Pages

Jan 30, 2013

የሙስሊም መሪዎች የችሎት ውሎ አስቂኝ ነው ተባለ


ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በዝግ ችሎት በሚካሄደው የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ 190 ምስክሮች እንደሚቀርቡ አቃቢ ህግ ቢያስታውቅም እስካሁን የቀረቡት  ምስክሮች  11 ናቸው። ምስክሮችን የመስማት ሂደቱ በ10 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ በአሁኑ አካሄድ  አቃቢ ህግ የምስክሮችን ቁጥር ካልቀነሰ በስተቀር በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ላይጠናቀቅ ይችላል።ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

የውስጥ ምንጮች እንደገለጡት አቃቢ ህግ ምስክሮችን  ሲያቀርብ የአባታቸውን ስም ብቻ በመጠቀም ነው። ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጋ ምስክሮቹ የመኖሪያ አድራሻቸው ፣ ስራቸውና ማንነታቸው እንዲገለጥ ለዳኞቹ ቢያመለክቱም፣ ዳኞቹ “የምስክሮችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ምስክሮቹ አድራሻቸውንም ሆነ ስራቸውን እንዲገልጡ አይገደዱም” የሚል ምክንያት በመስጠት ጥያቄውን አልተቀበሉትም።
አቶ ተማም ” በህገመንግስቱ አንቀጽ 20 መሰረት አንድ ጉዳይ በዝግ ችሎት ሊታይ የሚገባው አገር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆን ብቻ ነው በማለት ” ቢከራከሩም  ዳኞቹ ” የምስክሮች ድህንነትም የአገር ደህንነት ነው” በማለት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸውን ምንጫችን ገልጸዋል።
ጠበቃ ተማም ” በ1997 ዓም በቅንጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ሂደት ላይ  እንደተደረገው የተከሳሾች ቤተሰቦች እና ዘመዶች  ባይቀርቡ እንኳን ቢያንስ የውጭ እና የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የውጭ ዲፕሎማቶች እንዲገኙ ችሎቱ ፈቃድ ይስጥ በማለት ቢጠይቁም” ዳኞቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ክርክሩ ያለታዛቢ እንዲቀጥል ሆኗል።
ምስክሮቹ ተከሳሾች በአደባባይ የተናገሩትን ከመድገም ውጭ እስካሁን አንድም አዲስ ነገር አለመናገራቸው ታውቋል። ምስክሮቹ የተመሰከረባቸውን ተከሳሾች ጠቁሙ ሲባሉ ሌሎችን ሰዎች እንደሚጠቁሙ፣ እስረኞችም በምስክሮች ድርጊትና በፍርድ ቤቱ ሂደቱ ድራማ እየተዝናኑ መሆኑ ታውቋል።
አጠቃላይ የፍርድ ሂደቱ የተበላሸ ኧንደሆነ የተረዳው መንግስት፧ ከውርደት ለመዳን በሚል  የፍርድ ሂደቱን በዝግ ችሎት እንዲካሄድ ማድረጉን አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ህግ ባለሙያ ተናግረዋል።

Jan 26, 2013

ብስጭት በጨዋታ “…ቡርኪናፋሶ አበዛብኝ ለቅሶ!”



እንደምን አደራችሁ ብስጭት እናስነብባለን በመጀመሪያም አርዕስተ ብስጭት።
በትላንትናው ዕለት ብሄራዊ ቡድናችን ላይ በደረሰበት መጠነ ሰፊ ጥቃት በርካቶች መበሳጨታቸው ተሰማ።


በቅድሚያ፤

ብሄራዊ ቡድናችን፤ በደቡብ አፍሪካ ያለ ኮከብ በሚያበራው የኢትዮጵያ ባንዲራ፤ በባለ አንበሳው ሞአንበሳ ባንዲራ በባለኮከቡ የፌደራሉ ባንዲራ እንዲሁም በባለ ዋርካው የኦነግ ባንዲራ ምን እርሱ ብቻ በባለ ቀንበጡ የኤርትራ ባንዲራ ሁሉ ሲደገፍ ተመልክተን እማማ ኢትዮጵያ ብዙ ልጆች እንዳሏት አየን ደስም አለን!

የብስጭቱ ዝርዝር ቀጥሎ ይቀርባል፤

ጨዋታው እንደተጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ቁጭ ብድግ የሚያሰኝ ማራኪ ጨዋታዎችን አድርጎ የነበረው ብሄራዊ ቡድናችን በሽመልስ አማካይነት የተሞከረችው የጎል አጋጣሚ ለጥቂት በጣም ለጥቂት በግቡ ቋሚ አማካይነት መከነች። እንዴት ነው ነገሩ የግቡ ቋሚ የቡርኪናፋሶ ረዳት በረኛ ነው እንዴ ብለን በጣም ተበሳጨን! እርርር..ም አልን።

እያለ እያለ አንድ ጎል ገባብን አንድ የቡርኪናፋሶ ተጫዋች ኦፍሳይት ክልል ውስጥ ነበር። ምናልባት እርሱ አዘናግቷቸው ይሆን…? ብለን አሁንም ተበሳጨን። ትንሽ ቆይቶ አሉን ከምንላቸው ተጨዋቾች ውስጥ አዳነ ግርማ ከአንዱ የቡርኪናፋሶ ተጫዋች ጋር ተጋጭቶ ሲወድቅ አየነው። ሲገጭ ያየነው እግሩ አካባቢ ነው። አዳነ ግን የያዘው ብሽሽቱን ነበር። እንዴት ነው ነገሩ ሰዎቹ እግር ገጭተው ብሽሽት የሚያሳምሙት…? የአዴ ስልት ነው… ወይስ ህመም በእግር “ሜሴጅ” ያደርጋሉ። ብለን እየተጨነቅን ሳለ አዴ ህመሙ በረታበትና ከሜዳ ወጣ። ኤርሚ እንደዘገበልን፤ አዳነ የታመመው እግሩን ከተገቢው በላይ ከፍ በማድረጉ አማካይነት የሚመጣ የጡንቻ መሳሳብ ነው። ይህ ህመም ለሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሜዳ ያርቃል። ተበሳጨን አይገልፀውም፤ “ኦ…. ብስጭት ሆይ እንዲህ ደጋግመሽ የምትጎበኝን አንቺ የቤተሰባችን አባል ነሽን!?” አልን።

ከዛ በኋላማ አዳነ አለቀሰ ተመልካቹ አለቀሰ ጎሉም አልቀነሰ። እየወሰዱ ብቻ ጎል…! አረ የከልካይ ያለ። አረ የተከላካይ ያለ! ያ “አጭበርባሪ” በረኛቸው በቀይ ሲወጣ “ችርስ” ብለን እጃችንን አጋጭተን የነበርን ሁላ ዝም ብሎ ብቻ ጎል ሲቆጠርብን፤ መቁጠሩ ደከመንና “የወጣው በረኛ የእኛ ነው እንዴ!” ብለን አሁንም ተበሳጨን ተበሳጨን ተበሳጨን።

እንሆ ብዙ ተስፋ ያደረግነው ጨዋታ አራት ለምንም በሆነ በጣም የሚያበሳጭ ውጤት ተደመደመ። ያለቀሰ ሰውም በረከተ። የግጥም አዚምም ይህንን አስባለን

“ያሳለፍኩት ጊዜ

መጣ ተመልሶ

ጋሸ ቡርኪናፋሶ

አበዛብኝ ለቅሶ”

በመጨረሻም ተስፋ

ማክሰኞ ለጥር ማሪያም ዕለት 2005 በሚደርገው ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ነፍሴ ዛምቢያን ቢያሸንፍልን እና እኛ ደግሞ ናይጄሪያን ብናሸንፍ ወርቅ አድርገን እናልፋለን። ዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ አቻ ቢወጡ እና አሁንም እኛ ናይጄሪያን ብናሸንፍ አሁንም ተንደላቀን እናልፋለን። ስለዚህ ድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ለቡርኪናፋሶ ብሄራዊ ቡድን ማለት አለብን ማለት ነው።

ብስጭታችን በዚህ ያብቃ!

Jan 24, 2013

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ክፍያ ሳይፈጽም ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ ኤል ሲ ቱ የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ክፍያ ሳይፈጽም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛንቢያ ቡድን ጋር ያደረገውን ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ::

ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት የአፍሪካ ዋንጫ የቴሌቪዥን ስርጭት ባለመብት ለሆነው ለ ኤል ሲ 2 ክፍያ ሳይፈጽም ስርጭቱን ማስተላለፉ ተመልክቶል::

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተፈጸመውና ውንብድና የተሰኘው ለስርጭቱ ባለመብት የ 18 ሚሊዮን ብር ሳይከፍል ጠልፎ በህገወጥ መንገድ ባስተላለፈው ጨዋታ ባለመብት የሆነው ድርጅት በህግ ይጠይቀው አይጠይቀው የተባለ ነገር የለም::

የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያና የዛምቢያ ጨዋታ ሲደረግ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ክፍያ ሳይፈጽም ጫወታውን በውንብድና በመውሰድ እያስተላለፈ መሆኑን ከደቡብ አፍርካ የስፓርት ተንታኞቹ እየተቹበት እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል::

ምንጮች እንዳመለከቱት የኢትዮጵያና የዛምቢያ ጨዋታ እየተካሄደ እያለ ያለክፍያ በመጥለፍ ኢቲቪ ሲያስተላልፍ የነበረው ስርጭት ሲቆረጥ በዲኤስ ቲ ቪ ጨዋታውን የሚከታተሉ ያለችግር ማየታቸውን ለመረዳት ተችሎል::

አሁን ዘግይቶ በደረሰንመረጃ መሰረት የተቀሩትን ጨዋታዎች ከባለመብቱ ድርጅት ተከራይቶ ለማሳየት የ ኢቲቪ ሰዎች እየተደራደሩ መሆኑ ተመልክቶል::

በአለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰቃየ የለም ያሉት አቶ ስብሀት ነጋ ዛሬ ያ ሁኔታ መቀየሩን ገለጡ

ኢሳት ዜና:- አንዱ ጠግቦ ሲያድር ያልጠገበው ደግሞ በሰላም ተኝቶ ያድራል ብለዋል::

አዲስ አበባ ለሚታተመው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ከቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) መሪ የነበሩትና ዛሬ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ተጽዕኖቸው እየበረታ መሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስብሀት ነጋ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ወዲህ ሚዲያ ላይ በብዛት እየቀረቡ መገኘታቸውን በዚህም ለኢሳት ጭምር ቃለ ምልልስ የሰጡበትን ሁኔታን አስታውሰዋል::

“ከመለስ መታመም ጀምሮ ሚዲያውን ለምን አበዛህው ካልሆነ በቀር እኔ ከሚዲያ አልተለየሁም ፣ ፓል ቶክ የሚባል አለ ፣ በቪ ኦ ኤም ተሳትፌለሁ፣ ለኢሳት እንኮን ቃለ ምልልስ ሰጥቻለሁ፣ ለውለውልኝ ቃለምልልስ ሰጥቻለሁ” ብለዋል::

ከአቶ መለስ ማለፍ በሆላ ተጽዕኖቸው እየበረታ ስለመምጣቱ ለተነሳላቸው ጥያቄ ማስተባበያ የሰጡት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝን ካገኞቸው ሁለት አመት እንዳለፋቸው ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን አጭር ይሁኑ ረዥም ጨርሰው እንደማያውቆቸው አብራርተዋል::

እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በአለም የተሰቃየ ህዝብ ያለ አይመስለኝም፣ ይፈጠራል፣ ራቁቱን ይሞታል፣ ከተፈለገም ይገደላል” በማለት መናገራቸውን ተከትሎ ዛሬ ይህ ቀርቶል ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ስብሀት አሁን ያመጸ ህዝብ የለም፣ ተወልዶ ወደ ውትድርና ሂድ የሚል የለም ፣ ቀይ ሽብር የለም ፣ አንድ ዩኒቨርሲቲ ነበረን አሁን 32 ዩኒቨርሲቲ አለን ፣ አንዱ ጠግቦ ያድራል ባይጠግብም ተኝቶ ያድራል በማልት ምላሽ ሰጥተዋል:፡ ዛሬ የሚያለቅሱት ወላጅ አልባ የሆኑት የአፄ ሀይለስላሴ ስርአት ናፋቂዎች ፣ ኢሰፓዎች ፣ ኢህአታ እና መኤሶኖች ናቸው ሲሉ ፈርጀዋል::

በግምቦት 1981 በኮሌኔል መንግስቱ ሀ/ማርያም ላይ በተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በሻቢያ በኩል ተባባሪነታችንን ተጠይቀው በህውሀት በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን አስታውሰዋል::

