውን ቃለምልልስ ከዜናው በሁዋላ በትኩረት ክፍለ ጊዜ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ኢሳት ዜና:-የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ77 ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ፍቅሩ አያና ከምክር ቤት አባላቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም፣ ከፍተኛ አመራሮች ስለፈለጉዋቸው ብቻ እንዲሾሙ መደረጉን የኦህዴድ ምንጮች ገልጸዋል።


ከፍተኛ ሙስና ፈጽመዋል የተባሉት ግለሰብ የኦሮምያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ


ኢሳት ዜና:-የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ77 ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ፍቅሩ አያና ከምክር ቤት አባላቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም፣ ከፍተኛ አመራሮች ስለፈለጉዋቸው ብቻ እንዲሾሙ መደረጉን የኦህዴድ ምንጮች ገልጸዋል።

የምክር ቤት አባላት በአቶ ፍቅሩ ላይ ካቀረቡዋቸው የመቃወሚያ ሀሳቦች መካከል ግለሰቡ በሙስና የተዘፈቁ ናቸው፣ በዞናቸው ዳኛ ሆነው በሰሩበት ወቅት በህዝብ የተጠሉና ህዝብን ያንገላቱ ናቸው፣ የስነምግባር ችግር አለባቸው፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም የሚሉት ይገኙበታል። የክልሉ ባለስልጣናት ከምክር ቤት አባላት ለቀረበባቸው ተቃውሞ አጣርተን መልስ እንሰጣለን የሚል ድፍንፍን ያለመልስ በመስጠት ሹመቱ እንዲጸድቅ አድርገዋል።

የምክር ቤት አባላቱ በባለስልጣኑ አሰራር ላይ ነቀፌታ ሲያቀርቡ እንደነበር ታውቋል።

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን ጨምሮ የስራ አስፈጻሚዎች የስልጣን ሹም ሽር ይኖራል የሚል አጀንዳ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ አጀንዳው እንዲሰረዝ ተድርጓል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አቶ አለማየሁን ለመተካት ሀሳብ ቢቀርብም በሚተካው ሰው ላይ የስራ አስፈጻሚዎች ለመስማማት ባለመቻላቸው እንዲቀር ተድርጓል። አንዳንድ የስራ አስፈጻሚ አባላት ስብሰባ ረግጠው እስከመውጣት መድረሳቸውን ለማወቅተ ችሎአል።

በሰሞኑ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ አርብ እለት ከተገኙት ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ከአቶ አብዱላዚዝ በስተቀር ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በማጠቃለያው ጉባኤ ላይ አልተገኙም።

ሰሞኑን ለአቶ ሙክታር ከድር የተሰጠው የምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትርነት ቦታ በተወሰነ መጠን በምክር ቤቱ ውስጥ ይነሳል ተብሎ የተጠበቀውን ተቃውሞ ማብረዱ ታውቋል።

በሌላ ዜና ደግሞ አዳማ 5ኛውን ከንቲባ ሾማለች። ከሙስና ጋር በተያያዘ ከህዝብ በቀረበ ተቃውሞ ከስልጣን እንዲባረሩ በተደረጉት የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ በአቶ ጉታ ላንጮሬ በአቶ ባካር ሻሌ ተተክተዋል። አቶ ባካር ሻሌ አቶ በረከት የሚመሩት የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ምክት ሃላፊ የነበሩ ናቸው።

አንዳንድ ወገኖች ግለሰቡ በእርግጥም ከሙስናና ከአስተዳደር ብቃት ጋር በተያያዘ በከተማው ህዝብ ዘንድ ተቃውሞ ተነስቶባቸው የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ከስልጣናን የተባረሩት ግን ምናልባትም በኦህዴድ ውስጥ ከተፈጠረውን ችግር ጋር ተያይዞ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ።

ኢሳት የከንቲባውንና የከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊውን ከስልጣን መባረር መዘገቡ ይታወሳል።

ESAT Yehud weg” – December 2012 (እሁድ ወግ)

Raw Video Footage: Government brutality in Ethiopia

Raw Video Footage: Government brutality in Ethiopia (መታወቅ ያለበት ጭካኔ)

