ከኃይለገብርኤል አያሌው
የፍትህ ምንጭ የህግ ባለቤት በመንግስቱ አድሎ የሌለበት እንደ ክፋታችን ሳይሆን እንደቸርነቱ
ጠብቆ የሚያኖረን እውነተኛ ዳኛ የሆነው አምላካችን መድሃኒታችን እየሱስክርስቶስ እውነትና መንገድ
ዳኛና ፈራጅ እርሱ በመሆኑ ቀን ያነሳቸው ነፍጥና ጎመድ ለታጠቁት በሃይልና ጉልበታቸው የፍትህን
ምንጭ አድርቀው ግፍ ለሚፈጽሙ ደሃ ለሚበድሉትና ህግ ለሚያጣምሙት አህዛብ ፈርዖኖችን ድል
የሚያደርግ ሃያሉ አምላክ ይግባኝ የምንለው ከምክርና ተግሳጽ በላይ መከራ ሊመክራቸው ያልቻሉ
የታዘዘው መቅሰፍት ጥጋብና ትዕቢቱ ለከት አጥቶ የነበረው ለምህረትና ይቅርታ ልቡ ታውሮ ሕሊናው
በጥላቻ ጠቁሮ ይመራ ዘንድ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘውን የመሪነት ጸጋ አድፋፍቶ ከክፋት መንገድ ሊመለስ
ያልቻለውን መለስ ዜናዊን አምላክ በኪነጥበቡ በአጭር ሲቀጨው የደሃ እንባ የግፉአን በደል ሰማይ
መድረሱን ተገንዝበው ለመቻቻል ለእርቅና ሰላም በራቸውን መክፈት የነበረባቸው የዚሁ አረመኔ አልጋ
ወራሾች በበጎነት ፋንታ ያንንኑ ዴያቢሎሳዊ መንገዳቸውን አባብሰው መቀጠላቸውን ዳግም አረጋግጠውልናል። በፀሎተ ሐሙስ ነብሰ ገዳዩን ደም አፍሳሹን በርባንን ፈተው ክርስቶስን እንደሰቀሉት አይሁዶች የእኛዎቹ ተረፈ መለሶች ያንኑ የሃሰት የግፍና የበቀል እርምጃቸውን በህግ ስም በንጹሃኖቹ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተፈጸመውን ሕገ አራዊታዊ ፍርደ ገምድል ውሳኔ የህዝብን ልብ የሰበረ በህግ ተዳኝቶ ፍትህ የማግኘትን ተስፋን ያመከነ ዜጎች በከፋና በከረፋ ዘረኛ የወንበዴ መንጋ መዳፍ ስር የወደቁበት የአምላክ ቸርነት የሚያስፈልግበት ተስፋይቱ ምድር ኢትዮጽያ የምትቃትትበት ቃልኪዳኑን የምትጠብቅበት አስከፊ ወቅት በመሆኑ መከራ ያጸኑብንን ከላያችን አራግፈንእንድንጥል ወኔና ብርታት ሃይልና ጉልበት እዲሆነንና ከወደቅንበት ድቅድቅ ጨለማ ላይ ብርሃኑን እንዲፈነጥቅ‘’ኤሉሄ ላማ ሰበቅታኒ’’ (ጌታ ሆይ ለምን ተውከን) እያልን እንማፀን ዘንድ ግድ ብሎናልና ስለኛ ብለው በአራዊት ጉድጓድ የተጣሉትን መልካሞቹን የኛን ዳንኤሎች ከተከረቸሙበት እስር ቤት ወጥተው ነጻነታቸውን ይጎናጸፉ ዘንድ ለደጋጎቹ አባቶቻችን የተለመንህ አምላክ በምህረት ትጎበኘን ዘንድ ወዳንተ የሚደረገውን ይግባኝ እንደ እኔ አይነቱ
በሃጥያት ያለ ጎልማሳ ቢበድልህም እንደ ሰርካለም ያለውን ተምሳሌተ ራሄል መከራ የጎበኛት በእስር ወልዳ
ዛሬም ስንቅ ማመላለስ እጣ ፋንታዋ የሆነውን ልበ ንጹህ የሆነች እመቤት ስለ ብላቴናዎቹ የእስክንድርና
የአንዷለምን ህጻናት መቃተት ሰምተህ የሌሎቹንም በስደት በመከራ የሚጉላሉትን ተፈናቅለው በጎዳና
የወደቁትን የቀን ሃሩር የለሊት ቁር የሚፈራረቅባቸውን ወገኖች ተመልክተህ በቃችሁ ብለህ ከመከራም
ትታደገን በእለተ ስቅለትህ ይግባኝ ብለናል።
ጠባቡንና ሸለቋማውን እባብና ጊንጥ የበዛበትን የሃገራችንን የፍርድ ቤት የጨለማ ጉዞ