” በ1981 ግንቦት ወር በመፈንቅለ መንግስት መንግስቱ ሀ/ማሪያምን ለመገልበጥ የሞከሩት፣ ሻቢያን ላኩብን፣ ልንገለብጠው ነው ብለው ፣ መንግስቱ በግል ቢገለበጥ ባይገለበጥ ስርአቱ ካልተለወጠ ብለን ትግላችንን ቀጠልን እንጂ አላገኘናቸውም:: በማለት ሻቢያ ጭምር ለመተባበር የፈቀደውን ሂደት ህውሀት አለመቀበሉን አብራርተዋል::

አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ችሎታ ያንሳቸዋል በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ መለስም ከምክትሎቹ ከነ ተፈራ ዋልዋ፣ ከነ ዶ/ር ካሱ ኢላላ ነው ችሎታውን ያዳበረው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::

ወ/ሮ አዜብ የመለስ ፋውንዴሽንን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል

ዜና:-የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ያጸደቀውና በቢሊየን ብር የሚቆጠር ዓመታዊ በጀት ይኖረዋል ተብሎ
የሚገመተው የመለስ ፋውንዴሽንን ወ/ሮ አዜብ መስፍን በፕሬዚዳትነት ይመሩታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርበት
ያላቸው ምንጮች አመለከቱ፡፡
ባለቤታቸውን በድንገት በነሐሴ ወር 2004 አጋማሽ በሞት ካጡ በኋላ ከአራት ወራት በላይ በተመረጡበት
የፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጠው ያልታዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይኸን ሃላፊነት እንዲረከቡ የተፈለገው ከአቶ መለስ ጋር
የተያያዙ ብዙ ሥራዎች የቤተሰባቸውን ዕውቅናና ፈቃድ የሚፈልጉ በመሆናቸው ነው ተብሎአል፡፡ በዚሁ መሰረት ወ/ሮ አዜብ ፋውንዴሽኑን እንዲመሩ አስቀድሞ የማግባባት ሥራ መጀመሩን ምንጫችን አመልክቷል፡፡
በጸደቀው አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው ፋውንዴሽን ጠቅላላ ጉባዔ፣ቦርድ፣ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት
ይኖሩታል፡፡ ከ13 ተቋማት 45 ያህል የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ያሉት ሲሆን በውክልና ደረጃ ከአቶ መለስ ቤተሰብ
አራት ያህል ተወካዮች በጠቅላላ ጉባዔ ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡በተጨማሪም ከመከላከያ ሶስት፣ከገንዘብና
ኢኮኖሚ ልማት ፣ከውጪ ጉዳይ ፣ከትምህርት፣ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር መ/ቤቶች፣ከመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት፣ከቅርስ
ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ከወጣቶች እና ሴቶች ማህበራት ከእያንዳንዳቸው አንድ ከፍተኛ አመራር አባል የጠቅላላው
ጉባዔ አባላት ሲሆኑ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አምስት፣ከእያንዳንዱ ክልል አምስት ተወካዮች ይኖሩታል፡፡
በአዋጁ መሰረት የፋውንዴሽኑን ሰባት አባላት በጠቅላላ ጉባዔ ለአራት ዓመታት የሚመረጡ ሲሆን የአቶ መለስ ዜናዊ
አራት የቤተሰብ አባላት ግን በቀጥታ ያለምርጫ ቦርዱ ውስጥ እንዲገቡ አዋጁ ይፈቅዳል፡፡ ቦርዱ ደግሞ የፋውንዴሽኑን
ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መርጦ ይሾማል፡፡በዚሁ መሰረት በፋውንዴሽኑ ቦርድ ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ድምጽ
የያዘው የአቶ መለስ ቤተሰብና ወዳጆቻቸው ወ/ሮ አዜብን በፕሬዚዳንትነት ይመርጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
አራት ክፍሎችን፣ሃያ አራት አንቀጾችንና በርካታ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚደነግጉ ንዑስ አንቀጾችን የያዘውና በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ተረቅቆ ፓርላማው ያጸደቀው ይኸው አዋጅ ስለፋውንዴሽኑ ዓላማ ሲገልጽ “የፋውንዴሽኑ ዓላማ ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመናቸው ሲታገሉለት የነበሩትን የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ፣የሰዎች ዴሞክራሲያዊ ግንኙነት፣እኩልነት ክብርና ብልጽግና እንዲረጋገጥ የሰውና የተፈጥሮ ግንኙነት ሚዛናዊ እንዲሆን የሚያደርግ የህብረተሰባዊ ለውጥ አስተሳሰብ እና ሰላም ፈለግ ማስቀጠል እና
መርሆቻቸውን ማስፋፋት ይሆናል” ይላል፡፡
የፋውንዴሽኑ የገቢ ምንጮች ከውርስ ፣ከስጦታ እና ከዕርዳታ ከሚገኝ ገንዘብና ንብረት፣ከልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ
ዝግጅቶች፣ከመንግስት ከሚሰጥ ድጎማ እና ከመሳሰሉት እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ ለፋውንዴሽኑ ሥራ የሚያስፈልጉ
ዕቃዎች በሙሉ ያለምንም ገደብ ከቀረጥ ነጻ እንደሚገቡም በአዋጁ ተመልክቷል፡፡

ኢሳት በቅርቡ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በርካታ የኢህአዴግ አባላት የአቶ መለስ ፋውንዴሽን የሚዘልቀው ኢህአዴግ በስልጣን ላይ እስካለድረስ ብቻ መሆኑ እየታወቀ በቢሊዮን ብር ወጪ ማውጣቱ ጠቀሜታው ምንድነው በማለት ይጠይቃሉ።

በጥምቀት በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሸጡ የነበሩ ሰዎች ታሰሩ

በጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ብዙውን ጊዜ በጥምቀት በዓል ጊዜ የሚጠቀሰውንና ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያሰፈረውን ፦“አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተፃፈበት ቆብ የጥምቀት ዕለት ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ታፍሰው ታሰሩ።

እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ተከትለው በሞቀና በደመቀ ሃይማኖታዊ መንፈስ በማክበር ላይ እያሉ በፖሊስ የታሠሩት ስድስት ወጣቶች ሲሆኑ ፤ጥቅሱ የተጻፈበትን ቆብ ይሸጡ የነበሩት ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ገቢ ለማስገኘት እንደሆነ ተገልጿል።



ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ወቅት ወጣቶችን ሰብስበው ስለሀይማኖቶች ባደረጉት ገለፃ ፦ ተመሳሳይ ጥቅስ የተፃፈበትን ቲሸርት የለበሱ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን ፦<<አንዲት ሀይማኖት የሚሉ አክራሪዎች>>በማለት እንደዘለፏቸው ይታወሳል።



አንድ ኣማኝ ለሚያምንበት ነገር ምክንያቶቹን እንደሚያቀርብ ሁሉ ክርስቲያኖችም ስለ እምነታቸው በመጽሐፍ ቅዱሳቸው የተፃፈውን ጠቅሰው ለራሳቸው ትምህርትና ጥቅም ማዋላቸው እንዴት ከ አክራሪነት ጋር እንደተያያዘ ግልጽ አይደለም ያሉት የሀይሞኖቱ አባቶች፤ “አክራሪነት ማለት የራሱን እምነት በሌሎች ላይ በሀይልና በተጽዕኖ ለመጫን መሞከር ነው።መንግስት እያደረገ ያለው ግን የራሳችሁን እምነት አትከተሉ ይመስላል።ሰዎቹ የቀራቸው ነገር ጥቅሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሰረዝ አለበት የሚል አዋጅ ማውጣት ብቻ ነው>>ብለዋል።



ያለ በቂ ዕውቀት የሃይማኖት አክራሪነትን እዋጋለኹ ብሎ የተነሳው መንግስት ‘አንዲት ሃይማኖት…አንዲት ጥምቀት’ የምትለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ ለራሳቸው መማሪያ የሚያውሉትን ክርስቲያኖችን በሙሉ በማሳደድ ላይ ይገኛል ብሏል-ደጀ ሰላም።



የመጽሐፍ ቅዱስን ኃይለ- ቃል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔርን መናገር፣ ማስተማርም ሆነ በጽሑፍ መያዝ ፤ሌሎች እምነቶችን እንደመዋጋት ተደርጎ እንደሚቆጠር በመናገር በፖሊሶቹ አማካይነት ጥብቅ ማዋከብና እንግልት የሚፈጽመው መንግሥት እነዚህን ስድስት ልጆች ያሰረውም በዚሁ ምክንያት መሆኑን በወቅቱ በቦታው የነበሩ እማኞች ተናግረዋል።



ድረ-ገጹ አክሎም ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ ቀደምት መንግሥታት ሁሉ በባሰና በከፋ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ የውስጥ ጉዳይ ረዥም እጁን አስገብቶ የሚያምሰው ይህ መንግስት ፣ በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ላይ ሳይቀር ባለ ሥልጣኖቹን በመላክ የሲኖዶሱ ተሰብሳቢ ለመሆን በመሞከር ላይ ይገኛልም ብሏል።



መንግሥት በአገሪቱ ቀደምት እምነቶች ላይ ያለውን አቋም ለካድሬዎቹ በተከታታይ ሥልጠና በመስጠት የሚያስጠናበት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል።



ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ድረስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በሌሎች ኃላፊዎች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና እስልምና ላይ ያነጣጠረ እንደሆነም ደጀ-ሰላም አስፍሯል።



መንግሥት በነባር አገራዊ ቤተ እምነቶች ላይ እያስፋፋ የመጣው ጣልቃ ገብነት ድንበሩን አልፎ የእስልምና መሪዎችን በማሰር እና የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ በመዘወር መገለጡ ይታወቃል ብሏልም።



መንግሥት ለባለሥልጣኖቹ የሚሰጠውን ሥልጠና ለማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ ሙሉ ዶኩመንቱን ለማቅረብ እንደሚሞክር ድረ-ገጹ ገልጿል።

ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ

ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ በመሄድ አቤት ቢሉም ሶስት ሰዎችን በመወከል ችግራቸውን እንዲያቀረቡ ተነግሮአቸዋል። ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ነዋሪዎችን አባረዋቸዋል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአይን ምስክር ለኢሳት እንደገለጡት፣ ተማሪዎች ደብተራቸውን እንኳን ሳያወጡ ቤታቸው እንደተቃጠለባቸው፣ ብዙዎችም በከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል።

በኢትጵያ ውስጥ በልማት ስም እየተበራከተ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች ችላ እንዳሉት ተመልክቷል። በአላማጣ ላለፉት አንድ ወራት የከተማው ህዝብ በልዩ ፖሊሶች ሲዋከብ እንደነበርመዘገባችን ይታወሳል። በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው

ኢሳት ዜና:-በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአለት ተፈልፍለው የተሠሩት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ የመሰንጠቅ አደጋ ላይ መሆናቸውንና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኙም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ቅርሶችን የተመለከተው የፓርላማ ቡድን ማመልከቱን ሪፖርተር ዘገበ

የቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ ጐለጐታ፣ ቤተ መርቆርዮስና ቤተ ደናግል አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ደረጃ መጎዳታቸው ተገልጿል። ታሪካዊዎቹ ህንጻዎች እየተሰነጠቁ መሆናቸውም በዘገባው ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ተቋማቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን፣ አብያተ ቤተ ክርስቲያናቱ የተሠሩት ከአለት ተፈልፍለው በመሆኑ እንደሌሎቹ ዓይነቶች ቅርሶች በቀላሉ ጥገና በማድረግ የገጠማቸውን የመሰንጠቅ አደጋ ለማቆም በአገር ውስጥ ባለው የአቅም ደረጃ የሚቻል አለመሆኑን ገልጸው ፣ ችግሩን መፍትሔም ሊያጣ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አካባቢውን ተዘዋውሮ ለተመለከተው የፓርላማ አባላት ቡድን ተናግረዋል።
ባለሥልጣኑ በዚህ መሰል ቅርሶች ጥገና ላይ ልምድ ካለውና ከጣሊያን ወደ አገሩ ተቆራርጦ የገባውን የአክሱም ሐውልት በማያያዝ በአክሱም የተከለው ድርጅት፣ በላሊበላ ቅርሶች ላይ የተፈጠረውን ችግር በመመርመር መፍትሔ እንዲያመጣ ሀላፊነት መሰጠቱን ባለስልጣኑ ተናግረዋል።