Dec 1, 2012

በአገር የምትመሰለዏን ትልቅ ክብር ያላትን ውዶዋን ሴትን በዚህ መልኩ ያሰቃያሉ እህቶቻችን በፌደራል ታፍነው ሲወሰዱ

እህቶቻችን በፌደራል ታፍነው ሲወሰዱ

እንደው እስከ መች ነው እንደዚ እያየን ዝም የምንለው በዚህ በኩል አገራችን ለማች አደገች ይላሉ በሌላ በኩል ደግሞ ይኧው እንደምናየው በአገር የምትመሰለዏን ትልቅ ክብር ያላትን ውዶዋን ሴትን በዚህ መልኩ ያሰቃያሉ ። እንደው ከምን ይሆን የተፈጠሩት ከሴት ወይስ ? ምነው እነሱን እንኩዏን ቢተዋቸው ለራሳቸው በአረብ አገር  ላይ የሚደርሰው ሰብዓዊ መብት ረገጣ የነጻነት እጦት ሌላው ይቅርና የአለም ደቻሳ እንባን በደንብ  ሳያብሱ ዛሬ ደግሞ አፍነው ይወስዱዋቸዋል ። ለነገሩ ለካስ እነዚህ ሰዎች የተፈጠሩት ከሴት አደለም
                                                                                                                                  ከያሬድ ኤልያስ

ኢሳት ዜና:-በሩዋንዳ ተቋቁሞ በነበረው የተበባሩት መንግስታት ድርጅት አለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቢ ህግ በመሆን ያገለገሉት እና በህግ የማስተማር ሙያ ላይ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጡት ዶ/ር ያቆብ ሀይለማርያም ለኢሳት እንደተናገሩት የሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም። ዶ/ር ያቆብ ” የህገመንግስቱ አንቀጽ 75 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተክቶ እንደሚሰራ ይደነግጋል እንጅ ከሁለት ወይም ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች መካከል ተመርጦ አንዱ ይተካቸዋል አይልም” ብለዋል


የሁለቱ ም/ጠቅላይ ሚኒሰትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ ታዋቂ የህግ ባለሙያ ገለጹ


ኢሳት ዜና:-በሩዋንዳ ተቋቁሞ በነበረው የተበባሩት መንግስታት ድርጅት አለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቢ ህግ በመሆን ያገለገሉት እና በህግ የማስተማር ሙያ ላይ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጡት ዶ/ር ያቆብ ሀይለማርያም ለኢሳት እንደተናገሩት የሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም። ዶ/ር ያቆብ ” የህገመንግስቱ አንቀጽ 75 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተክቶ እንደሚሰራ ይደነግጋል  እንጅ ከሁለት ወይም ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች መካከል ተመርጦ አንዱ ይተካቸዋል አይልም” ብለዋል
ዶ/ር ያቆብ ሹመቱ ከመሰጠቱ በፊት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በጋራ  ተስማምተው ህጉን ማሻሻል ይችሉ እንደነበር ገልጸዋል።
ምናልባት ሌሎች ያልታዩ የህግ ድንጋጌዎች በመኖራቸው በነዚያ ድንጋጌዎች መሰረት የተደረገ ሹመት ሊሆን አይችሉም ወይ ተብለው ለተጠየቁት ዶ/ር ያቆም ፣ ምንም የሚያሻማ ነገር ነገር የለም በማለት መልሰዋል
ኢህአዴግ ስለ ህገመንግስት  መታስ በተደጋጋሚ ይናገራል፣ በዚህ ድንጋጌ ላይ ህገመንግስቱ በግልጽ እንደተጣሰ ተናግረዋል፣ ኢህአዴግ እሞትለታለሁ የሚለውን ህገመንግስት ለምን በአደባባይ ለመጣስ የፈለገ የመስልዎታል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ ዶ/ር ያቆም ኢህአዴግን በመሰረቱ 4 ድርጅቶች መካከል ያለውን የስልጣን ሽኩቻ ለማብረድ ታስቦ ሊሆን ይችላል ብለዋል
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የህወሀቱን ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልንና የኦህዴዱን አቶ ሙክታር ከድርን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ መሾማቸው ይታወሳል።