ለሰውም ለእግዚያብሄርም ይሆን ዘንድ ባለመታከት ዘጠናዘጠኝ በመቶ የታወቀ ቢሆንም ምን አልባት
ለህሊናው ያደረ ለሙያዊ ስነምግባሩ የታመነ ፈጣሪውን የሚፈራ ሰውን የሚያፍር ዳኛ ተገኝቶ ነገሩን
ቢለውጥ የመከነ ተስፋ ከነበረው የአራዊት ሸንጎ እንደተጠበቀው ክስ ፈጥሮ ምስክር አሰልጥኖ መበቀላዊ
መመሪያ ያነገቡ ዳኞችን አሰልፎ ይሉኝታ አልባ ውሳኔውን ያጸናው የዴያቢሎስ ቡድን እንደ እስክንድር
አይነቱን እግዚያብሄርን የሚፈራ ሰውን በሰውነቱ የሚያከብር ለህግ የተገዛ በምግባር የዳበረና በጨዋነት
የተሞላ ከማናቸውም ሱሶች የጸዳ ለትዳሩ የታመነ ገንዘብን የናቀ ዘወትር የወገኑ መራብ እረፍት የሚነሳው
የሃገሩ ተመጽዋችነት የሚያንገበግበው ሃገሩንና ወገኑን በሚችላውና ባለው አቅም ለመርዳት ህይወቱን
እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት የቆረጠ መልካም ዜጋ ባልሰራው ወንጀል ባልዋለበት ፖለቲካ እየተፈጸመበት
ያለው ግፍ እውነት በመናገሩ በመሆኑ ይዋል ይደር እንጂ የማይገለጥ የተሸፈነ የማይታወቅ የተደበቀ ነገር
ባለመኖሩ በህዝብ ትግልና በእግዚያብሄር ሃይል ፍርድ ገልባጮችና ሸፍጠኛ ገዠዎች የሃፍረት ካባ
የሚለብሱበት ግዜ እሩቅ አለመሆኑን አለም በአንድ ድምጽ ሃሙስ እለት የዋለውን የጋንጋሮ ፍርድ ቤት
ውሎ ማውገዙ የመጨረሻው መጀመሪያ መቅረቡን የሚያበስር ይመስለሻል።
ስለ እስክንድር ንጽህና ለመተረክ መሞከር ቃላት የማባከን ያህል ቢሆንም እንደ ታናሽ
ወንድም የማቀውን እናገር ዘንድ ግድ ስለሚለኝ አንድ ነገር ለማለት ዳዳኝ። በሃገር ቤት በነበርኩበት ግዜ
ከስራ ውጪ አብዛኛውን ግዜ ከእስክንድር ጋር አብረን የምናሳልፍበት ግዜ የሚበዛ በመሆኑ የነበረን
ቅርርብ የወንድማማች ያህል እስኪሆን ድረስ ከቤተሰቦቼ አልፎ ገጠር ያሉ ዘመዶቻችን ጭምር
በትሁትነቱና ያስታውሱታል። እክስከማስታውሰው ከእስክንድር ጋር ከሃገራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ውጪ
ስለሌሎች የግል ጉዳዮች የምንወያይበት ሁኔታ በጣም ውስን ነበር። እኔና እስክንድር በሃገራችን የፖለቲካ
ሁኔታ ላይ የነበረን ውይይት በምርጫ ዘጠና ሰባት የህዝባችን የዲሞከራሲና የለውጥ ተስፋ ከተቀለበሰ
በኋላ እኔም ወደ ስደት እርሱም ወደ እስርቤት የተለያየንበት ሁኔታ ተፈጥሮ ለተወሰነ ግዜ ቢቆይም
ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በስልክ የምናደርገው ውይይት ቀጥሎ እርሱ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ያለ አንዳች
ፍርሃት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን ስሜት እያጋራኝ እዚህ ስላለውም የማደርገለት ማብራራት
የወያኔ መረጃዎች ዘወትር እንደሚከታተሉትና ስልኩን እነደጠለፉት ስለሚያውቅ አንዳንዴ እየቀለደ
ሦስተኛው ሰው እያደመጠ ነው ይል ነበር ። እስክንድር ይህን ያህል በክትትል ውስጥ እንደተወጠረ