በላሊበላ ቅርሶች ላይ የታየው አደጋ የቆየ ቢሆንም መንግስት እስካሁን በቂ ትኩረት ሳይሰጠው ቆይቷል። የአካባቢው ባለስልጣናት የአለም ህዝብ ቅርሶችን እንዲታደጋቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ታዋቂ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያ ለኢሳት እንደገለጡት የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ቅርሶች በሰበብ አስባቡ ሲወድሙ ዝም ብሎ መመልከት እንደሌለበት ገልጸዋል። ጉዳዩን ከመንግስት ይልቅ በአገሪቱ ያሉ ታዋቂ ሰዎች ፋውንዴሽን በማቋቋም ቅርሶቹ እንዲጠገኑ ሀላፊነት ቢወስዱ የተሻለ መሆኑንም ግለሰቡ መክረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሙስሊሙ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ አንድ ሥራ-አስኪያጁን ማባረሩ ታወቀ

ኢሳት ዜና:-ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እየተባለ የሚጠራውን ክፍል በስራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብዱል ጀባር ሀሚድን ከስራ ያባረረው የአየር መንገዱ ሙስሊም ሰራተኞች ከሌሎች ወገኖች ጎን ተቀላቅለው ተቃውአቸውን እንዲገልጹ አደራጅቷል በሚል ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

በተያየዘ ዜናም በሱፐርቫይዘርነት ደረጃ ስትሰራ የነበረችው ትእግስት ደምሴ ከስራ በተቀነሰ ሰራተኛ ላይ የሀሰት ምስክርነት እንድትሰጥ ተጠይቃ ፈቃደኛ ባለመሆና መሆኑ ታውቋል።

ኢሳት የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ 50 የአየር መንገዱ ሰራተኞች መባረራቸውንና በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት መተካታቸውን ገልጸ ነበር። ከስራ የተቀነሱት የ36 ሰራተኛች ሙሉ ስም ዝርዝር እና አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሰን ሲሆን፣ ሙሉውን ዝርዝር በኢሳት ዌብሳይት ላይ ታትሞ መውጣቱን ለመግልጽ እንወዳለን።

በጉዳዩ ዙሪያ የአየር መንገዱን አመራሮች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Jan 23, 2013

የተከደነ ብቃት በዓለም አደባባይ ሲውል

“አንድ አዲስ ያልተጠበቀ ብርቅዬ ነገር”