ኢሳት ዜና:-የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ሰላማዊ ተቃውሞ በመምራታቸው በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የአመራር አባላት ዛሬ ልደታ በሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ለህዳር 27 ቀን 2005 ዓም የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።


የድምጻችን ይሰማ የኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ


ኢሳት ዜና:-የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ሰላማዊ ተቃውሞ በመምራታቸው በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የአመራር አባላት ዛሬ ልደታ በሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ለህዳር 27 ቀን 2005 ዓም የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።
የኮሚቴ አባላት ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጋ ለኢሳት እንደገለጡት የዛሬው ችሎት አቃቢ ህግ በጠበቆች በኩል ለቀረበው መቃወሚያ መልስ ለመስጠት  ተብሎ የተቀጠረ ነበር። አቃቢ ህግ መልሱን በንግግር ለፍርድ ቤት ማቅረቡን የገለጡት አቶ ተማም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን መከራከሪያ ሰምቶ ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ቃላቸውን ይስጡ አይስጡ በሚለው ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ የፊታችን ሀሙስ መቀጠራቸውን ተናግረዋል።
አቶ ተማም እንዳሉት ፍርድ ቤቱ በመጪው ሀሙስ ክሱ እንዲቀጥል፣ እንዲሻሻል፣ ወይም ውድቅ እንዲሆን ብይን ይሰጣል።
ጠበቆች ባለፈው ሳምንት ባቀረቡት መቃወሚያ በአቃቢ ህግ የቀረበው ክስ ህገመንግስቱን የጣሰና በርካታ የህግ እጸጾች ያሉበት ነው በማለት መገልጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኮሚቴ አባላቱ ድጋፋቸውን ለመስጠት ወደ ልደታ ያቀኑ ሙስሊሞች በፖሊሶች መባረራቸውን አንዳንዶችም በፖሊስ መኪኖች ተጭነው መወሰዳቸው ታውቋል።
ጉዳዩን በማስመልከት በአካባቢው የነበሩ የተለያዩ የእስልምና እምነት ተከታዮችን አነጋግረን እንደተረዳነው ፖሊሶች እናቶችን ብቻ በመለየት እየደበደቡ ወደ እስር ቤት ውሰደዋቸዋል
ሌላ ሙስሊም  በበኩሉ ” ወንዶችን ቢደበድቡ የተለመደ ነው፣ እናቶችንና እህቶቻችንን መደብደባቸው ግን ሊወጥልን አልቻለም” ብሎአል
የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ጊዜ መንግስት፣ ኮሚቴ አመራሩን የሚያወግዙ ሰልፎችን በተለያዩ ከተሞች እያዘጋጀ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
በኦሮሚያ ክልል አዳማን ጨምሮ በተለያዩ ዋና ዋነ ከተሞች ለማዘጋጀት የኮሚቴ አባላት መዋቀራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

TPLF Split 1993 E.C. - Historical Video [Mast Watch]

Nov 29, 2012



ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የ816 ሚሊዮን ብር የልማት ድጋፍ አገኘች


ኢሳት ዜና:-የድጋፍ ስምምነቱን የፈረሙት  የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሱፊያን አህመድና የአውሮፓ ኅብረት የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተርና የአፍሪካ ካሪቢያን ፓስፊክ አስተባባሪ ፍራንሲስካ ሞስካ ናቸው።
ድጋፉ የወጪ ምርቶችና በተመረጡ ኢንቨስትመንት መስኮች  በቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣ ጨርቃጨርቅ ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያና መድኃኒት ፋብሪካዎችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ፣ በልምድና ክህሎት እንዲሁም የገበያ ልማትን በማጠናከር ተወዳዳሪነታቸውን ለማጠናከር እንዲሁም  በቢዝነስ ፣በሥራ አመራርና በፈጠራ ሥራ ለግሉ ዘርፍና ለመንግሥት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ-አውሮፓ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ለመክፈት ይውላል ተብሎአል።

ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።


በአየር መንገድ ውስጥ በጉልበት ስራ ላይ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች በኢህዴግ ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ሊተኩ ነው


ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።
ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ ያዘኑ ሰራተኞች እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም በሚል ከስራ መባረራቸው ህገመንግስቱን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን ሳንወድ በግድ ለእንጀራ ብለን ኢህአዴግን እንድንደግፍ የሚያደርግ ነው።
ኢህአዴግ በቀጣዩ የወረዳና የከተማ ምርጫ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ያስችለው ዘንድ የወጣት ፎረም አባላትን በጊዜያዊ ስራ እየሸነገለ ነው በማለት ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ወቀሳ ያቀርባሉ።
በተያያዘ ዜናም ኢህአዴግ አንዳንድ አባላቱን ከድርጅት አባልነት ያስወጣ በማስመሰል በወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስመራጮች አድርጎ ሊያሾም መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
በይፋ የማይታወቁ የድርጅቱ አባላት በገለልተኛ ስም በምርጫ አስፈጻሚነት ለማወዳደርና ለማሰራት መታቀዱን ነው ለማወቅ የተቻለው።

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ የሀርቡ አካባቢ ሙስሊም ነዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የቀረበላቸውን የሰልፍ ጥሪ ባለመቀበል አንወጣም ማለታቸው ተገለጸ። ባለስልጣናቱ ተማሪዎቹን ከትምህርት ቤት በማስወጣት ሰልፍ እንዲያደርጉ ማድረጋቸውም ተዘግቧል።


በመንግስት በተጠራ ሰልፍ የሀርቡ ህዝብ ሳይገኝ ቀረ


ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ የሀርቡ አካባቢ ሙስሊም ነዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የቀረበላቸውን የሰልፍ ጥሪ ባለመቀበል አንወጣም ማለታቸው ተገለጸ።
ባለስልጣናቱ ተማሪዎቹን ከትምህርት ቤት በማስወጣት ሰልፍ እንዲያደርጉ ማድረጋቸውም ተዘግቧል።
በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የቀረበው የሰልፍ ጥሪ ያልተገኘ ነዋሪ 50 ብር እንደሚቀጣ ቢገለጽም ህዝቡ ለማስጠንቀቂያው ቦታ ባለመስጠት በሰልፉ ሳይገኝ ቀርቷል።
ከሬዲዮ ቢላል ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው የፌደራል ፖሊሶችና ያካባቢው ባለስልጣናት በየቤቱ እየዞሩ ለሰልፍ ውጡ በማለት ሲያስገድዱ የነበረ ቢኋንም አብዛኛው ሙስሊም አሻፈረኝ ሲል እምቢ ብሎል።
የሰልፉ አላማ በግልጽ አልተገለጸም ያለው የሬዲዮ ቢላል ዘገባ ሙስሊም ያልሆኒ የአካባቢው ባለስልጣናት ከትምህርት ቤት ይዘዋቸው ለሄዱት ህጻናት ሰልፈኞች አሸባሪነትን እንቃወማለን ፣ አካባቢያችን ሀርቡ ሰላም ናት የሚል መፈክሮችን እያሰሙ እንዲቀበሏቸው ሲሞክሩ እንደነበር ገልጾል።
በቀጥታ ከትምህርት ቤት ወደ ሰልፍ እንዲወጡ የተደረጉት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት.ቤት ተማሪዎች አብዛኞቹ በገዢው ፓርቲ አባላት ሰዎች የሚነገረውን መፈክር ተቀብለው እንዳላስተጋቡም ከዘገባው መረዳት ተችሎል።
በሰልፉ ላይ የአካባቢው መኪኖች ሰልፉን እንዲያጅቡ ታዘው እንደነበር ያመለከተው ዘገባ አናደርገውም ብለው ሳይገኙ መቅረታቸውን ገልጾል።