መሆኑን ቢያውቅም አንድም ቀን ሲጨናነቅና የሚሰማውን ከመግለጽ የሚፈልገውንም ከመጠየቅ ወደኋላ
ያለበት ሁኔታ አላስታውስም ስለታጋዩ ስለ ሃየሎች አሰላለፍ ስለ ፖለቲካ ድርጅቶች ስለ ስርዐት ለውጥ
ያለውን ግምገማ በስልክም በአደባባይም ሲገልጽ ምን ያህል በያዘው እውነት እንደሚተማመንና ሕጋዊነቱን
ጥያቄ ውስጥ በሚጥል ስሜታዊ ከሆነ ተግባር የሚጠነቀቅ አዋቂ ሰው ነው።
ሌላው እስክድርን እስከማውቀው ከውጭ ሆኖ ትግል ከዳር የመድረሱ ላይ ጥርጣሬው የጎላ
ከመሆኑም በላይ በሃሰት የተከሰሰበት የግንቦት ሰባት የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር እስክንድር አካል ሊሆን
ቀርቶ በሃገርቤት እንዳለ ዜጋና በጥብቅ የደህንነት ክትትል ስር ሆኖ አመጽ ከአወጁ ሃይሎች ጋር
የሚያሰተሳስር የፖለቲካ ድር ውስጥ ሚና ለመጋራት ፈጽሞ የማያስችል ሁኔታ ካለመኖሩመ በላይ ማንም
ሊረዳው የሚገባው እንደ እስክንድር ያለ ራሱን ለሞት እንኳ ቢሆን አሳልፎ ለመስጠት የቆረጠ ጀግና
የጠመንጃው ትግል ያስኬደኛል ብሎ ቢያምን ጫካ ለመግባት የማያመነታ ቆራጥ በመሆኑ የማንም አጀንዳ
አራማጅነት ሳያስፈልገው በተግባር ያደርገው ነበር። የእስክንድር አላማ ይህ አይደለም እውነትን በመጻፍና
በማንቃት በሃገር ውስጥ ከወገን ጋር ሆኖ በሰላማዊ እንቢተኝነት የስርዐት ለውጥ ማምጣት የሚል
ሳይገድሉ የመሞት መንፈሳዊ ትግል የማህተመ ጋንዲንና የማርቲን ሉተርን የትግል ተሞክሮ የመተግበር
አጀንዳ ነው እስክንድር የነበረው። ይህን ደግሞ በመለስ ትዕዛዝ የፖሊስ ኮሚሽነሩ የመጨረሻ ያለውንና
በከባድ ማስፈራረያ የታጀበው ትዕዛዝ መጻፍን አቁም እምቢ ብትል በራስህ ላይ ፈርደሃል መባሉን እራሱ
እስክንድር በቃልም በጽሁፍም ይፋ ማደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።
እስክንድር እንኳን ዜጎችን በሚያስጨርስ ሁለገብ አመጽ ሊሰማራ ይቅርና የወገኑ መቸገር
እንደ እግር ውስጥ ቁስል እረፍት የሚነሳው ለዚህ መከረኛ ወገኑ ደጋግሞ እንኳ ቢሞት ቅር የማይለው
መልካም ሰው ያለ ጥፋቱ መንገላታቱ እጅግ በጣም ያሰዝነኛል። ከእስክንድር በጎ ስራ የቱን አንስቼ የቱን
እንደምተው ይቸግረኛል፤እርህራሄ የተሞላ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ግዜ ለእናቱ የቤት ውስጥ ስራ የምትረዳ
ሰራተኛ ይፈልግና ስረና ሰራተኛ አገናኝ ደላሎች ጋር አብረን እንሄዳለን እዛም አንዲት በሃያዎቹ መጨረሻ
የምትሆን ልጅ ደላላው ያገናኘንና ልጅቷን ይዘን ጉዞ እንደጀመርን እስክንድር በልጅቷ ሁኔታ ልቡ ተነክቶ
ከጠየቀችው በላይ ደመወዝ እንደሚከፍላት ነገር ግን ትምህርቷን መከታተል የግድ እንዳለባት ነግሮ
የመጀመሪያ ወር ደመወዟን እንዳለው ጨምሮ በመስጠት እቃዋን ይዛ እንድትመጣ በማለት
ያሰናብታታል። ታዲያም ያቺ ልጅ ራስ ወዳድነት በነገሰበት ከጻጻሱ እስከ ካድሬው ለገንዘብ ጣዖት
በተንበረከከበት ራሱን ለመጥቀም የሌሎችን ህይወት እንኳ ቢያጠፋ ግድ የሌለው ሆድ አምላኩ በበዛበት