ከዛሬ የከሰዓት በኋላ ኢሮ ስፖርት ትንተና የተወሰደ
ከሥርጉተ ሥላሴ 22.01.2013
መቼም ፍቅር ከነተፈጥሮው የሚገኝበት ሚስጢር ከእናትና ከማልያ ላይ ብቻ ነው። የማልያ ፍቅር ተጫዋቹን ብቻ ሳይሆን ታዳሚውንም በሙሉ ፈቃደኝነት የሚሰደምም  … ዕጹብSouth Africa Ethiopian fans ድንቅ ጥበብ ነው። የበቃ!
እግር ኳስ የዓለምን ህዝብ በፍቅር ክንፍ የሚያደርግ ጨዋታ ነው። ሌላው ቀርቶ የእግር ኳስ ህግጋትን በሚመለከትም ከዳኞች ባላነሰ ታደሚዊቹ በቂ ዕውቀት እንዳላቸው እገምታለሁ። ስለምን? በእግር ኳስ ጨዋታ ታዳሚው በባለቤትነት ስሜት መንፈሱንና አካሉን በፈቃዱ ለድንቡልቡሏ ውብ ተዋናይ በውዴታ ስለገበረ፤ ሰለለገሰ በቀላሉ ሜዳ ላይ ባለው ትዕይንት ብቻ መማር ስለሚቻል።
የተቀባው እግር ኳስ ዕልፍ አዕላፋትን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በፍቅር ብቻ ቤተኛ በሚያደርገው  ስጦታው በሙያው የሰለጠኑ፤ በጸጋው የተካኑ የብርቅና ድንቅ ሰዎችም ማፍሪያ ተቋም ነው። እግር ኳስ በሰው ኃይል አሰላለፍና አደረጃጃትም ሆነ አመራር ከዓለም- ዓቀፍ ጀምሮ እስከታች ድረስ በተዋረድ ሰፊ ሰራተኞችን ያሰማረ የሥራ መስክ ነው።
እግር ኳስ በኢኮኖሚ አቅሙ ሆነ በዓለምዓቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ተጽዕኖ በማሰደር እረገድም አንቱ የተባለ ነው። ዘረኝነትን በመዋጋት እረገድም ግንባር ቀደም ሲሆን፤ በማህበራዊ ህይወትም ቢሆን ወሳኝ ድርሻ ያለው ዘርፍ ነው። እግር ኳስ የአንድ ሀገርን የባህል ደረጃ ከፍ ከሚያድርጉት ወሳኝ ክስተቶች አንዱ ሲሆን፤ አብሶ አዲሱን ትውልድ በፍቅር በመገንባት በኩልም የእራሱ መጠነ ሰፊ አስተዋፆ አለው።
በሌላ በኩል በህጉ አፈጻጸም አካሄድ በኩልም የእኔ የሚለው የችሎት አደባባይ ያለው ሲሆን አብሶ ሜዳ ላይ በትወና፤ በፊሽካ፤ በቢጫና በቀይ ካርድ ቅጣት፤  በነፃና በማዕዘን ምት ተንቆጥቁጦ በራሷ ጊዜ ድንቡልቡሏ መረብ ላይ ስተሞሽር ልብን በሐሤት የሚያስጨፍር፤ ፍጹም የሆነ ፍሰኃን የሚቸር ውበት ያለው የህበረት መንበር ነው።
ከሁሉ በላይ አስልጣኞች ከሜዳ ውጪ ሆነው ልጆቻቸው የሚያድረጉትን እንቅስቃሴ በመከታተል ጎል ሲጋባ፤ ሆነ ምቱን ሲስቱ፤ እንዲሁም ሲቀጡ፤ ሜዳ ላይ ተቀናቃኛቸው በሚፈጥረው ግፊያ ሲወድቁም ሆነ ሲነሱ፤  የሚያሳዩት ልዩ እንቅስቃሴ ሌላኛው የደስታ ማሳ ነው – ለእኔ። አብሶ ሲሸነፉ ጋዜጠኞች ሲያፋጥጧቸው የሚያቀርቧቸው ሰበቦች ልዩ ድራማ ነው – አሁንም ለእኔ፤ በለስ ቀንቷቸው ካሸነፉ ደግሞ ተዘጋጅተን ገባን፤ አሸነፍ በማለት በሙሉ ልብ ሲናገሩ ማዬት ውበቱ ጥንድ ነው። ቡድኖቻቸው ያሸነፉላቸው አሰልጣኞች አንዳንዶቹ ትንሽ ጣሪያ ጣሪያ ሲሰኛቸው ማዬቱ ደግሞ በራሱ ሌላው የህይወት ት/ቤት ነው። እኔ ያለበትን ማዕከላዊ እንብርት ያሳያል። ትችቱ፤ ድጋፉ ሲደማመር ደግሞ ውበቱን ያነጥረዋል።
ከእግር ኳስ ጨዋታው ጋር እጅግ በርካታ ጉዳዮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይታደማሉ … ፤ ወጌሻዎች ሲራወጡ፤ የህክምና ባለሙያዎች እርዳታ ለመቸር ሲጣደፉ፤ አራጋቢዎች ገራና ቀኝ ሲከንፉ፤ የመሃል ዳኛው ሜዳው አልበቃ ብሏቸው ሲባትሉ፤ የጸጥታ አስከባሪዎች አካባቢውን በቅኝት ሲያፋጥጡት፤ እራሷ ድንቡልቡሏ – ስትደለቅ – ስትረገጥ በጥፊ ስትናጥ፤ ሜዲያ ደረቱን ገልብጦ እንካችሁ እንደ አሻችሁ ጨፍሩብኝ ብሎ ሲያውጅ፤ ሆቴሎች ተሰናድተው ሲቀበሉና ሲሸኙ፤ ማለያዎች ከሙሸሮች ጋር ሲፍነሸነሹ፤ ሰንደቆች ከፍ ብለው አንገታቸውን ቀና አድርገው ሲወርቡ፤ ድምጽ ማጉሊያዎች ከባትሪ ጋር ተጋብተው በድምጽ ሲፈርሹ፤ ሰዓት ተሎ ተሎ እያለ አቅልን ሲዘቀዝቅ … ለባለ ድሉ እኔ አለሁ ሲል  ዋንጫው … ሳተናው ጋዜጠኛ ሁለገብ ተግባሩን ለመከወን ትጥቁን አሟልቶ ሲገሰግስ ሁሉም በዬፊናቸው ዬዬራሳቸውን መክሊት ይዘው ጨዋታውን በሁሉሙ መስክ ያስጌጡታል።
ከዚህም ሌላ በአፍሪካ ሆነ በዓለም የዋንጫ ውድድር ጨዋታውን ተከትሎ የሚፈጠሩ የዝምድና ግንኙነቶች እስከ ጋብቻ ድረስ የሚያደርሱ፤ ህይወትን መስመር ሊያስዙ የሚችሉ ገጠመኞች ሁሉ የእግር ኳስ አልማዛዊ ማህደሮቹ ናቸው። ከሁሉ በላይ እግር ኳስ ብሄራዊ ስሜትን የማነሳሳት አቅሙ የላቀና የመጠቀ ነው- እንዲያውም አንጡራ ሃብቱ ነው ማለት ይቻላል። ሰንደቅዓላማ ልደትህ መቼ ነው? ተብሎ ቢጠዬቅ በአህጉራዊና  በዓለምዓቀፋዊ  የእግር ኳስ ጨዋታ ብሎ እንደሚመልስ እርግጠኛ ነኝ። እግር ኳስ ይጠራል – ማንነትን፤ …. እግር ኳስ ያናገራል ውስጥን፤ እግር ኳስ ያስተሳስራል ህብረትን፤ … እግር ኳስ ልቡ – የሰላምና የፍቅር ማማ ሲሆን ጠንካራ ክንዱ ደግሞ ሐሤትን ማፍለቅ ነው። …
እኛም በ2013 እ.አ.አ በ2005 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ታዳሚ ለመሆን በቃን። እግዚአብሄር ይመስገን። ይህ ዕድል በብዙ መልኩ ሲመነዘርና ሲዘረዘር የድንቁ ባላወለታ፤ የተከበሩት የፓን አፍሪካኒስቱ ዬይድነቃቸው  ህልምና ስኬት ነው። የኪንግ ማርቲን  ህልም በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዕውን እንደ ሆነው ሁሉ የተከበሩ ዕንቁችን ዬይድነቃቸው ህልም ደግሞ በዕንቡጦቻችን ይኸው ዕውነት ሆነ ዛሬ።
በሌላ በኩል ዕድሉ ቁልፍ ነውና ይኸው ሰፊ በር ቧ ብሎ ተከፈተ። ትናትም ዛሬ ኢሮ ስፖርት ስለ ይድነቃቸው ፍሬዎች እጅግ አበረታች ትንተናዎችን እዬተሰጠ ነው። መጀመሪያ ላይ ኢሮ ስፖርት እርግጠኛ አልነበረም።  በቅድመ ዝግጅት ትንተናዎች ላይ በጥቅሉ ከ30 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ዕድሉ እንደተገኘ ሲዘግብ ሰነባበት። ስለምን? ብዙም የይድነቃቸውን ልጆች መሰረት ስላላጠና መሰለኝ። ትናንትና እና ዛሬ ግን እጅግ ምርጥ በሆኑ ቃላት ብሄራዊ ቡድናችነን እያሽሞነሞነው ይገኛል። „ፈጽሞ ዕውቅና ያልነበረው፤  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግልና የህብረት ጨዋታ ውብ የሆነ፤ ሳንጠብቅው በመንፈሳችን ላይ ተጽእኖ የፈጠረ ብቁ  አዝናኝ ጨዋታ ነው፤ ያልተጠበቅ ትልቅ ልዩ ብርቅና ድንቅ ነገር፤ የተመልካችን አትኩረትን በእጅጉ የሳበ፤“  ሲለው … በሌላ በኩልም የተቀናቃኙን  የዛንብያን ቡድን በሚመለከትም „የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛንብያን ተስፋ አሳጣ፤ የዋንጫ ባለቤት የነበረው ዛንቢያ ያልጠበቀው ሽንፈትና ሰቀቀን ገጠመው። ዛንብያ ውጤቱ እንደጠበቀው ሳይሆን ቀረ“ በማለት አጣጥሎ ዘገበው።  ኢሮ ኒውስ ብሄራዊ ቡድናችን አግኝቶት የነበረው  የፔናሊቲው ምት አለመሳካቱን አልደነቀውም። እቁብም አልሰጠውም ። ጨርሶም ሲያነሳው አልሰማሁም። ለኢሮ ኒውስ ልብና ቀልብ የሳበው እኩል ለእኩል መውጣቱንና፤ የጨዋታ ብልጫ ሆነ ጥበብም ከብሄራዊ ቡድናችን ያዬ መሆኑን ነው ዘጋቢው በደስታ የሚገልጸው …
ብዙ ዕድል ስል ከላይ ያነሳሁት ነጥብ ነበር … ኢሮ ስፖርት አሁንም ቅድምም የይድነቃቸውን ልጆች እያመጣ ሲሳዬን በውስጣችን ያለችውን እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን ሲያነሳሳ ደስ ይላል። ሌላም ስንት እጮኛ ተሰልፎ ይሆን ለቀንበጦቻችን? አንድ ሰው ብዙ ነው- ለእኔ።  (ማለት እራሱ ግለሰቡ፤ ቤተሰቦቹ፤ ደጋፊዎቹ፤ ሁሉ ሲደማማሩ የትዬሌሌ ነው። የቁጥር ተማሪ እባካችሁን ሁኑ።)
… አጋጣሚው እረድቶ ለውጪ ሀገር ክለቦች የመጫወት ዕድል ከኖረ ብዙ ነገር ይታፈስበታል። ለአዲስ ልምድና ተመክሮ መንገድ ይኖራል፤ ተጫወቾች ዕውቀታቸውን የማሻሻል ሆነ የመማር አጋጣሚ ይኖራቸዋል፤ የአኗኗር ደረጃ ከፍ ማለትን ያመጣል፤ የፕሮሚ ሰውነትንም ያስገኛል፤ ዬፕሮፌሽናል ተጫዋችነት ማዕረግንም ያክላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አጋጣሚዎቹ ስለሚያግዙ ተደማጭነትም ማግኘት ያስችላል። በተጨማሪም  …. የሌላ ሀገር የእግር ኳስ አፍቃሪ አዲስ ደጋፊ ማፈራትን ሁሉ ያካትታል … የሶሊዳሪቲ ማዕደኝነትም እንደ ማለት። ድንበር አልባ ፍቅርና  የጸሎት ጥበቃም … ያስገኛል … ጠንክሩና እፈሱ ውዶቻችን ….
አዎን 21ኛው ምዕተ ዓመት የእግር ኳስ ጨዋታ ዕድገቱ እንደ ዘመኑ ነው። በዚህ ዘመን በሁሉም ዘርፍ ታዳሚ መሆን መቻል ለነገ ሟተት ነው። አይቦሪ በ2006 ጀርመን ላይ፤ በ2010 ደቡብ አፍሪካ ላይ የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ አፍቃሪ ማህበረሰብ ፋቦሪቲ -ቀዳሚ ተዋዳጅነትን ያተረፈ ነበረ – በዝሆኑ ድርጎባ አማካኝነት። ያው እንደምታውቁት አፍሪካዊው ድርጎባ በዝሆን ቅጥል ስም በዓለም ከሚታወቁት አምስት ኮከብ ተጫዎቾች አንዱ ነው። ከነሜሲ፤ ከነክርስቲያን ሮናልዶ ወዘተ …  ይህ ዕድል በቀጥታም በተዘዋዋሪም ብቃቱን በማጎልመሱ አዎንታዊ ትርፍ ለአይቮሪ አስገኝቶለታል። የሚዲያ አትኩሮትንም ከሌሎች ሀገር ብሄራዊ ተጫዎች ለእሱ ጫን ያለ ነው። የ2012 በአውሮፓ ሊግ የዋንጫ ጨዋታም እኩል ያደረገውን ጎል ያስገባም፤ የፔናሊቲውን የመጨረሻ ወሳኝ ጎል ያሰቆጠረ ድርጎባ ነበር። በመሆኑም ለመጀመሪያ ጊዜ የእንግሊዙ ቻልሲ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን በቃ። ምን ለማለት ነው ነገ ተስፋው የፋፋ ነው … ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ እድገትና ዕውቅና – ግኝት የዘንድሮው ልዩ ናሙና ነው። በማስተዋል ሁነን ሁለገቡን ራዕይ እንዳስሰው …
ይገርማችኋል  ለእኔ አሸንፈዋል ዕንቡጦቻችን። የ30 ዓመት የታመቀ ህልም ፈተዋል። ትናንትና የፔናሊቲው ዕድል ሳይሳካ ሲቀር ምንም አልመሰለኝም። በፍጹም። ዋናው ፍሬ ነገር ታላቁ በር ተከፍቶ፤ ትብትቡ ተፈታቶ ከዚህ ደረጃ መድረሳቸው ነው። ነገ ሌላ አዲስ ብሩኽ  ቀን ነውና።
የብሄራዊ ቡዳናችን ሶስት አባላት ከሲዊዲን ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩትና ገረመኝ። ከእኛ እነሱ ይበልጣሉ። እነሱ ለኮፒ ራይት፤ ለልዩ ቅብ ሴሪሞኒ አይደለም የተሰናዱት። ለታላቁ ሚስጢር ለኢትዮጵያዊነት ብቻ  እንጂ። በማስተዋል የመለሷቸው ነጥቦች ሁሉ ጎሉን ማን አስገባ?! ሳይሆን የወል ዓላማቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀድመው የተመደቡላትና በውጤትም የሚመደቡላትን ተቀናቃኞቿን በመርታት  ለድል መብቃት ስለመሆኑ አስተማሩን። … ድንቅ ናቸው አይደል? መርቁልኝ። እርግጥ በጥያቄው እኔ ያልተመቸኝ አንድ ጥያቄ ነበር። „ስንት ጎል አስቆጥራለሁ ብለህ ታስባለህ?“ ይህን ጥያቄ አንድም ቀን በሌላ ጋዜጠኛ ሲጠዬቅ ሰምቼው ስላማለውቅ ምን ይመልስ ይሆን ብዬ ሳስብ መረቅ የሆነ መልስ ተሰጠበት። እኔ በእነሱ ኮራሁባቸው። በተረፈ ጎል ሁሉ ነገር ለተሟላላት ብሄራዊ ቡድን እንኳን ከነፃነት ጀምሮ ማለቴ ነው …
-        የአዬር ባህሪ፤
-        የተጨዋቾች ትንፋሽ ጤናማነት፤ የሥነ ልቦና ሰላማዊነት፤
-        የደጋፊዎች ብርታትና ጥንካሬ፤
-        የዕለቱ ዳኛ የአመራር ብቃት፤
-        የቀናት፤ የሰዓቱ ምቹነት … ዕድላማነት …
-       የተቀናቃኝ ጎል በቀኝ በኩል መገኘት፤
-       ከዚህ ሌላ ተቀናቃኝ መንፈሱ ሳይሰባሰብ የአጥቂውን ጉልበት ሳይመጥን  ቀድሞ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ማጥቃት መሰንዘር ወይንም መቅደም የመቻል ብቃት፤ ወይንም …
-       ባለቀ ሰዓት ተቀናቃኝ ደከም ብሎ ዛል ወይንም ሲጠነዝል ጥቃት የመሰንዘር ጥበብና ስልት …
-       ወይንም ተቀናቃኙ ቀድሞ በማስገባቱ ዘና ማለት ሲጀምር … ጎል ከመረብ ጋር የመገናኘት ዕድሉ ስምረት ያገኛል። የተዘራ ሁሉ እንደማይበቅል ሁሉ የተለጋ ሁሉ ወይንም ወደ ጎል የተቃጣ ሁሉ ግብ ሊሆን አይችልም። ብቻ ከላይ የጠቃቀስኳቸው እና ሌሎቹም ታክለው ጎል ጎል ጎል …  ይሆናሉ። ያስጨፍራሉ ያስደልቃሉ። ያሳብዳሉም።
ነገር ግን አንድ ተጫዋች እኔ በዚህ ጨዋታ በግሌ ይህን ያህል ጎል አስቆጥራለሁ ብሎ መገመትም ሆነ ማስላትም ግን ፈጽሞ የሚቻል አይመስለኝም። ጎል የህብረት ጥረት እንጂ የአንድ ሰው ውጤት አይደለም። አንድ ተጫዋች የማስገባት ዕድሉ እያለው ግን ለጎሏ ቅርበት ወይንም ለግብ ለተመቼው ተጫዋች ኳሷን ይልካታል። ከዛ በስልትና በጥበብ ቅብብል ኳስ ለመረብ ትዳራለች። ለዚህ የጀርመኑን ብሄራዊ ተጫዋች፤ በአሁኑ ወቅት የሪያሉ ክለብ ተጫዋች የሆነውን ኡዚልን ማናሳት በቂ ይመስለኛል። በ2010 ደቡብ አፍሪካ ላይ በነበረው ዓለምዓቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታ የባዬሩ ክለብ ተጫዋች ሙለር የእግር ኳስ ንጉስ ተብሎ የተሸለመው ሆነ የተወደሰው …  ኡዚልና ባስቲ ባመቻቸሉት ፍትፍት ነበር። በምድር ላይ ኢጎይዝምን ካለይግባኝ የገደለ የሰለጠነ የሙያ መስክ ቢኖር እግር ኳስ ነውና። … በማናቸውም የትግል ሕይወት ውስጥ ከዚህ መጠራቅቅ የወጣ ህዝብ ሆነ ፓርቲ  ነፃነቱን ይጎናጻፋል።
ሌላው አብክሬ ላስገነዝብ የምፈልገው እግር ኳስ በጣም ከስሜት ጋር የተጋባ ነው። ከሥነ ልቦናዊ ሁነቶች ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። በፍጹም ሁኔታ ከመንፈስ ጋር የተዋህደ ነው። ማሸነፍ የሚኖረው በራስ የመተማመን መንፈስ ሲጎለብት ነው። ይህ ለተጫዋቾች ብቻ ሳይሆን ታዳሚዎችንም ይጨምራል። በሙሉ ኃይልና በአንድነት ብሄራዊ ቡድናችነን ልናበረታታ፤ ልናደንቅ፤ ልንደግፍ ይገባል። ምንም ዓይነት ክፈተት ሳይኖር በአኃቲ ልቦናና በቅንነት አዘውትረን ልናስባቸው ይገባል። እባካችሁን!?
ወገኖቼ እግር ኳስ 13ኛው ፕላኔት ነው። በ13ኛው ፕላኔት ደግሞ ታዳሚዎች በፍቅር፤ በመተባበር፤ በመረዳዳት፤ በመተሳሰብና በቅንነት በኪናዊ ህብረት የሰለጠነ ተግባር መፈጸም አለብን። ባለው የኤሌትሮኒክስ የግንኙነት መስመር ሁሉ ድሌ! ድሌ! ማለት አለብን። እስኪ ትንሽ ንጹህ አዬር እንተንፍስ … ወያኔ ከፈጠረው፤ ካመጣው ትርምስ ወጣ ብለን በያለንበት ለዚህች ለተወሰነ ቀን ተ ጫዎቾቻችን መንፈሳቸው፤ ሃሳባቸው፤ ስሜታቸው ሳይከፋፈል እስከ ቻሉት ድረስ እንዲገፉ እንደግፋቸው አደራ!
ከዚህ ሌላ መብለጥ ወተታችን ይሁን። መቅደም ማር ወላላችን ይሁን። ተጫዎቾቻችን ሲፊ ደጋፊ አላቸው። እሱን ሁሉ ሃብት ማደረግ የመቻልን ሥነ -ጥበብ እንካንበት። … ተሽለን እንገኝ። ሁሉ አለን። ሁሉንም መሆን እንችላለን። ምን ሲገደን?! በደማችን ውስጥ ያለው ብሄራዊ ስሜት ቀልቡን ባይሆን በብሄራዊ ቡድኑ ላይ እስኪ ትንሽ አረፍ እንዲል እንርዳው።
አራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።
ድል ከክብር ጋር ለብሄራዊ ቡድናችን!
ዕልፍነታችን በድጋፍ እናንቆጥቁጠው!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የአዲስ አበባ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን በቃጠሎ ወደመች

                                                       ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተነሳ ፎቶ
                                            ቤታቸውን በፍቃደኝነት ዳግም በመስራት ላይ ያሉ ወጣቶች
                                                 ቀድሞ ቤተክርስቲያኒቱ እዚህ ቦታ ላይ ነበረች

  • ትላንትና ከቀኑ 7 ሰዓት በተነሳ እሳት ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ከሚገኙ ታቦታት   ከመጽፍትና ከመስቀል ውጪ ሙሉ በሙሉአውድሟታል :: ቤተክርስቲያኒቱ በጠራራ ጸሀይ ፤ በቆርቆሮ የተሰራው ግድግዳ እና ድንገት በተነሳ እሳት በአንድነት በመሆን የደረሰውነ ጉዳት  ከፍ አድርገውታል
  • ትላንትና 70 ሺ ብር ከምዕመኑ መሰብሰብ ተችሏል 
    •  እስከ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ከ200 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል ፤ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ምዕመናኖች ቦታው ላይ በመገኝት ቤተክርስቲያኒቱን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ 
    •      ከትላንት ማታ ጀምሮ የተጀመረው ስራ አሁንም ቀጥሏል ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከተቃጠለች 24 ሰዓት ሳይሞላት ማገር አቆመው የጎን ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተጠናቋል፡፡
      •     አካባቢው ያለው ሰው ስራውን ለሚሰሩት ሰዎች እንጀራ ወጥ ፤ ለስላሳ ውሃ እና አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ ከ48 ሰዓት በፊት ስራን ለመጨረስ እየተረባረበ ይገኛል
      •                የእሳቱን መነሻ አሁንም እየተጣራ ይገኛል  ; እሳት አደጋ ተደውሎለት በሰዓቱ ባለመምጣቱ አደጋውን የከፋ አድርጎታል 
  • የእመቤታችን የቅዱስ ዮሃንስና የቅዱስ ኡራኤል ታቦቶች ምንም አለመሆናቸው እጅጉን አስገርሟል
  • በርካታ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት ተረባርበው ነበር
  • የአካባቢው ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉት መረባረብ እጅግ ያስገረመ ነበር ፤ አሁንም ቤቷን ለማቆን ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛል ፤

ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?