ሞረሽ ወገኔ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት የማፍረስ እቅድ ተቃወመ


ኢሳት ዜና:-ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትን ለማፍረስ መንግስት ማቀዱ የአማራው ታሪክን ለማጥፋት የተያያዘው እርምጃ አካል በመሆኑ እናወግዘዋለን ሲል አስታወቀ።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንን የመንግስት እቅድ በመቃወም ድምጹን እንዲያሰማ ሞረሽ ወገኔ ጥሪ አቅርቧል።
ሞረሽ ወገኔ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የአማራው ህዝብ ላይ የማጽዳት እርምጃ ሲወስድ የቆየው ገዥው ፓርቲ ታሪኩንም ሲያጠፋ ቆይቷል ካለ በኋላ የአባቷቻችን የክብር አጽም ያረፈበትን ቦታ አፈረሰ፣ የዋልድባ ገዳምን አረሰ፣ የዝቋላ አቦን አቃጠለ ሲል በአብነት ዘርዝሮል በመግለጫው።
የአማራ ህዝብና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርገው ታሪክና ቅርስ የማጥፋት እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሎል ያለው ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የአቡና ጴጥሮስ ሀውልት ሳይፈርስ በአንድነት ተነስቶ ቁጣውንና አሻፈረኝ ባይነቱን ሊያሳይ ይገባል በማለት በመግለጫው አሳስቧል።
ድርጊቱን ለኢትዮጵያ ታሪክና አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ ጽኑ አላማ ያላቸው ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው የአቡኑን ሀውልት ለማፍረስ የታቀደውን እቅድ እንዲቃወሙ ጥሪውን አስተላልፏል።

ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።


በአየር መንገድ ውስጥ በጉልበት ስራ ላይ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች በኢህዴግ ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ሊተኩ ነው


ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።
ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ ያዘኑ ሰራተኞች እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም በሚል ከስራ መባረራቸው ህገመንግስቱን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን ሳንወድ በግድ ለእንጀራ ብለን ኢህአዴግን እንድንደግፍ የሚያደርግ ነው።
ኢህአዴግ በቀጣዩ የወረዳና የከተማ ምርጫ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ያስችለው ዘንድ የወጣት ፎረም አባላትን በጊዜያዊ ስራ እየሸነገለ ነው በማለት ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ወቀሳ ያቀርባሉ።
በተያያዘ ዜናም ኢህአዴግ አንዳንድ አባላቱን ከድርጅት አባልነት ያስወጣ በማስመሰል በወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስመራጮች አድርጎ ሊያሾም መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
በይፋ የማይታወቁ የድርጅቱ አባላት በገለልተኛ ስም በምርጫ አስፈጻሚነት ለማወዳደርና ለማሰራት መታቀዱን ነው ለማወቅ የተቻለው።

ጥንቃቄ


ይህ ነው ወንድማማችነት ምንም ቢሆን ክርስትያን ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችህ ከጎናችሁ ነን ምናልባት ነገ የመጀመሪያ ተግባሮቻችን እንጀምራለን ሁላችንም ሙስልም ወንድሞቻችን እን እህቶቻችን በፀሎት እናስባቸው ለሁሉም እንደሚፀለይ ፈጣሪ በቅዱስ ቃሉ ያዛልና

Photo: ጥንቃቄ

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!


አቶ ሃይለማም ሲፈሩሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸውመካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።
አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።
እኛ ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን ገልፀናል።
የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?
ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል)  እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!
ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!