ዘመን ላይ እንዲህ ያለ ደግነት ከትህትና የተላበሰ መልካም ዜጋ ልቧን ነክቶት እንባዋ መንታ ሆኖ እየወረደ
ለምስጋና ቃላተ ሲያጥራት የነበረበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል። ለምሳሌ ይህን ገጠመኝ አነሳሁት እንጂ
የእስክንድር ደግነትና ለወገኑ ያለው እርህራሄ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። እስክንድር ብዙ ግዜ
ከምንሄድበት የስድስት ኪሎ ያለው ስደተኛው መድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያን አምላክ ለሃገራችን እድገት
ለህዝባችን ነጻነትና እኩልነት እንዲሰጠ አዘውትሮ የሚጸልይ ቀና ሰው ሽብርተኛ መባሉ መታሰር መቸገሩ
ለሁላችን መሆኑ የገባን ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን
ቤተመንግስቱ በዘረኝነትና በኋላ ቀርነት በዘቀጠበት ቤተ እምነቱ በመንፈሳዊ ክስረትና በሞራል
አልባነት በወረደበት በተለይ ለኢትዮጽያ ታሪከና ህልውና ታላቅ ባለውለታ ከሆነችው አማናዊቷ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ ለመንጋቸው እረኛ ሊሆኑ ቀርቶ ልጆቿን
አሳልፈው የሚሰጡ ለጥቅምና ለምድራዊ ህይወት የቋመጡ ህዝብ ሲንገላታ ወገን ሲበደል ፍርድ ሲጓደል
አይተው እንዳላዩ በሚበዙበት በዚህ ዘመን በዚህ ትውልድ የበጎነት ተምሳሌት የሃቀኝነት እርሾ የሚሆን
አውራ ዜጋ ከመድረኩ በታጣበት ሁኔታ ላይ እግዚያብሄር እስክንድርን ሃቅ እንዲጽፍ አንዷለም ለወገን
እንዲጮህ ባያስነሳ ማን ነበር ምሳሌ የሚሆነን የሃገራችን ምድር የሃሰት ማቅ ብትለብስም የወጣትነት
ትኩስ እድሜያቸውን ከምንም በላይ ለማንም ፍጥረት የቀንበር ያህል ከባደ የሆነውን ከህጻናት ልጆቻቸው
ተነጥለው ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ለምድራዊ ስቃይ የመዳረጋቸው ምክንያት ለምንድን ነው ጥቅም
ስልጣን ዝና ወይስ ምን ለዚህ ሁሉ አይደለም እስክንድር ሚስጥረኛ ወንድሜ ነው አንዷለም ወዳጄ ነው
አበበ ቀስቶ የአፍላነት እድሜ የዛሬ 18 አመት ጀምሮ በሃገራዊ ጉዳይ አብሮኝ የጎለመሰ ጓዴ ነው በደንብ
አውቃቸዋለሁ ሁሉም ውስጥ ግለኝነት የለም ራዕያቸው ፍላጎታቸው የበለጸገችና እኩልነት የሰፈነባት ሃገር
ይኖረን ዘንድ ነው። ለዚህም ነው መከራ የሚቀበሉት በእነሱ ድካም እኛ እናርፍ ዘንድ ነው መቃብራቸው
የተማሰው እለተ ሞታቸው የቀረበው ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ስልጣን የተቀዳጁት እድሜ የጠገቡት
ጻጻሳትና ካህናት በፍርሃት የሸሹትን ለህዝብ የመሰዋትነ ጸጋ እስክንድር አንዷለም አበበ ሊወጡት
በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተተኩልሽ መጽሃፉ እንዲል በዚህ ድቅድቅ የተስፋ መቁረጥ ጭለማ ውስጥ
የብርሃን ወጋገን በፈነጠቁልን ጀግኖቻችን ፈለግ በመከተል ጅምራቸውን ከፍጻሜ ለማደረስ ሃገር ወዳድ ነን