የቀድሞው አለቃዬ እና የአሁን ወዳጄ ዳዊት ከበደ ሰሞኑን አወዛጋቢ ሆኖ ሰንብቷል። ለምን አወዛገበ? ምን አወዛገበ? እንዴት አወዛገበ? ማንን አወዛገበ…? ወዘተ የሚሉትን ሁሉንም ዘርዝሬ መዝለቄን እንጃ ግን እስቲ ትንሽ ነካ ነካ ላድረግማ፤
ባለፈው ጊዜ ዳዊት ከበደ ስለ ኢትዮ ሚዲያው አበርሃ የፃፈውን ወቀሳ በአውራምባ ታይምስ ድረ ገፅ ላይ አንብቤ ነበር። በኢትዮ ሚዲያ ላይ ስለ ዳዊት ከበደ የወጣውን ፅሁፍ አላየሁትም። የዳዊትን ምላሽ ግን አልወደድኩትም። ይህንን ለዳዊትም ነግሬዋለሁ። ሳስበው ዳዊት ያንን ፅሁፍ ሲፅፍ ክፉኛ ተበሳጭቶ እንደሆነ እገምታለሁ። ምን መገመት ብቻ በደንብ አውቂያለሁ እንጂ…
በተናደድን ጊዜ የምንወስናቸው ውሳኔዎች ብዙ ግዜ መልከ መልካም አይሆኑም። ወይም ውጤታቸው አያምርም። በብስጭት ሲወሰን እንኳን ሌላው ቀርቶ ራስን ማጥፋት እንኳ አይሳካም። ለሁሉም ነገር ስክነት ያስፈልጋል። በስክነት ውስጥ ብስለት አለ። በጥድፊያ ውስጥ ግን ያለው ጥፊያ ነው መጥፋት እና ማጥፋት።
ይህ በሆነ በስንተኛው ቀን እንደሆነ እንጃ እንደ ገጠር ቤተክርስቲያን ሰንበት ሰንበት ብቻ የሚከፈተው አባመላ የተባለ ፓልቶክ ሩም ዳዊት ከበደን ይዞ ባለፈው ቅዳሜ ብቅ ብሎ ነበር። ወዳጄ ዳዊት ከበደ ወደዚህ ፓልቶክ ሩም ለቃለ ምልልስ ሲሄድ በፊት ከነበረው አቋሙ በአንዳች ምክንያት ለውጥ እንዳደረገ ተገንዝቤ ነበር።
ምን አይነት አቋም…!?
ከዚህ በፊት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ እየሰራን ሳለ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለቃለ ምልልስ ቢጠራው እምቢኝ ብሎ እንደነበር አስታውሳለሁ። ዛሬ ግን የኢህአዴግ ዋነኛ አቀንቃኝ የሚባል ፓልቶክ ሩም ለቃለ ምልልስ ሲጠራው “ምን ችግር አለው” ብሎ ሄዷል። ይሄ በጣም ያስደሰተኝ ለውጥ ነው። ጥያቄዬ ለውጡ የመጣው በብስጭት ነው ወይስ በብስለት ነው? የሚለው ነው። መልሱም እኔው ዘንድ አለ። ዳዊት የአቋም ለውጥ ያመጣው በብስጭት ነው።
ዴቭ በዚህ ፓልቶክ ሩም ሁለት ነገሮችን አንስቷል። አንደኛው፤ በውጪ ሀገር ያሉ የተቃዋሚው ፓርቲ አመራሮች የመፃፍ ነፃነቴን ተጋፉት የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ትግሬ ስለሆንኩ በውጪ ሀገር ባሉት ተቃዋሚዎች ዘንድ በጥርጣሬ አይን እየታየሁ ነው። የሚል ነው።
ሁለቱም ነገሮች ቢሆን ተደርገው ከሆነ በእውነቱ በተቃዋሚዎቻችን እጅጉን ተስፋ ቆርጠን ፍራሽ አውርደን ልቅሶ መቀመጥ አለብን። በተለይም እዚህ ውጪ ሀገርም የፕሬስ አፈና የሚደረግብን ከሆነ በተለይ ከኢትዮጵያ ሸሽተን የመጣን ሰዎች ድጋሚ ሸሽተን ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ሊኖርብን ነው ማለት ነው።
ለማንኛውም ዳዊት በዚህ የተነሳ ብስጭቱን ገልጿል። እኛም “ጎበዝ ዳዊት” ብለን አሞካሽተን ችግሩ ግን ብለን እንቀጥላለን…
ችግሩ ግን ዳዊት በቃለ ምልልሱ ወቅት አባ መላ የተባለው ጠያቂው በቀደደለት ቦይ ዝም ብሎ ሲፈስለት መመልከቴ ነው። ይሄኔ ነው ዳዊት እየጠፋ ይሆንን!? ስል ሰጋት የገባኝ።
ነገር ቢያበዙት በአህያ አይጫንም እንዲሉ አንድ ለምሳሌ ላንሳ፤
ጠያቂው አባ መላ “እስክንድር ነጋ በአሸባሪነት ከተሰየሙ ድርጅቶች ጋር ሲፃፃፍ ተይዞ ለምን ታሰረ? የሚሉ ሰዎች ዛሬ ግኡሽ አበራ በፌስ ቡክ ላይ ስሜቱን በመግለፁ ሲቃወሙ አግባብ ነው ትላለህ?” ብሎ ሲጠይቀው የዳዊትም መልስ ለመስማት ጆሮዬን አቆምኩ ወዳጄ ዳዊትም “ልክ ነህ!” ብሎ ገና ሲጀምር ታመምኩኝ።
እንደኔ እምነት እና እንደ አቃቤ ህግ ማስረጃ እስክንድር ነጋ ከአሸባሪ ቡድን ጋር ኢሜል መለዋወጡን የሚያስረዳ ነገር አላየንም። እንደኔ እምነት እስክንድር ነጋ የታሰረው ሀቅን ስለፃፈ ብቻ ነው። እንደኔ እምነት ዳዊት ከበደም የተሰደደው ሀቅን ስለፃፈ ብቻ ነው። እናም ወዳጃችን ዳዊት ጠያቂው አባ መላ በመላ ወደ ስርጡ ሲወስደው ሰተት ብሎ ሲሄድለት አየሁ። ይሄኔም ሰጋሁ ዳዊት እየጠፋ ይሆን!?
በጥቅሉ ዳዊት ከፍቶታል። ጥሩ ነው መከፋት። “ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህዴግ ሰራዊት!” እንዲሉ ብሶት የለውጥ መነሻ ነው። ግን ምን አይነት ለውጥ!?
ዳዊት የትግራይ ተወላጅ ስለሆንኩ ተቃዋሚ ስለመሆኔ በጥርጣሬ ታየሁ እንደውም ተቃዋሚ አይደለሁም የማንም ሳይሆኑ መኖር ይቻላል ብሎናል።
ድሮውንም በግሌ ዳዊት ከበደ ተቃዋሚ ነው ብዬ አላምንም። ልክ እኔ ተቃዋሚ እንዳልሆንኩት ማለት ነው። መንግስትን መተቸት ተቃዋሚ መሆን አይደለም። ለገባው መንግስት እንደውም ትችት ደጋፍ ነበር። የእኛ መንግስት የገባው ሳይሆን ግራ የገባው በመሆኑ፤ ደጋፊ አልፈልግም ብሎ አባረረን እንጂ…!
በመጨረሻም፤
እንደኔ እምነት የትግራይ ተወላጆች ተቃዋሚውን ዳዊት በሚያይበት መነፅር እያዩ ከሆነ በእውነቱ ሀገራችን ትልቅ ኪሳራ ላይ ናት።
አሁንም እንደኔ እምነት ተቃዋሚዎች የትግራይ ተወላጆችን፤ ዳዊትን በሚያዩበት መነፅር እያዩ ከሆነ ትልቅ እብደት ውስጥ ነን!

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ ኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቀ

ኢሳት ዜና:- በኢትዮጵያና በዛምቢያ መካከል  ትናንት ምሽት የተደረገውን እግር ኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  ከማሰራጫ ቻናል  በድብቅ በመውሰድ ማስላለፉን ደርሸበታለሁ ሲል የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ)  መግለጹን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ዘገበ
እንደ ዘገባው  የ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን  ሌሎች የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያሰራጩትን ጨዋታ በመስረቅ ጫዋታውን እንዳስተላለፈ የተደረሰበት በእረፍት ሰዓት የጨዋታው ስፖንሰር እንደሆኑ አድርጎ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሢሰራ ነው።
በካፍ መግለጫ መሰረት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፈጸመው ማጭበርበር ሁለት  መልክ ያለው ነው።
አንዱ ማጭበርበር ጫዋታውን ክፍያ ሳይፈጽም በድብቅ ማስተላለፉ ሲሆን፤ሁለተኛው ደግሞ በዚያው በተሰረቀ  የ አየር ሰ ዓት <<ይህን ጨዋታ  ስፖንሰር በመሆን ያስተላለፉላችሁ እነ እገሌ ናቸው” እያለ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ መሥራቱ ነው።
ይህ የ ኢቲቪ ድርጊትም  በሁለተኛው ግማሽ  በጨዋታው ኮሜንታተር ሁለት ጊዜ   ተጋልጧል እንደ ጋዜጣው ዘገባ ።
ጨዋታውን ለማስተላለፍ ፈቃድ ያለው የቴሌቪዥን ጣቢያም በቸዋታው መሀል በፃፈው <<ቴክስት>> የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ድርጅት  ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይፈጽም ጨዋታውን  እያስተላለፈ ነው።>> በማለት ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሣስቧል።
የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ 31 ዓመት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ቢያልፍም፤ መንግስት  ለቴሌቪዥን ስርጭት ከፍተኛ ገንዘብ ተጠይቄያለሁ፤ ይህም ዋጋ በጣም ተወዶብኛል>> በማለት ላለማስተላለፍ  መወሰኑ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ በዘርፈ-ብዙ ሙስና በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ብር የሚዘረፍባትና  ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው  ግለሰቦች ሳይቀሩ በሆነ ባልሆነው  ከፍተኛ ገንዘብ የሚያፈሱባት አገር መሆኗን የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ቀደም ካሉት ቀናት አንስቶ አስተያዬት ሢሰጡ የነበሩ ሰዎች፡<<  18 ሚሊዮን ብር እንኳን ለመንግስት ለዘመኑ ባለሀብቶች ቀላል ነው፤ በዚያ ላይ ሁሉንም ባይሆን የተወሰነውን ከ አገር ውስጥ ማስታወቂያ መሸፈን ይቻላል።መንግስት ማሳዬት ያልፈለገው በ እርግጥ ገንዘብ አጥቶ ነው?ወይስ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄድን ተቃውሞ በመፍራት ነው?>>በማለት ሲጠይቁ ነበር።
ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ የተመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን፦<< በልጆቻችን በኮራንበት ቀን ለማይረባ ገንዘብ  ሲል ተራ ማጭበርበር ውስጥ በገባው መንግስት አፈርን፤ ግለሰብ ቢሰርቅ በህግ ይጠየቅ እንል ነበር። የሰረቀው <<ሌባ መቀጣት አለበት>>የሚል ህግ የፃፈው መንግስት ነው ሲባል ግን ከማፈር በስተቀር ምን እንላለን?>> ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም። 

በአላማጣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች ቀኑን ሙሉ በልዩ ሀይሎች ታግተው ዋሉ


ኢሳት ዜና:- ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጧት ወደ ስራ ለመሄድ ሲነሱ አካባቢያቸው በሙሉ በፌደራል    ልዩ ሀይል ፖሊሶች ተከቦ አግኝተውታል። ማንም ከቤት እንዳይወጣ በማገድ የመንግስት ባለስልጣናት በስም ጽፈው የያዙዋቸውን ከ300 በላይ ቤቶች ሲያስፈርሱ ውለዋል።
በእያንዳንዱ ቤት በር ላይ ሁለት ሁለት ልዩ ፖሊሶች ቆመው የእያንዳንዱን ሰው ቤት እንቅስቃሴ በሚከታተሉበት ሁኔታ የተለያዩ ሰዎችን አግኝቶ ለማነጋገር ባይቻልም አንድ ከቤት እንዳይወጡ የታገዱ ሰው እንደገለጡት ለመጸዳዳት እና ልጆቻቸውን ለማጫወት እንኳን ከቤት ሳይወጡ ታግደው መዋላቸውን ገልጸዋል።
ቤት አፍራሽ ግብረሀይሎች ቀኑን ሙሉ ሲያፈርሱ ውለው አካበቢውን ከ11 ሰአት በሁዋላ ለቀው የሄዱ ሲሆን ፣ ንብረቶቻቸው ሜዳ ላይ የወደቁባቸው ሰዎች ራሳቸውን ስተው ሲወድቁ ዘግይቶ ያነጋገርነው አንድ የአይን እማኝ ገልጿል 
ባለፈው ጥር ወር መግቢያ ላይ ተቃውሞውን መርተዋል ተብለው የታሰሩት ሰዎች ከእስር ቤት ሳይወጡ ቤታቸው እንዲፈርስ ተደርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከማንነት ጋር በተያያዘ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚነሳው ጥያቄ እየጨመረ መሆኑ ታውቋል። የትግራይ ክልል መንግስት ከዚህ ቀደም የነበሩ የተለያዩ በኦሮምኛና በአማርኛ የተጻፉ ወካይ ስሞችን በመለወጥ የአካባቢውን ታሪክና ባህል ለማጥፋት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። “የራያ ህዝብ ባህልና ታሪክ ” በሚል ርእስ በክብሮም አሰፋ የተጻፈው መጽሀፍ እንዳይሰራጭ መታገዱ በአካባቢው ያለውን ውጥረት እንደሚያሳይ ነዋሪው ገልጸዋል።
አላማጣ ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊት የወሎ ክፍለሀገር ግዛት እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ የአካባቢውን ሰዎች ለማነጋገር ጥረቶችን እያደረግን ነው እንደተሳካልን እናቀርባለን።
የአላማጣ ከተማ አስተዳዳር ጽህፈት ቤትን ለማነጋገር ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎችን ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም። 

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው ወጡ


ኢሳት ዜና:- በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኙት በፔዳ ፣ ፖሊ፣ ይባብና  ዘንዘልማ  ካምፓሶች ይማሩ የነበሩ ከ95 በመቶ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው መውጣታቸውን የተወሰኑትም ወደ መጡበት አካባቢ መመለሳቸውን  ተማሪዎች ገለጹ። ተማሪዎቹ ግቢአቸውን በመልቀቅ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የወሰኑት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው አስተዳዳሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚደረግ ጸሎት እንዲቆም፣ ሴቶች ጂሃብም ኒቃምብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ተከትሎ ነው።
አንዳንድ ተማሪዎች ከትናንት ጀምረው ትምህርት በማቋረጥ ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የነበረ ቢሆንም፣ የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች “ትእዛዙ ከበላይ አካል የመጣ ነው ምንም ማድረግ አንችልም” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል። አንድ ተማሪ እንደገለጸው የተወሰኑ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን ፣ ሌሎችም ትኬት በመቁረጥ ላይ ናቸው። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን እያበረረ በኢህአዴግ አባላት እየሞላ ነው

ኢሳት ዜና:- በአየር መንገዱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በኢህአዴግ አባሉ ስራ አስኪያጅ በአቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ በተጠባባቂው ስራ አስኪያጅ በአቶ ኢሳያስ ወልደማርያም እና በኦዲተሩ በአቶ ዋሱ ዘለለው አነሳሽነት ነባር ሰራተኞች ከስራ እየተቀነሱ  በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት እየተተኩ ነው። በቅርቡ 36 የትኬት ሽያጭ ሰራተኞች እና 14 ኤጀንቶች ከስራ ተባረው በፎረሙ አባላት ተተክተዋል።  ከእነዚህም መካከል 5 የትኬት ሰራተኞች እና 14 በተለያዩ ሀላፊነት ላይ ያሉ የድርጅቱ ሰራተኞች በሰበብ አስባቡ ወደ እስር ቤት እንዲላኩ መደረጉን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል ኢማም ያሲን፣ ሳሙኤል እንዳለ፣ ቤተልሄም ጌታቸው፣ ኤደን በየነ፣ የአመቱ ምርጥ የትኬት ሽያጭ ኤጀንት ተብሎ የተሸለመው ይርጋለም ታደሰ፣ ቤተልሄም ተፈራ፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛዊት ኤፍሬም፣ አንተንሳይ አማረ፣ ሰለሞን በቀለ ይገኙበታል።
ከታሰሩት ሰራተኞች መካከል ደግሞ ሳሙኤል እንዳለ፣ አማኑኤል ጸጋው፣ ብርሀኑ ሰለሞን፣ እኑ ገብረእግዚአብሄር፣ አይዳ ዘልኡል፣ እና በረከት ግርማ የሚገኙበት ሲሆን፣ በረከት ግርማ ስራውን ለቆ በቱርክ አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ በማገልገል ላይ ሳለ የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር አውለውታል።
ከስራ ከታገዱት መካከል ትንግርት ደምሴ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ሀይማኖት ንጉሴ፣ ሳምራዊት ገረመው፣ ሜላት አስራት፣ አማኑኤል በልስቲ፣ አማኑኤል ነጋሽ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤ፣ አንዱአለም ግርማ ይገኙበታል።
ከተባረሩት፣ ከታገዱትና ከታሰሩት መካከል ከ10 እሰከ 30 አመታት የሰሩ ነባር አየር መንገዱ ሰራተኞች የሚገኙበት ሲሆን፣ የተባረሩበት ወይም የታገዱበት ምክንያትም የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ተጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ሰራተኞች ይገልጻሉ።
አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኢትዮጵያን አየር መንገድ በስራ አስኪያጅነት  ለመምራት ስልጣኑን ከተረከቡ በሁዋላ፣ በተለያዩ መንገዶች የኢህአዴግ የወጣት አደረጃጀት አባላት በድርጅቱ ውስጥ በስፋት እንዲቀጠሩ አድርገዋል።
እቃዎችን በማውረድና በመስቀል ስራ ላይ የስሩ የነበሩ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተባረው በኢህአዴግ ወጣት ፎረም አባላት እንዲተኩ ማድረጋቸውን ከወር በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

Jan 22, 2013

ማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም!

መልዕክተ ተዋሕዶ – ዘሮኪ
እንዴት እንደሰነበትን፥ ሁላችንም
እናውቀዋለንና። ለመላው የቤተክርስቲያን
ልጆች እያሳለፍነው ያለው ሳምንት የሐዘንና፥
ተስፋችንን አጨላሚ፥ ሆኖ ነው
የሰነበተው። ይህ ሳምንት፥ ለሃያ አንድ
ዓመታት ፥ መከፋፈል በተባለ በሽታ ፥ ታማ
የነበረችው እናት ቤተክርስቲያን ፥ ስትሰቃይ
ኖራ ፥ ያረፈችበት ሳምንት ነው። ነገር ግን
አጥብቀን ከቀድሞው አብዝተን ከጮህን፥
ልክ በወንጌሉ እንደተጻፈው የሞተውን
የሚያስነሳው ትንሣኤና ሕይወት የሆነ
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ዳግመኛ እስትንፋሷን ሊመልሰው
ይቻለዋል። በእምነታችንም ጸንተን
እያንዳንዳችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ
ከማድረግ ወደ ኋላ አንበል፤ በማለት
ሰሞኑን አእምሮዬን ሲሞግቱኝ ወደ ከረሙት
ጉዳዮች ተራ በተራ ልግባ።
መጀመሪያ በአሁኑ ወቅት ከበሽታቸው ጋር እየታገሉ የሚገኙት ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ ብጹዕ
አቡነ ሉቃስ፣ ብጹዕ አቡነ ቄርሎስና ሌሎችም በአጠቃላይ፥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የሰጣችሁን፥ ከባድ አደራ
በመወጣት ላይ ለምትገኙ አባቶቻችን፥ ለእናንተ ያለን ፍቅርና አክብሮት እጅግ የላቀ መሆኑን ልንገልጽላችሁ
እንወዳለን። ባሳያችሁት ጽኑዕ አቋም ምክንያት ብዙዎቻችን ጨርሰን ተስፋ እንዳንቆርጥ ረድቶናል። እያደረጋችሁት
ያለውን ጥረትና ተጋድሎም፥ በእኛ ልጆቻችሁ ልቡና ለዘላለሙተቀርጾ በሃይማኖት ጸንተን እንድንኖር ይረዳናል።
ዋጋችሁም በማይጠፋው መዝገብ ተመዝግቦ ከእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ እንደምትቀበሉም ሙሉ እምነታችን ነው።
ይህ ስሜት የብቻዬ ስላልሆነ ጉዳይ በሚመለከተን የቤተክርስቲያን ልጆች ስምም፥ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።
ከሁሉ ያስደነቀኝ ደግሞ የብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ቆራጥ አቋም ነው። የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን
ጥመኞችንም አላገለግልም !ለዚህ የማመስገኛ ቃላት ያጥረኛል። ቤተክርስቲያን ውለታዎንና ተጋድሎዎን መቼም
አትረሳውም። ምናለበት፥ እንደርስዎ ሌሎቹም አባቶች ተከትለዎት ቢወጡ ኖሮ ፥ አሰኝቶኛል። አንዳንዴ እንዲህ ያለ
አቋም ቁጭ ብሎ ትርጉም የሌለው ንትርክ ከመነታረክ፥ አስር እጥፍ ይሻላል። ብጹአን አባቶቼ፥ መቼም መሣሪያ
ደቅነው ከያዙ ጨካኞች ጋር እንደምትጋፈጡ ይገባኛል፥ ነገርግን ቢያንስ የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆኑ፥ ብጹዕ አቡነ
ሕዝቅኤል ሲወጡ፥ ሌሎቻችሁም ብትከተሉና ፤በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አባቶቻችን በዕርቁ ጉዳይ ሳይስማሙ ተለያዩ
፤ ተብሎ ቢነገረን፥ ይሻል ነበር ብዬ አስባለሁ።