ESAT DC Daily News November 28 2012

Nov 27, 2012

በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ


በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ
(ከእየሩሳሌም አርአያ)
በትግራይ ተምቤን - አቢይ አዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ
የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን
ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።
በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ
ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ
መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች
ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው
ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን
ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ
ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።
ከምረቃው ጋር በተያያዘ የራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰርዞ “መለስ ዜናዊ ሁለተኛ ደረጃ
ት/ቤት” ተብሎ መሰየሙን ባለስልጣናቱ በይፋ እንደገለጹ ምንጮች አረጋግጠዋል። በት/ቤቱ
በይፋ የመለስ ስም ተፅፎ መለጠፉ ተጠቁሞዋል። በህዝብ ገንዘብ መዋጮ የተገነባን ት/ቤት
በጡንቻና በማን አለብኝነት ህዝብን በመናቅ የተፈጸመ ተግባር ነው ሲሉ የአካባቢው
ተወላጆች ማውገዛቸው ታውቁዋል።
በተለይ በአውስትራሊያ፡ ጀርመን፡ ኖርዌይ፡ አሜሪካ፡ ካናዳና… ሌሎች አገራት የሚኖሩ
የአካባቢው ተወላጆች ባካሄዱት ቴሌ ኮንፈረንስ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። ተሳታፊዎቹ እንዳሉት « የአፄ
ምንሊክን፡ የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ለማፍረስ የተጀመረው አፍራሽ እንቅስቃሴ ወደ ራስ አሉላ ተሻግሮዋል። ይህ
የሚያመለክተው የቆየውን የኢትዮጲያን ታሪክ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን ነው። ይህ ትውልድ ታሪኩን አስጠብቆ የማቆየትና
የተጀመረው አደገኛ አፍራሽ እንቅስቃሴ ከማውገዝ ባለፈ ለትግል መነሳሳት አለበት።ኢትዮጲያዊያን እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፤»
ብለዋል። አክለውም « የኢትዮጲያዊነት ጉልህ መታወቂያና መገለጫ የሆኑ አኩሪ ታሪኰችንና ታሪክ ሰሪ ጀግኖችን ለማጥፋት ኤርትራዊው
ቴውድሮስ ሃጎስ፡ በረከት ስሞንና ስብሃት ነጋ የሚመሩት አካል በአገራችን ላይ የጥፋት ዘመቻ ከፍተዋል» ሲሉ አንድ ተሳታፊ ተናግረዋል።
« የዶጋሊ ዘመቻ » በሚል በየአመቱ ራስ አሉላ የሚዘከሩበት ታሪካዊ ቀን እንደነበረና ሕወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በሑዋላ ግን ይህ
እንዲቀር መደረጉን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ።
በሌላም በኩል በመቀሌ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የአፄ ዮሃንስን መታሰቢያ ሃውልት ለማቆም ተጀምሮ የነበረው እንቀስቃሴ እንዲቆም
መደረጉን የቅርብ ምንጮች አጋልጠዋል። ባለፈው አመት ከህዝብ በተዋጣ ገንዘብ ሓውልቱን ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ እንደነበር
ጠቁመው፤ በኋላ ግን “የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ስለተቃወሙ ሃውልቱን መስራት አይቻልም» በማለት እነ ቴውድሮስ ሃጎስ
መወሰናቸውን ምንጮቹ ገልፀው፦ “አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ተራ ምክንያት» ሲሉ ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች
አጣጥለውታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአድዋ ከተማ አደባባይ ላይ ተሰቅሎ የነበረ የመለስ ፖስተር ተቀዳዶ መጣሉን ምንጮች ጠቆሙ። የክልሉ ካድሬዎች
«የመድረክ ተለጣፊ የሆነው አረና ፓርቲ ነው ይህን የፈፀመው » በማለት ያልተጨበጠ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩና እየዛቱ ነው ያሉት
ምንጮች አክለውም ድርጊቱን የፈፀመው የአካባቢው ህዝብ እንጂ የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ አይደለም ብለዋል።

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ (ስደተኛው መስፍን ነጋሽ፤ ከአገረ ስዊድን) ላለፉት ሰባት ወራት በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ምህዳር (public sphere) ሳይበርዱ ከሰነበቱት ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ እና መንግሥት ለጥያቄው የሰጠው ትርጉምና ምላሽ ይገኝበታል። ነገሩ ሰሞኑን ተካሮ ሰንብቷል። የመነጋገሪያ አጀንዳነቱም እንዲሁ በጣም ጨምሯል። በዚህ ንግግር ውስጥ በስሕተትም በእቅድም እየተምታቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መኖራቸውን ብዙዎች ያስተውሉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሆኖም ጉዳዮቹን ነቅሶ ማውጣቱ ለውይይት ብቻ ሳይሆን አቋምን ለመፈተሽም ይረዳል በሚል እምነት ነገሩን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ። ነገሩ ብዙ ጉዳዮችን የሚያሰናስል እንደመሆኑ ቁዘማዬም (reflection) ጥቂት ረዝሞ ልታገኙት ትችላላችሁ። ትእግስታችሁን እማጸናለሁ። በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በሁለት ምክንያቶች በሌላውም ኢትዮጵያዊ መደገፍ አለባቸው እላለሁ። ሕጋዊ ጥያቄዎቹ ”ከአክራሪነት/ሽብርተኝነት” ጋራ ተደባልቀውና ተምታተው እየቀረቡ ችላ መባልም ሆነ መረገጥ አይገባቸውም ስል እከራከራለሁ። I am at Awelia because injustice is there!

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ | Addis Neger

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ | Addis Neger

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ | Addis Neger

Total Pageviews

Translate