የምንል ዜጎች በትግሉ አውላላ ሜዳ ላይ ጥለውን ስለሸሹት ማላዘን ሳይሆን እነዚህን የዘመናችን የትውልድ
ክዋክብት የሆኑ ተምሳሌቶችን እንከተል ዘንድ ታሪክ ሞራል እግዚያብሄር ግድ ይሉናል።
እስክንድር እንደ አብዛኞቻችን ደሃ መንደር አላደገም በወርቅ ማንኪያ እየበላ ማርና ወተት
እየተጎነጨ በምቾትና በድሎት ያደገ ጥሩ ትምህርት ቤት ገብቶ በመልካም ምግባርና እውቀት የጎለመሰ

ችግርና ውጣ ውረድን ሳያይ የኖረ ከሞቀ የአሜሪካ ኑሮው ሃገሬና ወገኔን ብሎ እውቀቱን ማንነቱን ገንዘቡን
ይዞ በመግባት በእውቀቱ ሕዝብን ሊያገለግል በአቅሙ ሃገርን ሊያሰድግ የለውጥ እንቅፋት ሆኖ
ከተጫነብን የነጻ ሃሰብ እጥረት ተቆራኝቶን ከኖረው የስማ በለው ባህል ተላቀን ዐለም የደረሰበት ደረጃ
ለመድረስ ዋና መንገድ መሪ የሆነውን መረጃ ለህዝብ ለማድረስ ታክስ ከፋዩ ሰፊው ሕዝብ ወሳኝነት
እንዲኖረው ለማንቃት በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በሃገራችን በፈነጠቀው የነጻሚድያ እድል ተጠቅሞ ወገኑን
ለማገዝ የነበረው ተነሳሽነት ገና ከአፍላው እስርን ሽልማቱ ይመስል ባለፉት 22 አመታት ከአስር ግዜ በላ
በመታሰር አልበገር ያለው ይህ ታላቅ ሰው ለሃገርና ለወገን የከፈለው መስዋዕትነት ከበቂ በላይ ቢሆንም
ይህው ዛሬም በቀራኒዮ ኢትዮጽያ ግማደ መስቀሉ ስር ከጥቂት ወንድሞቹ ጋር በጽናት በመቆም የእኛ
ሃፍረት ለመሸፈን የወገንን መቃተት ለማስታገስ የግፍና የመከራ መንገድ ያለ ይግባኝ ተስፋ ይጓዙ ዘንድ
ፍርደኞች ጠመዋል ባለግዜዎች ወስነዋል፤ የኛስ መልስ ምንድን ነው? በተለይ ወጣቱ ከእስክንድር ምን
ትማራለህ? ከአንዷለም ምንስ አየህ? ይህን መመዘን ይገባሃል። የስራ እድል አድርባይ ካልሆንክ አታገኝም
ተብለሃል በልቶ ማደር ባለመቻሉ ከእርሃብ ጋር ስትታገል እድታድር ተፈርዶብሃል ስለ ፈራህ ከሞት
አታመልጥም ባለመቁረጥህ ችግርን ረሃብና መራቆትን አልሸሸህም ደርግ እንዲህ አድርጓል በቅንጅት ያ
ሆኖዐል የሚለውን የባልቴቶች ተረት አሽቀንጥረህ ጥለህ ለመብትና ነጻነትህ ሕዝባዊና ሰላማዊ ትግሉን
በመቀላቀል ለራስህም ለሃገርህም ትሆን ዘንድ በታሪክ ታስሮ ከመቆዘም ስለነጻነትህ ቤዛ እየሆኑ ያሉትን
ተመልክተህ ሞራልህን ታበረታ ዘንድ የክዋክብቶቹን የእነእስክንድርን ፈለግ ተከትለህ እንደ ግብጽና
ቱኒዝያ ወጣቶች አሮጌውን ዘመን ያለፈበትን ሕገአራዊቱን የወያኔ አገዛዝ አሽቀንጥረህ በመጣል ታሪክ ሠሪ
ሁን፤ ይህ ደግሞ ይቻላል ከአባቶችህ የወረስከው የጥሬ ስጋ አበላል ብቻ መሆን የለበትም ጀግንነታቸውን
ልትወርስ ይገባል ይህ ደግሞ ለቆረጠ ይቻላል! መቻልም አለበት! ተችሏልም!
ስል ሰው ልጆች ሃጥያት ቤዛ የሆነው አምላካችን
መድሃኒተዓለም እየሱስ ክርስቶስ ሕዝባችንን ከአራዊት አገዛዝ
ያድንልን!
የሃገራችንን የቀደመ ክብር ይመልስልን!
መልካም ትንሳዔ
ጎበዝ በፋሲካው ያለንን ለተራቡት እናካፍል የታሰሩትን ዘርና
ሃይማኖት ሳንል እንጠይቅ በርቱ እንኳ እንበላቸው!
እንበርታ