ለነገሩ አሁንም ቢሆን፥ ያለቀ የደቀቀ ነገር ስላልሆነ፥ ከዚህም በኋላ እነሱ በሚያደርጉት ማንኛውም የመሿሿሚያ
ስብሰባዎች ራሳችሁን ብትለዩ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ። አባቶቼ ዝምታም እኮ ተቃውሞ ነው፤ እነ አባ አብርሃምና
አባ ሳሙኤል እርስስ በርሳቸው ይሿሿሙ፥ ይሰብሰቡ፥ ነገ እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣል። ብጹአን አባቶቻችን ፥
ከቻላችሁ በአቋማችሁ የምትስማሙት አንድ ላይ በመሆን ተቃውሞአችሁን ቀጥሉ፥ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማወቅ ባለበት
መጠን አሳውቁ። በመንግስት አይዞአችሁ ባይነት እየተንቀሳቀሱ ያሉት አባቶች፥ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኝ እረኞች
ስለሆኑ እና በሥልጣን ጥመኝነትና በጥላቻ ስለሰከሩ፤ ከዚህ በፊት ለመጠቆም እንደሞከርኩት የተሰጣቸውን ተተልዕኮ
ከማስፈጸም ፥ ወደ ኋላ አይመለሱም። ብጹአን አባቶች፤ ውሃ ሽቅብ እንደማይፈስ አውቃለሁ። ነገር ግን ሁላችሁም
ከእግዚአብሔር ያገኛችሁት ትልቅ መንፈሳዊ ሀብት በእጃችሁ አለ። አስፈላጊውን ማሳሰቢያ ከሰጣችሁ በኋላ፥
በእንቢታቸው ጸንተው ፥ የእነ አባይ ጸሐዬን ጠብ መንጃ ተመክተው፥ እንመርጣለን ብለው ከተነሱም፥ በመጨረሻውን
ውሳኔ ስጡ! ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ በእጃችሁ ትገኛለችና!
ሁለተኛ፦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ እባካችሁን ስለቤተክርስቱያናችን የወደፊት
ሕልውናና ስለእኛ ስለተበተነው ልጆቻችሁ ስትሉ በተደጋጋሚ ያሳያችሁትን ትዕግስት አሁንም ቀጥሉ። ቢያንስ ቢያንስ
እነ አባ ሳሙኤል እና መሰሎቻቸው በስልጣን ጥመኝነት አእዕምሮአቸውን አጥተው እስኪለይላቸው ድረስ ሕዝቡን
የሚያጽናና፣ የሚያረጋጋና አንድነቱን የሚያጠናክርበትን መንገድ በማሳየት በጎቻችሁን በመልካምና በለምለም ሣር ላይ
አሰማሩ። እንዲህ ከሆነ ይህን፥ ወይም ያንን፥ እናደርጋለን ከማለት ከእልኸኝነት የሚመነጭ ውሳኔ ተቆጠቡ።
ሦስተኛ፦ የሰላምና አንድነት ኮሚቴም እስከ አሁን ድረስ የደከማችሁትን ድካም ልጆቻችሁ የሆንን ሁሉ እንረዳለን።
እግዚአብሔር በሰማያት ዋጋችሁን እንዲከፍላችሁ ጸሎቴ ነው። ከዚህ በኋላ ፥ ያጋጠማችሁን ፈተናና ሰላም እና
አንድነቱን ለማምጣት ስትሉ ከመናገር የተቆጠባችሁትን ሁሉ የመግለጽ ኃላፊነት ይጠበቅባችኋል። በአንድነት
ምዕመናኑን በመምራት ፥ ለሰላም ይበጃል የምትሉትን ሁሉ ሃሳብ ከመስጠት አትቆጠቡ። አቅማችሁ በቻለ መጠን
ከሁለቱም ወገን ይህ መከፋፈል ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ሞክሩ።
አራተኛ፦ለማህበረ ቅዱሳን አንድ ግልጽ መልዕክት አለኝ። ማህበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጀምሮ ትኩረቱን
በቤተክርስቲያን ብቻ ላይ በማድረግ፤ ከፖለቲካ ነጻ በሆነ መንገድ፥ ስብከተ ወንጌል በማስፋፋት፣ ቤተክርስቲያንን
ከመናፍቃንና ከተሐድሶያዊያን በመታደግ፣ አዲሱን ትውልድ ለቤተክርስቲያን የሚገደውና የሚቆረቆር አድርጎ
በመቅረጽ ጊዜ የማይሽረው ትልቅ አሻራ ጥሏል። ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን በምትፈልገው ቦታ ሁሉ
ስድብን፣መታሰርን፣መጉላላትንና ሌሎች በዚህች ጹሑፍ ዘርዝሬ ልገልጸው የማልችላቸውን ፈተናዎች ታግሶ፥በአዲሱ
ትውልድ ላይ፥ በእግዚአብሔር ቸርነት፥ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ፥ ለመሆንም በቅቷል። ይህን ሁሉ መከራና ዋጋ
የተከፈለላት ቤተክርስቲያንና ልጆቿ ያለ መሪ ሲቅበዘበዙ፥ ብጹአን አባቶቻችን በህቡዕ ሣይሆን በግልጽ ድጋፍ
ሲያስፈልጋቸው፥ ምንም እንዳልተፈጸመ ዝምታችሁ ሊገባኝ አልቻለም። ይልቁንም አንዳንድ የማህበሩ አባላት በዕርቁ
ዙሪያ ያላቸውን ሃሳብ ሲሰጡ፤ የማህበሩ ሃሳብ አይደለም! ብሎ እራሱን ከመንግስት ቁጣ ለማዳን የሚያደርገው
ድርጊት ትዝብት ላይ ከጣለው ሰነበተ። ቤተክርስቲያን ስትከፈል ደጆቿ ሲዘጉ የማህበሩ ጽሕፈት ቤት እንዳይዘጋ
የምታደርጓቸው ጥንቃቄዎችም አሳዝኖኛል!! ለቤተክርስቲያን የመከራ ቀን ድምጹን አሰምቶ እኛ አለንልሽ
ቤተክርስቲያን ካላለ፥ የዚህ ማህበር ፋይዳው ምንድን ነው? እኔ በበኩሌ ይህ ማህበር ፥በሰላሙ ሰዓት ብቻ ለስብከተ
ወንጌል የሚሯሯጡ ሰባኪያንን ብቻ ሳይሆን፥ በዓላውያን መንግስታት ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ የሰጡትን
ሰማዕታትን እነቅዱስ ጊዮርጊስን የሚተካ ትውድም የሚያፈራ አድርጌ እቆጥረው ነበረ። ከዚህ በላይ ምን እስኪሆን
ነው የሚጠበቀው? ከአፍቃሬ ማህበርነት የሚፈለግ ቢሆንም ከሁሉም በላይ አፍቃሬ ቤተክርስቲያን መሆኑን
የሚያሳይበት ወቅት አሁን መሆኑን ልገልጽ እወዳለሁ። ለዚህ ወቅታዊ ጥያቄ ምላሽ በአስቸኳይ ያስፈልገዋል!
በመጨረሻም፦ በውጭው ዓለም የምትገኙ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች በየቤተክርስቲያናችሁ በዚህ ጉዳይ
ተሰባስባችሁ አቋማችሁን ዛሬም ለመግለጽ ዛሬም ጊዜ አላችሁ። ከሕሊና ባርነት የአንድ ቀን ነጻነት ይሻላል። ብዙ አደር
ባዮች በበዙበት ዘመን እውነትን ለመናገር ዳተኛ መሆን ከክርስቲያን አይጠበቅም። የፈለገው ይሾም ስም ለመጥራት
ዝግጁ ነን፥ ቅዱስ ሲኖዶስ አይሳሳትም ፤ወለም ዘለም አንልም የሚባል ዜማ እያዜሙ የመንግስትን ሹመኞች
እንድንቀበል መድረኩን የሚያዘጋጁ ካህናትና ምዕመናን እየተስተዋሉ ነው። በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ነው የሚባለው
ሲኖዶስ ይኼ ነው ወይ? ብጹዕዓን አባቶቻችንን በገዛ ጽሕፈት ቤታችው እያስፈራራቸው ያለው ግለሰብ፥ አባይ ጸሐዬ፥
መቼ ነው የሲኖዶሱ አባል የሆነው? የሚገርመው እነአባ አብርሃም ፓትርያርኩ ያለ መንግስት ተጽዕኖ ነው መንበር
ጥለው የተሰደዱት ይበሉን? እንደው በእመ አምላክ የመንግስትን ተጽዕኖ መኖር የሚጠራጠር ሰው ይኖር ይሆንን?
እንኳን የዛሬ ሃያ አንድ ዓመት፥ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ሲያሳድዱ ይቅርና ፤ዛሬ ሰላም ነው ተብሎ
በሚለፈፍበት ጊዜ እንኳን አዳር ውሎአቸው ቤተክህነት አይደለምን? እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል። የሚቀብረን ነው
ያጣነው።
ይቅርታ ይደረግልኝና በታሪክ የምናውቃቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የድሮዎቹ፤ ወኔ የነበራቸው፥ እንኳን
ለቤተክርስቲያናቸው ቀርቶ ለሃገራችው ለእናት ኢትዮጵያ ሥጋቸውን ለአሞራ የሚሰጡ ነበሩ። ለዚህ መቼም ጥቅስ
ፍለጋ አልደክምም። በአጭሩ ግን፥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በር ተዘግቶ የካቶሊክ እምነት በር አይከፈትም

በማለት፤ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን፥ በአንድ ቀን ብቻ፥ ከመላው ኢትዮጵያ ሰማዕትነት አያምልጥህ እየተባባሉ፤ አስር ሺህ
ምዕመናን ጎንደር ላይ ሰማዕትነትን የተቀበሉበትንና የቅዱሱን ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስን ሰማዕትነት ለአንባቢ ማስታወስ
ግድ ይለኛል።
እንደው ለመሆኑ ሳናውቀው ጥሩ ጥሩ ነገሮች ላይ ብቻ የሚሳተፍ፥ ሀገር ጎብኚ፥ መረር ያለ ነገር ሲመጣ እነእገሌ ይህን
ያድርጉ፤ እኔ የለሁበትም የሚል ትውልድ ሆነን እንቅር? እንዲህ እንዲህ ይሸቱ የነበሩት እንኳን መናፍቃኑ ነበሩ። እረ
ጎበዝ ምን ነካን? እዚህ ላይ ይብቃኝ።
አምላከ ቤተክርስቲያን እባክህ ተመልከተን! እኛ ደክመናል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
መልዕክተ ተዋሕዶ – ዘሮኪ

በምዕራብ አባያ ገበሬዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ


ፍኖተ ነፃነት
በደቡብ ክልል ጋሞ ጐፋ ዞን በሚገኘው ምዕራብ አባያ ወረዳ ልዩ ስሙ አልገሌ
ቀበሌ ሺለሸኮ አካባቢ ሰፊ የፍርፍሬ እርሻ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን መደረጉ
ተጠቆመ፡፡ በተለይ የአቶ መሐመድ መጠሎ እና የአቶ ተቀባ መጠሎ የሙዝ እርሻ
አላግባብ መመንጠሩ ተገልፆል፡፡
ድርጊቱ የተፈፀመው ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 4 ሰዓት አካባቢ የወረዳው መስተዳደር ተወካይ አቶ
ከፍያለው ቦጋለ እና የወረዳው ሲብልሰርቪስ ኃላፊ አቶ አርባ ጐጃ በተገኙበት በመሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ማድረጉን
ምንጮቻችን ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በዕለቱ የማሳው ባለቤቶች በሥፍራው የነበሩ ሲሆን የአካባቢው ሞሌ የተባለ
አጐራባች ቀበሌ ነዋሪዎች በድርጊቱ ላይ የተሳተፉም እንዳሉ ተገልፆል፡፡
የጉዳዩን አሳሳቢነት አስመልክተው ጉዳት የደረሰባቸው የአካባቢው ገበሬዎች ለዞኑ መስተዳደር አካል ለሆኑት ለአቶ
እሸቱ ቅሬታቸውን በአካል ሄደው ማምልከታቸው ታውቋል፡፡ የመስተዳደሩ አካልም የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪ አቶ
አዲሱ አርባን ቅሬታ አቅራቢዎች በተገኙበት ስለጉዳዩ ሲጠይቋቸው “የፍራፍሬ ማሣው የተጨፈጨፈባቸው አላግባብ
ነው፤ ድርጊቱን የፈፀሙት ላይም እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው
ገበሬዎች ግን “እንኳን የፍራፍሬ ማሳችሁ ቀርቶ ገና ራሳችሁንም እናጠፋችኋለን የሚል ገና ማስፈራሪያ የወረዳው
አስተዳዳሪዎች ባሉበት ተሰጥቶናል፤ ስለዚህ አሁንም ጉዳዩ ግልፅ ስላልሆነ ስጋት አለን” ብለዋል፡፡
ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣም ስለጉዳዩ ለማጣራት የወረዳው ዋና አስተዳደር የሆኑትን አቶ አዲሱ አርባ ጋር ተደጋጋሚ ጥረት
ብናደርግም አልተሳካም፡፡

እንደ መከላከያ ሁሉ ኢትዮ ቴሌኮምም


ዘረኛው የወያኔ መንግስት ዘረኝነቱን በሚያጠናክርለት ና የራሱን ጀሌዎች ብቻ የስርአቱ ተጠቃሚ በማድረግ የአንድ ብሄር የበላይነቱን ይዞ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የሚያሳይ ሌላ መረጃ ሰሙኑን የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የጥናት ክፍል ይፋ አድርጓል ። ቀደም ሲልም  በየካቲት 2002 በመከላከያ ሰራዊት በአዛዥነት ቦታዎች ያለውን የብሄር ተዋጽኦ ማጋለጣችን ይታወሳል።

ወያኔ በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ ለረጅም ግዜ በየዘርፉ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች አባሮና አፈናቅሎ ታማኝ ያላቸውን የህወሃት ታጋዮችን “ከሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ያስመረታቸውን ምርቶች እና ከመቀሌ ኢንስቲዩት ቴክኖሎጅ ” በአብዛኛው ከአንድ ዘር በማምጣት መድቦ ኮርፕሬሽኑ የጀሮ መጥቢያ የስላላ ተቋምና የፓርቲው መሳሪያ በማድረግ የዜጎችን ሉዓላዊነት በመዳፈር ሀገራችንን በዚህ ዘመን የመረጃ ርሃብተኛ አድርጓታል።
በዚሁ ጥናት ሌላው አሳዛኙ ጉዳይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያላቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም።
ሌላው መራራ ሀቅ 66.2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት አራት ብቻ ነዉ (ሁለት ከኦሮሚያ ሁለት ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን ስምንት ሰዎች ኤን አንድ በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
ሌላው ወያኔዎች ለወደፊቱ የአለም ቴክኖሎጂ ሲያድግ ህወሃቶች የተቀረውን የሀገራችንን ህዝብ አድልሆ በማድረግ አንድን ዘር በኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ የማሳደግ ስውር አጀንዳም ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጥናቶች በተደጋጋሚ እያሳዩን ነው። ስለዚህ ይህንን የማስቆምና ዜጎች በሀገራቸው እንደዜጋ የሁሉም መብቶች እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ አስፈላጊውን መሰዋእትነት በመክፈል ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሁላችንም እንገባ ዘንድ የግድ ነው።
ወያኔ/ህወሃት ለደረሰብኝ በደል ካሣ አሁን ተራዬን ሌሎችን የመበደል መብቴ ነው ብሎ የሚያደርገውን የአንድ ዘር የበላይነትንና ጨቋኝነቱን በድርጊቱ እንዲህ እየነገረን፤ በግልባጩ ግን ነጋ ጠባ የሚነገረን እኩል መሆናችንን ነው። ይህ ግን ሀሰት መሆኑን ጥናቱ አረጋግጦልናል። በቀድሞ ሥርዓት የተበደለ በአዲሱ ሥርዓት በዳይ ሆኖ ቢገኝ ጥፋቱን አቅልሎ ማየት፤ የሥርዓት ለውጥ የበዳይና ተበዳይ ቦታ መለዋወጥ አድርጎ ከመገንዘብ የሚመጣ እጅግ አደገኛ የሆነ አመለካከት ነው እና የሀገራችን ህዝብ ይህንን አረመኔ ዘረኛ ስርአት ብሄራዊ አደጋ ውስጥ ሳያስገባን ልንታገለው ጊዜው አሁን ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ከእነዚህና ሌሎች እውነታዎች በመነሳት አሁን ግዜው የፍልሚያ ነው የሚለው፤ የቻለ በግንባር ያልቻለ በደጀንነት ይሰለፍ፣ ጠጠር ይወርውር ጠጠር ያቀብል! የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ሀገራችን ኢትዮጵያን ከሀገር በቀሉ ወራሪ ዘረኛ መንግስት የማዳን ጥሪ ጊዜው አሁን ነውና የምንችለውን ሁሉ በማድረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ! እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የረጅሙ ጉዞ ምእራፍ አሁን ነው እና የአንድ ዘር የበላይ ዘረኝነት ፓሊሲን እንዋጋ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ማፈራረስ ማተራመስ ማሸበር- የወያኔ ታላቁ ራዕይ

ከይኸነው አንተሁነኝ

ጥር 19 2013

“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል” ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም

ወያኔ ላለፉት 21 ዓመታት የሀገራችንን ታሪክ ለማፈራረስና ለመቀየር የቻለውን ሁሉ ሞክሯል። የሕዝባችንን የአልደፈርም ባይነት ወኔ ለመስለብና ለማኮላሸት ያልቆፈረው ጉድጋድ አልነበረም። ሃይማኖታዊ ስርአታችንንና ወጋችንን ለመናድ ብዙ መንገድ በመጓዝ ደክሟል። አብሮ በመቻቻል የመኖር ወጥ ባህላችንን ለመጨፈላለቅና ለማጥፋት ሞክሯል። በኢኮኖሚ የወያኔ ጥገኛ እንድንሆንና የመብት ጥያቄ እንዳናነሳ ፀጥ ብለን እንድንገዛ ለማድረግ ሲጥር ከርሟል። ለወገናችን ጠብ ባላለው ልማት ስም ስንቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው ከእርሻ ማሳቸው አፈናቅሏል። አሻፈረኝ ያሉትንም አስሯል ገድሏል። ራሱ የማያከብረውን የይስሙላ ህግም አስከብራለሁ እያለ የስንቶችን መብት ረግጧል። ወያኔ ከሳምንት እስከ ሳምንት ስገቴ ናቸው የሚላቸውንና ያላማሩትን ሁሉ አቅሙ እስከ ቻለ ተጉዞ በስደት ዓለምም ቢሆን ያፈናና የግድያ ሙከራ ከማድረግ ቦዝኖ አያውቅም። በዚህ የክፋት ድርጊቱም ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችን ላይመለሱ ክቡር ሂዎታቸውን ገብረዋል። ወያኔ ዛሬም ቢሆን በዓለም ዙሪያ እኩይ ስራውን አላቆመም።
በሀረር ከ30 ዓመታት በላይ በባለቤትነት ያስተዳደሯቸው ሱቆች ሊፈርሱ እንደሆነ የታወጀበትና በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸውን በማፍረስ ሽዎችን ለልመናና ለጎዳና ተዳዳሪነት የዳረገው የወያኔ ራዕይ ሳያባራ አሁን ደግሞ ጉዳዩ ወደ ክልል ከተሞች ወርዶ የአላማጣ ነዋሪዎችን እያስለቀሰ ይገኛል። ህጻናት፣ አዛውንትና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ቤቶቻቸው እየፈረሱ በመሆናቸው መፍትሄ ለማያመጣ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት ተገደዋል።
ወያኔ በህግ ስም ህግን እየረገጠ እንደገና ራሱ ቀድሞ እየጮኸ፤ በልማት ስም ያሻውን እየገፋ የውድቀት ራዒዉን እያሰፋ የፈለገውን እያስፋፋ ሀገር እያጠፋ ቀጥሏል። መብታችን ይከበር ለሚለው ጥያቄ መብት እንደገፈፈ እንዳሰረና እንደገረፈ አለ። በማይመለከተው ይመለከተኛል በማያገባውም ያገባኛል እንዳለና ሕዝባችንን እንዳመሰ ባጅቷል። ለአንድ ዓመት ሳይቋረጥ ለቀጠለው የሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የመብት ጥያቄ አሉታዊ መልስ ሲሰጥ የከረመው ወያኔ በራሱ መንገድ መሪዎቻቸሁ እነዚህ ናቸው ብሎ አስቀምጧል። ለመብት የሚደረገው እንቅስቃሴ ባለመብረዱም በገርባ ቀበሌ የፈጸመውን ግድያና አረመኔያዊ ጭፍጨርፋ ገና ሳንረሳ አሁን ደግሞ በሀረር ገና ላቅመ አዳም ያልደረሰ ከ10 እስከ 12 ዓመት እድሜ የሚገመት ህጻን ባደባባይ በመግደልና ጥቂት የማይባሉትንም በማቁሰል ማንነቱንና ትክክለኛ ራዕዩን አሳይቶናል። በኦርቶዶክስ እምነት ላይም እየደረሰ ያለው አፈናና እኔ አውቃለሁ ባይነት ቀጥሎ ወያኔ የፈለገውን ፓትሪያርክ በአባ ጳውሎስ ቦታ ለማስቀመጥ የሚያደረገው ሩጫ የተበላ እቁብ ያህል እርግጠኛ ወደ መሆን ተቃርቧል።
ሰላሳ ሶስት የምርጫ ፓርቲዎችን ያካተተው ሰብስብ የወያኔ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ህጉ ይገዛ፣ ከምርጫ በፊት የመሮጫ ሜዳው ይስተካከል፣ ጥያቄዎች አሉንና እንወያይ በማለታቸው “በባለቤቱ የተማመነ…” እንደሚባለው የወያኔው ምርጫ ቦርድ ሁሉንም ፓርቲዎች ከወያኔ የወረዳና የአካባቢ ምርጫ ውጭ አድርጓል።
የመሰብሰብ፣ የመናገር፣ የመጻፍና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን አስከብሬያለሁ እያለ ለዓለም የሚለፈው ወያኔ አንቱ የተባሉ ጋዜጠኞችን በእስር ከማማቀቅ ቀሪዎችንም ከማሰደድ ከማስገረፍና ከማሰሩም በተጨማሪ እንደ ባለራዕይ ወጣቶች አይነት ደፋር ለሀገር አሳቢ ማህበር ድንገት ብቅ ሲል ደግሞ ምክንያት እየፈጠሩ ከሕዝባቸው ጋር እንዳይገናኙና ዓላማቸውን እንዳያሳውቁ ከማስፈራራትና ጉሸማ አንስቶ ለእንደ አዲስ አበባ ወጣቶች ፎረም አይነቶች የተፈቀደውን የስብሰባ ቦታ ከመከልከሉም በላይ በራሳቸው ተሯሩጠው ካገኙት የስብሰባ አዳራሽ ድረስ ካድሬዎቹን አስርጎ በማስገባትና የመሰብሰብ መብታቸውን በመጋፋት ዓላማቸውን እንዳያሳውቁና ወደ ሕዝባቸው እንዳይደርሱ ለማድረግ ስራ በዝቶበት ከርሟል።
በጋምቤላና በአፋር በኢንቨስትመንት ስም የአካባቢውን ኗሪ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ለዘመናት ከኖረበትና እጅጉን ካለማው የእርሻ ማሳው በሃይል በማፈናቀል በሰፈራ ስም ወደ ቦዳ መሬቶች የማዛወሩ ስራ አርሶ አደር ወገኖቻችን ላይ የፈጠረው ቀውስ ሳይስተካከል ዛሬ ይኸው ተግባር በሱሪ በከፋ መልኩ ቀጥሏል። በሱሪ የቀጠለው አርሶ አደሮችን የማፈናቀሉ የወያኔ እኩይ ስራ እጅግ ተካሮ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሱሪዎች ያሰቃቂ ግድያ ምክንያት ሆኗል። ምስኪን ሱሪዎች የእርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው በሀገራቸው የመኖር መብታቸውን ተገፈው ባንድ ጉድጓድ ሰላሳ ሰባው እንዲህ እንደሰሞኑ እጅግ ሲከፋም እስከ አንድ መቶ ሃምሳ እየተቀበሩ ይገኛሉ። የወያኔ ራዕይም በሀገራችን በዚህ መልኩ ሳይበረዝና ሳይከለስ ተስተካክሎ ቀጥሏል።
በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው የሀገር ውስጡ ግፍና መከራ ሳይበርድ በምስራቅ አፍሪካ እንደልቡ የሚወጣውና የሚገባው ወያኔ በቀጠናው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በስደት ዓለም ሌላ ስደት ለመሆን መከራውን እያየ ይገኛል።
ኢትዮጵያዊያን በጅቡቲ ይታፈናሉ ተላልፈውም ለሀገር ውስጥ እስርና ከዚህም ሲከፋ ለግድያ ይዳረጋሉ። በኬንያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ያፈና ስጋት አለብን ሲሉ እየጮሁ ነው። በሱዳን በተለይም በደቡብ ሱዳን በቀድሞው የወያኔ ወታደር ያሁኑ ነጋዴ የይስሙላው ጀነራል ፃድቃን አቀነባባሪነት ወገኖቻችን የመታፈንና ወደ ሀገር አስር ቤት የመመለስ፣ ባሉበት የመገደል ወይም ወደ ሌላ ሶስተኛ ሀገር እንደገና የመከራ ስደት ለመጀመር በጭንቅ ላይ መሆናቸው ይሰማል። በሶማሊያ የወገኖቻችን ኑሮ የጭንቅ ነው። ወያኔ በእርግጥ ሰላም የማሳጣት ስራ በዝቶበት ከርሟል። ባንድ ጊዜ ሁሉም ላይ ለመገኘትና ጥቃት ለመሰንዘር እየሞከረ ይገኛል። ሁሉም ላይ ባንድ ጊዜ ለመገኘት መሞከር ግን አንዱንም ለመከወን አለመቻልን ሊያስከትል እንደሚችል የተረዳ አይመስልም። ኢትዮጵያዊያንን ለማጥመድ እጅግ በጣም ርቆ የብስና ውቅያኖስን አቆራርጦ ሲክለፈለፍ ከአሜሪካ የደህንነት ወጥመድ እንደዶለው የሰሞኑ ውርደቱ፤ አንድ ቀን እጅግ የከፋው የወያኔ እኩይ እንቅስቃሴ ወያኔን ላይመለስ ወደ መቃብር እንደማይከተው ምን ማረጋገጫ አለ… ምንም።

Total Pageviews

Translate